አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአውሮፓ ሕብረት ልዩ ተወካይ ጋር በቀጣናዊና ሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ 

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2016 (ኢዜአ)፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአውሮፓ ሕብረት ልዩ ተወካይ አኔት ወዌበር (ዶ/ር) ጋር በቀጣናዊና ሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል። 

 

የኢትዮጵያና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ  በአፍሪካ ቀንድ   የአውሮፓ ሕብረት  ልዩ ተወካይ አኔት ወዌበር(ዶ/ር) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ አካላት በቆይታቸው በአፍሪካ ቀንድ የጸጥታና የደህንነት ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሱዳን ሁለንተናዊ ሰላምን ለማስፈን እየተጫወቱ የሚገኘውን ቁልፍ ሚና አውስተዋል።


 

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካዊ ማዕቀፍ በሱዳን ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚያደርጉትን ጥረት በትኩረት መደገፍ እንደሚገባ በውይይቱ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተጨማሪም ሁለቱ አካላት በሱማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በቀጣናውና በቀይ ባህር ጉዳዮች ዙርያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በቀጣይም የኢትዮጵያና አውሮፓ ሕብረትን ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያጠናክሩ ምክክሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በውይይቱ ተነስቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም