ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በብሪክሱ ዓለም አቀፍ መድረክ ተባብሮ የመስራት ችሎታዋንና ዓለም አቀፋዊ አጋርነቷን ማስመስከር ችላለች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2016(ኢዜአ)፦በሩሲያ ቪላዲቮስቶክ የተካሄደው የብሪክስ አባል ሃገራት ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም በስኬት ተጠናቋል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎችም በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ 24 ነጥቦችን የያዘ የአቋም መግለጫ በማውጣት ለስኬታማነቱ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

በዚሁ መድረክም ኢትዮጵያ የላቀ የዲፕሎማሲ ድል ማስመዝገቧን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ገልፀዋል።

ብሪክስ ለፍትሐዊ የዓለም የኢኮኖሚና ፋይናንስ ስርዓት የሚሰራ የትብብር ማዕቀፍ ነው - አቶ አደም ፋራህ

/World majority for meltipolar order / ዓለማቀፋዊ ብዝሃነት ፣ ለብዝሃ ዋልታ ሥርዓት በሚል መሪ ቃል ከሰኔ 9 እስከ ሰኔ 12 በተካሄደው ፎረም ጥቂቶች ብቻ የሚወስኑባት ዓለም፣ በብሪክስ አባል እና አጋር ሀገራት ስር ለሚገኘው አብዝሃኛው የዓለም ህዝብ የፖለቲካ ተሳትፎ ፣ የሀብት ተካፋይነት ፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ፍትሃዊ መሆን እንዳለበት በአጽንኦት ተመክሮበታል ብለዋል። ኢትዮጵያም በብልጽግና ፓርቲ በኩል ጠንካራ የአብሮነት አቋሟን አሳውቃለች ነው ያሉት አቶ አዲሱ።


 

ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፋዊ የአብሮነት ተግባር ከሊግ ኦፍ ኔሽን እስከ አሁኑ የተባበሩት መንግስታት በግንባር ቀደም የተሳትፎ ሚና እንደምትታወቅ ፤ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት እስከ አፍሪካ ህብረት እድገት ደረጃም የላቀ አስተዋጽኦ እንዳላት በወርቃማ የታሪክ መዝገብ መፃፉን አቶ አዲሱ አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል እና አጋር ሀገራት ለተወከሉበት ለብዙሃኑ የዓለም ህዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም መከበር በሚደረገው የጋራ ትግል በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና በብልጽግና ፓርቲ የተጀመረውን ውጤታማ ተግባር እንዳሳየች አቶ አዲሱ ገልፀዋል።

ከጉባኤው ጎን ለጎን ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል እና አጋር ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር በመምከር ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ድል በማስመዝገብ ተባብሮ የመስራት ዓለም አቀፋዊ አጋርነቷን ማስመስከር ችላለች ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለቀጣናውና ለአፍሪካ ሠላም ቀጣይነት ባለው መልኩ እየሰራች ነው - ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)

ተሳታፊዎቹ ባወጡት የአቋም መግለጫ ከተመለከቱት ጉዳዮች መካከልም በአፍሪካ ጉዳይ ከአፍሪካ ውጭ ያሉ ሃገራት በፖለቲካ፣ በወታደራዊ ፖለቲካና በሰብዓዊ እርዳታ ላይ የሚያደርሱት ተጽእኖ ሊቆም እንደሚገባ ትኩረታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህም በብሪክስ እና በአፍሪካ ሃገራት ማካከል ያለውን ትብብር የማጠናከሩን አስፈላጊነትም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ይሄንን ለማሳካት ከብሪክስ አባልና አጋር ሃገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የህዝብ ተቋማት፣ ባለስልጣናትና ባለሙያዎች የሚሳተፉባቸው የባለ ብዙ ዘርፍ ተመሳሳይ የውይይት መድረኮችን አስፈላጊነትም ማስቀመጣቸውን ኢዜአ ከስፍራው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ዋና አስተባባሪ አደም ፋራህ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በተሳተፈበት የብሪክስ እና አጋር አገራት ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት ፎረም በርካታ የቀጥታና የጎንዮሽ ውይይቶች ተካሂደውበታል::


 

 


 

 

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም