ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ትብብራቸውን ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሸጋገር ተስማሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ትብብራቸውን ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሸጋገር ተስማሙ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 28/2017 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምዕራፍ ለማሸጋገር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ረመዳን መሐመድ አብደላ ጎክ ጋር ዛሬ በጁባ ተወያይተዋል።
በሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ደቡብ ሱዳን ገባ
ሚኒስትሮቹ በውይይቱ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳንን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከርና ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሸጋገር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
በተጨማሪም የሀገራቱን የኢኮኖሚ ትብብር እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር የበለጠ ለማጎልበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት ደቡብ ሱዳን ጁባ መግባቱ ይታወቃል።