ኢዜአ - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከል ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ቁጥጥር እየተደረገ ነው
Mar 29, 2024 0
ሶዶ ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከል ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገለጸ። ቢሮው ህገ-ወጥ ንግድን መከላከል ላይ ያተኮረ ስልጠና ከ12 ዞኖች ለተውጣጡ ፈጻሚ ባለሙያዎች በወላይታ ሶዶ ከተማ እየሰጠ ነው። የቢሮው ሃላፊ አቶ ገሌቦ ጎልቶሞ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በክልሉ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የገበያ ስርአቱን በማዛባት የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እያደረገ ነው። ከዚህም ባለፈ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴው ህጋዊ ነጋዴዎች ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን ገልጸዋል። ገበያው እንዳይረጋጋ ምክንያት የሆኑ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችና ህገ-ወጥ ደላሎችን ከገበያ ስርአት ለማስወገድ ቢሮው ከፍትህ አካላት ጋር እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ከፍትህ አካላት በተጨማሪ ቢሮው ከተለያዩ ባለደርሻ አካላት ጋር በመሆን የቁጥጥር ስራውን ማጠናከሩን አስረድተዋል። በሌላ በኩል በክልሉ በጉምሩክ ከተፈቀዱ 3 ኬላዎች ውጭ በርካታ ኬላዎች በየአካባቢው መኖራቸው ህገ-ወጥ ንግድን ከመቆጣጠር ይልቅ ምርት እንዳይንቀሳቀስ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ይህን ለማስተካከል በተደረገው ጥረት 33 ኬላዎችን ማንሳት እንደተቻለና ቀሪዎችን ለማስወገድ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ከነዳጅ ግብይት ጋር በተያያዘ እንደ ሀገር በተደረገው ንቅናቄ በክልሉ ካሉ 89 ነዳጅ ማደያዎች መካከል 86ቱ በቴሌ እና ሲቢኢ ብር መገበያየት እንዲችሉ መደረጉን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ዘርፉ አሁንም ከህገ-ወጥ ነጋዴዎችና ደላሎች አለመጽዳቱን ጠቁመው ይህን ለማስተካከል የዛሬው ስልጠና የተሳለጠ የገበያ ስርአት ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል። ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል በጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የሰብል ምርት ቡድን መሪ አቶ ሽፈራው ጀጉ፣ በዞኑ የሚስተዋለው ህገ-ወጥ ንግድ ገበያው እንዳይረጋጋ ማድረጉን ገልጸዋል። የንግድ ስርአቱ በአሰራር እንዲመራና የኑሮ ውድነቱ እንዲረጋጋ ህገወጥነትን ለመከላከል የበኩሌን እወጣለሁ ብለዋል። ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለማስቆም በዞኑ ባሉ ሁሉም ወረዳዎች ህገ-ወጥ የንግድ ቁጥጥር ግብረ-ሃይል ተቋቁሞ እየሰራ ነው ያሉት ደግሞ ከጋሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት የሰብል ምርት ግብይትና ጥራት ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ተሾመ ዳንኤል ናቸው። ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በሰብል ምርት ግብይት፣ በእንስሳትና በገበያ መሠረተ ልማት ላይ ያተኮረ መሆኑ ተጠቁሟል።
በጋምቤላ ክልል አልፎ አልፎ እየተከሰተ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ የፌደራልና የክልሉ የፀጥታ አካላት ውይይት አደረጉ
Mar 29, 2024 27
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል አልፎ አልፎ እየተከሰተ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በተገኙበት የፌደራልና የክልል የፀጥታ አካላት ውይይት አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሸነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በተካሄደው ውይይት ላይ አንዳንድ ግለሰቦች ጎራ እየለዩ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን እያደረሱ እንዳሉ በመገምገም ችግር ፈጣሪዎችን በአስቸኳይ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የፀጥታ አካላት የፀጥታ ችግሩን ለመቅረፍ ወደ ኦፕሬሽን በመግባት ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በቁጥጥር ሥር እያዋሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራሉ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ የፖሊስ ሠራዊቱን አባላት፣ የስደተኞች ካምፕንና በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሚጠበቁ ተቋማትን ጎብኝተዋል። ሠራዊቱ በተመደበባቸው አካባቢዎች ሁሉ እየተወጣ ያለውን ፖሊሳዊ ተልዕኮ አጠናክሮ እንዲቀጥል መመሪያ መስጠታቸውን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ለአራት መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዓረግ ሰጠ
Mar 29, 2024 37
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ለአራት መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዓረግ መስጠቱን አስታወቀ ። በጥናትና ምርምር ስራቸው የላቀ የፈጠራ ውጤት ላስመዘገቡት አራት ውጤታማ መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዓረግ ከመጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መስጠቱን የዩኒቨርሲቲው ሴኔት አረጋግጧል ። ከአውቶሞቲቭ ምህንድስና ዘርፍ ሌተናል ኮሎኔል ዶክተር ብስራት የሱፍ፣ ከሜካኒካል ዲዛይን ሻለቃ ዶክተር ሰሎሞን ሰይድ፣ ከኬሚካል ምህንድስና ሻለቃ ዶክተር ወንዳለም ምስጋነውና ከሜካትሮኒክ ምህንድስና ሻለቃ ዶክተር ርእሶም ወልደ ጊወርጊስ ናቸው የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረጉን ያገኙት። መምህራኑ በየስራ ዘርፋቸው ባስመዘገቡት ልዩ ውጤት የተመዘኑ መሆኑም ተገልጿል። በወታደራዊ አገልግሎት ስራ ላይ ለሚገኙ ምሁራን የተሰጠው የደረጃ እድገት በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገውም ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አምራች ኢንዱስትሪዎችን ከሸማቾች ጋር የሚያገናኝ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ
Mar 29, 2024 43
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦አምራች ኢንዱስትሪዎችን ከሸማቾች ጋር የሚያገናኝ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ፡፡ ኤግዚቢሽኑ አምራች ኢንዱስትሪዎች እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲያደርጉና የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ታስቦ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተገኝ ጓለ ኤግዚቢሽንና ባዛሩ አምራቾች የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩና ህብረተሰቡም አማራጭ ግብይት እንዲያገኝ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡ መንግስት በልዩ ትኩረት አምራቾች በስራ ሂደታቸው የሚገጥማቸውን ማንኛውንም ችግርና የመሰረተ ልማት ጥያቄ በመፍታት ምርታቸውን ተደራሽ እንዲያደርጉ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ እንደ ክፍለ ከተማው ነባራዊ ሁኔታ በምርት ሂደት ላይ ተግዳሮት የገጠማቸውን አምራቾች በመለየት መፍትሄ መስጠት መቻሉንም አስታውቀዋል፡፡ በኤግዚቢሽኑ ላይ የተሳተፉ አምራቾች እንዳሉት ባዛሩ በተለይ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች እርስ በርስ እንዲተዋወቁ ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡ ኤግዚቢሽንና ባዛሩ አምራቾችን እርስ በእርስ ከማቀራረብ ባለፈ ህብረተሰቡ የሀገር ውስጥ ምርቶችን እንዲጠቀም ሰፊ ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም አንስተዋል፡፡ በባዛሩ በቆዳ፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ አግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ ኬሚካል፣ በዕደ ጥበብ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ኤግዚቢሽንና ባዛሩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ለ5 ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።
አሰባሳቢ ትርክቶችን በማጠናከር በሀገሩ ብሔራዊ ጥቅም የማይደራደር ትውልድ መገንባት ይገባል - አቶ ብናልፍ አንዱዓለም
Mar 29, 2024 80
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦ ብዝሐነትን በአግባቡ የሚያስተናግድና አንድነትን የሚያጸና አሰባሳቢ ትርክት በማጠናከር በሀገር ብሔራዊ ጥቅም የማይደራደር ትውልድ መገንባት እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ ሰላም ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል "ቀጣናዊ ሰላምና አብሮነት ለዘላቂ የኢኮኖሚ ትስስር" በሚል መሪ ሃሳብ በጋራ ያዘጋጁት የፓናል ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፤ በመጠላለፍና በመጠፋፋት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ አካሄድ ኢትዮጵያን ብዙ ዋጋ ሲያስከፍል የኖረ በሽታ ነው ብለዋል። በመሆኑም ለሀሳብ የበላይነት ዋጋ ከማይሰጥና ጉልበትንና ኃይልን መሰረት ካደረገ የፖለቲካ ባህል በመላቀቅ የጋራ ልማትን ለማረጋገጥና የዜጎችን ህይወት ለማሻሻል ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። ለዚህ ደግሞ ከሚከፋፍሉና ከሚያራርቁ ነገሮች ይልቅ የሚያቀራርቡና የሚያስተሳስሩ ጉዳዮች ላይ የበለጠ በማተኮር የሁላችንም የጋራ ቤት የሆነችውን ኢትዮጵያን መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል። ይህን ማድረግ የሚቻለው ብዝሃነትን የሚያስተናግድና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ አሰባሳቢ ትርክት በመገንባት መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ በኩል እኔ አውቅልሃለው በሚል አስተሳሰብ የተቃኘ በሌላ በኩል ደግሞ ልዩነት ላይ ብቻ ያጠነጠነ ነጠላ ትርክት መንሰራፋቱን ገልጸው ሁለቱም አካሄድ አጥፊ መሆናቸውን አንስተዋል። የትውልዱን አስተሳሳሪ ገመድ ወደ ጎን የገፋ ነጠላ ትርክትን በመተው ብዝሐነትን በአግባቡ የሚያስተናግድና የጋራ ማንነትን የሚያጠናክር ትርክት መገንባት እንደሚገባ ገልጸዋል። ኢትዮጵያዊነትን ጠንካራ የጋራ ቤት አድረጎ የሚገነባ አዲስ አሰባሳቢ ትርክት መሬት እንዲይዝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። የጋራ ትርክት መገንባት ቢያንስ በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት በመፍጠር ጠንካራ አገረ መንግስት መገንባት እንደሚያስችል ገልጸዋል። በመሆኑም ቢያንስ በሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ሚኒስትሩ እነዚህም ብሔራዊ ጥቅም፣ ብሔራዊ ማንነትና አገራዊ እሴት መሆናቸውን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም የማይደራደር ትውልድ መገንባት እንዲሁም በጋራ ማንነት እና እሴቶች ዙሪያ መግባባት መፍጠር ጠንካራ ኢትዮጵያን መገንባት ማለት ነው ብለዋል። በዚህ መንገድ የኢትዮጵያን ቀጣይነትና ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ከተሰራ በቀጣናውም ሰላምና አብሮነትን ለማጽናት አጋዥ እንደሚሆንና ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ትስስርም አበርክቶ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ፖለቲካ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ጄን ቻርልስ ካራምባን ጋር ተወያዩ
Mar 29, 2024 80
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ጄን ቻርልስ ካራምባንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይታቸው በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ ጉዳዮች እና ከአሁን በፊት ሁለቱ ሀገራት በትብብር የሚሰሩባቸውን ጉዳዮች ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልበት ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል። ሩዋንዳ በኪጋሊ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚሠራበት ቦታ መስጠቷም ለግንኙነቱ መጠናከር አንዱ ማሳያ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተጠቅሷል። ሁለቱ አካላት በቀጣይ በአዲስ አበባ እና ኪጋሊ ከተሞች ያለውን እህትማማችነት የበለጠ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይም መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ፓርቲው ያጋጠሙትን ፈተናዎችና ጫናዎች በፅናት በማለፍ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድል እያስመዘገበ ነው -አቶ ሽመልስ አብዲሳ
Mar 29, 2024 65
አዳማ፣መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፡- ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ያጋጠሙትን ፈተናዎችና ጫናዎች በፅናት በማለፍ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድል እያስመዘገበ መሆኑን የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ። ''ቃል በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና'' በሚል መሪ ሀሳብ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የፓርቲው ኮንፈረንስ በአዳማ አባገዳ አዳራሽ እየተካሄደ ነው። አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ፓርቲው ባለፉት ዓመታት የኢኮኖሚ ስብራትን ለመጠገን የሚያስችል መሰረት የተጣለበት ተግባር አከናውኗል። ፓርቲው ሀገሪቷ ከነበረችበት ችግሮች እንድትወጣ በሙሉ አቅሙ በመስራት በፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ድል እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። ''በድርብ ፈተናዎችና ጫናዎች ተስፋ ሳንቆርጥ መላው ህዝቡንና አባላቱን በማሰባሰብ አሁን ያለንበትን ድል አስመዝግበናል'' ያሉት አቶ ሽመልስ ኮንፈረንሱ ያሉትን ችግሮች በመለየት ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ብለዋል። በቀጣይ ሁሉት ዓመት ተኩል የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ዕቅዶችን በአግባቡ በመለየት በጥራትና በፍጥነት መፈፀም እንደሚገባም አስረድተዋል። ብልሹ አሰራር፣ ሌብነትና ህገ ወጥ ተግባራትን በማረምና ስርዓት በማስያዝ የብልጽግና ጉዞን በአንድነት ለማሳካት ርብርብ እንደሚደረግም ገልጸዋል። መላውን የክልሉን ህዝብ በማንቀሳቀስ ለተሻለ ድል አባላቱና አመራሩ በሙሉ አቅሙ መረባረብ እንደሚገባውም አስገንዝበዋል። በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በበኩላቸው ፓርቲው ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በማንገብ አመርቂ ድል እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። ፓርቲው ሀገራዊ ማንነትና ህብረ ብሔራዊ አንድነት መሰረት ያደረገ የጋራ ትርክት ለመገንባት በርካታ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይ በመጀመሪያው የፓርቲው ጉባኤ ላይ የተቀመጡትን አቅጣጫዎች መሰረት በማድረግ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ተግባራዊ መደረጉን አስታውስዋል። በዚህም በምግብ ራስን ለመቻል፣ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በጥራትና በብዛት በማምራት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት እየተሰራ ነው ብለዋል። በቀጣይ ሰላምን ማጽናት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት አጠናክሮ ከማስቀጠል ባለፈ ጽንፈኝነትን ለማስወገድ በቁርጠኝነት ይሰራል ሲሉም ገልጸዋል። ኮንፈረንሱ ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ከቻይናው ኮሚዩኒስት ፓርቲ ጋር ስትራተጂካዊ አጋርነቱን ይቀጥላል - አቶ አዲሱ አረጋ
Mar 29, 2024 90
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦ ብልጽግና ፓርቲ ከቻይናው ኮሚዩኒስት ፓርቲ ጋር ያለውን ስትራተጂካዊ አጋርነት አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ህዝብ እና አለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ገለጹ። በአቶ አዲሱ አረጋ የሚመራ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተካተቱበት ልዑክ ቻይና ቤጂንግ ገብቷል። ጉብኝቱን አስመልክቶ አቶ አዲሱ ለኢዜአ እንደገለጹት የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲና ብልጽግና ፓርቲ ስትራተጂካዊ አጋርነትና ወዳጅነትን የበለጠ ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ከተለያዩ የፓርቲው አመራሮች ጋር ውይይት ይደረጋል። የፓርቲ ግንባታ፣ በህዝባዊ ንቅናቄ ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ፣ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጉዳዮች የልምድ ልውውጡ ዋና ዋና ጭብጦች መሆናቸውንም ገልጸዋል። በተያዘው መርሀ ግብር መሰረትም በቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ አመራሮች ለቡድኑ ገለፃ መደረግ ተጀምሯል። የቻይናን ብልፅግና ለማረጋገጥ የተወሰዱ እርምጃዎች፣ብዝሀዊ ማንነትን ሳይበርዙ እድገትን እውን ለማድረግ የተሄደበት ርቀት፣ከሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብ የሆነ የዲፕሎማሲ መርህ ያስገኘው ፍሬ በገለፃው ተካቷል። ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ዘመናትን የተሻገረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የገነባች መሆኗንና ፓርቲውም ይህ ግንኙነት ወደ ተሻለ ትብብር እና የጋራ ተጠቃሚነት እንዲያድግ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። የልኡካን ቡድኑ ቆይታም ከዚህ በፊት በፓርቲ ለፓርቲም ሆነ በመንግስታዊ ደረጃ በስልጠናና በተሞክሮ ልውውጥ ተባብሮ ለመስራት ከስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ጉዳዮች በፍጥነት እየተተገበሩ ስለመሆናቸው አመላካች መሆኑም ተገልጿል።
በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የብልጽግና ፓርቲ ኮንፈረንስ በአዳማ እየተካሔደ ነው
Mar 29, 2024 67
አዳማ፤ መጋቢት 20/2016 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ የብልጽግና ፓርቲ ኮንፈረንስ በአዳማ ከተማ አባገዳ አደራሽ መካሄድ ጀመረ። በኮንፈረንሱ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከፓርቲው የተወከሉ አባላትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
ፓርቲው በአዲስ ዕሳቤዎች በጀመራቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ስኬቶች እያስመዘገበ ነው - አቶ ደስታ ሌዳሞ
Mar 28, 2024 262
ሀዋሳ ፤ መጋቢት 19/2016 (ኢዜአ)፡- የብልጽግና ፓርቲ በአዲስ ዕሳቤዎች በጀመራቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ስኬቶች እያስመዘገበ ነው ሲሉ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ። በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል አባላት የማጠቃለያ ክልላዊ ኮንፈረንስ "ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ። በመድረኩ ላይ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደገለጹት፤ ፓርቲው በየጊዜው መልካቸውን እየቀያየሩ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች በተቀናጀ አግባብ በመመከት፣ አዳዲስ አሰራሮችንና ስልቶችን በመዘርጋት አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ነው። ፓርቲው አባላቱንና አመራሩን በማስተባበር በአዲስ ዕሳቤ በጀመራቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ታሪክ የማይረሳቸው ስኬቶች እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። ሲዳማ ክልልም የብልጽግና ፓርቲ አንዱ ትሩፋት ነው ያሉት አቶ ደስታ፤ ይህንን እድል በመጠቀም ክልሉ የሠላምና የፀጥታ ስራ ተምሳሌት ለማድረግ ባከናወናቸው ተግባራት ስኬት ማምጣት መቻሉን ተናግረዋል። ሰላማችንን ይዘን በመዝለቃችን አቅማችንን ሙሉ ለሙሉ ልማት ላይ እንድናውል አድርጎናል ያሉት አቶ ደስታ፤ በዚህም በሁሉም መስኮች የነዋሪውን ህይወት የሚቀይሩ ድሎች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል። በኮንፍረንሱ ላይ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሰማ ጥሩነህ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ፓርቲው አስተሳሳሪና ገዥ ትርክትን በመገንባት በቀጣናው ተሰሚነት ያላት አገር ከመገንባት ባለፈ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ራዕይ ሰንቆ እየተጋ ይገኛል። ፓርቲው የሲዳማ ክልልን ጨምሮ በሁሉም አካባቢዎች ባደረገው ግምገማ በሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ውሰጥ ያከናወናቸው ስራዎች ቃሉን በተግባር እየፈፀመ መሆኑን ያረጋገጡ ናቸው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት የሚቀሩትን ጉድለቶችን እያረመ ብልጽግናን በተግባር እያረጋገጠ የሚሄድ ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል። በክልል አቀፍ ኮንፍረንሱ ላይ ከክልል፣ ከዞኖች፣ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችና አባላት እየተሳተፉ ነው።
በባህር ዳር ከተማ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶችን ለማሳካት የመንግስት ሰራተኛው ሊረባረብ ይገባል
Mar 28, 2024 145
ባህር ዳር፤ መጋቢት 19 / 2016 (ኢዜአ)፡- በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶችን ለማሳካት የመንግስት ሰራተኛው ግንባር ቀደም ሆኖ ሊረባረብ እንደሚገባ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አሳሰቡ። አስተዳደሩ ከመንግስት ሰራተኞች ጋር በሰላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ዛሬ ተወያይቷል። ምክትል ከንቲባው አስሜ ብርሌ እንደገለጹት፤ በከተማ አስተዳደሩ የተገኘውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የሁሉንም አካላት ያልተቆጠበ ርብርብና ዕገዛ ያስፈልጋል። ባለፉት ስምንት ወራት በህብረተሰበቡ ተሳትፎ ሰላምን ከማስፈን ጎን ለጎን የከተማዋን ዕድገት ለማፋጠን የሚያግዙ የልማት ስራዎችን ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል። እንዲሁም ካለፈው ዓመት ከተሻገሩ በተጨማሪ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ አዳዲስ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም አስረድተዋል። የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋትና የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የስራ እድል የማመቻቸት ተግባር ማከናወን እንደተቻለም አብራርተዋል። የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቀጣይነት ለመቅረፍም ችግሮቹ ተለይተው ወደ ስራ መገባቱን አመልክተዋል። የመንግስት ሰራተኛውም የተገኘውን ሰላም አፅንቶ ከማዝለቅ ጎን ለጎን የታቀዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በቀሪ ወራት ለመፈፀም ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል። በተለይ ለመልካም አስተዳደር ችግሮች መንስኤ የሆኑ ብልሹ አስራሮችን የመንግስት ሰራተኛው በመታገልና በማጋለጥ ህብረተሰብ የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል። ከውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ታዬ መላኩ በሰጡት አስተያየት፤ ብልሹ አሰራርን በመታገል ህብረተሰቡ የሚፈልገውን የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ''የተቀጠርነው ህዝብን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ነው ፤ ሁላችንም ሚናችን በመገንዘብ ባለጉዳይን ሳናጉላላ ታማኝ ሆነን ልናገለግል ይገባል'' ብለዋል። በመድረኩም የክልልና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎችና የባህር ዳር ከተማ የመንግስት ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከተለያየ የማኅበረሰብ ዳራ ከተውጣጡ ከመላው ኢትዮጵያ ከመጡ ሴቶች ጋር ተወያዩ
Mar 28, 2024 187
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2016(ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከተለያየ የማኅበረሰብ ዳራ ከተውጣጡ ከመላው ኢትዮጵያ ከመጡ ሴቶች ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ በዛሬው ውይይት ከተለያየ የማኅበረሰብ ዳራ የተውጣጡ ከመላው ኢትዮጵያ የመጡ ሴቶችን ሀሳብ አዳምጫለሁ ብለዋል። በኅብረተሰባችን ውስጥ የሴቶች ሚና ብዙ መልክ እና ብዙ ገፅ ያለው ነው ሲሉም አክለዋል።

ማህበራዊ
በጋምቤላ ክልል አልፎ አልፎ እየተከሰተ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ የፌደራልና የክልሉ የፀጥታ አካላት ውይይት አደረጉ
Mar 29, 2024 27
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል አልፎ አልፎ እየተከሰተ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በተገኙበት የፌደራልና የክልል የፀጥታ አካላት ውይይት አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሸነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በተካሄደው ውይይት ላይ አንዳንድ ግለሰቦች ጎራ እየለዩ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን እያደረሱ እንዳሉ በመገምገም ችግር ፈጣሪዎችን በአስቸኳይ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የፀጥታ አካላት የፀጥታ ችግሩን ለመቅረፍ ወደ ኦፕሬሽን በመግባት ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በቁጥጥር ሥር እያዋሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራሉ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ የፖሊስ ሠራዊቱን አባላት፣ የስደተኞች ካምፕንና በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሚጠበቁ ተቋማትን ጎብኝተዋል። ሠራዊቱ በተመደበባቸው አካባቢዎች ሁሉ እየተወጣ ያለውን ፖሊሳዊ ተልዕኮ አጠናክሮ እንዲቀጥል መመሪያ መስጠታቸውን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ለአራት መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዓረግ ሰጠ
Mar 29, 2024 37
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ለአራት መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዓረግ መስጠቱን አስታወቀ ። በጥናትና ምርምር ስራቸው የላቀ የፈጠራ ውጤት ላስመዘገቡት አራት ውጤታማ መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዓረግ ከመጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መስጠቱን የዩኒቨርሲቲው ሴኔት አረጋግጧል ። ከአውቶሞቲቭ ምህንድስና ዘርፍ ሌተናል ኮሎኔል ዶክተር ብስራት የሱፍ፣ ከሜካኒካል ዲዛይን ሻለቃ ዶክተር ሰሎሞን ሰይድ፣ ከኬሚካል ምህንድስና ሻለቃ ዶክተር ወንዳለም ምስጋነውና ከሜካትሮኒክ ምህንድስና ሻለቃ ዶክተር ርእሶም ወልደ ጊወርጊስ ናቸው የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረጉን ያገኙት። መምህራኑ በየስራ ዘርፋቸው ባስመዘገቡት ልዩ ውጤት የተመዘኑ መሆኑም ተገልጿል። በወታደራዊ አገልግሎት ስራ ላይ ለሚገኙ ምሁራን የተሰጠው የደረጃ እድገት በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገውም ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ቀዳሚና ተመራጭ የመረጃ ምንጭ የሚያደርጉትን አሰራሮቹን ማጠናከር አለበት
Mar 29, 2024 49
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ቀዳሚና ተመራጭ የመረጃ ምንጭ የሚያደርጉትን አሰራሮቹን ማጠናከር አለበት ሲል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። ቋሚ ኮሚቴው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ቦንጋ ከተማ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ተገኝቶ ምልከታ አድርጓል። በምልከታውም ኢዜአ ለዜጎች ተመራጭና ቀዳሚ የመረጃ ምንጭነቱን በተሻለ ለማሳደግና የይዘት ስራዎችን በተለያዩ ቋንቋዎችም ተደራሽ በማድረግ ተመራጭና ተወዳዳሪ ሊሆን እንደሚገባውም ቋሚ ኮሚቴው አንስቷል። በተለይም ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮች ዜጎች በሚያውቁት ቋንቋ ብዝሃነትን በጠበቀ መልኩ ተደራሽ ቢደረጉ ተመራጭነቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ቋሚ ኮሚቴው ያስረዳው። የቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታ ቡድን አስተባባሪ አቶ ከድር እድሪስ ኢዜአ ዜና የሚያመርትበትንም ሆነ ለማህበራዊ ሚዲያ ተደራሽ የማድረግ አቅሙን ተጠቅሞ በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት በማስተዋወቅ ረገድ ብዙ ይጠበቅበታል ነው ያሉት። በሌላ በኩል ስለ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በስፋት በማቀድ ዜጎች ሃገሪቱ ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ እንዲያውቁ መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል። የምርመራ ጋዜጠኝነትን ቀዳሚ የተቋሙ ተልዕኮ በማድረግ ለሙስና ትግሉ የበኩሉን ሊያበረክት ይገባል ያሉት የቡድኑ አስተባባሪ ለዚህም ከሌሎች የዲሞክራሲ ተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባው ማሳሰቡን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደ ደቡብ ሱዳን ለሚሰማሩ የኢትዮጵያ ፖሊስ ከፍተኛ መኮንኖች ሽኝት ተደረገ
Mar 29, 2024 76
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደ ደቡብ ሱዳን ለሚሰማሩ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ መኮንኖች ሽኝት ተደርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በሽኝት መርሃግብሩ ላይ ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለሚሰማሩ የፖሊስ መኮንኖች ባስተላፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ፖሊስ ሠራዊት በሥነ-ምግባሩ እና በወታደራዊ አቅሙ በዓለም አቀፍ ተቋማት ተፈላጊ እና ተመራጭ እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡ በስምሪታቸው ለሚያገኟቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እና የተለያዩ ሀገራት የፖሊስ መኮንኖች የኢትዮጵያ ፖሊስ አሁን የደረሰበትን ደረጃ የሚያመላክት የላቀ ሥነ-ምግባርና ፖሊሳዊ ሙያ ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ዕድሉን ሳያገኙ በጡረታ በክብር የተሰናበቱ የፖሊስ ሠራዊቱ አባላትን በቀጣይ ለማካተት እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡ ለሰላም አስከባሪ ተጓዦች ተልዕኳቸው የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰላም ማስከበር ማዕከል ኃላፊ ኮማንደር ተገኝ አጋዥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ስምሪት ተቋርጦ እንደነበረ አንስተው ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና ማኔጅመንቱ ከፍተኛ ጥረት አድርገው እንደገና በማስጀመራቸው ላቅ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል። በተለያዩ ጊዜያቶች በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳንና በአብዬ ግዛቶችና በሐይቲ የተሰማሩ የፌደራል ፖሊስና የክልል ፖሊስ አመራሮች የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት በመወጣት የሀገራቸውንና የተቋማቸውን መልካም ገፅታ መገምባታቸውን ተናግረዋል፡፡ ለሰላም ማስከበር የሚሰማሩ የፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በሚሰማሩበት ሀገር ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎችን ባህልና እሴት በመጠበቅና በማክበር እንደቀደመው ሁሉ የሀገራችንና የተቋማችን ስም ከፍ ብሎ እንዲነሳ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። የሴት ፖሊስ ተሳታፊዎች ቁጥር እስካሁን ከነበረው የሰላም መስከበር ስምሪት በቁጥር ብልጫ ያለው እና 11 ሴት አመራሮች የሚሳተፉበት መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው እና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢኮኖሚ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከል ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ቁጥጥር እየተደረገ ነው
Mar 29, 2024 0
ሶዶ ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከል ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገለጸ። ቢሮው ህገ-ወጥ ንግድን መከላከል ላይ ያተኮረ ስልጠና ከ12 ዞኖች ለተውጣጡ ፈጻሚ ባለሙያዎች በወላይታ ሶዶ ከተማ እየሰጠ ነው። የቢሮው ሃላፊ አቶ ገሌቦ ጎልቶሞ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በክልሉ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የገበያ ስርአቱን በማዛባት የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እያደረገ ነው። ከዚህም ባለፈ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴው ህጋዊ ነጋዴዎች ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን ገልጸዋል። ገበያው እንዳይረጋጋ ምክንያት የሆኑ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችና ህገ-ወጥ ደላሎችን ከገበያ ስርአት ለማስወገድ ቢሮው ከፍትህ አካላት ጋር እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ከፍትህ አካላት በተጨማሪ ቢሮው ከተለያዩ ባለደርሻ አካላት ጋር በመሆን የቁጥጥር ስራውን ማጠናከሩን አስረድተዋል። በሌላ በኩል በክልሉ በጉምሩክ ከተፈቀዱ 3 ኬላዎች ውጭ በርካታ ኬላዎች በየአካባቢው መኖራቸው ህገ-ወጥ ንግድን ከመቆጣጠር ይልቅ ምርት እንዳይንቀሳቀስ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ይህን ለማስተካከል በተደረገው ጥረት 33 ኬላዎችን ማንሳት እንደተቻለና ቀሪዎችን ለማስወገድ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ከነዳጅ ግብይት ጋር በተያያዘ እንደ ሀገር በተደረገው ንቅናቄ በክልሉ ካሉ 89 ነዳጅ ማደያዎች መካከል 86ቱ በቴሌ እና ሲቢኢ ብር መገበያየት እንዲችሉ መደረጉን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ዘርፉ አሁንም ከህገ-ወጥ ነጋዴዎችና ደላሎች አለመጽዳቱን ጠቁመው ይህን ለማስተካከል የዛሬው ስልጠና የተሳለጠ የገበያ ስርአት ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል። ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል በጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የሰብል ምርት ቡድን መሪ አቶ ሽፈራው ጀጉ፣ በዞኑ የሚስተዋለው ህገ-ወጥ ንግድ ገበያው እንዳይረጋጋ ማድረጉን ገልጸዋል። የንግድ ስርአቱ በአሰራር እንዲመራና የኑሮ ውድነቱ እንዲረጋጋ ህገወጥነትን ለመከላከል የበኩሌን እወጣለሁ ብለዋል። ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለማስቆም በዞኑ ባሉ ሁሉም ወረዳዎች ህገ-ወጥ የንግድ ቁጥጥር ግብረ-ሃይል ተቋቁሞ እየሰራ ነው ያሉት ደግሞ ከጋሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት የሰብል ምርት ግብይትና ጥራት ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ተሾመ ዳንኤል ናቸው። ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በሰብል ምርት ግብይት፣ በእንስሳትና በገበያ መሠረተ ልማት ላይ ያተኮረ መሆኑ ተጠቁሟል።
ለቀጣናው የጋራ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚያበረክተው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ለጎረቤት አገራት ትልቅ የምስራች ነው
Mar 29, 2024 76
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦ለቀጣናው የጋራ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚያበረክተው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሊጠናቀቅ እየተቃረበ መሆኑ ለጎረቤት አገራት ትልቅ የምስራች ነው ሲሉ የግድቡ ተደራዳሪ ቡድን አባል ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው ተናገሩ። መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 95 በመቶ መድረሱን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ገልጿል። ግድቡን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ በግብጽና በሱዳን መካከል በሚደረገው የሦስትዮሽ ድርድር የኢትዮጵያ የተደራዳሪ ቡድኑ አባል ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው ጋር ኢዜአ ቆይታ አድርጓል። በዚህም በኢትዮጵያውያን እውቀትና ገንዘብ እየተገነባ ያለው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ መድረሱ የሚያኮራ መሆኑን ኢንጂነሩ አንስተዋል። ኢትዮጵያ የታላቁ የሕዳሴ ግድብን መሥራት መጀመሯን ተከትሎ ባለፉት ዓመታት ግንባታውን ለማስቆም ተጽዕኖ ለማድረግ የተሞከረበትና በግድቡ ዙሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ የተጻፈበት እንደነበር አስታውሰዋል። ይሁንና ኢትዮጵያ በእኩልነት፣ በፍትሃዊ ተጠቃሚነትና በሌሎች ላይ ጉዳት አለማድረስና አለመግባባቶችን በውይይት መፍታት በተመለከተ የምታራምደው መርህ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል እንዳስቻላት ጠቁመዋል። ይልቁንም ግድቡ የተፋሰስ አገራት ላይ ምንም ጉዳት የማያደርስ፣ የጋራ ተጠቃሚነትንና ትስስርን የሚያጠናክር እንዲሁም የጎርፍ ሥጋትን የሚቀነስና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት አስገንዝበዋል። ግድቡ ከኢትዮጵያ አልፎ ለቀጣናው የኃይል ምንጭ በመሆን የጋራ ልማት በማረጋገጥ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው ግድቡ አሁን ላይ ሊጠናቀቅ መቃረቡ ለአፍሪካ በተለይም ለጎረቤት አገራት ትልቅ የምስራች ነው ብለዋል። ግድቡ እዚህ እንዲደርስ አስቸጋሪውን የአየር ጸባይ ተቋቁመው ቀን ከሌት በትጋት ለሰሩ ኢትዮጵያውያን ምስጋና አቅርበው ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ኃብት በመጠቀም የምጣኔ ኃብት እድገቷን ለማፋጠን ተመሳሳይ ፕሮጀክቶችን ማከናወን እንዳለባት ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ በሦስቱ አገራት መካከል በሚደረገው ድርድር በሥምምነት እንዲቋጭ ያላሰለሰ ጥረት ማድረጓን አስታውሰዋል። እንዲያም ሆኖ በግብጽ በኩል በሚቀርቡ ተገቢነት የሌላቸው ኃሳቦች ሥምምነት ላይ መድረስ አለመቻሉን ጠቅሰው ኢትዮጵያ አሁንም ድርድሩ በሥምምነት እንዲቋጭ ያላትን ጽኑ ፍላጎት ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ አካታች የፋይናንስ ምሕዳር ለመፍጠር እያደረገች ያለችው ጥረት የሚበረታታ ነው- ዓለም ባንክ
Mar 29, 2024 62
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ አካታች የፋይናንስ ምሕዳር ለመፍጠር እያደረገች ያለችው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የዓለም ባንክ የአፍሪካ ስርዓተ ፆታ ማበልጸጊያ ጥናት ቡድን መሪ ማይክል ሱልቫን ተናገሩ። የጥናት ቡድን መሪው ማይክል ሱልቫን ለኢዜአ እንዳሉት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ የፋይናንስ ምሕዳር አካታችነት ላይ ሰፊ ክፍተት ይታያል። በኢትዮጵያ ያለውን የፋይናንስ አካታችነት ማሳደግ ከተቻለ እንደ ሀገር በየዓመቱ ከ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ሀገራዊ ዕድገት ማሳካት እንደሚቻል ገልጸዋል። አካታች የፋይናንስ ስርዓት መረጋገጥ በራሱ በሀገራዊ ጥቅል ምርት ዕድገት ላይ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡ የፋይናንስ ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን የሴቶች ድርሻ ማሳደግ ይገባል ብለዋል። የፋይናንስ አካታችነት የነፍስ ወከፍ ገቢ እድገት እንዲያስመዘግብ ከመርዳቱ ባለፈ ለዘላቂ ብልጽግና እንደሚበጅ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አካታች የፋይናንስ ምሕዳር ለመፍጠር አካታች ፋይናንስ ስትራቴጂ በመቅረጽ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ እንደሆነ ገልጸዋል። በትናንትነው ዕለት በይፋ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሴት የፋይናንስ ባለሙያዎች ኔትወርክም አካታች የፋይናንስ ስርዓት እንዲጎለበት ስለሚያግዝ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ነው የተናገሩት። ኔትወርኩ ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት፣ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ብሎም እንደ ሀገር ትልቅ ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገት እንዲመዘገብ የራሱ ሚና እንደሚኖረውም ነው ያስረዱት።
ኢትዮጵያ በቀጣናው የጀመረችውን የኃይል ትስስር አጠናክራ ትቀጥላለች
Mar 29, 2024 103
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በቀጣናው የጀመረችውን የኃይል ትስስር አጠናክራ እንደምትቀጥል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለጸ። የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት እያቀረበች ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል የበለጠ ለማስፋፋት እየሰራች ነው። ኢትዮጵያ ለሱዳን፣ ለጅቡቲና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበች መሆኑን ገልጸው ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል እስከ ደቡብ አፍሪካ የማድረስ ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል። በቅርቡም ለታንዛኒያ ኃይል ለማቅረብ ሥምምነት ላይ መደረሱን ጠቁመው ሌሎች የጎረቤት አገራትም ለአብነትም ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳና ሩዋንዳ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመውሰድ ፍላጎት ማሳየታቸውን ተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ከአገራቱ ጋር ንግግር መጀመሯን ገልጸው ኢትዮጵያ በቀጣይም በቀጣናው የጀመረችውን የኃይል ትስስር አጠናክራ እንደምትቀጥል ነው ያረጋገጡት። እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ፤ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ሥርቆት እየተበራከተ መሆኑን ጠቁመው ይህን ለመከላከል የኅብረተሰቡ ርብርብ ያስፈልጋል። የመሰረተ ልማቶች ስርቆት በኃይል የተለያዩ አገልግሎቶች የሚሰጡ ተቋማት ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል እንደሚፈጥር ጠቅሰው ይህም በአገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ እንደሆነ ተናግረዋል። ለዚህም ከወረዳ እስከ ቀበሌ በሚገኙ መዋቅሮች ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። በቅርቡም ኅብረተሰቡ በዚሀ ሂደት ተሳትፎውን ለማሳደግ ከመገናኛ ብዙኃን ጋር በመሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ ሥራዎችን መሥራት እንደሚጀመር ጠቁመዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
አምራች ኢንዱስትሪዎችን ከሸማቾች ጋር የሚያገናኝ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ
Mar 29, 2024 43
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦አምራች ኢንዱስትሪዎችን ከሸማቾች ጋር የሚያገናኝ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ፡፡ ኤግዚቢሽኑ አምራች ኢንዱስትሪዎች እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲያደርጉና የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ታስቦ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተገኝ ጓለ ኤግዚቢሽንና ባዛሩ አምራቾች የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩና ህብረተሰቡም አማራጭ ግብይት እንዲያገኝ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡ መንግስት በልዩ ትኩረት አምራቾች በስራ ሂደታቸው የሚገጥማቸውን ማንኛውንም ችግርና የመሰረተ ልማት ጥያቄ በመፍታት ምርታቸውን ተደራሽ እንዲያደርጉ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ እንደ ክፍለ ከተማው ነባራዊ ሁኔታ በምርት ሂደት ላይ ተግዳሮት የገጠማቸውን አምራቾች በመለየት መፍትሄ መስጠት መቻሉንም አስታውቀዋል፡፡ በኤግዚቢሽኑ ላይ የተሳተፉ አምራቾች እንዳሉት ባዛሩ በተለይ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች እርስ በርስ እንዲተዋወቁ ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡ ኤግዚቢሽንና ባዛሩ አምራቾችን እርስ በእርስ ከማቀራረብ ባለፈ ህብረተሰቡ የሀገር ውስጥ ምርቶችን እንዲጠቀም ሰፊ ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም አንስተዋል፡፡ በባዛሩ በቆዳ፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ አግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ ኬሚካል፣ በዕደ ጥበብ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ኤግዚቢሽንና ባዛሩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ለ5 ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ስኬታማ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመረጃ ማዕከል መሠረተ-ልማት ተገንብቷል - ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና
Mar 28, 2024 129
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2016(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ የዕውቀት ሽግግር የተገኘበት ስኬታማ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመረጃ ማዕከል መሠረተ-ልማት መገንባቱን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና ገለጹ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥነ-ምህዳር ግንባታ ላይ የሚመክር አውደ-ጥናት አካሂዷል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና፤ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የቴክኖሎጂ ልማት ጥናትና ምርምር የሚያደርጉ ሙያተኞች ተሳትፎ ለዘመናዊ ሁሉን አቀፍ የዜጎች አገልግሎት ፍላጎት መሳለጥ ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው አንስተዋል። በኢትዮጵያ የዕውቀት ሽግግር የተገኘበት ስኬታማ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመረጃ ማዕከል መሠረተ- ልማት መገንባቱን ጠቁመው፤ ለዘርፉ ልማትም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚና አላቸው ብለዋል። ለአብነትም የግብርና፣ ጤና፣ የፋይናንስ እና መሰል ተቋማትን የሥራ አቅምና ምርታማነት በሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች ተቀርፀው እየተሰራባቸው መሆኑን ተናግረዋል። የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የአስተዳደር ውጤታማነትን ለማሳደግም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የመረጃ ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቀዋል። ከተሞች በስማርት ሲቲ ግንባታ ሂደት ላይ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የቴክኖሎጂ ሥርዓት የታገዘ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መስክ ብቁ የሰው ኃይል እንዲኖር ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ድረስ ትምህርት እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል። ከዚህ ጎን ለጎንም እስከ 15 ቴታ ባይት መሸከም የሚችሉ ግዙፍ የመረጃ ማዕከል በመገንባት የዘርፉ ተመራማሪ ሙያተኞች ክህሎታቸውን የሚያበለጽጉበት የሥራ ክፍል እንደተዘጋጀ ገልፀዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቢቂላ ተክሉ፤ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ብዝኃ መስኮችን የሚነካ ዘርፍ በመሆኑ በቴክኖሎጂ ክህሎት ልማት እየሰራን ነው ብለዋል። ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር መሥራት የሚያስችል የትብብር ስምምነት በመውሰድ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥነ-ምህዳር ግንባታ የአውደ-ጥናት የምክክር መድረክም በዘርፉ ያሉ ዕድሎችን ወደ ጥቅም ለመቀየር ዓላማ ያደረገ መሆኑን አንስተዋል። በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ምሁራንና ተማሪዎች ተሳትፈዋል። በኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥነ-ምህዳር ግንባታ፣ የክህሎት ልማት እና አስተምህሮን የሚዳስሱ የመነሻ ጽሑፎች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል።
ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማስተሳሰር ከቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር መስራቱን ይቀጥላል - ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ
Mar 27, 2024 133
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2016(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደቱን በዲጂታል ለማስተሳሰር የተጀመረውን እንቅስቃሴ እውን ለማድረግ ከቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዩንቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ገለጹ። ሁዋዌ ኢትዮጵያ ''በኢትዮጵያ የዲጂታል ትምህርት ትግበራን ማፋጠን '' በሚል መሪ ሃሳብ የዲጂታል ሳምንት ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል። በመርኃ ግብሩ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስና የባህል ተቋም ተወካይ፣ የዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶችና በቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢኖቬሽን መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። የዩንቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ እኤአ በ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል። በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስማርት የመማሪያ ክፍሎችን በመገንባት የመማር ማስተማር ሂደቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማሳለጥ የሚረዱ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በዚህም ዩንቨርሲቲው ከሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በመተባበር ስማርት የመማሪያ ክፍሎችንና የዳታ ማዕከላት ዝርጋታን ተግባራዊ ለማድረግ የጀመራቸው ሂደቶች መኖራቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም ዩንቨርሲቲው ለዲጂታል የትምህርት ሴክተር ትኩረት በመስጠት እንደ ሁዋዌ ካሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋራ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስ የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ተወካይ ዶክተር ሪታ ቢሶናት በበኩላቸው፣ በአሁኑ ጊዜ ትምህርትን በዲጂታል መደገፍ የዓለም አገራት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል። በአፍሪካ የትምህርት ምህዳሩን ለማስፋትና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት በትኩረት መስራት ይገባል ነው ያሉት። በተለይም እንደ ሁዋዌ ያሉ ኩባንያዎች በአፍሪካ የዲጂታል ትምህርት ግንባታን ለማሳለጥ ያላቸው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን አስገንዝበዋል። ዩኔስኮ ከሁዋዌ ኩባንያ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ የአይሲቲ መሰረተ ልማት ግንባታንና ሌሎች ፕሮጀክቶችን እየተገበረ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የሁዋዌ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ማይክል ሊዩ ኢትዮጵያ በ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ወጥና እየሰራች መሆኗ ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። በዚህም ሁዋዌ በኢትዮጵያ የአይሲቲ መሰረተ ልማትና የዳታና የክላውድ ቤዝ መሰረተ ልማቶችን ዝርጋታ እና በዩንቨርሲቲዎች የስማርት ክፍሎችን እውን ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ግንባታ መሳተፍ ከጀመረ 25 አመታት አስቆጥሯል። በአሁኑ ወቅት ከ30 ዩንቨርሲቲዎች ጋር በመጣመር የዲጂታል ትምህርት ዝርጋታን እውን ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ የሞባይል አገልግሎት ደንበኞች ቁጥር 85 ሚሊዮን ደርሷል
Mar 26, 2024 312
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የመንግስትና የግል የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ደንበኞች ቁጥር 85 ሚሊዮን መድረሱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ ስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በተገኙበት ዲጂታል ኢትዮጵያን ለማሳካት የተከናወኑ ተግባራትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደርጓል። በመድረኩ በነበረው የፓናል ውይይት ላይ የተሳተፉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በቴሌኮም ዘርፉ የተደረጉ ማስፋፊያዎችና ለውጦችን ዘርዝረዋል። በዚህም በግልና በመንግስት የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች የሞባይል አገልግሎት ደንበኞች ቁጥር 85 ሚሊዮን መድረሱን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁለቱ የቴሌኮም የአገልግሎት አቅራቢዎች ከ96 ሚሊዮን በላይ ማስተናገድ የሚችል የኔትወርክ አቅም መፍጠራቸውንም ጠቅሰዋል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2018 በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 17 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 41 ሚሊዮን መድረሱን ተናግረዋል። በመንግስትና በግል አጋርነት በተሰራ ማስፋፊያ 6 ነጥብ 3 ሜጋዋት (አይቲ ሎድ) የመሸከም አቅም ያለው የዳታ ማዕከል መገንባቱን ጠቅሰዋል። ይህም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ወሳኝ ሚና እንዳለው ነው ያነሱት፡፡ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በማድረግ የዲጂታል ክፍያን ማሳደግ የተገነባውን መሰረተ ልማት እሴት እንዲጨምር ማድረግ የተቻለበትን አሰራርም አንስተዋል። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና በበኩላቸው በኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እድገት ውስጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የበኩሉን ሚና እንዲጫዎት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ዘርዝረዋል። በዚህም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ለማሳካት በጤናው ዘርፍ፣ ስማርት ሲቲ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ ግብር፣ በፍትህ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን ከማድረግ ጎን ለጎን ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንንነት አስተዳደር ዋና ዳሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ናቸው። የውይይት ተሳታፊዎች በበኩላቸው የዲጂታል አሰራርና አገልግሎትን በማቀላጠፍ፣ ለህብረተሰቡ ተደራሽ በመሆንና ጊዜና ወጪን በመቆጠብ እየተመዘገበ ያለውን ለውጥ አንስተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ በመሬት፣ግንባታ ፈቃድ፣ ወሳኝ ኩነትና ሌሎች ዘርፎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማሳለጥ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያን ብልጽግና እንዲሁም ዲጂታል ኢትዮጵያን በቀሪዎቹ አመታት እውን ለማድረግ የተጀመሩ የቅንጅት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበትም በመድረኩ ተገልጿል፡፡
ስፖርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት መርሃ ግብር በዛሬው እለት መካሄድ ይጀምራል
Mar 28, 2024 115
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2016(ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች በኋላ በ19ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ወደ ውድድር ይመለሳል። በመርሃ ግብሩ መሰረትም መቻል ከወላይታ ድቻ ከቀኑ 10 ሰዓት በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የሚሰለጥነው መቻል በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች በሁለቱ ድል ሲቀናው በሶስቱ ተሸንፏል። ክለቡ በ36 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በያሬድ ገመቹ የሚሰለጥነው ወላይታ ድቻ በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ምንም ጨዋታ አላሸነፈም። በሁለቱ ሲሸነፍ በሶስቱ አቻ ወጥቷል። ወላይታ ድቻ በ24 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሌላኛው የ19ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከነማ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ያገናኛል። በአሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ሁለቱን ሲያሸንፍ በሁለቱ ሽንፈት ገጥሞታል። አንድ ጊዜ ነጥብ ተጋርቷል። ቡናማዎቹ በ29 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በውበቱ አባቱ አባተ የሚሰለጥነው ፋሲል ከነማ በበኩሉ ባለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች በሁለቱ ሲያሸንፍ አንድ ጊዜ ተሸንፏል። ሁለት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። ክለቡ በ30 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ጨዋታ ነገም ቀጥሎ ሲውል አዳማ ከተማ ከፕሪሚየር ሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኑ 10 ሰዓት፤ ሀዲያ ሆሳዕና ከሀምበሪቾ ዱራሜ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። የፕሪሚየር ሊጉ 19ኛ ሳምንት መርሐ ግብር እስከ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያል። ቅዱስ ጊዮርጊስ በ37 ነጥብ ሊጉን እየመራ ይገኛል። የሀዋሳ ከተማው አሊ ሱሌይማን በ10 ግቦች የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ የግብ አስቆጣሪነት እየመራ ነው።
ኢትዮጵያ በ13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስፖርተኞች ባስመዘገቡት አኩሪ ውጤት ኮርታባቸዋለች
Mar 26, 2024 197
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2016(ኢዜአ)፦በ13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስፖርተኞች ፈታኙን ሞቃታማ የአየር ንብረት በመቋቋም ባስመዘገቡት አመርቂ ውጤት ኢትዮጵያ ኮርታባቸዋለች ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ። በጋና በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስምንተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል። ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ በሚኒስቴሩ የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉና ሌሎች የፌዴሬሽኑ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮችና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል። ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም በጋና የተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ9 የወርቅ፣ 8 የብር፣ 5 የነሐስ በአጠቃላይ 22 ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሁሉም የስፖርት አይነቶች ስምንተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ስፖርተኞቹ በጋና የነበረውን ሞቃታማ አየር በመቋቋም ያስመዘገቡት ውጤት የሚያኮራ ነው ብለዋል። በአትሌቲክስ የተመዘገበው ውጤትና የተገኙ ሜዳሊያዎች ለቀጣይ ተስፋ የሚሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል። መንግስት ለስፖርቱ እድገት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። የባህልና የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጨዋታዎች በዘጠኝ ስፖርቶች ተሳትፋ ከአትሌቲክስ በተጨማሪ በብስክሌትና ቦክስ ያስመዘገበችው ውጤት በሌሎች ስፖርቶች ላይ ከተሰራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል የሚያመላክት ነው ብለዋል። ለዚህም መንግስት ከብሔራዊ ስፖርት ፌዴሬሽኖችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰራ አመልክተዋል። በአህጉራዊው ስፖርታዊ ሁነት የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ በሚገባ ማስተዋወቅ መቻሉን ተናግረዋል። በአፍሪካ ጨዋታዎች የተመዘገበው ውጤት በፓሪስ ለሚካሄደው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ስንቅና አቅም እንደሚሆን ነው አምባሳደር መስፍን የገለጹት። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በአፍሪካ ጨዋታዎች ከተመዘገቡ 22 ሜዳሊያዎች 18ቱ በአትሌቲክሱ የተገኘ መሆኑን ገልጻ የተገኘው ውጤት አትሌቶች አስቸጋሪውን የአየር ንብረት ተቋቁመው ያገኙት እንደሆነ ተናግራለች። በተለያዩ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ የስፖርት ሁነቶች ላይ በአትሌቲክሱ አመርቂ የሚባል ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ ጠቅሳለች። እንደ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በተለያዩ ስፖርቶች በምትሳተፍበት 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በአትሌቲክሱ የተሻለ ውጤት ለማግኘት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ነው ብላለች። በ13ኛው አፍሪካ ጨዋታዎች በ20 ኪሎ ሜትር ሴቶች እርምጃ የብር ሜዳሊያ ያገኘችው አትሌት ስንታየሁ ማስሬና በ3 ሺህ ሜትር ሴቶች መሰናክል የነሐስ ሜዳሊያ ያገኘችው አትሌት ሎሚ ሙለታ በጋና የነበረው ሞቃታማ የአየር ንብረት ፈታኝ ቢሆንም ጫናውን በመቋቋም ሜዳሊያ ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል። በቀጣይ በሚኖሩ ውድድሮች ላይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ጥረት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ካገኘቻቸው በተጨማሪም በቦክስ ሁለት የወርቅና አንድ የነሐስ እንዲሁም በብስክሌት አንድ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። በ13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ለተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የእውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ኢዜአ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአፍሪካ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ይገባል
Mar 25, 2024 259
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2016(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስምንተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ይገባል። የአፍሪካ ጨዋታዎች ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም በጋና አክራ መካሄዱ ይታወቃል። በውድድሩ ከ53 ሀገራት የተወጣጡ ከ5 ሺህ በላይ ስፖርተኞች በ29 የስፖርት አይነቶች ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያም በአምስት የኦሊምፒክ ውድድሮችና አራት ኦሊምፒክ ያልሆኑ ስፖርቶች በድምሩ በዘጠኝ የስፖርት አይነቶች መሳተፏ ይታወቃል። በአትሌቲክስ፣ እግር ኳስ፣ ውሃ ዋና፣ የጠረጴዛና ሜዳ ቴኒስ፣ ቦክስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ብስክሌትና ወርልድ ቴኳንዶ ኢትዮጵያ የተሳተፈችባቸው የውድድር አይነቶች ናቸው። ኢትዮጵያ በ9 የወርቅ፣ 8 የብር፣ 5 የነሐስ በአጠቃላይ 22 ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሁሉም የስፖርት አይነቶች ስምንተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ካገኘቻቸው 22 ሜዳሊያዎች 18ቱ የተገኙት በአትሌቲክስ ነው፤ 7 የወርቅ 7 የብርና 4 የነሐስ ሜዳሊያ በአትሌቲክሱ ተገኝቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በቦክስ ሁለት የወርቅና አንድ የነሐስ እንዲሁም በብስክሌት አንድ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። በውድድሩ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድንም ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ የሚገባ መሆኑን ኢዜአ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ያደርጉለታል ተብሎ ይጠበቃል። በ13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ግብጽ 101 ወርቅ 46 ብር 42 ነሐስ በድምሩ 189 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን በበላይነት አጠናቃለች። ናይጄሪያ በ47 ወርቅ፣ 33 የብር እና 40 የነሐስ በድምሩ 120 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን የያዘች ሲሆን ደቡብ አፍሪካ በ32 ወርቅ 32 የብር እና 42 የነሐስ በድምሩ 106 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። በውድድሩ ከተሳተፉ 53 ሀገራት 45ቱ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ የገቡ ሲሆን አልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ጋና እና ሞሮኮ ከአራተኛ እስከ ሰባተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
አካባቢ ጥበቃ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ንቅናቄን አስጀመሩ
Mar 29, 2024 84
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ንቅናቄን በአዲስ አበባ ዛሬ አስጀመሩ። ንቅናቄው "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ኃሳብ ለቀጣይ ስድስት ወራት እንደሚካሄድ ተገልጿል። በማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የክልል የአካባቢ ጥበቃ ቢሮ ኃላፊዎችና የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የተጠናከረ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ እያከናወነች ትገኛለች። በዚህም የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርን ጨምሮ የወንዝ ዳርቻ ልማት፣ ከተሞችን ውብና ፅዱ ለማድረግ በርካታ ሥራዎችን እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል። ዛሬ የተጀመረው አገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ንቅናቄ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል እንደሚሰራ ገልጸው በዘርፉ የተጀመሩ ጥረቶችን ያጠናክራል ብለዋል። ንቅናቄው ከተሞች የሚያስወግዱትን ቆሻሻ በአግባቡ ሥርዓትን የተከተለ በማድረግ ውብና ምቹ ከተማ ለመገንባት ያለመ መሆኑም ተመላክቷል። የደምጽ ብክለትን መከላከልም ሌላው ንቅናቄው የሚሰራበት ዘርፍ መሆኑም እንዲሁ። የአየር፣ የውኃ፣ የአፈርና የድምፅ ብክለቶች ለመቀነስ ማኅበረሰቡን በማሳተፍ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር 6 ነጥብ 3 ቢሊየን ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል - ግብርና ሚኒስቴር
Mar 29, 2024 84
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2016(ኢዜአ)፦ በዘንድሮው የ2016 በጀት ዓመት አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር 6 ነጥብ 3 ቢሊየን ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ። በሚኒስቴሩ የተፈጥሮ ኃብት ልማትና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፋኖሴ መኮንን ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በመጪው የክረምት ወቅት 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዷል። ይህንንም ተከትሎ እስካሁን 6 ነጥብ 3 ቢሊየን ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ገልጸው ቀሪ ችግኞች ደግሞ በቀጣይ ወራት ለማዘጋጀት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው ያስረዱት። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከሚተከሉ ችግኞች ውስጥ 60 በመቶ የሚሆኑት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መሆናቸውን ተናግረዋል። እነዚህም የፍራፍሬ ችግኞች፣ ለእንስሳት መኖ የሚውሉና ለአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ችግኞች መሆናቸውን ገልጸዋል። ቀሪ 40 በመቶ የሚሆኑት ችግኞች የአየር ንብረት ተፅዕኖ ለመከላከል የሚረዱ የደን ዕፅዋቶች (አገር በቀል የዛፍ ችግኞች) መሆናቸውን ጠቁመዋል። የችግኝ ተከላ መርኃ ግብሩን ውጤታማ ለማድረግ የችግኝ መትከያ ጉድጓዶችን በበቂ ሁኔታ ከወዲሁ እየተዘጋጁ መሆኑንም ነው ያብራሩት። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር እስካሁን ከ32 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞች ተተክለዋል። በቀጣይ ሦስት ዓመታት ደግሞ 17 ነጥብ 5 ቢሊየን በመትከል 50 ቢሊየን ችግኞችን በስምንት ዓመታት ውስጥ ለመትከል እቅድ ተይዟል። እስካሁን ለተተከሉት ችግኞች በተደረገው ክትትልና እንክብካቤ የችግኞቹ የጽድቀት መጠን ከ90 በመቶ በላይ መድረሱን ጠቅሰዋል። ችግኞቹ የአየር ንብረትን ከለውጥን በመቋቋም እንዲሁም ደርቀው የነበሩ ኃይቆች ጭምር ውኃ መያዝ እንዲጀምሩ ማስቻሉን ገልጸዋል። መርኃ ግብሩ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠርም ትልቅ አስተዋጽዖ ማድረጉን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው የአረጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥ በመከላከል ለሌሎች አገራት አርአያ እንድትሆን ማስቻሉን ጠቁመዋል።
የድምጽ ብክለት በማስከተል ችግር የፈጠሩ 1 ሺህ 164 የተለያዩ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል- የመዲናዋ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
Mar 28, 2024 95
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2016(ኢዜአ):- በበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት የድምጽ ብክለት በማስከተል ችግር የፈጠሩ 1 ሺህ 164 የተለያዩ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ። የድምጽ ብክለት በሰዎች የጉዞ፣ የእንቅልፍ፣ የስራ፣ የትምህርት፣ የንግግር ወይም በመሳሰሉት መስተጋብር ላይ ስነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ይህንን ችግር ለመከላከል በኢትዮጵያ የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 300/1995) ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል። ለመኖሪያ አካባቢዎች፣ ለንግድ አካባቢዎችና ለኢንዱስትሪ ዞኖች መውጣት የሚገባው የድምጽ መጠን በድምፅ ልኬት መሳሪያ ዲሲቢልስ (dB) መሰረት በቀን እና በማታ የተመጠነ አድርጎ አስቀምጧል። በመሆኑም በሳይንሳዊ ልኬቱ መሰረት ለተጠቀሱት አካባቢዎች በቀን 55፣ 65 እና 75 ዲሲቢል ሲሆን በሌሊት ደግሞ 45፣ 57 እና 70 ዲሲቢልስ እንዳይበልጥ ያስገድዳል። ከዚህ ካለፈ ግን የድምጽ ብክለት የሚፈጥር በመሆኑ ማህበራዊ ችግር የሚያስከትል መሆኑ ይነገራል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ዲዳ ዲሪባ፤ የተቀመጠውን ህግ በሚተላለፉ ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በ1 ሺህ 164 በሚሆኑ ተቋማት ላይ ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ የገንዘብ ቅጣትና የመስሪያ ቦታ ማሸግን ያካተተ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል። እርምጃው ከተወሰደባቸው መካከል በርካቶቹ ከህብረተሰቡ የድምጽ ብክለት አቤቱታዎችን መነሻ በማድረግ መሆኑን ጠቁመዋል። በአሰራሩ መሰረት ህጋዊ እርምጃ ከመውሰድ ባለፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል። በንግድና በአምራች ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ተቋማት ባለስልጣኑ ባወጣው የድምጽ ልኬት መሰረት ሕግና ደንብ አክብረው እንዲሰሩ አሳስበው ተላልፈው በሚገኙት ላይ ፈቃድ እስከ መሰረዝ የሚያደርስ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ አሳስበዋል።
ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 15 ሚሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል- የመዲናዋ የውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ
Mar 28, 2024 112
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2016(ኢዜአ):- ለዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 15 ሚሊዮን ችግኞች መዘጋጀታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አስታወቀ። የአየር ንብረት ለውጥ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመከላከልና የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ መንግስት የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ደግሞ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት የላቀ ሚና እንዳለው ይታመናል። በዚህም መሰረት ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ ለሚካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል። በመዲናዋም ዘንድሮ ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ልማት በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ገልጿል። የቢሮው የችግኝ ጣቢያ የግብአት አቅርቦት ስርጭት ቡድን መሪ ጌትነት አድማሱ፤ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ልማት በዘጠኝ የችግኝ ጣቢያዎች የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን ችግኞች የማፍላት ስራ ተከናውኗል ብለዋል። በዚህም ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 15 ሚሊዮን ችግኞች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። በቢሮው የእንጦጦ ችግኝ ጣቢያ ተቆጣጣሪ ወጣት በረከት መርጋ፤ የሶስኒ የችግኝ ጣቢያ ተቆጣጣሪ ወይዘሪት አበበች መካ ለክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ችግኝችን በብዛትና በአይነት የማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። በመዲናዋ ለሚከናወነው የክረምት የችግኝ ተከላ የተለያዩ አይነት ዝርያ ያላቸውን ችግኞች ለማቅረብ ዝግጅት አድርገናል ብለዋል። 2011 ዓ.ም እስከ 2014 ዓ.ም በአራት ዙሮች በተካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 25 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸው ይታወሳል። በሁለተኛው ምእራፍ የመጀመሪያ ዓመትም (በ2015 ዓ.ም) 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በጅቡቲ ትላንት ሌሊት በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ደረሰ
Mar 28, 2024 108
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2016(ኢዜአ)፦በጅቡቲ ትላንት መጋቢት 18/07/2016ዓ.ም ለሊት በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ መድረሱ ተገለጸ። በተለይም በልበላ በተባለው አካባቢ የደረሰ የጎርፍ መጥለቅለቅ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ዝርዝር የጉዳቱን መጠን ለማጣራት ጥረት እየተደረገም ይገኛል። የጅቡቲ አየር ሀይል እና ድንገተኛ አደጋ መከላከል ክፍል ሰራተኞች በሂሊኮፕተር ጭምር በመታገዘ በጎርፍ አደጋ የገጠማቸውን ሰዎች በመርዳት ላይ እንደሚገኙ የኢዜአ ምንጮች ገልጸዋል።
በደቡብ ምስራቅ ብራዚል በጣለ ከባድ ዝናብ በትንሹ ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
Mar 25, 2024 214
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2016(ኢዜአ)፦በደቡብ ምስራቅ ብራዚል በጣለ ከባድ ዝናብ በትንሹ ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። ከሬዮዴጄኔሮ 65 ኪሎ ሜትሮችን በምትርቀው ፔትሮ ፖሊስ በደረሰው አደጋ በትንሹ ሰባት ሰዎች መሞታቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል። በአደጋው ለ16 ሰዓታት ያክል በጭቃ ተሸፍና ህይወቷን ማትረፍ የተቻለ የአራት ዓመት ታዳጊን ጨምሮ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ዝናቡን ተከትሎ ከተከሰተው የመሬት መንሸራተት ከ100 በላይ ሰዎችን ማዳናቸውም ተገልጿል። መቀመጫውን በሰሜን አሜሪካ ያደረገው ፒቢኤስ(public broadcasting service) እንደዘገበው ረዘም ላለ ሰዓት በጣለው ዝናብ ምክንያት በከተማዋ የመሬት መንሸራተትን ጨምሮ ቤቶችም ፈራርሰዋል። የከተማው ከንቲባ ክላውዲዮ ካስትሮ እንደገለጹት ካለፈው ሀሙስ ጀምሮ አደጋው ሊከሰት እንደሚችልና ነዋሪዎቹም እንዲጠነቀቁ መልዕክት ተላልፏል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለማዳን በአነፍናፊ ውሾች ጭምር በመታገዝ የነፍስ አድን ስራዎችን እያከናወኑ ሲሆን እስከ አሁን አንድ ሰው የደረሰበት እንዳልታወቀ ተገልጿል። የአየር ትንበያ ባለሙያዎች በፔትሮፖሊስ የተከሰተው ከባድ ዝናብ ኤስፒሪቶ ሳንቶ ወደተባለው አጉራባች ክልል ሊገባ እንደሚችልና አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል።
የቻይና- አፍሪካ የንግድ ልውውጥ ዕድገት
Mar 14, 2024 551
የቻይና አፍሪካ ግንኙነት ባለፉት አስርት አመታት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ በመምጣቱ ቻይና በአፍሪካ አህጉር በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በመሠረተ ልማት ዝርጋታ ዋነኛ ተዋናይ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ አድርጓታል። በቻይና እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት ከ47 ቢሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን የስፑትኒክ ዘገባ ያመለክታል። የንግድ ልውውጡ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ብቻ በ13.9 በመቶ ዕድገት አሳይቷል። ቻይና ወደ አፍሪካ የምትልከው ምርት በ21 በመቶ ማደጉን ያመለከተው ስፑትኒክ በአንፃሩ ቻይና ከአፍሪካ ሀገራት የምታስገባው ምርት መጠን በ4.5 በመቶ ዕድገት አሳይቷል። በፈረንጆቹ 2021 ይፋ የሆነው የቻይና አፍሪካ ትብብር ራዕይ 2035፤ "በአፍሪካ የተሰራ" የሚሉ ብራንዶችን በመፍጠር እና በማቋቋም ረገድ የአፍሪካ ምርቶች በዓለም ገቢያ ተመራጭ እንዲሆኑ ቻይና እየሠራች እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል። የቻይና አፍሪካ 2035 ራዕይ አፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን እንድታሳድግ እና ከአለም አቀፍ የኢንዱስትሪ እና የአቅርቦት ሰንሰለት ጋር እንድትተሳሰር ለማድረግ እቅድ እንዳለውም በዘገባው ተጠቁሟል። ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2023 መገባደጃ ላይ ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት የአፍሪካ ሀገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገሯ እንዲገቡ መፍቀዷን ያስታወሰው ዘገባው፤ ይህም የአፍሪካ ቻይና የንግድ ትስስርንና ትብብርን ከፍ እንዲል አድርጓል ብሏል። ከአፍሪካ ሀገራት ደቡብ አፍሪካ የቻይና ትልቁ የንግድ አጋር መሆኗን ያመለከተው ዘገባው፤ ናይጄሪያ፣ አንጎላ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንደቅደም ተከተላቸው የቻይና የንግድ አጋር መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።
በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በኢትዮጵያ
Mar 14, 2024 581
ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን የነዳጅ ፍጆታ ለመቀነስ እና የአየር ብክለትን ለመከላከል የሚደረገውን ሰፊ ጥረት እውን ለማድረግ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት በማዋል ከፍተኛ እምርታን አስመዝግባለች ይላል የአፍሪካ 24 ድረ ገጽ ዘገባ። በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ እየተዘዋወሩ የሚገኙት የኤሌክትሪክ ሚኒባሶች ድምጽ አልባና ለአካባቢው ተስማሚ መሆናቸውን ያተተው የአፍሪካ 24 ድረ ገጽ ዘገባ፤ ይህ የለውጥ ጅማሮ እየጨመረ በመጣው ፍላጎት እና በመንግስት ጠንካራ ድጋፍ የተገኘ መሆኑን አመልክቷል። መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በረጅም የጊዜ ማእቀፍ ውስጥ ከጎዳናዎች የማስወጣት እቅድ ነድፎ እየሰራበት በመሆኑ ምክንያት አሮጌዎቹን የነዳጅ ተሽከርካሪዎች ተክተው ለዜጎች ንጹህና ጤናማ አገልግሎት የሚሰጡት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከፍ ያሉ ማበረታቻዎች እየተደረገላቸው መሆኑንም ዘገባው አመልክቷል። ከእነዚህ ማበረታቻዎች መካከልም ለአካባቢ ጥበቃና ለጤና ምቹ ናቸው የተባሉት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ያለምንም ቀረጥ አሊያም በዝቅተኛ ቀረጥ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ወይም በከፊል ገብተው እንገጣጠሙ ማድረግ ተጠቃሽ ነው። እነዚህ ተሽከርካሪዎች ሃገር ውስጥ ገብተው መገጣጠማቸው ለኢትዮጵያውያን የእውቀትና የሙያ ሽግግር ከማድረጋቸው ባለፈ ለወጣት ክፍል የስራ እድሎችን እንደሚፈጥሩ ዘገባው አመልክቷል። በሃገር ውስጥ የተገጣጠሙት ተሽከርካሪዎች የዜጎችን እንቅስቃሴ ከማሳለጥ አኳያም ጉልህ አበርክቶ እንዳላቸውም ጠቁሟል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መስፋፋት ለነዳጅ ግዥ የሚወጣውን ከፍተኛ የሃገር ሃብት ለሌላ ልማት ለማዋልና ከአካባቢ ጥበቃና ከዜጎች ጤና ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግስት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት መሆኑን ያነሳው ዘገባው ተሽከርካሪዎቹ በስፋት ጥቅም ላይ ሲውሉ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻላቸውም ባሻገር ጤናማ የከተሞች ውስጥ እንቅስቀሴ በመፍጠር የአረንጓዴ አሻራ ትልሙን በማሳካት ያግዛሉ ብሏል።
ሐተታዎች
በህብር የተገነባ ገድል
Mar 25, 2024 240
"የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የትውልድ አሻራ ደምቆ የተፃፈበት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ይህ ቀን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የረባ ጥቅም ሳይሰጥ ወደ ጎረቤት አገራት ሲፈስ የኖረውን የአባይ ወንዝ ወደ ብርሃን ለመቀየር በቁርጠኝነት በመነሳት የማይቻልን ነገር በይቻላል ወኔ በመቀየር ለዓለም ያሳዩበት፤ ዓለም የተደመመበት ቀን ነው። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ወቅት በርካታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ታሳካው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አዘል ርእስ የያዘ ተከታታይ ዘገባ አስነብበዋል። ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተሰኘው ድረ ገጽ በፈረንጆቹ 2011 ‘Can Ethiopia Afford the Grand Renaissance Dam?’ በሚል ርእስ ባወጣው ሰፋ ያለ ዘገባ ግድቡን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሊያዋጡ የሚችሉት በጣም ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ግንባታው ሊሳካ አይችልም በሚል ትንበያውን አስቀምጦ ነበር። የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግሪን ፕሮፊት የተሰኘ ድረ ገጽ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ‘Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile River, but what kind of dam can they build without cash flow? ..... there’s one important problem: Ethiopia lacks the necessary funds to see the project to completion. In fact, they can barely get it off the ground.’ በማለት ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የሚያስችል ገንዘብ ስለሌላት ፕሮጀክቱ ሊተገበር አይችልም ሲል ደምድሟል፤ ተሳልቋልም። በወቅቱ የዚህ ዓይነት ግምት የብዙዎቹ ተንታኞች መንደርደሪያ ነበር። “ኢትዮጵያ ደሃ አገር ስለሆነች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር ካልተገኘ በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ፍፃሜ መድረስ አይችልም” የሚል ድምዳሜ ለመስጠት ተንታኞቹ ብዙም አይቸገሩም ነበር። ‘ግድቡ የጥራት ችግር ስላለበት ይደረመሳል’ ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ በግድቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ተደጋጋሚ የዛቻና የማስፈራሪያ መልእክቶች ተስተጋብተዋል። በጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም የቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብጽ ተጎጂ እንደሆነች አቋም በመያዝ "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው፤ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" የሚል ጠንከር ያለ የዛቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያውያን ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል ሲሉ የገለጹት ትራምፕ ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም ሲሉም አክለዋል። "ግብፅ የህዳሴ ግድብ እንዲገነባ መፍቀድ አልነበረባትም፤ የስምምነት ሀሳብ ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ገንዘብ አታገኝም " ብለዋል። አትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለመገንባትና ዳር ለማድረስ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ የተለያዩ ኃይሎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበር አገር ወይም ተቋም ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የነበረው አማራጭ አንድም ግድቡን አለመሥራት፣ አለበለዚያ ወጪውን በራስ አቅም መሸፈን ነበር፡፡ ከእነዚህ ከባድ ሁለት አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ወጪውን በራሱ አቅም በመሸፈን መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ኢትዮጵያውያን ገጠር ከተማ ሳይሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ከጫፍ እስከ ጫፍ በእልህና በቁጭት በመነሳሳት ግድቡን በራሳቸው አቅም ገንብተው ዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ያደረጉት። ለግንባታው የሚውል ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት በተለይም የቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር መልእክት እና በእጣ አገልግሎት ህዝቡ ተረባረበ፤ የማይቻለውን እንደሚቻል ለዓለም አሳየ። በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎችን ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው 99 በመቶ መድረሱንና የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በቅርብ ያወጣቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል የህዳሴው ግድብ ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" በማለት አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ቢኖሩባትም የግድቡን ሥራ ለአፍታም አላቋረጠችም። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ይከበራል፤ መሪ ሀሳቡም "በኅብረት ችለናል!" የሚል ሲሆን ኢትዮጰያውያን ችለው ያሳዩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። እዚህ ድል ላይ የተደረሰው በመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነው። ባለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ተሳትፎ ተጀምሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሊጠናቀቅ ወራቶች የቀሩት ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለጎረቤት አገራት ተደራሽ በማድረግ ቀጣናውን በማስተሳሰር በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው።
በከፍታ የታጀበ ስኬት
Mar 15, 2024 514
ለህጻናትና ታዳጊዎች መልካም ስብእና የሚያግዙ ጽሁፎችን ያዘጋጀችው ኤሪን ሶዴርበርግ ዶውኒንግ 'JUST KEEP WALKING' በሚለው መጽሃፏ ባደራጀችው ገጸባህሪ አማካይነት “አንተ መልካምና ስኬታማ ሆነህ ሳለ ጥቂት ሰዎች ስለአንተ መጥፎነት አብዝተው መጨነቅና ማውራት ከጀመሩ የምትሄድበት መንገድም ሆነ አካሄድህ ትክክል ነውና መራመድህን አታቁም። ብዙሃኑ የስኬትህ ተካፋይና የስኬትህ አጋር ስለሆኑ የጥቂቶቹን ጫጫታ ከምንም ካለመቁጠር ተራመድ ብዙ አፍራሽ ወሬዎች ያንተን ስኬት የመመስከር አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑን አትዘንጋ። መቆም የሽንፈት ምልክት ነውና” ትለናለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት 78 ዓመታት በከፍታ የዘለቀ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምና ዝናው የገነነ ተቋም ነው። አየር መንገዱ ታህሳስ 21 ቀን 1938 ዓ.ም ተመስርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ በረራውን መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ካይሮ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዘመኑ በአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅና አሰራሮችን በማዘመን ራሱን እያደራጀ የኢትዮጵያ ኩራት ከመሆን አልፎ የአፍሪካ ምልክት ሆኖ ዘልቋል። ዛሬ ላይ የ152 ዘመናዊ አውሮፕላኖች ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በምስረታው ወቅት ከአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል የተገዙና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ያገለገሉ አምስት አውሮፕላኖች ብቻ እንደነበሩት መረጃዎች ያመለክታሉ። በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ22 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን እንደሚያስተናግድ የሚነገርለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞችን ፍላጎትና ምቾት ለመጠበቅ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ጨምሮ 31 አውሮፕላኖች ለመግዛት ከአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል። እነዚህን ተጨማሪ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ቁጥር ጨምሮ የሚገነባቸው ዘመናዊ አየር መንገዶች ሲደመሩ በአፍሪካ ግዙፍ ተቋምነቱን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ያደርገዋል። የበረራ አድማሱን በየጊዜው እያሰፋ የሚገኘው አየር መንገዱ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ 134 መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን በሀገር ውስጥ ወደ 22 መዳረሻዎች ይበራል። ከዚህ ውስጥ 60 የበረራ መዳረሻዎቹ አፍሪካ ውስጥ ነው። አየር መንገዱ ከ55 ሚሊየን ዶላር በላይ አስገንብቶ ወደ ስራ ያስገባው ዘመናዊ የካርጎ ማእከል ከምስራቅ አፍሪካ ብሎም ከአፍሪካ ከፍተኛ ተብሎ ተመዝግቦለታል። በ15 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታው ያረፈው የካርጎ ማዕከል ለኤሌክትሮኒክስ ግብይት (ኢ ኮሜርስ) አገልግሎት የሚውል ሲሆን የካርጎ አገልግሎት እየሰፋ መምጣት አየር መንገዱ የሚሰራቸው ተያያዝ በርካታ ተግባራት መስፋት፣እንዲሁም የዲጂታል ግብይት ተመራጭ መሆን ለማእከሉ ግንባታ ምክንያት ተብለው ተጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ መስክ ከሚታወቅባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ሴቶችን በማብቃትና የጾታ እኩልነትን በማስተግበር ረገድ አርአያነት ያለው ተግባር መፈጸሙ ነው። በየዓመቱ የሚታሰበው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ማርች 8 በሚከበርበት ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት በርካታ አመታት ወደ ተለያዩ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሙሉ ለሙሉ በሴቶች ብቻ የተመራ በረራን በማደረግ ዓለም አቀፍ ዝናን አትርፏል። አየር መንገዱ ዘንድሮ ለ9ኛ ጊዜ "ሴቶችን በማብቃት አፍሪካን ማስተሳሰር" በሚል መሪ ቃል ከአዲስ አበባ ወደ ለንደን በሴቶች ብቻ የተመራ የተሳካ በረራ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞች በሚሰጠው ዘመኑን የዋጀና ቀልጣፋ አገልግሎት በየጊዜው የተለያዩ ሽልማቶች ባለቤት መሆን የቻለ ተቋም ነው። ለአብነት የቅርብ ጊዜያቶችን ለማንሳት ያህል ባሳለፍነው ዓመት በአየርላንዷ ደብሊን በተዘጋጀ መርሐ-ግብር ላይ በዓመታዊው የ“አፔክስ” የመንገደኞች ምርጫ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ሽልማትን አሸንፏል፡፡ በተመሳሳይ ዓለም አቀፍ የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ ጉባኤ "ኤር ካርጎ ኤሮፕ" እ.አ.አ በ2021 ባካሄደው የበይነ መረብ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካርጎና የሎጅስቲክ አገልግሎት የ2021 የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ የደንበኞች እንክብካቤ ዘርፍ ሽልማት አግኝቷል። በአውሮፓውያኑ 2024 ዓመታዊውን የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማት ላይ “የኮርፖሬት የዘላቂነት ስኬት ሽልማት” አሸናፊ ሆኗል። አየር መንገዱ በትላልቅ ስኬቶች የማለፉን ያህል ከባድ ፈተናዎችንም ተጋፍጦ በጽናትና በስኬት አልፏል። መላውን ዓለም ያዳረሰው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አንዱ ማሳያ ነው። በዚያን ጊዜ የመንገደኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ምክንያት በዓለም ደረጃ በርካታ አየር መንገዶች በረራ በማቋረጥ ችግር ውስጥ ወድቀዋል። በዚህ ፈታኝ ወቅት አየር መንገዱ የስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ አንዳንድ የመንገደኞች አውሮፕላኖቹን ወደ ዕቃ ጫኝ በመቀየር ጭምር ትኩረቱን ጭነት ማጓጓዝ ላይ አድርጓል። በዚያን ፈታኝ ወቅት አየር መንገዱ የቀየሰውን ስትራቴጂ በመቃወም ከውስጥም ከውጭም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ትችትን አስተናግዷል። ይሁን እንጂ አየር መንገዱ ፈተናውን በመቋቋም እንደሌሎቹ ሀገራት አውሮፕላኖች በረራ የማቋረጥ እጣ ሳይገጥመው በታላቅ ብልሃት ማለፍ የቻለ ተቋም መሆኑ ተመስክሮለታል። በዚህም በካርጎ አገልግሎት ገቢ ከማገኘቱም ባሻገር ክትባትን ለዓለም በማዳረስ ወረርሽኙ ለመግታት በተደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ የራሱን አሻራ አኑሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የራሱ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ሲኖረው የግል አብራሪ እና የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ በመስጠት የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ዜጎችን በማሰልጠን ከአራት አስርተ ዓመታ በላይ ልምድ አካብቷል። አየር መንገዱ በሚያስተዳድረው ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የበረራ ባለሙያዎችን በቅርቡ ያስመረቀ ሲሆን ምሩቃኑ ከታንዛንያ ከደቡብ ሱዳን ከኒጀር ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከቶጎ እና ከማዳጋስካር መሆናቸው ደግሞ የአየር መንገዱን የፓንአፍሪካኒስት መንፈስ አጉልቶ ያሳየ አድርጎታል። ስኬቶቹ በዚህ ያላበቁት አየር መንገዱ የእድገት ግስጋሴውን እንደቀጠለ ይገኛል። ከሰሞኑ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነ-ስርዓት ላይ ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል። በዚህ ወቅት ከተሸለሙት ተቋማት መካከል አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሆን ሽልማቱ ለወደፊትም ለላቀ ስኬት የሚያዘጋጀው እንደሆነ ይታመናል።
አድዋን የዘከሩ ስንኞች
Feb 29, 2024 914
የታሪክ ድርሳናት የአድዋ ድልን በተለያየ መንገድ ዘክረውታል። ምሁራንም አንድምታውን በየዐውዱ ዘርዝረዋል። በዚህም ለሰው ልጆች በተለይም ለጥቁሮች አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እንደሆነ ደምድመዋል። በርግጥም የአድዋ ድል ታሪክም፣ ትርክትም የለወጠ ትልቅ ሁነት ነው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ምዕራባዊያን 'አቢሲኒያ' በሚሏት ጥንታዊት አፍሪቃዊት ምድር የነበረው ክስተት ቀለምና ዘር ቀመስ በሆኑ በሰው ልጆች መካከል ድል መንሳትና መነሳት፣ ተስፋ እና ቀቢፀ ተስፋ፣ ሀሜትና ሀሞት፣ ብስራትና መርዶ... እያፈራረቀ አበሰረ። ለሀገሬው ዘመን-አይሽሬ አሻራ አነበረ። ውርስም ቅርስም ሆነ!! ይህ ክስተት በታሪኩ ልክ በኪነ ጥበብ ተዘክሯል ባይባልም ቅሉ በጥበብ ፈርጁ ተወስቷል። የኪነ-ጥበብ ሰዎች በየመክሊቶቻቸው ድሉን ለመዘከር ጥረዋል። ሙዚቀኞች በዜማዎቻቸው፣ የሲኒማ ሰዎች እና ፀሐፈ ተውኔቶች በተውኔታቸው፣ ሊቃውንት በቅኔዎቻቸው አድዋን ዘክረዋል። ዕውቅ ገጣሚያን ደግሞ ቃላት እያዋደዱ፣ በዘይቤና ዘመን እያዋሃዱ፣ ምዕናብና ገሀድ እያዛነቁ፣ ታሪክና ትዝብት እያሰባረቁ ... አድዋን በግሩም ስንኞቻቸው ከትበውታል። በአድዋ ድል ምርጥ ግጥሞች መካከል "ጥቂት ስንኞች" እየመዘዝን በወፍ በረር ቅኝት እንመልከት። ባለቅኔው ፀጋዬ ገብረመድህን በ‘እሳት ወይ አበባ’ ግጥም መድብሉ አድዋን መልክዓ ምድራዊና ሃሳባዊ ወሰኗን አድማስ ተሻጋሪ፣ ሰማይ ታካኪ፣ ታሪካዊ ስፍራዋ የአጽም ርስትና የደም ትቢያ የተሸበለለባት መቀነት አድርጎ መስሏታል። በዚህች ታሪካዊ ስፍራ በተከፈለው መስዋዕትነት ከባርነትና ነጻነት ስርየትን ሲያጎናጽፍ፣ የኩራት ቅርስ መሆኗንም ሰፊውን ታሪክ በጥቂት ስንኞች እንዲህ ቋጥሯል። ".... አድዋ ሩቅዋ፣ የዓለት ምሰሶ የአድማስ ጥግዋ፣ ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ... ዓድዋ የዘር አፅመ ርስትዋ- የደም ትቢያ መቀነትዋ ከሞት ከባርነት ሥርየት- በደም ለነጻነት ስለት አበው የተሰውብሽ እ’ለት የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ- የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ..." ገጣሚው አለፍ ሲልም በጦርነቱ የዋሉ መሳሪያዎችን፣ የጦር መሪዎችን እጅና ጓንትነት በፈረስ ስሞቻቸው በመቋጠር /ለአብነትም የዳግማዊ ምኒልክ፣ የራስ መኮንን፣ የደጃች ባልቻ ሳፎ፣ የፊታውራሪ ገበየሁና ሌሎችም/ ኢትዮጵያዊያንን ጀግንነትና ወኔ በአጭሩ ቋጥሮታል። ...ድው-እልም ሲል ጋሻዋ- ሲያስተጋባ ከበሮዋ፣ ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ፣ ያባ መቻል ያባ ዳኘው፤ ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው፣ ያባ ጎራው፣ ያባ በለው በለው ሲለው..." በሚል። ደራሲና ጋዜጠኛ ነብይ መኮነን ‘ስውር ስፌት’ በተሰኘ የግጥም መድብሉ የአድዋን ድል ሲያመሰጥረው አድዋን ‘በደም ግብርነት’ ይገልጸዋል፤ ታሪኩንም ላጥፋህ ቢሉት የማይጠፋ ሕያው ቀንዲል አድርጎታል። “አድዋ የደም ግብር ነው፤ አበው የለኮሱት ቀንዲል፣ አድዋ የአፍሪካ ዱካ ነው፤ አበሽ የከተበው ፊደል፣ ላጥፋህ ቢሉት መች ይጠፋል፤ ጠላት በልቶ ያፈራ ተክል፣ ለዛሬም ታሪክ ነው፣ ‘ነገም ሌላ ቀን ነው’ ለሚል...” የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ ምሁር ሰይፉ መታፈሪያ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) “የተስፋ እግር ብረት” መጽሐፍ “የድል በዓል ማለዳ” በሚል ርዕስ የአድዋን ድባብ ከማለዳው ምናባዊ ትዕይንት ጀምሮ ይቃኛል። ገጣሚው የሰንደቁን መውለብለብ፣ የሕብረ ቀለሙን ድምቀት ከልክ በላይ ውስጥን ኮርኩሮ የሚያስፈግግ ሐሴት እንዳለው በዘይቤያዊ ቃላት ገልፆታል። ገጣሚው በቅኔው የሠራዊቱን ቆራጥነት፣ በወኔ በደም ሲቅላላ፣ የመድፍ አረር ሲያፋጭ ይስለዋል። በስሜት ስካር አድዋ ደፍርሶ በስዕለ ህሊናው የነበረውን የጦርነቱ ማለዳዊ ድባብም እንዲህ ያብራራዋል። ዐይነ-ልቦናዬ ዐጽም ያያል፤ የድል ሜዳውን ይቃኛል። ባድዋ ድል በዓሉ ማለዳ፤ የበዓል መድፍ ሲንዱዋዱዋ (ዱዋ ዱዋ ዱዋ ዱዋ!) ከሞት እንቅልፍ ተቀስቅሶ፤ ያ-ዐጽም ዙርያውን ደባብሶ ጉሮሮውን ጠረገ፣ እህህህህ! እህህህህ!... እያለ ይቀጥላል። በአድዋ ኮረብታማ ተራሮች የተኙ ጀግኖችን በሕይወት ተኝተው የሚያንኮራፉ አስመስሎም አቅርቧቸዋል። ...ድንጋይ ተንተርሶ፤ አፈር ቅጠሉን ለብሶ፣ ከዚያን ያንኮራፋል፤ እንደዚሁም በቅብልብል የወደቀበቱ ሜዳው፣ ተረተሩ፤ ቀን የማይለውጠው ምስክሩ የዚያ ጀግና፣ የዚያ ኩሩ። ገጣሚ አበረ አያሌው “ፍርድና ዕርድ” በተሰኘው የግጥም ስብስቡ ባሰፈራቸው ስንኞች ‘ነገረ አድዋ’ን ከመንደር ወደ አገር፣ ከአገር ወደ አህጉር በመጨረሻም ከአህጉር አተልቆ ‘ዓለም’ ያደርገዋል፤ አድዋን የአፍሪካ ብርሀን ፈንጣቂ፤ ለእብሪተኞች ደግሞ የትካዜና ቅስም መስበሪያ ምስጢር አድርጓታል። በተለይም ኢትዮጵያ ለገጠማት አሁናዊ የዘር ፖለቲካ አዙሪት አድዋን ለሚያሳንሱ ወገኖች በቅኔው ምላሽ ይሰጣል። "...እነ ምኒልክ ጦር ይዘው ከመድፍ የተዋደቁ ጎራዴ መዘው የሮጡ በጠብ-መንጃ አፍ ያለቁ ለጓጉለት ነጻነት -ደማቸውን ያፈሰሱ ለሰፈር ብቻ አይደለም- የአህጉር ድል አታሳንሱ። ... ዓድዋ ሰፈር አይደለም - ዓድዋ መንደር አይደለም እሱ ዓለም ናት ዓድዋ ቤቱ - ሃገር ናት የድል ትራሱ ለጠበበ የዘር ቅኔ - የደም ድል አታሳንሱ!..." በማለት ገልጾታል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ምሁሩ ተሻገር ሽፈራው (ዶ/ር) ‘የነፍስ ርችቶች’ በተሰኘ የግጥም ስብስብ መፅሃፉ ከቋጠራቸው ስንኞች መካከል በአድዋ 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል የግጥም ውድድር ያሸነፈበትን ረጅምና ድንቅ ግጥም አካቷል። የዶክተር ተሻገር ግጥም አንጓ እና ስንኞች የአድዋን ምጡቅነት፣ ዝና፣ ነቅዓ ፍትሕ፣ ውበትና ቅኔ በውብ ቃላት ገልጠውታል። "... ዓድዋ አንቺ የዝና አጽናፍ ሕዝቦች እፍ ያሉብሽ ቁጣ - የነበልባል እቶን ጫፍ እጹብ ክስተት፤ ደቂቅ ረቂቅ፤ ምጡቅ ጠሊቅ ኬላ ድንበር፣ አድማስ ሰበር፣ የቅርብ ሩቅ ለትንግርትሽ ብቻ መጥኔ ትንግርት እውነት፣ ታምር ሁነት፣ የብርቅ ብርቅ፣ የድንቅ ድንቅ ለሰጠሽው ፍትህ መጠን - ለፍርድሽ ሚዛን ብያኔ ለንግስትሽ ሥነ ውበት - ለታሪክሽ ምስጢር ቅኔ…" ገጣሚው "... በምን ቀሰም፣ በምን ቀለም - በምን ብዕራና ሊከትበው..." ሲል የአፍሪካዊያን ሁሉን አቀፍ ድል ለመግለጽ የቀለም፣ የአንደበትና የብራና ወኔ እንዳጣባት ይናገራል። በመጨረሻም ይህችን የድል ቁንጮ የማትሞቺ ህያው ጀንበር ሁልጊዜም ተዘመሪ፤ ተወደሽ" ይላታል። "… እና ዓድዋ አንቺ በኩር የድል መኸር የቅኝ ግዛት ቀንበር ሰንሰለቱ እንዲሰበር ተጠቂዎች አጥናፍ አጥናፍ የመረጡሽ የትግል ዘር ህይወት ከፍለው እልፍ - ያርጉሽ የመረጡሽ ከአገር አገር የማታልፊ የማትከስሚ - የማትሞቺ ህያው ጀንበር ሰብዓዊ ድል ነሽና - ስምሽ ይወደስ ይዘመር…" (በአየለ ያረጋል)
ከተሜው ገበሬ - ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ
Feb 20, 2024 1292
የከተማ ግብርና ሥራ ኢኮኖሚን ከመደገፍ ባለፈ ጤናማ ማህበረሰብ እንዲፈጠር አበርክቶው የጎላ ነው። አዲስ አበባ በመኖሪያ እና በተቋማት ቅጥር ግቢዎች የጓሮ አትክልት፣ ፍራፍሬና መሰል የግብርና ልማት ስራዎች እየተስፋፉባቸው ከመጡ ከተሞች መካከል አንዷ ናት። በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች በግቢያቸው በሚያለሟቸው አትክልትና ፍራፍሬዎች ራሳቸውን ከመመገብ ባለፈ ለሌሎች መትረፍ ችለዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እህት ኩባንያ የሆነው ኮሜርሻል ኖሚኒስ ዳይሬክተር ጄኔራል የሆኑት ኮማንደር ጥላሁን ጸጋዬ በከተማ ግብርና አርአያ የሆነ ስራ እያከናወኑ ይገኛሉ። በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ ተወልደው ያደጉት ኮማንደር ጥላሁን የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ በማምረት ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ የገቢ ምንጭም ሆኗቸዋል። የከተማ ግብርና ስራን ከቤተሰቦቻቸው መውረሳቸውን ያስታወሱት ኮማንደር ጥላሁን የከተማ ግብርና የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም ከማገዙ ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እድል እንደሚፈጥር ይገልጻሉ። ከመደበኛ ሥራቸው ጎን ለጎን እንደ ጥቅል ጎመን፣ ቆስጣ፣ ሰላጣ፣ አፕል፣ ሙዝ፣ ቡና፣ ማር፤ ዘይቱን እና ሌሎች ተክሎችን በጓሯቸው በማምረት ለቤተሰቦቻቸው ፍጆታ እየተጠቀሙ ይገኛሉ። ከዚህም ባለፈ ቡና፣ ሸንኮራ፣ ማር በማምረት ከራስ ፍጆታ አልፎ ለሌሎችም መትረፍ መቻላቸውን ይናገራሉ። በተለይም በከተማ ግብርና ለመሰማራት ወሳኙ ሰፊ ወይም ጠባብ ቦታ መኖር ሳይሆን ያለውን ሃብት በአግባቡ በመጠቀም በፍላጎት መስራት መሆኑን ያነሳሉ። በዶሮ እርባታም በስፋት ለመሰማራት እየሰሩ ሲሆን በዚህም ከራሳቸው ፍጆታ አልፈው ቢያንስ ለአካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እንቁላል ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል። አሁን ላይ በመንግስት እየተተገበረ ያለው የከተማ ግብርና ከድህነት ለማምለጥ ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም በተለይም ስራውን ይበልጥ በማስፋት ከራሳቸው አልፈው ምርቶቻቸውን ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። ማንም ሰው ምንም አይነት ስራ ለመስራት በመጀመሪያ ደረጃ ፍላጎት ሊኖረው እንደሚገባ የገለጹት ኮማንደር ጥላሁን፤ በፍላጎት ወደ ስራ ከተገባ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ተናግረዋል። ሁሉም የቤተሰቡ አባላት አትክልትና ፍራፍሬዎችን በመንከባከብ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ለውጤታማነታቸው መሰረት መሆኑን ገልጸው አንድን ነገር ለማሳካት በቤተሰብ ውስጥ የሀሳብ መግባባትና መተባበር ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።
ትንታኔዎች
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 943
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ) የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች
Mar 2, 2024 1066
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች። የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው። የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡ መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ። የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል። ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 948
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።
በአጭር ጊዜ ትልቅ እመርታ በሌማት ትሩፋት
Feb 6, 2024 1772
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የምግብ ዋስትናን ለማረጋጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን የተመለከቱ ጥያቄዎች ይጠቀሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ በግብርና ልማት በተለይም በስንዴ ላይ እየተሰራ ያለው ስራ በምግብ እራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ እንዳለው አብራርተዋል። በግብርና ልማት እየተከናወኑ ባሉ ውጤታማ ስራዎች ላይ የሌማት ትሩፋት ተግባራት ሲታከሉ ከምግብ ዋስትና ባለፈ ስርአተ ምግብን በማስተካከል ረገድ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ለመሆኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ስርአተ ምግብን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚኖረው ፋይዳ እንዴት ይታያል? በእስካሁኑ አካሄድስ ምን ውጤቶች ተገኙ? ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ ‘የሌማት ትሩፋት’ መርሃ ግብርን ካስጀመሩ በኋላ በመህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሌማት አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑን ገልጸው ነበር። በወቅቱ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በቂ እና አመርቂ ምግብ ማግኘት መሆኑን ገልጸው በቂ የመጠን፣ አመርቂ የይዘት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። አክለውም በምግብ ራስን መቻል ከሀገር ሉዓላዊነትና ክብር ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ገልጸዋል። የሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር ዓላማ የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥና ክብርን ማስጠበቅ ሲሆን በተለይም ስጋ፣ እንቁላል፣ ማር እና ወተት ትርፍ ምርት ሆነው እንዲገኙ ማልማትና መጠቀምን መሰረት ያደረገ ነው። መርኃ-ግብሩ የኢትዮጵያን ደካማ የአምራችነት ታሪክ በመቀየር የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የኢኮኖሚ እድገትን የማፋጠን ግብ የሰነቀ መሆኑ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሌማት ትሩፋት ዘመቻው በቤተሰብ፣ ብሎም በሀገር ደረጃ በምግብ ራሳችንን ለመቻል የምናደርገውን ጥረት የሚያፋጥን ነው ብለዋል። የወተት፣ የዶሮ፣ የዕንቁላል፣ የማር፣ የዓሣ እና የሥጋ ምርቶችን ለማሻሻል ሀገራዊ የመንግሥት ፕሮግራም ሆኖ ከጥቅምት 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት በብዙ መልኩ ውጤት እያስገኘ ነው። በእርግጥም የሌማት ትሩፋት በአንድ ዓመት ጉዞው በተለይ በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና ስጋ ምርት መጠን አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑ የተረጋገጠበት ውጤት ተመዝግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በ2015 ዓ.ም፣ የወተት፣ የዶሮ እና የሥጋ ምርት መጠን በዕቅዱ መሠረት ጥሩ ውጤት ማምጣቱንና በተያዘው ዓመትም በበለጠ ለማሳካት የሁሉም ጥረት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሣ ሃብት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጽጌረዳ ፍቃዱ በሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በማር፣ በወተትና በዶሮ ልማት ከ20 ሺህ በላይ መንደሮችን በመለየት ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ለኢዜአ ገልጸዋል። ለአብነትም በወተት ልማት በተሰሩ ስራዎች 6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ሊትር የነበረውን የማምረት አቅም ወደ 8 ነጥብ 6 በሊዮን ሊትር ከፍ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በመጪዎቹ ዓመታትም ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ሊትር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በእንቁላል ምርት ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቅሰው የጫጩቶች ስርጭት ከነበረበት 26 ሚሊዮን ወደ 42 ሚሊዮን ማደጉን ተናግረዋል። የሌማት ትሩፋት መርኃ- ግብር የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን የሚናገሩት የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሣ ሃብት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጽጌረዳ ፍቃዱ በእንስሳት ሃብት ልማት ብቻ በዓመት ለ259 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም ለዘርፉ ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት አመርቂ ውጤት ሳያገኝ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ዘርፉ በቅንጅት ከተመራ፣ በቴክኖሎጂ ከታገዘ የምግብ አማራጭን ማብዛት ይቻላል። ወተት፣ ማር፣ ስጋ እና እንቁላል መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በገበያ ላይ ማትረፍረፍ፣ የሌማቱ በረከት ማብዛት የሚለው የብዙሃኑ እምነት ነው። የምግብ ዋስትና ጉዳይ ከተመጣጠነ ምግብ ጋር ያለው ቁርኝት የማይነጣጠል በመሆኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ፋይዳው ብዙ ነው። በሌማት ትሩፋት ገበታን በተመጣጠነ ምግብ መሙላት ከተቻለ የእናቶችንና የህጻናትን ፍላጎት በማሟላት በአካል የዳበረና በአዕምሮ የበለጸገ ትውልድ መገንባት ይቻላል። በተቃራኒው ያልተመጣጠነ አመጋገብ ጤና ላይ ከሚፈጥረው ችግር ባለፈ በሰዎች መካከል ያለውን የኑሮ አለመመጣጠን በማስፋት፣ ማህበራዊ ቀውስን በመፈልፈልና ኢኮኖሚውን በመጉዳት ምርትና ምርታማነትን ወደ ኋላ የሚጎትት ይሆናል። ይህ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት በከባድ ትግል ላይ የሚገኙ ሀገራትን የልማት ግስጋሴ በመግታት ቀድሞ ወደነበሩበት የድህነት አረንቋ እንዲመለሱ ያደርጋቸዋል። በኢትዮጵያ ከሚገኙና እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ከሆኑ ህፃናት ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት በዕድሜያቸው ልክ ዕድገት የማያስመዘግቡ ወይም የመቀንጨር ችግር ያለባቸው መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ። ለዚህ ነው በምግብ ራስን ከመቻል ጎን ለጎን የተመጣጠነ ምግብን ተደራሽ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ የሚሆነው። በዚህ ረገድ የሌማት ትሩፋት እየተጫወተ ያለው ሚና ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም። የተለያዩ ምግቦችን በገበታ ላይ ማካተት የሚያስችል ስልጠናን ከተግባራዊ የልማት ስራዎች ጋር ያካተተ ሲሆን አዲስ የአመጋገብ ባህልን የሚያለማምድ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ለተሰሩ ስራዎችና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላሳዩት የአመራር ቁርጠኝነት በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል። ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት፣ ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት የተበረከተ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ረሀብን ዜሮ ለማድረስ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ብቻ ሳይሆን የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ ብልጽግናን እውን እንደምታደርግ ገልጸዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተሰሩት ስራዎች ለመጪው ትውልድ ጥሩ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያን ለአብነት አንስተዋል። የምግብ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ጉዟችንን በፅናት እናስቀጥላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና ስራችን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የተመጣጠነ ምግብን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል። የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን ያስከበረች ነጻ አገር እውን ማድረግን ያለመ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አመራሩ ይህንን ተገንዝቦ እንዲሰራ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ህልም የሚመስሉ በርካታ አገራዊ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ የቻለችው በዜጎቿ የተባበረ ክንድ መሆኑ እሙን ነው። ከዚህ አኳያ በምግብ ራስን ከመቻል በላይ የኢትዮጵያን የአምራችነት ታሪክ የመቀየር ግብ ለሰነቀው የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ስኬታማነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር መስራት ይጠበቃል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 8496
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 13584
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት። እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 6893
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል። “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 7872
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
መጣጥፍ
በድላችን ሐውልት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት የተቀረጸላቸው የካራማራው ዘማች አቶ በቀለ ገመቹ
Mar 5, 2024 902
አቶ በቀለ ገመቹ ወይም በቅፅል ስማቸው አሚኮ ይባላሉ፤ በሙያቸው ኤሌክትሪሺያን ናቸው። በ1969 ዓ.ም በዚያድባሬ የሚመራው የሶማሊያ አገዛዝ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሀገር ስትደፈር ቁጭት ተሰምቷቸው ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸውን ይናገራሉ። ጦር ሜዳ ከመዝመታቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመሆናቸው "በራ በራ የድል ጮራ" የተሰኘውን ዓርማ በመቅረጽ በ14ቱ ክፍላተ ሀገር እንዲበራ ማድረጋቸውንም ያነሳሉ። በዚህም ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ከኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ መሸለማችውን ያወሳሉ። ታንክ ማራኪው አሊ በርኬ ጓደኛቸው እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ በቀለ፤ በተለያዩ ዐውደ ግንባሮች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። አቶ በቀለ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚገኘው የድላችን ሐውልት ላይ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት ተቀርጾላቸዋል። ሐውልት እንዲቀረጽ የተደረገበት ፎቶግራፍ በያኔው ሶስተኛው አንበሳው ክፍለ ጦር በኋለኛው ምሰራቅ ዕዝ በር ላይ በቀኝ እጃቸው መሳሪያ ከፍ አድርገው ይዘው የተነሱት ፎቶ ግራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። ከእርሳቸው ጎንም መንበረ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊ ዘማችና መትረጊስ ተኳሽ ሴት ባደረገችው አስተዋፅኦና በደረሰባት አካል ጉዳት ሐውልት እንደተቀረጸላት ያነሳሉ። የካራማራ ድል ታላቅ ድል ነው የሚሉት አቶ በቀለ ገመቹ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለውበት የተገኘና ሀገርን ያስከበረ መሆኑንም ይገልጻሉ። የካራማራ ዘማቹ አቶ በቀለ ገመቹ አሁናዊ ኑሯቸው ችግር ላይ እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ወረራ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል አደረገ፤ የኢትዮጵያ አሸናፊነትም በአደባባይ ታወጀ። ድሉ በየዓመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮም 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።
የአፍሪካ ዋንጫን በመሀል ዳኝነት የመራችው ብቸኛዋ ሴት ዳኛ
Jan 28, 2024 1990
በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ፡- በእግር ኳስ ውድድሮች የመሃል ዳኝነቱን ቦታ በብዛት የሚይዙት ወንዶች ሲሆኑ፤ አሁን ላይ አልፎ አልፎ ሴቶች ትልልቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ሲዳኙ አስተውለናል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተከናወነው 22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ፤ ፈረንሳዊቷ ስቴፋኒ ፍራፓርት፤ ኮስታሪካ እና ጀርመን ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኛነት መርታለች። በዚህም በወንዶች ዓለም ዋንጫ ታሪክ በመሀል ዳኝነት የእግር ኳስ ጨዋታን የመራች የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች ። ዘንድሮ ደግሞ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሞሮኳዊቷ ቦችራ ካርቡቢ፤ ውድድሩን እንዲመሩ ከተመረጡት 32 የመሀል ዳኞች መካከል ብቸኛዋ ሴት ናት። በዚህም በውድድሩ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ፤ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ ታሪክ ጽፋለች። የሞሮኮ ዓለም አቀፍ ማኅበር የእግር ኳስ ዳኛ የሆነችው ቦችራ ካርቡቢ፤ በወንዶችም ሆነ በሴቶች አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በርካታ የመጨረሻ ምዕራፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ዳኝታለች። 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ብቸኛ የሴት ዳኛ ሆና የመራችው ቦችራ ካርቡቢ ማናት? ቦችራ ካርቡቢ በሞሮኮ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው "ታዛ" ከተማ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1987 ተወለደች። የዘር ግንዷ በሰሜን ምሥራቅ ሞሮኮ ከሚገኙት ሪፊያን ከሚባሉት የበርበር ጎሳ ዝርያ ካላቸው ሕዝቦች የሚመዘዝ ሲሆን፤ ለቤተሰቦቿ አምስተኛና የመጨረሻ ልጅ ነች። ገና በልጅነቷ ለእግር ኳስ ፍቅር ያደረባት ቦችራ ካርቡቢ፤ ኳስ መጫወት የጀመረችው በአንድ ትንሽ የወጣቶች ቡድን ውስጥ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2001 በተወለደችበት ከተማ "ታዛ"፤ ለወንዶችና ለሴቶች የእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ተከፈተ ። ይኼ ትምህርት ቤት ቀልቧን የሳበው ቦችራ፤ ሥልጠናውን መውሰድ ጀመረች። "እግር ኳስን እወዳለሁ፤ ራሴንም ላስተምር ፈለኩ።ለምን አላደርገውም ብዬ ፍላጎቴን በመከተል የእግር ኳስ ጨዋታን ደንብ መማር ጀመርኩ" ስትል የእግር ኳስ ዳኝነት ትምህርት የጀመረችበትን ጊዜ ታስታውሳለች። ይኼ ድርጊቷ ካልተዋጠላቸውና፤ በበጎ ጎኑ ካልተመለከቱት ውስጥ ደግሞ፤ ወንድሞቿ ቀዳሚዎች ነበሩ። "በምኖርበት ከተማ አንድ ሴት አጭር ቁምጣ ለብሳ ከወንዶች ጋር ሥልጠና ስትወስድ መታየቷ፤ እንደ አሳፋሪ ድርጊት ስለሚታይ መነጋገሪያ ሆኜ ነበር" ትላለች። የቦችራ ካርቡቢ የዳኝነት ጉዞ እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በ2007፤ ሞሮኮ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒዮናን ጀመረች። ይህ መሆኑ ቡችራ ካርቡቢ ብሔራዊ ዳኛ እንድትሆን ዕድል የፈጠረላት ሲሆን፤ መኖሪያዋንም ከትውልድ ሥፍራዋ "ታዛ" ወደ ሞሮኮ ሌላኛዋ ከተማ "ሚከንስ" እንድትቀይር አደረጋት። "ይህን ዕድል ማግኘቴ ቤተሰቦቼ እንዲረዱኝና ሙያዊ ለሆነ ጉዳይ እንደምሄድ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል" በማለት የዳኝነት ሙያዋን በመጨረሻ እንደተቀበሉት ታስረዳለች። በሚከንስ ከተማ በእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና ላይ እያለች፤ አንድ ቀን አባቷ መጥቶ እንደተመለከታትና፤ ወንድሞቿ ምርጫዋን ሊያከብሩላት እንደሚገባ እንደነገራቸውም ገልፃለች። የ19 ዓመት ወጣት እያለችም፤ በሞሮኮ የሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ የሊግ ውድድር በመዳኘት፤ የዳኝነት ሥራዋን አንድ ብላ ጀመረች። ይህ ከሆነ ከ10 ዓመት በኋላ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ በመሆን ራሷን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረች። ከሁለት ዓመት በኋላም በ2018 በጋና አስተናጋጅነት በተከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ፤ በዛምቢያና በኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት አጫወተች። ይህም በአህጉራዊ የውድድር መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀል ዳኝነት ያጫወተችው ጨዋታ ሆኖ ተመዘገበላት። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020፤ "ቦቶላ" እየተባለ በሚጠራው በሞሮኮ የወንዶች ከፍተኛ የሊግ ውድድር ላይ በመሀል ዳኝነት በመዳኘት፤ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች ። ከአንድ ዓመት በኋላም በካሜሮን አስተናጋጅነት በተከናወነው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ሴኔጋልና ግብፅ ባደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ የቫር ዳኛ (video assistant referee) በመሆን ሰርታለች። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊትም የሞሮኮ የንጉሱ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን በመዳኘትም ቀዳሚዋ ሴት ናት። አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወድድርም፤ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ የመጀመሪያዋ ሰሜን አፍሪካዊት የአረብ ሴት ሆናለች። ቡችራ ካርቡቢ ከእግር ኳስ ዳኝነት ሥራዋ በተጨማሪ፤ የፖሊስ ኦፊሰር በመሆን ሀገሯን እያገለገለች ትገኛለች።