የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 19/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ቤተልሔም አበባው ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን ቢራቱ ጋር ተፈራርመውታል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በጋራ ለመሥራት ተፈራረሙ
በስምምነቱ መሰረት በብራንድ ኮሙኒኬሽን፣በህትመት እና ኤሌክትሮኒክስ ሚድያ ፕሮዳክሽን፣ በሁነት ዝግጅት እና ተያያዥ ስራዎች እንዲሁም በልዩ ልዩ የተግባቦት ስራዎች ዙሪያ የሚሰሩ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ቤተልሔም አበባው በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኢዜአ የዜና ስራን ጨምሮ በተለያዩ የይዘት ስራዎች እንዲሁም ትልልቅ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ማህበረሰቡ ሊያውቃቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ለማሳወቅ የሚያስችሉ የተለያዩ ሁነቶችን በማዘጋጀት ልምድ ያለው ተቋም መሆኑን ገልጸዋል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በርካታ ወደ ህዝብ መድረስ የሚገባቸው ህዝቡ ሊያውቀው የሚገባ በርካታ ጉዳዮች እንዳሉት ተናግረዋል።
ስምምነቱ እነዚህን ስራዎች ተገቢውን የሚድያ ሽፋን በመስጠት ወደ ህዝብ የሚያደርስበት ሁኔታ ማመቻቸት መሆኑን ጠቁመዋል።
በተበጣጠሰ መንገድ የሚሰሩ ስራዎች በተደራጀ አግባብ ተደራሽ ማድረግ የሚቻልበት መሆኑን ገልጸዋል።
እንዲሁም በተለያየ መንገድ መድረኮችን በማመቻቸት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን ግንዛቤ ማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች በጋራ ለመስራት መሆኑን አመላክተዋል።
ኢዜአ ከተሰጡት ተልእኮዎች ውስጥ አንዱ አገራዊ መግባባት መፍጠር መሆኑን ገልጸው፥ መልካም ውጤት የሚገኝበት ስምምነት መሆኑንም ነው የተናገሩት።
የሲቪል ማህበረሰብ ድረጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን ቢራቱ በበኩላቸው ከአገልግሎቱ ጋር መስራት መልካም አጋጣሚ መሆኑን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና ቲቪ ብሪክስ ኢንተርናሽናል ሚዲያ ኔትወርክ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
የለውጡ መንግስት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለቆሙለት አላማ ይበልጥ ህብረተሰቡን ተደራሽ እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል።
ለዚህም መንግስት ያላሳለሰ ጥረት ማድረጉን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር የተደረገው ስምምነትም ስራዎቹን በህብረተሰቡ ዘንድ በማስረጽ ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም ስራዎቹን ተደራሽ ለማድረግ በጉልህ የሚያግዘው መሆኑንም ነው የገለጹት።