አርእስተ ዜና
የሕብረት ሥራ ማህበራት በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ ትኩረት ተደርጓል -አቶ እንዳሻው ጣሰው
Apr 24, 2024 65
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረት ሥራ ማህበራት በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ የአመራርና የአደረጃጀት ማሻሻያ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ። “ህብረት ስራ ማህበራት ለዘላቂ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ የሕብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል። በስነስርዓቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው እንደገለጹት፣ ማህበራቱ በክልሉ የኑሮ ውድነትን ለማርገብና የአባሎቻቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ጉልህ ሚና አላቸው። በገበያ የዋጋ መናር በህዝብ ላይ ጫና እንዳይፈጥር የግብርናና የፋብሪካ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ እያበረከቱት ያለው አስተዋጾ ላቅ ያለ መሆኑንም ጠቅስዋል።   ማህበራቱ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ የሪፎርም ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ እነዚህ ተግባራት የማህበሩን አባላትና የነዋሪውን ተጠቃሚነት ይበልጥ ያሳድጋሉ ብለዋል። ማህበራቱ በብቁ ባለሙያ እንዲመሩ፣ አሰራራቸው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲያስደግፉ እንዲሁም የፋይናንስ ግልጸኝነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ማሻሻያው አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የፌዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ በበኩላቸው እንዳሉት ህብረት ሥራ ማህበራቱ ከቆይታቸውና ከአባሎቻቸው ብዛት ጋር ሲነጻጸር ብዙ ማደግ ሳይችሉ ቆይተዋል። ይህን በመለወጥ ጠንካራና ሀገራዊ ሚናቸውን ለማጉላት ችግሮቻቸውን ፈቶ በተጠና መንገድ ለማዋሀድና ተቀናጅተው እንዲሰሩ ለማድረግ ማሻሻያው መዘጋጀቱን ገልጸዋል። "ለማሻሻያው ምክንያት ከሆኑት ውስጥ የአደረጃጀት፣ የአመራርና የአሰራር እንዲሁም የፋይናንስ ክህሎት ችግሮች ይጠቀሳሉ" ያሉት አቶ ሺሰማ፣ እነዚህ ችግሮች ሲፈቱ የአገልግሎት አቅማቸው ይሰፋል ብለዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንዳሉት፣ በክልሉ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ 5 ሺህ 600 የሕብረት ስራ ማህበራት አሉ። ማህበራቱ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል እንዳላቸው ጠቁመው፣ እነዚህ ማህበራት የተሻሻለ ቴክኖሎጂን በማቅረብ፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ በገንዘብ ቁጠባና ብድር እንዲሁም ገበያን በማረጋጋት ረገድ የጎላ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። ማህበራቱ በክልሉ እያበረከቱት ያለውን አስተዋጾ ከዚህም በላይ ለማሳደግ በአዲስ መልክ ተዋህደውና ተደራጅተው ወደ ሥራ እንዲገቡ ክልሉ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ በክልሉ በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት፣ ዩኒየኖችና ፌዴሬሽኖች ተሳትፈዋል። ከንቅናቄ መድረኩ ጎን ለጎን የግብርና ምርቶች ለሸማቹ የቀረበበትና ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ባዛር በምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ተከፍቷል።      
በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞኖች በጸጥታ ሃይሎችና በህዝቡ ተሳትፎ በተከናወነ ተግባር ሰላምና መረጋጋት እየሰፈነ መሆኑ ተገለጸ
Apr 24, 2024 43
ነቀምቴ ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞኖች በጸጥታ ሃይሎችና በህዝቡ ተሳትፎ በተከናወነ ተግባር ሰላምና መረጋጋት እየሰፈነ መምጣቱን የአገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች ገለጹ። በአካባቢው ሰላምን የማጽናት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል። የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች ይህን የገለጹት የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ጸጥታ ፅህፈት ቤት የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸምን ዛሬ በነቀምቴ ከተማ በተገመገመበት ወቅት ነው። መድረኩ ላይ የተገኙት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት እንደገለጹት፤ በጸጥታ ሃይሎችና በህዝቡ ተሳትፎ በአካባቢው ሰላም የማስፈን ጥረት ውጤታማ ነው። ህብረተሰቡ ለሰላምና ደህንነት ማስከበር ስራው በአቅሙና መረጃዎችን በመስጠት ሀላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ጠቁመው ለፀጥታው መረጋገጥ ያሳየው አቋም ለጸረ ሰላም ቡድኑ አላማ መክሸፍ አስተዋጽኦ እንዳለው አመልክተዋል።   የኦነግ ሸኔ አባላት እየፈጸመ ያለውን የዘረፋ እና የወንጀል ድርጊት መሆኑን ተረድተው በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሊሰጡ እንደሚገባ ነው የተናገሩት። መንግስት ዛሬም ለሰላሙ የከፈተው በር ስላልተዘጋ ከጦርነቱ ይልቅ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል። የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ዞኖች በጸጥታ ሃይሎችና በህዝቡ ተሳትፎ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተገኝቷል። "የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በቁርጠኝነት በተሰራ ስራ በርካታ ለውጦች ተመዝግበዋል" ሲሉም አክለዋል። "የህብረተሰቡ ተሳትፎ ለስራው መሳካት ትልቁን ሚና እየተጫወተ ይገኛል" ያሉት ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ፤ ሰላምን የማጽናት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ለሜሳ ኦልጂራ በወቅቱ እንዳሉት፤ በዞኑ ባሉ ወረዳዎች የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተሰራ ስራ ውጤት ተመዝግቧል። ህብረተሰቡን ወደ ቀድሞ የልማት እንቅስቃሴ እየተመለሰ መሆኑን ጠቁመው፤ የተጀመረው የህግ ማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ወጋሪ ነገራ በበኩላቸው፤ በዞኑ ወረዳዎች ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆሙ በተከናወኑ ስራዎች ሰላምና ጸጥታን በማስከበር ረገድ ውጤት መገኘቱን አንስተዋል። ሁሉን አቀፍ ልማት ለማምጣትና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑት ተግባራት ለዘላቂ ሰላም መስፈን መሰረት እየጣሉ መምጣታቸውን ተናግረዋል ። የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠል ተሳትፏቸውን እንደሚያጠናክሩ ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል።
በዞኑ በመኸር ወቅት 22 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል የሰብል ምርት ለማግኘት ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል 
Apr 24, 2024 50
መተማ ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ በምዕራብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት 22 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል የሰብል ምርት ለማግኘት ታቅዶ የእርሻ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። "ያለ ግብርና የለም ልዕልና" በሚል መሪ ሃሳብ የ2016/17 ምርት ዘመን የመኸር ሰብል ልማት ንቅናቄ መድረክ ዛሬ ተካሂዷል። የመምሪያው ኃላፊና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አንዳርግ ጌጡ እንዳሉት፤ ዞኑ ለምግብ፣ በውጭ ገበያና ለፋብሪካ ግብዓት የሚሆኑ የግብርና ምርቶች በስፋት የሚመረትበት ነው። በምርት ዘመኑ መኸር ወቅት ከ518 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ የሰብል ዘር በመሸፈን 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምር ለማግኘት ታቅዶ የእርሻ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።   ያለውን ሰፊ የእርሻ መሬት የተሻሻሉ አሰራሮችን በመተግበርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ከወዲሁ እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልፀዋል። አርሶ አደሩን ከተበጣጠሰ የአስተራረስ ዘዴ ለመውጣት ጅምር ስራዎች እንዳሉ አመልክተው፤ ይህን በማስፋት በኩታ ገጠም የማልማት አሰራርን መከተልና ሜካናይዜሽንን ማሳደግ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። ከሚለማው መሬት ውስጥ 250 ሺህ ሄክታር የሚሆነውን በኩታ ገጠምና በትራክተር የሚታረስ መሆኑን አስገንዝበዋል። በእቅድ የተያዘውን ምርት ለማግኘትና በሄክታር የሚገኘውን አማካኝ ምርት መጠን ከ19 ኩንታል ወደ 24 ኩንታል ለማሳደግ ግብ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ በበኩላቸው በምርት ወቅቱ የተያዘው እቅድ እንዲሳካ ሁሉም ባለድርሻ አካል የሚጠበቅበትን እንዲወጣ አሳስበዋል ። የመተማ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት ፈቃዱ "በወረዳው በመኸር ወቅት 160 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ ነው" ብለዋል። አሁን ላይ የግብዓት ስርጭት ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አመልክተዋል። በወረዳው ለሃገራዊ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴው የጎላ ጠቀሜታ ያላቸው ሰሊጥ፣ ጥጥና አኩሪ አተር በምርት ወቅቱ በዋናነት ትከረት የተሰጣቸው መሆኑን አስታውቀዋል። መድረኩ ከሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።  
ኢትዮጵያ 4ኛው አለም አቀፍ የፋይናንስ የልማት ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ቁርጠኛ ናት - አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ 
Apr 24, 2024 45
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ በመጪው ሃምሌ የሚካሄደውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 4ኛው አለም አቀፍ የፋይናንስ ለልማት ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ ገለፁ። አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና መሀመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በዚህ ወቅት አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ፤ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 4ኛውን የፋይናንስ ልማት ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በመንግስታቱ ድርጅት መካከል ስላለው ዘርፈ-ብዙ አጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ተገልጿል። በተጨማሪም በዘላቂ የልማት ግቦች የትግበራ ሁኔታ፣ በመጪው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እና በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይም ውይይት ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
የሚታይ

በብሪክስ ጥምረት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ ነው
Apr 24, 2024 64
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ በብሪክስ ጥምረት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡ የብሪክስ ጥምረት 10 አገራትን በማቀፍ 37 በመቶ የኢኮኖሚ እና 45 በመቶ የዓለም አቀፍ የህዝብ ቁጥር የሚሸፍን ግዙፍ የትብብር ጥምረት መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። የኢትዮጵያ እና ሩሲያ የጥናትና ምርምር ተቋማት የባለሙያዎች ቡድን በብሪክስ ጥምረት ስር ትብብርን ማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡   የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ፤ በመድረኩም በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ሌሎች ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ግንዛቤ ያላቸው ምሁራንና የምርምር ተቋማት መሳተፋቸውን ገልጸዋል። በወቅቱ በሩሲያ ሊቀመንበርነት የሚመራው የብሪክስ አባል አገራት ጥምረት የመሪዎች ጉባኤ በመጪው ግንቦት ወር በሩሲያ ሞስኮ እንደሚካሄድም አስታውቀዋል። መድረኩም በመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ መፍትሔ አመላካች አጀንዳዎች ላይ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ የሚያቀርቡበት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ እነዚህ ሃሳቦችም በመሪዎች አማካኝነት የጥምረቱ የጋራ አጀንዳዎች እንደሚሆኑ ነው የተናገሩት፡፡ የኢትዮጵያ ባለሙያዎችም ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ በብሪክስ ጥምረት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በሩሲያ የብሪክስ ምክር ቤት ኃላፊ ቪክቶሪያ ፓኖቫ (ዶ/ር)፤ በብሪክስ ማዕቀፍ ስር የሚካሄዱ የምክክር መድረኮችም ለመሪዎች ጉባኤ ውሳኔ የሚበጁ ምክረ ሃሳቦችን ለማፍለቅ ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖራቸውም ገልጸዋል።   በብሪክስ አባል አገራት መካከል የሚደረገው ትብብር ከጥምረት ባሻገር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚበጁ ችግር ፈቺ ሃሳቦች እንዲተገበሩ እንደሚያደርግም አንስተዋል፡፡ በመድረኩም የኢትዮጵያ ምሁራንም ከሀገራቸው ብሔራዊ ጥቅም በመነሳት የብሪክስ አባል አገራትና ቀሪውን ዓለም የሚጠቅም የጥናት ውጤት እንዲያቀርቡ እድል የፈጠረ መሆኑንም ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን ጨምሮ ከሁለቱ ሀገራት የጥናትና ምርምር ተቋማት የተወከሉ ምሁራን ተሳትፈዋል። በመድረኩ የብሪክስ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችሉ በአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ፣ በግብርና፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል። በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ በተካሄደው 15ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የብሪክስ አባልነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል።  
በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ ከብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ
Apr 24, 2024 366
በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ ከብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣ ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን የሀገረ መንግሥትነት ታሪኳ፣ የፖለቲካ ልዩነቶችን፣ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ፣ በንግግር፣ በውይይት እና በሕጋዊ አግባብ የመፍታት ልምምድ የላትም። እንደ አለመታደል ሆኖ ፖለቲካችን የዜሮ ድምር ፖለቲካ ነው። በሀገራችን የተለመደው በጉልበት አሸንፎ ሥልጣን የያዘ ኃይል፣ በጉልበት ተሸንፎ ሥልጣን እስኪለቅ ድረስ ሁሉንም ጠቅልሎ የሚቆጣጠርበት እና የፈቀደውን የሚያደርግበት የፖለቲካ ባህል ነው። የለውጡ መንግሥት ወደ ሥልጣን የመጣው በጉልበት አይደለም። ይሄም አዲስ የፖለቲካ ባህል ነው። ይሄን አዲስ የፖለቲካ ምእራፍ የሚያጸና ሌላ ሰላማዊ የፖለቲካ ባህል ደግሞ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሕዝብ ይሁንታ አግኝቶ መንግሥት በመመሥረት አሳይቷል። ከዚህም በመሻገር ልዩ ልዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላትን በመንግሥት ኃላፊነት በመመደብ፣ ኢትዮጵያ የጋራ ቤት መሆንዋን አስመስክሯል። ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግር ብቻውን ግብ አይደለም። ሌሎች ግቦችን ለማሳካት መሣሪያ እንጂ። የኢትዮጵያ ችግር የአሁኑን አካሄድ በማስተካከል ብቻ አይፈታም። በታሪክ ውስጥ የወረስናቸውን ስብራቶች መጠገንም የግድ ይለናል። እነዚህን የታሪክ ስብራቶች ለመጠገን ሦስት ዓይነት መፍትሔዎች ተቀምጠዋል። ነባሩን ፖለቲካዊ ችግር በሀገራዊ ምክክር መፍታት፤ የቅርብ ዘመናችንን የፖለቲካ ችግር ደግሞ በሽግግር ፍትሕ እና በተሐድሶ ማረም። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንድ መንግሥት በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን ቢይዝም እንኳን ብቻውን ሊወስናቸው የማይገቡ፣ ሀገራዊ እና አካታች ምክክር የሚፈልጉ ጉዳዮች አሉ። ይሄ ድምጽ መሰማት ከጀመረ ግማሽ ምእተ ዓመት እየዘለቀው ነው። የለውጡ መንግሥት እስከመጣበት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ግን ሰሚ አላገኘም ነበር። የለውጡ መንግሥት ሐሳቡን መቀበል ብቻ ሳይሆን ይሄንን የሚያሣልጥ ገለልተኛ ተቋምም አቋቁሟል። በዚህ ተቋም ውስጥ በኃላፊነት የተሰየሙት ክፍተኛ ልምድ እና ብቃት ያላቸው ገለልተኛ ኮሚሽነሮች ናቸው። እነዚህ ኮሚሽነሮች አካታች ሀገራዊ ምክክሩን የማከናወን ሰፊ ሥልጣን በሕግ ተሰጥቷቸዋል። በዚሁ መሠረት ባለ ድርሻ አካላትን በማማከር ሂደቱ ምን መምሰል አለበት የሚለውን ዝርዝር አካሄድ እና አሠራሩን ነድፈዋል። በአሁኑ ወቅት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በነደፈው አካሄድ መሠረት በ10 ክልሎች እና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች ከየወረዳው በምክክሩ ሂደት የሚሳተፉ ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራ አጠናቋል። በእያንዳንዱ ክልል እጅግ ጥብቅ እና አድካሚ የሆነ ሥራ ተከናውኗል። ማኅበረሰቡን ከታችኛው የአስተዳደር መዋቅር ጀምሮ አሳትፏል። በዚህም በምክክሩ አካሄድ የሚሳተፉ ዜጎች ተለይተዋል። ከ679 ወረዳዎች፣ እስካሁን 12,294 ተሳታፊዎች ተለይተዋል። ይሄ አካሄድ የጉዳዩ ባለቤት የሆነውን ሕዝብ ማዕከል ያደረገ ነው። አጀንዳዎች እና የመፍትሔ ሐሳቦች ከላይ ወደ ታች ብቻ ሳይሆን ከማኅበረሰቡም ፈልቀው፣ በውይይት ዳብረው ወደ መሐል የሚመጡበት አካሄድ ነው። በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ኮሚሽኑ በክልል ደረጃ የሚደረጉ የምክክር መድረኮችን ማካሄድ እንደሚጀምር ይጠበቃል። እንዲሁም የተሳታፊ ልየታ ባልተደረገባቸው ሁለት ክልሎች ላይ የተሳታፊዎች ልየታ በቅርቡ ይጠናቀቃል። በጉጉት የሚጠበቀው አካታች ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄድ ተስፋ ይደረጋል። ይሄንን በትውልድ መካከል አንዴ የሚገኝ ዕድል ሳናባክን፤ እያቃናንና እየደገፍን፣ ለኢትዮጵያ ነባር ችግሮች መፍትሔ አዋላጅ እንዲሆን፣ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባናል። ዕድሎችን በሰበብ አስባቡ እያባከንን፣ ራሳችንን በችግር አዙሪት የማክረም አካሄድ ማብቃት አለበት። ሁለተኛው የሽግግር ፍትሕ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች በደል፣ ግፍ እና መሠረታዊ የመብት ጥሰቶች ተከሥተዋል። ይህ በሌሎች ሀገራት ታሪክም የሚታይ ክሥተት ነው። እስከዛሬ ባለው አካሄዳችን በጉልበት አሸናፊ ሆኖ ሥልጣን የያዘው አካል፣ ሌሎችን በዳይ እና አጥፊ አድርጎ ይኮንናል፤ ይቀጣል። ይህ አካሄድ ግን ፍትሕን አያሰፍንም። እልህን፣ ቁጭትን እና የበቀል ጥማትን ያገነግናል እንጂ። የቁርሾ እና የቂም በቀል አዙሪት፣ የተበዳይነት እና የብሶት ትርክት በሀገራችን ዋነኛው የፖለቲካ ማጠንጠኛ የሆነበት አንዱ ምክንያትም ይሄው ነው። ይሄንን የበዳይ ተበዳይ አዙሪት ለመስበር የሽግግር ፍትሕ አንዱ ተመራጭ ስልት ነው። ስለዚህም የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት የፖሊሲ ማሕቀፍ ጸድቋል። የፖሊሲው ዝግጅት የሚመለከታቸውን አካላት ያሳተፈ፣ ዓለም አቀፍ ልምድን መሠረት ያደረገ ነው። በቅድመ ፖሊሲ ማርቀቅ ሂደቱ ብቻ 60 የክልል እና 20 ሀገራዊ የግብአት ማሰባሰቢያ መድረኮች ተካሂደውበታል። የፖሊሲው ዓላማ የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት እና የሚተገበርበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዘላቂ ሰላምን፣ ዕርቅን፣ የሕግ የበላይነትን፣ ፍትሕን እና ዴሞክራሲን ማረጋገጥ ነው። ይሄንን ዓላማ ለማሳካት እንደ አግባብነቱ የወንጀል ምርመራ እና ክስ፣ እውነት ማፈላለግ፣ ዕርቅ፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ምሕረት፣ ማካካሻ እና ተቋማዊ ማሻሻያ እንደ ሽግግር ፍትሕ ስልቶች በሀገራችን ተግባራዊ ይደረጋሉ። እንደሚታወቀው በሀገራችን ከመንግሥት ውጭ የሚኖር የታጠቀን ኃይል ሕገ መንግሥታችን አይፈቅድም። የመንግሥትም አንዱ መብት በብቸኝነት ኃይልን መጠቀም ነው። ነገር ግን በሀገራችን በወረስነው የፖለቲካ ስብራት የተነሣ የታጠቁ ኃይሎች ተፈጥረዋል። ሰላማችንን የጸና ለማድረግ፣ እነዚህ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅ ፈትተው፣ የተሐድሶ ሂደት ውስጥ መቀላቀል አለባቸው። የፖለቲካ ጥያቄዎቻቸውንም በሀገራዊ ምክክር ሂደት በመሳተፍ መፍታት ይችላሉ። ለዚህ የሚሆን የተሐድሶ ኮሚሽን ተቋቁሟል። ዓላማውም መሣሪያ ማስፈታት፣ የትጥቅ ቡድኖችን ሰላማዊ ማድረግና ከማኅበረሰቡ ጋር መቀላቀል ናቸው። ይሄንን የተሐድሶ ሥራ በማሳካት ፖለቲካችን ከግንባር ወደ ጠረጴዛ፣ ከጫካ ወደ አዳራሽ እንዲመለስ ማድረግ አለብን። እነዚህን ስልቶች በሚገባ ተግባራዊ በማድረግ፣ ከበዳይ ተበዳይ አዙሪት ልንወጣ ያስፈልጋል። በምሕረት፣ በይቅርታ፣ በካሣና፣ በፍትሕ ታክመን ወደፊት መጓዝ መቻል አለብን። ለዚህ ስኬትም ኢትዮጵያውያን ሁሉ በንቃትና በብቃት ልንሳተፍ ይገባናል። መንግሥትም የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አተገባበርን ከሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ጋር የተናበበ እና የሚመጋገብ እንዲሆን በማድረግ ኃላፊነቱን ይወጣል። ነባር ሀገራዊ ችግሮቻችንን በሀገራዊ ምክክር እና በሽግግር ፍትሕ እያረምን የገጠሙን የግጭትና የጦርነት ፈተናዎች ለመሻገር ደግሞ ሰላማዊ የፖለቲካ አካሄዶችን ተመራጭ ማድረግ አለብን። ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ስምምነት ለመፍታት የተፈለገውም ለዚህ ዓላማ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ በተለያዩ ወቅቶች የእርስ በርስ ግጭቶች እና ጦርነቶች በተደጋጋሚ ተከሥተዋል። በእነዚህ ጦርነቶች እንደ ሀገር ከባድ ኪሣራ ደርሶብናል። የዚህም ምክንያቱ ግጭቶችን በንግግር እና በስምምነት የመፍታት የፖለቲካ ልምምድ ብዙም ስለሌለን ነው። የለመድነው በጠላታችን መቃብር ላይ ሐውልት መገንባት ነው። የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ይሄንን ነባር ልማድ ቀይሮታል። ጦርነትን በፖለቲካዊ መፍትሔ የመቋጨት ባህል አምጥቷል። ይሄ የሰላም ስምምነት ለትውልድ የአሸናፊ ተሸናፊ ትርክትን ከቂም ጋር ላለማውረስ የተደረገ በሳልና ቆራጥ ውሳኔ ነው። ይሄንን አማራጭ ተከትለን፣ ደም መፋሰስ እና ግጭትን ማቆም ችለናል። በአማራ፣ በአፋርና በትግራይ ክልሎች የመልሶ ግንባታ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ተጀምረዋል። ሰብአዊ ድጋፍም ያለመሰናከል ወደ ትግራይ መድረስ የሚችልበትን ዐውድ ፈጥረናል። የሰላም ስምምነቱ በተፈረመ ማግሥት መንግሥት በሰላም ስምምነቱ ከገባው ግዴታ ያለፈ፣ መተማመን ለመፍጠር እና ሰላምን ለማጽናት አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ርምጃዎች በተከታታይ ወስዷል። በሰላም ስምምነቱ እስካሁን የተገኘው ውጤት እና እፎይታ እንደተጠበቀ ሆኖ ቀሪ ሥራዎችም አሉ። በተለይ በስምምነቱ መሠረት የሕወሐት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው። የማንነት እና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ጉዳይ እልባት ለመስጠት እንዲቻል የተቀመጠው አቅጣጫ ተግባራዊ መደረግ አለበት። በጦርነቱ የተፈናቀሉትን ለመመለስና ለማቋቋም የተጀመረው ሥራ እልባት ማግኘት አለበት። ካለፈ ስሕተት አለመማር የመጀመሪያውን ስሕተት ከመሥራት የባሰ ነው። ካለፈው ስሕተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉትን ሁላችንም ተባብረን አደብ ማስገዛት ይኖርብናል። ከትዕግሥት በኋላ የሚከሠት ሕግ የማስከበር ሥራ የሚኖረውን አስከፊ ውጤት ከቅርቡ ታሪካችን ልንማር ይገባልና። መንግሥት የተቋረጡ መሠረት ልማቶችን እና አገልግሎቶችን ለመጠገን እና መልሶ ለማስጀመር ወገቡን አሥሮ እየሠራ ነው። የፋይናንስ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በትግራይ ክልል ለማሣለጥ እጅግ ከፍተኛ ወጪ አውጥቷል። የሰላም የትርፍ ድርሻው ታላቅ በመሆኑ መንግሥት ከሚጠበቅበትም አልፎ ቁስልን ለመሻር የሚያስችል ሥራ እየሠራ ነው። ይሄ ግን መንግሥታዊ ኃላፊነት እንጂ ፍርሃት ተደርጎ መወሰድ የለበትም። በፕሪቶሪያ ስምምነት እንደተገለጸው፣ በሕገ መንግሥታችንም እንደተደነገገው፣ እንደ ሀገር የሚኖረን አንድ የመከላከያ ሠራዊት ብቻ ነው። ክልሎች በክልል ደረጃ ሕግ ለማስከበር ከሚያስፈልጋቸው ፖሊስ እና ሚሊሺያ ያለፈ የታጠቀ እና የተደራጀ ሠራዊት ሊኖራቸው አይችልም፤ አይገባምም። በዚህ መሠረት ትጥቅ መፍታት እና ተያያዥ ሂደቶች በተሐድሶ ኮሚሽኑ ዕቅድ መሠረት በፍጥነት ሊተገበሩ ይገባል። ወንድሞቻችን/እኅቶቻችን በተለይም ወጣቶች በተለያዩ ምክንያቶች ተገፋፍተው በጽንፈኞች እና በግጭት ጠማቂዎች ወደ ጦር ዐውድማ የሚማገዱበት አጋጣሚ አለ። መንግሥት ይሄንን ሁኔታ ከአንድ አቅጣጫ ብቻ አያየውም። እንቅስቃሴያቸው ሕገ ወጥ ስለሆነ ብቻ ጉዳዩን በጉልበት ብቻ ይፈታ ማለት እንደሌለበት ይገነዘባል። ስለዚህ ከጥፋት መንገድ ለመመለስ እና ማኅበረሰቡን ተቀላቅለው ሰላማዊ ሕይወት ለመኖር ፍላጎት ያላቸውን ታጣቂዎች ሁሉ፣ በተዘረጋ እጅ ለመቀበል መንግሥት ፈቃደኛ ነው። ይሄንን ፈቃደኝነቱን እና ፍላጎቱን በተግባር በተለያዩ ክልሎች አሳይቷል። በቤነሻንጉል ጉሙዝ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጥተዋል። እነዚህም የተሐድሶ ሥልጠና ወስደው፣ ከማኅበረሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ተደርጓል። ይሄንንም በተሐድሶ ኮሚሽን በኩል ከክልሎች ጋር በመቀናጀት አጠናክረን እንቀጥላለን። ጥረቱን የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች እንዲደግፉ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ እናደርጋለን። እነዚህን ዘላቂ መፍትሔ አምጪ ሥራዎች በአንድ በኩል እያከናወንን የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት የሚያስከብሩ አሁናዊ ተግባራትንም ማከናወናችንን እንቀጥላለን። ጽንፈኛ የፖለቲካ አመለካከቶች እንዲሁም የተደራጁ የወንጀል እና የዘረፋ ፍላጎቶች በአንዳንድ አካባቢዎች እየታዩ ናቸው። እነዚህን በገጠርም ሆነ በከተማ የሕዝብን ሰላም የሚያውኩ እንቅስቃሴዎች ለመቆጣጠር መንግሥት ሰፊ ሥራ እየሠራ ነው። የዚህ ሥራ አንዱ አካል፣ የሕግ አስከባሪ ተቋማትን እያሻሻሉ ፤ ቅንጅታቸውን እና ከሕዝብ ጋር ያላቸውን ትሥሥር እያጠናከሩ እንዲሄዱ ማድረግ ነው። በገጠር ቀበሌዎች እና መንደሮች፣ የየአካባቢው ነዋሪ በአግባቡ ሠልጥኖ አካባቢያዊ ሰላሙን ለማስከበር እንዲችል ይደረጋል። በዚህ ረገድ በአንዳንድ ክልሎች በጎ ጅምር አለ። እንደ ኢትዮጵያ ላለ እጅግ ሰፊ እና ብዙ ሕዝብ ላለበት ሀገር፣ የአካባቢ ሚሊሽያ እና ሌሎች አጋዥ ሰላም አስከባሪ አደረጃጀቶች አካባቢያዊ ሰላም እና ጸጥታን ለማስከበር ትልቅ ሚና አላቸው። ከዚያ በተጨማሪ፣ የክልል ፖሊስ ኃይሎችን መልሶ በማደራጀት እና በሁለንተናዊ መልኩ በማጠናከር፣ ሕገ መንግሥታዊ ተልዕኳችውን በአግባቡ እንዲወጡ እየተደረገ ነው። በየአካባቢው ካሉት ሚሊሺያዎች እና የክልል ፖሊሶች ጋር በመቀናጀት፣ የፌደራል ፖሊስ የሀገር ውስጥ ሰላም እና ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ቀጣይነት ያለው ተቋም ግንባታ እና ማሻሻያ እየተካሄደ ነው። ከእነዚህ ሕግ አስከባሪ ተቋማት ያለፈ ሥጋት ካጋጠመ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰላም የማስጠበቅ እና ሕግ የማስከበር ተግባሩን እየተወጣ ይገኛል። ይሄንን ዓይነት የጸጥታ አካላትና የሕዝብ ቅንጅት በመኖሩ፣ በአማራ ክልል የክልሉን መንግሥት አፍርሶ በኃይል ሥልጣን ለመያዝ ያሰበው ኃይል ፍላጎቱን ለማሳካት እንዳይችል ተደርጓል። በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ፣ የክልሉን መንግሥት እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመታደግ ተችሏል። በኦሮሚያ ክልልም በአንዳንድ የክልሉ ዞኖች የነበረው የታጣቂ ኃይሎች ሰፊ እንቅስቃሴ እና አንዳንድ ወረዳዎችን የመቆጣጠር አዝማሚያ ተቀልብሷል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም የጸጥታና የደኅንነት ሁኔታው በእጅጉ ተሻሽሏል። በአዲስ አበባ እና በሌሎችም የሀገሪቱ ትላልቅ ከተማዎች የተለያዩ የሽብር ጥቃቶችን ለመፈጸም አቅደው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ዕቅድ ለማክሸፍም ተችሏል። የተሠራው ሥራ ወሳኝ ቢሆንም በቂ ግን አይደለም። ፖለቲካ ቅብ የሆኑ የተደራጁ የዝርፊያ እና የወንጀል ቡድኖችን በሚገባ መቆጣጠር ይገባናል። ይሄንን ለማድረግም ጠንካራ እና ውጤታማ ሕግ አስከባሪ እና የጸጥታ መዋቅር እንዲኖረን የተጀመረው ሥራ ይቀጥላል። በዚህ ረገድ የሕዝብ ተሳትፎ እና እገዛ ወሳኝ ነው። እየዘረፈ፣ እየነጠቀ እና እያገተ ያለን ቡድን በተለያየ ሰበብ መሸከም እና ማባባል ማብቃት አለበት። በድኻ ገንዘብ የተሠሩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን የሚያወድም ቡድን የማንንም ፍላጎት አያስከብርም። ሕዝቡ ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር የሕግ የበላይነትን ማስከበር ይገባዋል። በየአካባቢው የሚገኙ የፖለቲካ እና የአስተዳደር መዋቅሮችም፣ ሌላ አካል መጠበቅ ሳይሆን፣ ሕግን ማስከበር ቀዳሚ ኃላፊነታቸው እንደሆነ ተገንዝበው ሊንቀሳቀሱ ይገባል። በአንድ በኩል ሕግ የማስከበርና ሰላምና ደኅንነትን የማጽናት ሥራ እያከናወንን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የተፈናቀሉ ሰዎችን የመመለስ ተግባር መከናወን አለበት። ሰላምና ጸጥታ ሕዝብ ሲረጋጋ የሚፈጠሩ ሥርዓቶች በመሆናቸው። በሀገራችን በተለያዩ ምክንያቶች፣ ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል። እነዚህ ዜጎች ከመጠለያ ካምፖች ወጥተው ወደቀያቸው መመለስ ይኖርባቸዋል። በዘላቂነት ተረጋግተው ወደ መደበኛ ኑሮ መግባት አለባቸው። ይሄንን እውን ለማድረግ መንግሥት ሲተጋ ቆይቷል፣ አሁንም ሰፊ ሥራ እየሠራ ይገኛል። ለምሳሌ በሶማሌ እና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች፣ እንዲሁም በጌዴኦ አካባቢ ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እና ዘላቂ መኖሪያ እንዲያገኙ ለማድረግ ተችሏል። በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ባጋጠመው ግጭት፤ እንዲሁም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ባጋጠሙ የጸጥታ ችግሮች የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች አሉ። እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ እየሠራን ነው። የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል አመራሮች በጋራ ሠርተው ብዙዎችን ከመጠለያ ጣቢያ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አድርገዋል። በዚህ ሂደት በማኅበረሰቡ ዘንድ ወትሮም የነበረውን መተሳሰብ እና ጥብቅ ትሥሥር ለማየት ተችሏል። የተፈናቀሉ ጎረቤቶቻቸው እንዲመለሱ በየአካባቢው ከፍተኛ ፍላጎት አለ። ለሚመለሱት ተፈናቃዮች የየአካባቢው ማኅበረሰብ የሚያደርገው አቀባበል ልብ የሚጠግን ነው። በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለምሳሌ በራያ እና አላማጣ አካባቢ ከተፈናቀሉ ዜጎች መንግሥትን ሳይጠብቁ በማኅበረሰባዊ መተሳሰብ ብቻ በርካታዎች ወደ ቤታቸው ገብተዋል። በዚህ ሂደት የተፈናቃዮችን ጉዳይ እንደ ፖለቲካ አጀንዳ አድርገው ሊጠቀሙ የሚፈልጉ አካላት መኖራቸው ታይቷል። ተፈናቃዮች ከተመለሱ የልመናና፣ የተቃውሞ አጀንዳችን ይከስራል ብለው ይፈራሉ። እነዚህ ኃይሎች ተፈናቃዮቹ ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ ፕሮፖጋንዳ እና ማስፈራሪያ ይደረድራሉ። አንዳንዴም በኃይል ጭምር የተፈናቃዮችን መመለስ ለማሰናከል ይቃጣቸዋል። መንግሥት ካለበት የሞራል እና የሕግ ኃላፊነት የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸውና ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ይቀጥላል። ከክልሎች ጋር የተጀመረው ሥራም ይጠናከራል። ሰላምና ጸጥታን ለማደፍረስ፣ የተፈናቀሉ ወገኖች እንዳይመለሱ ለማድረግና የልማት ተግባራትን ለማሰናከል አንዱ የመዋጊያ መሣሪያ የተዛባ፣ የተሳሳተና የተመረዘ መረጃን ማሠራጨት ነው። እንደሚታወቀው የመገናኛ ቴክኖሎጂ ዕድገት ዕድልም፣ አደጋም ይዞ መጥቷል። በዚህ ዘመነ መረብ ሽኩቻ እና ፉክክር ይበዛል። ነባር ተቋማት እና ሥርዓቶች በእጅጉ ፈተና ላይ ይወድቃሉ። በዚህ ዐውድ ውስጥ ሀገራት ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር ያለ ይሉኝታ እና ያለ ብዙ ልጓም የቻሉትን ሁሉ ያደርጋሉ። በዚህ ወቅት ሁኔታውን በአግባቡ በመረዳት፣ ይሄንን ማዕበል እና ወጀብ እንዴት ማለፍ አለብን የሚለውን በጥንቃቄ ተልመን ካልተንቀሳቀስን አደጋው ከባድ ነው። በዚህ ረገድ ውጤታማ ለመሆን የውስጥ አንድነት እጅግ ወሳኝ ነው። እንደ ኢትዮጵያ ያለ ትልቅ ሀገር የውስጥ አንድነት ካለው ነጥሮ ይወጣል። እንደ ሀገር እና እንደ ሕዝብ ለአንድ ዓላማ በጋራ ከተሰለፍን ወቅቱ ሀገራችንን ከፍ ለማድረግ የራሱን በጎ አጋጣሚዎች ይዞ ይመጣል። ከተከፋፈልን ደግሞ የሀገር ህልውና አደጋ ላይ ይወድቃል። ስለዚህም የሚመጡ መረጃዎችን መምረጥ፣ መመዘንና ማንጠር አስፈላጊ ነው። በምድር ያሸነፍናቸው ጠላቶቻችን በአየር እንዲመጡ መፍቀድ የለብንም። እነዚህን ሁሉ የምናከናውነው መጀመሪያ ዘላቂ ሰላም፤ በዘላቂ ሰላም በኩልም ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ነው። እንደ መንግሥት ግባችን በአቋራጭ መንገድ፣ ከላይ ከላይ በሆነ እድሳት የሚመጣ ጊዜያዊ ጸጥታ አይደለም። ዘላቂ ሰላም ነው። ዘላቂ ሰላም የጦርነት አለመኖር ብቻ አይደለም። በመርሕ እና በሥርዓት ላይ የተመሠረተ፣ በቀላሉ የማይናወጥ ሰላም ነው። ግጭትን፣ እና አለመግባባትን በሰላማዊ እና በሕጋዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዐቅም እና ሥርዓት መኖር ነው። በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ በመግባባት፣ ያለፈን ቁርሾ እና የታሪክ ጠባሳን አልፎ ወደፊት ለመሄድ መቻል ነው። ይሄንን ዘላቂ ሰላምና ዘላቂ ብልጽግና ለማምጣት አዲስ የፖለቲካ ባህል የግድ ነው። ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክር፣ የሽግግር ፍትሕ እና የተሐድሶ ተግባራት የዚህ ማከናወኛ ዋነኞቹ መሣሪያዎች ናቸው። ማንም እንደሚያውቀው አካታች የሆነ መንግሥታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ፈር ቀዳጅ እየሆንን ነው። ይህ ጥረት ውጤታማ እንዲሆን ግን የመንግሥት ተግባር ብቻውን በቂ አይሆንም። ገዢው ፓርቲ አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማስተዋወቅ - አብረን እንሥራ፣ እንምከር፣ በጋራ ለሀገራችን ጉዳዮች መፍትሔ እንፈልግ እያለ ነው። አንዳንዶች ደግሞ በድሮ በሬ እያረሱ በጉልበት፣ በኃይልና በጠመንጃ መንግሥትን ጥለን ሥልጣን ጠቅልለን ካልወሰድን እያሉ ናቸው። እንደዚህ በተቃራኒ መንገዶች ተጉዘን የተጀመሩት ጥረቶቻችን ሊሳኩ አይችሉም። የ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ባህልን ይዞ በ22ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መሄድ ርግማን እንጂ ለውጥ አያመጣም። ጦርነት ሁላችንንም ያከስራል። ሰላም ሁላችንንም አትራፊ ያደርጋል። እኛ ከአባቶቻችን ስለጦርነት እየሰማን አደግን፤ ይበቃናል። በእኛ ትውልድ እንኳን ሁለትና ሦስት ከባድ ጦርነቶች አለፉ። ለቀጣይ ትውልድ ግን ብልጽግናን እንጂ ቁስልን ማውረስ የለብንም። የኢትዮጵያን ዘመናዊ የፖለቲካ ቅኝት ለሃምሳ ዓመት የበየነው የ1966ቱ አብዮት ከተከሠተ ግማሽ ምእተ ዓመት ሆኖታል። አዙሪቱ ያልለቀቃቸው ግን አሁንም አሉ። ካለፈው ተምረን፣ የራሳችንን እና የዘመናችንን ዐውድ ተገንዝበን፣ በራሳችን ቅኝት እና አጀንዳ ወደፊት ልንራመድ ይገባል። የዚህ ትውልድ የሃምሳ ዓመት አጀንዳ ዘላቂ ሰላም እና ሁለንተናዊ ብልጽግና ነውና። የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሚያዚያ 16፣ 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ ከኡጋንዳ ጋር ያላትን ወዳጅነት በንግድና ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር እየተሰራ ነው - አምባሳደር እጸገነት በዛብህ
Apr 24, 2024 108
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከኡጋንዳ ጋር ያላትን ታሪካዊ ወዳጅነት በንግድና ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እጸገነት በዛብህ ተናገሩ፡፡ በኡጋንዳ፣ ቡርንዲ፣ ሲሸልስ፣ ኮሞሮስና መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እጸገነት በዛብህ፤ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በ1964 በኡጋንዳ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የሁለቱ አገራት ግንኙነት በይፋ መጀመሩን ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡ ይህን ተከትሎም በሁለቱ አገራት መካከል ጠንካራ ግንኙነት መፈጠሩን ጠቅሰው፤ አገራቱ በተለይ በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም በፓን-አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ትብብር ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡ በቅርቡ የኡጋንዳ የትምህርት ጉዳዮች ልዑክ ኢትዮጵያ በዘርፍ እያከናወነች ካለው ስራ ልምድ ለመቅሰም መምጣቱን አስታውሰው፤ ይህም የአገራቱ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን አመላከች ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በኡጋንዳ እንደሚኖሩና የሁለቱ አገራት ህዝቦችም በርካታ የሚጋሯቸው እሴቶች እንዳሏቸው አመላክተዋል፡፡ በመሆኑም ይህንን ታሪካዊ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ለማጠናከር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ የኢትዮ-ኡጋንዳ ቀን በማዘጋጀት የሁለቱን አገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከርም እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ ከህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ባሻገር በንግድ ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር እንደሚሰራ ጠቅሰው፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ረገድ ትልቅ አቅም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ከኡጋንዳ በተጨማሪ ቡርንዲ፣ ሲሸልስ፣ ኮሞሮስና መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ መሰል ስራዎችን በማከናወን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ይበለጥ ለማጠናከር እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡                    
ማስታወቂያ
ኢዜአ
Feb 7, 2023 17982
ኢዜአ
ፖለቲካ
በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞኖች በጸጥታ ሃይሎችና በህዝቡ ተሳትፎ በተከናወነ ተግባር ሰላምና መረጋጋት እየሰፈነ መሆኑ ተገለጸ
Apr 24, 2024 43
ነቀምቴ ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞኖች በጸጥታ ሃይሎችና በህዝቡ ተሳትፎ በተከናወነ ተግባር ሰላምና መረጋጋት እየሰፈነ መምጣቱን የአገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች ገለጹ። በአካባቢው ሰላምን የማጽናት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል። የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች ይህን የገለጹት የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ጸጥታ ፅህፈት ቤት የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸምን ዛሬ በነቀምቴ ከተማ በተገመገመበት ወቅት ነው። መድረኩ ላይ የተገኙት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት እንደገለጹት፤ በጸጥታ ሃይሎችና በህዝቡ ተሳትፎ በአካባቢው ሰላም የማስፈን ጥረት ውጤታማ ነው። ህብረተሰቡ ለሰላምና ደህንነት ማስከበር ስራው በአቅሙና መረጃዎችን በመስጠት ሀላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ጠቁመው ለፀጥታው መረጋገጥ ያሳየው አቋም ለጸረ ሰላም ቡድኑ አላማ መክሸፍ አስተዋጽኦ እንዳለው አመልክተዋል።   የኦነግ ሸኔ አባላት እየፈጸመ ያለውን የዘረፋ እና የወንጀል ድርጊት መሆኑን ተረድተው በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሊሰጡ እንደሚገባ ነው የተናገሩት። መንግስት ዛሬም ለሰላሙ የከፈተው በር ስላልተዘጋ ከጦርነቱ ይልቅ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል። የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ዞኖች በጸጥታ ሃይሎችና በህዝቡ ተሳትፎ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተገኝቷል። "የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በቁርጠኝነት በተሰራ ስራ በርካታ ለውጦች ተመዝግበዋል" ሲሉም አክለዋል። "የህብረተሰቡ ተሳትፎ ለስራው መሳካት ትልቁን ሚና እየተጫወተ ይገኛል" ያሉት ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ፤ ሰላምን የማጽናት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ለሜሳ ኦልጂራ በወቅቱ እንዳሉት፤ በዞኑ ባሉ ወረዳዎች የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተሰራ ስራ ውጤት ተመዝግቧል። ህብረተሰቡን ወደ ቀድሞ የልማት እንቅስቃሴ እየተመለሰ መሆኑን ጠቁመው፤ የተጀመረው የህግ ማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ወጋሪ ነገራ በበኩላቸው፤ በዞኑ ወረዳዎች ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆሙ በተከናወኑ ስራዎች ሰላምና ጸጥታን በማስከበር ረገድ ውጤት መገኘቱን አንስተዋል። ሁሉን አቀፍ ልማት ለማምጣትና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑት ተግባራት ለዘላቂ ሰላም መስፈን መሰረት እየጣሉ መምጣታቸውን ተናግረዋል ። የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠል ተሳትፏቸውን እንደሚያጠናክሩ ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ 4ኛው አለም አቀፍ የፋይናንስ የልማት ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ቁርጠኛ ናት - አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ 
Apr 24, 2024 45
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ በመጪው ሃምሌ የሚካሄደውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 4ኛው አለም አቀፍ የፋይናንስ ለልማት ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ ገለፁ። አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና መሀመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በዚህ ወቅት አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ፤ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 4ኛውን የፋይናንስ ልማት ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በመንግስታቱ ድርጅት መካከል ስላለው ዘርፈ-ብዙ አጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ተገልጿል። በተጨማሪም በዘላቂ የልማት ግቦች የትግበራ ሁኔታ፣ በመጪው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እና በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይም ውይይት ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
በብሪክስ ጥምረት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ ነው
Apr 24, 2024 64
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ በብሪክስ ጥምረት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡ የብሪክስ ጥምረት 10 አገራትን በማቀፍ 37 በመቶ የኢኮኖሚ እና 45 በመቶ የዓለም አቀፍ የህዝብ ቁጥር የሚሸፍን ግዙፍ የትብብር ጥምረት መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። የኢትዮጵያ እና ሩሲያ የጥናትና ምርምር ተቋማት የባለሙያዎች ቡድን በብሪክስ ጥምረት ስር ትብብርን ማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡   የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ፤ በመድረኩም በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ሌሎች ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ግንዛቤ ያላቸው ምሁራንና የምርምር ተቋማት መሳተፋቸውን ገልጸዋል። በወቅቱ በሩሲያ ሊቀመንበርነት የሚመራው የብሪክስ አባል አገራት ጥምረት የመሪዎች ጉባኤ በመጪው ግንቦት ወር በሩሲያ ሞስኮ እንደሚካሄድም አስታውቀዋል። መድረኩም በመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ መፍትሔ አመላካች አጀንዳዎች ላይ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ የሚያቀርቡበት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ እነዚህ ሃሳቦችም በመሪዎች አማካኝነት የጥምረቱ የጋራ አጀንዳዎች እንደሚሆኑ ነው የተናገሩት፡፡ የኢትዮጵያ ባለሙያዎችም ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ በብሪክስ ጥምረት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በሩሲያ የብሪክስ ምክር ቤት ኃላፊ ቪክቶሪያ ፓኖቫ (ዶ/ር)፤ በብሪክስ ማዕቀፍ ስር የሚካሄዱ የምክክር መድረኮችም ለመሪዎች ጉባኤ ውሳኔ የሚበጁ ምክረ ሃሳቦችን ለማፍለቅ ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖራቸውም ገልጸዋል።   በብሪክስ አባል አገራት መካከል የሚደረገው ትብብር ከጥምረት ባሻገር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚበጁ ችግር ፈቺ ሃሳቦች እንዲተገበሩ እንደሚያደርግም አንስተዋል፡፡ በመድረኩም የኢትዮጵያ ምሁራንም ከሀገራቸው ብሔራዊ ጥቅም በመነሳት የብሪክስ አባል አገራትና ቀሪውን ዓለም የሚጠቅም የጥናት ውጤት እንዲያቀርቡ እድል የፈጠረ መሆኑንም ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን ጨምሮ ከሁለቱ ሀገራት የጥናትና ምርምር ተቋማት የተወከሉ ምሁራን ተሳትፈዋል። በመድረኩ የብሪክስ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችሉ በአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ፣ በግብርና፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል። በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ በተካሄደው 15ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የብሪክስ አባልነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል።  
ለከተማችን ሰላም መከበርና ልማት መጠናከር የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ
Apr 24, 2024 96
ደሴ ፤ ሚያዝያ 16 / 2016(ኢዜአ)፡-በደሴ ከተማ ሰላምን በማስከበር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የድርሻቸውን እንደሚወጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ከከተማው የተወጣጡ ነዋሪዎች በደሴ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ ከጎብኚዎቹ መካከል ወይዘሮ የኔነሽ ደምሴ በሰጡት አስተያየት፤ በከተማው ነዋሪዎች የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ የግንባታ እንቅስቃሴዎች መመልከታቸውን ተናግረዋል። በከተማው ያለውን ሰላም በማስከበር እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም የመናሃሪያና ሌሎች ልማቶች የደሴን ሁለንተናዊ እድገት የሚያፋጥኑ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ልማቶች በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት እንዲጠናቀቁ በሚችሉት አቅም ሁሉ የጀመሩትን እገዛ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።   ሌላው የጉብኝቱ ተሳታፊ አቶ መሃመድ የሱፍ በበኩላቸው፤ ዛሬ ተዘዋውረው የተመለከቷቸው የልማት ስራዎች የነዋሪውን ህዝብ ጥያቄ ለመመለስ የሚያግዙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ያዋጡት ገንዘብ በተግባር ልማት ላይ ውሎ የከተማውን እድገት ለማፋጠን ድርሻው የጎላ በመሆኑ በከተማው ዘላቂ ልማት እንዲኖር የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ''መንግስት ህብረተሰቡን በማሳተፍ ዘላቂ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል'' ያሉት ደግሞ የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቃሲም አበራ ናቸው፡፡   ከስምንት ኪሎ ሜትር በላይ የአስፋልት መንገድ፣ ሁለት መናሃሪያ፣ ድልድይና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች እየተገነቡ መሆኑን ጠቁመው፤ አብዛኛዎቹ የልማት ፕሮጀክቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ህብረተሰቡ ልማቱን በተግባር ያለበትን ሁኔታ ተመልክቶ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጉብኝቱ መካሄዱን አክለዋል፡፡ የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፤ ህብረተሰቡ አንድነቱንና ሰላሙን ጠብቆ በከተማው ልማት አሻራውን እያሳረፈ መሆኑን ገልጸዋል።   ዘንድሮ ብቻ ከአንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት የተለያዩ ልማቶች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ልማቱ በስኬት እንዲቀጥል ህብረተሰቡ የጀመረውን ሁለተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመልክተዋል። በጉብኝቱ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ነጋዴዎችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡  
የመዲናዋን የዲፕሎማሲ ከተማነት የሚመጥን የሰላምና ጸጥታ ስራዎች እየተሰሩ ነው
Apr 24, 2024 78
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፡-በአዲስ አበባ ነዋሪውን ያሳተፈና የዲፕሎማሲ ከተማነቷን የሚመጥን የሰላምና ጸጥታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ምክትል ሃላፊ ጌታሁን አበራ አዲስ አበባ የተለያዩ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ተቋማት የሚገኙባት የዲፕሎማቲክ ማዕከል በመሆኗ ከልማት ባለፈ ሰላምና ጸጥታዋን አስተማማኝ የማድረግ ተግባራት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እየተሰራ ነው ብለዋል። ሰላምን ማስጠበቅ የአንድ ተቋም ኃላፊነት ብቻ ባለመሆኑ ነዋሪውን በማሳተፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ውጤት እያስገኙ መሆኑን ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ አንስተዋል። አዲስ አበባ የዲፕሎማሲ ከተማነቷን የሚመጥኑ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። የመዲናዋ ነዋሪ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የከተማዋን ሰላም በማስጠበቅ ስራ ላይ መሰማራቱን ገልጸው የጸጥታ መዋቅሩ በበኩሉ ስምሪት በሚሰጠው ቦታ ላይ በንቃት እየሰራ ነው ብለዋል። በከተማዋ የሚከበሩ የተለያዩ ባህላዊና ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር የሚከበሩት ህብረተሰቡ ፣ተቋማትና በየደረጃው ያሉ የጸጥታ መዋቅር በከፍተኛ ቅንጅት በመስራታቸው ነው ብለዋል። የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ አስተማማኝ ለማድረግ የወንጀል ድርጊቶችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ አደረጃጀቶችና ጠንካራ የመረጃ ስርዓት መፈጠሩንም አንስተዋል። ለወንጀል ድርጊቶች መነሻ የሆኑ ቦታዎችን በመረጃ ላይ ተመስርቶ በመለየት ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል እየሰሩ መሆኑንም አስረድተዋል። በውስጥና በውጭ ያሉ የተለያዩ ሃይሎች በአዲስ አበባ ላይ የራሳቸው ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ተከትሎ ችግር ለመፍጠር የተለያዩ ሙከራዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል። የጸጥታ መዋቅሩ ከህዝብ ጋር ተቀናጅቶ በሚሰራው ስራ በከተማዋ በተለያዩ ጊዜያት ሊፈጠሩ የነበሩ የወንጀል ድርጊቶችን ማክሸፍ መቻሉንም አንስተዋል። የሰላምና ጸጥታን ጉዳይ ህዝባዊ የማድረጉ ስራ ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑንና ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
የኢትዮ-ጅቡቲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚቴ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው
Apr 24, 2024 82
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፡- የኢትዮ-ጅቡቲ 16ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚቴ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በጅቡቲ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ እና የጅቡቲ የመሠረተ ልማት ሚኒስትር ሀሰን ሁማድ ተገኝተዋል።   ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) መድረኩ በ16ኛው የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ስምምነት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች እንዲሁም ከስምምነቱ በኋላ በተከሰቱ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ መፍትሄዎችን ለማስቀመጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ስብሰባው በሁለቱ ሀገራት የትብብር ማዕቀፎች፣ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና በጠረፍ ንግድ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡ በተጨማሪም በዲኪል ጋላፊ መንገድ ግንባታ መጓተት ዙሪያ እና በመሰል ነጥቦች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ በጅቢቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
አቅሞችንና ሀብቶችን አቀናጅቶ በመጠቀም ትልቅ የልማት ጉልበት ለመገንባት የመንግስታትን ግንኙነት ማጠናከር ወሳኝ ነው
Apr 24, 2024 120
አዳማ፣ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፡-የተለያዩ አቅሞችና ሀብቶችን አንድ ላይ አቀናጅቶ በመጠቀም ትልቅ የልማት ጉልበት ለመገንባት የመንግስታት ግንኙነት ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ቸሩጌታ ገነነ ገለጹ። የደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የመንግስታት ግንኙነት የጋራ ፎረም ምስረታ የውይይት መድረክ በአዳማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዚሁ ወቅት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ቸሩጌታ ገነነ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ክልሎች የጋራ ችግሮቻቸውን ተወያይተው በጋራ እንዲፈቱ ለማስቻል ግንኙነታቸው መጠናከር አለበት። ግንኙነታቸው ሲጠናከር ችግሮቻቸውን የሚፈቱበት፣ የመነጋገርና የመደራደር ልምዳቸው የሚጎለብትበት አሰራር እንዲያመቻቹ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል። ችግሮቸውን ተነጋግረው ከመፍታት በተጓዳኝ የጋራ የመልካም አስተዳደርና ልማት አጠናክረው ለማስቀጠል እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የመንግስታት ግንኙነት ፎረም መመስረት ሚናው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል። የመንግስታት ግንኙነት መጠናከር የጋራ ፍላጎቶችን ከማሳካት አልፎ ህብረ ብሔራዊ የፌዴራል ስርዓቱን እና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልጸው፤የሰላም ሚኒስቴርም ከፌዴሬሽን ምክርቤትና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።   በፌዴሬሽን ምክር ቤት የመንግስታት ግንኙነት የዴሞክራሲያዊ አንድነትና የህገ መንግስት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ ወይዘሮ ባንችይርጋ መለሰ በበኩላቸው ፤ ከተናጥል ጥረቶች ይልቅ የጋራ አቅሞችን በተገቢው መልኩ አቀናጅቶና አዋህዶ መጠቀም ዘርፈ ብዙ የልማትና መልካም አስተዳደር ስኬቶችን እንደሚያጎናጽፍ ገልጸዋል። የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታትና የጋራ ልማትን ለማፋጠን የክልል መንግስታት ግንኙነት ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አመልክተው፤ በዚህ ረገድ አዋጆችና የህግ ማዕቀፎች መዘርጋታቸውን ተናግረዋል። ህጎቹን ወደ መሬት ለማውረድ ደግሞ መሰል የፎረሞች ምስረታ አስፈላጊ መሆኑን ተናግሯል። መድረኩ የአጎራባች ክልሎች የመንግሥታት ግንኙነት የፎረም ምስረታ እውን ለማድረግ ያለመ መሆኑንም አክለዋል።   ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሳዓዳ አብዱረህማን እንዳሉት፤ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከርና የመንግስታት ግንኙነትን ለማጠናከር ፎረሙ ወሳኝ ነው። በተለይም የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና ሌሎች አለመግባባቶችን በጋራ ለመፍታት ፎረሙ የጎላ ፋይዳ አለው ብለዋል። በመድረኩ ከኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ጋምቤላ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሎች የተውጣጡ አፈ ጉባኤዎችና ምክትል አፈ ጉባኤዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።    

ማህበራዊ
በክልሉ አዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅን ተግባራዊ ለማድረግ የግንዛቤ ሥራዎችን መስራት ይገባል - ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ
Apr 24, 2024 57
ቦንጋ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉን ያሳተፈ ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን መስራት እንደሚገባ ተገለጸ። በህዝብ ተወካዮች ምክር በቅርቡ በጸደቀው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 አስፈላጊነትና ተግባራዊ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ገለጻ ተደርጓል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እንዳሉት በክልሉ አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉን ያሳተፈ ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን መሥራት ያስፈልጋል። በክልሉ በኪራይ ቤት የሚኖሩ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ጠቁመው፣ አዋጁ የተከራይና አከራዩን መብት ከማስጠበቅ ባለፈ መንግስትም ከዘርፉ ማግኘት ያለበትን ገቢ እንዲያገኝ የሚያስችል ነው ብለዋል። በተጨማሪም በአከራይና ተከራይ መካከል ሲፈጠሩ ለነበሩ ችግሮች መፍትሔ ስለሚሰጥ በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ለተግባራዊነቱ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል። የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ የማታዓለም ቸኮል በበኩላቸው ቢሮው ለአዋጁ ተፈጻሚነት የተለያዩ ተግባራትን እንደሚያከናውን ገልፀዋል። በቀጣይ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በመውረድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እንደሚሰሩ የገለጹት ሀላፊው፣ በየደረጃ ያሉ ባለድርሻ አካላትም ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። በመድረኩ የአዋጁ ዝርዝር ሀሳቦች ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት የተደረገ ሲሆን ለተግባራዊነቱ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል። አዲሱ የመኖሪያ የቤት ክራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ምክንያታዊና ፍትሀዊ ያልሆኑ የቤት ኪራይ ጭማሪዎችን እንደሚያስቀር ተመላክቷል። መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም በህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት የጸደቀው አዋጁ የመኖሪያ ቤት ችግር በስፋት በሚስተዋልባቸው ከተሞች ተግባራዊ የሚደረግ ስለመሆኑና ዝርዝር አፈጻጸሙ ግን ለከተማ መስተዳድሮችና ለክልሎች እንደሚሰጥ ተገልጿል።  
በክልሉ ፍርድ ቤቶች ላይ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በመፍታት የተሳለጠ የፍትህ አሰጣጥን ማጎልበት ይገባል
Apr 24, 2024 73
ሐረር፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል ፍርድ ቤቶች ላይ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በመፍታት የተሳለጠ የፍትህ አሰጣጥ ማጎልበት እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሱልጣን አብዱሰላም አስገነዘቡ። በሀገር አቀፍ ደረጃ በመተግበር ላይ ያለውን የፍትህ አስተዳደር ሪፎርም በክልሉ በሚተገበርበት ሁኔታና ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።   በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም እንደገለጹት በክልሉ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ለህዝቡ የተሳለጠ ፍትህ ለመስጠት በርካታ ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ። ፍርድ ቤቶቹ በሚያከናውኗቸው የፍትህ አሰጣጥ ሂደት ላይ ጠንካራ የሆኑ አሰራሮች ቢኖሩም ውስንነቶችም እንደሚታዩ አልሸሸጉም። በተለይም በክልሉ ፍርድ ቤቶች ላይ ከፍትህ አሰጣጥና ከሌሎች ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በመፍታት ለህብረተሰቡ የተሳለጠ የፍትህ አሰጣጥ መስጠት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ሊሆን ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል። ከዚህም ባለፈ ህብረተሰቡ የሚተማመንበትና እውነተኛ ፍትህ የሚያገኝበት ፍርድ ቤቶችን መገንባት እንደሚገባ በማከል። እንደ አፈ ጉባዔ ሱልጣን ገለፃ መድረኩም በፍርድ ቤቶች ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመለየት እገዛ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። በሀገር ደረጃ እየተሰሩ ያሉ የፍትህ አካላት ሪፎርምን በክልሉም ተግባራዊ ለማድረግ ፍርድ ቤቶቹ፣ ከዐቃቤ ህግ፣ ከፓሊስና ማረሚያ ቤቶች ጋር እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ ይኸም እስከታችኛው የእርከን ደረጃ እንዲወርድ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የሐረሪ ክልል ምክር ቤት የህግ አስተዳደር፣ ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ኢማን መሐመድ በበኩላቸው ከፍርድ ቤቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ መድረኩ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። በተጨማሪም በሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ በአጠቃላይ የፍትህ አሰጣጡና አሰራሩ እንዲሁም ከህዝቡ እርካታ አንጻር የተከናወኑ ስራዎች በሰፊው ለመገምገምና ምክር ቤቱም የሚያደርገውን የድጋፍና ክትትል ስራዎች ለማጠናከር መድረኩ አስፈልጓል ብለዋል። ለሁለት ቀናት በተሰናዳው መድረኩ የክልሉ አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፣ ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሐመድን ጨምሮ የክልሉ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንትና የምክር ቤቱ አባላትና ሌሎችም ተገኝተዋል።
ሐረርን ለነዋሪዎቿና  ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ 
Apr 24, 2024 106
ሐረር፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፦ሐረርን ለነዋሪዎቿ ና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ። የከተማው ማዘጋጃ ቤት በከተማው የሚስተዋለውን የፕላስቲክ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከኪዩቢክ ኢትዮዽያ ፕላስቲክ ማምረቻ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር ተፈራርመዋል። በስምምነቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደተናገሩት ሐረርን ለነዋሪውና ለጎብኚው ምቹ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። በተለይም በከተማው የአካባቢ ብክለትን እያባባሱ ከሚገኙት መካከል የፕላስቲክ ቆሻሻዎች አንዱ ስለመሆኑም አውስተዋል።   የፕላስቲክ ቆሻሻ ከአካባቢ ብክለት ባለፈም የአፈር ለምነትን በመቀነስ ምርትና ምርታማነት ላይ ተጽዕኖ እያስከተለ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈም በእንስሳት ህይወትና ዕፅዋት ላይም ጉዳት እያስከተለ እንደሚገኝ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ለመከላከል በአገር አቀፍ ደረጃ "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ሐሳብ ንቅናቄ መጀመሩንም አስታውሰዋል። በዚህ ረገድ በፕላስቲክ ተጽዕኖ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመከላከልና በዘርፉም የስራ እድል ለመፍጠር ጥረቶች ሲካሄዱ መቆየታቸውን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም ኪዩቢክ ኢትዮዽያ ፕላስቲክ ማምረቻ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን መልሶ ለመጠቀምና ለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ያለመ ስራ ይዞ መምጣቱ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም በተለይም በክልሉ ያለውን ውስን መሬት ከቆሻሻ በማዳን በአግባቡ ለልማት መጠቀም ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል። የሐረር ከተማ መዘጋጃ ቤት ስራአስኪያጅ አቶ አሰፋ ቶልቻ በበኩላቸው ኩባንያው የሚያከናውነው ስራ ደረቅ ቆሻሻ የሆነውን ፕላስቲክ ወደ ሀብት የሚቀይር ነው። እንዲሁም ስነ ምህዳርን በመጠበቅና የስራ እድል በመፍጠር የጋራ ተጠቃሚነትን ያጎለብታል ብለዋል። የኪዩቢክ ኢትዮዽያ ፕላስቲክ ማምረቻ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ስራ አስኪያጅ አቶ ቅዱስ ፍስሃ እንዳሉት ኩባንያው የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን በመፍጨት ጡብ፣ ብሎኬት፣ኮለንና ሌሎች ለግንባታ የሚያገለግሉ ቁሶችን ያመርታል። በዚህም የአካባቢንና የከተሞችን ውበት በማስጠበቅ ለዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል። የመግባቢያ ሰነዱንም የከተማው ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ቶልቻ እና የኪዩቢክ ኢትዮዽያ ፕላስቲክ ማምረቻ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ስራ አስኪያጅ አቶ ቅዱስ ፍስሃ ተፈራርመዋል።  
ኢዜአ ዓለም አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋት ለሚያከናውናቸው ሥራዎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበኩሉን ድጋፍ ያደርጋል- አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ
Apr 24, 2024 108
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዓለም አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋት ለሚያከናውናቸው ሥራዎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበኩሉን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለፁ። አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን አዲስ የሚዲያ ኮምፕሌክስ እና የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል። ኢዜአ ለሀገር ውስጥና ለውጭ መገናኛ ብዙኃን የመረጃ ምንጭ ሆኖ ለሀገር ገጽታ ግንባታ ባለውለታ ተቋም እንደሆነ ገልጸው፤ በጉብኝታቸው ኢዜአ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ አደረጃጃት መፍጠሩን መመልከታቸውን ገልጸዋል። ኢዜአ ተደራሽነቱን በማስፋት ለመንግሥት፣ ለግልና ለዲጂታል መገናኛ ብዙኃን የመረጃ ምንጭ በመሆን የመረጃ ክፍተትን በመሙላት ረገድ አቅምና ደረጃውን እያሳደገ መምጣቱን እንደተረዱም ተናግረዋል። በሀገር ውስጥ ተደራሽነቱን በማስፋት መረጃን ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ ትልቅ ሥራ እየሰራ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በብዙ መለኪያዎች ትልቅ የመረጃ አመንጪ ሀገር እንደሆነች ጠቅሰው፤ ይህን መረጃ አደራጅቶና አጠናቅሮ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማድረስ ለሀገር ገጽታ ግንባታ ያለውን ሚና አንስተዋል። በተለይም የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ባገናዘበ አግባብ በበርካታ የውጭ ቋንቋዎች የመረጃ ተደራሽነትን በማስፋት በቀጣናው፣ በአህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን ማስተዋወቅ ይገባል ብለዋል። በዚህ ረገድ ኢዜአ የዓለም አቀፍ የመረጃ ምንጭነቱን ለማስፋት ከቀጣናዊና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ጋር ትብብርና አጋርነትን ለማስፋት የጀመረውን ጥረት አድንቀዋል። ኢዜአ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተደራሽነትና አጋርነትን ለማስፋት የሚያደርጋቸውን ጥረቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። ኢዜአ ብሔራዊ መግባባት የመፍጠርና የሀገር ገፅታ ግንባታ ተልዕኮውን ለማሳካት ዜና እና ዜና ነክ መረጃዎችን ለመገናኛ ብዙኃን በማሰራጨት የኢትዮጵያ ብቸኛው የዜና ወኪል ነው። ዘመኑን በዋጁ ቴክኖሎጂዎች ራሱን እያደራጀ የሚገኘው ኢዜአ በሀገር ውስጥ 38 ቅርንጫፎች፣ በስምንት ቋንቋዎች እና በተለያዩ አማራጮች መረጃን ለሕዝብ ተደራሽ እያደረገ ነው። በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ተደራሽነቱን ለማስፋትም ከዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ጋር የትብብር አድማሱን እያሰፋ ሲሆን በቀጣናው አገራትም ቅርንጫፎችን ለመክፈት በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ኢኮኖሚ
የሕብረት ሥራ ማህበራት በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ ትኩረት ተደርጓል -አቶ እንዳሻው ጣሰው
Apr 24, 2024 65
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረት ሥራ ማህበራት በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ የአመራርና የአደረጃጀት ማሻሻያ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ። “ህብረት ስራ ማህበራት ለዘላቂ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ የሕብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል። በስነስርዓቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው እንደገለጹት፣ ማህበራቱ በክልሉ የኑሮ ውድነትን ለማርገብና የአባሎቻቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ጉልህ ሚና አላቸው። በገበያ የዋጋ መናር በህዝብ ላይ ጫና እንዳይፈጥር የግብርናና የፋብሪካ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ እያበረከቱት ያለው አስተዋጾ ላቅ ያለ መሆኑንም ጠቅስዋል።   ማህበራቱ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ የሪፎርም ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ እነዚህ ተግባራት የማህበሩን አባላትና የነዋሪውን ተጠቃሚነት ይበልጥ ያሳድጋሉ ብለዋል። ማህበራቱ በብቁ ባለሙያ እንዲመሩ፣ አሰራራቸው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲያስደግፉ እንዲሁም የፋይናንስ ግልጸኝነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ማሻሻያው አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የፌዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ በበኩላቸው እንዳሉት ህብረት ሥራ ማህበራቱ ከቆይታቸውና ከአባሎቻቸው ብዛት ጋር ሲነጻጸር ብዙ ማደግ ሳይችሉ ቆይተዋል። ይህን በመለወጥ ጠንካራና ሀገራዊ ሚናቸውን ለማጉላት ችግሮቻቸውን ፈቶ በተጠና መንገድ ለማዋሀድና ተቀናጅተው እንዲሰሩ ለማድረግ ማሻሻያው መዘጋጀቱን ገልጸዋል። "ለማሻሻያው ምክንያት ከሆኑት ውስጥ የአደረጃጀት፣ የአመራርና የአሰራር እንዲሁም የፋይናንስ ክህሎት ችግሮች ይጠቀሳሉ" ያሉት አቶ ሺሰማ፣ እነዚህ ችግሮች ሲፈቱ የአገልግሎት አቅማቸው ይሰፋል ብለዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንዳሉት፣ በክልሉ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ 5 ሺህ 600 የሕብረት ስራ ማህበራት አሉ። ማህበራቱ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል እንዳላቸው ጠቁመው፣ እነዚህ ማህበራት የተሻሻለ ቴክኖሎጂን በማቅረብ፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ በገንዘብ ቁጠባና ብድር እንዲሁም ገበያን በማረጋጋት ረገድ የጎላ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። ማህበራቱ በክልሉ እያበረከቱት ያለውን አስተዋጾ ከዚህም በላይ ለማሳደግ በአዲስ መልክ ተዋህደውና ተደራጅተው ወደ ሥራ እንዲገቡ ክልሉ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በመድረኩ ላይ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ በክልሉ በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት፣ ዩኒየኖችና ፌዴሬሽኖች ተሳትፈዋል። ከንቅናቄ መድረኩ ጎን ለጎን የግብርና ምርቶች ለሸማቹ የቀረበበትና ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ባዛር በምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ተከፍቷል።      
በዞኑ በመኸር ወቅት 22 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል የሰብል ምርት ለማግኘት ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል 
Apr 24, 2024 50
መተማ ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ በምዕራብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት 22 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል የሰብል ምርት ለማግኘት ታቅዶ የእርሻ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። "ያለ ግብርና የለም ልዕልና" በሚል መሪ ሃሳብ የ2016/17 ምርት ዘመን የመኸር ሰብል ልማት ንቅናቄ መድረክ ዛሬ ተካሂዷል። የመምሪያው ኃላፊና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አንዳርግ ጌጡ እንዳሉት፤ ዞኑ ለምግብ፣ በውጭ ገበያና ለፋብሪካ ግብዓት የሚሆኑ የግብርና ምርቶች በስፋት የሚመረትበት ነው። በምርት ዘመኑ መኸር ወቅት ከ518 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ የሰብል ዘር በመሸፈን 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምር ለማግኘት ታቅዶ የእርሻ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።   ያለውን ሰፊ የእርሻ መሬት የተሻሻሉ አሰራሮችን በመተግበርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ከወዲሁ እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልፀዋል። አርሶ አደሩን ከተበጣጠሰ የአስተራረስ ዘዴ ለመውጣት ጅምር ስራዎች እንዳሉ አመልክተው፤ ይህን በማስፋት በኩታ ገጠም የማልማት አሰራርን መከተልና ሜካናይዜሽንን ማሳደግ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። ከሚለማው መሬት ውስጥ 250 ሺህ ሄክታር የሚሆነውን በኩታ ገጠምና በትራክተር የሚታረስ መሆኑን አስገንዝበዋል። በእቅድ የተያዘውን ምርት ለማግኘትና በሄክታር የሚገኘውን አማካኝ ምርት መጠን ከ19 ኩንታል ወደ 24 ኩንታል ለማሳደግ ግብ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ በበኩላቸው በምርት ወቅቱ የተያዘው እቅድ እንዲሳካ ሁሉም ባለድርሻ አካል የሚጠበቅበትን እንዲወጣ አሳስበዋል ። የመተማ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት ፈቃዱ "በወረዳው በመኸር ወቅት 160 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ ነው" ብለዋል። አሁን ላይ የግብዓት ስርጭት ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አመልክተዋል። በወረዳው ለሃገራዊ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴው የጎላ ጠቀሜታ ያላቸው ሰሊጥ፣ ጥጥና አኩሪ አተር በምርት ወቅቱ በዋናነት ትከረት የተሰጣቸው መሆኑን አስታውቀዋል። መድረኩ ከሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።  
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት ተችሏል
Apr 24, 2024 61
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ። "ኢትዮጵያ ታምርት፤ እኛም እንሸምት" በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ አውደ ርዕይና ባዛር ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፍቷል።   የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለውጪ ንግድ፣ ገቢ ምርቶችን በመተካት በስራ እድል ፈጠራ ለውጥ እያስመዘገበ ነው፡፡ ለአብነትም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን ተናግረዋል፡፡ ይህም ዜጎች በሀገራቸው ምርት እምነት እንዲኖራቸው በማድረግ ረገድ የአመለካከት ለውጥ እንዲፈጠር ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡ አውደ ርዕይና ባዛሩም አምራችና ሸማቾችን በቀጥታ የሚያገናኝ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ በተለያዩ አካባቢዎች 81 አውደ ርዕዮች መካሄዳቸውን ጠቅሰው፤ አምራችንና ሸማቹን በማገናኘት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ በበኩላቸው በመዲናዋ ከ3 ሺህ 700 በላይ አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡   የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ቀደም ሲል ከነበረበት 42 ነጥብ 6 በመቶ ወደ 85 በመቶ ለማሳደግ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑንም አውስተዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን በመቅረፍ ረገድ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡ ዛሬ በተከፈተው አውደ ርዕይና ባዛር ከ200 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ለአራት ተከታታይ ቀናት ለህዝብ ክፍት እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡  
ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር እየሰራች ነው- አምባሳደር አባቢ ደምሴ
Apr 24, 2024 83
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በኢኮኖሚው መስክም አጠናክሮ ለመቀጠል እየሰራች መሆኗን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር አባቢ ደምሴ ገለጹ። አምባሳደሩ ይህን ያሉት በአዲስ አበባ በተካሄደው የኢትዮ-ኬንያ ባለሀብቶች የቢዝነስ ፎረም ላይ ነው። ኢትዮጵያ እና ኬንያ በታሪክ፣ በህዝብ ለህዝብና ሌሎችም ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ረጅም ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት እንዳላቸው እንስተዋል። ሁለቱም ሀገራት ለሁለንተናዊ እድገት በቅንጅት እየሰሩ ነው ያሉት አምባሳደር አባቢ፥ የማህበራዊ መስተጋብሮች መጠናከር ለኢኮኖሚያዊ እድገት መሳለጥ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። የሀገራቱ የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነት በሚፈለገው ደረጃ ጠንካራ አለመሆኑን ጠቅሰው፥ የኢትዮጵያ እና የኬንያ መንግስታት ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማጠናከር ስምምነቶችን መፈራረማቸውን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲውን ከፍ ወዳለ ምዕራፍ ለማሻገር በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኗን አስረድተው፥ የሁለቱ ሀገራት ባለሃብቶችም በጋራ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። መንግስት ኢንቨስተሮችን በግብርናው፣ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በአይሲቲ ለመሳብ ምቹ የንግድ አካባቢን እየፈጠረ መሆኑን አብራርተዋል። በመሆኑም የኬንያ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል። በኢትዮጵያ የኬኒያ አምባሳደር ጆርጅ ኦሪና በበኩላቸው በፎረሙ በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድ ትስስር ከምንጊዜውም በላይ ለማጠናከር የሚያስችል ምክክር መደረጉን ገልጸዋል። ኬንያውያን በኢትዮጵያ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ መሰማራት የሚያስችላቸውን ምቹ ዘርፎች የሚለዩበት ዕድል መጠፈሩን አንስተዋል። በተመሳሳይ ፎረሙ ኢትዮጵያዊያን በኬንያ ምቹ የንግድ እና የኢንቨስትመንት እድሎችን እንዲያውቁ የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል ኢትዮጵያና ኬንያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ተጠቃሚ ለመሆን እርስ በእርስ ያላቸውን የንግድ ልውውጥ በማጠናከር የትብብር ስራቸውን ያስቀጥላሉ ብለዋል። የአዲሰ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መሰንበት ሸንቁጤ በበኩላቸው ፎረሙ የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነትን ለማጠናከር ባለሃብቶች ልምድ ለውውጥ የሚያደርጉበት መሆኑን ገልጸዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በመላ ሀገሪቱ በተመረጡ የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ተጀመረ
Apr 24, 2024 170
ሐረር/ጅማ/አሶሳ/ድሬዳዋ/ሶዶ/ነቀምቴ/አዳማ/ጋምቤላ፤ ሚያዝያ 16 / 2016 (ኢዜአ)፡- ኢትዮ ቴሌኮም በመላ ሀገሪቱ በተመረጡ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል። የተቋሙ የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ ማስጀመሪያ መርሃግብሩ የተካሄደባቸው ሐረር፣ ጅማ፣ አሶሳ፣ ድሬዳዋ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ነቀምቴ፣ አዳማና ጋምቤላን ጨምሮ በ29 ዋና ዋና ከተሞች መሆኑ ተገልጿል። በሐረር በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ በኢትዮ-ቴሌኮም የማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ሰዒድ እንዳሉት፤ ዛሬ የተጀመረው የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ በሐረሪ ክልልና በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ባሉ 28 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ይሰጣል።   በተመሳሳይ ኢትዮ-ቴሌኮም የደቡብ ምዕራብ ሪጅን የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ በጅማ ከተማ ተካሄዷል። የደቡብ ምእራብ ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ካሳ በብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ ማስጀመሪያ መርሀግብር እንደገለጹት፤ ግልጽና አካታች አሰራርን ለማስፈን፣ የሳይበር ማጭበርበርን ለመከላከልና የተሻለ አገልግሎትን ለመስጠት ብሎም የዜጎችን የአኗኗር ደረጃ ለመቀየር ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያው ጉልህ ድርሻ አለው። ተቋሙ በአሶሳም የምዝገባ አገልግሎቱን ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በተመሳሳይ መካሄዱን አመልክተዋል፡፡ በኢትዮ- ቴሌኮም የምዕራብ ምዕራብ ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን እጅጉ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ የማህበረሰቡን የእለት ተዕለት ኑሮ በማቀላጠፍ እና የተቋማትን አሰራር በማዘመን ረገድ ጉልህ ድርሻ አለው። ለዚህም ማሳያው ደግሞ ለዜጎች አገልግሎት የዲጂታል ግብይት ማቀላጠፉ፣ የፋይናንስ አካታችነትን የሚጨምሩ የብድር አገልግሎት ዋስትና አገልግሎት ማግኘት ማስቻሉን በአብነት ጠቅሰዋል፡፡ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አገልግሎት በድሬደዋም በይፋ ተጀምሯል። የምዝገባ ማስጀመሪያ መርሃግብሩን በድሬዳዋም ባካሄደበት ወቅት የኢትዮ-ቴሌኮም የኔትወርክ ኦፕሬሽን ማዕከል ቺፍ ኦፊሰር አቶ አበበ አምባው ተቋሙ ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ እያካሄዳቸው ባሉት ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶችና ለውጦች እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። በወላይታ ሶዶ ማዕከል ላይ የተከናወነውን መርሃግብር ያስጀመሩት የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ፋሲሊቲና ፍሊት ኦፊሰር አቶ አይናለም አልበኔም ፤ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ የተቀናጀና ወጥ የሆነ አሰራርን በማስፈን ለዜጎች የዘመነ አገልግሎት ለመስጠት ይረዳል ብለዋል። ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት በመፍጠር የሀገርን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ጨምሮ ለበርካታ ዘርፎች ጠቀሜታ ያለው መሆኑንም አስረድተዋል። በተቋሙ ምዕራብ የሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ አስረስ ብረሃኑ እንዳሉት ኢትዮ-ቴሌኮም ከግንኙነት አገልግሎት በተጨማሪ የማህበረሰባችንን የእለት ተእለት ኑሮ ለማቃለል፣ የኢንተርፕራይዝ ስርአቶችን ለማዘመን እና ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፋ ያለ ዲጂታል መፍትሄዎችን ለማቅረብ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። በአዳማ በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር የኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞች አገልግሎት ዋና ኦፊሰር አቶ ተሬሳ በለጠ እንዳሉት ኢትዮ-ቴሌኮም የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ዜጎች በኢኮኖሚ ማህበራዊና ሌሎች አገልግሎቶች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዲያገኙ የተጀመረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይም የኦንላይን ግብይትን ምቹ በማድረግ፤ የብድር አገልግሎቶችና የቢሮዎችን የስራ ትስስር በመፍጠር የተሻለ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል መሆኑ ጠቀሜታውን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ የምዝገባ መርሃ ግብሩ በጋምቤላ ከተማም ተጀምሯል። ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላቱ ለዜጎች ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለማቅረብ የምዝገባ፣ የማከፋፈያ እና የማጣራት ስራ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።    
ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ
Apr 24, 2024 68
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፡- ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ። በምዝገባ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 2018 ዓ.ም ለ90 ሚሊዮን ዜጎች አገልግሎቱን ለመስጠት መታቀዱን እና ኢትዮ ቴሌኮም 32 ሚሊዮን ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግ ግብ ማስቀመጡ ተገልጿል። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አስቻይ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ተዓማኒነት ያለው የማንነት መለያ ዲጂታል መታወቂያ ነው ብለዋል። ዲጂታል የክፍያ አገልግሎቶችን በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም ነው ያስታወቁት። ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ወደ ስራ መግባቷን አውስተው፥ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ አካታች ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባትና ዜጎች በኢኮኖሚው ዕኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ የዲጂታል ዕድሎችን በመጠቀም ፈጠራ የታከለበትና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ እንደሆነም አንስተዋል። የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባው አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች ዛሬ በይፋ የተጀመረ ሲሆን፥ ዜጎች ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ ምዝገባውን ማከናወን እንደሚችሉም ነው የተገለፀው። በቀጣይም አገልግሎቱን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ ከተሞች የማስፋፊያ ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።  
በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ጥራትና ዘመናዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው
Apr 24, 2024 98
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ጥራት፣ ዘመናዊነትንና ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው ሲል የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የ2016 በጀት ዓመት የመንግሥት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት የፌዴራል ተቋማት የሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ የመስክ ምልከታ እንዲያደርግ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል። በፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሚመራው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን በኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝቶ የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል።   የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሮባ፤ ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ሰጪዎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው እንዲሰሩ ፈቃድ በመስጠትና በቁጥጥር ሥራ ያከናወናቸውን ተግባራት አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን በ2012 ዓ.ም ሥራ በመጀመር የቴሌኮም ዘርፍ ሪፎርሙን ለማሳካት ዘርፈ-ብዙ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልፀዋል። በዚህም በኢትዮጵያ አዲስ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ (ሳፋሪኮም) ገብቶ እንዲሰራ በተደረገው መሠረት የቴሌኮም ዘርፍ በውድድር እንዲሰጥ መሠረት መጣሉን አንስተዋል። ክትትልና ቁጥጥርን ለማጠናከር ከ18 በላይ የሕግ ማዕቀፎችና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ሥራ ላይ ማዋሉን ገልፀዋል። በተመሳሳይ ሁሉን አቀፍ የኢንተርኔት ተደራሽነት ክፍተት ጥናት በማድረግና ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራትን ተናግረዋል። ከ28 ሺህ በላይ ልዩ ልዩ የቴሌኮሙኒኬሽን መሳሪያዎችን ብቃት በማረጋገጥ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ፈቃድ መስጠቱንም ጨምረዋል። በተለይም የአገልግሎት ጥራትን በመቆጣጠር በኩል በዳታ አገልግሎት፣ በአጭር መልዕክትና በሞባይል ድምፅ በአንድ ጊዜ እስከ ሦስት አገልግሎት ሰጪዎችን ኔትወርክ መለካት የሚያስችል መሳሪያ መኖሩን ጠቅሰዋል። የሰው ኃይል በበቂ ሁኔታ አለመሟላት፣ በአቅም ግንባታና ሌሎች ተቋሙ ሥራዎቹን ለማከናወን ተግዳሮቶች እንደሆኑም ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል። የኮሚቴው የኮሙኒኬሽን ሱፐርቪዥን ቡድን አስተባባሪ ገብሬ አላምኔ፤ ባለሥልጣኑ የአገሪቱን የቴሌኮም ሥርዓት ከመቆጣጠር ውድድርና ጥራትን ለማረጋገጥ የተገበራቸው ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን በሱፐርቪዥን ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።   ከተደራሽነት፣ በሰው ኃይል ማብቃት፣ ለቁጥጥርና ክትትል ሥራ የሚያግዙ መሠረተ-ልማቶችና ዘመናዊ አሠራሮችን መዘርጋቱን መገንዘባቸውን ጨምረዋል። ተቋሙ በአገልግሎት ጥራት፣ እራሱን በማስተዋወቅና በሌሎች ጉዳዮች ከሱፐርቪዥን ቡድኑ የተሰጡትን አስተያየቶች በመተግበር ጠንካራ ተቆጣጣሪ ለመሆን እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያን በማሳካት ሂደት ጠንካራ አሠራር ለመዘርጋት በሲምካርድ ምዝገባ ላይ የተጀመሩ ሥራዎች በቀጣይም በትኩረት እንደሚሰራ አንስተዋል። በሱፐርቪዥን ወቅት በተቋሙ ሥራዎችን ለማከናወን የተነሱ ጥያቄዎች ለሚመለከተው አካል እንደሚያቀርቡ ጠቁመዋል።                                        
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ሀገርን ከተለዋዋጭ የሳይበር ጥቃት መመከት የሚያስችል አቅም ገንብቷል-የፌደራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን
Apr 24, 2024 103
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2016 (ኢዜአ)፦የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተለዋዋጭ የሆኑ የሳይበር ጥቃቶችን በብቃት በመመከት የሀገርን ጥቅም ማስከበር የሚያስችል የተሟላ አቅም መፍጠሩን የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የ2016 በጀት ዓመት የመንግሥት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት የፌዴራል ተቋማት የሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ የመስክ ምልከታ እንዲያደርግ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል። በፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሚመራው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝቶ የመስክ ምልከታ አድርጓል። የአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች በመሰረተ ልማት፣ በተቋም አደረጃጀት፣ ተተኪ የሰው ኃይልን በማፍራትና ሌሎች ተቋሙ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን ለሱፐርቪዥን ቡድኑ ገለጻ አድርገዋል። የሱፐርቪዥን ቡድኑ አስተባባሪ ዘሪሁን ከበደ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃትን መከላከል የሚያስችል ሁሉን አቀፍ አቅም እየገነባች መሆኑን በመስክ ምልከታው እንደተረዱ ገልጸዋል። በተለይም ተለዋዋጭ የሆነውን የሳይበር ጥቃት መመከት የሚያስችሉ፣ ዘመኑ የደረሰባቸውን መሰረተ ልማቶች በመዘርጋትና በሰው ኃይል ዘርፍ የተሰሩ ተግባራት የሚበረታቱ መሆኑን አንስተዋል። በተመሳሳይ በስታርት አፕ እንዲሁም የሳይበርና ቴክኖሎጂ ችሎታ ያላቸው ታዳጊዎች ላይ እየተሰራ ያለው ተግባር ለቀጣይ ሀገራዊ ግብ መሳካት መሰረት የሚጥል መሆኑንም ተናግረዋል። አስተዳደሩ በቀጣይም ያሉትን ጥንካሬዎች በማስቀጠል ክፍተቶችን እያረመ ሀገራዊ ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ አሳስበዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳሬክተር ትግስት ሃሚድ በበኩላቸው የሳይበር ጥቃት ሳይፈጸም የመከላከልና ጥቃት ሲያጋጥም ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም መገንባቱን ገልጸዋል። የቁልፍ ተቋማትን ደህንነት ማስጠበቅ፣ ቴክኖሎጂዎችን በአገር ውስጥ የማልማት፣ የስጋት ዳሰሳ መስራትና ሌሎች የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸውም አስረድተዋል። እንደዋና ዳሬክተሯ ገለጻ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ ቁልፍ በሆኑ ተቋማት ላይ 24 ሰዓት የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ተልዕኮ እየተወጣን ነው ብለዋል። ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም የሳይበር ጥቃትን የመከላከል ስራ የሁሉንም ተቋማት ጥረትና የህብረተሰቡን የሳይበር ግንዛቤ ማሳደግ የሚፈልግ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት አብረው ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።   የአስተዳደሩ ምክትል ዋና ዳሬክተር ዳንኤል ጉታ እንዳሉት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳይበር ምህዳሩ የሚያስተናግደው የጥቃት ዓይነትና መጠን እየጨመረ መጥቷል። ኢትዮጵያም ይህንን ታሳቢ በማድረግ የሳይበር ጥቃትን በአግባቡ ለመመከት በቴክኖሎጂና በሰው ኃይል አስፈላጊውን አደረጃጀት በመገንባት የሁልጊዜም ዝግጁነት መፍጠሩን ገልጸዋል። የፌደራል ተቋማት የሱፐርቪዥን ቡድን በተመረጡና ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች የሚያደርገው የመስክ ምልክታ እስከ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል፡፡          
ስፖርት
በቬና በተካሄደ የማራቶን ውድድር አትሌት ጫላ ረጋሳ በአንደኝነት አጠናቀቀ
Apr 21, 2024 179
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 13/2016(ኢዜአ)፡- በቬና የተካሄደውን የወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ጫላ ረጋሳ አንደኛ በመወጣት አጠናቀቀ፡፡ አትሌት ጫላ ረጋሳ ውድድሩን 2 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት አሸንፏል። በለንደን ማራቶን ደግሞ ትዕግስት አሰፋ እና ቀነኒሳ በቀለ ውድድራቸውን በተመሳሳይ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ የብር ሜዳልያ አሸናፊዎች ሆነዋል። የሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ዛሬ በተደረገው በ44 ኛው የለንደን ማራቶን በ 2ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በሁለተኛ ደረጃ ውድድርዋን አጠናቃለች። በወንዶች ማራቶን ውድድር ደግሞ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ውድድርን በ2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ15 ሰኮንድ በሁተኝነት በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል። በለንደን የሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት መገርቱ አለሙ በ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ34 ሰኮንድ 4ኛ፣ አትሌት ትዕግስት ከተማ 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ 7ኛ፣ አትሌት ያለምዘርፍ ይሁአለው 2 ሰዓት ከ 23 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ 8ኛ እንዲሁም አትሌት ፅጌ ሀይለስላሴ 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ03 ሰከንድ 10ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል። እንዲሁም አትሌት ክንዴ አተናው በ2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ03 ሰከንድ 8ኛ ደረጃን ይዞ በመግባት ውድድሩን አጠናቋል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን ውድድር የገባበት ሠዓት ከ2019 ወዲህ ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ዘንድ ሲመዘገብ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለጽ የዓለም አትሌቲክስ አድናቆት መግለጹን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል
Apr 21, 2024 162
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 13/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል። በወጣው መርሃ ግብር መሰረት ኢትዮጵያ ቡና ከመቻል ከቀኑ 10 ሰዓት ሲጫወቱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና ደግሞ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ሲያሸንፍ፣ በሶስቱ ሽንፈት ገጥሞች አንድ ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በዚሀም መሰረት በሊጉ በ33 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። መቻል በበኩሉ ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች በሁለቱ ድል ሲያደርግ ሁለት ጊዜ ተሸንፎ አንድ ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። በዚህም መሰረት መቻል በ40 ነጥብ በሊጉ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በድሬዳዋ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት ይጨወታሉ። የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከሲዳማ ቡና ዛሬ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። በ43 ነጥብ ሊጉን እየመራ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበኩሉ ባለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ፣ አንድ ጊዜ ተሸንፎ፣ ሁለት ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። በአንፃሩ ሲዳማ ቡና ባለፉት አምስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት አላጋጠመውም። በሁለቱ ሲያሸንፍ በሶስቱ አቻ ወጥቶ በ27 ነጥብ በሊጉ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በሊጉ 22ኛ ሳምንት ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ሻሸመኔ ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል። የዛሬ ጨዋታዎችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የድሬዳዋ ቆይታ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከ16ኛ ሳምንት አንስቶ የሊጉ ጨዋታዎች በድሬዳዋ ስታዲየም ሲደረጉ እንደነበር ይታወቃል። ከ23 እስከ 27ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚደረጉ የሊጉ አክሲዮን ማህበር መግለጹ ይታወሳል።
በመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ የተገነቡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳዎች ተተኪዎችን ለማፍራት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው
Apr 21, 2024 164
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 13/2016(ኢዜአ)፡- በአዲስ አበባ በመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ የተገነቡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳዎች ለታዳጊዎች የኳስ ብቃትና ክህሎት ጥሩ መሰረት እየጣሉና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትም አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን አሰልጣኞች ገለጹ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተፃፈው የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ተሽጦ ገቢው በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለልማት ሥራ እንዲውል ተደርጓል። በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። በመዲናዋ የእግር ኳስ፣ የፉት ሳል፣ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የሜዳ ቴኒስና ሌሎች የመጫወቻ ስፍራዎች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ነው። በመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ ተገንብተው ወጣቶችና ታዳጊዎች እየተጫወቱባቸው ከሚገኙ የእግር ኳስ ሜዳዎች መካከል የኢዜአ ሪፖርተር በመዘዋወር አሰልጣኞችና ሰልጣኞችን አነጋግሯል።   በፈረንሳይ 41 ማዞሪያ ራስ ካሣ ሜዳ እና በልደታ ክፍለ ከተማ ቢሊሞ ሜዳ ልምምድ ሲያሰሩ ያገኘናቸው አሰልጣኝ ሰላምሰው ምዳ፤ መደመር በስፖርቱ ዘመን ተሻጋሪ አሻራ እያሳረፈ መሆኑን ገልጸዋል። በመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ የተገነቡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳዎች ለታዳጊዎች የኳስ ብቃትና ክህሎት ጥሩ መሰረት እየጣሉና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትም አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ብለዋል።   በራስ ካሣ ሜዳ በስልጠና ላይ ያገኘናቸው ይስሐቅ ኃይለማርያም እና አቤሜሌክ ኤርሚያስ፤ ከመገንባቱ በፊት ሜዳው ለጨዋታ አስቸጋሪና ለጉዳት የሚዳርግ እንደነበር አስታውሰው ከተገነባ በኋላ በብዙ መልኩ ደረጃውን የጠበቀና ለስልጠና ምቹ መሆኑን ተናግረዋል።   በቢሊሞ ሜዳ ሲያሰለጥኑ ያገኘናቸው አሰልጣኝ መንግሥቱ አረጋ፤ የሜዳው በዘመናዊ መልኩ መሰራት የኢትዮጵያን እግር ኳስ የሚቀይሩ ልጆች ለማፍራት ያግዛል ብለዋል። በሜዳው ሲሰለጥኑ ያገኘናቸው ታዳጊ ልዑል ዮናስ እና ሰላዲን ሀሰን በዘመናዊ መልኩ አዲስ የተሰራው ሜዳ እኛን ጨምሮ ለበርካታ ልጆች ጥሩ የኳስ መሰረት እያስያዘ ነው ብለዋል። በመዲናዋ ከሚገኙ 24 የስፖርት ማዘውተሪያዎች መካከል ሰባቱ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ በተገኘ ገቢ የተገነቡ ሲሆኑ ቀሪዎቹ በመንግሥት በጀት የተሰሩ መሆናቸው ታውቋል።
አካባቢ ጥበቃ
የምግብ ዋስትናና የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከተ አህጉራዊ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
Apr 23, 2024 93
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፦ የምግብ ዋስትናና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከልን የተመለከተ አህጉራዊ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። መድረኩ“ለአየር ንብረት ለውጥ ቴክኖሎጂ ተኮር መፍትሔዎች እና በአፍሪካ ለምግብ ዋስትና የማይበገር አቅም መገንባት፤ እድሎችና ፈተናዎች” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው። 14ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ማዕቀፍ (UNFCCC) የአፍሪካ ፈራሚ አገራት ስብስባ (COP 14) በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ከስብስባው ጎን ለጎን የአፍሪካ የምግብ ስርዓቶች እና የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን የተመለከተ የምክክር መድረክ ነው። በመድረኩ ላይ የአፍሪካ ሪስክ ካፓሲቲ ዳይሬክተር ጀነራል ኢብራሂማ ቼክ ዲዮንግ፣ የአፍሪካ ሕብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ “ብሉ ኢኮኖሚ” እና ዘላቂ ከባቢ አየር የስራ ክፍል አመራሮች፣ የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ፣ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማንደፍሮ ለማና የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሌሎች የአፍሪካ አገራት የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሮች፣ የልማት አጋሮችና የዘርፉ ተዋንያን ተገኝተዋል። የምክክር መድረኩን ያዘጋጁት የአፍሪካ ሕብረት ልዩ ተቋም የሆነው የአፍሪካ ሪስክ ካፒሲቲ(ARC)፣ከግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢኒስቲትዩትና የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ነው። በውይይቱ የአፍሪካ አገራት የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም፣ የምግብ ሉዓላዊነትን በመገንባት፣ የግብርና የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የመሰረተ ልማት ችግሮችን ለመቅረፍና ዓለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ አኳያ የግብርና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎችን እያከናወኗቸው ያሉ ተግባራትና በገጠሟቸው ፈተናዎች ላይ ምክክር እንደሚያደርጉ ተገልጿል። ስብስባው ትናንት በባለሙያዎች ደረጃ መካሄዱ ይታወቃል።  
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2025 ተጨማሪ የካርበን ሽያጭ ማግኘት የሚያስችላትን መስፈርት አሟልታለች - የኢትዮጵያ የደን ልማት
Apr 23, 2024 117
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ 2025 ተጨማሪ የካርበን ሽያጭ ገቢ ማግኘት የሚያስችላትን መስፈርት ማሟላቷን የኢትዮጵያ የደን ልማት አስታወቀ። ባለፉት አምስት አመታት ዜጎችን በማሳተፍ በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሮች የደን ሽፋን እንዲጨምር ማድረግ ተችሏል፡፡ ከመርኃ ግብሩ ጎን ለጎን የደን ጭፍጨፋን ለመከላከል በተከናወኑ ተግባራት የደን ጭፍጨፋን በግማሽ መቀነስ መቻሉን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያሳያል ። በኢትዮጵያ የደን ልማት የብሔራዊ ሬድ ፕላስ አስተባባሪ ዶክተር ይተብቱ ሞገስ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የተራቆቱ አካባቢዎችን በደን በመሸፈን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም የራሷን ድርሻ እየተወጣች ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ ከሚገኘው የደን ልማት ከካርበን ሽያጭ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። የካርቦን ሽያጭ ገቢ ለማግኘት የተቀመጡ ዓለም አቀፍ መስፈርቶች እንዳሉ ጠቁመው ኢትዮጵያ ከካርቦን ሽያጭ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት የሚያስችሏትን መስፈርቶች እንዳሟላች ተናግረዋል። የካርበን ሽያጭ ገቢ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በአካባቢና በአየር ንብረት ሚዛናዊነት ጥበቃ ላይ የሚያበረክቱት የካርበን መጠን ተለክቶ የሚፈጸም የክፍያ ሥርዓት መሆኑን አስረድተዋል። በሰው ሰራሽ የደን ሽፋን የተራቆቱ አካባቢዎችን የማልማት ተግባሩ በባለሙያና በሳተላይት መረጃ ተንትኖ የሚቀርብ ሲሆን በዚህም ለአየር ንብረት ተጽዕኖና የካርበን ክምችት ያበረከተው አስተዋጽኦ ተለክቶ ለሽያጭ የሚቀርብ መሆኑን አንስተዋል። በኢትዮጵያ እየተሰራበት በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የደን ሽፋኑን ከ17 በመቶ በላይ ማድረስ መቻሉ ሀገሪቷ ወሳኝ የአካባቢ ጥበቃ ምዕራፍ ላይ መሆኗን እንደሚሳይ ተናግረዋል። በዚህም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ 2025 ከካርበን ሽያጭ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወኗን ገልጸዋል። የካርበን ሽያጭ ለመፈጸም የሚተከሉ ችግኞችን ደን በማድረግ፣ መረጃን በዲጂታልና በጂፒኤስ በመመዝገብ የተቀመጡ መስፈርቶችን አሟልቶ ማቅረብ እንደሚጠይቅ አንስተዋል። በኢትዮጵያ የተከናወኑ የደን ልማት ተግባራትን በአግባቡ አደራጅቶ በመመዝገብ ሪፖርት ቀርቦ ባለሙያዎች በአካልና በሳተላይት ምልከታ አድርገው ተጨማሪ የካርበን ሽያጭ ገቢ ማግኘት የሚያስችላትን መስፈርት ማሟላቷን የሚገልጽ ምላሸ እንደተሰጠ አስታውቀዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የሚያስከትለውን ጫና ለመቀነስ የሚሰሩ አበረታች ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከዓለም ባንክ፣ከኖርዌይና የአሜሪካ ኩባንያዎች ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሆነም አስረድተዋል። ኢትዮጵያ እስካሁን ከካርበን ሽያጭ ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን ጠቁመው፥ በሬድ ፕላስ በተደገፈው የባሌ ደን ካርበን ሽያጭ ብቻ በሁለት ዙር 12 ሚሊዮን ዩሮ ገቢ ተገኝቷል ብለዋል። ከካርበን ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ለህብረተሰብ ተሳትፎና ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት በመስጠት ቀጣይነት ያለው የደን ጥበቃና እንክብካቤ ስራ እንደሚውል ተናግረዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ዘመቻን በማስቀጠል ከደን ልማት የካርበን ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የአካባቢ ጥበቃ ሙያተኞች የዜጎችን ተሳትፎ በማሳደግ ለደን ችግኝ ልማት ትኩረት እንዲሰጡ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የአካባቢ ጥበቃ እና ደን ልማት ስራ ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ መሰረት በመሆኑ ቀጣይነት ያለው ስራ ማከናወን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።  
በሲዳማ ክልል የፕላስቲክ ውጤቶች በአካባቢ ብክለት ላይ የሚያስከትሉትን ተጽዕኖ ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቷል
Apr 23, 2024 177
ሐዋሳ፣ሚያዚያ 15/2016 (ኢዜአ)፡-በሲዳማ ክልል የፕላስቲክ ውጤቶች በአካባቢ ብክለት ላይ የሚያስከትሉትን ተጽዕኖ ለመከላከል ከማህበራት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን አስታወቀ። የፕላሲቲክ ውጤቶችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የተደራጁ ማህበራት በበኩላቸው የአየር ብክለትን ለመከላከል እንደ ሀገር የተጀመረውን ንቅናቄ ውጤታማ ለማድረግ ተግተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በባለስልጣኑ የአካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ቲቦ ለኢዜአ እንደገለጹት"ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ቃል ክልል አቀፍ የንቅናቄ መድረክ በይፋ ተጀምሯል። በንቅናቄው ለስድስት ወራት የሚከናወኑ የዘመቻ ሥራዎች እንዳሉ ጠቁመው፣ስለአካባቢ ብክለት ከግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ባለፈ ባለድርሻ አካለትን ንጹህና ጤናማ አካባቢን ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል። እንደ ሀገር የብክለት መነሻ ተብለው የተለዩ የፕላስቲክ፣ የአየር፣ የውሃ፣ የአፈርና የድምጽ ብክለቶች እንዳሉ አስታውሰው፣ ብክለት በአካባቢ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ከግምት ያስገባ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መገባቱን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም የፕላስቲክ ብክለት በአካባቢ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመከላከል ከተደራጁ ማህበራት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ማህበራቱ በተለያዩ ከተሞች የፕላስቲክ ወጤቶችን ሰብስበው መልሶ ጥቅም ላይ መዋል በሚቻልበት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን የንቅናቄው አካል እንዲሆኑም የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል። ፕላስቲክ ከ500 እስከ 1000 ዓመት አፈር ውስጥ የመቆየት አቅም እንዳለው በጥናት መረጋገጡን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ በአካባቢ ብክለት ላይ ያለውን ተጽዕኖ ለመከላከል የህብተረተሰቡ ድርሻ የጎላ መሆኑን አስረድተዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ፕላስቲክ ቆሻሻውን ለይቶ ለተደራጁ ማህበራት በመስጠት የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የተጀመረውን ዘመቻ እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል:: የሃዋሳ ውበት ደረቅ ቆሻሻ ማስወገድና ሪሳይክሊንግ ሥራ ማህበር መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሄኖክ ዶንጋቶ በበኩላቸው ከ2010 ጀምሮ በተደራጀ መንገድ ቆሻሻን የመሰብሰብና ጥቅም ላይ የማዋል ስራ እያከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።   ማህበሩ 86 ቋሚ እና ከ1ሺህ 500 በላይ ጊዜያዊ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን በአምስት ተሽከርካሪዎች በመታገዝ ከየቤቱ ቆሻሻ የማሰባሰብ ሥራ ያከናውናል። ከሚሰበስቡት ቆሻሻ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ኮምፖስት ከማዘጋጀት በተጨማሪ ለአካባቢ ብክለት ተጽዕኖ ያላቸውን ፕላስቲክ ወጤቶች መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል የማድረግ ስራ እያከናወነ ይገኛል "ቆሻሻ ሃብት ነው" ያሉት አቶ ሄኖክ በዘፈቀደ የሚጣሉ የፕላስቲክ ምርቶችን በመሰብሰብ የሀዋሳን ሐይቅ እና አካባቢን ከብክለት ከመከላከል ባለፈ ለመልሶ ጥቅም በማዋል ገቢ ማግኘት እንደሚቻል ተናግረዋል። ፕላስቲክ በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ ለመቀነስ ማህበሩ ከክልሉ አካባቢ ደንና አየር ንብረት ባለስልጣን ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በቀን ከ2ሺ 400 ኪሎ ግራም በላይ ፕላስቲክ እንደሚሰበስቡ የገለጹት ስራ አስኪያጁ ከሃዋሳ በተጨማሪ 11 በሚደርሱ የክልሉ ከተሞች፣ በሻሻመኔና ጥቁር ውሃ ኮፈሌና ሃላባ ከተሞች እንደሚሰበሰብ ተናግረዋል፡፡   በዚህም አንድ ኪሎ ፕላስቲክ ከ8እስከ 10 ብር እንደሚገዙ ገልጸው በዘርፉ የሚሰሩ ማህበራትን በማበራከት የአካባቢ ብክለትን መከላከልና ቆሻሻን ወደ ሃብት መቀየር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የኩል ፕላሲቲክ ሪሳይክልንግ ኢንተርፕራይዝ ማህበር አስተዳዳር ክፍል ሃላፊ ኢዮብ ኢያሱ ማህበሩ ለአካባቢ ብክለት ትልቅ ድርሻ ያላቸውን ፕላስቲኮች መልሶ የመጠቀም ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡   በፕላስቲክ ተረፈ ምርቶቹ በዋናነት ለችግኝ መትከያ የሚሆኑ "ፖሊ ባግ" እንደሚያመርቱ ገልጸው ፖሊ ባጎቹን በአረንጓዴ ልማት ለተሰማሩ ማህበራት እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል፡፡ በዚህም ፕላስቲክ በአካባቢ ላይ የሚያሳድረውን ብክለት ለመቀነስ ከክልሉ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ጋር በቅንጅት እየሰራን ነው ብሏል፡፡ ከክልሉ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በወራት የተከፋፈሉ ስድስት ተግባራት የፕላስቲክ፣የአየር፣የውሃ፣የአፈርና የድምጽ ብክለትን ጨምሮ አካባቢና ማህበራዊ ተጽእኖ ግምገማ እስከ መጪው መስከረም የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው፡፡  
በክልሉ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የተቀናጀ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚጠበቅ ተገለጸ
Apr 22, 2024 128
ባህር ዳር ፤ ሚያዚያ 14/2016 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አባላትና ባለሙያዎች የአካባቢ ብክለት ለመከላከል የተቀናጀ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ አሳሰቡ። ‘‘ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ!’’ በሚል መሪ ሃሳብ የአካባቢ ጥበቃና ብክለትን የመከላከል ዘመቻ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ተካሂዷል።   ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ አረጋ ከበደ እንደገለጹት፤ በአየር ንብረት ለውጥ መባባስ በየጊዜው እየተስተዋለ ያለው ድርቅ፣ ጎርፍና ረሃብ ለዜጎች ፈተና እየሆነ መጥቷል። ለዚህም የአካባቢ ብክለትን በዘላቂነት ለመከላከል መንግሥት ለአረንጓዴ ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እያከናወነ ያለው ሥራ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ያለውን ብክለት በዘላቂነት ለመከላከል በየተቋማቱ የሚገኙ አመራር አባላትና ባለሙያዎች ተገንዝበው የተቀናጀ ርብርብ እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል። በተለይም በትላልቅ ከተሞች የብክለት ምንጭ የሆኑና በየቦታው የሚጣሉ የፕላስቲክ ውጤቶች ለገቢ ማስገኛና ለኑሮ ማሻሻያ እንዲውሉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል። የክልሉ የአካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን አለምነህ በበኩላቸው፤ በከተሞች የሚስተዋለው የአካባቢ ብክለት ለማስወገድ የሁሉንም አካላት ቅንጅታዊ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።   በተለይ በየቦታው የሚጣሉ ፕላስቲኮችን በቀላሉ መከላከል ካልተቻለ ኅብረተሰቡን ለከፋ የጤና ችግሮች ከማጋለጡም በላይ፤ የከተሞች ውበትና ደህንነት ችግር ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል። ለዚህም ለቀጣይ ስድስት ወራት የሚካሄደው የአካባቢ ጥበቃ የግንዛቤ ፈጠራና የህዝብ ንቅናቄ ዘመቻ ከዚህ በፊት የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም ክልሉ ከአካባቢ ብክለት ነፃ፣ ምቹና ለሰው ልጆች መኖሪያ ተስማሚ እንዲሆን ባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን እንዲወጡም ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል። ''በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየተራቆተ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሃብት መልሶ ለመተካት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እየተተገበረ ይገኛል'' ያሉት ደግሞ የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ ለማ ናቸው።   በከተሞች አካባቢ የሚስተዋለውን የፕላስቲክ ቆሻሻን ለመከላከል የተለያዩ የህዝብ ንቅናቄ ስራዎችን ማገዝና ውጤቱን ለማፅናት ትኩረት የተሰጠው ሀገራዊ ተግባር መሆኑን አመልክተዋል። ወጣት አይቸው ደባስ በበኩሉ፤ የወዳደቁ ፕላስቲኮችን ሰብስቦና ፈጭቶ ለተለያዩ ፋብሪካዎች እያቀረበ መሆኑን ገልጿል።   በወር ውስጥም እስከ 40 ሺህ ኪሎ ግራም የወዳደቁ ፕላስቲኮችን በመፍጨትና በመጨፍለቅ ለፋብሪካዎች ግብዓት እንዲሆኑ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል። በመድረኩ የክልል፣ የፌዴራልና የዞን የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Apr 15, 2024 1117
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- አለም ተጨማሪ ጦርነት እንድታስተናግድ እድል ባለመፍጠር በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ኢራን እስራኤል ከሳምንታት በፊት ሶርያ በሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጥቃት አድርሳብኛለች በሚል ባሳላፍነው ቅዳሜ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በቀጣናውና በአለም ሀገራት የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የጸጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባውም አለም ተጨማሪ ጦርነት የምታስተናግድበት ምንም አይነት አቅም ስለሌለ ሀገራት በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ችግሩ በቸልታ የሚታይ ከሆነ አስከፊ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸውን ያስነበበው ፍራንስ 24 የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በአስቸኳይና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሊያስቆሙት እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም ዘግቧል።
በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
Apr 8, 2024 2019
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ በተከሰተ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናምፑላ ግዛት 130 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በግዛቷ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመሸሽ ወደ ሌላ አካበቢ ለመሄድ በጀልባ በተሳፈሩበት ወቅት አደጋው እንደተከሰተ የገለጹት ባለስልጣናቱ ጀልባዋ መሸከም ከምትችለው የሰው መጠን በላይ በመጫኗ አደጋው እንደደረሰ አመልክተዋል። በዚህም ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይታቸው እንዳለፈ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሰዎችን ከአደጋው በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ያመለከተው ዘገባው ተጨማሪ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስነብቧል። የናምፑላ ግዛት ባለፈው አመት በሞዛምቢክ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል አንዷ መሆኗም በዘገባው ተመላክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ
Apr 5, 2024 1307
በዓለማችን ላይ እየተስተዋለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ የተወሳሰበ ችግር እያስከተለ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነምህዳር ላይ እያደረሰ ያለው አደጋ ሊቀለበስ ወደ ማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ሞደርን ዲፕሎማሲ ድረገጽ አስነበበ። ድረ ገጹ በዓለማችን በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው ድርቅ፣ ጎርፍ እና ተዛማጅ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደሚገደዱ አስነብቧል። የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በይነመንግስታት ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ያለው የዓለማችን የሙቀት መጠን ወደ 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እየተጠጋ በመምጣቱ በስነምህዳር፣ በከባቢ አየር እና በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘላቂ ልማት እንቅፋት በመሆን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የሚፈጥራቸውን ችግሮች በማባባስ ለሰዎች መፈናቀልና የህይወት መጎሳቆል እያደረሰ ይገኛል። እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በማዕከላዊ አሜሪካ እና ደቡባዊ ሜክሲኮ የተከሰተው ሃሪኬን ኤታ የተባለው የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ያስከተለው የሰብል ውድመትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የደረሰው አደጋ ከባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ አደጋ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በዚህም በጎርፍ፣ በመሬት መንሸራተትና በሰብል ውድመት ምክንያት ከ1 መቶ 20 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞቀ መኖሪያቸው ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽንን መረጃ ዋቢ አድርጎ አትቷል። የአየር ንብረት ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆመው ድረ ገጹ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አመልክቷል። በአውሮፓውያኑ 2022 ወደ 32 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ይህ አሃዝ በ2008 ከተከሰተው በ41 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው አመልክቷል። ይህም የዓለማችን የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን እንጂ ምንም ዓይነት የመቀነስ አዝማሚያ ያላሳየ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው በቺሊ፣ ካናዳ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሜክሲኮ፣ ኢክዋዶር፣ ሊቢያ እና በሌሎችም አገራት ሃሪኬን በተሰኘው የአየር ለውጥ፣ በሰደድ እሳት፣ በጎርፍ እና በድርቅ ምክንያት ለባለፉት በርካታ ወራት መፈናቀልን እንዳስከተለ ተገልጻል። የአለም ባንክን የትንበያ መረጃ ዋቢ ያደረገው ድረ ገጹ በአውሮፓውያኑ 2050 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ 216 ሚሊዮን ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ድረገጹ ይሄ ክስተት የሚያስከትላቸው ችግሮች እንዳይቀጥሉ መቆጣጠር ካስፈለገ ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ግንዛቤን የሚያሳድጉ ትምህርቶች፣ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውነተኛ ውይይቶች እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማሳሰብ መሪዎች የሚጠበቅባቸውን ሊተገብሩ ይገባል ሲል ምክሩን አስቀምጧል።  
ሐተታዎች
ነገረ - አስተውሎት
Apr 24, 2024 43
ሰው በሀሳብ ከሕይወታዊያን ፍጥረት ይለያል። ከፍጥረቱ ጀምሮ ኑሮውን ቀላል ለማድረግ አስቧል። ሀሳቡም መላ ፈጥሯል። ድንጋይ አፋጭቶ እሳትን አንድዷል። እንስሳትን አላምዶ፣ ሰብልን አባዝቶ፣ መጠለያውን ቀልሶ… ኑረቱን አሳልጧል። ዕለታዊ ተግባሩን ለማቃለል በቁስ ላይ ተመራምሮ አጋዥ ቁስ ፈጥሯል። በሂደትም የኢንዱስትሪን አብዮት አፈንድቷል። በ18ኛው ክፍለ ዘመን በባተው የኢንዱስትሪ አብዮት ዓለም አዲስ ክስተት አስተናግዳለች። ፋብሪካዎች፣ መኪናና አውሮፕላን፣ የእንፋሎትና የኤሌክትሪክ ኃይልና የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች ተፈብርከው ምርትና ምርታማነት ጨምሯል። ከተሜነት አብቧል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽን፣ ሮቦቲክስና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች በሰው ተፈጥረዋል። ሳይንስን ለመፍትሔ-እንከን አውሏል። ቴክኖሎጂን ለሁለንተናዊ ሕይወት ማቃለያ ተጠቅሟል። ጊዜ፣ ጉልበትና ሀሳብን ከፈጠራ ጋር አዋዶ ኑሮና ሕይወት አቅልሏል። ኮምፒዩተር ፈበረከ፤ ኢንተርኔትን ፈጠረ፣ ዓለምን አስተሳሰረ። የተዓምር ዘመን ሆነ። ሰው እያስተዋለ... እያስተዋለ… በረቀቀ ጥበብና ግኝት ዛሬ ከዘመነ-አስተውሎት ደረሰ። ሰው ሰራሽ አስተውሎት!! የዘመኑ ቴክኖሎጂ ልህቀት ደረጃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) እንደሆነ ይጠቀሳል። ዳሩ የቴክኖሎጂው እምርታ የዘመን ክስተት ሳይሆን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት ጀምሮ እርሾ ሲያቦካ እንደነበር የዘርፉ ምሁራን ይጠቅሳሉ። ዋረን ማክኩሎች እና ዋልተር ፒትስ ለዛሬው ሰው ሰራሽ አስተውሎት እርሾ የሆነ በነርቭ አውታረ መረብ የሚታገዝ ሒሳባዊ ሞዴል የፈጠሩት በ1943 ዓ.ም ነበር። በ1950 ዓ.ም ደግሞ አለን ተርኒግ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ማሽን ፈለሰፈ። በተመሳሳይ በ1960ዎቹ አጠቃላይ ችግር ፈቺ፣ ሎጂክ ቴዎሪስትና መሰል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፕሮግራሞች በልፅገዋል። በ1950 ዓ.ም ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ራሱን ችሎ እንዲጠና ተወሰነ። ለውስብስብ ችግሮች አይነተኛ መፍትሄ መሆኑ ታመነበት። በ1970 እና 80ዎቹ የዘርፉ ሊቃውንት የሰውን ልጅ የመወሰን አቅም የሚተካ የኮምፒውተር ፕሮግራም ለማበልጸግ ጥረት አድርገዋል። በ1990ዎቹ ምርምሮቹ መቀዛቀዝ ጀምረው ነበር። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዳግም አንሰራርቷል። ስልተ ቀመርን (algorithm) የሚረዱ ማሽኖች ስራ ላይ ውለዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት የጥናት ዘርፍ የሰውን ስራና ሃሳብ በኮምፒዩተር መራሽ ቁሶች መተካት ነው። የሰው ልጅ ፍጥረት የሆኑ ማሽኖች መገንዘብ፣ መማርና ችግሮችን እንዲቀርፉ ማስቻልም ነው። ማሽኖች በሰው ልጅ ምትክ አካባቢን ማመዛዘን፣ መማር፣ ማቀድና መፍጠር፣ መተንተንና እንከኖችን ማምከን እንዲችሉ ማድረግ ነው። የሰውን የማሰብ ኅይል በኮምፒዩተር አዳብሮ በሰውኛ ጥበብ ሕይወትን ማቅለል ነው። አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰው ልጅ ያሉትን የስሜት ህዋሳት ክህሎቶች ለማሽኖች በማስተማር ሰዎች ነገሮችን በቀላሉ እንዲያገኙና እንዲተገብሩ ማስቻል ነው። በዚህም የኮምፒውተር ሊቃውንት ስልተ ቀመር ወይም አልጎሪዝምና አስበው የሚሰሩ ማሽኖች ወደ ስራ እያስገቡ ነው። ለአብነትም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ጥበብ ቤት የሚያጸዱ ሮቦቶች፣ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች፣ ሰው አልባ ጦር መሳሪያዎች፣ የደህነንት ጥበቃ ካሜራዎች፣… በልጽገው ስራ ላይ ውለዋል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጀመረው ይህ ቴክኖሎጂ ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተስፋም ስጋትም ይዞ መምጣቱ ይነገራል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዛሬ ላይ በሁሉም መስክ ገቢራዊ እየተደረገ ነው። በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በግብርና ዘርፎች ምርትና አገልግሎትን ለማቀላጠፍና ለመጨመር ቁልፍ አማራጭ ተደርጓል። ቴክኖሎጂው ከዓለም ገበያ ከ350 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድርሻ አለው። አፍሪካም እያደገ የመጣውን ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ገበያ 10 በመቶ ድርሻ መያዝ ከቻለች እኤአ 2030 አሁን ያለው አህጉራዊ ጥቅል ምርቷ (ጂዲፒ) 50 በመቶ ይጨምራል። ኢትዮጵያ ከአራት ዓመታት በፊት ዘርፉን የሚመራ ተቋም መስርታለች፤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን። ኢንስቲትዩቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምህዳር ተጠቃሽ ሀገር ለማድረግ አበክሮ እየሰራ ነው። በቅርቡ የተመረቀው “አስተውሎት” የተሰኘ ፊልም ደግሞ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው። ሰው ሰራሽ አስተውሎት በሰው ልጅ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ የማይገባበት ሕይወት እንደሌለ ፊልሙ ያስረዳል። በጤና፣ በማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ በመረጃ ፍለጋ፣ በፖለቲካ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በማዕድን ፍለጋና፣ በአገልግሎት አሰጣጥ የዚህ ቴክኖሎጂ ቁልፍ ሚና ተንጸባርቋል። ዘርፉ ከቅንጦት ይልቅ አስፈላጊነቱ ጨምሯል። ለበሽታ መከላከል፣ ለጤና እንክብካቤ፣ ለትምህርት መሻሻልና ድህነት ቅነሳ ይውላል። ለዚህም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረቱ መተግበሪያዎች ፈጠራና አቅም እያደገ መምጣቱ በፊልሙ ተገልጿል። ፊልሙ የኢትዮጵያ የቡና ዛፎችን የበሽታ ስርጭት ለይቶ ለማከም ያለውን ውጤታማነት ያወሳል። ሰው ሠራሽ አስተውሎት የአገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ የሳይበር ደህንነትን ለመጠበቅ፣ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ፣ ምርታማነትን ለመጨመር፣ ገበያን ለማስፋት እና ለመሳሰሉት ሥራዎች በእጅጉ አስፈላጊ ነው። በአሁኑ ወቅት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እየተስፋፉ ከሚገኙ አገልግሎቶች መካከል ማሽን ትራንስሌት ወይም የቋንቋ ትርጉም አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያም አንዱን ቋንቋ ወደ ሌላ በመተርጎም አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በዚህም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም በአንድ መተግበሪያ የተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን መማር እንዲሁም ከድምጽ ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችል ሥርዓትን አበልጽጎ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል። መተግበሪያው አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን በድምጽ እና በጽሁፍ ለመማር የሚያስችል ሲሆን ድምጽን ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችለው የመተግበሪያው አካል ድምጽን በመቅዳት ወይም ከመዛግብት (አርካይቭ) የድምጽ ፋይሎችን ወደ መተግበሪያው በማስገባት የጽሁፍ ቅጂውን ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን ከፊልሙ መገንዘብ ተችሏል። በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የደረሰበትን ልህቀት ያማከሉና ከዘርፉ ውጤት ለማግኘት በአጭር ጊዜ ውስጥ የተኬደው ርቀት ይበል የሚያሰኝ ነው። ነገር ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልህቀት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የዘርፉን ውጤቶች የበለጠ ማላቅ ያስፈልጋል። በዓለም የዕለት ተለት እንቅስቃሴ ውስጥ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እያሳደረ የሚገኘውን ተጽዕኖ በመረዳት ለዘርፉ ምርምሮች የሚደረገውን ድጋፍ የበለጠ ማጠናከር ያሻል። ዓለም የሚሄድበትን ፍጥነት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶችን ለመተግበር በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል። (በሰለሞን ተሰራ)      
ብሩህ ነገን የሰነቁ እንስቶች
Apr 19, 2024 349
የሰው ልጆች ከፍጥረት እስከ ዕለተ ሞት ባሉት የሕይወት ዑደቶች ውስጥ በሚገጥሟቸው መልከ ብዙ ፈተናዎች ሳቢያ ራሳቸውን ለቀቢጸ ተስፋ ይዳርጋሉ፤ ተገደውም ወደ ማይፈልጉት ሕይወት ይገባሉ። በተለይም ሴቶች በሚገጥሟቸው አይነተ ብዙ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጫናዎች ሳቢያ በበርካታ የህይወት ውጣ ውረድ ወስጥ ያልፋሉ፤ በሂደቱም ለአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የተዳረጉ በርካቶች ናቸው፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ቃልኪዳን በላይነህ (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በወጣትነቷ ትዳር መስርታ፣ልጆችን ወልዳ ለመሳም በቅታለች፡፡ ዳሩ ግን ባለቤቷ በድንገተኛ አደጋ በመሞቱ ምክንያት ህጻን ልጆቿን ይዛ ለአስከፊ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጓን ትናገራለች። በዚህም ራሷንና ልጆቿን ህይወት ለማቆየት ወደ ማትፈልገው የወሲብ ንግድ ሕይወት ውስጥ ለመግባት መገደዷን ነው የገለጸችው፡፡ በህፃንነት ዕድሜ ለአካል ጉዳተኝነት የተዳረገችው ሳምራዊት (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በበኩሏ በአካል ጉዳተኝነቷ ምክንያት ተንቀሳቀሳ መስራት ባለመቻሏ ከተወለደችበት ገጠራማ ስፍራ ወደ አዲስ አበባ መምጣቷን ትናገራለች፡፡ በአዲስ አበባም ህይወቷን በልመና ስትመራ ቆይታለች፡፡ ሌላኛዋ ባለታሪካችን ሔዋን (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) ወደ ማትፈልገው ህይወት ውስጥ ስትገባ የሚያጋጥማት ማህበራዊ ፣ አካላዊ ጥቃት እና ስነልቦናዊ ጫና ቀላል አይደለም ትላለች። እሷም ኑሮን ለማሸነፍ የገባችበት የህይወት መስመር ወደ አላስፈላጊ ሱስ ውስጥ እንድትገባና ለስነ ልቦናዊ ቀውስ እንድትጋለጥ እንዳደረጋት ገልጻለች። መንግስት በመሰል ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመታደግ የሚያስችልና “ለነገዋ” የተሰኘ የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል አንዱ ነው፡፡ ማዕከሉ ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች የተጋለጡ ሴቶችን በስነ ልቦና የምክር አገልግሎት እና በተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች በመስጠት ብሩህ ነገን ለማቀዳጀት ስራ ጀምሯል። እነ ቃልኪዳን፣ ሳምራዊት፣ ሔዋንና ሌሎች በችግር ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ‘የነገዋ’ የተሰኘውን የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን ተቀላቅለው የተሻለ ነገን ለመኖር ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በማዕከሉ በሚሰጣቸው ሙያዊ ስልጠናና የምክር አገልግሎትም ወደ ተረጋጋ መንፈስ እንዲመለሱ፣ የሕይወት ተሞክሮ እንዲቀስሙ፣ ነጋቸውን ለማሳመር እንዲነሳሱ ስለማድረጉም ይናገራሉ። ማዕከሉ በአዲስ አበባ መከፈቱ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች ትልቅ ብስራት መሆኑን ገልጸው፤ መሰል ማዕከላትም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋ እንደሚገባ ጠቁመዋል።   “የነገዋ” የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሄርጳሳ ጫላ ማዕከሉ ወደ ስራ ከገባ አንድ ወር በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ 500 ሴቶችን ተቀብሎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሰልጣኞች ከማዕከሉ ሲወጡ ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲችሉ የሚያደርግ በልዩ የክህሎት፣ የስነ ልቦና እና የሙያ በአጠቃላይ በ18 አይነት የስልጠና ዘርፎች እያሰለጠነ መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ስፌት፣ ስነ ውበት፣ የምግብ ዝግጅት፣ የከተማ ግብርና፣ የሕጻናት እንክብካቤና ሌሎች ዘርፎች ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር እንደሚያሰለጥን ነው የገለጹት። ከስልጠናው በኋላ ለሰልጣኞች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ማዕከሉ በትብበር እየሰራ መሆኑም ተናግረዋል፡፡ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማእከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ከፍት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ''እራትም... መብራትም'' የመሆን ጅማሬ
Apr 14, 2024 1443
ሲሳይ ማሞ (ከአሶሳ) ያኔ! 2003 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ የተነገሩ ተስፋዎች የማየፈቱ ህልሞች ብለን ስንቶቻችን አስበናቸው ይሆን? በአካባቢው ሊኖር ስለሚችለው ታላላቅ ክስተቶች፣ ስለሚፈጠሩት መልካም ነገሮች በሰማንበት ቅጽበት በህልም ዓለም ውስጥ እንዳለን ስንቶቻችን አስበን ይሆን? "አዬ ህልም!?" በሚል ሲደርስ እናየዋለን በሚል ቀናት ቆጥረናል። ያኔ! ነገሮች ሲነሱና ሲተረኩ ስንቶቻችን እንሆን እዚህ ቀን ላይ ደርሰን እናይ ይሆን!? የሚል ሃሳብ በእዝነ ህሊናችን የተመላለሰው? ያኔ! የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ ኋላ ከ240 በላይ ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነ ውሃ ሐይቅ ሰርቶ ተንጣሎ እንደሚተኛ እያለምን መጩውን ዘመን በጉጉት የጠበቅን ስንቶቻችን ነን? ግድቡ ግንባታው ሲገባደድ አገር የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በዘለለ "ከሰው ሰራሽ ሐይቁ በሚወጣ ዓሳ ሌላ የገቢ ምንጭ ይፈጠርላታል፤ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ የጀልባ ትራንስፖርትና የመዋኛ አገልግሎቶች ይጀመራል" የሚሉት መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ከመገናኛ ብዙሃኑ ስንሰማ እንደርስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ያልመጣ ቢኖሩ ጥቂቶች ሳይሆኑ አየቀሩም። ያኔ! እንደትንቢት የተነገረው ዛሬ ጊዜው ሲደርስ "ይሆናል" የተባለው ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየሆነ" መጣ። ስለታላቁ ግድብ በህልም ደረጃ ሲገለፁ የነበሩ በዕውን ወደማሳየቱ እየተንደረደረ ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ገጠመኜን ጀባ ልበላችሁ! ዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ነው፡፡ አፍንጫዋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰካች አንድ የሞተር ጀልባ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንጣለለውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለሁለት እየከፈለች ትጓዛለች ከማለት ትበራለች ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰው ሰራሽ ሐይቁ ውሃውን እንደልቧ እየቀዘፈች ለመጓዝ አስችሏታልና! ከምዕራብ በኩል የኮርቻ ግድብ (Saddle dam) ተጠማዞ እና በኩራት ደረቱን ገልብጦ ይታያል፡፡ በስተምስራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የግድቡ ሃይቅ ደግሞ ለስለስ ያለ ሃምራዊ ቀለም ለተመላካቹ ያሳያል። የማለዳዋ የፀሐይ ጨረር ያረፈበት የውሃው ክፍል ለእይታ ባያስቸግርም ገና ከማለዳው ከአካባቢው ሞቃታማ አየር ጋር ተዳምሮ ወላፈን የሚመስል ሙቀቱን መርጨት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ደግሞ በረጅም ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያቆረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፊት ለፊት ተንጣሎ ይታያል፡፡ የተሳፈርንባት የሞተር ጀልባ ስምንት ያህል መንገደኞችን ይዛለች፡፡ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ የሚደረግ ጉዞ ለተጓዡ ሐሴትን ጀልባዋን ለሚዘውራት ከዕለት ገቢ የዘለለ ተድላን እንደሚለግስ አያጠራጥርም። የአካባቢውን ድባብ እየተመለከትን ጉዟችንን ቀጠልን። በጉዞው ቅፅበትም ዓይኖቻችን በአንድ ወጣት አሳ አስጋሪ ላይ አረፉ። ወጣቱ በጀልባዋ ላይ ሆኖ በአንደኛው አቅጣጫ በኩል አጎንብሶ በመንጠቆ ያጠመዳቸውን ግዙፍ አሳዎችን አጥብቆ እየያዘ ወደ ጀልባዋ ይጨምራል። ከአቅሙ በላይ ሆነው ሊያመልጡት የሚታገሉ አሳዎችን ደግሞ በብረት አንካሴ ወገባቸውን እየወጋ ለመያዝ ይታገላል፡፡ ተጠግተን ለመርዳትና አሳዎቹን በመያዝ ለማገዝም ሆነ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ አልደፈርንም፡፡ ወጣቱ ግዙፍ አሳዎቹ ጋር የገጠመውን ግብግብ በካሜራ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ግን አልዘነጋሁትም። ወጣቱ ኢትማን መሃመድ ይባላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ላይ አሳ የማስገር ስራ ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ “ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከ13 ዓመት በፊት ግድቡን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አሁን በሞተር ጀልባ የምንጓዝበት ሃይቅ ይፈጠራል የሚል እምነት በአካባቢው ነዋሪዎች እሳቤ ውስጥ ፈጽሞ አልነበረም።” ሲል ይናገራል ወጣቱ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሃይቅ ለእርሱ እና ለሌሎች ከእርሱ ጋር ለተደራጁ 25 ወጣቶች የሥራ እድል በር መክፈቱን አጫወተኝ፡፡ ከታላቁ ግድብ ያገኙት ትሩፋት እርሱ እና የማህበሩ አባላት በአገራቸው ላይ ሰርተው የመለወጥ ተስፋቸውን በእጅጉ እንዳለመለመላቸው አጫውቶኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚገኙ ወንዞች አሳ ቢያመርቱም በህዳሴው ግድብ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚያገኙት ግን በዓይነትም በመጠንም የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ከሐይቁ እስከ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ነጫጭና ሌሎች ዓሳዎችን እያሰገረ መሆኑን በአድናቆት ጭምር ይገልፃል። ማህበሩ በቀን እስከ ሁለት ኩንታል ወይም ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ገደማ ዓሳ ያመርታል፡፡ “የህዳሴው ግድብ የምግብ ዋስትናም ፤ የገቢ ምንጭም ሆኖናል” ሲልም ወጣቱ ሃሳቡን ቋጭቷል። ለሰዓታት በቆየሁበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ የአሳ ማስገር እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ከገነቡት ግድብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ጅማሬን ይስተዋላል። ነገሩ እንዲህ ነው! በባህር ዳር ጣና ሃይቅ ላይ ያካበተውን የአሳ መረብ አሰራር እና የሞተር ጀልባ አጠቃቀም ልምድ ለማካፈል ወደ ስፍራው ያቀናው ወጣት የሻምበል ወርቁ በማህበር ተደራጅተው አሳ ለሚያሰግሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጥ ማግኘቴ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን መረጃ እውነታነት ያሳያል። “አንዱ ወንድሜ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ይሄም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እኔም ከአማራ ክልል ነኝ፡፡ ሁላችንም እኩል የግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በአካል የማንተዋወቀውን ኢትዮጵያውያንን ግድቡ አስተዋውቆናል” ብሎኛል የሻምበል። ሌላው የመንጠቆ አጣጣል ስልጠና ለመስጠት ከአርባምንጭ ተጉዞ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ መጥቶ ያገኘሁት ደግሞ ወጣት አልማው ደሳለኝ ነው። ''ለአካባቢው ወጣቶች ልምዴን እና ያለኝን ዕውቀት በማካፈሌ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ'' የሚለው ወጣቱ፤ በሃይቁ ላይ የተመለከተው ከፍተኛ የአሳ ሃብት እንደ እርሱ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጥቀም ለአገሪቷም የተሻለ ገቢን ሊያመጣ እንደሚችል ያምናል። “ተባብረን በመስራት አገራችንን እንለውጣለን” በማለት ህብረትና አንድነት ከድህነት ለመውጣት የሚያስችል ዘመኑ የሚፈልገው ታላቅ መሳሪያ መሆኑን ያምናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ...ተብለው ሲነገሩ የነበሩ የወደፊት ትልሞች አሁን እውን ሆነው 'ስራን ለሰሪው....ፍፁማዊ የገፅታ ለውጥን ለአካባቢው መልክዓ ምድር እንዲሁም ሰፊ የቱሪዝምና ሌሎች የስራ መስኮችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት የተግባር ጅማሬ እየታየ ነው። በግድብ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማኖር ወቅት "በይሆናል" ሲባሉ የነበሩ ዕቅዶች እውን ወደ መሆን...ወደ መጨበጥ እየመጡ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው። ለኢትዮጵያውያን የ”ይቻላል” ተምሳሌት የሆነው ግድብ ዋነኛ በይበልጥ ሲጠቀስ ከነበረው የኃይል አቅርቦት ባሻገር ለዜጎች ሌላ የስራ መስክ በመፍጠር ' እራትም መብራትም' ሆኖ እስከመጨረሻው ሊዘልቅ እነሆ ውጤቱን እያሳየ ነው። እንግዲህ የነገ ሰው ብሎን ትሩፋቱን በይበልጥ ያሳየን !!  
በህብር የተገነባ ገድል
Mar 25, 2024 2361
  "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የትውልድ አሻራ ደምቆ የተፃፈበት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ይህ ቀን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የረባ ጥቅም ሳይሰጥ ወደ ጎረቤት አገራት ሲፈስ የኖረውን የአባይ ወንዝ ወደ ብርሃን ለመቀየር በቁርጠኝነት በመነሳት የማይቻልን ነገር በይቻላል ወኔ በመቀየር ለዓለም ያሳዩበት፤ ዓለም የተደመመበት ቀን ነው። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ወቅት በርካታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ታሳካው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አዘል ርእስ የያዘ ተከታታይ ዘገባ አስነብበዋል። ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተሰኘው ድረ ገጽ በፈረንጆቹ 2011 ‘Can Ethiopia Afford the Grand Renaissance Dam?’ በሚል ርእስ ባወጣው ሰፋ ያለ ዘገባ ግድቡን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሊያዋጡ የሚችሉት በጣም ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ግንባታው ሊሳካ አይችልም በሚል ትንበያውን አስቀምጦ ነበር። የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግሪን ፕሮፊት የተሰኘ ድረ ገጽ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ‘Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile River, but what kind of dam can they build without cash flow? ..... there’s one important problem: Ethiopia lacks the necessary funds to see the project to completion. In fact, they can barely get it off the ground.’ በማለት ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የሚያስችል ገንዘብ ስለሌላት ፕሮጀክቱ ሊተገበር አይችልም ሲል ደምድሟል፤ ተሳልቋልም። በወቅቱ የዚህ ዓይነት ግምት የብዙዎቹ ተንታኞች መንደርደሪያ ነበር። “ኢትዮጵያ ደሃ አገር ስለሆነች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር ካልተገኘ በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ፍፃሜ መድረስ አይችልም” የሚል ድምዳሜ ለመስጠት ተንታኞቹ ብዙም አይቸገሩም ነበር። ‘ግድቡ የጥራት ችግር ስላለበት ይደረመሳል’ ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ በግድቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ተደጋጋሚ የዛቻና የማስፈራሪያ መልእክቶች ተስተጋብተዋል። በጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም የቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብጽ ተጎጂ እንደሆነች አቋም በመያዝ "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው፤ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" የሚል ጠንከር ያለ የዛቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያውያን ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል ሲሉ የገለጹት ትራምፕ ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም ሲሉም አክለዋል። "ግብፅ የህዳሴ ግድብ እንዲገነባ መፍቀድ አልነበረባትም፤ የስምምነት ሀሳብ ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ገንዘብ አታገኝም " ብለዋል። አትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለመገንባትና ዳር ለማድረስ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ የተለያዩ ኃይሎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበር አገር ወይም ተቋም ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የነበረው አማራጭ አንድም ግድቡን አለመሥራት፣ አለበለዚያ ወጪውን በራስ አቅም መሸፈን ነበር፡፡ ከእነዚህ ከባድ ሁለት አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ወጪውን በራሱ አቅም በመሸፈን መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ኢትዮጵያውያን ገጠር ከተማ ሳይሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ከጫፍ እስከ ጫፍ በእልህና በቁጭት በመነሳሳት ግድቡን በራሳቸው አቅም ገንብተው ዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ያደረጉት። ለግንባታው የሚውል ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት በተለይም የቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር መልእክት እና በእጣ አገልግሎት ህዝቡ ተረባረበ፤ የማይቻለውን እንደሚቻል ለዓለም አሳየ። በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎችን ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው 99 በመቶ መድረሱንና የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በቅርብ ያወጣቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል የህዳሴው ግድብ ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" በማለት አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ቢኖሩባትም የግድቡን ሥራ ለአፍታም አላቋረጠችም። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ይከበራል፤ መሪ ሀሳቡም "በኅብረት ችለናል!" የሚል ሲሆን ኢትዮጰያውያን ችለው ያሳዩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። እዚህ ድል ላይ የተደረሰው በመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነው። ባለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ተሳትፎ ተጀምሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሊጠናቀቅ ወራቶች የቀሩት ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለጎረቤት አገራት ተደራሽ በማድረግ ቀጣናውን በማስተሳሰር በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው።  
ትንታኔዎች
መልከ ብዙው የ"ዳሞታ ተራራ"
Apr 23, 2024 112
የዳሞታ ተራራ ወላይታዎች የሚታወቁበት የራሳቸው የሆነ ባህል፣ ቅርስ እንዲሁም መለያ ምልክት ነው። ዳሞታ የወላይታ የልምላሜ መገለጫና የተፈጥሮ መስህብ ነው። ተራራው በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ በሚገኝ 12 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ32 ምንጮችና በ12 ጅረቶች ታጅቦ በኩራት ተንሰራፍቶ የሚገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ መጠሪያ ነው። ከዚህ የተነሳ የወላይታ ሶዶ ከተማን ተፈጥሮ ካደላት የዳሞታ ተራራ ሞገሷ የተነሳም ተራራው ፀዳሏ ነው ብለው የሚጠሩትም አልጠፉም። የዳሞታ ተራራ ለአካባቢው ነዋሪም ሆነ አካባቢውን ሊጎበኙ ለሚመጡ እንግዳ ተቀባይነቱን በአረንጓዴ የተፈጥሮ መስህቦቹ በማሸብረቅ ውበቱን በመግለፅ የሚያሳይ ተራራ ነው። ተራራውን ወደ ላይ ለሚመለከተው ዳሞታ ብዙ የሚያሳየውና የሚነግረው ታሪክ እንዳለው ያሳብቃል። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት የዳሞታ ተራራ ለ800 ዓመታት ገደማ የቆየ ታሪካዊ የመስህብ ስፍራ ነው። በጥቅጥቅ ደኖች፣ በወራጅ ወንዞችና ጅረቶች፣ ለመድኃኒትነት በሚያገለግሉ ቁጥር ስፍር በሌላቸው የእፅዋት ዘሮችም የተሸፈነ ነው። በወላይታ ዞን እምብርት በወላይታ ሶዶ ከተማ ሰሜናዊ አቅጣጫ ከፍታ ላይ የሚገኘው የዳሞታ ተራራ ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 3000 ሜትር እንዲሁም የዙሪያ ልኬቱ ከ68 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሆነም ይነገራል። በአንድ ወቅት ተራራው በአካባቢ መራቆት፣ በአየር ሚዛን መዛባትና በሌሎች ምክንያቶች ግርማውንና ልምላሜውን እያጣ መጣ። ይህም የወላይታን ህዝብ በማሳሰቡ ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ ልጅ አዋቂ ሳይል ርብርብ በማድረግ ወደ ቀደመ አቋሙና ሙላቱ ለመመለስ ብርቱ ተፈጥሮን የመከላከል ፍልሚያ አደረገ። ፍልሚያውም በአካባቢው ማህበረሰብ አሸናፊነት በመጠናቀቁ ተራራው ልምላሜውን ጠብቆ አሁን የተላበሰውን ግርማ እንዲይዝ በማድረግ ሊያጣው የነበረውን ጥቅጥቅ ደን በመመለስ የመሬት መሸርሸርን ከመከላከልና የመንገድና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አልፎ ትልቅ የአይበገሬነት ታሪክ እንደፃፈም ይወሳል። ለዚህም ነው ዳሞታን ከወላይታዎች ማህበረሰቡን ከተራራው ለመለየት እንደማይቻልና ጠንካራ ተዛምዶን የመሰረቱ መሆናቸው የሚገለፀው። የወላይታ ዞን የሀገር ሽማግሌ አቶ አብርሃም ባቾሬ እንደሚሉትም ዳሞታ በርካታ የቱሪስት መስህቦች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የሀገር በቀል እፅዋት፣ የዱር እንስሳትና ጥንታዊ የወላይታ ነገስታት መናገሻ ስፍራዎች ባለቤት ነው። የዳሞታ ተራራ ከወላይታ ህዝብ ታሪክና ጀግንነት እንዲሁም ከአሸናፊነት ወኔው ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑም ያነሳሉ። በዙሪያው ዘመናትን ያስቆጠረ የጥቅጥቅ ደንና የነገስታት መኖሪያ እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትና አድባራት የሚገኙበት መሆኑን አንስተው ለወላይታ ሶዶ ከተማም የተለየ ግርማ ሞገስን እንዳላበሳት ተናግረዋል። በዳሞታ ተራራ ዙሪያ የተኮለኮሉት ወንዞችም መነሻቸውን ከተራራው በማድረግ ወደ ታች እየተገማሸሩ ይነጉዳሉ። ወይቦ፣ ቁሊያ፣ ካልቴ ቶቦቤ፣ ሀመሳ፣ ሊንታላ፣ አይከሬ፣ ዋላጫ፣ ጫራቄ፣ ቦልዖ፣ ካዎ ሻፋ፣ ጋዜና ሻፋና ሌሎች ወንዞች ከዚሁ ተራራ ተጎራብተው፣ ከተራራው ያገኙትን መዳኛ ፀበል ለሌሎች ለማቋደስ አየተንደረደሩ ይወርዳሉ። ለአካባቢው ማህበረሰብም ልምላሜያቸውን ያጋባሉ፤ ብርቱውን መሬቱን ምሶ ገበታውን እንዲያበለፅግ ያተጋሉ። ሁሉም ግን የዳሞታ መልዕክተኞች፣ የዳሞታ ተጧሪዎች ናቸው። እንደ አቶ አብርሃም ገለፃ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገደማ የክርስትና ሀይማኖትን በአካባቢው በማስፋፋት ስመ ገናና የሆኑት አቡነ ተክለሃይማኖት ክርስትናን ለመስበክና መንፈሳዊ ክዋኔዎች ለመፈጸም ዳሞታ ተራራን ይወጡ እንደነበረ ከልጅነታቸው ይነገራቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የመንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲያከናውኑ ድካም ሲሰማቸው እረፍት የሚያደርጉበት ለመንፈስ ሃሴትን የሚያጎናፅፍ ስፍራ ነው የዳሞታ ተራራ። በዚህ ምክንያት "ጦሳ ፔንጊያ" የእግዜር መተላለፊያ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠውና "ጣዛ ጋሯ" የንጉስ ሞቶሎሚ ቤተ-መንግስት፣ የንጉስ ሞቶሎሚ የጥምቀት ሥፍራ፣ ቆሊ ቦርኮታ፣ ዳጌቾ፣ ቦቄና ሶዶ፣ ጦማ ገሬራና ሌራቶ ጎዳ የተሰኙ ታሪካዊና የሚጎበኙ ስፍራዎች ይጎበኙበታል በዳሞታ ተራራ። ካዎ ሞቶሎሚ፣ ካዎ ዳሞቴ፣ ካዎ ጎቤና ካዎ ጦና የሚባሉ የወላይታ ነገስታት ቤተ-መንግስታቸውን በተራራው አናትና ግርጌ ላይ ይገነቡ እንደነበር አቶ አብርሃም ይናገራሉ። የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዳሞታ ተራራ በወላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያለው መሆኑን ይገልፃሉ። ከተራራው አናት መነሻቸውን የሚያደርጉ ወንዞች የወላይታን ምድር አጥግበው ሰዎችና እንስሳቱን አጠጥተው ወደ ብላቴ እና ኦሞ ወንዝ ይፈሳሉ። የዳሞታ ተራራ ሌላው ጠቀሜታው መሬት እንዳይሸረሸር ቀጥ አድርጎ በዛ ግዝፈቱ ይዟል ይሄም ለመንገድ ደህንነትና የአካባቢውን አየር ተስማሚ ከማድረግ አኳያ አይተኬ ሚና አለው። በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነው የዳሞታ ተራራ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከዘመናት በፊት ተጀምሮበታል ይላሉ አስተዳዳሪው። ንፁህ የመጠጥ ውሃን በከፊል ለሶዶ ከተማ የሚያጠጣውን የዳሞታ ተራራ የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ ከዩኒቨርስቲና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነውም ብለዋል። የዳሞታ ተራራ ታሪካዊ ይዘቱን ስንመለከት አካባቢው ቀደም ሲል የነገስታት መናገሻ ቦታ ነበር የሚሉት ደግሞ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ተመራማሪ ዶክተር አበሻ ሽርኮ ናቸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከወላይታ ሥርወ-መንግስት መካከል ካዎ ሳቴ ሞቶሎሚና የሌሎች ነገሥታት መናገሻ ስፍራ ስለነበር በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያለው ታሪካዊ ስፍራ ነው። የዳሞታ ተራራ ለአብዛኞቹ በወላይታ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች የስያሜያቸው መነሻ ነው። ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞታ ወይዴ፣ ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎችና ሌሎች ቀበሌያት የተራራውን ስም መነሻ ያደረጉ መሆኑ ተራራውን ታሪካዊ ያደርገዋል። እዚሁ ተራራ ላይ ካሉ የተለያዩ መስህቦች መካከል የጥንታዊ ዋሻ "ሞቼና ቦራጎ" ዋሻ አንዱ ነው። ይህ ዋሻ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ የጥንት ሰው መኖሪያ ዋሻ ነበር። ዋሻው በዳሞታ ተራራ ከሚገኙ ከአምስት በላይ ዋሻዎች አንዱ ሲሆን በተራራው በስተምዕራብ አቅጣጫ በኩል የሚገኝና ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ሰዎች በዚሁ ዋሻ ይኖሩ እንደነበረም ታሪክ ያስረዳል። ሞቼና ቦራጎ ዋሻ ስፋቱ 38 ሜትር፣ የጣሪያው ከፍታ 33 ሜትር፣ የዋሻው ዙሪያ ልኬት ደግሞ 58 ሜትር፣ እንዲሁም በውስጡ ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች የመያዝ አቅም ያለው እንደሆነም መረጃዎች ያመላክታሉ። ሌላው ከዳሞታ ተራራ መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን ደብረ-መንክራት አቡነ ተክለኃይማኖት ገዳም ላስተዋውቃችሁ። ይህ ገዳም ለአቡነ ተክለኃይማኖት መታሰቢያነት በ1887 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ከመመስረቱ ጋር በተያያዘ የተገነባና በዳሞታ ተራራ ምዕራባዊ ራስጌ የሚገኝ የቱሪስት መስህብ ሥፍራ እንደሆነ ነው ዶክተር አበሻ የሚናገሩት። ገዳሙ የአምልኮና የፀበል አገልግሎት እየሰጠ ከአንድ ክፈለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ በወላይታ ዞን ካሉ መንፈሳዊ ስፍራዎች አንዱ ሲሆን በውስጡ በርካታ ሐይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ያሉት በመሆኑ በኢትዮጵያ ሐይማኖታዊ ጉዞ ከሚደረግባቸው መዳረሻዎች አንዱ ነው። በመሆኑም አካባቢው ለቱሪስት መዳረሻነት፣ ለአካባቢው ልማት ብሎም ለአየር ንብረት ሚዛንን መጠበቅ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።            
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 3710
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች 
Mar 2, 2024 2496
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል።   የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡   መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ።   የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል።   ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።  
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 2368
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11671
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16055
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 8272
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 9282
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 25716
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 21673
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16055
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12232
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11671
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 11089
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 10856
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 10416
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 25716
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 21673
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16055
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12232
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
መጣጥፍ
በድላችን ሐውልት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት የተቀረጸላቸው የካራማራው ዘማች አቶ በቀለ ገመቹ 
Mar 5, 2024 3613
አቶ በቀለ ገመቹ ወይም በቅፅል ስማቸው አሚኮ ይባላሉ፤ በሙያቸው ኤሌክትሪሺያን ናቸው። በ1969 ዓ.ም በዚያድባሬ የሚመራው የሶማሊያ አገዛዝ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሀገር ስትደፈር ቁጭት ተሰምቷቸው ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸውን ይናገራሉ። ጦር ሜዳ ከመዝመታቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመሆናቸው "በራ በራ የድል ጮራ" የተሰኘውን ዓርማ በመቅረጽ በ14ቱ ክፍላተ ሀገር እንዲበራ ማድረጋቸውንም ያነሳሉ። በዚህም ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ከኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ መሸለማችውን ያወሳሉ። ታንክ ማራኪው አሊ በርኬ ጓደኛቸው እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ በቀለ፤ በተለያዩ ዐውደ ግንባሮች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። አቶ በቀለ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚገኘው የድላችን ሐውልት ላይ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት ተቀርጾላቸዋል። ሐውልት እንዲቀረጽ የተደረገበት ፎቶግራፍ በያኔው ሶስተኛው አንበሳው ክፍለ ጦር በኋለኛው ምሰራቅ ዕዝ በር ላይ በቀኝ እጃቸው መሳሪያ ከፍ አድርገው ይዘው የተነሱት ፎቶ ግራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። ከእርሳቸው ጎንም መንበረ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊ ዘማችና መትረጊስ ተኳሽ ሴት ባደረገችው አስተዋፅኦና በደረሰባት አካል ጉዳት ሐውልት እንደተቀረጸላት ያነሳሉ። የካራማራ ድል ታላቅ ድል ነው የሚሉት አቶ በቀለ ገመቹ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለውበት የተገኘና ሀገርን ያስከበረ መሆኑንም ይገልጻሉ። የካራማራ ዘማቹ አቶ በቀለ ገመቹ አሁናዊ ኑሯቸው ችግር ላይ እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ወረራ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል አደረገ፤ የኢትዮጵያ አሸናፊነትም በአደባባይ ታወጀ። ድሉ በየዓመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮም 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።    
የአፍሪካ ዋንጫን በመሀል ዳኝነት  የመራችው ብቸኛዋ ሴት ዳኛ
Jan 28, 2024 3419
  በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ፡- በእግር ኳስ ውድድሮች የመሃል ዳኝነቱን ቦታ በብዛት የሚይዙት ወንዶች ሲሆኑ፤ አሁን ላይ አልፎ አልፎ ሴቶች ትልልቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ሲዳኙ አስተውለናል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተከናወነው 22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ፤ ፈረንሳዊቷ ስቴፋኒ ፍራፓርት፤ ኮስታሪካ እና ጀርመን ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኛነት መርታለች። በዚህም በወንዶች ዓለም ዋንጫ ታሪክ በመሀል ዳኝነት የእግር ኳስ ጨዋታን የመራች የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች ። ዘንድሮ ደግሞ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሞሮኳዊቷ ቦችራ ካርቡቢ፤ ውድድሩን እንዲመሩ ከተመረጡት 32 የመሀል ዳኞች መካከል ብቸኛዋ ሴት ናት። በዚህም በውድድሩ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ፤ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ ታሪክ ጽፋለች። የሞሮኮ ዓለም አቀፍ ማኅበር የእግር ኳስ ዳኛ የሆነችው ቦችራ ካርቡቢ፤ በወንዶችም ሆነ በሴቶች አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በርካታ የመጨረሻ ምዕራፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ዳኝታለች። 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ብቸኛ የሴት ዳኛ ሆና የመራችው ቦችራ ካርቡቢ ማናት? ቦችራ ካርቡቢ በሞሮኮ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው "ታዛ" ከተማ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1987 ተወለደች። የዘር ግንዷ በሰሜን ምሥራቅ ሞሮኮ ከሚገኙት ሪፊያን ከሚባሉት የበርበር ጎሳ ዝርያ ካላቸው ሕዝቦች የሚመዘዝ ሲሆን፤ ለቤተሰቦቿ አምስተኛና የመጨረሻ ልጅ ነች። ገና በልጅነቷ ለእግር ኳስ ፍቅር ያደረባት ቦችራ ካርቡቢ፤ ኳስ መጫወት የጀመረችው በአንድ ትንሽ የወጣቶች ቡድን ውስጥ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2001 በተወለደችበት ከተማ "ታዛ"፤ ለወንዶችና ለሴቶች የእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ተከፈተ ። ይኼ ትምህርት ቤት ቀልቧን የሳበው ቦችራ፤ ሥልጠናውን መውሰድ ጀመረች። "እግር ኳስን እወዳለሁ፤ ራሴንም ላስተምር ፈለኩ።ለምን አላደርገውም ብዬ ፍላጎቴን በመከተል የእግር ኳስ ጨዋታን ደንብ መማር ጀመርኩ" ስትል የእግር ኳስ ዳኝነት ትምህርት የጀመረችበትን ጊዜ ታስታውሳለች። ይኼ ድርጊቷ ካልተዋጠላቸውና፤ በበጎ ጎኑ ካልተመለከቱት ውስጥ ደግሞ፤ ወንድሞቿ ቀዳሚዎች ነበሩ። "በምኖርበት ከተማ አንድ ሴት አጭር ቁምጣ ለብሳ ከወንዶች ጋር ሥልጠና ስትወስድ መታየቷ፤ እንደ አሳፋሪ ድርጊት ስለሚታይ መነጋገሪያ ሆኜ ነበር" ትላለች። የቦችራ ካርቡቢ የዳኝነት ጉዞ እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በ2007፤ ሞሮኮ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒዮናን ጀመረች። ይህ መሆኑ ቡችራ ካርቡቢ ብሔራዊ ዳኛ እንድትሆን ዕድል የፈጠረላት ሲሆን፤ መኖሪያዋንም ከትውልድ ሥፍራዋ "ታዛ" ወደ ሞሮኮ ሌላኛዋ ከተማ "ሚከንስ" እንድትቀይር አደረጋት። "ይህን ዕድል ማግኘቴ ቤተሰቦቼ እንዲረዱኝና ሙያዊ ለሆነ ጉዳይ እንደምሄድ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል" በማለት የዳኝነት ሙያዋን በመጨረሻ እንደተቀበሉት ታስረዳለች። በሚከንስ ከተማ በእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና ላይ እያለች፤ አንድ ቀን አባቷ መጥቶ እንደተመለከታትና፤ ወንድሞቿ ምርጫዋን ሊያከብሩላት እንደሚገባ እንደነገራቸውም ገልፃለች። የ19 ዓመት ወጣት እያለችም፤ በሞሮኮ የሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ የሊግ ውድድር በመዳኘት፤ የዳኝነት ሥራዋን አንድ ብላ ጀመረች። ይህ ከሆነ ከ10 ዓመት በኋላ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ በመሆን ራሷን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረች። ከሁለት ዓመት በኋላም በ2018 በጋና አስተናጋጅነት በተከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ፤ በዛምቢያና በኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት አጫወተች። ይህም በአህጉራዊ የውድድር መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀል ዳኝነት ያጫወተችው ጨዋታ ሆኖ ተመዘገበላት። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020፤ "ቦቶላ" እየተባለ በሚጠራው በሞሮኮ የወንዶች ከፍተኛ የሊግ ውድድር ላይ በመሀል ዳኝነት በመዳኘት፤ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች ። ከአንድ ዓመት በኋላም በካሜሮን አስተናጋጅነት በተከናወነው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ሴኔጋልና ግብፅ ባደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ የቫር ዳኛ (video assistant referee) በመሆን ሰርታለች። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊትም የሞሮኮ የንጉሱ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን በመዳኘትም ቀዳሚዋ ሴት ናት። አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወድድርም፤ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ የመጀመሪያዋ ሰሜን አፍሪካዊት የአረብ ሴት ሆናለች። ቡችራ ካርቡቢ ከእግር ኳስ ዳኝነት ሥራዋ በተጨማሪ፤ የፖሊስ ኦፊሰር በመሆን ሀገሯን እያገለገለች ትገኛለች።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም