ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም
ይጫኑ

1

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የተስፋ መንገድ



2





3



4

በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በየሁለት ወሩ የምትታተም መጽሔት መስከረም 2009 ዓ.ም ተመሰረተች

ፋክስ ቁጥር +251-11-55-16-09 enanegari@gmail.com

ማውጫ

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

አድራሻ፦ አራዳ ክፍለ ከተማ

ስልክ ቁጥር +251-11-55-00-11 +251-11-56-39-31 +251-11-56-52-21



5

ዋና አዘጋጅ ተስፋዬ ቦካ

ም/ ዋና አዘጋጅ የሺመቤት ደመቀ

ከፍተኛ አዘጋጅ ፍቅርተ ባልቻ

ሰለሞን ተሰራ

አርት ዳይሬክተር ነብዩ መስፍን nebiyou1st@gmail.com

ድረ-ገፅ www.ena.et/web/negari

የኢትዮጵያ የተስፋ መንገድ. . . 06

ከዓባይ እስከ ቀይ ባህር የዘለቀው ፍጥጫ 22

በሀሳብ ልዕልና የታተመ አዲስ ውል 34

የአዲስ ዘመን አዲስ ምዕራፍ 46

ስኬት ያጀበው ጉዞ 54

ከተረጂነት ወደ ትርፍ አምራችነት 64

ከእንፋሎት አብዮት እስከ “ኢትዮጵያ ታምርት” 72

ችግር የወለደው - አኩቴክ ዲያግኖስቲክስ 86

አረንጓዴው ቴክኖሎጂ ኢኮስትሪል 250 92

መልዕክት

ውድ አንባቢያን ሠላም በያላችሁበት ይሁን! ነጋሪ እንደ ወትሮው ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ልታስቃኝ ወደ እናንተ ደርሳለች።

በዚህ ዕትሟ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው፤ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ የታየበትና ለአዲስ መንግሥት ምስረታ ትልቅ የፖለቲካ ካፒታል የፈጠረውን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማንሳት አገሪቷ የተጓዘችበትን የዴሞክራሲ ግንባታ ፈታኝ ጉዞ፣ የለውጥ ፍኖት እንዲሁም በለውጡ ማግሥት የመደመር መንግሥት አፈጻጸምና ሁለንተናዊ የዕድገት ጉዞዋን በመዳሰስ ቀጣዩን የኢትዮጵያ የተስፋ መንገድ የሚያስቃኘውን ፅሁፍ ዓቢይ ጉዳይዋ አድጋለች።

በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር ዙሪያ የሚታየው ፈጣንና ጥልቅ የጂኦ-ፖሊቲካዊ ተለዋዋጭነት የኢትዮጵያ፣ የግብፅ እና የቀጣናውን ሀገራት የወደፊት ዕጣ ፈንታ በመሠረታዊነት እየቀየረው ይገኛል። የኢትዮጵያ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አማራጭ የባህር መዳረሻ ፍለጋ ከቀላል የንግድ አማራጭነት አልፎ የሀገሪቷን ብሔራዊ ደህንነት እና የማክሮ ኢኮኖሚ ህልውና የሚወስን ስትራቴጂያዊ ግዴታ ሆኗል። ነጋሪ በጉዳዩ ላይ ያተኮረ ትንታኔ ይዛለች።

አሮጌው ዓመት የመጨረሻዎቹን ቀናት በትዝታ ሲያጠናቅቅ፤ ኢትዮጵያዊያን በምናባችን ሰፊ የሸራ ሰሌዳ ላይ አዲስ ርዕይ፣ አዲስ ተስፋና አዲስ መዳረሻ መሳል እንጀምራለን። አዲሱ ዓመት ተራ የዘመን መለወጫ ሳይሆን፤ ይልቁንም በውስጣችን የቀበርናቸውን ታላላቅ ሕልሞችና ተስፋዎች ዳግም ቆፍረን በማውጣት ራሳችንን ወደ ስኬት ማማ ለማሸጋገር የምንደክምበት፣ ውስጣችንን ከአልችልም መንፈስ በማላቀቅ ሀገራችን ከደረሰችበት አዲስ ምዕራፍ ጋር ራሳችንን ለማስተሳሰር ሥራ የምንጀምርበት ወቅት ነው - ነጋሪ የምትለው አላት።

ነጋሪ በሌላው ርዕሰ ጉዳይዋ፤ ኢትዮጵያ ለዘመናት ልዩነቶቿን በኃይልና በጠመንጃ አፈ-ሙዝ ለመፍታት ያደረገችውን ታሪካዊና ፖለቲካዊ አዙሪት በማሳየት፣ ሀገራዊ ምክክር ለዘላቂ ሰላምና ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ያለውን አስፈላጊነት ትዳስሳለች። ከዘውዳዊው ሥርዓት፣ ከደርግ ወታደራዊ አገዛዝና ከኢሕአዴግ የብሔር ፖለቲካ ውጣ ውረዶች የሚቀዱ ሀሳቦች፣ ግጭቶችና አግላይ ትረካዎች ሀገሪቷን የከፈሏት መሆኑን ታወሳለች። “በአርባ ቀናት ምክክሮች የተገኙ ምክረ ሀሳቦች እየተመነዘሩ ነገን ይገነባሉ። ትውልድ መጪውን ዘመን በሰላም፣ በመግባባት ይዘልቃል” ትላለች።

ዓለም በእንፋሎትና በኤሌክትሪክ የፈጠራ ስልቶች ታግዛ ወደፊት ስትራመድ፤ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማጠናቀቂያና በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያም አዲስ ታሪክ እያቆጠቆጠ ነበር። የወቅቱ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሀገሪቷን ወደ ዘመናዊነት ለማምጣት ጉዟቸውን አንድ ብለው ጀምረዋል . . . የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ አሃዱ እስከ “ኢትዮጵያ ታምርት” የሚያስቃኘው ጽሁፍ በነጋሪ የውስጥ ገጽ ተሰንዷል።

ስኬት ያጀበው የአረንጓዴ አሻራ መር`ሃ ግብር፣ ከተረጂነት ወደ ትርፍ አምራችነት የመሸጋገር ሀገራዊ ንቅናቄ ላይ ያተኮሩ እንዲሁም አረንጓዴው ቴክኖሎጂ - ኢኮስትሪል 250 እና ችግር የወለደው - አኩቴክ ዲያግኖስቲክስ በሚሉ ርዕሶች የጤናውን ዘርፍ የዳሰሱ ጽሁፎች በነጋሪ ተካተዋል።

መልካም ንባብ!



6

ፖለቲካ

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የተስፋ መንገድ. . .



7

የኢትዮጵያ የተስፋ መንገድ. . .

ከምርጫ ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ፍኖት

በቁምልኝ አያሌው

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው፤ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ የታየበትና ለሚመሠረተው አዲስ መንግሥት ትልቅ የፖለቲካ ካፒታል የፈጠረው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነው። ምርጫው በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ጉዞ ውስጥ ታሪካዊ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል። 42 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሳተፉበት በዚህ ምርጫ፤ ዜጎች ከማለዳ እስከ እኩለ ሌሊት ተሰልፈው ድምፃቸውን “ይሠራልኛል” ላሉት በመስጠት ለጠንካራ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር አስመስክረዋል። ይህም ምርጫው ከተቋማዊ ሂደት በላይ የሕዝብ ባለቤትነት ያለው ሀገራዊ ክስተት መሆኑን ያረጋግጣል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሕዝብ ፈቃድ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ የሚገለጽበትን ባህል በማጠናከር ፋና ወጊ ሆኗል።

ኢትዮጵያዊያን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት የነበራቸውን ቁርጠኝነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተዓምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል” በማለት ገልጸውታል።



8

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ሰባተኛውን ምርጫ በጨረፍታ

በታሪካዊው የምርጫ ዕለት የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፤ የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው፤ ሠርግ፣ ሀዘን፣ የመውለጃ ሠዓት መቃረብና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዷቸው፤ ረጃጅም ሰልፎች ያላታከቷቸው፤ የአካል ጉዳት ድምፅ ከመስጠት ያልገደባቸው፤ ሕመምና እርጅና የሀገርን ተስፋ ከማየት ያላገዳቸው፤ የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸውና ከምንም በላይ የውጭ ጠላትና የባንዳ ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤ ጀግንነትን በዴሞክራሲ ገፅታው አሳይተዋል። ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) “በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባችኋል” ሲሉ አድንቀዋል።

ሕዝቡ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ይጠቅመኛል፣ ይበጀኛል ያለውን ፓርቲ ድምጹን በመስጠት አዲስ መንግሥት እንዲመሠረት ፈቅዷል። በቀጣዮቹ ዓመታት በትጋት እንዲያገለግለው በድምጹ ቃል ኪዳኑን አፅንቷል። ከሌሊት እስከ እኩለ ሌሊት ተራውን ጠብቆ ድምፁን የሰጠውን ሕዝብ ስለማገልገል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

(ዶ/ር) ሲናገሩ “ይህንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ፤ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ” በማለት ነው አደራቸውን የገለጹት።

የምርጫው አንዱ ጉልህ ገፅታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ያደረጉት ከፍተኛ ተሳትፎ ነው። ዕውቅና የተሰጣቸው 55 ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከ60 ሺህ በላይ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ሂደቱን በቅርብ ተከታትለዋል፤ አሳታፊ፣ ዴሞክራሲያዊና በሁሉም መለኪያ የነቃ ተሳትፎ የተደረገበት ነው።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አሕመድ ሁሴን፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማስፈጸም አቅም በተግባር የታየበት መሆኑን “ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያዊያንና የፖለቲካ ፓርቲዎች ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና በሁሉም መለኪያ የነቃ ተሳትፎ ያደረጉበት ሆኗል። ኢትዮጵያዊያንና የፖለቲካ ፓርቲዎች ለጠንካራ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ መሠረት በመጣል ቁርጠኝነታቸውን በተግባር አሳይተዋል” ሲሉ ገልጸውታል።

የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ታዛቢዎችን መመደቡ ሀገራዊው ምርጫ ግልጽነት፣ ተዓማኒነትና የሕዝብ መተማመንን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል። ለዜጎች የምርጫ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን በመስጠት የመራጮችን ንቃተ ህሊና ለማሳደግ አግዘዋል።

ምርጫው ሁሉንም ወገኖች ያሳተፈ፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሴቶች የነቃ ተሳትፎ የታየበት እንደነበር የተለያዩ ወገኖች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። “በኢትዮጵያ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ሴቶች ያለምንም ስጋት ሕገ- መንግሥቱ የሰጣቸውን ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲጠቀሙ ተደርጓል። የምርጫው ሂደትም ከቅድመ ምርጫ እስከ ምርጫው ዕለት ድረስ የሴቶች ደህንነት ተጠብቆ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ለማድረግ አበረታች ሥራ ተሠርቷል” በማለት የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ዋና ዳይሬክተር ሕብረት አባሆይ የገለጹትን ሀሳብ እዚህ ላይ ማንሳቱ ተገቢ ነው።

የምርጫው ተዓማኒነት በሀገር ውስጥ ተቋማት ብቻ ሳይሆን በአህጉራዊ ታዛቢዎችም ተገምግሟል። የአፍሪካ ኅብረትና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ታዛቢ ቡድኖች ኢትዮጵያዊያን ለዴሞክራሲያዊ



9

አጠቃላይ ምርጫም አንድ ወሳኝ እርምጃ ሆኖ ይጠቀሳል። የፓርላማ ብዝሃነት መጨመር፣ አዳዲስ የፖለቲካ ተወዳዳሪዎች መሳተፍና የምርጫ ሂደቱ ላይ የተለያዩ ተሞክሮዎች መፈጠራቸው ዴሞክራሲያዊ ተቋማት በሂደት እንደሚጠናከሩ የሚያመለክቱ ናቸው። ሆኖም ይህ ጉዞ ቀጥተኛና ከተግዳሮት የፀዳ አልነበረም። ዴሞክራሲ የሚገነባው በሕጎችና በተቋማት ብቻ ሳይሆን እነዚህን ሕጎችና ተቋማት በተግባር በሚያከብሩ ንቁ ዜጎች ጭምር ነው። ስለዚህ የሕግ የበላይነትን ከማንኛውም የፖለቲካ ፍላጎት በላይ ማስቀመጥ፣ የፖለቲካ ውይይትንና የመቻቻል ባህልን ማጠናከር፣ የሀገራዊ ምክክርን ውጤቶች ወደ ተግባር መቀየር እንደ ቀጣይ የቤት ሥራዎች ይታያሉ።

በተመሳሳይ ወጣቶችንና ሴቶችን በዴሞክራሲያዊ ሂደቶች ውስጥ ይበልጥ ማሳተፍ፣ ሐሰተኛ መረጃንና የጥላቻ ንግግርን በሕጋዊና በማኅበራዊ መንገድ መከላከል፣ የመገናኛ ብዙኃንን ነፃነትና ኃላፊነት ማስተሳሰር እንዲሁም የምርጫ ሂደቶችን የበለጠ ግልጽ፣ ተዓማኒና አካታች ማድረግ የሚጠበቅ ነው። ዋናው ጉዳይ የፖለቲካ ትግልን ከግለሰብና ከቡድን ፉክክር ወደ ሀሳብና ፖሊሲ ፉክክር መቀየር ነው።

የታሪክ ትልቁ ትምህርት ጠንካራ ሀገራት የሚገነቡት በጠንካራ ተቋማት፣ በንቁ ዜጎችና በጋራ ርዕይ መሆኑን ያሳያል። ስለዚህ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ የለውጥ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ያሉትን ተቋማት የማጠናከር፣ አዳዲስ ተቋማትን የመገንባትና የዜጎችን የዴሞክራሲ ባህል የማሳደግ የረጅም ጊዜ ጉዞ ነው። የዚህ ጉዞ ውጤትም በተቋማት ጥንካሬ፣ በሕግ የበላይነት፣ በዜጎች ተሳትፎና በልዩነት ውስጥ የጋራ ሀገራዊ ርዕይ በመገንባት ይለካል።

የኢትዮጵያ የለውጥ ፍኖት

የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ ጥንካሬ የሚለካው በምርጫ ውጤት ብቻ ሳይሆን በተገነቡ ገለልተኛ ተቋማት፣ በጠንካራ የሕግ የበላይነትና በዜጎች ተሳትፎ ነው። በስድስተኛው ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር ማሳየታቸውን በመግለጽ ምርጫው ለሀገሪቱ የፖለቲካ ዕድገት ጠቃሚ ምዕራፍ ነው ሲሉ አረጋግጠዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የዴሞክራሲ ጉዞው መጨረሻ ሳይሆን የጠንካራ ተቋማት ግንባታ ቀጣይ ምዕራፍ መጀመሪያ ነው።

የዴሞክራሲ ግንባታ ፈታኝ ጉዞ

የዴሞክራሲ ግንባታ እንደ አንድ የፖለቲካ ውሳኔ በአንድ ቀን የሚጠናቀቅ ሂደት አይደለም። በጊዜ የሚገነባ፣ በጠንካራ ተቋማት የሚጠናከርና በዜጎች ተሳትፎ የሚለካ የረጅም ጊዜ ጉዞ ነው። ኢትዮጵያም ዴሞክራሲን ለማስፈን ባላት ቁርጠኝነት፣ ከለውጥ ወደ ተቋማዊ ግንባታ የሚወስዱ በርካታ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።

ይህ ሽግግር ከምርጫ ሥርዓቱ ማሻሻያ ጀምሮ በተለያዩ አስረጂዎች ይታያል። የምርጫ ቦርዱን ነፃነትና ተቋማዊ አቅም ለማጠናከር የተደረጉ ማሻሻያዎች፣ የምርጫ ሕጎችን ማሻሻልና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተሳትፎ ለማስፋት የተወሰዱ እርምጃዎች የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረት ለመጣል የተደረጉ ጥረቶች ናቸው።

በዚሁ መስመር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መቋቋሙ ፓርቲዎች ልዩነታቸውን በግጭት ሳይሆን በውይይት እንዲያስተናግዱ መድረክ ፈጥሯል። የሲቪል ማኅበረሰብ ተሳትፎ መስፋፋትና የመገናኛ ብዙኃን ሕጎች ማሻሻል በዴሞክራሲ ግንባታው ውስጥ የዜጎችን ድምፅ ለማጠናከር የተደረጉ ሌሎች ተጨባጭ እርምጃዎች ናቸው።

ከምርጫና ከፓርቲ ፖለቲካ ባሻገር የተጀመረው የሀገራዊ ምክክር ሂደትም ሌላው የዚህ ሽግግር ጉልህ አስረጂ ነው። በሀገር ደረጃ የቆዩ ልዩነቶችንና ጥያቄዎችን በኃይል ሳይሆን በውይይት ለመፍታት የተወሰደው አቅጣጫ የዴሞክራሲ ባህል ከምርጫ ቀን ባሻገር የሚዘልቅ መሆኑን ያሳያል። ልዩነትን መቀበል፣ ሌላውን ማዳመጥና በጋራ መፍትሔ መፈለግ የዴሞክራሲ ተቋማት እንዲያድጉ የሚያደርጉ መሠረታዊ እሴቶች ናቸው።

በዚህ የሽግግር ጉዞ ውስጥ የ2013 ዓ.ም



10

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ጠቅላላ ምርጫ ማግሥት የተፈጠረው ፖለቲካዊ ምኅዳር በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ያለፈ ቢሆንም ተስፋ ሰጪ የተቋማት ማሻሻያና የብሔራዊ መግባባት እርምጃዎችን ያስመዘገበ አዲስ የሽግግር ምዕራፍ ነው።

የምርጫ ቦርድ ገለልተኝነት

ከተፅዕኖ መላቀቅ፦ ቦርዱ በአንድ ፓርቲ ተፅዕኖ ሥር ከነበረበት አሠራር ወጥቶ በሕግና በአዲስ መዋቅር ተዓማኒነቱ እንዲጠናከር አድርጎታል። ቦርዱ ከተፅዕኖ ነፃ ሆኖ እንዲሠራ በሕግና በአዲስ መዋቅር የተደረጉ ማሻሻያዎች የምርጫ ሂደቱን ተዓማኒነት ለማጠናከር የተወሰዱ ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው። የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ከፖለቲካዊ ተፅዕኖ ሲላቀቅ፣ ምርጫው የፓርቲዎች የሥልጣን ፉክክር ብቻ ሳይሆን የዜጎች ድምፅ የሚወሰንበት ተቋማዊ ሂደት ይሆናል።

የሕዝብ እምነት፦ ተቋሙ ለሕግ ብቻ ተገዢ ሆኖ በገለልተኝነትና በግልጽነት መሥራቱ በምርጫ ሂደት ላይ የዜጎችንና የፖለቲካ ፓርቲዎችን እምነት ለማሳደግ ወሳኝ ነው። የምርጫ ውጤት በሚታወጅበት ጊዜ የውጤቱ ተቀባይነት የሚወሰነው በቁጥሩ ብቻ ሳይሆን፣ ውጤቱን ያመነጨው ሂደት በሕዝብ ዘንድ ተዓማኒ በመሆኑ ጭምር ነው።

የተቋም ጥንካሬ፦ ነፃና ገለልተኛ የምርጫ ተቋም የምርጫ ቀንን ብቻ የሚያስተዳድር አካል አይደለም። የመራጮች ምዝገባ፣ የፓርቲዎች ምዝገባ፣ የምርጫ ዘመቻ፣ የድምፅ አሰጣጥና የቆጠራ ሂደት እንዲሁም የቅሬታና የይግባኝ ሥርዓት በግልጽ ሕግና በተመሳሳይ አሠራር እንዲመሩ የሚያደርግ ቋሚ የዴሞክራሲ ተቋም ነው።

የተቋሙን ነፃነት በሕግ ብቻ ሳይሆን በተግባርም ማረጋገጥ፣ የምርጫ ሂደቱን ይበልጥ ግልጽና አካታች ማድረግ፣ የምርጫ ቅሬታዎችን በፍትሐዊና በፈጣን ሥርዓት ማስተናገድ የተቋሙን ተዓማኒነት የሚያጠናክሩ ቀጣይ ሥራዎች ናቸው። ዴሞክራሲ የሚገነባው በግለሰቦች ፈቃድ ሳይሆን በሕግ የበላይነትና በጠንካራ ተቋማት ላይ ነው። የምርጫ ቦርድ ገለልተኝነትም ይህን መርህ በተግባር ከሚያሳዩ ዋና የዴሞክራሲ መሠረቶች አንዱ ነው።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አዲስ ባህል

ከግጭት ወደ ውይይት፦ የሀሳብ ልዩነቶች ወደ ግጭት ከመሸጋገራቸው በፊት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት፣ በጋራ ለመወያየትና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችል ዘላቂ መድረክ መፈጠሩ ከተቋማዊ ለውጦች አንዱ ነው። ይህም የፖለቲካ ተቃርኖን እንደ ግጭት ምንጭ ሳይሆን እንደ ውይይትና መፍትሔ መንገድ ለመጠቀም ዕድል ይፈጥራል።

አዲስ የፖለቲካ ባህል፦ ፖለቲካዊ ውድድርን ከጠላትነት ወደ ጤናማ ፉክክር በመቀየር፣ ከዜሮ-ድምር (Zero-Sum) አስተሳሰብ ወደ ጋራ ሀገራዊ ግብ ለመሻገር መሠረት ጥሏል። በዚህ አዲስ ባህል የፖለቲካ ተፎካካሪ የግድ ጠላት ሳይሆን፣ የተለየ ሀሳብ የሚያቀርብ የሀገራዊ ውይይት አካል እንደሆነ የሚታይበት አቅጣጫ ይጠናከራል።

የልዩነት አስተዳደር፦ ዴሞክራሲ ልዩነትን ማጥፋት ሳይሆን ልዩነትን በሰላማዊና በተቋማዊ መንገድ ማስተናገድ ነው። የጋራ ምክር ቤቱም ይህን መርህ በተግባር ለማሳየት የሚችል መድረክ ሲሆን ፓርቲዎች የሀገሪቷን የፖለቲካ ልዩነት በንግግር፣ በምክክርና በመግባባት ለማስተናገድ የሚማሩበት ሂደት ይሆናል።

ከፉክክር ወደ ትብብር፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሀገሪቷ የወደፊት አቅጣጫ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችን ቢያቀርቡም ሰላም፣ ልማት፣ የሕግ የበላይነትና የሀገር አንድነት የጋራ ጉዳዮች ናቸው። በመሆኑም የጋራ ምክር ቤቱ የፖለቲካ ፉክክርን ሳያስወግድ በጋራ በሚያግባቡ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትብብርን ለማሳደግ የሚያግዝ ምኅዳር ሊሆን ይችላል።

በቀጣይ ይህ አዲስ የፖለቲካ ባህል የሚጠናከረው በመድረኩ መኖር ብቻ ሳይሆን ውይይቱ ወደ ተጨባጭ የፖለቲካ ልምምድ ሲቀየር ነው። ስለዚህ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተጀመረውን የውይይት ባህል በማስቀጠል፣ የፖለቲካ ልዩነቶች ወደ ግጭት ሳይሆን ወደ ሀሳብ ፉክክርና የሰላማዊ ሥልጣን ሽግግር የሚያመሩበትን ባህል መገንባት ይጠበቅበታል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አቅም

የምኅዳሩ መስፋት፦ በተደረጉ የሕግ ማሻሻያዎች የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በሰብዓዊ መብት፣ በመልካም አስተዳደር፣ በሰላም ግንባታና በማኅበራዊ ፍትሕ ዙሪያ የበለጠ የተሳተፉበት ምኅዳር ተፈጥሯል። ይህም የመንግሥትና የሕዝብ ግንኙነትን ከአስተዳደር



11

ባሻገር ወደ ትብብርና ተጠያቂነት ለማሸጋገር ዕድል ይፈጥራል።

የዜጎች ተሳትፎ፦ ጠንካራ ሲቪል ማኅበረሰብ ዴሞክራሲን በምርጫ ቀን ብቻ እንዳይወሰን ያደርጋል። የዜጎችን ድምፅ በማሰማት፣ የመንግሥትን አፈጻጸም በመከታተልና የሕዝብ ጥያቄዎችን ወደ ፖሊሲ ውይይት በማምጣት ተጠያቂነትን ያጠናክራል። በዚህም ዴሞክራሲ የምርጫ ሂደት ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት የዜግነት ባህል እንዲሆን ያግዛል።

የመገናኛ ብዙኃን ነፃነትና ኃላፊነት

የመረጃ ፍሰት፦ አዲሱ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ የጋዜጠኞችንና የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት በማጠናከር፣ ከቀድሞው የቁጥጥር አካሄድ ወደ ክፍት የሕዝብ ውይይት የሚያመራ ምኅዳር ፈጥሯል። የመረጃ ተደራሽነት መስፋፋት ዜጎች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በዕውቀት እንዲሳተፉና መንግሥታዊ ተቋማትም ለሕዝብ የበለጠ ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚያግዝ መሠረት ይፈጥራል።

የሚዲያ ብዝሃነት፦ የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት፣ አስተያየቶችና የአመለካከት ልዩነቶች መኖራቸው የሕዝብ ውይይትን ያዳብራል። የተለያዩ ድምፆች የሚሰሙበት የሚዲያ ምኅዳርም ዜጎች በተለያዩ ሀሳቦች መካከል በመመዘን አመለካከታቸውን እንዲያዳብሩ ያግዛል።

ነፃነትና ኃላፊነት፦ ነፃ ሚዲያ የሕዝብ ጥቅምን በመጠበቅ፣ ተቋማትን በመጠየቅና ተጠያቂነትን በማጠናከር በዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ የማይተካ ሚና አለው። የተረጋገጠ መረጃን በመመርመር፣ ምንጮችን በማረጋገጥና የግለሰቦችን ክብርና መብት በማክበር ሙያዊ ጋዜጠኝነትን ማጠናከር ያስፈልጋል።

ዲጂታል ሚዲያና ፈተናዎቹ፦ የማኅበራዊ ሚዲያ መስፋፋት የመረጃ ፍሰቱን ከመቼውም ጊዜ በላይ አፋጥኖታል። ይህ ለዜጎች የመረጃ ተደራሽነትን ቢያሰፋም ሐሰተኛ መረጃ፣ የጥላቻ ንግግርና የተዛባ መረጃ በፍጥነት እንዲሰራጭ አድርጓል። ስለዚህ የሚዲያ ተቋማት ብቻ ሳይሆኑ ዜጎችም የመረጃ ንባብና የማጣራት ክህሎት እንዲኖራቸው ማድረግ የዴሞክራሲ ግንባታው አካል ነው። በመሆኑም የወደፊቱ ትኩረት ነፃነትን በማስጠበቅ እና ኃላፊነትን በማጠናከር መካከል ሚዛን መፍጠር ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል። ሚዲያው የሕዝብ ድምፅ ብቻ ሳይሆን የሕዝብን ውይይት በእውነተኛ፣ በተመጣጠነና በሙያዊ መረጃ የሚያበለጽግ ተቋም መሆን ሲችል የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሥራም ጠንካራ መሠረት ያገኛል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳታፊነት

የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተጀመረውን የውይይት ባህል በማስቀጠል፣ የፖለቲካ ልዩነቶች ወደ ግጭት ሳይሆን ወደ ሀሳብ ፉክክርና የሰላማዊ ሥልጣን ሽግግር የሚያመሩበትን ባህል መገንባት ይጠበቅበታል።



12

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

የብዝኅ ፓርቲዎች ድምፅ፦ ከስድስተኛው ምርጫ በኋላ የተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ምክር ቤቱን መቀላቀላቸው በፓርላማው ውስጥ የሃሳብ ብዝኃነትን ለማስፋፋት ዕድል ፈጥሯል። የተለያዩ ፖለቲካዊ አመለካከቶች በምክር ቤቱ እንዲወከሉ መደረጉም የሕዝብ ውይይትን በማስፋት የሕግ አወጣጥና የፖሊሲ ውይይት ሂደቱን ለማጠናከር አስችሏል።

ተቋማዊ ቁጥጥር፦ የፓርላማው የፖለቲካ ስብጥር የአስፈጻሚውን አካል ተጠያቂነት ለማጠናከር፣ የመንግሥት ሥራዎችን በጥያቄና በውይይት ለመፈተሽ እና የዜጎችን የፖለቲካ ውክልና ለማስፋት የበለጠ ዕድል ይፈጥራል። ፓርላማው የሕግ አውጪ ተቋም ብቻ ሳይሆን የአስፈጻሚውን አካል የሚጠይቅና የሕዝብ ጥያቄን የሚያስተጋባ ተቋም እንዲሆን ያግዛል።

የሕዝብ ውክልናና ተሳትፎ፦ የተለያዩ ፓርቲዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች በምክር ቤቱ መወከላቸው የዜጎች ጥያቄዎችና አመለካከቶች ወደ ሕግ አውጪው ተቋም እንዲመጡ ሰፊ መድረክ ይፈጥራል። ይህም የፓርላማ ውክልናን ከምርጫ ውጤት ባሻገር ከዜጎች ተጠያቂነትና ከሕዝብ ጥቅም ጋር የሚያገናኝ የተቋማዊ ዴሞክራሲ ባህል ያጠናክራል።

በቀጣይም የፓርላማው የብዝኅነት ዋጋ የሚለካው በውክልና ብቻ ሳይሆን በውይይት ጥራት፣ በአስፈጻሚው አካል ላይ በሚደረግ ውጤታማ ቁጥጥር፣ በሕዝብ ጥያቄዎች ላይ በሚሰጥ ተገቢ ምላሽና በሕግ አወጣጥ ጥራት ነው። ስለዚህ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተግባራዊ የዴሞክራሲ መድረክ እንዲሆን የፓርላማ ቁጥጥርን፣ የአባላትን የሕግ አወጣጥ አቅምና የዜጎችን ተሳትፎ ማጠናከል ይገባል።

በአገራዊ ለውጡ ማግሥት የመደመር መንግሥት አፈጻጸም

በዘመናዊው ዓለም የሀገራት ኢኮኖሚያዊ ስኬት በመንግሥት ብቻ በሚመሩ ፕሮጀክቶች ሳይሆን የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነትን ባማከለ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የተመሠረተ ነው። ይህንን መርህ መሠረት ያደረገው የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ኢኮኖሚውን ከመንግሥት መር ሥርዓት ወደ ይበልጥ ተወዳዳሪ፣ ነፃና በግሉ ዘርፍ ወደሚደገፍ ሥርዓት ለማሸጋገር የተጀመረ ታሪካዊ ሂደት ነው።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መንግሥት በኢኮኖሚው ላይ የነበረውን ከፍተኛ ቁጥጥር በመቀነስ፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግና ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት በማድረግ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። የኢኮኖሚ አፈጻጸምን በማሻሻል ኢትዮጵያን ከዓለም ኢኮኖሚ ጋር ይበልጥ የማስተሳሰር ዋና ዓላማ ሪፎርሙ፤ ለዜጎች አዳዲስ የሥራና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱን አረጋግጧል።

ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት፣ የገበያ ውድድርን በማበረታታትና የፋይናንስ ዘርፉን በማዘመን ኢኮኖሚው ከአንድ ዘርፍ ጥገኝነት ወደ ብዝኅ የምርትና የአገልግሎት ሥርዓት እየተሸጋገረ ይገኛል። ይህም “የተጀመረውን አዲስ ምዕራፍ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ በሁሉም መስክ በሚቆጠር ውጤት ገልጧል” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለጹትን ሀሳብ ያፀናል።

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የአጭር ጊዜ ለውጥ ሳይሆን ለዘላቂ ብልፅግና መሠረት የተጣለበትና አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሣሌት አገር ለመገንባት የሚያስችል እመርታዊ ዕድገት የሚመዘገብበት ታላቅ ጉዞ ነው።

በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሀመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት ለውጡን ተከትሎ ቀደም ሲል የነበሩት የፖሊሲ ማነቆዎች ተወግደው በምትኩ ምቹ ምህዳር መፈጠሩ የኢኮኖሚውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግና የግሉን ዘርፍ ለማነቃቃት ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም እንደ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ የባንክ አገልግሎት፣ የችርቻሮ ንግድ እና የኮንስትራክሽን ዘርፎችን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት በማድረግም አዲስ የገበያ ዕድል ፈጥሯል።

በተለይ ከለውጡ ማግሥት ጀምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት እያደረጉ ይገኛሉ። ይህም በሀገር ደረጃ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳለጥ፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና የአገልግሎት ጥራትና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል። እንደ ከፍተኛ ተመራማሪው ገለጻ በሪፎርሙ የውጭ ምንዛሬ በገበያ እንዲወሰን መደረጉ፣ የመንግሥት



13

ገቢና ወጪን የማመጣጠን ሥራ እና የታክስ መሠረቱን ማስፋት ለኢኮኖሚው ስኬት ትልቅ መገለጫዎች ናቸው።

በበኩላቸው “ሪፎርሙ የውጭ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገ ይገኛል። በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉን ዲጂታላይዝ ማድረግ መቻሉ፣ ሀገሪቷ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነት አጎልብቷል” ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማኅበር ከፍተኛ ተመራማሪ ሞላ አለማየሁ (ዶ/ር) ናቸው።

በመደመር መንግሥት እሳቤ የተቃኘው ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ኢትዮጵያ ለዘመናት ሲገጥማት የነበረውን የኢኮኖሚ ስብራት በማከም አዳዲስ የዕድገትና ብልጽግና ዕድሎችን ፈጥሯል። ሪፎርሙ የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛኖችን ከማስተካከል ባለፈ የምርት አቅምን ማሳደግ፣ ኢንቨስትመንትን ማበረታታት፣ የፋይናንስ ዘርፉን ማዘመንና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማስፋት የሚያስችል መሠረት ገንብቷል። በሁለት ምዕራፎች በተከፈለ መርኃ ግብር ተግባራዊ የተደረጉ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርኃ ግብሮች የዘርፎችን እመርታዊ ውጤት በማላቅ የኢትዮጵያን ማንሰራራት እያፋጠኑ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ማጠቃለያ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት፤ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ከተጠበቀው በላይ አመርቂ ውጤት አምጥቷል። በእመርታ የታጀበው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማንሰራራት ስኬት በአፍሪካ ፈጣን ዕድገት ካላቸው ግንባር ቀደም ሀገራት አድርጓታል።

ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውም የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶችን በማከም ከነባሩ የግብርና መር ክፍለ ኢኮኖሚ ወደ ብዝኅ ዘርፍ በማሸጋገር ጥራት ያለው ዕድገት እንድታስመዘግብ እያስቻለ ሲሆን፤ ይህም የኢኮኖሚ ማንሰራራትን በጽኑ መሠረት በማነጽ በሁሉም ዘርፍ የተቀናጀና ቀጣይነት ያለው የዕድገት ሽግግር የሚሳለጥበትን ሁኔታ ፈጥሯል።

ከግብርና መር ወደ ብዝኅ ዘርፍ ዕድገት

ግብርና ለኢትዮጵያ ከአንድ የኢኮኖሚ ዘርፍ በላይ ሆኖ የሕይወት ምንጭ፣ የምግብ ዋስትና፣ የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ አቅራቢና የውጭ ምንዛሬ ዋና ምሰሶ ነው። ሆኖም የ21ኛው ክፍለ ዘመን እውነታ በአንድ ዘርፍ ላይ ብቻ ተመርኩዞ ዘላቂ ዕድገት ማስመዝገብ እንደማይቻል ስለሚያሳይ፤ ኢትዮጵያ የግብርናውን ሚና ሳትቀንስ ኢንዱስትሪን፣ አገልግሎትን፣ ማዕድንን፣ ቱሪዝምና ዲጂታል ኢኮኖሚን በአንድ ላይ በማስኬድ ወደ ብዝኅ ዘርፍ ዕድገት እየተሸጋገረች ትገኛለች። የግብርናው ዘርፍም የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን፣ የመስኖ ልማትና ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴዎችን በመጠቀም ከባህላዊ ወደ ምርታማ ሥርዓት በመሸጋገር ላይ ይገኛል። ይህ ሽግግር ግብርናን ከጥሬ ምርት አቅራቢነት ወደ ዕሴት ፈጣሪነት በማሳደግ ለሀገራዊ ለውጡ ሰፊ መሠረት እየጣለ ስለመሆኑ አብነት መጥቀስ ይቻላል።

የስንዴ አብዮት፤ ከአስመጪነት ወደ ራስን መቻል

በቅርብ ዓመታት ከተመዘገቡ አስደናቂ ስኬቶች መካከል የስንዴ ልማት አብዮት በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ለብዙ ዓመታት በውጭ ገበያ ላይ ተመርኩዞ የነበረውን የስንዴ ፍላጎት በራስ አቅም ለመሸፈን የተወሰዱ የፖሊሲ እርምጃዎችና የመስኖ ልማት መስፋፋት ውጤታማ ሆነዋል።

የሜካናይዜሽን እርሻ ልማት የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ እመርታ እያስገኘ ነው። የስንዴ ልማቱን ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥና ለውጭ ገበያ የማቅረብ ተግባርም አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው። በክረምት ብቻ ሳይሆን በበጋ መስኖ የሚከናወነው የስንዴ ልማት የምርት ወቅትን ከአንድ ጊዜ ወደ ዓመቱን ሙሉ እንዲቀየር በማድረግ ሀገሪቷን ከምግብ ዋስትና ስጋት አላቋታል። የስንዴ አብዮቱ የውጭ ምንዛሬ ቁጠባን ከማስገኘት ባለፈ የገጠሩን ኢኮኖሚ በማነቃቃት የዘር፣ የማዳበሪያና የቴክኖሎጂ አቅርቦትን ጨምሮ ሰፊ የሥራ ዕድል የፈጠረ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አካል ነው።

የሌማት ትሩፋት፤ የዘርፈ ብዙ በረከት ምዕራፍ

የሌማት ትሩፋት መርኃ ግብር የግብርናውን ዘርፍ ከሰብል ምርት ጠባብ ዕይታ በማውጣት



14

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ከእንስሳት፣ ከዓሣ፣ ከአትክልትና ፍራፍሬ ጋር በማስተሳሰር የምግብ ዋስትናና የሥርዓተ ምግብ ልዩነትን ለማረጋገጥ የተጀመረ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው። ይህ መርኃ ግብር የቤተሰብን የምግብ ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር በሕፃናት ዕድገትና በእናቶች ጤና ላይ ትልቅ ለውጥ እያመጣ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርባ ምንጭ ከተማ የሌማት ትሩፋት የልማት ዘመቻን ሲያስጀምሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሌማት ትሩፋት መርኃ ግብር አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ ነው። መርኃ ግብሩም በቂና አመርቂ ምግብ ማግኘት ነው፤ በቂ የመጠን፣ አመርቂ የይዘት ጉዳይ ነው። በምግብ ራስን መቻል ከሀገር ሉዓላዊነትና ክብር ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው። የሌማት ትሩፋት ዘመቻው በቤተሰብ፣ ብሎም በሀገር ደረጃ በምግብ ራሳችንን ለመቻል የምናደርገውን ጥረት ያፋጥንልናል።

በዶሮ እርባታ፣ በወተት ላሞችና በዓሣ ሀብት ልማት ላይ የተጀመረው አዲስ እንቅስቃሴ ለሴቶችና ለወጣቶች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ከመፍጠሩም በላይ ጤናማና ብቁ ዜጋ በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። ሲሉ ገልጸዋል።

የሌማት ትሩፋት መርኃ ግብር ዜጎች የተመጣጠነ የምግብና የሥነ-ምግብ ሥርዓት የሚያገኙበትን ዕድል እያስገኘ ነው። በተለይም የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ዘርፍ ላይ ጉልህ የምርታማነት ዕድገት ተገኝቷል።

የአረንጓዴ አሻራ፤ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ መሰረት

የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከችግኝ ተከላ ዘመቻ በላይ አካባቢን፣ ኢኮኖሚን፣ ግብርና እና የትውልድ ደህንነትን የሚያገናኝ ሀገራዊ ርዕይ ነው። ለረጅም ዓመታት በደን መጨፍጨፍ እና በአፈር መሸርሸር ሲፈተን የቆየውን ሀገራዊ መልክዓ ምድር ወደ ቀድሞ ሁኔታው በመመለስ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያስችል የኢኮኖሚ መሠረት እየተጣለ ነው። የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሩ የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን ለመቋቋምና ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል አቅም ፈጥሯል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ የተጎዱ መሬቶች እንዲያገግሙ ማድረግ፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ኢኮኖሚ የሚሉትን ዓላማዎች ሰንቋል። ነባር ደኖችና የውሃ ሀብቶች የሚጠበቁበት እንዲሁም ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ የሚያደርግ እና ሥርዓተ ምግብን ለማሻሻል ወሳኝ ሚና እያበረከተ የሚገኘው መርኃ ግብሩ በከፍተኛ የፖለቲካ ቁርጠኝነትና የማኅበረሰብ ተሳትፎ እየተተገበረ የሚገኝ፣ ሁሉም ዜጋ ለአካባቢ ጥበቃ በአዲስ ዕይታ እንዲነሳ ያደረገ ነው።

የኢንዱስትሪ ዕመርታ፤ ከውድቀት ወደ ምርታማነት

ኢትዮጵያ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ለምታደርገው መዋቅራዊ ሽግግር የኢንዱስትሪ ልማት መስፋፋት የማይተካ ሚና አለው። መንግሥት የዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባትና ወደ ሥራ በማስገባት



15

ለውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እና ለሀገር ውስጥ አልሚ ባለሀብቶች መነቃቃት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። ይህ የተቀናጀ ጥረት በሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ የኢንዱስትሪው ድርሻ እንዲያድግ በማስቻል ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማምጣት ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የዘርፉ ስትራቴጂካዊ ማነቆዎችና የመፍትሔ እርምጃዎች

የኢትዮጵያ የልማት ጉዞ በግብርና ላይ ብቻ በማተኮሩ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ከሚጠበቀው በታች ሆኖ ቆይቷል። የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ችግር፣ ዝቅተኛ የፋብሪካዎች የማምረት አቅም፣ የገበያ መዛባትና የፋይናንስ ጫናዎች ለዘርፉ ውድቀት ዋና ዋና ምክንያቶች ነበሩ። ይሁን እንጂ በ2010 ዓ.ም በሀገራዊ ለውጡ ማግሥት የተተገበሩ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ የ‘ኢትዮጵያ ታምርት’ ንቅናቄ እና የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ስትራቴጂዎች ዘርፉን ከመቀዛቀዝ ወደ መነቃቃት አሸጋግረውታል። መንግሥት ልዩ ኮሚቴ በማቋቋም ባደረገው የተቀናጀ ድጋፍ ቀድሞ ከ47 በመቶ በታች የነበረው የፋብሪካዎች የማምረት አቅም ወደ 67 በመቶ ከፍ ማለቱ ዘርፉ እያሳየ ያለውን እመርታዊ ለውጥ ያሳያል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ምርቶች ተወዳዳሪነት እንዲጨምርና ምርታማነትን እንዲያሳድጉ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ኢትዮጵያ ታምርትም የሀገር ውስጥ ምርታማነት እንዲጨምር እያደረገ ነው።

የኢንዱስትሪ ልማት ውጤቶችና የወደፊት ተስፋዎች

የዘርፉ መነቃቃት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። ቀደም ሲል 100 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኝ የነበረው ዘርፍ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር የማመንጨት አቅም ላይ እንዲደርስ እየተሠራ ሲሆን፤ በ2018 በጀት ዓመት ብቻ ከውጭ የሚገቡ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ወደ አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሀገራዊ ቁጠባ ተገኝቷል። በሴራሚክ፣ በሲሚንቶ፣ በመስታወት፣ በብረት እና በሶላር ምርቶች ላይ የተከናወኑ ሰፋፊ ሥራዎች የውጭ ጥገኝነትን እየቀነሱ ይገኛሉ። አጠቃላይ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ 20 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል። ኢትዮጵያ እንደ ደቡብ ኮሪያ እና ቬትናም ሁሉ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ በሚደረገው ስልታዊ ሽግግር በትክክለኛው የዕድገት ጎዳና ላይ ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፤ ከምርት ተቀባይነት ወደላኪነት

’ኢትዮጵያ ታምርት’ የምርት ባህልን በመቀየር ኢንዱስትሪን የኢኮኖሚ ሽግግር ዋና ሞተር ለማድረግ የተቀረፀ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው። ትኩረቱም ከምርት መጠን ይልቅ በጥራት፣ እሴት በመጨመር (ለምሣሌ ቡና እና ቆዳን አቀነባብሮ ለገበያ በማቅረብ) እና በፈጠራ ላይ ያተኮረ በመሆኑ፤ አምራቾች የዓለም ገበያ ደረጃዎችን እንዲያሟሉና ሸማቾች የሀገር በቀል ምርቶችን የኩራትና የሉዓላዊነት ምልክት አድርገው እንዲደግፉ እያደረገ ነው።

ከሸማችነት ወደ ራስን መቻል፤ የተኪ ምርት ፖሊሲ መርህ

የተኪ ምርት ፖሊሲ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን (እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ መድኃኒት፣ ጨርቃ ጨርቅና ምግብ) በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሬን ለመቆጠብና የሥራ ዕድልን ለማስፋት እያገዘ ነው። ይህ ስትራቴጂ በጥራትና በተወዳዳሪነት ላይ በመመሥረት ሀገሪቷን ከአስመጪነት ወደ አምራችነትና ወደ ወጪ ንግድ ለማሸጋገር መሠረት ሆኗል።

ወጪ ንግድ፤ ከአካባቢ ወደ ዓለም ገበያ የሚደረግ ሽግግር

ኢትዮጵያ በጥቂት የግብርና ጥሬ ዕቃዎች ላይ የነበራትን ጥገኝነት በመቀነስ እሴት የጨመሩ የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን ወደ አፍሪካና መላው ዓለም ገበያ በመላክ ላይ አዲስ አቅጣጫ ይዛለች። ይህም የውጭ ምንዛሬ ገቢን ከማሳደግ ባለፈ “በኢትዮጵያ የተመረተ” የሚለውን ስያሜ የዓለም የጥራትና የሀገር ገጽታ ግንባታ ምልክት እያደረገው ይገኛል።

በሴራሚክ፣ በሲሚንቶ፣ በመስታወት፣ በብረት እና በሶላር ምርቶች ላይ የተከናወኑ ሰፋፊ ሥራዎች የውጭ ጥገኝነትን እየቀነሱ ይገኛሉ። አጠቃላይ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ 20 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ፤ የታዳሽ



16

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ኃይልና የመቻል ተምሣሌት

ታዳሽ ኃይል (የውሃ፣ የንፋስ፣ የፀሐይና ጂኦተርማል) የኢንዱስትሪ፣ የግብርናና የዲጂታል ኢኮኖሚ ዋና ሞተር ነው። የዚህ ታዳሽ ኃይል አብዮት ማሳያ የሆነው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከአምስት ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ኤሌክትሪክ በማመንጨት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን እያሟላና ለጎረቤት ሀገራት እየሸጠ ቀጣናዊ ትስስርን እያጠናከረ ይገኛል። ግድቡና በውስጡ የተፈጠረው የንጋት ሐይቅ ለዓሣ ሀብትና ለቱሪዝም ዕድል ከመፍጠራቸው ባለፈ የኢትዮጵያዊያን “በራስ አቅም የመቻል” ስነ- ልቦና እና የብልፅግና መሠረት ሕያው ምስክር ናቸው።

የምድር ሀብት፤ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ

ኢትዮጵያ በግብርና እና ቱሪዝም ብቻ ሳይሆን በምድር ውስጥ ባላት እምቅ የማዕድን ሀብትም ትታወቃለች። ላለፉት በርካታ ዓመታት ዘርፉ በሚፈለገው ልክ ሳይለማ የቆየ ቢሆንም በቅርብ ጊዜ በተደረጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች እና የምርምር ሥራዎች ምክንያት ትልቅ መነቃቃት አሳይቷል።

ዛሬ የማዕድን ዘርፉ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን፤ የሥራ ዕድል ፈጠራንና የኢንዱስትሪ መሠረትን በመገንባት ረገድ ለሀገሪቷ የኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ ተስፋ ሆኗል።

በሀገራዊ ለውጡ ማግሥት መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት የማዕድን ፍለጋ፣ የፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት እና የጂኦሎጂ መረጃዎችን የማደራጀት ሥራዎች ዘምነዋል። በዚህም ወርቅ፣ ታንታለም፣ ኦፓል፣ ሊቲየም፣ ፖታሽ፣ ኮፐር፣ ኒኬል እና የተፈጥሮ ጋዝ በስፋት በመገኘታቸው ኢትዮጵያን የአፍሪካ ማዕድን መልህቅ አድርጓታል።

ቱሪዝምና አገልግሎት፤ የብዝኅ ዕድገት አቅም

ቱባ ባህል፣ ታሪክ እና ቅርሶችን ለያዘችው ቀደምት የሰው ልጅ መገኛ - ኢትዮጵያ፤ እንደ ፋሲለደስ ግንብ፣ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት፣ አክሱም ሃውልት፣ አልነጃሺ መስጂድ፣ የሐረር ጀጎል እና ጅማ አባ ጅፋር ቤተ-መንግሥት ያሉ ቅርሶች የጥንታዊ ሥልጣኔ ምስክሮች ናቸው። በተጨማሪም እንደ መስቀል፣ ጥምቀት፣ ኢሬቻ፣ አሸንዳ/አሸንድዬ፣ ፊቼ ጨምበላላ እና ጊፋታ ያሉ ማራኪ የአደባባይ ባህላዊና ሃይማኖታዊ በዓላት እሴቶች አሏት።

ሀገሪቷ በአጠቃላይ 16 የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኒስኮ) አስመዝግባለች። በቅርቡ ከተመዘገቡት መካከል የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር እና የሐረር ሸዋል ኢድ ይገኙበታል። እነዚህ ቅርሶች የጎብኚዎችን ቀልብ በመሳብ ለውጭ ምንዛሬ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው።

ጭስ አልባውን ኢንዱስትሪ ይበልጥ ለማነቃቃት መንግሥት የመሠረተ ልማት እና ተጨማሪ የመስህብ ስፍራዎችን የመገንባት ሥራዎችን አከናውኗል። በ”ገበታ ለሸገር” ፕሮጀክት በአዲስ አበባ የተገነቡት የእንጦጦ፣ የአንድነትና የወዳጅነት ፓርኮች ለጎብኝዎች ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል። ይህንን ተሞክሮ በማስፋፋት በ”ገበታ ለሀገር” ስር ሦስት ግዙፍ የቱሪስት መዳረሻዎች ተገንብተዋል።

ከእነዚህ የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል ከጎንደር ከተማ በ61 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በጣና ሐይቅ ዳርቻ የምትገኘው የታሪክና የገዳማት መገኛ ጎርጎራ ከተማ ናት። ከነበረባት የእርጅና እና የትኩረት ማጣት ጫና ወጥታ በፕሮጀክቱ አማካኝነት “የመጻዒ ዘመን ሙሽራ” በሚል ተስፋ ውብ መስህብ ለመሆን በቅታለች።

ከአዲስ አበባ በ150 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ፣ ማራኪ ሐይቅ፣ ደን፣ ፍልውሃ እና የቅዱስ ቂርቆስ ገዳምን የያዘው ተፈጥሯዊ ስፍራ ወንጪ-ደንዲ ሌላው ግዙፍ የቱሪስት መዳረሻ ነው። እ.አ.አ በ2021 የዓለም የቱሪዝም ድርጅት “ምርጥ የቱሪዝም መንደር” አድርጎ የመረጠው ሲሆን ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ጥቅም ተቀይሯል።

ኮይሻ፤ በኦሞ ወንዝ ላይ ከተገነባው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅ ጋር ተያይዞ በዳውሮ ዞን የለማ ስፍራ ሲሆን በውስጡ የያዘው የ”ሃላላ ኬላ ሪዞርት” ለደቡብ ኢትዮጵያ ቱሪዝም አዲስ ዕድል ፈጥሯል።

መንግሥት ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና በጀት በጥራት የማጠናቀቅ ተሞክሮን በመውሰድ የተረሱ ውብ ስፍራዎችን አልምቶ ለትውልድ ለማስተላለፍ “የገበታ ለትውልድ” ፕሮጀክትን ቀርጾ ተግባራዊ አድርጓል። በኦሮሚያ- ጅማ፣ በአማራ - ሐይቅ፣ በደቡብ - አርባ ምንጭ፣ በአፋር -የፓልም ፋርም፣ እንዲሁም በሶማሌ ክልል የጅግጅጋ ሸበሌ ሪዞርት በዚህ ፕሮጀክት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተገነቡት ተጨማሪ ስምንት



17

የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

የዲጂታል አብዮት፤ የኢኮኖሚ ሽግግር አዲስ ምዕራፍ

በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሀገራት ውድድር የሚወሰነው ዲጂታል አቅምን ወደ ኢኮኖሚያዊ እሴት በመቀየር ነው። ኢትዮጵያም በ”ዲጂታል 2025” ስትራቴጂ የጀመረችውን ጉዞ ወደ “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂክ ርዕይ በማሸጋገር ቴክኖሎጂን የኢኮኖሚና የማኅበረሰብ ለውጥ ማፋጠኛ በማድረግ ላይ ትገኛለች።

የስኬት መሠረቶች፦ በ”ዲጂታል 2025” አማካኝነት የቴሌኮም ዘርፍ ለውድድር ክፍት ሆኗል፤ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶች ተስፋፍተዋል፤ የመንግሥት አገልግሎቶች ወደ ኦንላይን ተሸጋግረዋል የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓትም ተዘርግቷል። “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ደግሞ በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI)፣ በፈጠራ ሥራዎች እና በተቀላጠፈ አገልግሎት ላይ ያተኩራል።

የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና፦ ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን በኮዲንግ፣ ፕሮግራሚንግና ዲጂታል ክህሎት በማልማት የሥራ ፈላጊዎችን አቅም ወደ ሥራ ፈጣሪነትና ወደ ቴክኖሎጂ ስታርትአፕነት እያሸጋገረ ይገኛል።

የዘርፎች መሳለጥ

ፋይናንስ፦ የሞባይል ገንዘብ፣ ዲጂታል ክፍያ እና የኦንላይን ባንክ አገልግሎት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የከተማና የገጠር ነዋሪዎችን ወደ ፋይናንስ ሥርዓት አስገብተዋል።

ግብርና፦ የሳተላይት መረጃ፣ የአየር ሁኔታ ትንበያ እና የዲጂታል ገበያ መረጃዎች የገበሬዎችን ምርታማነትና ገቢ እያሳደጉት ነው።

ማዕድንና ቱሪዝም፦ የጂኦሎጂ መረጃዎች ዲጂታላይዝ መሆን የኢንቨስትመንት መስህብነትን ሲጨምር፤ የሞባይል መተግበሪያዎች እና ምናባዊ ጉብኝቶች (Virtual Tours) የቱሪስት ፍሰቱን አሳድገውታል።

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት፦ ዜጎች በአንድ ማዕከል ውስጥ በተቀናጀ መንገድ የመንግሥት አገልግሎቶችን በፍጥነት፣ በግልጽነትና በተጠያቂነት እንዲያገኙ በማድረግ የጊዜ ብክነትን እያስቀየረ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ከፍታ እና ስኬት

ከአጀንዳ ተቀባይነት ወደ ተፅዕኖ ፈጣሪነት፡ - የአንዲት ሀገር እውነተኛ ኃይል በጦር ሜዳ ብቻ የሚለካ ሳይሆን በዲፕሎማሲዋ በሚገኘው ክብር፣ በአጋርነቷ በሚፈጠረው እምነት እና በዓለም መድረክ በሚያስከብረው ብሔራዊ ጥቅም የሚረጋገጥ ነው። በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሀገራት ኃይል በወታደራዊ አቅም ብቻ ሳይሆን በውጭ ፖሊሲ ብቃት፣ በኢኮኖሚ ትስስር፣ በቴክኖሎጂ ትብብርና በቀጣናዊ ተፅዕኖ የሚለካበት ዘመን በመሆኑ ዲፕሎማሲ የብሔራዊ ልማትና ደኅንነት ማዕከላዊ መሣሪያ ሆኗል። ኢትዮጵያ ከዓድዋ ድል ጀምሮ እስከ አፍሪካ ሕብረት መናገሻነት ድረስ የዘለቀ የረጅም ጊዜ ታሪካዊ የዲፕሎማሲ አሻራ ያላት ናት። በአሁኑ ጊዜ የመደመር መንግሥት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት በሚያስጠብቅ አዲስ ምዕራፍ እየተመራ ይገኛል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ትልቅ ገበያ፣ የቀጣና መገናኛ ማዕከል እና የታዳሽ ኃይል አቅራቢ በመሆኗ አጀንዳ ተቀባይ ሳይሆን አጀንዳ ሰጪ ሆና በመውጣት ላይ ትገኛለች።

የብሪክስ (BRICS) ጥምረት፦ የኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆን በታሪካዊ የዲፕሎማሲ ምዕራፍ የሚታይ ስኬት ነው። ይህ ምርጫ የተመሠረተው በሀገሪቷ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ሲሆን፤ የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ አዳዲስ የውጭ ገበያዎችን በመፍጠር፣ የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን ለማስፋፋት፣ የኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማጠናከር እና አዳዲስ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።

በተለይም የቡድኑ የአዲስ ልማት ባንክ (NDB) ለመሠረተ ልማት፣ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ፣ ለኃይልና ለዲጂታል ልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ የሚያደርግ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል። ይህ አባልነት ለኢትዮጵያ ግብ ሳይሆን ወደ ልማት የሚወስድ ስትራቴጂካዊ መንገድ በመሆኑ ውጤታማነቱ በተቋማዊ አቅምና በውጤታማ ዲፕሎማሲ ይረጋገጣል።

ይህንን የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቅጣጫ የበለጠ ያጎላው በቅርቡ (እ.ኤ.አ. መስከረም 12 እና 13 ቀን 2026) በህንድ ኒውዴልሂ “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርንና ዘላቂነትን



18

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

መገንባት” በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው 18ኛው የብሪክስ ጉባዔ ነው። የጉባዔው የጋራ አቋም የብሪክስን ትብብር ከፖለቲካና ደኅንነት፣ ከኢኮኖሚና ፋይናንስ፣ ከሕዝቦች ግንኙነትና ከዘላቂ ልማት ጋር በማጣመር ዓለም አቀፉን ሥርዓት የበለጠ ፍትሐዊ፣ አካታችና የሁሉንም ድምፅ የሚያንጸባርቅ ለማድረግ ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት አሳይቷል።

በዚህ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብሪክስ ያለውን ካፒታል፣ ቴክኖሎጂና ገበያ በማቀናጀት በአባል ሀገራት ያሉ ሀብቶችና ዕድሎች የበለጠ እሴት እንዲያመነጩ ጠንካራ ትብብር እንዲጎለብት ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያም በማዕድን፣ በታዳሽ ኃይልና በኢንዱስትሪ ዘርፎች አባል ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር ለማስፋት ዝግጁ መሆኗን አሳውቀዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቋም በኢኮኖሚ ትብብር ብቻ የተገደበ ሳይሆን ኢትዮጵያ በቀጣናውና በዓለም አቀፍ መድረክ የሚኖራትን ስትራቴጂካዊ ሚና የሚያጎላ ነው። በተለይ ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር አካባቢ ያለውን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ከቀጣናው ሰላም፣ ደኅንነትና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ጋር በማያያዝ የባሕር በር ጉዳይን እንደ የረጅም ጊዜ ብሔራዊ ጥቅም ማስቀመጧ ይህንን ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባዔው ላይ “ለኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚው እና ወሳኙ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ከፍታን ከማላቅ ባሻገር የኢኮኖሚ ሽግግርን፣ የቴክኖሎጂ ትብብርን፣ የገበያ ትስስርንና የቀጣናዊ ሰላምን ከብሔራዊ ጥቅም ጋር ለማስተሳሰር የሚያገለግል ስትራቴጂካዊ መድረክ ነው። ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም በማስጠበቅ በብሪክስ የጋራ አቋም ውስጥ የአፍሪካና የግሎባል ሳውዝ ድምፅ እንዲጎላ የምታደርገው ተሳትፎ የዲፕሎማሲያዊ ከፍታዋን የሚያመላክት ምዕራፍ ሆኗል።

የአፍሪካ የኢኮኖሚ ውህደትና የገበያ ተደራሽነት፡ - የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) አህጉሩን በአንድ የንግድ ማዕቀፍ ለማስተሳሰር የተጀመረ ታሪካዊ ፕሮጀክት ነው። ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ በምግብ ማቀነባበርና በግብርና ምርት እሴት ጭመራ ያላት ተወዳዳሪነት፣ ይህንን ስምምነት በመጠቀም የአፍሪካ የምርት ማዕከል ለመሆን የሚያስችል ዕድል ፈጥሮላታል። የዚህ ቀጣና ስኬት ከሎጂስቲክስ ብቃት ጋር በጥብቅ የተያያዘ በመሆኑ ኢትዮጵያ የባቡር መስመር ግንባታን፣ የደረቅ ወደቦችን ማጠናከርና ዲጂታል የጉምሩክ ሥርዓትን በማዘመን የንግድና የሎጂስቲክስ ማዕከልነቷን እያጠናከረች ትገኛለች። በመሆኑም ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ከንግድ ስምምነት በላይ የሀገሪቷን የኢንዱስትሪ ፖሊሲና የክልላዊ ትስስር አጀንዳ የሚያሳድግ የልማት ስትራቴጂ ነው።

“ቅድሚያ ለጎረቤት” እና ቀጣናዊ መረጋጋት፡ - በ21ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ “ቅድሚያ ለጎረቤት” የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፤ የአፍሪካ ቀንድን ሰላም፣ የኢኮኖሚ ትስስርና የጋራ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ አቅጣጫ ሆኗል። ከጅቡቲ ጋር ያለው የባቡር፣ የመንገድና የኃይል ትስስር፤ ከኬንያ ጋር ያለው የንግድና የደኅንነት ትብብር እንዲሁም በሶማሊያና በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ውስጥ ያላት ሚና የቀጣናዊ መረጋጋት መሰረቶች ናቸው። ኢትዮጵያ በውኃ፣ በፀሐይና በጂኦተርማል ኃይል ያላት አቅም ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የምትፈጥረው ኢኮኖሚ ተደጋጋፊነት፣ የዲፕሎማሲያዊ መተማመንን የሚያጠናክር መሣሪያ ሆኗል። ይህ አቀራረብ ሰላም፣ ንግድና መሠረተ ልማት የተሳሰሩ የቀጣናዊ መረጋጋት ምሰሶዎች መሆናቸውን ያሳያል።

የባሕር በር እና የዘመናዊ ዲፕሎማሲ አቅጣጫ፡- የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የታሪክ ትዝታ ብቻ ሳይሆን የወደፊት የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የንግድ ተወዳዳሪነትና የቀጣናዊ ትስስር ስትራቴጂካዊ ጉዳይ ነው። ይህ አጀንዳ የግዛት ጥያቄ ሳይሆን የንግድ መተንፈሻና የሎጂስቲክስ ዋስትና መሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እያገኘ መጥቷል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከባህላዊ ዲፕሎማሲ ወደ ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና አረንጓዴ ልማት በተደገፈ ዲፕሎማሲ በመሸጋገር እመርታን እያሳየች ነው። ሀገሪቷ በታዳሽ ኃይልና በአካባቢ ጥበቃ ያላትን ልምድ በዓለም መድረኮች በማጋራት፣ የጋራ ብልፅግናን ማዕከል ያደረገ ዲፕሎማሲ በመገንባት ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያ ታሪካዊ የዲፕሎማሲ ቅርሷን በማስጠበቅ፣ የዘመኑን ዕድሎች በጥበብ በመጠቀም በአፍሪካና በዓለም መድረክ ያላትን ተፅዕኖ ለማሳደግ በፅኑ እየተጋች ነው።

የመሠረተ ልማት እመርታ ለሁለንተናዊ ብልፅግና

የአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ማኅበራዊ ለውጥ በጠንካራ መሠረተ ልማት ላይ የተመሠረተ ነው። በቅርብ ዓመታት የተከናወኑ የመንገድ መስፋፋት፣ የድልድዮችና የሎጂስቲክስ መስመሮች ግንባታ የሰዎችንና የሸቀጦችን እንቅስቃሴ በማፋጠን የንግድ ግንኙነትን አጠናክረዋል። በኃይል ዘርፍ የተከናወኑ ሰፊ የማመንጨትና የሥርጭት ፕሮጀክቶች ለኢንዱስትሪ፣ ለአገልግሎት ዘርፍና ለገጠር ልማት አዲስ ዕድሎችን የፈጠሩ ሲሆን፤ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የቴሌኮሙኒኬሽንና የዲጂታል መሠረተ ልማቶች መስፋፋት ዜጎች አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ አድርገዋል። እነዚህ እመርታዎች በግንባታ ብዛት ብቻ የሚለኩ ሳይሆኑ የሀገሪቷን አምራችነትና የዜጎችን የኑሮ ጥራት በማሻሻል ለሁለንተናዊ ብልፅግና ዘላቂ መሠረት እየጣሉ የሚገኙ ናቸው።

የኢትዮጵያ ከተሞች ትንሣኤ፤ ከጉስቁልና ወደ ልዕልና

ከተሞች የአንድ ሀገር ሥልጣኔ መለኪያና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ማዕከላት ናቸው። ዘመናዊ የከተማ ልማት ከኮንክሪት ግንባታ ወጥቶ ሰውን፣ ተፈጥሮና ልማትን በአንድ ማዕቀፍ የሚመለከት በመሆኑ በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሀገራዊ የለውጥ መለያ ሆኗል። ለዓመታት በብክለት የተሸፈኑ ወንዞች ወደ አረንጓዴ መናፈሻዎችና መዝናኛ ማዕከላት ሲቀየሩ፤ የከተማ አደባባዮችና የእግረኞች መንገዶች የዘመናዊ ከተማ ሕይወት መለያዎች ሆነዋል። ይህ የከተማ እድሳት በደረጃ ወደ ሌሎች ክልል ከተሞችና የገጠር ኮሪደሮች እየተስፋፋ በመሄድ የከተሞችን ውበት፣ ጽዳትና ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ማራኪ አካባቢዎችን እየፈጠረ ይገኛል።

ሰው ተኮርነት፤ የማኅበራዊ ልማት እመርታዊ ባህል

የኢትዮጵያ የልማት ጉዞ በኢኮኖሚ አኃዞች ብቻ ሳይሆን በዜጎች የኑሮ ጥራት መሻሻል ላይ የተመሠረተ ሰውን ያማከለ አቅጣጫ ይዟል። በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ለትምህርት፣ ለጤና እና ለአቅመ ደካሞች



19

ድጋፍ በማድረግ ልማት የሕዝብ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አሳይተዋል። ለአቅመ ደካማ ዜጎች የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች፣ የምገባ ማዕከላትና የማኅበራዊ ጥበቃ መር``ሃ ግብሮች በተጋላጭ ዜጎች ሕይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ ነው። ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ አቅም ማብቃትና የወጣቶች የሥራ ዕድል መርኃ ግብሮች ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች ያሳተፈ አካታች ልማት በመገንባት ላይ ይገኛሉ።

እነዚህ ድሎች ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ናቸው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ተመልክቶ አጢኖ ለጉዳዩ ሚዛን ሰጥቶ በምርጫው ለብልፅግና ፓርቲ ይሁንታውን ሲሰጥ ስኬቶቹን በዋቢነት ጠቅሶ ነው። ትናንት የጀመርከውን አስቀጥል፤ የበለጠ ሥራ የሚል መልዕክት በማስተላለፍ የሠራቸውን ተግባራት ቆጥሮና መዝኖ ድምጽ በመስጠት ቀጣዮቹን አምስት ዓመታት ሀገር እንዲመራ ፈቅዶለታል።

የኢትዮጵያ የተስፋ መንገድ - እንደ ማጠቃለያ

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያለፈችበት መንገድ በአንድ ወቅት የተጀመረ የፖለቲካ ሙከራ ብቻ ሳይሆን ወደ ተቋማዊ ዴሞክራሲ፣ ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትና ዓለም አቀፍ ተሰሚነት የሚያደርስ ሰፊ አገራዊ ጉዞ መሆኑን ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሚገባ አሳይቷል። ግንቦት 24 ቀን 2018 የተካሄደው ምርጫ ዜጎች ከሌሊት እስከ እኩለ ሌሊት ተሰልፈው የሰጡት ድምፅ ለአንድ ፓርቲ ብቻ የተሰጠ ውሳኔ ሳይሆን ላለፉት ዓመታት ለተመዘገቡ ስኬቶች፣ የሕዝብ እውቅና እና ለቀጣዩ የልማት ጉዞ የተሰጠ ኃላፊነት ጭምር ነው። ይህ ውሳኔ በ42 ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል በተካሄደ ግልጽና ሰፊ ውድድር የተገኘ በመሆኑ የመደመር መንግሥት የቀጣዮቹን አምስት ዓመታት ኃላፊነት የተረከበው ከጠንካራ የፖለቲካ ካፒታልና ከሕዝብ እምነት በመነሳት ነው። ይህ ውጤት በተጨባጭ ቁጥር ሲገለጽ ብልፅግና ፓርቲ 438 የፓርላማ መቀመጫዎች በማሸነፍ ያገኘው ግዙፍ አብላጫ ድምፅ የሕዝብን የቀጣይነት ምርጫ በግልጽ ያንጸባርቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀጣዩ አምስት ዓመታት የሚያገለግለውን የአዲስ መንግሥት ዘመናቸውን በመስከረም 2019 ዓ.ም መጀመራቸው በራሱ የኢትዮጵያ የተስፋ መንገድ ቀጣይነት ያለው ጉዞ መሆኑን የሚያረጋግጥ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው። የአዲስ መንግሥት ምስረታው ባለፉት ዓመታት በተገኙ ስኬቶች ላይ ተመሥርቶ ወደፊት የሚራመድ እንጂ ከባዶ የሚጀመር ጉዞ ባለመሆኑ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የተመሠረተው መንግሥት የተጣለውን መሠረት አጠናክሮ ወደ ላቀ ውጤት የሚያሸጋግርበት አዲስ ምዕራፍ ተደርጎ ሊታይ ይችላል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በአዲሱ ዘመን የፖለቲካ ብዝኅነትን አስተናግዶ የቀጠለ በመሆኑ የመንግሥት ሽግግሩ ራሱ የተገነባውን ዴሞክራሲያዊ ባህል በተግባር የሚያሳይ ምስክር ሆኗል።

የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ ጉዞ ገና በሂደት ላይ ያለ ቢሆንም፤ የተጣሉት መሠረቶች የወደፊቱን አቅጣጫ በግልጽ ያመለክታሉ። ገለልተኛ ምርጫ ቦርድ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የተጠናከረ የሲቪል ማኅበረሰብ ተሳትፎ፣ ነፃ የመገናኛ ብዙኃን ምኅዳርና የብዙኃን ድምፅ ያለበት ፓርላማ ኢትዮጵያ ከግጭት ወደ ውይይት፣ ከዜሮ-ድምር አስተሳሰብ ወደ ጋራ ሀገራዊ ግብ የምታደርገውን ሽግግር የሚያመለክቱ ናቸው። ይህ ባህል በአዲሱ መንግሥት ዘመንም ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው፣ የሕግ የበላይነትን ማስከበር፣ የፖለቲካ ምክክርን ማጎልበትና የወጣቶችና የሴቶች ተሳትፎን ይበልጥ ማስፋት የሚጠይቅ የቤት ሥራ ሆኖ ይቀጥላል።



20

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

በኢኮኖሚው ረገድ የተመዘገቡት ውጤቶች የመደመር መንግሥት ቀጣይነት ላለው ብልፅግና የጣለውን መሠረት በግልጽ ያሳያሉ። አገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ኢትዮጵያን ከመንግሥት መር ወደ በግሉ ዘርፍ ወደሚደገፍ ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ በማሸጋገር በተከታታይ ዓመታት ከሥምንት በመቶ በላይ ዕድገት እንድታስመዘግብ አስችሏታል። የስንዴ አብዮቱ ሀገሪቷን ከውጭ ጥገኝነት ወደ ራስን መቻል ያሸጋገረ ሲሆን፣ የሌማት ትሩፋት መርኃ ግብር የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን እያረጋገጠ፤ የአረንጓዴ አሻራ ደግሞ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ እየገነባ ይገኛል። እነዚህ ስኬቶች የግብርናውን ዘርፍ ከማጠናከር ባሻገር ኢንዱስትሪን፣ ማዕድንን፣ ቱሪዝምና ዲጂታል ኢኮኖሚን ባካተተ ብዝኅ የዕድገት ስልት ላይ የተመሠረቱ በመሆናቸው ለቀጣይ የልማት ምዕራፍ ጠንካራ መሠረት ጥለዋል።

የኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፋብሪካዎች የማምረት አቅም ማደግ አንስቶ እስከ ወጪ ንግድ መስፋፋት ድረስ ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ ነው። የ’ኢትዮጵያ ታምርት’ ንቅናቄና የተኪ ምርት ፖሊሲ ሀገሪቷን ከሸማችነት ወደ አምራችነት እያሸጋገሩ ሲሆን፤ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ መስፋፋትና ለቀጣናዊ ትብብር ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በተመሳሳይ የማዕድን ዘርፍ አዲስ መነቃቃት እያሳየ፣ ቱሪዝምም በ”ገበታ ለሸገር”፣ በ”ገበታ ለሀገር” እና በ”ገበታ ለትውልድ” ፕሮጀክቶች አማካኝነት ወደ አዲስ የኢኮኖሚ ምንጭነት እየተቀየረ ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂም ቴክኖሎጂን የኢኮኖሚና የማኅበረሰብ ለውጥ ዋና ማፋጠኛ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በዲፕሎማሲው መስክ ኢትዮጵያ ከአጀንዳ ተቀባይነት ወደ አጀንዳ ሰጪነት እየተሸጋገረች መሆኑን የብሪክስ አባልነትዋ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ተጠቃሚነቷና “ቅድሚያ ለጎረቤት” ፖሊሲዋ ያሳያሉ። የባሕር በር ጉዳይ እንደ ስትራቴጂካዊ ብሔራዊ ጥቅም መነሳቱም ሀገሪቷ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚና የደኅንነት ራዕይዋን በጥበብ እየገነባች መሆኑን ያመለክታል። ከመንገድና ከኃይል መሠረተ ልማት ማስፋፋት እስከ ከተሞች ትንሣኤ እንዲሁም ከማኅበራዊ ጥበቃ መርኃ ግብሮች እስከ ትውልድ ማነጽ ድረስ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ልማት የሕዝብ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን በተግባር አረጋግጠዋል።

እነዚህ ሁሉ ስኬቶች የተገኙት ባለፉት ዓመታት ቢሆንም የሕዝብ ተስፋ ግን ወደ ኋላ የሚመለከት ሳይሆን ወደፊት የሚሻገር ነው። ሕዝቡ ለብልፅግና ፓርቲ ዳግም ድምፁን የሰጠው የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ ያልተነኩ ዕድሎች ወደ ተጨባጭ ውጤት እንዲቀየሩ ነው። በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሕዝብ ተስፋ የሚያነጣጥረው የምርጫ ተቋማት ነፃነት ይበልጥ እንዲጠናከር፣ የፖለቲካ ምክክር ባህል ወደ ተግባር እንዲቀየር፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ሁለተኛ ምዕራፍ ወደ ተጨባጭ የሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሸጋገር፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ሙሉ አቅም እንዲደርሱ፣ የማዕድን ዘርፍ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ፣ የቱሪዝም መዳረሻዎች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እንዲላበሱ እና የዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይ ወደ ተግባር እንዲለወጥ ነው።

ከዚህም በላይ የባሕር በር ጉዳይ በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እልባት እንዲያገኝ፣ የቀጣናዊ ትብብር ወደ ዘላቂ ሰላምና የጋራ ብልፅግና እንዲያመራ፣ የብሪክስና የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና አባልነት ለአገር ውስጥ አምራቾችና ላኪዎች ተጨባጭ ጥቅም እንዲያስገኝ በሕዝቡ ዘንድ ጽኑ ተስፋ አለ። እነዚህ ተስፋዎች ከምኞት ያለፉ፣ ባለፉት ዓመታት በተግባር በታዩ ውጤቶች ላይ የተመሠረቱ በመሆናቸው የመደመር መንግሥት በቀጣዩ ዘመንም ተመሳሳይ ቁርጠኝነት ይዞ እንደሚቀጥል ሕዝቡ በጽኑ ያምናል።

ለዚህም መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የተከናወነው የመንግሥት ምስረታ ለኢትዮጵያዊያን ልዩ ትርጉም ያለው ነው፤ ምክንያቱም ከአዲሱ ዓመት መባቻ ጋር የተገጣጠመ በመሆኑ “አዲስ ዓመት፣ አዲስ ተስፋ” የሚለውን ብሔራዊ መንፈስ ከመንግሥት ቀጣይነት ጋር በማስተሳሰር ልዩ ብሔራዊ ትርጉም ይላበሳል። ይህ አጋጣሚ ሕዝብ ላሳየው ድምፅና ላቀረበው አደራ ምላሽ የሚሰጥበት፤ መንግሥት ራሱን ለቀጣይ ኃላፊነት ያዘጋጀበት ነው።

አዲስ የተመሠረተው መንግሥት ትኩረት ሊደረግባቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ቀጣይ ምዕራፍ ወደ ዜጎች ተጨባጭ ተጠቃሚነት መቀየር፣ የሰላምና የብሔራዊ መግባባት ሂደቱን ማጠናከር፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይን



21

ወደ ሙሉ ትግበራ ማሸጋገር ይገኙበታል።

ተቋማት እየጠነከሩ፣ ኢኮኖሚው እየተመነደገ፣ ዲፕሎማሲው እየተከበረ በሄደ ቁጥር ኢትዮጵያ ለራሷም ለቀጣናውም ተስፋ ሆና የመቀጠል ዕድሏ እየሰፋ ይሄዳል። ሕዝብ የሰጠው ድምፅ ለዚህ ተስፋ የተሰጠ አደራ በመሆኑ የቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ስኬት የሚለካው ይህ አደራ በምን ያህል ታማኝነትና ውጤታማነት ወደ ተግባር ተቀየረ በሚለው ይሆናል።

አዲሱ የመንግሥት ዘመን በተለይ ወጣቱን በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የማሳተፍ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ የመደመር ራዕይ ወደ ተጨባጭ የትውልድ ብልፅግና የሚቀየርበት ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ ሊታይ ይችላል።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የተስፋ መንገድ የተጀመረው ጉዞ ማብቂያ ሳይሆን፤ በተጣለው ጠንካራ መሠረት ላይ ተገንብቶ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያመራ ቀጣይ ምዕራፍ ነው። ዴሞክራሲያዊ አዲሱ የመንግሥት ዘመን በተለይ ወጣቱን በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የማሳተፍ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ የመደመር ራዕይ ወደ ተጨባጭ የትውልድ ብልፅግና የሚቀየርበት ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ ሊታይ ይችላል።



22

ፖለቲካ

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ከዓባይ እስከ ቀይ ባህር የዘለቀው ፍጥጫ



23

በጌታቸው ያለው

የታሪክ እና የመልክዓ ምድር መገናኛ

የሰው ልጅ ሥልጣኔ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ውኃ የመኖርና ያለመኖር፣ የዕድገትና የኃይል ሚዛን ዋነኛ መወሰኛ ሆኖ ቆይቷል። የሰው ልጅ ሥልጣኔ እና የውኃ አካላት ማለትም ወንዞች፣ ባሕሮችና ውቅያኖሶች ያላቸው ቁርኝት እጅግ ጥልቅና የማይነጣጠል ነው። ታሪክ እንደሚያስረዳው ታላላቅ የዓለም ሥልጣኔዎች ዕድገት የታየው በወንዞች አልያም በባህር ዳርቻ ላይ ነው።

የሰው ልጅ ሥልጣኔ እና የውኃ አካላት ያላቸውን ዓበይት ትስስሮች በማሳያነት ማንሳት ይቻላል። በታሪክ የሜሶፖታሚያ ሥልጣኔ በሚል የምትታወቀው የአሁኗ ኢራቅ ሥልጣኔ መፈጠር ምክንያት የሆኑ የጤግሮስና የኤፍራጠስ ወንዞች ናቸው። ለጥንታዊ የሕንድ ሥልጣኔ መነሻ የሆነው ደግሞ ታላቁ የኢንዱስ ወንዝ ሸለቆ ነው። የአረንጓዴ ወንዝ (ኋንግ ሄ) ለጥንታዊው የቻይና ሥልጣኔ መከሰት መሠረት የጣለ ነው። በተመሳሳይ የዓባይ ወንዝ ለጥንታዊ የግብፅ ሥልጣኔ መገኛና ህልውና መሠረት ነው። ወንዙ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ይዞት የሚመጣው ለም አፈር ለግብርና ምርታማነት ወሳኝ ነበር።



24

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

በምሥራቅ በኩል አፍሪካን ከሚያዋስኗት ግዙፍ የውኃ አካላት መካከል ቀይ ባህር በቀዳሚነት ይነሳል። ይህ ባህር በሰሜን እና በምሥራቅ አፍሪካ እንዲሁም በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል የሚገኝ የጂኦ-ኢኮኖሚክስ፣ የውኃ ደህንነት እና የባህር ላይ አድማስን ለዘመናት አቆራኝቷል። ቀይ ባህር በአፍሪካ እና በእስያ መካከል የሚገኝ፣ ከህንድ ውቅያኖስ የተገነጠለ ጠባብ የባህር አካል ሲሆን በስዊዝ ቦይ (Suez Canal) በኩል ከሜዲትራኒያን ባህር ጋር የተገናኘ ነው።

ወዲህ ደግሞ 6 ሺህ 650 ኪሎ ሜትር ያህል የተዘረጋው ከምሥራቅ እና መካከለኛው ምሥራቅ አፍሪካ ተነስቶ ወደ ሜዲቴራኒያን ባህር የሚፈሰው ታላቁ የዓባይ ወንዝ 11 ያህል የአፍሪካ አገራትን በጋራ ኃብት አስተሳስሮ ለሺህ ዓመታት ዘልቋል።

ዓባይ እና ቀይ ባህር በተፈጥሮ የማይገናኙ፣ ሙሉ በሙሉ የተለያዩ እና የተነጣጠሉ የውሃ አካላት እንደሆኑ የሚታዩ ቢመስሉም፤ በዘመናዊ ጂኦፖለቲካ እና ስትራቴጂያዊ ትስስር ውስጥ ጥልቅ ታሪካዊ ቁርኝት ያላቸው የው``ኃ `አካላት ናቸው። እነዚህ ሁለት ታላላቅ የውኃ አካላት የሰሜን ምሥራቅ እና የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዎችን የታሪክ፣ የኢኮኖሚ እና የደህንነት ሁኔታ በየዘመኑ መልክ ሲያሲይዙ ኖረዋል።

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕዝቦች የሕይወት መሠረት የሆነው የዓባይ ወንዝ እና የዓለም አቀፍ የንግድና የደህንነት ወሳኝ መተላለፊያ የሆነው ቀይ ባህር የቀጣናውን ጂኦፖለቲካዊ ምኅዳር አንዴ ሲያሞቁት ሌላ ጊዜ ሲያቀዘቅዙት ተስተውለዋል። እነዚህ ሁለት ውኃዎች ለዘመናት በተለያዩ የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ገጽታዎች ሲቃኙ ቢቆዩም አሁን ግን የማይነጣጠሉ የስትራቴጂያዊ ተፎካካሪነት እና የጂኦ- ኢኮኖሚክስ ቁልፍ ማዕከላት ሆነዋል።

በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር ዙሪያ የሚታየው ፈጣንና ጥልቅ የጂኦ-ፖሊቲካዊ ተለዋዋጭነት የኢትዮጵያ፣ የግብፅ እና የቀጣናውን ሀገራት የወደፊት ዕጣ ፈንታ በመሠረታዊነት እየቀየረው ይገኛል። የኢትዮጵያ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አማራጭ የባህር መዳረሻ ፍለጋ ከቀላል የንግድ አማራጭነት አልፎ የሀገሪቷን ብሔራዊ ደህንነት እና የማክሮ ኢኮኖሚ ህልውና የሚወስን ስትራቴጂያዊ ግዴታ ሆኗል።

በሌላ በኩል የዓባይ ወንዝ የውኃ አስተዳደር ከቅኝ ግዛት ዘመን የብቸኝነት እና የበላይነት ውሎች ተላቆ ወደ ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ የጋራ አጠቃቀም ሕጋዊ ማዕቀፍ እየተሸጋገረ ይገኛል። በዚህ ጽሁፍ የሁለቱ ወሳኝ የውኃ አካላት ማለትም የዓባይ ወንዝና የቀይ ባህርን ወግ ከወቅታዊ የጂፖለቲካ ስትራቴጂ አኳያ የሚዳሰስ ይሆናል።

ሁለቱ ውኃዎች ለምን የግጭት ማዕከል ሆኑ?

የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ተፋሰስ ትልቅ የሆነ የጂኦ-ፖለቲካዊ አሰላለፍ ለውጥ እያስተናገዱ ነው። በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የዓባይ ወንዝ አለመግባባት ከአፍሪካ እጅግ ወሳኝ ከሆኑ የጂኦፖለቲካ እና የውኃ ደህንነት ጉዳዮች አንዱ ሲሆን፣ ጉዳዩ ከግድቡም አልፎ ሰፊ አንድምታ ያለው ነው። የባህር ላይ ንግድና ደህንነት፣ የመንግሥታት ሉዓላዊነት፣ የኃይል አቅርቦት ትስስር፣ የውኃ ኃብት አስተዳደር እና ቀጣናዊ የመሠረተ-ልማት ጉዳዮች እርስ በእርስ እየተሳሰሩ መጥተዋል።

በእርግጥም ሰሜን-ምሥራቅ አፍሪካ ዓባይ፣ ቀይ ባህር፣ ኢትዮጵያ የተለያዩ የባህር መውጫዎችን ለማግኘት የምታደርገው ጥረት፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንዲሁም የግብፅ፣ የሱዳን፣ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የደህንነት ሥጋቶች እርስ በእርስ በተጠላለፈ መልኩ የተሳሰሩበት ውስብስብ የሆነ ዲፕሎማሲያዊ የቼዝ ጨዋታ መድረክ ሆኗል።

የዓባይ ወንዝ እና ቀይ ባህር የግጭት ማዕከል የሆኑበት አንዱ ምክንያት በምሥራቅ አፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ያለውን የኃይል ሚዛን፣ የኢኮኖሚ ህልውና እና የጂኦፖለቲካ የበላይነትን ስለሚወስኑ ነው። እነዚህ ሁለት የተፈጥሮ ፀጋዎች ለቀጣናው ሀገራት የመኖርና ያለመኖር ዋስትና መሆናቸው የፍጥጫ አምባ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

ቀይ ባህርና የዓባይ ወንዝ በአፍሪካ ቀንድና በመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና የጂኦ-ፖለቲካዊ ፉክክር፣ የኢኮኖሚ ህልውና እና የብሔራዊ ደኅንነት ቁልፍ መገናኛዎች በመሆናቸው ዋነኛ



25

ረገድ የኢትዮጵያ አስተዋጽኦ የላቀ እንደሆነ ግልጽ አድርገዋል። ዕውነታውን የተረዳ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ማሳየት ከተቻለ ፍትሃዊ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የሚችል ስምምነት ላይ መድረስ ይቻላል የሚል እምነት አላቸው።

በቀጣናው የሕዝብ ቁጥር በፍጥነት ማደግ እና የኢንዱስትሪ መስፋፋት የው`ኃ ኃብት ፍላጎትን በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮታል። በተፋሰሱ ሀገራት የሕዝብ ቁጥር መጨመር (በተለይም በኢትዮጵያ፣ በግብፅ እና በሱዳን ወደ 310 ሚሊዮን ሕዝብ መኖር) ቁጥሩ በፍጥነት ማደጉ የውኃ፣ የምግብ እና የኃይል ፍላጎትን በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር አድርጎታል። ይህ ደግሞ በቀጣናው የሚስተዋለው የጂኦ-ፖለቲካዊ ፉክክር፣ የዓባይ ወንዝ የውኃ አጠቃቀም እና የቀይ ባህር የባህር በር ይዞታ ትስስር የወቅቱ ታላቅ የፖለቲካና የደህንነት የስበት ማዕከል አድርጎታል።

የኢትዮጵያ የመልማት ፍላጎት (ፍትሐዊ የውኃ አጠቃቀም ጥያቄ) በግብፅ በኩል በበጎ አለመታየቱ ሌላው ለወጥረቱ መጦዝ መንስኤ የሆነ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ በሚሊዮኖችን የሚቆጠሩ ዜጎቿን ከጨለማ ለማውጣትና ለኢንዱስትሪ ዕድገቷ መፋጠን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ገንብታ ማጠናቀቋና ወደ ሥራ ማስገባቷ የኃይል ሚዛኑን ቀይሮታል። ከውኃ ፖለቲካና ከቆየ የጠቅላይነት መንፈስ ጋር ተያይዞ ጉዳዩ ግብጽን አላስደሰተም። ግን ደግሞ ሃቁ ይኸው ነው። መቀበል ግድ ሲሆን ሸብረክ ብሎ መቀበል ይገባልና።

በአንፃሩ ግብጽ ሃቁን ተቀብላ ወደ ዕውነተኛ ድርድር ከመምጣት ይልቅ የስትራቴጂ ለውጥ ማድረግን መርጣለች። ግብፅ ከግድቡ መጠናቀቅ በኋላ የዓባይን ጉዳይ ከውኃ ድርድር ባለፈ በቀይ ባህር እና በአፍሪካ ቀንድ በኩል የስትራቴጂያዊ ተፅዕኖ መፍጠሪያ አድርጋ የግጭት ማዕከል የሆኑበት ሌላው ምክንያት ነው። በተለይ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ያለው ታሪካዊና ወቅታዊ ፍጥጫ የሁለቱን የውኃ አካላት ስትራቴጂያዊ ትስስር ይበልጥ አጉልቶታል።

እዚህ ላይ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የገነባችው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል አቅርቦቷን ለማሳደግ ወሳኝ ቢሆንም፣ የታችኛው ተፋሰስ ሀገር የሆነችው ግብፅ ግን የውኃ እጥረት ይፈጥርብኛል በሚል እንደ ህልውና ስጋት ትመለከተዋለች። ይህ ደግሞ የተፋሰሱን የውኃ ፖላቲካ (Hydro-politics) ወደለየለት ፍጥጫ ወስዶታል።

በእነዚህ የውኃ አካላት ሌላው የግጭት መንስኤ እየሆነ ያለው የቅኝ ግዛት ዘመን ውሎች የፈጠሩት አግላይነት እና ኢ-ፍትሃዊነት ነው። በፈረንጆቹ 1929 እና 1959 የተደረጉት የዓባይ (ናይል) ውኃ ስምምነቶች ለግብፅ እና ለሱዳን ሰፊ የውኃ ድርሻ የሰጡና የላይኛውን ተፋሰስ ሀገራት (በተለይ 85% ውኃ አመንጪ የሆነችውን ኢትዮጵያን) ያገለሉ በመሆናቸው ለዘመናት ለዘለቀው አለመግባባት መነሻ ሆነዋል።

የአሜሪካ የቀድሞ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናጊ በቅርቡ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምለልስ ግልጽ እንዳደረጉት ግብፅ በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን ላይ በተመሠረቱ አቋሞች ላይ ከመዳከር ይልቅ አሁን ላይ በዓባይ ተፋሰስ እየተከሰቱ ያሉትን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ስትራቴጂያዊ እውነታዎች ተገንዝባ አቀራረቧን ማስተካከል ይኖርባታል።

በቀጣናው ያለው የኃይል ሚዛን እንደተቀየረና ኢትዮጵያም ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ዕድገት እንዳሳየች ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚጠቅም አውስተዋል። እናም ግብጽ ዘመኑን የዋጀ የትብብር መንፈስ ይዛ መቅረብ ከቻለች “ሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚ የሚያደርግ” (win-win) ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ሊያግዝ እንደሚችል አመላክተዋል።

መቀመጫቸውን ኦስሎ ያደረጉት የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተንታኝ መሐመድ ኸይር ኦመር በጉዳዩ ላይ ቲቦር ናጊ ካነሱት ሃሳብ ጋር የሚጣጣም ምልከታ አላቸው። ከፈርስት ፖስት (First Post) ጋር በነበራቸው ቆይታ የግብጽ ሥልጣኔ ከዓባይ ውጭ ሊታሰብ እንደማይችልና በዚህ



26

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

መውሰድ ጀምራለች፤ ኢትዮጵያን ለመጫንና በዓባይ ላይ ያላትን ይዞታ ለማስከበር እንደ ስልት እየተጠቀመችበት ትገኛለች።

በተመሳሳይ የቀይ ባህር ስትራቴጂያዊ እና የላቀ የንግድ ጠቀሜታ እና ቁልፍ የዓለም አቀፍ ንግድ መስመር መሆኑ ከቀጣናው ሀገራት ባሻገር የስበት ማዕከል አድርጎታል። በተለይም የባብ ኤል መንደብ የባህር ወሽመጥ እና የስዊዝ ካናል ከዓለም አቀፍ የባህር ንግድ ከ10-15 በመቶ ያህሉ የሚስተናገድበት በመሆኑ ለኃያላን ሀገራት እና ለባህረ ሰላጤው መንግሥታት የጥቅም መናኸሪያ ነው። በዚህ ላይ የበላይነት ለመያዝ የሚደረገው ሩጫ በቀጣናው ውጥረት እንዲባባስ እያደረገ ይገኛል።

አሁን ላይ ነገሩን ወደ ጡዘት የወሰደው ጉዳይ የባህር በር ፍላጎት እና የወደብ ፖለቲካ ሆኖ እናገኘዋለን። ኤርትራ እ.አ.አ በ1993 ነጻነቷን ካወጀች በኋላ ኢትዮጵያ የባህር በር አልባ ሆና ቆይታለች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ከመጣው ሕዝቧ ብሎም ኢኮኖሚያዋ ጋር የሚመጣጠን የባህር በር እና ወደብ እንደሚያስፈልጋት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዓለም ይወቀው ብለዋል። በጥቅሉ ኢትዮጵያ የራሷ የባህር በር እና ወደብ ያስፈልጋታል ማለት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመደመር መንግሥት መፅሃፋቸው ገጽ 61 ላይ “ኢትዮጵያ በምትገነባው ኢኮኖሚ ልክ የሆነ ወደብ ማግኘት አለባት። የአካባቢ ሀገሮች የኢኮኖሚ ዕድገት ከኢትዮጵያ ጋር መሳ ለመሳ የሚሄድ ባለመሆኑ የቴክኖሎጂ፣ የሎጂስቲክስ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የብቃት ችግር ሊያጋጥም ይችላል። ስለዚህም ራስዋ የምታስተዳድረው፤ በሚያድገው ኢኮኖሚዋ ልክ የምታሰፋውና የምታዘምነው የወደብ መሠረተ ልማት ያስፈልጋታል” ሲሉ የኢትዮጵያን መሻት በግልጽ አስቀምጠዋል። ይህ የኢትዮጵያ ጥያቄ በቀጣናው አዳዲስ ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫን ቀስቅሷል። ከግብጽ እስከ ኤርትራና ሶማሊያ ኩርፊያን አስከትሏል።

በኢትዮጵያ እና በቡርኪና ፋሶ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዴቪድ ሺን ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲን የባህር በር ለማግኘት ብቸኛ እና አስተማማኝ መንገድ አድርጋ መውሰዷን አንስተው ይህ ጥረት ስኬታማ እንዲሆን ከጎረቤት ሀገራት ጋር ወሳኝ ስምምነቶች ማድረግና



27

ላይ ሙሉ በሙሉ በመተሳሰሩ የሁለቱ ውኃዎች መስተጋብር እና የኃይሎች መቧደን (የመክበብ ስትራቴጂ ማለት ይቻላል) ፈጥሯል። ግብፅ በህዳሴው ግድብ ሳቢያ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን ተቃውሞ ለማጠናከር፣ ከቀይ ባህር ወሰን ተጋሪ ሀገራት (ከሶማሊያ እና ኤርትራ) ጋር ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን እያጠነከረች ትገኛለች። ይህ አካሄድ በኢትዮጵያ ዘንድ “የመክበብ ስትራቴጂ” (Circumscription) ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን፤ የዓባይን ውዝግብ ወደ ቀይ ባህር የ`ኃይል ፉክክር እያሸጋገረው ይገኛል።

እነዚህ ሁለት ተደራራቢ የውኃ-ፖለቲካ ግንባሮች አንድ ላይ ሆነው የዓባይ ተፋሰስ እና የቀይ ባህር የንግድ መስመሮችን በመቆጣጠር በምሥራቅ አፍሪካ ያለውን ሰፊ የብሔራዊ ደህንነት ስሌት የሚገልጹበት ዓውድ ከትብብር ይልቅ ውጥረት፤ ከሠላም ይልቅ ግጭት የነገሰበት ድባብ አድርጎታል።

ውኃን መነሻ ያደረጉ ግጭቶች

በዓለም ላይ ውኃን መነሻ ያደረጉ ግጭቶች (Water Conflicts) በተፈጥሮ ኃብት እጥረት፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በሕዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት በየጊዜው እየተባባሱ የመጡ አሳሳቢ ችግሮች ናቸው። ው`ኃ ውስን የተፈጥሮ ኃብት እንደመሆኑ መጠን የውኃ አካላትን በሚጋሩ ሀገራት ወይም በአንድ ሀገር ውስጥ ባሉ ማኅበረሰቦች መካከል አለመግባባቶች ሲፈጥር ይስተዋለል።

ከግትርነት የራቀ የፖለቲካ ማስተካከያዎች እንደሚያስፈልጉ ጠቁመዋል። የራቁም የቀረቡም ጎረቤት ሀገራት ከኩርፊያ ወጥተው በሰጥቶ መቀበል መርህ ለጋራ ተጠቃሚነት ሊሰሩ እንደሚገባም ያነሳሉ።

የፀጥታ ሥጋቶች እና የኃያላን ፉክክር ደግሞ በቀይ ባህር ቀጣና ሌላው የቀውስ መንስኤ ሆኖ ቀጥሏል። አንሳር አላህ (በስፋት ሁቲ) በመባል የሚታወቀው የየመኑ አማፂ በባህር መስመሩ ላይ የሚፈጽመው ጥቃት እና እንደ አሜሪካ፣ ቻይና፣ እንዲሁም የባህረ ሰላጤው ሀገራት በባህር ዳርቻዎች ላይ የጦር ሰፈር ለመመስረት የሚያደርጉት ፉክክር ቀጣናውን ይበልጥ ተጋላጭ አድርጎታል።

የዓባይ ወንዝ እና የቀይ ባህር ፖለቲካ አሁን



28

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

በውኃ ምክንያት የሚፈጠሩ ግጭቶች በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ከፍሎ ማየት ይቻላል። የመጀመሪያው በሀገር ውስጥ የሚከሰቱ ማኅበራዊ ግጭቶች (Intrastate Conflicts) ሲሆኑ በአንድ ሀገር ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ማኅበረሰቦች፣ ክልሎች ወይም የሥራ ዘርፎች መካከል የሚቀሰቀሱ ግጭቶች ናቸው።

ሁለተኛው ግን ደግሞ በጣም ወሳኝ ው`ኃን መሠረት ያደረጉ የግጭት ዓይነቶች በሀገራት መካከል የሚፈጠሩ ዓለም አቀፍ ግጭቶች (Interstate Conflicts) ናቸው። እነዚህ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችንና የውኃ አካላትን በሚጋሩ ሀገራት መካከል የሚፈጠሩ ውጥረቶችና ግጭቶች ናቸው፤ ማሳያዎችን እናንሳ።

የዓባይ ወንዝ ተፋሰስ ውጥረት አንዱና ተጠቃሽ የውሃ ውዝግብ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በላይኛው እና በታችኛው የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት በወንዙ ውኃ አጠቃቀምና አስተዳደር ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶች የድንበር ተሻጋሪ የውኃ ግጭቶች አካል ናቸው። ሌላው የኢንዱስ ወንዝ ውዝግብ በሚል የሚታወቀው በሕንድ እና በፓኪስታን መካከል ከ1960ዎቹ ጀምሮ በወንዙ አጠቃቀምና በግድቦች ግንባታ ዙሪያ የሚነሳውና እስከ አሁንም የቀጠለው አለመግባባት ይጠቀሳል።

በተመሳሳይ የኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች ውጥረት በቱርክ፣ በሶርያ እና በኢራቅ መካከል የውኃ ፍሰትን መሠረት አድርገው የሚነሱ የይገባኛል ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል። የሄልማንድ ወንዝ ውዝግብ ደግሞ በአፍጋኒስታንና በኢራን መካከል የሚገኘውን ወንዝ በፍትሃዊነት የመጠቀም ጉዳይ የዚህ መገለጫ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።

ወዲህ ወደ አፍሪካ መለስ ስንል ደግሞ ውኃን መሠረት ያደረጉ ሁለቱንም ዓይነት ግጭቶች ስታስተናግድ እንታዘባለን። አፍሪካ ውስጥ በሰው ሠራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት በውኃ ዙሪያ የሚስተዋሉ ግጭቶች እና አለመግባባቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፉ መጥተዋል።

በዚህ ረገድ በአፍሪካ የጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረት መንስኤ እንደሆኑ ከሚነገርላቸው በዋናነት የዓባይ ወንዝ ተፋሰስ አንዱ ሲሆን፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን ተከትሎ በውኃ አጠቃቀም ዙሪያ የነበረውን የቆየውን የኃይል ሚዛን በሚገርም መልኩ የቀየረ ሆኗል። ይህን ተከትሎ በኢትዮጵያ እና እንደ ግብፅ ባሉ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መካከል ውጥረት ነግሷል። ሌሎች መሰል ግጭቶችም በአህጉሪቱ የታዩ ቢሆንም በዋናነት ግን ለጂኦ- ፖለቲካዊ ውጥረት መነሻ የሆኑትን ብቻ እናንሳ።

የኦካቫንጎ ወንዝ ተፋሰስ

የኦካቫንጎ ወንዝ በደቡብ ምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ እና ሦስት የቀጣናው አገራት (አንጎላ፣ ናሚቢያ እና ቦትስዋና) የሚጋሩት የወንዝ ተፋሰስ ነው። ወንዙ በቦትስዋና ኦካቫንጎ፣ በአንጎላ ኩባንጎ እንዲሁም በናሚቢያ ካቫንጎ በሚሉ ስሞች ይታወቃል።

ኦካቫንጎ በደቡባዊ አፍሪካ አራተኛው ረጅሙ የወንዝ ተፋሰስ ሲሆን፤ ወደ ደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ 1 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር እርዝማኔን ይሸፍናል። ይህ ወንዝ መነሻውን በአንጎላ ደጋማ አካባቢዎች በማድረግ ከባህር ወለል በላይ በ1 ሺህ 300 ሜትር ከፍታ ላይ የሚነሳ ነው። ወንዙ ወደ ደቡብ በማምራት የአንጎላ እና ናሚቢያ ከፊል ድንበር ተንተርሶ ወደ ቦትስዋና ይገባል።

ኦካቫንጎ ወደ ባህር የሚፈስበት መውጫ የሌለው በመሆኑ በካላሃሪ በረሃ ውስጥ በሚገኝ ዝግ ተፋሰስ (Endorheic Basin) ውስጥ ወደሚገኘው የኦካቫንጎ ዴልታ ማለትም ረግረጋማ አካባቢ ይፈስሳል። የኩይቶ ወንዝ ደግሞ የኦካቫንጎ ዋነኛ ገባር ወንዝ ነው።

የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት በሆኑት አንጎላ እና ናሚቢያ በኩል የወንዙን ውኃ የመጠቀም ሰፊ ፍላጎት መኖር እንዲሁም በቦትስዋና በኩል በወንዙ ሥነ-ምህዳር እና በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ካላት ጥገኝነት የተነሳ አለመግባባት ተፈጥሮ ነገሮች ወደ ግጭት እንዳያመሩ ስጋት ደቅኗል።

ናሚቢያ እና ቦትስዋና ሁለቱም ድርቅ የሚጠቃቸው ሀገራት እንደመሆናቸው መጠን በኦካቫንጎ ወንዝ ውኃ አጠቃቀም ዙሪያ የግጭት ሥጋት አጥልቶባቸዋል። ናሚቢያ ወደ 300 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የውኃ ቦይ የገነባች ሲሆን፤ የድርቁን ጫና ለመቋቋም እንዲረዳት ከወንዙ ውኃ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ለማድረስ የሚያስችል የ250 ኪሎ ሜትር የቦይ መስመር ዝርጋታ የፕሮጀክት ትልም አቅርባለች።

ይሁን እንጂ የታችኛው ተፋሰስ ሀገር የሆነችው ቦትስዋና የኦካቫንጎ ረግረጋማ አካባቢን (Okavango Delta) ለቱሪዝም ገቢ እና ለውኃ



29

ምንጭነት በስፋት የምትጠቀምበት በመሆኑ የናሚቢያን የመልማት ፕሮጀክት በሥጋት ትመለከተዋለች። የቦትስዋና የውኃ ጉዳዮች መምሪያ እንደሚለው በኦካቫንጎ ወንዝ ውስጥ ካለው ውኃ 97 በመቶው በትነት ስለሚጠፋ ሀገሪቱ ተጨማሪ ውኃ ማጣት አትሻም። ከዚህ አኳያ የናሚቢያን በውኃው የመልማት ፍላጎት የሥጋት ምንጭ አድርጋ ትወስደዋለች።

ናሚቢያ በበኩሏ ከወንዙ ፍሰት ውስጥ ግማሽ በመቶውን ብቻ ወደ ቀሪው የአገሪቷ ክፍሎች ለማዳረስ እንደምትሻ እና በግዛቷ በሚያልፈው ውኃ ላይ የመጠቀም መብት እንዳላት ትከራከራለች። ጉዳዩ ከክርክር አልፎ ወደ ቀውስ የማደግ አዝማሚያው እየሰፋ በመሄዱ ወደ ግጭት እንዳይገቡ ሥጋት ደቅኗል።

ለጉዳዩ የተለየ ትኩረት በመሥጠት አንጎላ፣ ናሚቢያ እና ቦትስዋና እ.አ.አ በ1994 የኦካቫንጎ ወንዝ ተፋሰስ ቋሚ የውኃ ኮሚሽን (Permanent Okavango River Basin Water Commission) በማቋቋም ግጭቶችን ማስወገድ የሚያስችል የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል። ይህ ኮሚሽን የኦካቫንጎ ወንዝ ኃብቶችን በተሻለ መንገድ ተጋርተው እንዲጠቀሙ ለሦስቱ ሀገራት ምክረ-ሃሳብ የመስጠት ኃላፊነት ተሰጥቶታል። እናም ሀገራቱ የጋራ ኃብት በፍትሃዊነት መጠቀም የሚያስችላቸውን ኮሚሽን አቋቁመው ከግጭት ይልቅ ትብብርን አስቀድመው ወደ ልማት ገብተዋል።

የኒጀር ወንዝ ተፋሰስ የኒጀር ወንዝ ከዓባይ እና ከኮንጎ ወንዞች በመቀጠል በአፍሪካ ሦስተኛው ረጅሙ ወንዝ ሲሆን፤ 4 ሺህ 180 ኪሎ ሜትር ያህል እርዝማኔ አለው። ወንዙ ልዩ የሆነ የጨረቃ ቅርጽ ያለውና ጊኒን፣ ማሊን፣ ኒጀርን፣ የቤኒን ድንበር እና ናይጄሪያን ጨምሮ ዘጠኝ የተፋሰሱን ሀገራት በማቋረጥ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ (ወደ ጊኒ ባህረ ሰላጤ) ይገባል። ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ሕይወቱ በተፋሰሱ ላይ እንደተመሠረተ መረጃዎች ያሳያሉ።

በኒጀር ወንዝ አካባቢ የሚከሰቱ ግጭቶች ድንበር ተሻጋሪ እና ሰፊ አካባቢዎችን የሚሸፍኑ ናቸው። የግጭቶቹ መነሻም በአብዛኛው በአካባቢ መራቆት፣ በኃብት እጥረት (Resource



30

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

Scarcity)፣ በጂኦ-ፖለቲካዊ ክፍፍል እና በትጥቅ ከተደገፈ የታጣቂዎች ጥቃት ጭምር የሚመነጩ ናቸው። እንደ የአየር ንብረት ለውጥ ያሉት ሥጋቶች ደግሞ አባባሽ ሚና ያላቸው በመሆናቸው ተፋሰሱ ለተለያዩ የግጭት ዓይነቶች ተጋላጭ ሆኗል።

በተፋሰሱ ከታዩት ጂኦ-ፖለቲካዊ እና ድንበር ተሻጋሪ አለመግባባቶች መካከል የቤኒን እና ኒጀር ውዝግብ ይጠቀሳል። የቤኒን-ኒጀር ቀውስ እ.አ.አ በ2023 በኒጀር በተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት የተቀሰቀሰና አሁን ድረስ የቀጠለ ሲሆን መንስኤውም በሕዝብ የተመረጠውን የኒጀር ፕሬዚዳንት መሐመድ ባዞምን ከሥልጣን በማውረድና በምትኩ ወታደራዊ መንግሥት መቋቋሙን ተከትሎ ቤኒን በኒጀር ወንዝ ላይ የጣለችው ማዕቀብ ነው።

እ.አ.አ በ2024 ቤኒን በማላንቪል የኒጀር ወንዝ ድንበር በሀገረ ኒጀር ላይ የጭነት እና የመጓጓዣ ፍሰት እንዳይኖር በመከልከሏ የአካባቢውን ንግድ አቀዛቅዞ ወታደራዊ ፍጥጫዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል።

ሌላው በወንዙ የላይኛው እና የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መካከል የሚፈጠር የውኃ ፖለቲካ ውዝግብ ነው። እንደ ማሊ ያሉ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ግዙፍ ግድቦች እና የመስኖ መሠረተ ልማቶች መገንባታቸው በወንዙ ተፈጥሯዊ ፍሰት ላይ አሉታዊ ጫና መፍጠሩ ውጥረት አስከትሏል። እንደ ናይጄሪያ ባሉ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትም ግልፅ የሆነ ጫና በመፍጠሩ የአደጋ ሥጋት ደቅኗል።

እነዚህ የተፋሰሱ ተጋሪ ሀገራት ከወንዙ ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚረዳ ተቋም መሥርተዋል። ይህም የኒጀር ተፋሰስ ባለሥልጣን (Niger Basin Authority) የተሰኘ ሲሆን የኒጀር ወንዝ ተፋሰስን ዘላቂ እና የተቀናጀ ልማት ለማረጋገጥ ሲባል በዘጠኝ አባል ሀገራት መካከል ትብብርን ማጎልበት ታሳቢ ያደረገ የበይነ-መንግሥታት ድርጅት ነው። ቀደም ሲል እ.አ.አ በ1964 “የኒጀር ወንዝ ኮሚሽን” (River Niger Commission) በሚል ተቋቁሞ በኋላም እ.አ.አ በ1980 “የኒጀር ተፋሰስ ባለሥልጣን” (Niger Basin Authority) በሚል እንደገና ተቋቁሟል።

የባለሥልጣኑ ዋና ተልዕኮ የውኃ ኃብቶችን እና ተያያዥ ሥነ-ምህዳሮችን በዘላቂነት በማስተዳደር በወንዙ ተፋሰስ ውስጥ የሚኖረውን ሕዝብ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ነው። ትኩረቱም የኃብት አስተዳደር፣ በውኃ፣ በኃይል፣ በግብርና፣ በእንሥሳትና በዓሣ ኃብት፣ በደን እና በትራንስፖርት ዘርፎች ላይ ያሉትን ሀገራዊ ፖሊሲዎች ማቀናጀት ነው። የተፋሰሱ ሀገራት በወንዙ ዙሪያ የሚጋጥማቸውን አለመግባባት እንዲህ ባለ ተቋማዊ ስሪት ለመፍታት የሄዱበት ርቀት ሌሎች ሊጋሩት የሚገባ ልምድ ነው። እንደ ግብፅ ያሉ የታችኛው የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ዘመኑ ካለፈበት እና ፍትሃዊነት ከጎደለው “ብቸኛ የታሪካዊ መብት” ባለቤትነት እሳቤ ተላቀው ወደ ተቋማዊና ፍትሃዊ የጋራ ተጠቃሚነት አሠራር ሊገቡ ይገባል። ከላይ ከተጠቀሱት ልምዶች የሚወሰደው ትምህርትም ይኸው ነው።

ውኃ ከፖለቲካም በላይ ነው

በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል በሁለቱ ውኃዎች ዙሪያ ያለው ፍላጎት ከፍተኛ የፖለቲካና የደህንነት ልዩነት አስተናግዷል። በግብጽ በኩል በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና በዓባይ ወንዝ ላይ የተያዘው አቋም ታሪካዊ የሚባሉ የ”ቅኝ ግዛት መብቶችን” ማስጠበቅ ሲሆን፤ በወንዙ ላይ የነበራትን የበላይነት (Hydro- hegemony) ማስቀጠል እና የውኃ ፍሰት መዋዠቅ ሥጋትን መከላከል ነው።

በአንፃሩ ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ እና በዓባይ ውኃ ዙሪያ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (Cooperative Framework Agreement- CFA) የኢነርጂ ልማትን ማረጋገጥ፣ ከ130 ሚሊዮን በላይ የሚሆነውን ሕዝቧን ከኃይል አቅርቦት እጥረት ማውጣት እና ፍትሃዊ የውኃ አጠቃቀምን ማጽናት ነው።

ቀይ ባህርን በተመለከተ ደግሞ ሁለቱ ሀገራት ያላቸው ስትራቴጂያዊ አቋም እና ግብ ተፃራሪ ሆኖ እናገኘዋለን። በኢትዮጵያ በኩል የተያዘው አቋም የመልክዓ ምድራዊ ወጥመድን በመበጣጠስ አስተማማኝ፣ አማራጭ እና ሉዓላዊ የባህር በር በማግኘት የደህንነትና የማክሮ ኢኮኖሚ ተጋላጭነትን መቀነስ ነው።

ግብጽ ቀይ ባህርን አስመልክቶ ያላት አቋም ከዚህ ፍፁም ተፃራሪ ሆኖ እናገኘዋለን። በዋናነት ደግሞ የኢትዮጵያን የባህር ኃይል እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መገደብ ቀዳሚ ግቧ አድርጋ ይዛዋለች። በቀይ ባህር ዙሪያ የደህንነት ጥምረት በመፍጠር ኢትዮጵያን የመክበብ ዲፕሎማሲ መከተልን ደግሞ ዓይነተኛ ፖሊሲ አድርጋ እየሠራችበት ትገኛለች።

በቅርቡ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ ከኤርትራ አቻቸው ኦስማን ሳልህ ጋር በካይሮና በአስመራ ያደረጉት ውይይት ከቀይ ባህር ጋር ቀጥተኛ ድንበር የሌላቸው አካላት በቀይ ባህር ቀጣና ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል የሚያደርጉትን ማንኛውንም ዓይነት ሙከራ እንደማይቀበሉ አረጋግጠዋል።

በዚህ ረገድ የግብጽ ዋና ስትራቴጂያዊ አካሄድ በቀይ ባህር ወሰን ተጋሪ ሀገራት ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ ከስዊዝ ቦይ ጋር የተሳሰሩትን ወሳኝ የሀገር ውስጥ ደህንነት እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቿን የማስጠበቅ ግብን ታሳቢ ያደረገ ነው።

ግብፅ ቀይ ባህርን የማስተዳደር መብት ለባህር ወሰን ተጋሪ ሀገራት (Littoral States) ብቻ የተሰጠ መሆኑን በማስመር፣ ካይሮ የውጭ ጣልቃ ገብነቶችን ለመግታት፣ ተቀናቃኝ የጂኦ-ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ለመመከት እንዲሁም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ከባህር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የሌላቸው ሀገራት (Landlocked Countries) ወደ ባህር የሚያደርስ ነፃ መዳረሻ እንዳያገኙ ለማድረግ ትሻለች።

እዚህ ላይ መነሳት ያለበት ወሳኝ ጥያቄ ግብፅ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር የመድረስ ፍላጎቷን ለምን ማገድ ትፈልጋለች የሚለው ነው። ግብፅ የኢትዮጵያን ወደ ቀይ ባህር የመድረስ መሻትን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ከስዊዝ ቦይ የኢኮኖሚ ደህንነት ጋር በማቆራኘት የኢትዮጵያን የባህር ጥያቄ እንዳይሳካ ማድረግ ትፈልጋለች።

ኢትዮጵያን ከቀይ ባህር በማግለል እና በጎረቤት ሀገራት ላይ ጥገኛ በማድረግ ለውጭ ጫና ተጋላጭ ሆና እንድትቀጥል፣ የባህር ኃይል እንዳትፈጥር አሊያም በአፍሪካ ቀንድ ኃያል እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገር እንዳትሆን በትኩረት ትሠራበታለች። ይህ ሁሉ የሚመነጨው ግብፅ ስትራቴጂያዊ ጥቅምዋን ለማስጠበቅ እና በዓባይ ወንዝ እና በተፋሰሱ የውኃ ድርድር ውስጥ ያላትን ቅጥ ያጣ የበላይነት ለማስጠበቅ የውጭ ተጽዕኖን መገደብ ከሚል የተዛነፈ እሳቤ ነው።



31

በጂኦ-ፖለቲካ ውስጥ ሁለት የተለመዱ አባባሎች አሊያም ፅንሰ-ሃሳቦች አሉ። እነዚህ ፅንሰ-ሃሳቦች በጂኦ-ፖለቲካ ውስጥ መልክዓ ምድር የዓለምን የኃይል አሰላለፍ እንዴት እንደሚወስን ተቃራኒ አመለካከቶችን የሚያንጸባርቁ ሁለት ዓይነተኛ ፅንሰ-ሀሳቦች ናቸው። እነሱም የመሃል ሀገር (Heartland) እና የዳር ሀገር (Rimland) ፅንሰ- ሀሳቦች በመባል ይታወቃሉ።

የመሃል ሀገር ፅንሰ-ሀሳብ (Heartland) መሃል ሀገሩን የተቆጣጠረ ዳር ሀገሩን (ግዛቱን) ሁሉ ይቆጣጠራል (Who Control the Hinter Land Control the Periphery) የሚል እሳቤ ሲኖረው፤ በአንፃሩ የዳር ሀገር ፅንሰ-ሃሳብ ዳር ሀገሩን (ጠረፉን) የተቆጣጠረ መሃሉን ሁሉ ይቆጣጠራል (Who Controls the Periphery Controls the Hinterland) የሚል አቋምን የሚያንጸባርቅ ነው።

ይህ ጽንሰ-ሀሳብ ያለ ምክንያት አልተነሳም። ግብጽ ሰሜን አፍሪካንና መካከለኛው ምሥራቅን የምታገናኝ እንዲሁም በስዊዝ ቦይ አማካኝነት የአፍሪካ፣ የእስያ እና የአውሮፓን ንግድ የምታስተላልፍ ወሳኝ ሀገር ናት፡፡ በዚህ የተነሳ በዓለም እጅግ ስትራቴጂያዊ አስፈላጊነት ካላቸው ሀገራት መካከል ከቀዳሚዎቹ አንዷ ያደርጋታል፡፡ በመሆኑም ኃያላን ሀገራት ሁሉ ስትራቴጂያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የግድ አብረዋት እንዲሠሩ የሚገደዱበት አጋጣሚ የሰፋ ነው፡፡

በአንፃሩ ግብጽ ሰፊ መሬት ቢኖራትም 97 በመቶ ያህሉ ግዛቷ በረሃማ ነው፡፡ ቀሪው ሦስት በመቶ ግዛቷ ግን በዓባይ ውሃ የለማ ምድር ገነት ነው፡፡ የግብጽ ሕዝብ 115 ሚሊዮን በመድረሱ እንዲሁም ወደፊት እየጨመረ የሚሄደውን የሀገሪቱን ሕዝብ የውሃ ተደራሽነት ለመጨመር የዓባይን ውሃ ከበፊቱ ይበልጥ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በካናል በመውሰድ ሰፋፊ የግብርና መሬቶችን ማልማትና ሕዝቡን ከዓባይ ሸለቆ አውጥቶ በሌሎች ያልተጨናነቁ አካባቢዎች የመውሰድ ሃሳብ አላት፡፡

በመሆኑም የዓባይን ውሃ ሙሉ በሙሉ የመጠቀም ፍላጎት እንዳላት የበዙ የልማት ፕሮጀክቶቿ ያሳብቃሉ። ይህንን ለማድረግ ግን የዓባይ ተፋሰስ የላይኛው ሀገራት ምንም አይነት ውሃ እንዳይጠቀሙ ትፈልጋለች፤ ትፈልጋለች ብቻ ሳይሆን ቀይ መስመር አስምራለች።

ኢትዮጵያም የባህር በር ባይኖራትም ከግብጽ



32

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ያልተናነሰ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡ ለግብጽ የስዊዝ ቦይንና መካከለኛው ምሥራቅን የምትቆጣጠርበትን ዕድል የሰጠች ተፈጥሮ ለኢትዮጵያ ደግሞ ግብጽን የምትቆጣጠርበትን ሁለት ወሳኝ ዕድሎችን ጀባ ብላለች፡፡ ሁለቱን ውኃዎች - ዓባይ እና ቀይ ባህርን፡፡

ግብጽን የያዘ ሀገር መካከለኛው ምሥራቅንና የዓለምን ንግድ ይቆጣጠራል፡፡ ዓባይን የተቆጣጠረ ደግሞ ግብጽን ይቆጣጠራል፡ ፡ ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ከተቆጣጠረች ወደ ግብጽ የሚሄደውን የንግድ መስመር ሁሉ ትቆጣጠራለች፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ሁለቱን ግቦቿን ካሳካች ስትራቴጂያዊ አስፈላጊነቷ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ይላል፡፡ ያለተነገረው የግብፅ ሥጋትም መነሻው ይኸው ነው። ከውኃ ይልቅ ፖለቲካዊ አንድምታው የሚበዛው በዚህ ምክንያት ነው።

ኢትዮጵያ ከዓባይ ወንዝ ጋር በተያያዘ ከግብጽ ጋር ወደ ጦርነት ብትገባ ቀይ ባህርን በመዝጋት የግብጽን ኢኮኖሚ ዜሮ ማውረድ ትችላለች፡፡ በመሆኑም ግብጽ ቀጥታ ጦርነት እንዳትከፍት ስለሚያደርግ ቀይ ባህርን መያዝ የሰላም ዋስትና ነው፡፡ ያ ከሆነ ኢትዮጵያ ከዓባይ ወንዝ የሚገባትን ድርሻ መጠቀም ያስችላታል፡፡

የግብፅ መንትያ የመግቢያ እና መውጫ በር ስትራቴጂ (Egypt’s Twin Gateway Strategy) የሰሜኑን የስዊዝ ቦይ ደህንነት ከደቡባዊው የባብ ኤል-መንደብ የባህር ወሽመጥ ጋር ያገናኛል። ይህም እንደ አንድ ቀጣይነት ያለውና እርስ በእርስ የሚደጋገፉ የደህንነት ኮሪደሮች ተደርገው ይወሰዳሉ። ለዚህ ነው የግብጽ ጦር ኃይል ዶክትሪን የባብ ኤል መንደብን የስዊዝ ካናል ደህንነት አካል አድርጎ የሚወስደው፡፡

በመሆኑም ግብፅ፤ ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪ ሀገር እንዳትሆን መከላከል ማለት በቀይ ባህርና በመካከለኛው ምሥራቅ ሊፈጠር የሚችልን ኃያል ሀገር በእንጭጩ ማስቀረት አድርጋ ትቆጥረዋለች። ምክንያቱም ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ወሳኝ ሀገር ከሆነች የግብጽ ስትራቴጂያዊ አስፈላጊነት ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ይሸፈናል የሚል ሥጋት አላት።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያን ከባህር አግልሎ ማቆየት የግብጽን በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተደማጭነት ከፍ የሚያደርግ ነው። በተቃራኒው የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር ተጋሪነት መምጣት የኢትዮጵያን ማንሰራራት እጅግ ስኬታማ ለማድረግና ቁልፍ ሀገር እንድትሆን የሚያስችል ነው። ይህ እንዳይሆን ነው ግብጽ ከተዋሳኝ ሀገራት ማለትም ከሳውዲ ዓረቢያ፣ ከሶማሊያ፣ ከጅቡቲ፣ ከሱዳን፣ ከኤርትራ እና ከሌሎች ጋር በመሆን ቀይ ባህርን የዓረብ ባህር አድርጎ ለማቆየት የምትሠራው። ኢትዮጵያ የዓረብ ሊግ አባል እንዳትሆንም ግብጽ አበክራ የምትሠራው በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ ይህንን ማድረግ የግብጽን ስትራቴጂያዊ አስፈላጊነት እንደሚጨምር በግብጾች በኩል ስለታመነበት ጭምር፡፡

በጥቅሉ ግብጽ ተፈጥሮ ለኢትዮጵያ የቸረቻቸውን ሁለት ቁልፎ ፀጋዎቿን ለመንጠቅ ለበርካታ አሥርት ዓመታት ስትሠራ የኖረችው በዚህ ምክንያት ነው። እዚህ ላይ ለኤርትራ መገንጠል ከተለያዩ የግብፅ መሪዎች አንስቶ እስከ የቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፃሃፊ ግብፃዊው ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊ የሠሩትን የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ሴራ ታሪክ ይቅር የማይለው መሆኑ አይዘነጋም።

አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያን እየመራ ያለው የመደመር መንግሥት ከቀደሙት ሥርዓቶች



33

የወረሳቸውን የውስጥ ችግሮች ለመፍታትና አገሪቷን ወደ ብልጽግና ለመውሰድ የሚያደርገውን ጥረት የተመለከተችው ግብጽ እንደ መልካም ዕድል ተጠቅማ ኢትዮጵያን ለማዳከም ላይ ታች ማለቷ አልቀረም። ይህም በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ያለው የውኃ ጉዳይ በእርግጥም ውሃ ከፖለቲካ በላይ መሆኑን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።

የዋዲ አራባ አብነት

በመካከለኛው ምሥራቅ የውኃ እጥረት በሚያጠቃቸው ምድሮች ውስጥ አንድ ትልቅ ትምህርት ሰጪ ውል ተፈጽሟል። የዋዲ አራባ ሥምምነት። ይህ ሥምምነት እ.አ.አ በ1994 በእስራኤል እና በዮርዳኖስ መንግሥታት መካከል የተፈረመ የሠላም ስምምነት ነው።

ሥምምነቱ ከ1948ቱ የዓረብ-እስራኤል ጦርነት ወዲህ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረውን የከረረ የጦርነት እና የግጭት አዙሪት ያስቆመ፤ የጋራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሠረተ ሥምምነት ነው። ሥምምነቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ሰላም ከመፍጠሩ በተጨማሪ የግዛትና እና የውኃ ውዝግቦችን መፍታት አስችሏል፤ ፈትቷል። በቱሪዝም እና በንግድ መስኮች ሰፊ ትብብር እንዲኖር አስችሏል።

በዋዲ አራባ ሥምምነት መሠረት የዮርዳኖስ ወንዝ፣ የያርሙክ ወንዝ እና የአራቫ/አራባ የከርሰ ምድር ውኃዎች ቋሚ የውኃ መጋራትና የትብብር አስተዳደር ተቋቁማል። ሥምምነቱ እስራኤል የዮርዳኖስ እና የያርሙክ ወንዞች ወደ ወደ ሀገረ ዮርዳኖስ እንዲፈስ በማድረግ የሚጠበቅባትን የውኃ መጠን (የበጋና የክረምት መጠንን ይጨምራል) እና ወቅታዊ ፍሰት እንዲኖር የሚያደርግ ነው።

ከዚህ መሠረታዊ የሥምምነት ማዕቀፍ በተጨማሪ እስራኤል እ.አ.አ በ2021 ሀገረ ዮርዳኖስ የሚገጥማትን የከፋ የውኃ እጥረት ለመታደግ በየዓመቱ ተጨማሪ 50 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ ለማቅረብ ተስማምታለች። ይህን የሚከታተል የሁለትዮሽ የጋራ ኮሚቴ አቋቁመው የውኃ ሀብታቸውን በፍትሃዊነት እና በሰጥቶ መቀበል መርህ እየተጠቀሙ ይገኛሉ።

ይህም በዓባይ ተፋሰስ ውኃዎች አልፎ ለግብፅም ሆነ ለኢትዮጵያ ታላቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው። የዋዲ አራባ ስምምነት ውኃን የግጭት መሣሪያ ከማድረግ ይልቅ ለጋራ ዕድገትና ብልጽግና የጋራ ሀብት አድርጎ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።

በዋዲ አራባ ሥምምነት እስራኤል እና ዮርዳኖስ ውኃን “የጋራ የልማት ሀብት” አድርገው በመቀበል የዘመናት ግጭታቸውን ተሻግረዋል። ይህ ሥልጡን የአስተሳሰብ ለውጥ ባላንጣዎችን ወደ ወዳጅነት የለወጠ ሲሆን፣ ውኃ ለብቻው ተወስኖ የሚቀመጥ ሳይሆን በጋራ የሚጠበቅና የሚለማ ወሳኝ ሀብት መሆኑን በግልጽ አሳይቷል።

በዓባይ ወንዝ ላይ ታሪካዊ የእኔነት ስሜት ውስጥ ለተዘፈቀችው ግብፅ ይህ ሥምምነት ውኃ በጋራ ተጠቃሚነት መነፅር እንጂ በቅኝ ግዛት ቅርስነት መታየት እንደሌለበት ጥልቅ ትምህርት ይሰጣል።

በቅን የትብብር መንፈስ እና ማዕቀፍ ሥር እስራኤል ለዮርዳኖስ በዓመት ከ50 እስከ 100 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ማቅረቧን ቀጥላለች። ይህም እንደ ስጦታ ሳይሆን በጋራ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን የሁለቱንም ሀገራት ደህንነት ያጠናክራል።

በተመሳሳይ አስደናቂ የሽርክና እርምጃ፣ ዮርዳኖስ ከእስራኤል ጋር “ውኃ በኃይል” የሚል ስምምነት በመመሥረት በፀሐይ ኃይል ምትክ ውኃ መግዛት ጀምራለች። ይህ ሞዴል የውኃን ጠቃሚነት ብቻ ሳይሆን የንግድ እሴቱን ያሳያል።

ግብፅ ተመሳሳይ ስትራቴጂ እና መሰል ሥምምነት ከኢትዮጵያ ብሎም ከላይኛው የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ጋር ብትደርስ የሚፈጠረው ትብብር ጠቃሚነቱ ምን ያህል የጎላ እንደሚሆን መገመት አይከብድም። ከዓባይ ወንዝ ውኃ የነፃ አጠቃቀም ጥያቄን ሙጥኝ ከማለት ይልቅ ግብፅ ከኢትዮጵያ የኃይል ግዥ መፈጸም ብትጀምር፤ ቅሬታን ወደ ወዳጅነት በመቀየር የኢትዮጵያን ሕጋዊ የመልማት መብት እያረጋገጠች የራሷንም የውኃ እጥረት ስጋት መቅረፍ በቻለች ነበር።

የእስራኤል እና የዮርዳኖስ ሥምምነት መሠረቱ የጋራ እውቅና እና ሉዓላዊነትን ማክበር ነው። የትኛዋም ሀገር በሌላዋ የውኃ ሀብት ላይ የባለቤትነት ጥያቄ አታነሳም፤ ይልቁንም በጋራ ኮሚሽን በኩል ፍትሃዊ የውኃ አጠቃቀም እንዲኖር በትብብር ይሠራሉ እንጂ። ግብፅ የትብብር ማዕቀፍ ሥምምነቱን (CFA) በመቀበል ይህንን የትብብር መንፈስ አክላ ቢሆን ኖሮ በመካከለኛው ምሥራቅ ከተወሰደው ተመሳሳይ የሆነ የጋራ ተጠቃሚነትን ማግኘት ትችል ነበር። ፍትሃዊ ድርድሮች በመከባበር ላይ የተመሠረቱ ናቸው፤ ይህም ታሪካዊ ቅሬታዎችን ወደ የጋራ ተጠቃሚነት የሚቀይር እሴት ነው። ይህን ሃቅ ግብጽ መቀበል ግድ ይላታል።

እስራኤል እና ዮርዳኖስ ያለፈው ታሪክ ላይ ከማተኮር ይልቅ በጋራ መፃኢ ተስፋቸው ላይ በማተኮር የዘመናት ግጭታቸውን ሲሻገሩ ዓለም ምስክር ሆኗል። በመግባባት ላይ የተመሠረተው የውኃ ስምምነታቸው አንድ ጥልቅ እውነትን ያሳያል፤ ታሪካዊ ስህተቶች በፍትሃዊ እና ትክክለኛ ሥምምነቶች በእርግጥም ሊታረሙ ይችላሉ።

በዚህ ረገድ ግብፅን ወደፊት የሚያራምደው መንገድ እ.አ.አ በ1929 እና 1959 ከተደረጉ ያረጁና ያፈጁ የቅኝ ግዛት ውሎች ግትር እሳቤዎች በመውጣት አርቆ አሳቢና ፍትሃዊ ወደ ሆነ የውኃ አጠቃቀም ሥምምነት በመምጣት ከዓባይ እስከ ቀይ ባህር የዘለቀውን ቀጣናዊ ፍጥጫ መቋጨት ይገባታል።



34

ፖለቲካ

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

በሀሳብ ልዕልና የታተመ አዲስ ውል



35

በጌታቸው ሠናይ

ዕይታ

ይህ ጽሑፍ ኢትዮጵያ ለዘመናት ልዩነቶቿን በኃይልና በጠመንጃ አፈ-ሙዝ ለመፍታት ያደረገችውን ታሪካዊና ፖለቲካዊ አዙሪት በማሳየት፣ ሀገራዊ ምክክር ለዘላቂ ሰላምና ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ያለውን አስፈላጊነት ይዳስሳል። ጽሑፉ ከዘውዳዊው ሥርዓት፣ ከደርግ ወታደራዊ አገዛዝና ከኢሕአዴግ የብሔር ፖለቲካ ውጣ ውረዶች የሚቀዱ ሀሳቦችን፣ ግጭቶችና አግላይ ትረካዎች ሀገሪቷን ዋጋ ያስከፈሏት መሆኑን ያነሳል።

እንደ ደቡብ አፍሪካ እና ቱኒዚያ ያሉ የዓለም ሀገራትን ስኬታማ የምክክር ተሞክሮዎችና የምሁራንን (እንደ ፕሮፌሰር ዩቫል ኖኅ ሃራሪ፣ ዳንኤል ያንክሎቪች እና ማርታ ሚኖው ያሉ) ሳይንሳዊ እይታዎችን በማቀናጀት፣ የምክክርን የሐሳብ ልዕልና ያመላክታል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን “ከታች ወደ ላይ” የሚከተሉ አካታች አሠራሮችን፣ የ1 ሺህ 234 ወረዳዎችን ተደራሽነት፣ የ200 ሺህ ዜጎችን ተሳትፎና የተለዩትን ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ያሳያል።

በመጨረሻም፣ ሀገራዊ ምክክሩ አሸናፊና ተሸናፊን የሚለይ ሳይሆን፣ የተቃረኑ ታሪካዊ ትረካዎችን



36

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

በማስታረቅና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት፣ በሕዝቡ ሙሉ ፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ አዲስ “ማኅበራዊ ውል” ለመፍጠርና የኢትዮጵያን ብሩህ መጪ ዘመን ለማረጋገጥ የሚያስችል ታሪካዊ “ብዕርና ብራና” ያመላክታል።

የአሸናፊነት ቀንዲል

ኢትዮጵያዊያን ከ40 ቀናት በላይ በአንድ ከትመው ያሳለፉትን ዘመን ተሻግሮ በመመልከት፤ “ዛሬ የተሠራ ነገ ያሻግራል” የሚለው እምነታቸው ጽኑ ሆኖ፤ በጽናት፣ በትጋት ነገን እያሰቡ አንዳቸው የሌላቸውን ጥያቄዎች አዳምጠው እንደየመረዳታቸው መጠን ተንትነዋል። ዛሬ ላይ ብዝሃ ሀሳብን በብዝሃ አቅም ሞግተዋል። በቃላት ጦርነት ሰላምን አውጀዋል። ከጠብ፣ ከግርግር፣ ከጠመንጃ መማዘዝ ወጥተው የሰላም መሠረት ጥለዋል።

“የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከጸብና ከደመኝነት ስሜት ወጥቶ በይቅርታ፣ በሰላምና በመደማመጥ ጎዳና እንዲራመድ መሠረት ተጥሏል” በማለት የሀገራዊ ምክክሩ ጉባዔ ማጠናቀቂያ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የኢትዮጵያ ቀጣይ ዘመን በምክክርና ሀሳብን በሀሳብ በመሞገት ላይ የሚመሠረት መሆኑን ከተግባር ከተገኘው ተሞክሮ በመነሳት አረጋግጠዋል።

በርግጥ ኢትዮጵያ በየአካባቢው የመመካከር፣ ችግርን በሀገር ሽማግሌ፣ በሃይማኖት አባቶች ግሳፄ የመፍታት የዘመናት ሀብት አላቸው።

ይህን ጠንካራ በይቅርታና በምህረት ዘመን የሚያሻግርን ባህል በአንድ ቀምሮ በማምጣትና ሀገራዊ ትሩፋት እንዲኖረው በማድረግ በኩል ብዙ አልተሠራም። ምሁራንም የተጨበጠና ዘመንን የሚዋጅ መፍትሔ ቀምረው በማምጣት መንግሥታትን አልሞገቱም። በዚህ ዘመን ግን ችግሮቻችንን በዘላቂነት ለመፍታት አዋጅ ወጥቶ፣ ተቋም ተመሥርቶ ደንብና መመሪያ ተሠርቶ ምክክር ተደረገ። ምክክሩ ከታች ጀምሮ ወደ ላይ የመጣ ብዝሃነትን ያረጋገጠ ነው።

“ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ የኢትዮጵያ ብዝሃነት ጎልቶ የታየበት ነው” ያሉት ፕሬዚዳንት ታዬ፤ ምክክሩ በሰከነ መንፈስ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት የሚያስችል አዲስ ባህል የፈጠረ መሆኑን ነው አጽንኦት የሰጡት።

የሀገራችን ምክክር ልዩ ባሕርያት ያሉት ነው። የመጀመሪያው ጉዳይ ከሕዝብ ለሕዝብ የተካሄደ መሆኑ ነው። በጥቂት የፖለቲካ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ወይም የተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የተካሄደ አይደለም። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አዝመራው አንደሞ ሲገልጹ “ምክክሩ ከሕዝብ ለሕዝብ በሕዝብ የተካሄደ ነው” ብለዋል። ይህም ከሌሎቹ ልዩ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ መሠረት የሆነውም ይሄው ነው።

እርሳቸው እንደሚሉት፤ ኮሚሽነሮች የተመረጡት ከሕዝብ ነው፤ አጀንዳ የተሰበሰበው ከሕዝብ ነው፤ አመካካሪ የተመረጠው ከሕዝብ ነው፤ ተመካካሪዎች የተመረጡት ከሕዝብ ናቸው። ከሕዝብ የተሰበሰበው አጀንዳ ከሕዝብ በተመረጡ ተወካዮች በኩል ምክክር ተደርጎበት ለመጻኢ ዕድል፣ ለሕዝቦቻችን ጥቅም ሀሳብ መንጭቶበታል።

ኢትዮጵያ ያለፈችበት ምክክር፣ በሀገር በቀል እሳቤ፣ በሀገር ልጆቿ፣ በሀገር አጀንዳዎቿ ራሱ ሕዝቡ በቀረጸው አጀንዳ ላይ የተመካከረበት ሲታይ ከሌሎች ዓለማት ላይ ከተደረገው እጅግ መሰረታዊ ልዩነት አለው።

ከምክክሩ ልዩ ባህሪያት መካከል ሀገር በቀል መሆኑ ነው። ሀገር በቀል የሚያደርገው የሀሳብ ምንጩ ከሕዝብ ለሕዝብ በሕዝብ የተካሄደ መሆኑ ተጠቃሽ ነው። ሁሉን አቃፊነቱ ዋነኛ ማጠንጠኛ ተደርጎ ይወሰዳል። ከመላው ኢትዮጵያዊያን ከሁለት ሺህ በላይ አጀንዳዎች ተሰብስበው በስምንት ዋና ዋና ጭብጦች ተደራጅተው በመጨረሻው ምዕራፍ ኢትዮጵያዊያን በአንድ ማዕድ ላይ ተሰባስበው ሀሳብ ከሀሳብ አፋጭተው ይሆነናል፤ ቀጣዩ ትውልድ በተረጋጋና ዘላቂ ሰላሙ በተረጋገጠ ሀገር ይኖራል በማለት መክረዋል፤ ምክረ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

“የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ጊዜያዊ የፖለቲካ መፍትሔ ፍለጋ ሳይሆን የኢትዮጵያን የፖለቲካና ማኅበራዊ ጉዞ ወደ ብልጽግና የሚያሻግር ታላቅ



37

የምክክር ሂደት መነሻው ምንድን ነው? በማለት መጠየቅ ግድ ይለናል።

የታሪክ ዕይታ

ለዘመናት ልዩነትን የያዝንበት መንገድ ሀገራዊ ምቾት አሳጥቶናል፤ እርስ በእርስ እየተጋጨን አንዳችን ለሌላችን መከታና ጋሻ ከመሆን ይልቅ መጠፋፋትን እንደ መፍትሔ ቆጥረን ዘልቀናል። በየአካባቢው ያለውን የሽምግልና እና የእርቅ ጥበብ ሳናሳድግ በያለበት እንዲቆይ አድርገናል። ከጎረቤታችንም ሆነ ከወንድማችን ጋር ለሚፈጠር ትንሽ አለመግባባት መፍትሔ አድርገን የመረጥነው ኃይልን ነበር። መሣሪያ አንግቦ ወደ ጫካ መግባት፣ ጦር ሰብቆ መዋጋት ለሁሉም የፖለቲካ ጥያቄዎች ብቸኛ ንጉሥ ሆኖ ለዘመናት ሰፍኖ ቆይቷል።

ኢትዮጵያዊያን በችግሮቻቸው ጊዜ የሚሰባሰቡ፣ ጠላት ሲገጥማቸው በጋራ የሚመክቱና ዓለም በሚያስደንቅ ጀግንነት ድል የሚነሱ ቢሆኑም፤ በውስጥ ግን ግጭቶቻቸው ትኩረታቸውን ከዕድገት ላይ እንዲነጥቅ አድርጎታል። ምንም እንኳን “ኢትዮጵያዊያን ለብዙ ሺህ ዘመናት ተከባብረው፣ ተጋብተውና ተዋልደው ላይለያዩ እርስ በእርስ ተጋምደው፣ ቋንቋና ባህላቸውን አዋህደው አብረው ኖረዋል” በማለት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የገለጹት እውነት ቢሆንም፤ በሥርዓተ መንግሥት አወቃቀርና አስተዳደር ተቀባይነት ላይ ጥያቄያቸው የገዘፈ፣ እርስ በእርስ ያጋጫቸው ጉዳይ ሆኗል።

ኢትዮጵያ እስከ 1967 ዓ.ም አብዮት ድረስ በንጉሠ ነገሥት የምትተዳደር ሀገር እንደነበረች የታሪክ ድርሳናት አስፍረውት የቆየ፣ ዘውዳዊ ሥርዓትን ለመገርሰስ የታገሉ የሚመሰክሩት እውነት ነው። ሕዝቦች በእርስ በእርስ መስተጋብር ያላቸውን አስተዋፅኦ የሚያዩት ከመለኮታዊ ኃይልና ከንጉሠ ነገሥቱ መልካም ፈቃድ ጋር አያይዘው ነበር። ሁሉንም ነገር የሚያዩት በሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት መነጽር እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ምስክር ናቸው። “በኢትዮጵያ ፊውዳላዊ ሥርዓት ውስጥ ቅቡልነት የሚመነጨው ከፈጣሪ ወይንም ከሠማይ በተሰጠ ሥልጣንና ከዘር ማዘንበል በሚወረስ የሥልጣን መብት ምክንያት እንደነበር ይታወቃል” በማለት ዶክተር ተስፋዬ በልጅጌ በ”ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ፍለጋ” በሚለው መጽሐፋቸው የገለጹትን ሀሳብ ማጤን ይቻላል። ለዘመናት የቆየው አይነኬው ኃይል በ1967 ዓ.ም ሕዝባዊ ንቅናቄ ሲገረሰስ ሁሉም ነገር ተቀየረ፤ ከመለኮታዊ ኃይል የተገኘ ሥልጣን የሚለው ትርክት ፈረሰ፤ “ንጉሥ አይከሰስ፤ ሰማይ አይታረስ” የሚለው የወግ ማጠንጠኛ ከሰመ።

የ1967 ዓ.ም አብዮት ፈነዳ፤ በርዕዮተ ዓለም የሚመራ ሥርዓት ተፈጠረ። ቀኝ እና ግራ ዘመም በሚል መለያየት የወቅቱ ፋሽን ሆነ። ማርክሲዝም-ሌኒኒዝም ከፊውዳል አስተሳሰብ ጋር ተፋለሙ። ዓለም አቀፍ ሁኔታው የማርክሲዝም-ሌኒንዝምን የበላይነት ሲያስረግጥ ሀገራችን በሙሉ አቅሟ ገባች። “መመሪያችን ማርክሲዝም-ሌኒኒዝም ነው፤ ግባችን ኮሙኒዝም” በሚል አስተሳሰብ ሀገር ተናወጠች። ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ከመፍታት ይልቅ ኃይል የመጨረሻ መፍትሔ ሆነ። በካርል ማርክስ እና በቭላድሚር ሌኒን ሐሳቦች ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ፍልስፍና ሀገሪቷን ተቆጣጠረ።

ታሪካዊ ክንውን ነው” በማለት ፕሬዚዳንት ታዬ የገለጹት ኢትዮጵያዊያን የመከሩበትን ጉዳይ ግብ ጥልቀት ያሳያል።

የሀገራዊ ምክክሩ መካሄድና በስኬት መጠናቀቅ የሀገር ማሸነፍ ትዕምርት ነው። ሕዝቦች ዘላቂ ሰላምን የሚያሰፍን ምክክር ማድረጋቸው የነገን ብሩህ ተስፋ፣ የሀገሪቷን አሸናፊነት ያሳያል።

“የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የሀሳብ ልዩነቶችን በግጭትና ጠመንጃ ለመፍታት ይደረግ የነበረውን የታሪክ አዙሪት በመቀየር አዲስ የፖለቲካ ባህልን የገነባ ነው” በማለት ነው በምክክሩ ከተሳተፉ ተመካካሪዎች መካከል አቶ ጉዩ ዋሪዮ የገለጹት።

የእርሳቸውን ሀሳብ ተመካካሪ መሐመድ ቦሩ ይስማሙበታል። “ኢትዮጵያ አሸንፋለች፤ ያሸነፈችበት ትልቅ ስኬት ነው” በማለት ሀሳቡን አጠናክረውታል።

ዛሬ ኢትዮጵያ አሸነፈች ለማለት ያስቻለን



38

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ወታደራዊው መንግሥት ልዩነትን በመሣሪያ አፈሙዝ በሚፈታ፣ እርስ በእርስ በመገዳደል ሥልጣኑን ለ17 ዓመታት አቆየ። በመንግሥት፣ በሕዝብና በሕዝብ መካከል የነበረው ልዩነት በእጅጉ እየሰፋ መጣ፤ ማኅበራዊ ውሉ ተበጣጠሰ። ከመጀመሪያውኑ የደርግን መንግሥት የተቃወሙ ታጣቂ ኃይሎች በትጥቅ ትግል ሥርዓቱን ለመገርሰስ ተፋለሙ፤ የሕዝብ ብሶትና የውስጥ ለውስጥ ተቃውሞ እየገነፈለና ማኅበራዊ መሠረቱ እየተናጋ በመጣበት በ1983 ዓ.ም ደርግ ወደቀ፤ ኢሕአዴግም አገሪቷን ተቆጣጠረ።

ኢሕአዴግ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)፣ የብሔራዊ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ብአዴን/ አዴፓ)፣ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) እና የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ (ደሕዴን) ያካተተ ነበር። ይህ ግንባር ለብሔር/ዘውግ ከፍተኛውን ቦታ የሰጠና ሰዎች ነገሮችን ሁሉ ከመንደራቸውና ከብሔራቸው አኳያ እንዲያዩ ያደረገ እንደነበር ታሪክ የሚያወሳው እውነት ነው። በኢትዮጵያ በዜግነትና በብሔር መብት መካከል ያለው ሚዛን ተዛባ። ኢትዮጵያዊነት እየደበዘዘ የብሔር ፖለቲካ እየገዘፈ መጣ።

ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን የመጣበት መንገድ በጠመንጃ አፈሙዝ በመሆኑ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባባሱ። ከተለያዩ አካባቢዎች ተወክለዋል በተባሉ ሰዎች አማካኝነት አዲስ ሕገ መንግሥት ተረቅቆ ጸደቀ። በዚያው መሠረት ዜጎች ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር ጀመሩ ቢባልም፣ ኢትዮጵያዊነትን ያገለለና ለብሔር ብሔረሰቦች ያደላ ስለነበር በብዙዎች ዘንድ ቅሬታና ጥያቄ ፈጥሮ ቆየ። ይህም ብዙዎች ይፈልጉት የነበረውን የዴሞክራሲ ባህል በመደፍጠጥ የአንድ ግንባር የበላይነት የነገሠበት ሥርዓት እየሰፈነ እንዲመጣ በር ከፈተ።

“ኢሕአዴግ በማኅበረሰብ ማንነቶችና ሀገራዊ ማንነት (ሲቪክ ማንነት) መካከል የፈጠረው ትርክት አግላይና ከፋፋይ እንዲሆን ያደረገው ኢ-ዴሞክራሲያዊነትም ኢ-ፍትሐዊነትም ስለሚታይበት ነው። በኢኮኖሚ ቅቡልነት ለማግኘት ያደረገው ጥረት ከኢ-ፍትሐዊነቱ በሚመነጩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች የተሞላ በመሆኑ አልተሳካም” በማለት የፖለቲካ ሥርዓቱ የመውደቁን ምክንያት ዶክተር ተስፋዬ በልጅጌ በመጽሐፋቸው ሰንደውታል። ይህ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሀገሪቷን ወደ ከፋ ደረጃ በማድረሱ በውስጡ ለውጥ ተረገዘ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥም ተወለደ።

በእነዚህ ዘመናት ግጭቶች ተፈጥረዋል፤ የዜጎች ሕይወት ተቀጥፏል፤ ንብረት ወድሟል። ሰዎች በርካታ ጥያቄዎችን እያነሱ ችግራቸውን በጠመንጃ ለመፍታት መንገድ ጀምረዋል።

ይህ የሚያመለክተው እርስ በእርስ ስንወቃቀስ፣ ስንጋጭና ችግሮቻችንን ለመፍታት ጦር ሰብቀን ሕይወት ስንቀጥፍ፣ ንብረት ስናወድም ዘመናትን ማሳለፋችንን ነው። ልዩነታችን ከቃላት አልፎ በጦር እንድንሰለፍ ያደረገን የታሪክና የፖለቲካ ልዩነት ሊሆን ይችላል። የፖለቲካ ኃይል የሚያጋጥመውን ልዩነት በውይይትና በንግግር አይፈታም፤ ጭራሹን በኃይልና በመገዳደል የሚያምን፣ “ከእኔ የተለየ ርዕዮተ ዓለም መኖር የለበትም” በሚል እሳቤ ጦር የመምዘዝ፣ አዲስ የልዩነት ትርክት የመፍጠር መንገድ ተከትለን ወርቃማ የመሥሪያ ጊዜያትን አሳልፈናል። ለዘመናት በአዙሪት ውስጥ ገብተናል።

“ሰዎች መረጃን፣ ቁጥርን፣ ቀመርንና ቀላል ታሪኮችን ከመቀበል ይልቅ በታሪክ ነው የሚያስቡት፤ እያንዳንዱ ግለሰብና ብሔር የራሱ የሆኑ ታሪኮችና አፈ ታሪኮች አሉት” በማለት የ21ኛው ክፍለ ዘመን የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ዩቫል ኖኅ ሃራሪ እንደገለጸው፣ በታሪክና በአፈ ታሪኮች ላይ ተመስርተን አሁንነታችንን እና መጪውን ዘመን ስናጠፋ ቆይተናል። ከልማትና ከሥልጣኔዎቻችን ተቆራርጠን መሄጃ አጥተናል።

የበርካታ ችግሮቻችን መንስኤዎች መነሻ ውስጣዊ አለመቻቻልና አለመወያየት መሆኑ



39

እሙን ነው። ይህን አለመቻቻልና አለመቀበል አቀጣጣይ ሆነው ያባባሱት ደግሞ የውጭ ኃይሎች ናቸው። ከዘመናት ግጭት፣ ከተደጋገሙ የሥርዓት ለውጦችና ደም ከሚያፋስሱ ግጭቶች መውጣት የግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ከጠመንጃ ፈንታ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ መምጣት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ሆኗል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዞ በኃይለ ቃል ጀምሮ በኃይል እርምጃ የሚደመደምበትን አዙሪት ሰብረን በንግግርና በውይይት የምንተካበት ወቅት ላይ እንገኛለን” እንዳሉት፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ በምክክር አዲስ ታሪክ መጻፍ ያስፈልጋል።

ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል። ግን ወደ ምክክሩ ሀሳብ ለመግባት እንዴት አሰብን?

የምክክር ሀሳብ ጽንሰት

“ዘመኑ ብዝሃነታችንን በጌጥነት ተቀብለን መታረቅ የሚችሉ ሀሳቦቻችንን አስታርቀን፣ መከበር የሚገባውን ልዩነታችንን አክብረን፣ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን አጠናክረን ወደ ከፍታ የምንተምበት ጊዜ ይሆናል። ይህም እንዲሳካ የፖለቲካ ልዩነታችንን ለማጥበብ አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ እናካሂዳለን። የምክክር ሂደቱ ችግሮቻችን በጠረጴዛ ዙሪያ ይፈታሉ ብለው የሚያምኑትን የሚያካትት፤ በፖለቲካ ልሂቃን መካከል የሚደረግ ሂደት ብቻ ሳይሆን የሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ያገናዘበ፣ አጠቃላይ ሂደቱ አካታችና አሳታፊ እንዲሁም በኢትዮጵያዊያን እየተመራ ሀገር በቀል መፍትሔዎችን ለማፍለቅ ታልሞ የሚከናወን ይሆናል”።

ይህ ሀሳብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ “አዲስ ምዕራፍ” በሚል በተዘጋጀው የመንግሥት ምሥረታ ሥነ-ሥርዓት ወቅት ለሕዝብ ባደረጉት ንግግር የገቡት ቃል ነው። የምክክር ሀሳብ ጽንሰት ይፋ የተደረገው በዚህ ነጥብ ላይ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወቅቱ የገለጹት ሀሳብ ሀገራዊ ችግሮችን በመደጋገፍና በመወያየት ለመፍታት የሚያስችል አዎንታዊ እና ተስፋ ሰጪ ሀገራዊ ርዕይን ያቀፈ ነው። የእርሳቸው ንግግር የኢትዮጵያን ብዝሃነት እንደ ጌጥ መቀበል፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት፣ ልዩነትን በማክበር ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር፣ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚያሳትፍ አካታች ብሔራዊ የምክክር ሂደት ማካሄድ እና በኢትዮጵያዊያን የሚመራ ሀገር በቀል መፍትሔ መፈለግ ላይ ያነጣጠረ መሠረታዊ ቃል ኪዳን ነበር።

ይህ ቃል ኪዳን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን ለማስጀመር ከቀረቡት ዋና ዋና የፖሊሲ መነሻዎች አንዱ ተደርጎ ይጠቀሳል። ቃል ኪዳኑ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታትና ሰፊ የሕዝብ ተሳትፎ ያለው ሂደት ለማካሄድ ቁርጠኝነት የተገለጸበት ነው።

ይህ አቀራረብ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን እና ብዝሃነትን ለማጽናት መታሰቡን የሚያመለክት መነሻ ነው። ብዝሃነትን እንደ ሥጋት ሳይሆን እንደ «ጌጥ» የመቀበል እሳቤን ያጎላ፣ ለዘመናት አግላይ ከሆነ የፖለቲካ አስተሳሰብ ተላቀን ብዝሃነትን ከሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ጋር አዋህዶ ማስኬድ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት የሰጠ ነው።

በሌላ በኩል አካታችነትና ሰላማዊ ውይይት ችግሮችን ከኃይል ይልቅ «በጠረጴዛ ዙሪያ» የመፍታት እሳቤን ያጎሉበት ነበር። ይህም ከአሸናፊ-ተሸናፊ (Zero-sum game) ፖለቲካ ይልቅ ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበትን (Win-Win) ሀሳብ ያመላከተ የምክክር ሥርዓትን ለመገንባት ያለውን ርዕይ ያሳያል።

የሕዝባዊ ባለቤትነት እና የሀገር በቀል መፍትሔ ሂደቱ “በፖለቲካ ልሂቃን ብቻ የሚደረግ ሳይሆን” ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚያሳትፍ እና “በኢትዮጵያዊያን የሚመራ” መሆኑን መግለጻቸው፣ ዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከተው ቀድሞ የታሰበበት ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት መሆኑን ያረጋግጣል። ይህም የውጭ ጫናን የሚከላከል እና ሕዝባዊ ቅቡልነትን የሚያረጋግጥ ሀገር በቀል ፍልስፍናን በመቀበል ታሪክ ለመሥራት ዝግጁ መሆንን ያጸናል።

ይህን ርዕይ ዕውን ለማድረግ የሕዝብ ተወካዮች



40

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ምክር ቤት ጥር 5 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን አጸደቀ።

“ኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን አቋቁማ ወደ ተግባራዊ ውይይት ለመግባት መወሰኗ ትልቅ እርምጃ ነው። ይህ አካሄድ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ ረገድ የጎላ ሚና ይኖረዋል” በማለት ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም የገለጹት ሀሳብ ሚዛን የሚደፋ ሲሆን፤ የኮሚሽኑን መቋቋም አስፈላጊነት ያሳያል።

አዲስ ምዕራፍ

“አራት ዓመት እንዴት ረጅም ነው፤ እንዴትስ አጭር ነው!” በማለት የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሲናገሩ በሰማሁበት ቅጽበት በርካታ ነገሮች ወደ አዕምሮዬ መጡ። ንግግራቸው የጊዜ፣ የኃላፊነት እና የሀገራዊ ሂደት ተቃርኗዊ እውነትን የሚያሳይ ጥልቅ ስሜት ነው።

የምክክሩ ሂደት “ዘገየ” ከሚለው አቤቱታ ይልቅ “እንዴት ሊሆን ቻለ?” የሚለው ሀሳብ ገዝፎ መምጣቱ፣ እዚህም እዚያም የሚከሰቱ ግጭቶች የሚያስነሱትን የሕዝብ ልዩነት አጥብቦ በጋራ ጠንካራ ሀገረ-መንግሥት የመገንባት ፍላጎት ሲስተዋል የኮሚሽኑ ተግባር ምን ያህል ከባድ እንደነበር ማጤን አይከብድም።

ሕዝብ በፍጥነት ውጤት ይፈልጋል። አሁን ያለውን ሁኔታ ሊቀይር ወደሚችል አካታች፣ አሳታፊና ተጠባቂ ምክክር ተካሂዶ የጋራ መግባባት በመፍጠር ፊቱን ወደ ዘላለም ጠላቱ ድህነት ማዞር ይሻል። ድህነትን በልማት ድል ነስቶ ለልጆቹ የተመቸች ሀገር ማስረከብ ያልማል። ስለዚህ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ረጅም ጊዜ ወስዷል ቢባል፣ በቀላሉ የሚታይና ከእውነት የራቀ ነው ተብሎ ሙግት መግጠም አይቻልም። ከዚህ አኳያ ዋና ኮሚሽነር መስፍን የተናገሩት ሀሳብ ትክክለኛ ስሜታቸውን ያንጸባረቁበት ነው። አራት ዓመት ረጅም ነው።

በሌላ በኩል አራት ዓመት አጭር ነው። ምክክር ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 ሲቋቋም ከተሰጡት ሰባት ዓላማዎች መካከል አንደኛው “በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለተፈጠሩ ልዩነቶች ወሳኝ ምክንያቶችን በመለየት እና ውይይቶቹ የሚካሄድባቸውን ርዕሰ ጉዳዮች በመለየት ምክክር እንዲደረግባቸው ማመቻቸት” የሚለው አንቀጽ ነው። ይህን ደግሞ “ውጤታማ የሆነ ሀገራዊ የምክክር ሂደት ተግባራዊ ማድረግ” በሚል ጠንካራ ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ አግኝቶ ለማነጋገር ጊዜው አጭር እንደነበር መጥቀሱ ለክርክር አይጋብዝም።

እዚህ ላይ “የተለያዩ የኅብረተሰብ አካላት” የሚለው የአዋጁ መልዕክት የፖለቲካ ልሂቃን ብቻ እንዳልሆኑ፣ ምሁራን የምንላቸው ብቻቸውን እንደማይሳተፉ የሚያረጋግጥ ነው። ይህ በሌሎች ሀገራት ከተከናወኑ ምክክሮች ይለየዋል።

ኮሚሽኑ ከፖለቲካ ወገንተኝነት፣ ከማንኛውም የመንግሥት ወይም ሌላ አካል ተጽዕኖ ነፃ የሆነ፣ ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው አካል ሆኖ በአዋጅ መቋቋሙ፣ ኃላፊነቱ መላውን ኅብረተሰብ ባሳተፈ መልኩ አወያይቶ አጀንዳዎችን ማሰባሰብና ተወካዮችን መምረጥ መሆኑን ያሳያል።



41

ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ዋና ዓላማ አኳያ ለዘመናት የዘለቁ፣ ሥር የሰደዱ ሀገራዊ ልዩነቶችን፣ የታሪክ ትረካዎችን እና ፖለቲካዊ ውዝግቦችን በምክክር ለመፍታት እንዲቻል ሂደቱን ከሥር ጀምሮ ማካሄድ ቀላል ኃላፊነት አይደለም። የብዙ አሥርታት ዓመታት ውስብስብ ችግሮችን በአራት ዓመት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለመፍታት የሚያስችል መፍትሔ ይዞ መምጣት እጅግ አጭር እና ጠባብ የጊዜ ገደብ መሆኑን ላስተዋለ፤ “አራት ዓመት አጭር ነው” የሚለው የፕሮፌሰሩ ሀሳብ ትክክል ነው ማለቱ አይቀርም።

በሌላ በኩልም ከመላው ሀገሪቷ ወረዳዎች የምክክር መድረኮችን ማዘጋጀት፣ ተወካዮችን መምረጥ፣ አጀንዳ ማሰባሰብ እና የሁሉንም ወገኖች አመኔታ ማግኘት ረጅም ጊዜ እና ትዕግሥት የሚጠይቅ ታላቅ ተግባር ነው። ስለሆነም አራት ዓመት ለቴክኒካዊ ሥራው አጭር ነው ቢሉም አይፈረድም።

የፕሮፌሰር መስፍን ሀሳብ በዋናነት የተስፋ እና የትዕግሥት መመጣጠን አስፈላጊነትን ያመላከተ ነው። ሕዝቡ እና ፖለቲከኞች የችግሩን ውስብስብነት በመረዳት ለኮሚሽኑ ሥራ ትዕግሥት ማድረጋቸውን አድናቆት የሚቸር፤ በሌላ በኩል ደግሞ ኮሚሽኑ የሕዝቡን ሥቃይ እና የጊዜውን አጣዳፊነት በመረዳት በፍጥነት እና በትጋት የመሥራቱ ጉዳይ እንቅልፍ እንደነሳቸው የሚያሳይ ነው።

ይህን ሀሳብ ያነሱት በመጨረሻው የስኬት ምዕራፍ ላይ ሆነው፣ አራት ሺህ የሕዝብ ተወካዮች ለምክክር አዲስ አበባ በከተሙበት ቀን መሆኑ የሀሳቡን ተቃርኖ እንድንረዳ ያደርገናል። እዚያው ላይ ኮሚሽነሮቹ ያለፉበትን ጊዜ እናስተውላለን፤ በዘመናቸው ያካበቱትን ዕውቀት ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ፍሬ በሚያፈራ መልኩ ለመስጠት ያለፉበትን ድካም ያሳያል።

የሀሳብ ልዕልና

ሀገራዊ ምክክር ጥልቅ የሆኑ ፖለቲካዊ ቀውሶችን ለመፍታት፣ ልዩነቶችን በመመካከር የጋራ መግባባት ለመያዝ እና ሊመጣ የሚችለውን ችግር ለመከላከል የሚደረግ የሕዝብ ፖለቲካዊ እርምጃ ነው። የተለያዩ ሀገራት በምክክር ችግሮቻቸውን በመፍታት ለጋራ ሀገራዊ ልማት የሚቆሙበትን ሁኔታ ፈጥረዋል።

ሀገራት ከታሪካዊ ግጭቶች፣ ከከባድ ፖለቲካዊ ቀውሶች፣ ከእርስ በእርስ ጦርነቶች እና ከሽግግር ወቅቶች በሰላማዊ መንገድ ለመውጣት ሀገራዊ ምክክርን በሰፊው ተጠቅመውበታል። ዋና ዓላማው የተለያዩ የፖለቲካ፣ የማኅበረሰብ፣ የሃይማኖት፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የሴቶች፣ የወጣቶችና የሌሎች ባለድርሻ አካላት በጋራ በመወያየት ለሀገራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ በመፈለግ ስኬታማ መሆን ነው።

በዓለም ላይ በተለያዩ ወቅቶች ሀገራዊ ምክክርን በተሳካ ሁኔታ ያካሄዱ ወይም የሞከሩ ሀገራት ከሚከተሉት መካከል ይገኛሉ፦

ደቡብ አፍሪካ፦ ከአፓርታይድ (ዘረኛ ሥርዓት) ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸጋገር በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ያካሄደችው እና ተከታታይ የብዙ ፓርቲዎች ድርድር ሂደት በዓለም የተሳካ የሀገራዊ ምክክር ምሣሌ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ሂደት በ1994 ዓ.ም የመጀመሪያውን ነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ መሠረት ጥሏል።

ቱኒዚያ፦ በ2011 ዓ.ም ፍራፍሬ ሻጭ በነበረው ወጣት ሞሃመድ ቡአዚዝ ራሱን በእሣት ማቃጠሉን ተከትሎ በተከሰተው የዓረብ ፀደይ አብዮት፣ ሀገሪቷ ወደ ውስጣዊ ግጭት እንዳትገባ ለመከላከል በሲቪል ማኅበራት የተመራ ሀገራዊ ምክክር አካሂዳለች። በዚህም የተረጋጋች ሀገር መፍጠር ችለዋል።

የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት፦ እንደ ቤኒን፣



42

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ማሊ፣ ኒጀር እና ቶጎ ያሉ ሀገራት በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከአንድ ፓርቲ አገዛዝ ወደ ብዙ ፓርቲ ዴሞክራሲ ለመሸጋገር “ብሔራዊ ጉባዔዎችን” (National Conferences) በሰፊው ተጠቅመዋል። እነዚህ ጉባዔዎች ለፖለቲካ ማሻሻያና ለአዳዲስ ሕገ-መንግሥቶች መዘጋጀት ጠቃሚ ሚና ተጫውተዋል።

ሌሎችም ምክክር በማድረግ የተጠቀሙ ሀገራት እንዳሉ ሁሉ፣ ሳይሳካላቸው የቀሩ መኖራቸውም ይታወቃል። ይህ የሚያሳየው ሀገራዊ ምክክር ለእያንዳንዱ ሀገር እንደ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ሁኔታው በመመካከር ግጭቶችን ለመፍታት፣ ሀገራዊ መግባባትን ለማጠናከር፣ በሕዝብ መካከል መተማመንን ለመፍጠር እና ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት የሚያገለግል መሆኑን ነው።

ሀገራዊ ምክክር ግጭትን ለመፍታት ወይም ለማስቀረት የሚደረግ የመግባቢያ መሣሪያ ነው። ይህም ውጥረቶችን ለማርገብና በጋራ ጠንካራ መሠረት ያላት ሀገር ለመገንባት በተቃራኒ አካላት መካከል በጠረጴዛ ዙሪያ የሚካሄድ ነው። በታላላቅ ፖለቲካዊ ቀውሶች፣ ከግጭቶች በኋላ ባሉ ሁኔታዎች ወይም በታላላቅ ፖለቲካዊ ሽግግሮች ወቅት በሰፊ ሀገራዊ ባለድርሻ አካላት መካከል ስምምነት ላይ ለመድረስ ያለሙ፣ በባለቤትነት የተያዙ ፖለቲካዊ ሂደቶች ተደርገው ሊወሰዱም ይችላሉ።

ምክክር የቀድሞውን ልዩነት በመፍታት፣ በሰጥቶ መቀበል መርህ “እኔ ለጋራ ሁኔታችን ስል ይህን ትቻለሁ”፣ ሌሎች ደግሞ “እኔም ትቻለሁ” በማለት በመግባባት፣ በጋራ ሀገር ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ለመፍጠር የሚረዳ ነው።

ዳንኤል ያንክሎቪች (Daniel Yankelovich) “The Magic of Dialogue: Transform- ing Conflict into Cooperation” በሚለው መጽሐፋቸው፦ “ምክክር ማለት እርስ በእርስ በመደማመጥ እና በመከባበር አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን ወደ ተሻለ ትብብርና የጋራ ግንዛቤ የመቀየር ጥበብ ነው” በማለት የምክክርን ፋይዳ ይገልጹታል። እንደ ያንክሎቪች ገለጻ ምክክር የዕለት ተዕለት ወሬ ሳይሆን ልዩ ክህሎትና ትዕግሥት የሚጠይቅ ሂደት ነው። ሰዎችን የሚያራርቁ አመለካከቶችን፣ አለመተማመኖችን እና የባህል ልዩነቶችን ለማጥበብ እውነተኛ ምክክርን መለማመድ ትብብርንና ስኬትን ያመጣል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር መነሻና መድረሻው ለዘመናት በተፈጠሩት ልዩነቶች ላይ በጥልቀት በመምከር ሀገራዊ መግባባትን የሚፈጥሩ አንኳር ምክረ-ሐሳቦችን ማመነጨት ነው። በምክክር የሚፈጠረው የፖለቲካ አስተሳሰብ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እሳቤዎችን ለማጠናከር የሚረዳ፣ ጠንካራ ተቋማትን የመፍጠርና የማሳደግ እንዲሁም በመንግሥትና በሕዝቡ መካከል ጠንካራ ማኅበራዊ ውል መፍጠር የሚያስችል፣ መሠረታዊና የወደፊቱን የሚያይ ይሆናል።

የታሪክ ኤምሬተስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ እንደገለጹት፤ ሀገራዊ ምክክሩ ሥር የሰደዱ ችግሮች የሚፈቱበት አማራጭ የሌለው ሂደት ነው። ኢትዮጵያዊያን ከሚያራርቋቸው ጉዳዮች ይልቅ የሚያቀራርቧቸው ይበልጣሉ። “ይህም ምክክሩ ችግሮችን በሰከነ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ልዩ የታሪክ አጋጣሚ ነው” በማለት በቃላቸው ያጸኑታል።

ይህ የጋራ መግባባትና ስምምነት ሲፈጠር ተቋማዊ ለውጥ እና ለጠንካራ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ትልቅ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው።

“ሀገራዊ ምክክሩ በመመካከርና በመነጋገር የጋራ ግንዛቤ የሚፈጠርበት ትልቅ መድረክ ነው። ይህ ሂደት ኢትዮጵያን በተሟላ ሁኔታ ተጠቃሚ እንደሚያደርግና ምክክሮቹም ወደ ሀገራዊ መግባባት የሚወስዱ ናቸው” በማለት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማካሪ ፕሮፌሰር አድማሱ ገበየሁ የገለጹትን ሀሳብ እዚህ ላይ መጥቀስ ተገቢ ነው።

አሳታፊነትና አካታችነት

“ሀገራዊ የምክክር ጉባዔው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በእኩልነት የሚመክሩበት ነው” በማለት ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የገለጹት ሀሳብ ተጨባጭ መሆኑን ለማስረገጥ ትንሽ ወደ ኋላ ዞር ብሎ መመልከት ያስፈልጋል። ኮሚሽኑ ከተመሠረተበት ጊዜ



43

ጀምሮ ያከናወናቸው ተግባራት ለዚህ ዓቢይ ምስክር ናቸው።

የሀገራዊ ምክክር ሂደት ውጤታማ እና ተአማኒ እንዲሆን ጽንሰ-ሀሳቡን በጥልቀት መረዳት፣ በቂ የቅድመ-ዝግጅት ጊዜ መውሰድ፣ አጀንዳዎችንና ተሳታፊዎችን በጥንቃቄ መለየት እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን በሁሉም ደረጃ ማሳተፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው። በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዝግጅት ምዕራፉ በፊት የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን፣ የአዋጁን ዓላማና ይዘት በጥልቀት በመረዳት፣ ከተዛማጅ ተቋማትና ባለሙያዎች ጋር በመመካከር እንዲሁም የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮና የምርምር ግኝቶችን በማጥናት ለሂደቱ የሚመጥን ተቋማዊ አቅም ለመገንባት ጥረት ማድረጉ አሁን ለደረሰበት ደረጃ መልካም መሠረት ሆኖታል።

ኮሚሽኑ በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት በመድረስ ሕዝብ አወያይቷል። በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ- ኢትዮጵያዊያንም እንዲሳተፉ በማድረግ አጀንዳዎቻቸውን ተቀብሏል። በዚህም ግልጽና አሳታፊ የምክክር ምዕራፎችን አልፏል። በምክክር ሂደቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ 1 ሺህ 234 ወረዳዎችን በመሸፈን ተደራሽነቱን በግልጽ አሳይቷል።

በተለይም ምክክሩ “ከታች ወደ ላይ” የሚለውን አካታች ስልት በመከተል ከወረዳ፣ ከክልል፣ ከፌዴራል፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማኅበራት እንዲሁም በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን ጋር በመወያየት አጀንዳዎችን አሰባስቧል።

ታጥቀው ወደ ጫካ ገብተው የነበሩ አካላት እንኳ “ከተመካከርን ነገ ተስፋችን ይለመልማል፤ ጥያቄያችንም ይመለሳል” በማለት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥተዋል። ዛሬም የዚሁ ሂደት ተወያይ እና ተሳታፊ ሆነዋል።

ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ከተሳተፉበት ሰፊ ሂደት የተቀዱ የሀገር ግንባታ፣ የመንግሥት አደረጃጀትና የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፌዴራል ከተሞች ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች፣ የተቋማት ግንባታና የሕግ የበላይነት፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣ ሙስናና መልካም አስተዳደር እና የሰላም ግንባታ (ስምንት) ዋና ዋና አጀንዳዎች ለዋናው ጉባዔ ተለይተው ቀርበዋል፦

እነዚህ አጀንዳዎች ሙሉ በሙሉ ከታች ወደ ላይ የተሰበሰቡ ናቸው። አጀንዳዎቹ በተሰበሰቡበት ወቅት ተሳታፊዎቹ “ድምፃችንን ያሰማሉ፣ ሀሳባችንን ያጋራሉ” ያሏቸውን ተወካዮቻቸውን መርጠዋል። ለዚህም ነው አራት ሺህ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ ላይ ከትመው በእነዚህ አጀንዳዎች ላይ የመከሩት።

“ትናንት አባቶቻችንና እናቶቻችን በዓድዋ ለሀገር ነፃነት፣ ለሉዓላዊነትና ለክብር ሲሉ በደማቸውና በአጥንታቸው እንደተዋደቁላት ሁሉ… ዛሬ ሀገራችን የምትሻው ጠመንጃ ያነገቡ ሳይሆኑ በሃሳብ ብስለት፣ በእውነት፣ በዕውቀትና በጽናት ታጥቀው የተሰናዱ የሰላም ታጋዮችን ነው” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የሰላም አርበኞች ኢትዮጵያን ለማሻገር እየተጉ ይገኛሉ።

እንደ መውጫ

“ሀገራዊ ምክክሩ የጋራ ዕድል ፈንታን ለመወሰን እንጂ፣ አሸናፊና ተሸናፊን ለመለየት የሚደረግ አይደለም” በማለት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እንደገለጹት፤ ከምክክሩ የሐሳብ ልዕልና ገዝፎ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና ወደ ከፍታ በሚያደርሳት ሰረገላ ላይ ትሆናለች።

ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸው አንድነት፣ ለመጪው ትውልድ ትሩፋት ከምክክሩ የሚጠብቁት የኢትዮጵያን ብሩህ ዘመን የሚያበስር፣ ከፍታዋን የሚያረጋግጥና ዘመኗን ለመዋጀት የሚያስችላትን አቅም ነው። የኢትዮጵያዊያንን ሰላም ቀምተው፣ የራሳቸውን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚሹ የውጭ ጠላቶች፣ ትልቁን ሀገራዊ ጉዳይ ከማየት ይልቅ በጥቃቅን ጉዳዮች የሀገራቸውን ጥቅም አሳልፈው የሚሰጡትን የሚያሳፍር ውጤት ተገኝቷል። ኢትዮጵያዊያን መክረው ያመጧቸው ምክረ-ሐሳቦች ወደ ተግባር ሲተረጎሙ የሀገራችንን ኃያልነት የማረጋገጥ አቅም ይኖራቸዋል።

ኢትዮጵያዊያን ተመካክረው ከደረሱባቸው ውጤቶች መካከል ማኅበራዊ ውላቸውን ማደስ የሚያስችላቸውን ግዙፍ ሐሳብ ማፍለቃቸው ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያዊያን በመካከላቸው ልዩነት የፈጠሩባቸውና የተመካከሩባቸው ስምንት አጀንዳዎች ሊያግባቧቸው በሚችሉት እና ለጋራ ሰላምና መተማመን የጋራ ስምምነት የፈጠሩባቸውን በምክረ ሀሳብ አስረክበዋል።

ዛሬ ሕግ እና መንግሥታዊ ሕጋዊነት የሚገኙት ሕዝብ በሙሉ ፈቃደኝነት ከሚሰጠው መብት መሆኑን የሚያረጋግጡበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህም በኢትዮጵያ ምድር አብሮነታችን ሳይናጋ፣ ልዩነታችን እንደተጠበቀ ሆኖ “እንዴት እንኑር?” ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል።

በዚህ ማኅበራዊ ውል መሠረት ዜጎች ለመንግሥት ታዛዥነታቸውንና ግብራቸውን በሕግ ሲያስረክቡ፣ መንግሥት ደግሞ የዜጎችን ደኅንነት፣ ፍትህ፣ ነፃነት እና እኩልነት የማስከበር ግዴታውን የሚወጣበት መሠረታዊ ውል ይፈጸማል። በዚህም የጋራ እሴቶችና መብቶች ጎልተው ይወጣሉ። በሀገሪቷ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ሥርዓት ውስጥ አብዛኛው ሕዝብ የሚስማማባቸው የጋራ መብቶች ዕውቅና ያገኛሉ። አዲሱ ማኅበራዊ ውል ሕዝቦች



44

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

በቃላቸውና በልባቸው የሚቀበሉት የጋራ ሕልውና መሠረት ይሆንላቸዋል።

ሌላው ከምክክሩ ከመነጩት ምክረ ሀሳቦች መካከል፤ የተቃረኑ ታሪካዊ ትረካዎችን ማስታረቅ የሚችል የሀሳብ ልዕልና የሚገለጽበት ስልት ነው። የጋራ የሆኑ ታሪኮችን በማጉላት እና አወዛጋቢ የታሪክ ጠባሳዎችን በይቅርታና በእውነት ላይ ተመስርቶ በመፈተሽ ለጋራ ሀገራዊ ማንነት ጠንካራ መሠረት መጣልም የምክክሩ ትሩፋት ነው።

በኢትዮጵያ በብሔሮች፣ በማኅበረሰቦች ወይም በፖለቲካ ኃይሎች ዘንድ የተለያዩና አንዳንዴም ለግጭት የዳረጉ ትርክቶችን በእውነት ላይ ፈትሾ ወደ ጋራ መግባባት በመምጣት፣ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ታሪኮቻቸው ላይ እንዲያተኩሩ ማድረግ ልዩ በረከት ነው። ለአንዱ ጀግና ለሌላው በዳይ የሆነበትን ትረካ በመተው፣ በግዙፉ ምስል ላይ በማተኮርና በሚያግባባው ጉዳይ ላይ በመመካከር ውሳኔ ላይ ተደርሷል።

ለዚህ ደግሞ በምክክሩ ሂደት አንዱ የሌላውን ሕመም እና እውነት መቀበል፣ ታሪክን ለጭቅጭቅና ለልዩነት መሣሪያ ከማድረግ ይልቅ ለወደፊት ጠንካራ ሀገር ግንባታ ማዋል፣ እንደ ታላቁ ዓድዋ ያሉ ከሀገር አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ የገዘፉ የጋራ ታሪኮችን ማጉላት፣ ጉዳትና ቁርሾ ያስከተሉ የታሪክ ክስተቶችን በይቅርታ ማለፍ የሚያስችሉ የምክክር ትሩፋቶች መገኘታቸው ነገን በናፍቆት ያስጠብቃል።

“እውነቱን ማውጣትና ታሪክን በጋራ መገምገም ለዘላቂ ሰላም መሠረት ነው” በማለት ማርታ ሚኖው (Martha Minow) “Between Vengeance and Forgiveness” በሚለው መጽሐፏ የጠቀሰችውን ሐሳብ መጋራት ያስፈልጋል። በታሪክ ዛሬ ታሞ ነገን መግደል አያስፈልግም።

በምክክሩ “አንዳንድ አጋጣሚዎች ያሻችሁን እንድትጽፉ ብዕርና ብራና ያቀብሏችኋል… ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ በገዛ እጇ አዲስ ታሪክ ለመጻፍ የሚያስችላትን ‘ብዕርና ብራና’ ያገኘችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም ተሞክሮ የሚሆን የአሸናፊነትና የበላይነት አዲስ ታሪክ ጽፋለች።

ማጠቃለያ

“የማይታረቁ ሀሳቦች በአዳራሽ ውስጥ ገብተው ታርቀዋል። ተግባብተዋል። ተስማምተዋል። ቅንነትንም ፍለጋ ይዘው ሂደዋል። እውነትንም ፍለጋ ይዘው ሂደዋል። ‘የኢትዮጵያ ከእኛ ያለፈ ለነገይቱ ኢትዮጵያ’ የሚል ሀሳብ መጥቷል” በማለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አዝመራው አንደሞ የምክክሩን ትሩፋት የገለጹበት ሀሳብ የከበረ ነው።

ኢትዮጵያዊያን በምክክር ከግጭት ወደ መደማመጥ ባህል መሻገርን፣ የመፍትሄ ሀሳብ



45

ከምክክሩ ከመነጩት ምክረ ሀሳቦች መካከል፤ የተቃረኑ ታሪካዊ ትረካዎችን ማስታረቅ የሚችል የሀሳብ ልዕልና የሚገለጽበት ስልት ነው። የጋራ የሆኑ ታሪኮችን በማጉላት እና አወዛጋቢ የታሪክ ጠባሳዎችን በይቅርታና በእውነት ላይ ተመስርቶ በመፈተሽ ለጋራ ሀገራዊ ማንነት ጠንካራ መሠረት መጣልም የምክክሩ ትሩፋት ነው።

በማመንጨት ምክረ ሀሳብ ማቅረብን፣ የሀሳብ ልዕልና እንዲገዝፍ ዕድል መስጠትን ከምክክሩ ያገኟቸው ትሩፋቶች ናቸው።

የሀገራዊ ምክክር ጉባዔው ታሪካዊ ሂደት፣ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ወሳኝ ጉዳዮች ላይ በሰከነ መንፈስ፣ በግልጽነትና በጋራ መግባባት ለመመካከር ባሳዩት ቁርጠኝነት በርካታ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ምክረ ሀሳቦች ተገኝተዋል።

እነዚህ ምክረ ሀሳቦች ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት ይሰነዳሉ። በአሁኑ ወቅት “በምክክሩ ሂደት የተነሱ አጀንዳዎችን፣ የተካሄዱ የምክክር ሂደቶችን እና የተገኙ ምክረ ሀሳቦችን በየፈርጃቸው የማደራጀትና የማጠናቀር ሥራ እያከናወነ ይገኛል” በማለት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማስታወቁን እዚህ ላይ መጥቀስ ይገባል።

የምክክር ሰነዶችና ምክረ ሀሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለአስፈጻሚ አካላት ይቀርባሉ፤ ለአገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ማኅበረሰብ ክፍሎችም በይፋ ተደራሽ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኮሚሽኑ በአዋጁ እንደተደነገገው፤ መንግሥት የሀገራዊ ምክክሩን ግኝቶችና ምክረ ሀሳቦች በተግባር ለመተርጎም የሚያስችል ግልጽ፣ ተጨባጭና ውጤታማ ዕቅድ እንዲያዘጋጅ አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ ያደርጋል።

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ሀገራዊ መግባባትና የጋራ መጻኢ ዕድል እንዲጠናከር የድርሻውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይጠበቃል።

በአርባ ቀናት ውስጥ በተደረጉ ምክክሮች የተገኙት ምክረ ሀሳቦች እየተመነዘሩ ነገን ይገነባሉ። ትውልድ መጪውን ዘመን በሰላም፣ በመግባባት ይዘልቃል። በሀሳብ ልዕልና የሚታተም አዲስ ማኅበራዊ ውል የዛሬውን መሠረት አጠንክሮ ነገን በዘላቂነት ይገነባል።



46

ማኅበራዊ

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

የአዲስ ዘመን አዲስ ምዕራፍ



47

በሰለሞን ተሰራ

የአዲስ ዘመን አዲስ ዓመት እንደ እሸት መሬት ይመሰላል፤ ምንም እንዳልተነካ ድንግል መሬት፤ ዘር እንዳልተዘራበት ባዶ መስክ፤ አረንጓዴ ተስፋ እንዳዘለ ድንግል መሬት። ብሩህ ተስፋ የሰነቅነው እኛ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በዚህ ጠፍ መሬት ላይ የላባችንን እና የጥረታችንን ፍሬ ለማኖር ቆርጠን የምንነሳበትና አዲስ ብርሃን የሚፈነጥቅበት ነው።

አሮጌው ዓመት የመጨረሻዎቹን ቀናት በትዝታ ሲያጠናቅቅ፤ ኢትዮጵያዊያን በምናባችን ሰፊ የሸራ ሰሌዳ ላይ አዲስ ርዕይ፣ አዲስ ተስፋና አዲስ መዳረሻ መሳል እንጀምራለን። አዲሱ ዓመት ተራ የዘመን መለወጫ ሳይሆን፤ ይልቁንም በውስጣችን የቀበርናቸውን ታላላቅ ሕልሞችና ተስፋዎች ዳግም ቆፍረን በማውጣት ራሳችንን ወደ ስኬት ማማ ለማሸጋገር የምንደክምበት፣ ውስጣችንን ከአልችልም መንፈስ በማላቀቅ ሀገራችን ከደረሰችበት አዲስ ምዕራፍ ጋር ራሳችንን ለማስተሳሰር ሥራ የምንጀምርበት ወቅት ነው።

የክረምቱ ጨለማ ተገፎ ሰማይ በደማቅ ብርሃን ስትሞላ እኛም ካለፉት ዓመታት ስህተቶቻችን ብዙዎችን አራግፈን በመጣል ነጋችንን ለማሳመር ዛሬ በድፍረት መቆም እንዳለብን የምንወስንበት ነው አዲስ ዓመት። ፍርሃትና ጥርጣሬን በአሮጌው ዓመት መቃብር ላይ በመጣል፤ በውስጣችን የሚመላለሰውንና “እችላለሁ” የሚለውን ብቸኛ ስሜት የድል ብስራት ነጋሪታችን በማድረግ ወደ ስኬት ማማ የምንገሰግስበትም ነው።

በምናባችን ያስቀመጥናቸውንና በዕቅዳችን ያካተትናቸው ስኬቶች እውን የሚሆኑት ዕለት በዕለት



48

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ያለድካም በምናከናውነው ሥራና በሥነ ልቦና ጥንካሬያችን ብቻ ሳይሆን በሀገራችን የሰላም መሠረት ላይ ነው። “እችላለሁ” የሚለው አዲሱ የብርታት መፈክራችን በየማለዳው ከአልጋችን የሚቀሰቅሰን ታላቅ ኃይላችን ነው። በአዲሱ ዓመት ዕውቀታችንን ለማስፋት፣ ስብዕናችንን በበጎ መንፈስ ለመገንባትና ሰላማችንን ለማደስ አዳዲስ ልማዶችን መተግበር ግድ ይለናል። በዙሪያችን ከሚገኙ ሰዎች ጋር ስለ ሰላም በመዘመርና ለሰላም በመሥራት፣ የፍቅርና የመደጋገፍ ድልድይ በመገንባት፣ ሕይወታችንን በደስታና በትርጉም ለመሙላት ማንኛውንም መስዋዕትነት መክፈል ደግሞ ቀጣዩ ሥራችን ይሆናል።

በአዲሱ ዓመት ከብዙ ጨለምተኞችና የሰላም ፀሮች የፈተናዎች ማዕበል ሊያጋጥመን እንደሚችል እንገምታለን፤ ነገር ግን የሰነቅነው ተስፋ እና በዕቅዳችን ያስቀመጥናቸው ግቦች ከማንኛውም ማዕበል በላይ የጠነከሩ ናቸው። ነገን በብሩህ ዓይን እንመለከተዋለን፤ ምክንያቱም ብርሃኑ ያለው ከውጭ ሳይሆን ከውስጣች ነውና። ሀገራችን በሁሉም መስኮች ያስመዘገበቻቸውና ዓለም የተደመመባቸው የልማት ስኬቶች ደግሞ የሕልማችን መዳረሻ፣ የተስፋችን ማሳረጊያና የነጻነታችን ሃውልት በመሆን ያገለግሉናል።

የሕልማችን አዲስ አሻራ

የአዲስ ዓመት መጋረጃ ተገልጦ፤ የአሮጌው ዓመት የመጨረሻ ፅልመት በዝምታ ሲሸኝ፤ በውስጣችን አዲስ የስኬት ብርሃን ይበራል። አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያዊያን ተራ የዕለታት



49

መፈራረቅ ሳይሆን፤ በምናባችን ማህፀን ውስጥ ለረጅም ጊዜ የኖሩ የብርሃን ሕልሞቻቸን የሚወለዱበት፣ የተስፋ ክንፎቻችን የሚዘረጉበት የነገ ተስፋችን እውን እንደሚሆን መለከት የሚነፋበት ነው።

አዲሱ ዘመን የነገን ስንቅና ፍሬ አምቆ የያዘ ለምለም መስክ ነው። ያለፉት ዓመታት ውድቀትና ድክመቶቻችንን በማረም የጥረታችንን ፍሬ የምንለቅምበት ብሩህ ነጋችን ነው። ፍርሃትን፣ ጥርጣሬን፣ ክፋትን፣ ጥላችን፣ ብሔርተኝነትን፣ ሌብነትን እና የትናንትናን ክፉ ጥላ በጨለማው ከርሥ ውስጥ ቀብረን ዛሬን በብርቱ እምነትና በልዩ ወኔ የምንጋፈጥበትም ነው አዲሱ ዓመት። እያንዳንዱን ቅፅበትና እያንዳንዱን ቀን በሕይወታችን ላይ ለውጥ ወደሚያመጣ ብርቱ ሃብት ለመቀየር የምንተጋበትም ነው።

ይህ ዘመን የህልማችን ጥማት የሚቆረጥበት፣ እንደ ሀገር በሁሉም መስክ የጀመርነውን ስኬት ወደ ከፍታ የምናሸጋግርበት ልዩ የጸደይ ወራት እንደሚሆን ጥርጥር የለንም። በውስጣችን አምቀን ያስቀመጥነውና በየማለዳው የሚቀሰቅሰን የመዳረሻ ግባችን የብርታትና የጥንካሬ መፈክራችን፣ በፈተናዎች መካከል እንደ ቋጥኝ የሚያቆመን ጠንካራ ምርኩዛችን ነው። ግባችንን ለማሳካት ብቻችንን መፍጨርጨር ዋጋ ስለማይኖረው አንድ ሀገር አንድ ሕዝብ በሚል ብሔራዊ ስሜት እጅ ለእጅ ተያይዘን የልማት አጋርነት በመፍጠር የሃሳብ ልውውጥ በማድረግና በመመካከር፣ የስኬታችንን ድልድይ በጋራ መገንባት የአዲሱ ዓመት ቀዳሚ ግባችን ሊሆን ይገባል። ማዕበልና አውሎ ነፋስ ቢወዘውዙንም፤ በውስጣችን ያነገብነው የተስፋ መልህቅ በጋራ ማንነታችን የታነፀ በመሆኑ ምንም አይነት ወጀብ አያናውጠውም።

የሀገራችን የብልፅግና ንጋት ሩቅ ሳይሆን ቅርብ ነው፣ የስኬት ጉዞዋ ደግሞ የውስጥ ብርሃናችን ፍልቅላቂ ነው፤ እኛ ኢትየጵያዊያን የነገ ፈጣሪ፣ የሕልሞቻችን መሀንዲስ ነን። አዲሱ ዓመት የጉልበታችን ጥንካሬ የሚታይበት፣ የሀሳብ ልዕልናችን አሸናፊነት የሚጎላበትና የድል አክሊላችንን የምንጎናፀፍበት ነው።

የማንነት አዲስ መባቻ

ዘመን የቀን ለውጥ ብቻ ሳይሆን፣ እኔነትም አብሮ የሚለወጥበት ድንቅ የተፈጥሮ መስተጋብር ነው። መስከረም ሲጠባ፣ የምድር አረንጓዴ ካባ መደረብና የአደይ አበባ ወርቃማ ፈገግታ በውስጣችን አዲስ የሕይወት እስትንፋስ ይዘራሉ። የሥነ ልቦና ምሁራን ይህንን ስሜት “የአዲስ ጅማሮ ውጤት” (Fresh Start Effect) በማለት በምሁራዊ እይታ ቢተረጉሙትም፤ ለሰው ልጅ ግን የማንነቱ ነፃነት አዋጅ እና



50

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

የውስጡ ድብቅ ዜማ ናቸው።

ባለፈው ዓመት ማዕበል የበዛበትን የሕይወት ውቅያኖስን አቋርጠን ይሆናል። የታቀዱና ያልተሳኩ ግቦች፣ ያጋጠሙን ውድቀቶችና ስህተቶች የልባችንን ስንቅ አክብደውትም ይሆናል። ይሁን እንጂ ታዋቂው የሥነ ልቦና ምሁርና የሥነ ማንነት ግንባታ መሀንዲስ ቪክቶር ፍራንክል እንደሚያስተምረን በደረሰብን መከራ እና በምንሰጠው ምላሽ መካከል ሰፊና ነፃ የሆነ ክፍተት አለ። በዚያ ክፍተት ውስጥ ደግሞ ምላሻችንን በራሳችን የመወሰን ሙሉ ሥልጣንና አቅም አለን። ሁላችንም በዘመን መለወጫ ዋዜማ የትናንቱን ከባድ ሸክም አራግፈን በመጣል የነገ አዲስ ግባችንን ለማሳካት የምንወስንበት አዲስ ቀን መሆኑንም የሥነ ልቦና ባለሙያው ጠቁሞናል።

በአዲስ ዓመት የሰነቅነው አዲስ ተስፋ በምኞት የሚዳክር በባዶ ሰማይ ላይ ያለአቅጣጫ የሚንሳፈፍ ደመና እንዳይሆን የሚረዳንን ምክር ከሌላዋ የሥነ ልቦና ጠቢብ ማርሻ ሊንሃን የዕውቀትና የሕይወት ተሞክሮ እንጋራ፤ ምሁሯ እንደምትለው “ቁጭ ብሎ በማለም ብቻ አዲስ ማንነትን መቅረጽ አይቻልም፤ ይልቁኑ እግሮቻችን በአዲስ መንገድ መራመድ ሲጀምሩ፣ አዕምሯችንም አዲሱን የብርሃን መንገድ መከተል ይጀምራል” ትላለች። ስለዚህ ከአቅማችን በላይ የሆኑ ከባድ ዕቅዶችን በማውጣት ራሳችንን በጭንቀት ሰንሰለት ከመቀፍደድ ይልቅ በየቀኑ ፍሬ የሚያፈሩና በተግባር ሊተረጎሙ የሚችሉ የሕይወት ዘሮችን በመዝራት የሀገራችንንም፣ የራሳችንንም ነገ ለማሳመር እንትጋ።

አሜሪካዊው የሥነ ልቦና አባት ዊሊያም ጄምስ “ከዚህ በኋላ መሆን የምትፈልገውን ማንነት፣ ከዛሬ ጀምረህ መኖር ጀምር” እንዳለው፤ እኛም አዲሱን ዓመት ሀገራችን ከእኛ የምትፈልገውንና እኛም ልንሰጣት የምንችለውን ፍሬ ከአሁኑ በመዝራት ለልጆቻችን የምትመች ታዛ ለመሥራት ጉዟችንን እንጀምር። አዲሱ ዓመት ዕድሜያችን ብቻውን የሚጨምርበት ተራ የቁጥር ሰንሰለት ሳይሆን አመለካከታችንን በተግባር የምንቀይርበት፣ አፍራሽ ሀሳቦችን በብርሃን እሳቤዎች የምንተካበት እና በሕይወታችን አዲስ ታሪክ የምንፅፍበት ወርቃማ ጊዜ ነው። አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋ ነው፤ ያ ተስፋ ደግሞ የሚጀምረው ከራሳችን አዕምሮ መታደስና ዛሬ ከሚፈነጥቀው የተግባር ብርሃናችን ነው።

የኢትዮጵያ ትንሣኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የአዲስ ዓመትና የአዲስ ተስፋ መግለጫ እሳቤዎችን በተለያዩ ምሶሶዎች ይመስሏቸዋል። ቀዳሚው ማንጠሪያቸው ጊዜን በአግባቡ መጠቀም እና ሥራ (Utilizing Time and Hard Work) ሲሆን ይህንኑ ከግብ ለማድረስ ደግሞ የተግባር ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ያሰምሩበታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ጊዜን በአግባቡ መጠቀም”



51

ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣሉ። ያለ ዛሬ ታታሪነትና ጠንካራ ሥራ ያለፉ ስኬቶች ዋጋ እንደሚያጡና ሀገር ወደኋላ እንደምትቀር በተደጋጋሚ ያስገነዝባሉ። የዕለት ተዕለት ትጋት፣ እያንዳንዱን ቀንና እያንዳንዱን ወቅታዊ ዕድል በመጠቀም ማምረት፣ መሥራትና መጽናት ደግሞ ተስፋን ወደ እውነት የመቀየሪያ ብቸኛ መንገድ እንደሆነ ይገልጻሉ።

በተጨማሪም ያለፉ ቁስሎችን መፈወስ (Healing Past Wounds) የአዲስ ምዕራፍ መክፈቻ መሆኑን አበክረው ያስገነዝባሉ፡፡ “አዲስ ዓመት ያለፉ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ቁስሎችን የምናክምበት፣ አሮጌ ቂምና ስብራቶችን የምንጠግንበት መሆን አለበት” ይላሉ። ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ ቅርስ መተው ደግሞ የእያንዳንዱ ዜጋ ግዴታና የውስጥ እርካታ ምንጭ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ትናንትን በመተው ዛሬ ላይ የምንገነባው ሰላምና አንድነት ልጆቻችን የሚኮሩባትን የበለጸገች ሀገር የማስረከቢያ መሰረት እንደሆነ ያምናሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሁሉ ነገር መሰረት መሆኑን በአጽንኦት የሚያሳስቡበት የመደመር እሳቤ የእኛነታቸን መጋመጃ ዋነኛው ምሰሶ ነው ይላሉ፡፡ የመደመር እና የኅብረት አቅም (Resilience and Cooperation) የጋራ ጥንካሬ እንደሚፈጥር ብዙ ማሳያዎችን በማንሳትም ያስረዳሉ፡፡ እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ (GERD) ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን አብነት በመጥቀስ አዲስ ተስፋ የሚለመልመው ኢትዮጵያዊያን በኅብረትና በመደመር ሀሳብ በአንድነት ሲቆሙ ብቻ ነው ይላሉ። “ሌሎች የሚወረውሩብን እንቅፋት ሁሉ ወደ ላይ ሊገፋን ይገባል” በማለት አሸናፊትን የሚያንፀባርቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የማይደረስበት ተራራና የማይሳካ ህልም እንደሌለ ያሰምሩበታል።

ከሁሉ በላይ የሰላም ሻምፒዮን መሆን (Champions of Peace) የአስተሳሰብ ብስለት ማሳያ እንደሆነ የሚያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አዲሱ ዘመን የሚፈልገው ጠመንጃ ያነገቱ ሰዎችን ሳይሆን በአስተሳሰብ ብስለት፣ በእውነት፣ በዕውቀትና በሰላማዊ ውይይት ሀገራዊ መግባባትን የሚፈጥሩ “የሰላም ጀግኖችን” ነው ብለው ያምናሉ።

በሀገራዊ ምክክር - ወደ አዲስ ተስፋ

የዘመን መለወጫ በራሱ አዲስ ተስፋን፣ አዲስ እቅድን እና አዲስ ጥንካሬን ይዞ የሚመጣ የተፈጥሮ ስጦታ ነው። ይሁን እንጂ ለኢትዮጵያዊያን ዘንድሮ የምንቀበለው አዲስ ዓመት ከወትሮው የተለየ ትርጉም ያዘለ ነው። ሀገሪቷ ለዘመናት የተሸከመቻቸውን ውስብስብ የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ስብራቶች በዘላቂነት ለመጠገን ያከናወነችው ታሪካዊው ሀገራዊ ምክክር ፍሬ ማፍራት መጀመሩ በግልጽ መታየቱ አዲሱን ዓመት የተለየ ያደርገዋል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባሕል በብሔር አንጓ የተተበተበ፣ ጎጠኝነት የሞላበት፣ በጠላትነት፣ በቂም በቀል እና ልዩነቶችን በኃይል ለመፍታት በመሞከር የተሞላ እንደነበር የአደባባይ ምስጢር ነው። ይህ አካሄድ ለሀገሪቷና ለሕዝቧ ከውድመት እና ከልብ ስብራት ውጭ ያተረፈው አንዳች ነገር የለም። ላለፉት አራት ዓመታት በተደረገው ከፍተኛ ጥረት እውን የሆነው ሀገራዊ ምክክር ግን ይህንን የጥፋት አዙሪት የሰበረ አዲስ የታሪክ እጥፋት ሆኖ ተመዝግቧል። በሺህዎች የሚቆጠሩ የሀገር ልጆች የተለያዩ አመለካከቶቻቸውን ይዘው፣ በመላ ሀገሪቷ የሚገኙ ብሔሮችንና ብሔረሰቦችን እንዲሁም ማኅበራዊ ክፍሎችን ወክለው በአንድ አዳራሽ ተቀምጠው፣ በመከባበር ተደማምጠው፣ ይበጃል ያሉትን ወስነው በፍቅር ተለያይተዋል። ምክክሩ “ችግሬ ከችግርህ አይበልጥም” የሚል ሰብዓዊ እና ብልህ እሳቤ የተንጸባረቀበት፣ ጥላቻን በሠለጠነ የሃሳብ የበላይነት ለመተካት የተደረገ ታላቅ የሽግግር ምዕራፍ ነው።

የምክክር ጉባዔው ስኬታማ የሆነበት ዋነኛ ምክንያት አካታችነቱ ነው። በሰፊ የሕዝብ ተሳትፎ የተመረጡ ተወካዮች በዋና ዋና የሀገር ግንባታ አጀንዳዎች ላይ በነጻነት ተከራክረዋል። በምክክር ሂደቱ የተለያዩ ቅራኔዎች እና ቅሬታዎች ቢንፀባረቁም በውይይቱ ማጠናቀቂያ በተነሱት አጀንዳዎች ላይ 99 በመቶ የምክረ ሃሳብ ስምምነት መደረሱ የሚደነቅ ስኬት ነው። በተለይም የሴቶችና የወጣቶች ድምፅ በጉልህ መሰማቱ የነገዋ ኢትዮጵያ በልጆቿ እኩልነት እንድትገነባ መሠረት ለመጣሉ ዋነኛው ማሳያ ነው።

እያንዳንዱ አዲስ ምዕራፍ የራሱ ፈተናዎች እንዳሉት አይካድም፡፡ በዚህ ረገድ አዲሱ ዓመት እነዚህን ክፍተቶች በመለየት በጋራ መክረን ቀዳዳውን የምንደፍንበት እንጂ ቂም ቋጥረን የምንከርምበት መሆን የለበትም። በምክክር ሂደቱ የተገኘው ትልቁ ዕድል ኢትዮጵያዊያን



52

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ተቀምጠው መነጋገር እንደሚችሉ በተግባር ማረጋገጣቸው ነው። በአዲሱ ዓመት ትልቁ የቤት ሥራ ምክረ ሃሳቦቹን ወደ መሬት ማውረድ እና የተገኘውን የሰላም አየር ዘላቂ ማድረግ ነው።

ማንኛውም ሀገር ከገጠመው ዘላቂ ስብራት ወጥቶ አዲስ የተስፋ ምዕራፍ መጀመር የሚችለው በሕግ እና በፖለቲካዊ ውሳኔዎች ብቻ አይደለም። ይልቁንም በማኅበረሰቡ ውስጥ ትልቅ የመደመጥ እና የመከበር አቅም ያላቸው መሪዎች ኃላፊነታቸውን በጋራ ሲወጡ ነው። ኢትዮጵያ ካካሄደችው ታሪካዊ ሀገራዊ ምክክር ማግሥት ወደ አዲስ ዓመት ስትሻገር የተፈጠረውን አዲስ ተስፋ ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለመቀየር ከእምነት አባቶች፣ ከፖለቲከኞች እና ከታዋቂ ሰዎች ብዙ ይጠበቃል።

የእምነት አባቶች የሕሊና እና የሰላም ጠባቂዎች መሆን እንዲሁም በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ውስጥ ካላቸው የላቀ የሞራል የበላይነት አንጻር ለሰላም ግንባታ ዋነኛ ምሰሶዎች ናቸው። በጥላቻ፣ በጥርጣሬና በግጭት የቆሰሉ ልቦችን የመፈወስ ታላቅ ኃላፊነት የወደቀው በእነርሱ ትከሻ ላይ ነው። በዚህ አዲስ ምዕራፍ የእምነት አባቶች ከተለመደው የሃይማኖት ስብከት ባሻገር ይቅርታን፣ እርቅና የወንድማማችነትን እሴቶችን በተግባር ሊሰብኩ ይገባል። ግጭቶች እና አለመግባባቶች ሲነሱ ወገን ሳይለዩ በመሃል ገብተው የማስታረቅ እና የሰላም አምባሳደር የመሆን ሚናቸውን ማጠናከር ይኖርባቸዋል። ማኅበረሰቡ ከሰነፍ ወሬ እና ከአግላይ አመለካከቶች ወጥቶ እውነትንና ፍቅርን እንዲይዝ ማስተማር የአባቶች ቀዳሚ ተግባር ነው።

የሠለጠነ የሃሳብ መድረክ ፈጣሪዎች ተብለው የሚሞካሹት ፖለቲከኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠሩ በርካታ ምስቅልቅሎች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ለተፈጠሩ ቁርሾዎች መነሻ አስኳል መሆናቸው የሚካድ አይደለም። በዚህ ረገድ የሀገሪቷ የፖለቲካ ልሂቃን ካለፉት ስህተቶች ተምረው ለአዲሱ ትውልድ የተሻለ እና የሠለጠነ የፖለቲካ ባሕል የማስረከብ ታሪካዊ አደራ አለባቸው። ፖለቲካ ማለት ልዩነቶችን በኃይል ወይም በሴራ መፍታት ሳይሆን በሃሳብ የበላይነት ማሸነፍ መሆኑን በተግባር ማሳየት በአዲሱ ዓመት ከእነሱ የሚጠበቅ ግዴታ ነው።

ሌላው ከፖለቲከኞች የሚጠበቀው ትልቁ ተግባር ከጠበበ የቡድን ወይም የፓርቲ ጥቅም ወጥቶ



53

ለሀገር ሕልውና እና ለዜጎች ደህንነት ቅድሚያ መስጠት ነው። ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ፣ ብሔርንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እና ትርክቶችን ሙሉ በሙሉ ማቆም አለባቸው። ሀገራዊ ምክክሩ የከፈተውን የውይይት በር በመጠቀም ልዩነቶቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ፣ በምክንያታዊነት እና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

የአንድነት እና የበጎነት አምባሳደሮች ተብለው የሚጠሩትና በሀገሪት በተለያዩ መስኮች ተሰልፈው የሚገኙ ምሁራን፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ስፖርተኞች እና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ተከታይ ያላቸው በመሆኑ የሚናገሩት እያንዳንዱ ቃል እና የሚያንፀባርቁት አቋም በማኅበረሰቡ፣ በተለይም በወጣቱ ትውልድ ላይ ፈጣን ተጽዕኖ የማሳደር አቅሙ ከፍተኛ መሆኑ እሙን ነው። በዚህ ረገድ ሰፊ የሆነውን ተደራሽነታቸውን በመጠቀም በኪነ ጥበብ ሥራዎቻቸው የኢትዮጵያዊያንን የዘመናት አብሮነት፣ ውበት እና የባህል እሴቶች ማጉላት አለባቸው። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ኃላፊነት የተሞላበት አጠቃቀምን በማሳየት፣ ሰላምን የሚያበረታቱ መልዕክቶችን ማጋራትና ከሐሰተኛ መረጃዎች መራቅ ይጠበቅባቸዋል። ወጣቱን ኃይል ወደ ልማት፣ ትምህርት እና በጎ ፈቃደኝነት በመምራት ረገድ የእውነተኛ ዓርአያነት (Role Model) ሚናቸውን መወጣት በአዲሱ ዓመት የሚጠበቅባቸው ቀዳሚ ተግባር ነው።

እናም አዲሱ ዓመት የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን፤ የምክክሩን ውጤቶች ወደ ተግባር በመቀየር አዲስ የተስፋ ማዕድ የምንዘረጋበት ታሪካዊ ወቅት ነው። ባለፈው ዘመን በነበሩ ግጭቶች እና ፖለቲካዊ መናቆሮች የዛለው የሕዝባችን ልብ ዘንድሮ በሰላም እና በንግግር ብስራት ሊጠገን ጅምር አሳይቷል። ይህንን አዲስ ተስፋ ይዞ ወደ ፊት መራመድ የሁላችንም የዜግነት ድርሻ ነው። አዲሱ ዓመት የይቅርታ፣ የመደማመጥ፣ የአንድነት እና የብልጽግና ዘመን እንደሚሆን እሙን ነው።

የልማት ተስፋዎቻችን

አዲሱ ዘመን በሀገራዊ የልማት ስኬቶች ማማ ላይ ቆመን ትልማችንን እውን የምናደርግበት ልዩ የድል ምዕራፍ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ሀገራችን በጽኑ ክንዶቿ ያስመዘገበቻቸው ታሪካዊ ስኬቶች ለእኛነታችን የግል ጥንካሬና ለነገው ተስፋችን ዋስትና እና ምሰሶዎች ናቸው። የሀገራችን ዕድገት በሕዝቦቿ ብርቱ ትጋት፣ የጋራ ትብብር፣ ርዕይ ባለው አመራር፣ በጽናትና በተጠና መዳረሻ በተቀመጠ ዕቅድ እውን ሆኗል፡ ፡ ይህንን ሁለንተናዊ ስኬት ለእኛ የነገ ተስፋ እውን መሆን እንደተነጠፈ ግዙፍና ለምለም መስክ እንቆጥረዋለን።

በከተሞችና በገጠር መንደሮች የሚስተዋለው የኮሪደር ልማት ሥራና ውበት የብዙዎቻችንን የአልችልም ስሜት የሰበረ፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ያወጀ፣ የነገ ተስፋችንን ያለመለመ ስኬት ነው፡፡ ይህ የማይናወጥ የመዳረሻ ግባችን የነገ ጉዟችንን የሚያቃናና ሁላችንንም የሚያጠግብ የማይነጥፍ ማዕዳች ነው።

ባለፉት ሥምንት ዓመታት በብርቱ ክንዶች የጋራ ርብርብ በአረንጓዴ አሻራ የተሸፈኑት የተራቆቱ መሬቶች፣ እርቃናቸውን ቀርተው የነበሩና ወዛቸው የተመለሰላቸው ተራሮች፣ ወርቃማ እሸት የለበሱት የስንዴ ማሳዎች ሀገራችን ራሷን ችላ ለመቆሟ፣ የእኛም ሕልሞች እንደሚለመልሙ የሚያረጋግጡ ሃውልቶች ናቸው።

ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚፈነጥቀው ብርሃን የውስጣችንን ተስፋ የሚያበራና የወዛችንን ዋጋ የሚከፍለን ሲሆን፤ እንደ ገበታ ለሀገር ባሉ ፕሮጀክቶች የፈኩት አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች ደግሞ የነገዋን ውብ ኢትዮጵያ በኩራት እንድንመለከት ያደርጉናል። ኢትዮጵያ በወጣት ልጆቿ ምጡቅ እሳቤ በመታገዝ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገትና በዘመናዊ ፈጠራዎች የጀመረችው ፈጣን ጉዞ “እኔም በግሌ ታሪክ መሥራት እችላለሁ” የሚል የውስጥ ቁጭት እንዲያድርብን ከማድረግ ባለፈ ግባችንን ለማሳካት የሚያግዝ ወኔን አላብሰውናል።

በአዲሱ ዓመት፤ እንደ ሀገር ከተጀመረው የልማት ማዕበል ጋር እኩል በመገስገስ ህልማችንን ለማሳካት እንተጋለን፣ በየማለዳው የምናያቸውና የምንሰማቸው አዳዲስና አስደማሚ ስኬቶች የብርታት መፈክሮቻችን ናቸው። እኛም እንደ ዜጋ ከውድቀት ወደ ብልፅግና ለመሸጋገር አዕምሯችንን በጥበብና በዕውቀት ለመገንባት ቃል እንገባለን፤ ምክንያቱም የበለጸገች ሀገር የምትቆመው በበለጸገ ዜጋ ትከሻ ላይ ነውና።

በግብርና፣ በቴክኖሎጂና በቱሪዝም ዘርፍ የተመዘገቡት ታላላቅ ስኬቶች፤ የያዝናቸውን ግቦች ለማሳካትና ዕቅዳችንን ከዳር ለማድረስ እንዲሁም በግል ሕይወታች ጠንካራ የሥራ ባህል እንድንላበስና በትጋት እንድንቆም የብርታት ምንጭ ይሆኑናል። የሀገራችን ስኬት የሚገጥሙንን መሰናክሎች በድል እንድንሻገር መሠረት ሆነውናል፤ ምክንያቱም በውስጣችን የሰነቅነው የተስፋ ብርሃን ከሀገራችን ጋር የተቆራኘ ነውና።

አዲሱ ዓመት የሀገራችን ከፍታ በድጋሚ ለዓለም የሚገለጽበት፤ ስኬቷ ደምቆ የሚቀጥልበት፤ የዜጎቿ ፍላጎቶች እውን የሚሆኑበትና የጋራ የድል አክሊል የምንደፋበት የብርሃን ዘመን እንደሚሆን አያጠራጥርም።

መልካም አዲስ ዓመት!



54

ኢኮኖሚ

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ስኬት ያጀበው ጉዞ



55

በፍቅርተ ባልቻ

የአየር ንብረት ለውጥ፣ የመሬት መራቆት፣ የደን ሽፋን መመናመንና የብዝሃ ሕይወት መቀነስ ዓለምን እየፈተኑ ከሚገኙ ዋነኛ የዘመናችን ችግሮች መካከል ናቸው። እነዚህ ችግሮች የአካባቢ ጥበቃን ብቻ የሚመለከቱ ጉዳዮች አይደሉም፤ ከምግብ ዋስትና፣ ከውኃ ሀብት፣ ከግብርና ምርታማነት፣ ከሥራ ዕድልና ከኢኮኖሚ ዕድገት ጋር በቀጥታ የተሳሰሩ ናቸው።

ለዓለም ሕዝቦች ያለውን አሳሳቢነት የተረዱ አገራት የአየር ንብረት ለውጥን በሣይንሳዊ ጥናቶች በማስደገፍ ተደጋጋሚ ውይይቶችን አካሂደዋል። በተለይ እ.አ.አ በ1972 ዓ.ም በስቶክሆልም ስዊድን የተካሄደውንና የ114 አገራት ተወካዮች የተሳተፉበትን ዓለም አቀፍ ጉባዔ (United Nations Conference on the Human Environment) ተከትሎ በየዓመቱ በመሪዎች ደረጃ የተለያዩ ምክክሮች ተካሂደዋል።

ቀደም ሲል በተጠቀሰው እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ መድረኮች የአየር ንብረት ለውጥ በተለይም ደግሞ የአካባቢ መራቆት እና ብክለት ለፍጥረታት እልቂት ምክንያት ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል። የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለው አደጋ ፍጥረታትን ከመጨረሱ በፊት እርምጃ መወሰድ አለበት የሚል ሣይንሳዊ ጥናት በተደጋጋሚ ጊዜ ለመሪዎች ጉባዔ ቀርቧል።

ለዚህም ይመስላል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአንድ ወቅት ከ2021 እስከ 2030 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የተራቆቱ መሬቶችን መልሰው



56

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

እንዲድኑ የሚደረግበት፣ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር የሚታረቅበት ጊዜ መሆን እንዳለበትና በየትኛውም ቦታ፣ በሁሉም ማኅበረሰብ የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶት መሠራት እንዳለበት ያሳሰቡት።

የመስኩ ምሁራን እንደሚገልጹት፤ ደኖች ከካርቦን ልቀት ጋር በመዋጋት የዓለምን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቀነስ ጉልህ ድርሻ ያበረክታሉ። የካርቦን ክምችትን በከፍተኛ ሁኔታ በእንጨታቸው አምቀው ይይዛሉ፤ ካርቦንዳይኦክሳይድን በመውሰድ ወደ ኦክሲጅን ይቀይራሉ። ደኖች ለሰው ልጆች እስትንፋስ ህልውና የሆነውን ንጹህ አየር ይፈጥራሉ። ደኖችን መጠበቅ ለሰው ልጆች እና ሕይወት ላላቸው ሁሉ ወሳኝ ነው የሚባለውም በዚህ ምክንያት ነው። በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ትኩረት የተሰጠው አጀንዳ የሆነውም ከፍጥረታት ህልውና ጋር በቀጥታ የተያያዘ በመሆኑ ነው።

ለምን ተጀመረ?

ኢትዮጵያ በመሬት መደህየትና መቆርቆዝ የተጠቃች አገር ናት። ይህም የእጽዋት ሽፋን መራቆትን እንዲሁም ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የአፈር መከላት፣ የደረቃማና ለምርት ምቹ ያልሆኑ ቦታዎች መስፋፋትን ያካተተ ነው። ቀደም ሲል የተጠቀሱትን ችግሮች ለመቀልበስ የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች የተቀናጁ ባለመሆናቸው አመርቂ ውጤት አልተገኘም።

በአገራችን ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ከፍተኛ የደን ጭፍጨፋ እንደነበር ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ የሚጠቅሰው የኢትዮጵያ የደን ልማት፤ በተለይ በ1950ዎቹ መጨረሻ እና በ1960ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ኢትዮጵያ ውስጥ በዓመት ስምንት መቶ ሺህ ሄክታር ደን ይጨፈጨፍ እንደነበረ ያሳያል። የአገራችን ደን በአብዛኛው ተፈጥሯዊ ሲሆን የሚሸፍነውም ተራሮችን ነው። ይህም ለድርቅ እና ለጎርፍ አደጋዎች ተጋላጭ አድርጎናል።

ኢትዮጵያ ከ40 በመቶ በላይ የደን ሽፋን የነበራት ብትሆንም፤ የነበረውን ለመጠበቅና አዲስ ለመትከል ይደረጉ የነበሩ እንቅስቃሴዎች ውጤታማ ባለመሆናቸው የደን ሽፋኗ ተመናምኖ ከሦስት በመቶ በታች የደረሰበት ጊዜ ነበር። ይህም የመሬትን ምርታማነት በመቀነስ በርካታ ጉዳቶችን አስከትሏል።

እ.አ.አ ከ2000 እስከ 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ዘጠና ሁለት ሺህ ሄክታር ደን በዓመት ይጨፈጨፍ እንደነበር በጥናት ተረጋግጧል። ይህ አሃዝ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የአካባቢ መራቆት እንዲሁም ከፍተኛ የአፈር መከላት ስለመኖሩ አስረጂ ነው። ከኢትዮጵያ ከሁለት ቢሊዮን ቶን በላይ አፈር እየታጠበ እንደሚሄድም ጥናቶች ያመላክታሉ። ከ54 ሚሊዮን ሄክታር በላይ የሚሆነው መሬትም የመጎሳቆል አደጋ ደርሶበታል።



57

በዚህ ሳቢያም ‘የሰዎች እልቂት፣ የእንስሳትን ሞት አስተናግደናል’ ሲሉ የችግሩን ስፋትና ጥልቀት የጠቆሙት የኢትዮጵያ የደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም ናቸው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለረሃብ ተምሣሌት መደረጋችን ለአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር መጀመር ትልቅ ገፊ ምክንያት ስለመሆኑም ኃላፊው አንስተዋል። በጥቅሉ እነዚህ ዓለም አቀፋዊ እና አገራዊ ችግሮች የአረንጓዴ አሻራን መርኃ ግብር ለመጀመር በምክንያትነት የሚጠቀሱ ናቸው።

የአየር ንብረት ለውጥ ካመጣው ዓለም አቀፍ ፈተና የማታመልጠው ኢትዮጵያ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብርን በማስፋፋት የተራቆቱ መሬቶችን መልሳ ለማልማት፣ የደን ሽፋኗን ለማሳደግ፣ የውኃና የአፈር ሀብቷን ለመጠበቅ እና የሕዝብ ተሳትፎን ወደ ሀገራዊ ንቅናቄ ለመቀየር ሰፊ ጥረት አድርጋለች።

በዚህም የአገሪቷን የደን ሽፋን መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል እና አካባቢን መንከባከብን ዋና ዓላማ ያደረገውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው አገራዊው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር (Green Legacy Initiative) በይፋ የተጀመረው በሐምሌ 2011 ዓ.ም ሲሆን የመጀመሪያው አገር አቀፍ የችግኝ ተከላ ዘመቻም በዚያው ዓመት ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም ተካሂዷል።

ዕለቱ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና የተራቆቱ መሬቶቿን ለማልማት በ2011 ዓ.ም የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ዜጎች በነቂስ በመውጣት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል



58

የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር አፈጻጸም

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

አሻራቸውን ያኖሩበት ትልቅ ታሪካዊ ክስተት ሆኗል።

“40 ዛፍ በነፍስ ወከፍ” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው በዚሁ በመጀመሪያው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርኃ ግብር በአንድ ጀንበር 200 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ከ353 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያ እ.አ.አ ሐምሌ 2017 በሕንድ የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻ በ12 ሠዓታት 66 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረወሰን መረከብ ችላለች።

የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሩ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ተቋማት ባልተደራጀ እና በተበታተነ መልኩ ሲከናወኑ የነበሩትን የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ሰብሰብ አድርጎ በተናበበ መንገድ እንዲተገበር ማድረግ አስችሏል። ይህም ኢትዮጵያ የደን ሽፋኗን ለመጨመር እና ከካርቦን ልቀት ጋር ለመታገል የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር እየተመናመነ ለመጣው የደን ሽፋን ፍቱን መድኃኒት ሆኗል። በመርኃ ግብሩ የደን፣ የመኖ፣ የፍራፍሬ፣ የከተማ ውበት፣ እና የመሳሰሉት ችግኞች እየተተከሉ ነው።

መርኃ ግብሩ የአገር ሉዓላዊነትን ከማሳደግ፣ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነትን ከማጠናከር አንጻር ያለው ጥቅም በጉልህ የሚጠቀስ ነው። ምርትና ምርታማነትን የመጨመር፣ የውሃ አካላት በደለል እንዳይሞሉ የማድረግ ፋይዳ አለው።

መርኃ ግብሩ በከተማና በገጠር ሳይወሰን፣ የአንድ ተቋም ሥራ ነው ተብሎ ሳይተው በጋራ እየተተገበረ ያለ ነው። ይህ የጋራ እሳቤ ንቅናቄው በስኬታማነት እንዲቀጥል ትልቅ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አለው። አብዛኛው ኅብረተሰብ ስለ አረንጓዴ አሻራ ያለው ግንዛቤ እና ምላሽ ቀና መሆን ሌላው የስኬታማ ጉዞው ስንቅ ነው። መንግሥታዊ መዋቅሩ፣ የፖለቲካ አመራሩ፣ በተለይም የከተማውና የገጠሩ ማኅበረሰብ በባለቤትነት መንፈስ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ አንዱ የመልካም አፈጻጸሙ ማሳያ እንደሆነ መግለጽ ይቻላል።

የመርኃ ግብሩ ስኬታማነት ዋናው ምክንያት ሥራው የመሪ አጀንዳ መሆኑ ነው። ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅር የዕለት ተዕለት አጀንዳ አድርጎ መያዙ ለሥራው ውጤታማነት ትልቅ አበርክቶ አለው። አመራሩ እና የመንግሥት መዋቅር፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጭምር የሰጡት ትኩረት እና በባለቤትነት መንፈስ መሳተፋቸው መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ አቅም ፈጥሯል።

በየዓመቱ በሚካሄዱት መርኃ ግብሮች ዓመቱን ሙሉ ዝግጅት የሚደረግባቸው ሲሆን ምን ያህል ችግኝ እንደሚተከል እየታቀደ ነው ሥራው ሲመራ የቆየው። በየዓመቱ መሪ ቃል ይዘጋጃል፣ የአንድ ጀንበር ተከላም ባለፉት ዓመታት በተከታታይ ተካሂዷል።

በዘንድሮው መርኃ ግብር በአንድ ጀንበር 26 ሚሊዮን ሕዝብ ሲተክል መዋሉን እና 800 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል የተያዘው ዕቅድ መሳካቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አብስረዋል። በዘንድሮው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ንቅናቄ 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተያዘው ግብ በኢትዮጵያዊያን የተቀናጀ ትብብርና ንቁ ተሳትፎ ከዕቅድ በላይ ማሳካት ተችሏል።



59

መርኃ-ግብሩ በአንድ ሄክታር መሬት ላይ ይደርስ የነበረውን የአፈር መሸርሸር መጠን ከ130 ቶን ወደ 54 ቶን ዝቅ ማድረግ አስችሏል። የደረቁ የውሃ አካላት ማገገምና የውሃ መጠናቸው መጨመር ከሚጠቀሱ ውጤቶች መካከል ናቸው።

የመርኃ ግብሩ ስኬቶች

የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ሲጀመር 17 ነጥብ 2 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተሠራው ሥራ ሽፋኑን ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደግ ተችሏል። ይህ ለውጥ ከደን ሽፋን መጨመር ባሻገር የአፈር ጥበቃን፣ የውሃ ሀብትና የሥነ- ምህዳር ጤናን ከማሻሻል ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው።

መርኃ-ግብሩ በአንድ ሄክታር መሬት ላይ ይደርስ የነበረውን የአፈር መሸርሸር መጠን ከ130 ቶን ወደ 54 ቶን ዝቅ ማድረግ አስችሏል። የደረቁ የውሃ አካላት ማገገምና የውሃ መጠናቸው መጨመር ከሚጠቀሱ ውጤቶች መካከል ናቸው።

እ.አ.አ ከ2000 እስከ 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ በኢትዮጵያ በአማካኝ 92 ሺህ ሄክታር ደን ይጨፈጨፍ እንደነበረና ከ2014-2019 ዓ.ም የደን ጭፍጨፋው ወደ 38 ሺህ ሔክታር ዝቅ ማለቱን መረጃዎች ያሳያሉ። አሁን ደግሞ በዓመት የደን ጭፍጨፋ የሚፈጸምበት ከባቢ ወደ 27 ሺህ 703 ሄክታር ዝቅ ብሏል፡፡

የአካባቢ መራቆትና የአየር ንብረት ለውጥ ድንበር የማይገድባቸው ችግሮች ናቸው። በመሆኑም የአረንጓዴ አሻራ ጥቅም በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ብቻ የሚቀር አይደለም። ኢትዮጵያ ችግኞችን፣ ቴክኒካዊ ልምድንና የመሬት ማገገሚያ ተሞክሮዎችን ለጎረቤት አገራት ማካፈሏን ቀጥላለች። ይህ በአፍሪካ የተራቆቱ መሬቶች እንዲያገግሙ ከሚደረጉ ሰፊ አህጉራዊ ጥረቶች ጋር የሚገናኝ ሲሆን፣



60

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

አካባቢ ጥበቃን ከቀጣናዊ ትብብርና ከአየር ንብረት ዲፕሎማሲ ጋር ለማስተሳሰር ዕድል ይፈጥራል።

የኢትዮጵያ የደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም፤ በመርኃ ግብሩ የተገኙ ስኬቶችን ዓለም አቀፍ እና አገራዊ ፋይዳቸውን በሁለት ከፍለው ነው የገለጿቸው። አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ወንዞች ድንበር ተሻጋሪ ናቸው። እነዚህ ወንዞች ከአገሪቷ አፈር ይዘው ነው ወደ ጎረቤት አገር የሚሄዱት። የወንዞቹ ሕይወት የተመሠረተው በኢትዮጵያ ደን ነው። የኢትዮጵያ ተራሮች ደን በለበሱ ቁጥር ወንዞቹ ውሃ ይኖራቸዋል። በሁሉም አቅጣጫ ባሉት ወንዞች እና ተፋሰሶች አማካኝነት ውሃዎቹ ድንበር ተሻግረው ይጓዛሉ።

ኢትዮጵያ ባታለማ ጥፋቱ በአገር ውስጥ ብቻ የተወሰነ አይሆንም። የኢትዮጵያን ደን መጠበቅ የአፍሪካን ደን መጠበቅ ነው የሚባለውም በዚህ ምክንያት ነው። እንደ አቶ ከበደ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ ደን ካርቦንዳይኦክሳይድ አምቆ ይዟል፤ ይህ ደን ቢጨፈጨፍ አምቆ የያዘው ካርቦን ዓለምን ይበክላል። ስለሆነም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ለዓለም ማኅበረሰብ አስተዋጽኦ እያደረግን በመሆኑ ስኬቱ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጭምር ነው።

እንደ አገር እየተተገበረ ባለው መርኃ ግብር ኅብረተሰቡ በጓሮው ዛፍ እንዲተክል፤ መትከልንም ባህሉ እንዲያደርገው በተሰራው ሥራ ለውጥ ተገኝቷል። ኅብረተሰቡ የተፈጥሮውን ደን ሳይነካ ከራሱ ጓሮ ማግኘት ጀምሯል። በሰው ሰራሽ መንገድ ደን ማልማት አንዱ የችግሩ መፍትሔ ሆኗል።

አሁን ያለውን ደን መራቆት ሳናስከትልበት፣ የደን ሽፋኑ ዕድገት ሳይገታ፣ ዘላቂ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ብናውለው በዓመት ምን ያህል ደን ማምረት እንችላለን የሚለው ላይ ጥናት ተካሂዷል የሚለው የኢትዮጵያ የደን ልማት መሥሪያ ቤት፤ በኢትዮጵያ አሁን ካለው ደን 100 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ እንጨት ማምረት የሚያስችል አቅም መፈጠሩን ገልጿል።

ሌላው ስኬት ማኅበረሰቡ ላይ የመጣው የአመለካከት ለውጥ ነው። ከደን ልማት ሥራው ጋር፣ እፅዋትን በቤት ውስጥና ከግቢ ውጪም በመትከል ረገድ ለውጥ መጥቷል። ከዚህ ቀደም የአንድ ተቋም ሥራ ነው ተብሎ ይወሰድ ነበር። አሁን በሁሉም ዘንድ ‘ይመለከተኛል’ የሚለውን ግንዛቤ ማዳበር ተችሏል። ይህ በሚቀጥሉት ዓመታት ለሚካሄደው ሥራ ትልቅ ጉልበት እና አቅም የሚሆን ነው።

ከችግኝ መትከል ባሻገር

ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ተግባራዊ የተደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የችግኝ ተከላን ወደ አገራዊ ንቅናቄ ለመቀየር የተደረገ ሙከራ ብቻ አይደለም። ይልቁንም አካባቢን፣ ግብርናን፣ ውሃን፣ ምግብን፣ ሥራንና ኢኮኖሚን የሚያገናኝ ሰፊ የልማት አቅጣጫ ሆኖ የቀጠለ፤ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎችም የሥራ ዕድል የፈጠረ የስኬት ተምሣሌት ነው።

የተራቆቱ መሬቶችን መመለስ፣ የተፋሰስ ልማትን ማጠናከር፣ የውኃ ምንጮችን መጠበቅ፣ የአፈር መሸርሸርን መቀነስ፣ ብዝሃ- ሕይወትን መጠበቅና ግብርናን ከደን ልማት ጋር ማቀናጀት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርኃ-ግብሩ አካላት ናቸው።

ችግኞች ሲጸድቁ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ፣ የውኃ ምንጮችን በማጠናከር፣ የሥነ-ምህዳር ጤናን በማሻሻልና ለግብርና ምርታማነት ተስማሚ ሁኔታ በመፍጠር ዘላቂ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣሉ። የተፋሰስ ልማትም የደረቁ ምንጮች እንዲያገግሙ ከማድረጉ ባሻገር የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እና የጎርፍና የአፈር መሸርሸር ችግሮችን ለመቀነስ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ ነው።

በዘህ ረገድ የአባይ ተፋሰስ ልዩ ትኩረት ያገኘ ሲሆን፤ በተፋሰሱ ዙሪያ የሚካሄደው የደንና የመሬት ልማት የአፈር ደለልን በመቀነስ የውኃ ሀብትን ለመጠበቅና የውኃ አካላትን ዘላቂነት ለማጠናከር ያግዛል።

ከመርኃ-ግብሩ ዋነኛ ትኩረቶች አንዱ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ተግባር ሲሆን የሚተከሉት ችግኞች ለምግብነት፣ ለመድኃኒት እና ለገቢ ምንጭነት የሚውሉና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬና ሌሎች ዝርያዎችንም አካተዋል። ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ 60 በመቶ የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ ፍራፍሬዎች በመሆናቸው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ እያገዘ ይገኛል።

በተለይም ቡና፣ አቮካዶና ሌሎች የፍራፍሬ ሰብሎች በጥምር ደን እርሻ አማካይነት ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተያይዘው እየተስፋፉ ነው። ይህም የአርሶ አደሩን የምግብ ምንጭ ከማሻሻል ባሻገር የገቢ ምንጮችን ለማስፋት ያግዛል።

ከአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ጋር በተያያዘ የቡና ምርትና የኤክስፖርት አቅምም እየጨመረ መጥቷል። የቡና ኤክስፖርት ገቢ ከ700 ሚሊዮን ዶላር ወደ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ማደጉን እና የቡና ኤክስፖርት መጠንም ከ230 ሺህ ቶን ወደ 475 ሺህ ቶን ማደጉን መረጃዎች ያሳያሉ።

በሂደቱ የሥራ ዕድል የሚያስገኙ መልካም አጋጣሚዎችም ተፈጥረዋል። ዘር ከመሰብሰብ ጀምሮ በችግኝ ማፍላት ሂደት ውስጥ የሚመጡ ሥራዎች አሉ። በችግኝ ጣቢያ ውስጥ በጣም ሰፊ ቁጥር ያለው የሥራ ዕድል ነው የሚፈጠረው። ለምሣሌ አንድን የአገር በቀል ዛፍ ችግኝ ለማፍላት አሥራ ሁለት ወራት ይፈጃል። በእነዚህ ወራት ውስጥ ሥራ ፈላጊው የመሥራት ዕድሉን ያገኛል።

ከለሙ ተፋሰሶች ጋር ተያይዞ በበጋ የሚሠራው ከክረምቱ ጋር ተቀናጅቶ ስለሚሄድ በለሙ ተፋሰሶች ላይ ወጣቶች ንብ በማነብ፣ ከብት በማድለብ ሥራዎች ውስጥ ተሰማርተው እንዲጠቀሙ ማድረግ መቻሉ የመርኃ ግብሩ አንደኛው ስኬት ነው።

የአረንጓዴ አሻራ ትልቁ ትሩፋት ተፈጥሮን የመጠበቅ ኃላፊነትን ከመንግሥት ፖሊሲ አውጥቶ የዜጎች የዕለት ተዕለት ባሕልና አስተሳሰብ ማድረግ ማስቻሉ ነው። ምድርን ማልበስ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። ዛሬ የምናኖረው አረንጓዴ አሻራ የዛፎች ስብስብ ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ የምናስረክበው የተሻለች ምድር፣ የተጠበቀ ተፈጥሮ እና ዘላቂ የልማት መሠረት ነው።

ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ምድርን ከመራቆት ወደ ልምላሜ፣ ከአካባቢ ጥበቃ ወደ ኢኮኖሚያዊ ዕድል፣ ከግለሰብ ጥረት ወደ የጋራ ኃላፊነት እና ከችግኝ ተከላ ወደ አረንጓዴ አስተሳሰብ የሚያሸጋግር የትውልድ ጉዞ ነው።

ዓለም አቀፍ አንድምታ

አረንጓዴ አሻራ ደን እና ችግኝ የመትከል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከዚያም ያለፈ ፋይዳ ያለው፤ ጠንካራ ኢኮኖሚ፣ ጠንካራ መንግሥት፣ ጠንካራ አገር የመገንባት ጉዳይ ነው። መርኃ ግብሩ በጥቅሉ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከፍ ብላ እንድትታይ የሚያስችሉ ተግባራት የተከናወኑበት፤ የሚከናወኑበት ነው።

የተራቆቱ መሬቶችን ወደ ምርታማነት የመመለስ፣ የውሃ ሀብት ፍሰቱን በማሻሻል የኃይል አቅርቦቱን ማሳደግ፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ማሳደግ ነው። እነዚህ ሁሉ የተሳሰሩ እና ተያይዘው ኢኮኖሚያችንን



61

ለማሳደግ የሚያግዙ ሰፊ ሚና ያላቸው ሥራዎች ናቸው።

ለምሣሌ ዘላቂ የልማት ግቦች እና አጀንዳ 2063 ከአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ሥራዎች ጋር የተሳሰሩ ናቸው። የዘላቂ ልማት ግቦች (Sustain- able Development Goals) በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ናቸው። ይህን አስመልክቶ አቶ ከበደ ሲያብራሩ አስራ ሰባቱም ግቦች የመሬትን ለምነት ከመጠበቅ፣ በረሃማነትን ከመከላከል እና ምርታማነትን ከማሳደግ ጋር በጥብቅ

የተሳሰሩ በመሆናቸው በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከሚሠራው ሥራ ጋር በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ይቆራኛሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል አገራት ተስማምተውበት እ.አ.አ በ2015 ዓ.ም የተቀረጸውና 17 ግቦችን ያካተተው ይህ ዕቅድ በዋናነት እ.አ.አ በ2030 ዓ.ም ከምድር ላይ ድህነትን ለማጥፋት፣ ሰላምን እና ብልጽግናን እውን ለማድረግ ያለመ ነው። ግቦቹ ከውሃ፣ ከመሬት ለምነት፣ ከምርታማነት፣ ከአየር ንብረት ለውጥ፣ ከታዳሽ የኃይል ምንጮች እና ከመሳሰሉት ጋር በተያያዘ የዓለም አገራት መተግበር ያለባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች ያካተቱ ናቸው፤ ኢትዮጵያ እነዚህን ግቦች ለማሳካት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በእጅጉ እያገዛት ስለመሆኑ ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እ.አ.አ 1992 ዓ.ም ሪዮ ዲጄኔሪዮ ላይ የተካሄደውን ጉባዔ ተከትሎ ሦስት ስምምነቶች ጸድቀዋል። አንዱ በረሃማነትን መከላከል፤ ሁለተኛው የብዝሃ ሕይወት ሀብታችንን መጠበቅ ሲሆን ሦስተኛው የአየር ንብረት ለውጥን የመከላከል ጉዳይ ነው። እነዚህ ስምምነቶች የሚሳኩት በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር አማካኝነት ነው።

የአፍሪካ 2063 አጀንዳ “ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ማኅበረሰብ እና ኢኮኖሚ መፍጠር አለብን” ብሎ ነው የተነሳው። ይህ ዕቅድ ያለ አረንጓዴ አሻራ የሚሳካ አይደለም። እ.አ.አ በ2030 ዓ.ም 100 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግም ለማድረግ ተወስኖ እየተሠራ ነው፤ የዚህ 22 በመቶው ድርሻ የኢትዮጵያ ነው። ስለዚህ አህጉራዊ ድርሻችን ከፍተኛ ነው።

የኢትዮጵያ ወንዞች አብዛኞቹ ድንበር ተሻጋሪዎች ናቸው። ድንበር ተሻግረው እያለሙ ናቸው። እነዚህ ተራሮች በደን ባይሸፈኑ ውሃ ሊታሰብ አይችልም፣ አይደለም ጎረቤት አገር ተሻግሮ መሄድ ለእኛም የሚሆን በቂ ውሃ ልናገኝ አንችልም። ለዚያም ነው አረንጓዴ አሻራ ድንበር

የተራቆቱ መሬቶችን ወደ ምርታማነት የመመለስ፣ የውሃ ሀብት ፍሰቱን በማሻሻል የኃይል አቅርቦቱን ማሳደግ፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ማሳደግ ነው። እነዚህ ሁሉ የተሳሰሩ እና ተያይዘው ኢኮኖሚያችንን ለማሳደግ የሚያግዙ ሰፊ ሚና ያላቸው ሥራዎች ናቸው።



62

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ተሻጋሪ የሆነ ጥቅም ያለው ነው የምንለው። ስለሆነም ኢትዮጵያ በአህጉራዊም ሆነ በዓለም አቀፍ ስምምነቶች የገባችውን ቃል እየተወጣች ትገኛለች።

የመርኃ ግብሩ ሌላው ዓለም አቀፍ ገጽታ የሙቀት አማቂ ጋዝ ወደ አየር እንዳይለቀቅ እያደረግን ያለው አበርክቶ ነው። በየዓመቱ ይጨፈጨፍ የነበረው (እ.አ.አ በ2013) 92 ሺህ ሄክታር ደን ወደ 27 ሺህ ዝቅ ሲል 65 ሺህ ሄክታር ደን እንዳይጨፈጨፍ አድርገናል።

በእነዚህ ሥራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና አግኝተናል፤ በሁለተኛው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባዔ እንዲሁም በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዋን ያስተዋወቀች ሲሆን የአፍሪካ አገራትም ለአህጉሪቱ ትልቅ ተምሣሌት ብለውታል።

ይህም ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ባትሆንም የሚደርስባትን ጫና ለመቀነስ አስተዋጽኦ አለው። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታዘጋጅ መመረጧ በአየር ንብረት ለውጥን መከላከል እያከናወነች ላለው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘችበት ነው፤ ይህም የዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ውጤት ነው። ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት አገራት ችግኞችን በመለገስ የአካባቢ ጥበቃ የጋራ አጀንዳ መሆኑን በተግባር አሳይታለች። በተጨማሪም በአፍሪካ ኅብረት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች የአህጉሪቱን ፍላጎትና ጥቅም ለማስከበር ግንባር ቀደም ተሟጋች ሆናለች።

ለአየር ንብረት ለውጥ አነስተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ነገር ግን ለጉዳቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ የአፍሪካ አገራት ፍትሃዊ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲያገኙ ድምጽ በመሆን አህጉራዊ መሪነቷን አስመስክራለች። በዚህም አፍሪካዊያን በራሳቸው አገር በቀል መፍትሔዎች የአየር ንብረት ጥበቃን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሆኗል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና አምባሳደሮች የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ ለአካባቢ ጥበቃ ዓርአያ የሚሆን ዓለም አቀፍ ሞዴል ሲሉ አድንቀውታል።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን ከመጠቀም፣ የካርቦን ልቀትን ከመቀነስ እና ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መስፋፋት ጋር



63

አጣጥማ የምታካሂደው እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባዔዎች ላይ እውቅና አስገኝቶላታል።

ጉዞውን ማስቀጠል

የአረንጓዴ አሻራ ስኬት የሚለካው በአንድ ቀን በተተከሉ ችግኞች ቁጥር ብቻ አይሆንም። ችግኞቹ ምን ያህል ጸድቀዋል? እንዴት እንንከባከባቸው? ከግጦሽ፣ ከሕገ-ወጥ የደን ጭፍጨፋና ከውኃ እጥረት እንዴት ይጠበቃሉ? የተመለሱ የውኃ ምንጮችና የተሻሻሉ የአፈር ሀብቶችስ እንዴት ይጠበቃሉ? የሚሉት ጥያቄዎች የመርሃ-ግብሩ ቀጣይ ምዕራፍና ፈተናዎች ናቸው።

በመሆኑም የሕዝብ ባለቤትነትን ማጠናከር፣ ጥምር የደን ልማትን ከሳይንሳዊ የግብርና ምርምር ጋር ማስተሳሰር፣ በደን ላይ የሚደርሰውን ጫና የሚቀንሱ አማራጭ የኃይል ምንጮችን ማስፋፋትና የተተከሉ ችግኞችን በተከታታይ መንከባከብ ቀጣይ ትኩረት ሊሆኑ ይገባል።

የችግኝ ማፍላት እና የጉድጓድ ቁፋሮ ከጽድቀት ጋር የተያያዙ የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ተግባራ ናቸው፤ ችግኞችን አፈር፣ አሸዋ እና ንጥረ ነገሮችን በማመጣጠን የማፍላት ዘዴን መጠቀም የጽድቀት ምጣኔ እንዲጨምር ያደርጋል። ሌላው ከጽድቀት ጋር የሚያያዘው ከሥነ ምህዳር ወይም ከአካባቢ የአየር ንብረት ጋር የሚስማሙ ዝርያዎችን በመለየት እንዲተከሉ የሚደረገው ድጋፍ እና ክትትል ነው። በከተሞች ከመሠረተ ልማት ጋር የተጣጣመ ተከላ እንዲኖር ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ስለመሆኑ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

የድህረ ተከላ እንክብካቤ በውስጡ ጥበቃ፣ አረም፣ ኩትኳቶ፣ ውሃ ማጠጣት፣ የመሳሰሉት ችግኞች ከተተከሉ በኋላ የሚከናወኑ ሥራዎችን ያካትታል። እነዚህ እንቅስቃሴዎች በዋናነት ችግኞቹ እንዲጸድቁ ዓይነተኛ ሚና አላቸው። እንደ ሚኒስቴሩ መረጃ፤ በቢሊዮን የሚቆጠረው ችግኝ ያረፈው በአርሶ አደሩ እጅ በመሆኑ ችግኝ በተተከለባቸው አካባቢዎች ከብቶች እንዳይሰማሩ የአርሶ አደሩን ጥበቃ ይሻል።

አረንጓዴ አሻራ - የመጪው ትውልድ ድልድይ

ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ጉዞ የችግኝ ተከላን ወደ አገራዊ ንቅናቄ ለመቀየር የተደረገ ሙከራ ብቻ ሳይሆን፣ አካባቢን፣ ግብርናን፣ ውኃን፣ ምግብን፣ ሥራ እና ኢኮኖሚን በአንድ ላይ የሚያገናኝ ሰፊ የልማት አቅጣጫ ሆኖ ቀጥሏል።

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት በዚህ መርኃ- ግብር እስከ አሁን ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። የአገሪቷ የደን ሽፋንም ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ አድጓል፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የአፈር መሸርሸር ቀንሷል፣ የውኃ አካላት አገግመዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችም የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል።

ነገር ግን የአረንጓዴ አሻራ ትልቁ ትሩፋት ተፈጥሮን የመጠበቅ ኃላፊነትን ከመንግሥት ፖሊሲ አውጥቶ የዜጎች የዕለት ተዕለት ባሕልና አስተሳሰብ ማድረግ ነው። ምድርን ማልበስ የቅንጦት ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው። ዛሬ የምናኖረው አረንጓዴ አሻራ የዛፎች ስብስብ ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ የምናስረክበው የተሻለች ምድር፣ የተጠበቀ ተፈጥሮ እና ዘላቂ የልማት መሠረት ነው።

ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ምድርን ከመራቆት ወደ ልምላሜ፣ ከአካባቢ ጥበቃ ወደ ኢኮኖሚ ዕድል፣ ከግለሰብ ጥረት ወደ የጋራ ኃላፊነት እና ከችግኝ ተከላ ወደ አረንጓዴ አስተሳሰብ የሚያሸጋግር የትውልድ ጉዞ ነው።



64

ኢኮኖሚ

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ከተረጂነት ወደ ትርፍ አምራችነት



65

በማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር)

መግቢያ

ሉዓላዊነት ሲነሳ ብዙዎች የሚያስቡት የድንበር መከበርን ወይም የፖለቲካ ነፃነትን ብቻ ነው። ሆኖም ከእነዚህ ሁሉ ቅድመ-ሁኔታዎች በፊት የሚቆመው መሠረታዊ ጉዳይ ሕዝብን በራስ ምርት የመመገብ አቅም ነው። የራሱን ምግብ ማምረት የማይችል ሀገር ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ውሳኔዎቹን በሙሉ በራሱ ለመወሰን ይቸገራል። ስለዚህ በምግብ ራስን መቻል የኢኮኖሚ መለኪያ ብቻ ሳይሆን የአገር ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነፃነት፣ የማኅበራዊ መረጋጋትና የሕዝብ ክብር መሠረት ነው።

አንድ ሀገር የሕዝቧን መሠረታዊ የምግብ ፍላጎት በራሷ ማምረት ሳትችል ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥም ሆነ በዓለም አቀፍ መድረክ በእኩልነት መቆሟ አዳጋች ይሆናል።



66

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ አስፈላጊነት - ለኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ፣ በተለያየ ሥነ- ምህዳሯ፣ በሰፊ የእርሻ መሬቷና በሰው ኃይሏ ከአፍሪካ ትልልቅ የግብርና አቅም ካላቸው አገራት አንዷ ናት። ከ38 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ለእርሻ ተስማሚ መሬት፣ በርካታ የውሃ ሀብቶችና የተለያዩ የአየር ንብረት አቀማመጦች ያላት አገር ከራሷ አልፋ ሌሎችንም የመመገብ አቅም አላት።

ይሁን እንጂ ይህ እምቅ አቅም ለረጅም ጊዜ በሚገባው መጠን ወደ ምርት አልተቀየረም። በዝናብ ላይ የተመሠረተ ግብርና፣ የቴክኖሎጂ ውስን አጠቃቀም፣ የእሴት ሠንሰለት ክፍተቶች፣ የገበያ አለመደራጀትና በሌሎች መዋቅራዊ ችግሮች ምክንያት ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ ልክ ሳይሆን በድህነትና በእርዳታ ተቀባይነት ስትነሳ ቆይታለች።

ይህ ሁኔታ ከኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ ባሻገር በአገሪቷ መልካም ገጽታ እና በዜጎቿ ሥነ-ልቦና ላይ የራሱን ተጽዕኖ አሳድሯል።

በተጨማሪም፡-

የጂኦ - ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚ ግፊቶችን መቀነስ፡ - በምግብ እርዳታ ወይም አስመጪነት ላይ የተመሠረተ ሀገር የውጭ ኃይሎችን ፖለቲካዊ ፍላጎት ለመቀበል የሚገደድ መሆኑ፤

የዓለም አቀፍ ገበያ እና የአቅርቦት ሰንሰለት መበታተን (Global Supply Chain Crises) እንደ ሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ያሉ ዓለም አቀፍ ቀጣናዊ ግጭቶች እና የኮቪድ-19 ዓይነት ወረርሽኞች ከውጭ ሀገር እህል ማስገባት ምን ያህል ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን ማሳየታቸው፤

የውጭ ምንዛሬ ጫናን መቀነስ፡- በየዓመቱ ለስንዴ እና ለምግብ እህሎች ግዥ ይወጣ የነበረውን አጠቃላይ የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት ለሌሎች የልማት ዘርፎች ማዋል አስፈላጊ መሆኑ፤

የዜጎችን ክብርና ሥነ-ልቦና መገንባት፡- የረጅም ጊዜ የተረጂነት ታሪክ በዜጎች ሥነ-ልቦና ላይ ያሳደረውን አሉታዊ ጥላ በመገርሰስ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መንፈስ መፍጠር የሚሉት ዋና ዋና ምክንያቶች የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዳይ አስገዳጅ አድርገውታል።

የአገራት ተሞክሮ - ከስንዴ እና አግሪ-ትራንስፎርሜሽን ምን እንማራለን?

ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለው የግብርና ትራንስፎርሜሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተመዘገቡ ስኬታማ አገራዊ ተሞክሮዎች ጋር ተመሳሳይነት አለው።

የህንድ “አረንጓዴ አብዮት” (Green Revo- lution) - በ1960ዎቹ ህንድ በከባድ የምግብ እጥረትና እርዳታ ጥገኝነት ውስጥ ነበረች። ነገር ግን በጥቃቅን አርሶ አደሮች ተሳትፎ፣ በከፍተኛ የመስኖ ማፋጠን፣ በምርጥ ዘር አጠቃቀም እና በመንግሥት የፖሊሲ ድጋፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከምግብ አስመጪነት አልፋ ትልቋ የስንዴና የሩዝ ላኪ አገር መሆን ችላለች።

የብራዚል የግብርና ተዓምር (Embrapa Mod- el) - ብራዚል ሳይንሳዊ ምርምርን፣ የአፈር ማሻሻያንና ሰፊ የመስኖ ልማትን በመጠቀም አሲዳማና ለእርሻ የማይሆን የተባለውን “ሴራዶ” (Cerrado) መሬት ወደ ዓለም አቀፍ የምግብ ቅርጫትነት ቀይራዋለች።

የቬትናም የሩዝ እና አግሪ-ኤክስፖርት ሽግግር - ቬትናም ከጦርነት በኋላ ከነበረችበት የምግብ እጥረት ተነስታ አርሶ አደሮችን በክላስተር በመደራጀት እና ጥቃቅን አምራቾችን ከማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር ዛሬ የዓለም አቀፍ የግብርና ምርቶች መሪ ሆናለች።

የእነዚህ አገራት ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት የፖሊሲ ቁርጠኝነት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የመስኖ ልማት ከተዋሃዱ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ነው።

አገራዊው ንቅናቄ እና የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶች

ዛሬ የኢትዮጵያን ስም ከእርዳታ ተቀባይነት ጋር የሚያስጠራውን ታሪክ ታሪክ ለመቀየር የተጀመረው ጉዞ የሚታይና የሚለካ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል። በምግብ ራስን መቻል ላይ የተጀመረው አገራዊ እንቅስቃሴ የግብርና ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን አዲስ የሀገር እሳቤ ሆኗል። የሀገር ኢኮኖሚን በራስ አቅም መገንባት፣ የውጭ ጥገኝነትን መቀነስ፣ የዜጎችን የሥራ ዕድል ማስፋትና ለቀጣይ ትውልድ የተረጋጋ ኢኮኖሚ መፍጠር የዚህ ጉዞ ዋና ዓላማዎች ናቸው። በተለይም ከለውጡ ወዲህ በአገራችን



67

የተተገበሩት የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ግብርናን እንደ የኢኮኖሚ ሽግግር ዋና ሞተር በመመልከት የተለያዩ የፖሊሲ፣ የተቋማትና የመስክ ማሻሻያዎችን አስተዋውቀዋል።

የመስኖ ስንዴ ልማት አብዮት

ከግብርና ዘርፉ ከተገኙ ውጤቶች መካከል የመስኖ ስንዴ ልማት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚጠቀስ የለውጥ ምሣሌ ሆኗል። ትናንት በየዓመቱ በብዙ መቶ ሚሊዮን ዶላር የስንዴ ምርት ከውጭ ታስገባ የነበረችው ኢትዮጵያ፤ ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ የስንዴ አምራች ሆና ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ መብቃቷ የቁጥር ለውጥ ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰብ፣ የፖሊሲና የትግበራ ለውጥ ጭምር መሆኑን ያሳያል።

በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በመኸርና በመስኖ በድምሩ 8 ነጥብ 28 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ በመሸፈን 308 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገኝቷል። የ2018 በልግ ምርት በ10 ሚሊዮን ኩንታል በመጨመሩ የዓመቱን አጠቃላይ ምርት 318 ሚሊዮን ኩንታል አድርሶታል። በ2012 ዓ.ም 20 ሺህ ሄክታር ብቻ የነበረው በመስኖ ስንዴ የለማ መሬት በ2018 ዓ.ም ወደ 3 ነጥብ 78 ሚሊዮን ሄክታር አድጓል፤ ምርቱም ከ600 ሺህ ኩንታል ወደ 149 ሚሊዮን ኩንታል ከፍ ብሏል።

በመኸር ስንዴ የለማ መሬት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር ወደ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር ሲያድግ፤ ምርቱም ከ53 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 159 ሚሊዮን ኩንታል አድጓል።

ይህ ብሔራዊ ንቅናቄ ኢትዮጵያን ከስንዴ አስመጪነት ወደ ራሷን በራሷ የምትችል አገር በመቀየር ብቻ አልተወሰነም። በ2013 ዓ.ም ከውጭ ይገባ የነበረውን 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ በ2017 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርት መተካት በመቻሉ፤ አገሪቷ በዓመት በአማካይ ለስንዴ ግዥ ታወጣ



68

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

የነበረውን 1 ቢሊዮን ዶላር ማስቀረት ችላለች። ከዚህ የተቆጠበው የውጭ ምንዛሬም ለአገር ውስጥ ልማት፣ ለኢንቨስትመንትና ለሌሎች ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚ ዘርፎች እንዲውል አስችሏል።

በአሁኑ ወቅት የመንግሥት የስንዴ ከውጭ ግዥ ሙሉ በሙሉ የቆመ ቢሆንም፣ በከተሜነት መስፋፋት፣ በሕዝብ ቁጥር መጨመርና በምግብ ፍጆታ ልምድ ለውጥ ምክንያት የዳቦ፣ የፓስታ፣ የብስኩትና ሌሎች የስንዴ ውጤቶች ፍላጎት በቀጣይነት እየጨመረ በመሆኑ በግል ዘርፍ የሚፈጸም የስንዴ ከውጭ ግዥ እንዳለ መገንዘብ ያስፈልጋል። ይህም የአገሪቷ የምግብ ፍላጎትና የገበያ መስፋፋት እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ ነው።

ይህ ስኬት የተገኘው በመስኖና በመኸር ስንዴ ላይ በተካሄደው ብሔራዊ ንቅናቄ ሲሆን፤ የስንዴ ልማትን በስፋት በማስፋፋት የሀገሪቷን የምግብ ዋስትና ማጠናከር፣ የውጭ ጥገኝነትን መቀነስና የውጭ ምንዛሬን ማዳን ተችሏል።

ከስንዴ ባሻገር በሩዝ፣ በአኩሪ አተር፣ በገብስና በሌሎች የስትራቴጂክ ሰብሎች የተመዘገበው ዕድገት ኢትዮጵያ ከምግብ ራስን መቻል ወደ ግብርና ኮሜርሺያላይዜሽን ተወዳዳሪነት እየተሸጋገረች መሆኗን ያሳያል። ይህ ደግሞ ለኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃ አቅርቦትን ከማረጋገጥ ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ግፊትን በመቀነስ የአገሪቷን የማክሮ ኢኮኖሚ ለማረጋጋት ጭምር አስተዋጽኦ እያደረገ ነው።

ያልተገደበው የግብርና ለውጥ

የለውጡ ሌላው ጉልህ መገለጫ አርሶ አደሮችን በምርት ክላስተር ማደራጀት ነው። ለረጅም ጊዜ በተበታተነ መልኩ ይመረት የነበረው ግብርና በተቀናጀ መልኩ መመራት ሲጀምር የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የሜካናይዜሽን አገልግሎት፣ የግብዓት አቅርቦትና የገበያ ተደራሽነት በእጅጉ ተሻሽሏል። በዚህ አካሄድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ባለ አነስተኛ ይዞታ አርሶ አደሮች በአንድነት በመሥራት የምርታማነት ጭማሪ እና የገቢ መሻሻል አስመዝግበዋል።

የሌማት ትሩፋት - የግብርናው ለውጥ በሰብል ልማት ብቻ የተገደበ ባለመሆኑ፤ በእንስሳት

ሀብት ዘርፍም መሠረታዊ ለውጥ ተመዝግቧል። የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ በወተት፣ በእንቁላል፣ በሥጋ፣ በማርና በዓሣ ምርት የተገኘውን ዕድገት በማፋጠን የምግብና የሥነ-ምግብ ዋስትናን ከማጠናከር ባሻገር ለሚሊዮኖች ዜጎች የገቢ ምንጭና የሥራ ዕድል ፈጥሯል። ይህ ኢኒሼቲቭ በምግብ ራስን መቻል ማለት እህልን ብቻ በብዛት ማምረት ሳይሆን፣ ለተመጣጠነ ሥነ- ምግብ የሚያስፈልጉ ሁሉንም የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች በበቂ መጠንና በተደራሽነት ማምረት መሆኑን በተግባር አረጋግጧል።

በዚህም በ”ሌማት ትሩፋት” ኢኒሼቲቭ በአራት ዓመታት ውስጥ የወተት ምርት ከ6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ወደ 15 ነጥብ 8 ቢሊዮን ሊትር፣ የእንቁላል ምርት ከ3 ነጥብ 2 ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን፣ የዶሮ ሥጋ ከ90 ሺህ ቶን ወደ 253 ሺህ ቶን፣ የማር ምርት ከ147 ሺህ ወደ 427 ሺህ ቶን፣ የዓሣ ምርት ከ78 ሺህ ወደ 307 ሺህ ቶን ማሳደግ መቻሉ ከተመዘገቡ ውጤቶች መካከል መጥቀስ ይቻላል።

በተጨማሪም በ2018 ዓ.ም ብቻ 184 ሚሊዮን የአንድ ቀን ጫጩቶች፣ 17 ነጥብ 6 ሚሊዮን



69

የዓሣ ጫጩቶች እና 3 ነጥብ 01 ሚሊዮን ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች ተሰራጭተዋል፤ 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን አርሶ እና አርብቶ አደሮችም የኤክስቴንሽን አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል።

በኢኒሼቲቩ የዶሮ፣ የወተት፣ የዓሣ እና የማር መንደሮችን በማቋቋም የተቀናጀና የተሟላ የኤክስቴንሽን ሥርዓት ተዘርግቷል። ይህም የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ በምርት መጠን ላይ ብቻ ሳይሆን የአርሶ አደሮችን አቅም በመገንባት፣ የምርት ሠንሰለቱን በማጠናከርና ዘላቂ የሥነ- ምግብ ዋስትና ሥርዓት በመገንባት ጭምር ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ያረጋግጣል።

የአረንጓዴ አሻራ እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ - ዘላቂ የግብርና ልማት የተፈጥሮ ሀብትን ሳይጠብቅ ሊሳካ አይችልም። በዚህ ረገድ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአካባቢ ጥበቃን ከግብርና ልማት ጋር በተሳካ ሁኔታ ያስተሳሰረና በዓለም የሚጠቀስ ተምሣሌታዊ ፕሮግራም ሆኗል። ዛሬ በኢትዮጵያ የተመዘገበው የቡና ምርትና የውጭ ንግድ ገቢ መጨመር ከዚህ ሰፊ የአካባቢ ተሃድሶና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጋር በቅርበት የተሳሰረ መሆኑን ያሳያል።

በመርሃ ግብሩ በተከናወኑ ተከታታይ ተግባራት የሀገሪቷ የደን ሽፋን በ2011 ዓ.ም ከነበረው 17 ነጥብ 2 በመቶ በ2018 ዓ.ም ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ ብሏል። ይህ ስኬት ባለፉት ሥድስት ዓመታት 56 ነጥብ 8 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል፣ ኅብረተሰቡን በደን ጥበቃና አያያዝ ዙሪያ በማንቀሳቀስ እና የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምን በማሻሻል የተገኘ ነው። በተመሳሳይ በ2011 ዓ.ም በዓመት ይጠፋ የነበረውን 38 ሺህ ሄክታር የደን ሀብት በ2017 ዓ.ም ወደ 28 ሺህ ሄክታር ዝቅ ማድረግ ተችሏል። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሃሳብ በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ንቅናቄ ተከናውኗል፤ በውጤቱም ከ805 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል።

የአረንጓዴ አሻራ ውጤት በደን ሽፋን መጨመር ብቻ የሚለካ ባለመሆኑ፤ ለምግብ የሚውሉ የፍራፍሬና የቡና ችግኞችን በስፋት በማሰራጨት ለሥነ-ምግብ መሻሻልና ለአርሶ አደሮች የገቢ ምንጭ መፍጠር አስተዋጽኦ አበርክቷል፤ በዚህም ወደ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚጠጋ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፤ በየዓመቱም በአማካይ ከ40 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በችግኝ ተከላና በአካባቢ ተሃድሶ በማሳተፍ የሕዝብ የልማት ባለቤትነትንና የጋራ ኃላፊነትን

አጠናክሯል። በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም፣ የካርቦን ልቀትን በመቀነስና ዘላቂ የግብርና ልማትን በማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።

በዚህ የተቀናጀ ተግባር የአፈር መሸርሸር በዓመት ከ130 ቶን በሄክታር ወደ 54 ቶን በሄክታር ዝቅ ብሏል፤ ወደ ወንዞች የሚወርደው የደለል መጠንም ከ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ቶን ወደ 208 ሚሊዮን ቶን በመቀነሱ የተፈጥሮ ሀብቶችን ከመጠበቅ ባሻገር የውሃ ሀብቶችን፣ የግድቦችን ዘላቂነትና የግብርና ምርታማነትን ለማሻሻል ጉልህ ሚና ተጫውቷል። ይህ የአረንጓዴ አሻራ መር`ሃ ግብር የችግኝ ተከላ ዘመቻ ብቻ ሳይሆን የአገሪቷን ኢኮሎጂያዊ ሚዛን በመጠበቅ ዘላቂ የኢኮኖሚ እና የግብርና ልማት መሠረት የሚጥል ትውልድ ተሻጋሪ የልማት ንቅናቄ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

ዲጂታል ግብርና፣ መሠረተ ልማትና የአርሶ አደሩን አቅም ማጎልበት

የኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነት ጉዞ በማሳ ላይ በሚመረት ምርት ብቻ የሚያበቃ አይደለም። የአርሶ አደሩን አቅም ማጎልበት፣ ግብርናውን ሙሉ በሙሉ ወደ ዘመናዊ ኢኮኖሚ ለማሸጋገር ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣ የድህረ- ምርት ብክነትን መቀነስ እና የፋይናንስ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ድልድዮች ናቸው።

ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ውጪ ሊታሰብ የማይችለው የዘመናችን ግብርና፤ የምክር አገልግሎት፣ የገበያ መረጃ፣ የአርሶ አደሮች ምዝገባ፣ የግብዓት ሥርጭት እና የፋይናንስ ተደራሽነት በዲጂታል ሥርዓት ሲደገፍ ከባህላዊ አሠራር ወደ ዘመናዊ ኢንዱስትሪ እየተሸጋገረ ነው። ይህ ሽግግር በተለይ ለወጣቶች ግብርናን እንደ አንድ የሥራ እና የቢዝነስ ዕድል እንዲመለከቱት አዲስ መንገድ ከፍቷል።

የሳተላይት መረጃዎችንና የዲጂታል ኤክስቴንሽን አገልግሎቶችን በመጠቀም ለአርሶ አደሮች የሚሰጠውን የምክር አገልግሎት ማዘመን፣ የአፈር ለምነትን በዲጂታል ካርታ ማወቅ እና የአርሶ አደሮች የኤሌክትሮኒክስ ምዝገባ (Dig- ital Farmer Registry) ሥራዎች በስፋት እየተተገበሩ ይገኛሉ።

የድህረ-ምርት ብክነትን በመቀነስ ተግባር የተመረተው ምርት ለገበያ ሳይደርስ የሚባክንበትን አሠራር ለማስቀረት የዘመናዊ



70

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ጎተራዎች፣ የማቀዝቀዣ መጋዘኖች እና የተቀናጁ የትራንስፖርት አማራጭ ግንባታዎች እየተስፋፉ ነው።

ሴቶችና ወጣቶችን በማብቃት ረገድም ወጣቶች በግብርና ሜካናይዜሽን፣ በቴክኖሎጂ አቅርቦት እና በንግድ ሠንሰለቱ ውስጥ በስፋት እንዲሳተፉ በማድረግ ግብርናን ማራኪ የቢዝነስ ዘርፍ ማድረግ ተችሏል። በተጨማሪም በገጠር ኢኮኖሚ ውስጥ የሴቶችን የመሬት እና የፋይናንስ ተደራሽነት ማረጋገጥ የትራንስፎርሜሽኑ አካል ሆኗል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የአርሶ አደሩን የብድርና የመድን ተደራሽነት በማሳደግ አርሶ አደሩ ከአየር ንብረት መዛባትና ከገበያ መናጋት ራሱን እንዲጠብቅ ያስቻለው የፋይናንስ ብድር እና የግብርና መድን ተደራሽነትና አቅርቦት ትልቅ አቅም ፈጥሯል።

ተግዳሮቶች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ኢትዮጵያ በምግብ ራስን መቻል ላይ ብቻ አትቆምም። እስከ አሁን የተመዘገቡት ለውጦች ሁሉ የሚያሳዩት አንድ ትልቅ እውነት አለ፤ ቀጣዩ የአገሪቷ ግብ በአፍሪካ የግብርና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ መገንባት፣ እሴት የሚጨምሩ ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት እና ከምግብ ራስን መቻል ወደ የምግብ ሉዓላዊነት መሸጋገር ነው።

እርግጥ ነው፤ ከፊታችን ያሉ ተግዳሮቶች አሁንም ቀላል አይደሉም። የምርት ብክነት፣ የሎጂስቲክስ ውስንነት፣ የፋይናንስ ተደራሽነት፣ የውጭ ገበያ ውድድር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ እና ተቋማዊ አቅምን ማጠናከር አሁንም የቤት ሥራዎቻችን ናቸው። ነገር ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታየው አፈጻጸም ትልቅ ተስፋን ይሰጠናል - በጋራ ራዕይ፣ በጽናት እና በሳይንስ



71

በተደገፈ አሠራር ማንኛውንም ፈተና ወደ ዕድል መቀየር እንደምንችል።

በምግብ ራስን መቻል ለኢትዮጵያ የመጨረሻ መዳረሻ ሳይሆን ወደ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር የሚወስድ መነሻ ነው። የምናስበው ኢትዮጵያ የራሷን ፍላጎት ብቻ የምታሟላ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ በግብርና ምርት፣ በምግብ ኢንዱስትሪ እና በአግሪቢዝነስ ተወዳዳሪ የሆነ ኢኮኖሚ የገነባች ሀገር እንድትሆን ነው። ይህን ራዕይ ለማሳካት የምርት መጠንን ማሳደግ ብቻ በቂ አይደለም፤ ጥራትን ማሻሻል፣ የእሴት ጭመራን ማስፋፋት፣ የገበያ ተወዳዳሪነትን ማጠናከር እና ግብርናን ዘመናዊ ንግድ እንዲሆን ማስቻል ይጠይቃል።

በዚህ ጉዞ የእሴት ሠንሰለትን ማጠናከር ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ፤ የአርሶ አደሩ ምርት በማሳ ላይ ብቻ የሚለካ ሳይሆን ከማምረት ጀምሮ እስከ ማከማቸት፣ ማጓጓዝ፣ ማቀነባበር፣ ማሸግ እና ለተጠቃሚው ማድረስ ድረስ ባለው በእያንዳንዱ ሂደት የሚፈጠረውን እሴት ማሳደግ ያስፈልጋል። ይህ ከፍተኛ የድህረ ምርት ብክነትን ይቀንሳል፣ የአርሶ አደሩን ገቢ ያሳድጋል፣ ለሸማቹም ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲደርስ ያደርጋል።

የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ እውን ለማድረግ የሚያዳግቱ መዋቅራዊ ተግዳሮቶች አሁንም የቤት ሥራዎች በመሆቸው ይህንን ለማስተካከል በቅርቡ የፀደቀው የአግሪቢዝነስ ኩባንያዎች አዋጅ አርሶ አደሮችን ከተናጠል አምራችነት ወደ ንግድና ኢንቨስትመንት ተሳታፊነት የሚያሸጋግር እና በአግሪቢዝነስ ኢኮኖሚ ውስጥ ባለ አክሲዮን የሚያደርግ ታሪካዊ የሕግ ማዕቀፍ ነው። አዋጁ አርሶ አደሩ የልማት ተቀባይ ብቻ ሳይሆን የልማቱ ባለቤትና ተጠቃሚ እንዲሆን ያደርገዋል።

እዚህ ላይ የግሉ ዘርፍም የሽግግሩ ዋና ተዋናይ ሊሆን ይገባል። መንግሥት ምቹ የፖሊሲ ማዕቀፍና አስቻይ ከባቢ ሲፈጥር፤ ባለሀብቱ በማቀነባበር፣ በሎጂስቲክስ፣ በኤክስፖርት፣ በቴክኖሎጂ እና በፋይናንስ አገልግሎቶች ያለውን አቅም በመጠቀም የግብርና ዘርፉን ከምርት ወደ ንግድ ኢኮኖሚ ሊያሸጋግረው ይችላል። የአገራችን የግብርና ዕድገት ዘላቂ የሚሆነው የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ይበልጥ ሲጠናከር ነው።

በተመሳሳይ ሁኔታ ሴቶችና ወጣቶች የዚህ ለውጥ ተጠቃሚዎች ብቻ ሳይሆኑ መሪዎች ሊሆኑ ይገባል። ከአገሪቷ የሰው ኃይል አብዛኛው ወጣት ነው፤ በገጠር ኢኮኖሚ ውስጥ ደግሞ ሴቶች የማይተካ ሚና ይጫወታሉ። እነዚህን ሁለት ኃይሎች በክህሎት፣ በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስ እና በገበያ ተደራሽነት ማብቃት የኢትዮጵያን የግብርና ትራንስፎርሜሽን የሚያፋጥን ትልቅ አቅም ነው።

የአየር ንብረት ለውጥ በግብርናችን ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ የዝናብ መዛባት፣ የሙቀት መጨመርና የተፈጥሮ ሀብት መራቆት የምግብ ዋስትና ፈተና ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ የመስኖ ልማትን ማስፋፋት፣ ውሃን በብቃት መጠቀም፣ የአፈር ጥበቃን ማጠናከር፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋሙ ዝርያዎችን ማልማትና የዲጂታል የአየር ሁኔታ መረጃዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ማድረግ ከፍ ያለ ትኩረትን የሚሹ ጉዳዮች ናቸው።

ማጠቃለያ

የኢትዮጵያ የግብርና ታሪክ ዛሬ አዲስ ገፅ እየጻፈ ነው። ይህ ገፅ የተረጂነት ሳይሆን የምርታማነት፤ የጥገኝነት ሳይሆን የሉዓላዊነት፤ የእጥረት ሳይሆን የብልጽግና ታሪክ ነው። ይህንን ታሪክ የሚጽፉት ደግሞ መንግሥት ብቻ ሳይሆን በየቀኑ በማሳው ላይ የሚደክሙ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች፣ ተመራማሪዎች፣ ባለሀብቶች እና መላው ኢትዮጵያዊያን ናቸው።

እዚህ ላይ ከግንዛቤ ማስገባት የሚያሻው ትልቅ ጉዳይ፤ የመንግሥት ተቋማት፣ የምርምር ማዕከላት፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የግሉ ዘርፍ፣ የልማት አጋሮች እና አርሶ አደሮች በተቀናጀ መልኩ ሲሠሩ ዘላቂ ውጤት ማምጣት እንደሚቻልና የግብርና ለውጥ የአንድ ተቋም ኃላፊነት ብቻ እንዳልሆነ በተግባር አረጋግጠናል። ይህ ቅንጅት በቀጣይም የበለጠ መጠናከር አለበት፤ ምክንያቱም የግብርና ትራንስፎሜሽን የአንድ ተቋም ስኬት ሳይሆን የመላው ሀገር ነውና።

አሁን በምግብ ራስን መቻል ለኢትዮጵያ የመጨረሻ መዳረሻ ሳይሆን ወደ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር የሚወስድ መነሻ ነው። ዋናው ራዕይ ኢትዮጵያ የራሷን ፍላጎት በሙሉ አሟልታ በአፍሪካ በግብርና ምርት፣ በምግብ ኢንዱስትሪ እና በአግሪቢዝነስ ተወዳዳሪ የሆነች፣ ለቀጣይ ትውልድ የተረጋጋች እና ብልጽግናን ያረጋገጠች አገር ማድረግ ነው።



72

ኢኮኖሚ

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ከሣንቲም ህትመት እስከ ኢትዮጵያ ታምርት”



73

በሰለሞን ተሰራ

በታላቋ ብሪታኒያ ቀዝቃዛ አየር ውስጥ አዲስ የለውጥ ማዕበል መታየት ሲጀምር ዘመኑ እ.አ.አ 1760ዎቹ ላይ ነበር። የሰው ልጅ ለዘመናት በጉልበቱ፣ በእንስሳት እርዳታና በእጅ መሣሪያዎች በመታገዝ የዕለት ሕይወቱን ለመምራትና ፍላጎቶቹን ለማሟላት የተለያዩ ምርቶችን ሲያመርት የኖረበት ዘመን ሊያበቃ፤ አዲስም ጥበብ ሊወለድ መሆኑን የሚያሳዩ ጭላንጭሎች ብቅ እያሉ፤ በሌላ በኩል ከሰው ልጅ አዕምሮ የፈለቀውና አዲስ የጥበብ ፍንጣቂ የሆነው የእንፋሎት ኃይል ዓለምን ከእንቅልፏ እየቀሰቀሳት የነበረበት ነው ወቅቱ።

ይህ የእንፋሎት ኃይል የሰው ልጅን የታሪክ ጉዞ እና የአኗኗር ዘይቤ ከለወጡ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ግኝቶች መካከል አንዱ ሆኖ ተቀምጧል። ቴክኖሎጂው ከተለያዩ ሙከራዎች ተነስቶ፣ በኢንዱስትሪ አብዮት ወቅት እውን በመሆን ዓለምን ወደ ማሽን ያሸጋገረበት ታሪክ የዘመኑ ቁልፍ እጥፋት ሆኖ እስከዛሬ ይወሳል። የሰው ልጅ ምጡቅ እሳቤ በወለደው የእንፋሎት ኃይል በመታገዝ የሚሠሩት ግዙፍ ማሽኖች ከዓለም ጋር የተዋወቁት ያኔ ነው።

ይህ አዲስ ግኝት የጨርቃጨርቅ ማምረቻዎች ቀን እና ሌሊት ያለ ዕረፍት በመሥራት ምርታቸውን እንዲያዘምኑ፣ የብረት ማቅለጫ እቶኖች ግለታቸው ሳይበርድ እንዲሠሩ፣ የባቡር ትራንስፖርት ከአንዱ ጫፍ ወደ ሌላው ጫፍ ያለምንም መስተጓጎል እንዲተም ትልቅ መንገድ ከፍቷል። ይህ የመጀመሪያው የኢንዱስትሪ አብዮት ተደርጎ የሚቆጠር ሲሆን የፈጠራ ብርሃኑም የብሪታኒያን ድንበር ጥሶ ወደ ቤልጂየም፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ጀርመንና ጃፓን



74

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ተሻገረ። ዓለም ዳግም እንደ ትናንቱ ላትሆን ወደፊት ተስፈነጠረች፤ የሰው ልጅ አዕምሮ የወለዳቸው ግዙፍ ማሽኖችም የዕለት ተዕለት ሕይወት ዋና መሪ ሆነው ብቅ አሉ።

የሰው ልጅ አዕምሮ ያለ ዕረፍት ፈጠራውን አጠናክሮ ሲቀጥል ዓለም አዲስ መልክ መላበስ ጀመረች። ዕድገቱ እንዲህ እንዲያ እያለ በመጓዝ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ተከሰተ። ፋብሪካዎች በአስደማሚ ሁኔታ አዳዲስ ምርቶችን በብዛት ለገበያ አስተዋወቁ፤ ምድርም በደማቅ ብርሃን ተሞላች፤ የጅምላ ምርት (Mass Production) ሥርዓትም ተጀመረ። ጊዜው ያለማቋረጥ ወደፊት ሲገሰግስ የሰው ልጅ አዕምሮም የጥበብ ፍሬውን ማዝነቡን ቀጠለ።

በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ዘመናዊ ኮምፒዩተሮችና የረቀቁ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች በየቤቱ ደረሱ። በዚህም ማሽኖች ከሰው ንክኪ በጸዳ መልኩ የራሳቸውን ሥራ በራሳቸው የሚያከናውኑበትን የኦቶሜሽን ዘመን ፈጠሩ። ዛሬ ላይ ደግሞ ማሽኖች ከሰው ጥገኝነት ይበልጥ በመላቀቅ በራሳቸው ማሰብና መወሰን ጀምረዋል። ዓለምም ልጆቿን ወደኋላ አስቀርታ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂና በሮቦቶች የምትመራበትን አዲሱን እውነታ ለመቀበል እየተገደደች መሆኗን በተግባር እያሳየች ትገኛለች።

የኢንዱስትሪ አሃዱ

ዓለም በእንፋሎትና በኤሌክትሪክ የፈጠራ ስልቶች ታግዛ ወደፊት ስትራመድ፤ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማጠናቀቂያና በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያም አዲስ ታሪክ እያቆጠቆጠ ነበር። ለቴክኖሎጂ ጥልቅ ፍላጎት የነበራቸውና ሀገሪቷን ወደ ዘመናዊነት ለማምጣት ጉዟቸውን አንድ ብለው የጀመሩት የወቅቱ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ፤ በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ ብርና ሣንቲሞች ፈረንሳይ አገር ይታተሙ ስለነበር የትራንስፖርት ወጪን ለመቀነስና ሀገሪቱ በራሷ ሉዓላዊ የገንዘብ ማምረቻ እንድትጠቀም ለማድረግ በማሰብ የመጀመሪያውን ዘመናዊ የሣንቲም ማምረቻ (Minting Machine) ወደ ሀገር ውስጥ በማስመጣት ሥራ እንዲጀምር አደረጉ።

በመቀጠልም የረጅም ርቀት የስልክ መስመሮችን በማስዘርጋት ሀገሪቷን ከዳር እስከ ዳር ማገናኘት የቻሉ ሲሆን ከጅቡቲ አዲስ አበባ የሚተመው የምድር ባቡርም የብረት ሐዲዱ ተዘርግቶለታል። አነስተኛ የጨርቃጨርቅ እና የምግብ ማቀነባበሪያዎችም ተከፈቱ። የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤትም የፊደላትን ጥበብ በይፋ ማተም ጀመረ። የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፅንስ በዚህ መልኩ ተቀረጸ።ከ1920ዎቹ እስከ 1960ዎቹ ባለው ጊዜ ውስጥ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት፤ የሀገሪቷ የኢንዱስትሪ መዋቅር ይበልጥ መልክ መያዝ ጀመረ። የውጭ ባለሀብቶች ወደ በስፋት መጡ። የድሬዳዋ ጨርቃጨርቅ፣ የወንጂ ስኳር እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካዎች ተቋቁመው የሀገሪቷን የኢኮኖሚ ምሰሶ መደገፍ ጀመሩ።

ነገር ግን በ1967 ዓ.ም የመንግሥት ለውጥ ሲደረግ የደርግ ሥርዓት የሶሻሊዝም ፖሊሲን ይዞ መጣ። ትናንት በግል ጥረት የቆሙ ፋብሪካዎች በሙሉ በአንድ ጀንበር “ብሔራዊ” በሚል ቀጭን ትዕዛዝ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ተደረገ። ይህ ወቅት የሀገሪቷን የኢንዱስትሪ ጉዞ በእጅጉ ወደ ኋላ የጎተተ፣ ተወዳዳሪነቷን ገደል የከተተና ዘርፉን ለብዙ ዘመናት ወደኋላ የመለሰ እንደነበር ብዙዎች ይስማሙበታል። ይህንን ታሪካዊ ማሽቆልቆል ተከትሎም የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ጉዞ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ በግብርና መር ኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ታግዞ አዲስ ምዕራፍ ጀመረ። ይህ ስትራቴጂ የሀገር ውስጥ አምራቾችን በአነስተኛ ሁኔታ በማሳተፍ እና ለውጭ ኢንቨስትመንት ቅድሚያ በመስጠት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት ከፍተኛ የመሠረተ ልማት አውታሮችን አስፋፍቷል። ምንም እንኳን ኢኮኖሚው ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚጠበቀውን ያህል በፍጥነት ባይሸጋገርም የጨርቃጨርቅና የግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፎች የሀገሪቷን ገጽታ በመለወጥ ረገድ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

መደመር እና ኢትዮጵያ ታምርት



75

ከንድፈ-ሐሳብ ወደ ሀገራዊ ብልጽግና፡- በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የልማት ጉዞ ውስጥ ውጤታማ የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ፍልስፍናዎችን ከተግባራዊ የኢኮኖሚ ንቅናቄዎች ጋር ማጣመር መሠረታዊ ስትራቴጂ ሆኖ ያገለግላል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የ”መደመር” ፍልስፍና እና የ”ኢትዮጵያ ታምርት” ብሔራዊ የኢንዱስትሪ ልማት ንቅናቄ ደግሞ የዚህ መስተጋብር ዋነኛ መገለጫዎች ናቸው። “መደመር” ሀገራዊ የልማት መዘውር ሆኖ ሲያገለግል፤ “ኢትዮጵያ” ታምርት ደግሞ የዚሁ ፍልስፍና ተግባራዊ የኢኮኖሚ ሞተር በመሆን የአገሪቷን የአምራች ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ እየለወጠ ይገኛል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የተደረገው “የመደመር መንግሥት“ እሳቤ በአራት ዋና ዋና መዋቅራዊ ምሶሶዎች ላይ የተገነባ ነው። የመጀመሪያው ምሶሶ መነሻ ሲሆን የኢትዮጵያን ታሪካዊ ስኬቶች በማስቀጠል ላይ የሚመሠረትና ያለፉ መዋቅራዊና ፖሊሲ ነክ ስብራቶችን በጥናትና በሳይንሳዊ መንገድ ለመጠገን የሚነሳ ነው። ሁለተኛው ምሶሶ የዜጎችን ሁለንተናዊ ፍላጎቶች ያሟላች፣ በራሷ የምትተማመንና የበለጸገች ሀገርን የመገንባት መድረሻ ነው። ሦስተኛው ምሶሶ መንገድ ሲሆን ከውጭ የሚመጡ ፖሊሲዎችን በጭፍን ከመቅዳት በመውጣት አገር በቀል እውቀትን፣ ሀብትንና የሰው ኃይል አቅምን ማዕከል ያደረገ የኢኮኖሚ ሪፎርም መከተልን ያመለክታል። አራተኛውና የመጨረሻው ምሶሶ መንግሥት ሲሆን ራሱ ነጋዴ ሆኖ የግሉን ዘርፍ ከማጨናገፍ ይልቅ ለአምራቾች ምቹ ሁኔታዎችን፣ ብድርንና መሠረተ-ልማት የሚያመቻች አስቻይና መሪ መንግሥት መሆንን የሚገልጽ ነው።

ይህ የመደመር ፍልስፍና ያነገባቸው አገር በቀል እሳቤዎች እና ስብራትን የመጠገን መርሆዎች በ”ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ አማካኝነት በተግባር መሬት ወርደው ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችለዋል። የመደመር ስብራትን የመጠገን መርህ በተግባር የታየበት ዋነኛው ስኬት በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ተዘግተው የነበሩ ከ830 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች በመንግሥት ድጋፍ ወደ ሥራ መመለሳቸው ነው። ይህም ሀገራዊ የፋብሪካዎች የማምረት አቅም አጠቃቀምን ከ46 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ያደረገው ሲሆን ከ26 ሺህ በላይ አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ገበያ እንዲገቡ አስችሏል።

ንቅናቄው አገር በቀል ምርታማነትን በማበረታታት አምሥት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ማዳን የቻለ ሲሆን የሀገር ውስጥ ምርቶች በሀገር ውስጥ ገበያ ያላቸው ድርሻም ወደ 45 በመቶ አድጓል።

የመደመር መንግሥት ዋነኛ መድረሻ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻልና ሥራ አጥነትን



76

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

መቅረፍ በመሆኑ ይህ ስኬት ከሥራ ዕድል ፈጠራና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ጋር በቀጥታ ይገናኛል። በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አማካኝነት ለአነስተኛ፣ ለመካከለኛና ለከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች የሚቀርበው የፋይናንስ ብድር በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ተደርጓል። ይህ አሠራር አዳዲስ ፋብሪካዎች እንዲስፋፉና ለብዙ ሺህ ወጣቶችና ሴቶች ቋሚና አስተማማኝ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር አድርጓል። የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ወደ 65 በመቶ ማደጉ ደግሞ የወጣቶችን የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ባለቤትነት ያረጋገጠ ሌላው ተጠቃሽ ስኬት ነው። በአጠቃላይ የመደመር መንግሥት እሳቤ እና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የማይነጣጠሉ የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው።

መደመር የልማት ጉዞውን መስመር እና መርህ ሲያስቀምጥ፤ ኢትዮጵያ ታምርት ደግሞ ያንን መርህ ወደ ተጨባጭ ምርት፣ የሥራ ዕድል እና የውጭ ምንዛሬ ማዳን ቀይሮታል። ይህ ዓይነቱ የተቀናጀ አቀራረብ ኢትዮጵያ ከተቀባይነትና ከጥገኝነት ወጥታ ራሷን ወደ መቻልና ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን በመሆኑ ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ ነው።

ኢትዮጵያ ታምርት

ታሪኩ ዛሬም ቀጥሏል፤ “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል አገር በቀል ንቅናቄ የሀገር ውስጥ ምርትን የማሳደግና ከውጭ የሚገቡትን የመተካት ታላቅ ጉዞ በስፋት እውን የሆነው ከለውጡ መንግሥት በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ታሪክ ከአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የተለያዩ ምዕራፎችን ቢሻገርም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋፅኦ ከሰባት በመቶ አልፎ የማያውቅ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በግብርና መር ኢኮኖሚ ውስጥ ለዘመናት በመቆየቷ ምክንያት ለተኪ ምርቶች የሚሆን የኢንዱስትሪ መሠረት በበቂ ሁኔታ ሳይጣል ቆይቷል።

በዚህ ረገድ የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ብሔራዊ ንቅናቄ የሀገሪቷን የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ መዋቅራዊ ችግሮች ለመፍታት፣ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካትና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳሳቢነት በሚያዚያ 2014 ዓ.ም ይፋ የተደረገ ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ መርኃ ግብር ነው።



77

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ በ2014 ዓ.ም ይፋ ከመደረጉ በፊት የሀገሪቷ አምራች ዘርፍ በከፍተኛ መዋቅራዊ ቀውስ ውስጥ ይገኝ ነበር። ይሁንና የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ሲመራበት ከነበረው ስትራቴጂ በመውጣት አሁን አዳዲስ ሀገራዊ ፖሊሲዎችንና መዋቅራዊ ሪፎርሞችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ታላቅ የኢኮኖሚ ሽግግር በአዲሱ የፖሊሲ ማሻሻያ፣ በ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ፣ በማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና በተቀናጁ የግብርና-ኢንዱስትሪ ፓርኮች ዙሪያ በርካታ ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ ይገኛል።

በሪፎርም ምዕራፍ ውስጥ ከታዩት ዋና ዋና ለውጦች መካከል የመጀመሪያው የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ማሻሻያ ሲሆን ይህም ቀደም ሲል ለውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ብቻ ይሰጥ የነበረውን ቅድሚያ በመቀየር ለሀገር ውስጥ አምራቾች ሰፊ ማበረታቻና ትኩረት መስጠት አስችሏል። ይህንን መዋቅራዊ ሽግግር በተግባር ለመደገፍም የሀገር ውስጥ አምራቾች የማምረቻ ማሽነሪዎችን በኪራይና ግዢ እንዲሁም ለዕለታዊ ሥራቸው የሚሆን የሥራ ማስኬጃ ብድር በቀላሉ የሚያገኙበት ምቹ የፋይናንስ አቅርቦት አሠራር በስፋት ተዘርግቷል።

ይህንን የፖሊሲ ለውጥ ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳሳቢነት የተጀመረው “ኢትዮጵያ ታምርት” አገራዊ ንቅናቄ በዘርፉ ይስተዋሉ የነበሩ ዋና ዋና ማነቆዎችን በመፍታት ረገድ ከፍተኛ ስኬት አስመዝግቧል። በዚህም መሠረት ቀደም ሲል በኤሌክትሪክ መቆራረጥ፣ በፋይናንስ እና በጥሬ ዕቃ እጥረት ምክንያት ከግማሽ በታች ማለትም በ47 በመቶ ብቻ ተገድቦ የቆየው የፋብሪካዎች አማካይ የማምረት አቅም ወደ 67 በመቶ ከፍ ብሏል። በተጨማሪም ቀደም ሲል ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ይወጣባቸው የነበሩ እንደ የፖሊስና የመከላከያ የደንብ ልብሶች፣ የውሃ ቆጣሪዎች፣ የምግብና የመድኃኒት ግብዓቶች በአገር ውስጥ ምርቶች ሙሉ በሙሉ እንዲተኩ በማድረግ ረገድ ንቅናቄው ውጤታማ ተኪ ምርቶችን ማፍራት ችሏል።

የሀገሪቷ የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉን ተከትሎ የመጣው የማክሮ- ኢኮኖሚ ሪፎርም ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ አምራቾች የሚያገኙት ገቢ እንዲጨምር ማስቻሉ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ያላቸው ተወዳዳሪነትና ዕድል በእጅጉ እንዲሰፋ አስችሏል። የሀገሪቷን የግብርና ምርቶች እሴት ለመጨመር የተነደፈው ሌላው ትልቅ ስኬት ደግሞ የተቀናጁ የግብርና-ኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት ነው። ለዚህም ማረጋገጫ የሚሆኑት በይርጋለም (ሲዳማ)፣ በቡሬ (አማራ)፣ በቡልቡላ (ኦሮሚያ) የተገነቡት ግዙፍ ፓርኮች ወደ ሙሉ ሥራ የገቡ ሲሆን፤ የአቮካዶ ዘይት፣ የወተትና የማር ውጤቶች እንዲሁም የታሸጉ የምግብ ምርቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በስፋት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2018 ዓ.ም በተካሄደው አራተኛው “ኢትዮጵያ ታምርት” ብሔራዊ ንቅናቄ ኤክስፖ ላይ “የአራት ዓመታት ተከታታይ ጥረት እና የሚጨበጥ ውጤት የታየበት እንዲሁም ከሸማችነት ወደ አምራችነት የተደረገ የሀገራዊ ርዕይ ስኬት ማሳያ” ሲሉ የተገኘውን ተጨባጭ ውጤት አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክታቸው የአምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የማምረት አቅም ከነበረበት 47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑን፤ ባለፉት አራት ዓመታት ከ2 ሺህ 800 በላይ አዳዲስ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ እንደተቻለ ጠቅሰዋል። በበጀት ዓመቱ በሀገር ውስጥ ተኪ ምርቶች አማካኝነት ስድስት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል። ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበው የፋይናንስ አቅርቦትም ከ8 ነጥብ 1 ቢሊዮን ወደ 50 ቢሊዮን ብር አድጓል።

በንቅናቄው የፋብሪካዎች መስፋፋት እና የተግባር እመርታ በግልጽ የታየ ሲሆን የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ዓለም አቀፍ ጥራትን የሚያሟሉ የሴራሚክ ምርቶችን የሚያመርተው የዚህ ፋብሪካ ወደሥራ መግባት የንቅናቄው ትልቅ ማሳያ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፋብሪካው ለምርቱ የሚሆነውን ከ80 በመቶ በላይ ጥሬ ዕቃ ከሀገር ውስጥ የሚጠቀም መሆኑን አውስተዋል። ሌላው ማሳያ የሁዋጂያን ፓርክ ቴክኖሎጂ ነው፤ በፓርኩ ውስጥ “ጎበዝ” (Gobez) የተሰኘው የሶላር ሴል ማምረቻ ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት ሁለት ጊጋ ዋት እያመረተ እንደሚገኝና በቬትናም የታየው ቴክኖሎጂ በሀገር ውስጥ መተግበሩን አብስረዋል።

ዘርፉን ለማሻገር ያስችላል ያሉትን ቀጣይ



78

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

አቅጣጫ ያስቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መላው አምራቾች፣ ስታርትአፖች እና ባለሀብቶች በጋራ በመሆን ይህንን ጠንካራ መነቃቃት በማስቀጠል ለሚመጣው ትውልድ በኢንዱስትሪ የበለጸገች እና ራሷን የቻለች ጠንካራ ሀገር እንዲገነቡ ጥሪ ሲያስተላልፉ፤ የጀመርናቸውን ሥራዎች “ነክሶ መጨረስ” እና ክፍተቶችን እያዩ መሙላት ከተቻለ በሚቀጥሉት 5 እና 10 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ራሷን በራሷ የመቻል ዕድሏ ሰፊ መሆኑን ጠቁመዋል።

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ብሔራዊ ንቅናቄ አስተባባሪና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ንቅናቄው በሀገሪቷ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መስኮች ላይ የፈጠረው ታሪካዊ ስኬትና መዋቅራዊ ሽግግር በተጨባጭ የሚታይ መሆኑን ደጋግመው አስገንዝበዋል፡ ፡ ንቅናቄው ከመጀመሩ በፊት የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች በብዙ ፈተናዎች ተከበው እንደነበር በመጠቆም የፋብሪካዎች የማምረት አቅም ዝቅተኛነት፣ የኃይል አቅርቦት፣ የፋይናንስ እና የመሠረተ ልማት እጥረትን በዋናነት አስታውሰዋል። ንቅናቄው እነዚህን ለዓመታት የዘለቁ ማነቆዎች “ደረጃ በደረጃ በመስበር” የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ነጻ ማውጣት እንደቻለም አረጋግጠዋል። መንግሥት፣ የግሉ ዘርፍና የፋይናንስ ተቋማት በጋራ በመቆማቸው የአምራቾች አማካይ የማምረት አቅም ፈጣንና የሚጨበጥ ዕድገት ማስመዘግብ መቻሉን ለስኬቱ ማሳያነት አስቀምጠዋል።

ምርት ማለት ኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የሀገር ነጻነትና ሉዓላዊነት ጭምር መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ አንድ ሀገር ሙሉ ሉዓላዊነቷ የሚረጋገጠው ራሷን በምርት ስትችል መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው “ኢትዮጵያ ታምርት” ለዚህ ትልቅ ማረጋገጫ እንደሆነና ቀደም ሲል ከውጭ በከፍተኛ ወጪ ይገቡ የነበሩ በርካታ ምርቶች ዛሬ በሀገር ውስጥ



79

መመረት መጀመራቸውን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ትልቁ ስኬት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን በሀገር ውስጥ ተኪ ምርቶች ማዳን መቻሉ ነው። ይህም ኢትዮጵያ ለውጭ ምርቶች የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በመቀነስ በራሷ እንድትቆም አድርጓታል። ከዚህ በተጨማሪም መንግሥት የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለመደገፍ “ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ቅድሚያ ሰጥተው የሀገር ውስጥ ምርቶችን እንዲገዙ” መመሪያ ማስተላለፉንና ይህም ለአምራቾች የማይናወጥና አስተማማኝ የገበያ ትስስር መፍጠሩን ያስረዳሉ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን “በሀገር ውስጥ ምርት የመኩራት ባህልን ማሳደግ አለብን” በሚል ጽኑ እምነት፤ ንቅናቄው ያስመዘገበው ውጤት የማይቀለበስ የብልጽግና መሠረት መጣሉንና ይህም ለቀጣዩ ትውልድ በኢንዱስትሪ የበለጸገች ጠንካራ ሀገር ለማስረከብ ዋስትና መሆኑን በልበ ሙሉነት ያረጋግጣሉ።

እንደ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስክርነት የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ይበልጥ ውጤታማ ሊሆን የቻለው ክልላዊ መዋቅሮችንም ማካተት በመቻሉ ነው። እያንዳንዱ ክልል እንደየአካባቢው እምቅ ሀብትና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ንቅናቄውን መርቷል። በዚህ ረገድ ሰፊ የመሬትና የግብርና ሀብት ያለው የኦሮሚያ ክልል ንቅናቄውን ከግብርና ማቀነባበር እና ከኮንስትራክሽን ማዕድናት ጋር አስተሳስሮታል። ይህንን ተከትሎ በሰበታ፣ በገላን፣ በዱከምና በቢሾፍቱ የኢንዱስትሪ ኮሪደሮች ውስጥ ተዘግተው የነበሩ ከ200 በላይ ፋብሪካዎች ዳግም እንዲያንሰራሩ ተደርጓል። በተለይም በምግብና መጠጥ፣ በሲሚንቶና በብረታብረት ዘርፎች ከፍተኛ የምርት ዕድገት ተመዝግቧል። የክልሉ መንግሥትም ለአምራቾች የመስሪያ ቦታና የቴክኒክ ድጋፍ አቅርቧል።

በተመሳሳይ በአማራ ክልልም ንቅናቄው በዋናነት በጨርቃጨርቅ፣ በምግብ ዘይትና በቆዳ ምርቶች ላይ በማተኮር አካባቢያዊ ተፈጻሚነትን አግኝቷል። ንቅናቄውን መሠረት በማድረግ በኮምቦልቻ፣ በባህር ዳርና በጎንደር የኢንዱስትሪ ማዕከላት ውስጥ ሰፋፊ የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖዎች ተካሂደዋል። በደብረ ማርቆስና በባህር ዳር ግዙፍ የዘይት ፋብሪካዎች ሥራ እንዲጀምሩ ተደርጓል። በተጨማሪም በጸጥታ ችግር ምክንያት ተጎድተው የነበሩ በርካታ ፋብሪካዎች በልዩ ሁኔታ ተለይተው የፋይናንስና የዕዳ ሽግሽግ ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ሥራ ተመልሰዋል።

የሲዳማ ክልል በበኩሉ የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና-ኢንዱስትሪ ፓርክን መሠረት በማድረግ አስደናቂ አፈጻጸም አሳይቷል። በአቮካዶ ዘይት ማቀነባበር፣ በወተት ምርቶችና በቡና እሴት መጨመር ላይ ያተኮሩ በርካታ ፋብሪካዎች በንቅናቄው ተደግፈዋል። ክልሉ የሀገር ውስጥ ምርትን ለዓለም ገበያ በጥራት በማቅረብና የአርሶ አደሩን ምርት በቀጥታ ከፋብሪካዎች ጋር በማስተሳሰር ረገድ ቀዳሚ መሆን ችሏል።

የደቡብ ኢትዮጵያ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሎችም በቅመማ ቅመም፣ በቤት ዕቃዎች ማምረትና በአነስተኛ ብረታብረት ሥራዎች ላይ አተኩረው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ። በእነዚህ አካባቢዎች የወጣቶችና የሴቶች አምራች ማኅበራትን በማደራጀት፤ የሼዶችና የአነስተኛ ማሽነሪዎች አቅርቦት ተመቻችቷል። ይህም እንደ እንሰት እና የቀርከሃ ሀብት ያሉ የአካባቢውን የጥሬ ዕቃ አቅሞች ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት የመጠቀም ልምድ እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ የሀገር ውስጥ ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ስኬት እያስመዘገበ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና መተግበር መጀመሩ



80

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ለሀገሪቷ የማይተካ ሰፊ የገበያ ዕድል ፈጥሯል። ኢትዮጵያ በቅርቡ ከ24 በላይ ለሚሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ምርቶቿን ከቀረጥ ነፃ መላክ መጀመሯ፣ በሀገር ውስጥ የተመረቱ ምርቶች በቀጥታ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ ወዳለው ግዙፍ የአህጉሪቱ ገበያ እንዲገቡ በር ከፍቷል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል፤ “የኢትዮጵያ ታምርት” ብሔራዊ ንቅናቄ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ የነበሩ መዋቅራዊና የፖሊሲ ማነቆዎችን በመስበር፣ አገራዊ የምርት አቅምን ያሳደገ ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበበት ስኬት መሆኑን በተለያዩ አገራዊ መድረኮች ላይ ገልጸዋል። ንቅናቄው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ዋነኛ መሣሪያ ማድረጉንም ጠቁመዋል። በዚህም የአምራች ዘርፉን የማምረት አቅም በማነቃቃት፣ ተዘግተው የነበሩ በርካታ ፋብሪካዎች ዳግም ተከፍተው ወደ ምርት እንዲገቡ ማስቻሉን አውስተዋል።

በአጠቃላይ በማምረቻው ዘርፍ የነበሩ በርካታ ተግዳሮቶችን መፍታት በመቻሉ፤ ቀደም ሲል 46 በመቶ የነበረው የሀገሪቷ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም ወደ 66 ነጥብ 3 በመቶ አድጓል። በተለያዩ ምክንያቶች ምርት አቁመው የነበሩ 900 የሚሆኑ ኢንዱስትሪዎችኝም በንቅናቄው አማካኝነት ችግሮቻቸው ተቃሎላቸው ወደ ሙሉ ማምረት ሥራ እንዲመለሱ ተደርጓል።

የገቢ ምርቶችን በመተካት የውጭ ምንዛሬ ጥገኝነትን መቀነስ በመቻሉ በአንድ ዓመት ውስጥ ከውጭ ይገቡ ለነበሩ ምርቶች ይወጣ የነበረን 5 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን፤ በተለይም የሕክምና መገልገያዎችንና መድኃኒቶችን ጨምሮ በሀገር ውስጥ ምርት አጠቃቀም ላይ ተጨባጭ እና ስር ነቀል የባሕርይ ለውጥ መምጣቱን ነው ያብራሩት።

ከፋይናንስ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል የነበረውን ከፍተኛ ፍላጎትና የተደራሽነት ክፍተት መሙላት በመቻሉ፤ በአጠቃላይ ከባንክ ከሚሰጠው ብድር ውስጥ ለማኑፋክቸሪንግ የሚሰጠው ድርሻ ከ12 በመቶ ወደ 18 ነጥብ 8 በመቶ አድጓል። የዘርፉ ዓመታዊ ዕድገት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር፣ የምርት መጠንን 195 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መረጃዎች ያሳያሉ።

ንቅናቄው ከፍተኛ የሆነ የገበያ ትስስርና የኤክስፖርት አቅም ለመፍጠር ማስቻሉ የሚታይ ሀቅ ሲሆን፤ በተለያዩ ጊዜያት በተዘጋጁት የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖዎች ላይ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎችና ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል፣ በቢሊዮን ብር የሚቆጠር የገበያ ትስስርም ተፈጥሯል። አቶ መላኩ፤ ስኬቱን አስመልክተው “በንቅናቄው የተገኘው ውጤት ኢትዮጵያን በአምራች ኢንዱስትሪ የበለጸገችና ራሷን የቻለች ሀገር የማድረግ ህልማችን ሩቅ እንዳልሆነ ያመላከተ ነው” ሲሉ ገልጸውታል።

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ብሔራዊ ንቅናቄ እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ውህደት፤ ለኢትዮጵያ ማክሮ-ኢኮኖሚ እና ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እጅግ ከፍተኛና ስትራቴጂካዊ ፋይዳ ያለው ነው። “ኢትዮጵያ ታምርት” የሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን ለማሳደግና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚሠሩ ሥራዎችን የሚያጠናክር ሲሆን፤ የአፍሪካ ነጻ ገበያ ደግሞ እነዚህ ምርቶች ያለ ቀረጥና ገደብ የሚሸጡበትን የ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ህዝብ ሰፊ ገበያ ይከፍታል።

የሁለቱ መስተጋብር የአምራች ዘርፉን የገበያ መዳረሻ ከአካባቢ ወደ አህጉራዊ ደረጃ በማሳደግ ተጠቃሚነታቸውን በእጅጉ ያሳድገዋል። “ኢትዮጵያ ታምርት” ቀደም ሲል ትኩረቱን የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ማሟላትና ገቢ ምርቶችን መተካት ላይ አድርጎ የቆየ ሲሆን፤ የአፍሪካ ነጻ ገበያ ደግሞ የሀገር ውስጥ አምራቾች ምርቶቻቸውን ለጠቅላላው አህጉር ገበያ እንዲያቀርቡ ዕድል ይሰጣል። የነጻ ገበያ ዕድሉ ሰፊ የገበያ መዳረሻ የሚፈጥር በመሆኑ የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች በከፍተኛ መጠን (Mass Production) እንዲያመርቱ ያበረታታል። ይህ ደግሞ የአንድ ምርት የማምረቻ ወጪን (Unit Cost) በመቀነስ፣ ምርቶች በዋጋ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል።

ንቅናቄው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) መሳቢያ አንዱ ማግኔት መሆኑ ታምኖበታል። ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት የሚያደርጉት ለኢትዮጵያ ገበያ ብቻ ሳይሆን፣ ምርታቸውን ወደ መላው አፍሪካ ለመላክ ጭምር ይሆናል። “ኢትዮጵያ ታምርት” ለኢንቨስተሮች የሚፈጠሩ የፖሊሲና የመሰረተ ልማት ማነቆዎችን ስለሚቀርፍ፤



81

ኢትዮጵያ የአህጉሪቱ ዋነኛ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል (Manufacturing Hub) እንድትሆን ያግዛል። የውጭ ኢንቨስትመንት ከሀገር ውስጥ አምራቾች ጋር በሚፈጥረው የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር፤ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ይበልጥ ይዘምናል፣ ጥራቱ የተጠበቀ ምርት ማምረትም ይቻላል።

ኢትዮጵያ ለዓመታት በቡና፣ በቅባት እህሎችና በባህላዊ የግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ (ኤክስፖርት) ላይ ጥገና ሆና የቆየች ብትሆንም “ኢትዮጵያ ታምርት” በጨርቃጨርቅ፣ በቆዳ፣ በምግብና መጠጥ እንዲሁም በኬሚካል ኢንዱስትሪዎች ላይ ያሳደረው መነቃቃት ምርቶች በአፍሪካ ነጻ ገበያ አማካኝነት ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በቀላሉ እንዲላኩ መንገድ ከፍቷል። በአህጉሪቱ ውስጥ የሚኖረው የንግድ ልውውጥም የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በዘላቂነት ለመቅረፍ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።

“ኢትዮጵያ ታምርት” ሙሉ በሙሉ ውጤታማ ለመሆን አንዳንድ የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃዎችን ከውጭ ማስገባት ሊኖርባት ይችላል። በአፍሪካ ነጻ ገበያ ሕግ መሠረት፤ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚመጡ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችንና ጥሬ ዕቃዎችን ያለ ቀረጥ በማስገባት፣ በሀገር ውስጥ መልሶ በማቀነባበር ለውጭ ገበያ ማቅረብ ይቻላል። ይህም የሀገር ውስጥ አምራቾች የምርቶቻቸውን ጥራት፣ ማሸጊያ (Packaging) እና ደረጃ ዓለም አቀፍ መመዘኛውን የጠበቀ በማድረግ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ለመወዳደር እንዲተጉ ያስገድዳቸዋል።

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ እና የአፍሪካ ነጻ ገበያ (AfCFTA) ስትራቴጂካዊ ትስስርን ለማጠናከርና ከዘርፉ በሚገባው ልክ ተጠቃሚ ለመሆን በሎጂስቲክስና ወደብ አጠቃቀም ዙሪያ በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው።መንግሥት ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግና አገሪቷን የአፍሪካ የማምረቻ ዘርፍ መዳረሻ ለማድረግ የሎጂስቲክስ እና የወደብ አጠቃቀም ፖሊሲ እና ማሻሻያዎች በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ምርት ማምረት ብቻውን በቂ አለመሆኑን በሚገባ የተረዳው የኢትዮጵያ መንግሥት፤ ምርቶቹን በፍጥነትና በአነስተኛ ወጪ ለገበያ ለማቅረብ አበክሮ እየሠራ ይገኛል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነጻ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን በማሰብ የሎጂስቲክስ ዘርፉን ለማሳደግ የሚከተሉትን ስር ነቀል የፖሊሲ ለውጦች እያደረገች ነው፡፡ መንግሥት የሎጂስቲክስ ዘርፉን ለውጭ ባለቤትነት ሙሉ በሙሉ ክፍት አድርጓል (ቀደም ሲል የነበረውን የ49 በመቶ ገደብ በማንሳት)። ይህ ሪፎርም ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂና ካፒታል ይዘው እንዲገቡ ስለሚያደርግ በንቅናቄው ታግዘው የሚመረቱ ምርቶች በፍጥነትና በአስተማማኝ ሁኔታ ወደ አፍሪካ ገበያ እንዲጓጓዙ ይረዳል። የኢትዮጵያ-ጅቡቲ የምድር ባቡር በቀጥታ ከዶራሌ ሁለንተናዊ ወደብ (Doraleh Port) እና ከነዳጅ ተርሚናሎች ጋር እንዲገናኝ አዲስ ስምምነት ተደርጓል። ይህ የባቡር ትስስር የጭነት ተሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ የሚያጠፉትን ሦስት ቀናት ወደ 12 ሠዓታት የሚያሳጥር በመሆኑ የሎጂስቲክስ ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ያገዛል።



82

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነጻ ገበያ ስር የመጀመሪያ ደረጃ የወጪ ንግድ ሥራዎቿን (በተለይም ስጋ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን) ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ አፍሪካ በዋናነት በአየር ትራንስፖርትና በየብስ በኩል መላክ ጀምራለች። የአየር መንገዱ ሰፊ የአፍሪካ የበረራ መረብ ለንቅናቄው እንደ ትልቅ የጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለግላል። ኢትዮጵያ 90 በመቶ የሚሆኑትን የምርት አይነቶች በ10 ዓመታት ውስጥ (እስከ 2030) ሙሉ በሙሉ ከቀረጥ ነጻ (Duty-free) ለማድረግ የታሪፍ ቅናሽ ደንብ አውጥታ እየተገበረች ነው። ይህም የሀገር ውስጥ አምራቾች ግብዓቶችን ያለ ቀረጥ ከአፍሪካ አስገብተው እንዲያመርቱና ምርታቸውንም ያለ ቀረጥ እንዲልኩ ህጋዊ መንገድ ከፍቷል።

“ኢትዮጵያ ታምርት” እና ነፃ ገበያ

ሥራ አቁመው የነበሩ 900 የሚጠጉ ግዙፍ ፋብሪካዎች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አማካኝነት ወደ ማምረት የተመለሱ ሲሆን፣ ከ26 ሺህ በላይ አነስተኛና መካከለኛ አምራቾች ወደ ሥራ ገብተዋል። ይህ መነቃቃት ለውጭ ገበያ የሚተርፍ ምርት በብዛት ለማምረት መሠረት ሆኗል። ንቅናቄው በፈጠረው ዕድል ተጠቃሚ የሆኑ የሀገር ውስጥ አምራቾች በኢትዮጵያ ምርት ገበያ እና በሌሎች የጥራት መቆጣጠሪያ መስፈርቶች ታግዘው ተወዳዳሪ ምርት ማቅረብ ጀምረዋል። ንቅናቄው የሀገር ውስጥ ምርት የገበያ ድርሻን ወደ 45 በመቶ በማሳደግ ቀደም ሲል ለገቢ ምርቶች ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ማዳን አስችሏል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ ገበያ የሚፈጥራቸውን ዋና ዋና ዕድሎች በአግባቡ መጠቀም የሚያስችል ብሔራዊ የማስፈጸሚያ ስትራቴጂ አጽድቃ ወደ ተግባር መግባቷ በርካታ ጠቃሚ ዕድሎች አስገኝቷል፡፡ በእነዚህ ዕድሎች በመጠቀም ኢትዮጵያ ስጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ባቄላ፣ በቆሎ እና ቡና የመሳሰሉ የግብርና እና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ አፍሪካ ከቀረጥ ነፃ መላክ ጀምራለች። በስምምነቱ መሰረት እስከ 90 በመቶ የሚደርሱ የንግድ ታሪፎች ወይም ቀረጦች በሂደት የሚነሱ በመሆናቸው፣ የኢትዮጵያ ምርቶች በአፍሪካ ገበያ በቀላሉ ተወዳዳሪ መሆን ይችላሉ።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ሲተገበር በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እየጎለበቱ የመጡት የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ምርቶች ወጪ ንግድ በከፍተኛ መጠን ያድጋል። የውጭ አምራቾች ኢትዮጵያ ውስጥ ፋብሪካ በማቋቋም ምርቶቻቸውን ወደ መላው አፍሪካ ያለ ቀረጥ መላክ ስለሚችሉ ሀገሪቷ ያሏትን የኢንዱስትሪ ፓርኮች በከፍተኛ ሁኔታ ለመጠቀም ትልቅ አጋጣሚ ይፈጥራል። የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ የሀገር ውስጥ አምራቾችን አቅም ሲያጠናክር፣ የአፍሪካ ነፃ ገበያ ደግሞ ኢንዱስትሪዎቹ ያመረቱትን ምርት በስፋት ተደራሽ የሚያደርጉበትን ሰፊ የገበያ ዕድል አመቻችቷል። ንቅናቄው በር የከፈተላቸው አምራቾች የተፈጠረላቸውን ሰፊ ዕድል ተጠቅመው ምርታቸውን በጥራትና በብዛት በማቅረብ ያልተነካውን የአፍሪካ የገበያ ዕድል በአግባቡ መጠቀም ቀጣይ ሥራቸው ሊሆን ይገባል።

እንደ አገር ሥራ ላይ የዋለው የአምራች ኢንዱስትሪ ሪፎርም የሀገር ውስጥ አምራቾችን አቅም በማሳደግ እና ተኪ ምርቶችን በማስፋፋት ረገድ ተጨባጭና ተስፋ ሰጪ ለውጦችን አምጥቷል። አሁን የሚታየውን የጥሬ ዕቃ ዋጋ ንረት በዘላቂነት ለመቋቋም፣ የሀገር ውስጥ የግብርና እና የኮንስትራክሽን ምርቶች በቀጥታ ለፋብሪካዎች የሚቀርቡበትን የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ሰንሰለት ይበልጥ ማጠናከርና ለአገር ውስጥ አምራቾች የሚሰጠውን የቴክኖሎጂ እንዲሁም የዕውቀት ሽግግር ድጋፍ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።

የዘርፉ ባለሙያዎች፤ የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ዘላቂነት እንዲኖረውና አገሪቷን ወደ ሙሉ የኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለማሸጋገር የሚከተሉት ስልታዊ የፖሊሲ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው ይላሉ። በዋናነት ለአምራች ዘርፉ ዝቅተኛ ወለድ ያላቸውና የረጅም ጊዜ መክፈያ ጊዜ ያላቸው ብድሮችን ማመቻቸት፣ የማኑፋክቸሪንግ ልማት ባንክ ማቋቋም፣ ለጥሬ ዕቃና ለማሽነሪ መለዋወጫዎች የሚሆን የውጭ ምንዛሬ ቅድሚያ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች



83

የሚሰጥበት ወጥ መመሪያ መተግበር፣ ፋብሪካዎች በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት የሚያጡትን የምርት ጊዜ ለመቀነስ ለኢንዱስትሪ ቀጠናዎች የተለየና የማይቆራረጥ የኃይል መስመር መዘርጋት እንዲሁም ዲጂታል የገበያ መድረክን እስከ ወረዳና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ድረስ በማውረድ የአቅርቦት ሰንሰለቱን ማሳለጥ ያስፈልጋል።

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት የአገሪቷን የኢኮኖሚ ገጽታ ሙሉ በሙሉ የመቀየር እምቅ አቅም እንዳለው ማረጋገጥ ተችሏል። በጥናት ላይ የተመሠረቱ የወደፊት ትንበያዎች እንደሚያሳዩት በቀጣይ የሀገር ውስጥ ምርቶች የገበያ ድርሻ አሁን ካለበት ከ45 በመቶ ድርሻ በ2030 ዓ.ም ወደ 65 በመቶ ያድጋል ። የምግብ ዘይት፣ ስንዴና መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ ሙሉ በሙሉ በመተካት ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ምክንያት የሚፈጠረውን የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይቻላል።

በአሁኑ ወቅት የአምራች ኢንዱስትሪው ለአጠቃላይ አገራዊ ምርት (GDP) ያለው አስተዋጽኦ ከ11 በመቶ በታች ሲሆን በዕቅዱ ማጠቃለያ ላይ ይህንን ድርሻ ወደ 17 ነጥብ 2 በመቶ ማሳደግ ዋነኛው መዋቅራዊ ግብ ነው። በዚህም የተያዘው የ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ግብ እንደሚሳካ ይታሰባል። ንቅናቄው በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ብቻ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ለተጨማሪ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅም አለው።

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ ያመጣቸውን ተጨባጭ ስኬቶች እና መሬት ላይ ያሉ መዋቅራዊ ፈተናዎችን በተመለከተ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ታዋቂ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማት ሰፊና ጥልቅ ትንታኔዎችን እየሰጡ ይገኛሉ።

የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ንቅናቄው በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳያቸውን ተጨባጭ ውጤቶች በአዎንታ ከሚያነሱት ተጠቃሽ ምሁራን አንዱ ናቸው። አቶ ዘመዴነህ እንደሚሉት ንቅናቄው ከመጀመሩ በፊት በተለያዩ የኢኮኖሚ ቀውሶች፣ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ተዘግተው የነበሩ ከ900 በላይ ትልልቅና መካከለኛ ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ምርት ማምጣት መቻሉ የሀገሪቷን የኢኮኖሚ ደም ስር ያነቃቃ ትልቅ ስኬት ነው። ከዚህም በላይ ቀደም ሲል ከ46 በመቶ በታች ወርዶ የነበረው የኢንዱስትሪዎች አጠቃላይ የማምረት አቅም (Capacity Utilization) በአሁኑ ወቅት ከ67 በመቶ በላይ ከፍ እንዲል መደረጉ፣ መንግሥት የዘርፉን ችግሮች በቅርብ ተከታትሎ ለመፍታት ያሳየው የፖለቲካ ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለው ያምናሉ። ይህ የሀገር ውስጥ ምርት መነቃቃት በተለይ ምግብና መጠጥ፣ ጨርቃጨርቅ እና ሌጦን የመሰሉ ምርቶች ላይ የገቢ ምርትን ለመተካት (Import Substitution) በማስቻሉ፣ ለውጭ ምርቶች ይወጣ የነበረውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ማዳን መቻሉን እና ይህም ለሀገሪቱ የክፍያ ሚዛን መረጋጋት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ያስረዳሉ።

ይህንን አዎንታዊ ስኬት በተመለከተ የውጭ ሀገር የምጣኔ ሀብት ምሁራን እና ዓለም አቀፍ ተቋማትም ምስክርነታቸውን እየሰጡ ነው። የዓለም ባንክ (World Bank) የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ባወጡት ጥናት፤ የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ የሀገሪቷን ኢኮኖሚ ከመንግሥት መሪነት ወደ ግሉ ዘርፍ መሪነት (Private Sector-Led Growth) ለማሸጋገር ለተያዘው ግብ ትልቅ አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል። የባንኩ ምሁራን እንደሚጠቁሙት ንቅናቄው የአነስተኛና መካከለኛ አምራቾችን ቁጥር ከ8 ሺህ ወደ 26 ሺህ በማሳደግ ረገድ ያሳየው ስኬት ለሴቶችና ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል የፈጠረና የሀገር ውስጥ ምርታማነትን ያሳደገ ነው። በተመሳሳይ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች በቅርብ ባወጡት ሪፖርት፤ በኢትዮጵያ የታየው ጠንካራ የወጪ ንግድ (Export) አፈፃፀም ንቅናቄው ካስገኛቸው ውጤቶችና የኢንዱስትሪ ማሻሻያዎች ጋር የተያያዘ መሆኑን አምነዋል። የውጭ ባለሙያዎቹ እንደሚገልጹት የሀገር ውስጥ ምርትን ማሳደግ መቻሉ ኢትዮጵያ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ረገድ ተጨባጭ መሻሻል እያሳየች መሆኑን ያረጋግጣል።

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ወደ ቋሚ የኢኮኖሚ መዋቅር እንዲቀየር የሀገር ውስጥና የውጭ ምሁራን ወሳኝ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ይጠቁማሉ። በዚህም ፋብሪካዎች ጥሬ ዕቃ ከውጭ ከማስገባት ወጥተው የሀገር ውስጥ ግብርና እና ማዕድንን በጥሬ ዕቃነት የሚጠቀሙበት የኋሊት ትስስር (Backward Integration) መፈጠር እንዳለበት ምሁራኑ በአንድነት ይመክራሉ። ለምሣሌ የሀገር ውስጥ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ከጥጥ አምራቾች ጋር፣ የምግብ ማቀነባበሪያዎች ደግሞ ከሀገር ውስጥ አርሶ አደሮች ጋር ቀጥተኛና አስተማማኝ ትስስር መፍጠር ይኖርባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ መንግሥት ለአነስተኛና መካከለኛ አምራቾች የሚሰጠውን የፋይናንስና የብድር አቅርቦት ማቅለል፣ አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታን ማስፈን፣ እንዲሁም የመሠረተ-ልማት (የኤሌክትሪክ ኃይል) አቅርቦትን ማረጋጋት ከተቻለ ንቅናቄው ወደ ተሟላና ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ሊሸጋገር እንደሚችል ምሁራኑ በስፋት ይስማማሉ።

ማጠቃለያ

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ መፈክር ሳይሆን የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ታሪክ የቀየረና የአምራችነት ባህልን የገነባ ብሔራዊ ንቅናቄ ነው። ከትናንት የፋብሪካዎች መዘጋትና የውጭ ጥገኝነት ተነሥቶ፣ ዛሬ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን ወደ መፍጠርና የቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬን ወደ ማዳን የተሻገረ ነው። ክልሎች ያሳዩት ተነሳሽነትና የታዋቂ ባለሀብቶች ተሞክሮ እንደሚያሳየው ሀገሪቷ ያላትን እምቅ ሀብት በትክክል ከተጠቀመች የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነቷን ማረጋገጥ ትችላለች። የተገለጹትን የፖሊሲ ማሻሻያዎች በተግባር በመተርጎም ንቅናቄው ኢትዮጵያን የአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል የማድረግ ራዕይን በቅርብ ዓመታት ውስጥ እውን ያደርጋል።

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ብሔራዊ ንቅናቄ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ 900 የሚጠጉ የቆሙ ፋብሪካዎችን በማንቃት፣ የሀገር ውስጥ ምርት የገበያ ድርሻን ወደ 45 በመቶ በማሳደግና ከ5 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ በተኪ ምርት በማዳን፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ተጨባጭና ስር ነቀል የኢኮኖሚ ሽግግር ማስመዝገቡ ተረጋግጧል። በቅርቡ በተካሄደው የ2018 ዓ.ም የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ላይ ብቻ ከ57 ቢሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስርና ስምምነት መደረጉ የንቅናቄውን ውጤታማነት በአደባባይ ያረጋገጠ ነው፡፡

“ኢትዮጵያ ታምርት” አገራዊ ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች በቁጥር (በግራፊክስ ቢሠራ)



84

1. የምርት እና የአቅም ሽግግር ስኬቶች

2. የገቢ ምርቶች ተኪነት እና የውጭ ምንዛሬ ቁጠባ

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም



85

3. የፋይናንስ፣ የመሠረተ ልማት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ



86

ማኅበራዊ

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ

ችግር የወለደው አኩቴክ ዲያግኖስቲክስ



87

አኩቴክ ዲያግኖስቲክስ

በፍቅርተ ባልቻ

የሕክምና ሳይንስ ጉዞ የሰው ልጅ ሕመምን፣ ሥቃይን እና ሞትን ለማሸነፍ ያደረገው ረጅም እና አስደናቂ ትግል ታሪክ ነው። በጥንት ዘመን የሕመም መንስኤዎችን በግምት እና በባህላዊ እምነቶች ለመፈወስ ይደረግ የነበረው ጥረት፣ የላቦራቶሪ ምርመራ ግኝት በመጣ ጊዜ ሙሉ በሙሉ አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ። ጥቂት ጠብታ ደም፣ ትንሽ ፈሳሽ ወይም የሕዋስ ቅንጣት በአጉሊ መነጽር (Mi- croscope) ስር ገብተው የሕመሙን ትክክለኛ ማንነት ቁልጭ አድርገው ማሳየት ሲጀምሩ፣ ሕክምና ከግምት ወደ ተረጋገጠ ሳይንስ ተሸጋገረ። ዛሬ ላይ ደግሞ የላቦራቶሪ ምርመራ ተራ የታካሚ ሕመም መለያ ብቻ ሳይሆን፤ የበሽታዎችን መከሰት አስቀድሞ የሚተነብይ፣ የጂን እና የሴል ደረጃ ምስጢሮችን የሚፈታ እንዲሁም ዘመናዊው የሕክምና ዓለም ያለ እሱ አንድ እርምጃ መራመድ የማይችልበት የሕክምናው እሳቤ አከርካሪ ሆኗል።

በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት መንግሥት የተለያዩ አሠራሮችን በማፍለቅ ሲተገብር ቆይቷል፤ አሁንም በመተግበር ላይ ይገኛል። የአገሪቷ የጤና ፖሊሲ በሽታን አስቀድሞ በመከላከል ላይ ያተኮረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በጤና ኤክስቴንሽን እና በሌሎችም መርኃ ግብሮች አማካኝነት የዜጎችን ጤና የመጠበቅ እና የመከላከል ሥራዎች ላይ በርካታ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው። ይህ አገር አቀፍ እንቅስቃሴ በራሱ እያስገኘ ያለው ውጤት እንዳለ ሆኖ፤ የጤና



88

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

እክል ገጥሟቸው መፍትሄ ፍለጋ በየጤና ተቋማቱ በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ የሚያልፉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም።

በዚህ የሕመምተኞች እንግልት እና እንክብካቤ መሃል ደግሞ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ያሉ የጤና ተቋማት ሚና ጎልቶ ይታያል። በየዕለቱ ከአዲስ አበባም ሆነ ከተለያዩ የአገሪቷ ማዕዘናት መፍትሔ ፍለጋ ወደ ተቋሙ የሚመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወገኖች ለገጠማቸው የጤና እክል ፈጣን እና ትክክለኛ መፍትሔ ለማግኘት በሂደቱ ውስጥ እጅግ አታካች እና በርካታ ፈተናዎች የተሞሉበትን መንገድ ለማለፍ መገደዳቸውን በጥብቅ አስተውሏል።

ትክክለኛ ሕክምና የሚጀምረው ከተረጋገጠ የላቦራቶሪ ውጤት መሆኑን የተረዳው ሜዲካል ኮሌጁ፤ የታካሚዎችን እንግልት የሚታደግ፣ የምርመራ ጥራት እና ፍጥነትን አዲስ ደረጃ ላይ የሚያሸጋግር መፍትሔ አመነጨ። ያንን የታለመውን ታላቅ ሀሳብ እውን ለማድረግ ሌት ከቀን በመትጋት ለተግባራዊነቱ ሲሠራ ቆይቷል፤ ያለመውንም አሳክቷል!

ነገሩ እንዲህ ነው፤ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እያከናወነች ያለው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ ቢሆንም፣ በውስጡ ግን ገና ያልተፈቱ እውነታዎች ነበሩ። ለምሣሌ እንደ የጉበት በሽታዎች (Hepatitis B & C) ያሉ ሕመሞች መነሻ መለያ ምርመራዎች በአገር ውስጥ ቢካሄድም፣ የበሽታውን ስርጭትና የሕክምናውን ውጤታማነት ለማወቅ በአንድ ሚሊ ሊትር ደም ውስጥ የሚገኘውን የቫይረስ መጠን ለመለካት የሚደረጉት የቫይራል ሎድ (Viral Load) ምርመራዎች ወደ ውጭ አገራት ለመላክ ይገደዱ ነበር።

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሰው ልጅ ሕይወት የሚታደግ የኩላሊት ንቅለ ተከላ (Kidney Transplant) በስኬት ይከናወናል፤ ነገር ግን ለተከላው ስኬት ወሳኝ የሆነው እና የቲሹ ተስማሚነትን የሚያረጋግጠው የላቦራቶሪ ምርመራ ወደ ውጭ ሀገር ከመላክ አይድንም። ይባስ ብሎ፣ የሰዎችን ሕይወት እና ማኅበራዊ ህልውና የሚወስኑት የአባትነት እና የእናትነት (Paternity Test) የዲ.ኤን.ኤ (DNA) ምርመራዎች እንኳ በተመሳሳይ መልኩ የባህር ማዶ ጉዞ ይጠብቃቸዋል። በዚህ መልኩ በየዕለቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያዊያን የደም፣ የቲሹ እና የፈሳሽ ናሙናዎች ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት ለምርመራ ይሰደዳሉ። ይህ የናሙናዎች ስደት ደግሞ በቀላሉ የሚታይ ሳይሆን በታካሚው፣ በቤተሰብ፣ በሕክምና ባለሙያው እና በአጠቃላይ በሀገር ላይ የሚያሳድረው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ የከፋ ነበር።

በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የሜዲካል ማይክሮባዮሎጂ ባለሙያ ብርሃነመስቀል ተገኔ ይህንን አስከፊ እውነታ ሲገልጹ፤ “እየወጣ ያለው አገራዊ ሀብት የሆነው ዶላር ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተገልጋዩ እጅግ አጣዳፊ እና ለሕይወቱ ስጋት በሆነ ሕመም ውስጥ ሆኖ የምርመራ ውጤቱን ለማግኘት ሦስት ሳምንታትን ሙሉ በጭንቀት ይቆጥራል” ነበር ያሉት።

ይህ ዕለት በዕለት የሚደጋገም የዜጎች እንግልትና የሀገር ሀብት ብክነት የተቋሙን አመራሮች እና ባለሙያዎች እንቅልፍ ነሳቸው። ይህንን ብሔራዊ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እና የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅን ሙሉ በሙሉ የሚቀይር አዲስ ሀሳብ እና አሠራር ለማፍለቅ ተገደደ።

አዲሱ ምዕራፍ

ሀገራት ለዜጎቻቸው የሚያቀርቡት የጤና አገልግሎት አቅምና ስፋት በብዙ መልኩ የሚወሰነው በዘርፉ ላይ በሚደረገው አጠቃላይ የኢንቨስትመንት መጠን ነው። እንደ አሜሪካ እና ሌሎችም የበለፀጉ ሀገራት ለጤና የሚመደበው ሀብት ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል፤ ከኢትዮጵያ በአንፃራዊነት በአፍሪካ እንደ ጉረቤት ኬንያ ባሉ ሀገራት ለጤና ዘርፉ የሚመደበው ሀብት ከፍተኛ በመሆኑ፣ የዜጎቻቸው የሕክምና ተደራሽነት እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ በዚያው ልክ የበለፀገ ሆኖ እናገኘዋለን። በኢትዮጵያ ምንም እንኳ በጤናው ዘርፍ የሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ቢሆንም ከሕዝብ ቁጥር ዕድገት እና ከዘመናዊ ሕክምና ውድነት አንጻር ለእያንዳንዱ ዜጋ የሚደርሰው የሕክምና አገልግሎት ሽፋን ገና ብዙ የሚቀረውና ሰፊ ክፍተት የሚስተዋልበት ነው።



89

ይህንን የተደራሽነት እና የጥራት ክፍተት በባህላዊ የሕክምና አሠራር ብቻ መሙላት እንደማይቻል የተረዱት የበለፀጉ ሀገራት ትልቅ ስኬት ያስመዘገቡበትን መንገድ በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ መካከል የሚደረግ ስልታዊ ቅንጅትና ትብብር (Public-Private Partner- ship - PPP) ነው። ይህ አሠራር መንግሥት ብቻውን ሊሸከመው የማይችለውን ግዙፍ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ጫና ከግሉ ዘርፍ ጋር በመጋራት፣ የጤና አገልግሎትን በጥራት፣ በፍጥነትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለዜጎች ለማድረስ ያስቻለ ነው።

ይህንን የሀገራችንን የጤና ፖሊሲ ክፍተት እና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ዕድል መነሻ በማድረግ፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ አዲስ ሀሳብ ተወጠነ፤ እሱም “ሚሊኒየም ሄልዝ ኬር ኢንተርፕራይዝ”ን የማቋቋም ታላቅ ዕቅድ ነበር።

ረዳት ፕሮፌሰር ብርሃነመስቀል ተገኔ እና የሥራ ባልደረቦቻቸው በ2014 ዓ.ም ያመነጩት ይህ ሀሳብ በተቋሙ ማኔጅመንት እና ቦርድ ዘንድ ሙሉ ተቀባይነትን አገኘ። የሥራ ኃላፊዎች ባደረጉት እገዛ፣ ጥብቅ ክትትል እና ድጋፍ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሀሳቡ ወደ መሬት ወረደ። በአዋጅ ቁጥር 1152/2011 እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 456/2011 በተሰጠው የሕግ ማዕቀፍ መሠረት ኢንተርፕራይዙ ህጋዊ ህልውናን ተላበሰ። የዚህ ኢንተርፕራይዝ ዋና ዓላማ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ማስፋት፣ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በተመጣጣኝ ክፍያ ማቅረብ፣ ፈጠራና የትብብር ሥራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለሜዲካል ኮሌጁ ተጨማሪ ገቢ ማመንጨት ነበር።

“ኢንተርፕራይዝ” የሚለው እሳቤ አብዛኛውን ጊዜ ከሌሎች የንግድ እና የሙያ መስኮች ጋር እንጂ በሕክምናው ዘርፍ ከዚህ ቀደም የተሠራበት ባለመሆኑ፣ ሀሳቡን በበርካታ አካላት ዘንድ ለማስረፅ እና ለማሳመን ያደረግነው ጥረት እጅግ ፈታኝና ወሳኙ የማቋቋሚያ ምዕራፍ ነበር” ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰሩ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሳሉ።

በወቅቱ የነበሩትን ተቋማዊ ውጣ ውረዶች ለማለፍ፣ የጤና ኢንተርፕራይዝን ፋይዳ ለከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሳይቀር ለማስረዳት እና ባለድርሻ አካላትን ለማሳመን ረጅም መንገድ ተጓዙ። ይሁን እንጂ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት እንደዚህ ባሉ የንግድ አሠራሮች ተሰማርተው ገቢ ማመንጨት እንደሚችሉ በአዋጅ መደንገጉ የሕግ ከለላና ትልቅ ብርሃን ሆነላቸው።

ይህ ኢንተርፕራይዝ ለመንግሥትም ሆነ ለሕዝብ እጅግ ታላቅ ድል ነው። ለሕዝቡ አጣዳፊ የሕክምና ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ሲሆን፣ መንግሥትንም አላስፈላጊ በጀት ከመጠየቅ ነፃ ያደርጋል፤ በተለይም ለምርመራ ወደ ውጭ ሀገራት ይፈስ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሀብት በማስቀረት ለሀገር ኢኮኖሚ ግዙፍ እፎይታን ይሰጣል። ኢንተርፕራይዙ ኮሌጁን በማገልገል የራሱን ወጪ ከመሸፈን አልፎ፣ ለማኅበረሰቡ ቀደም ሲል በሀገር ውስጥ ያልነበሩ ዘመናዊ የምርመራ አገልግሎቶችን ከግል ተቋማት እና ከባህር ማዶ ክፍያዎች ጋር ሲነፃፀር እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባል። በተጨማሪም በራሱ መተዳደሪያ ደንብ እና በንግድ ህግ መሠረት ለመንግሥት ግብር እየከፈለ የሚጓዝ፣ በቀጣይም ግዙፍ ትርፍ የሚያመነጭ ብሔራዊ ተቋም ሆኖ ተቀርጿል።

ይህን ህግ፣ ደንብ እና ግልጽ የአሠራር ሥርዓት የተዘረጋለት ኢንተርፕራይዝ፣ አገልግሎቱን በተግባር ለማስጀመር አቅም እና ፍላጎት ካለው የግል ድርጅት ጋር የመጣመር (Joint Venture) አማራጭን አቀረበ። በዚሁ መሠረት ከሜዲካል ኮሌጁ ጋር ለረጅም ጊዜ ሲሰራ የቆየው እንደ Roche Diagnostics ያሉ የዓለም አቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ብቸኛ ወኪል የሆነውና በዘርፉ በርካታ ስኬቶችን ያስገኘው ሀገር በቀል ኩባንያ “ሬቲና ፋርማሲዩቲካልስ” የቀረበውን ጥሪ ተቀበለ። ይህ ታሪካዊ የጋራ አጋርነት ከመንግሥት ሙሉ እውቅና እና ይሁንታን አግኝቶ “አኩቴክ ዲያግኖስቲክ ሴንተር” (AC- CU-TECH DIAGNOSTIC CENTER) ተወለደ!

በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ይዞታ ውስጥ የሚገኘው ባለ ሁለት ወለል (G+2) ዘመናዊ የሕንፃ ግንባታ ሙሉ በሙሉ በሬቲና ፋርማሲዩቲካልስ ወጪ ተከናወነ። ይህም ብቻ



90

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

አይደለም በዓይነታቸው ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆኑት የቶታል ላቦራቶሪ ኦቶሜሽን (Total Laboratory Automation - Cobas TLA) ማሽኖች እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ጥራታቸው የተረጋገጠላቸው የምርመራ ቴክኖሎጂዎች በሬቲና ፋርማሲዩቲካልስ ሙሉ የፋይናንስ ወጪ ተገዝተው ተተከሉ። የአኩቴክ ዲያግኖስቲክስ አመራሮች እና ከፍተኛ የሙያ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችም ተመደቡ። ማዕከሉ ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ!

የአኩቴክ ዲያግኖስቲክስ ገፅታ

በአኩቴክ ዲያግኖስቲክስ የቦርድ አባል ሆነው ሥራዎችን የሚያስተባብሩት የላቦራቶሪ ባለሙያ አቶ አሸብር ጉርሜሳ በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን እና ዘመናዊ መሣሪያዎችን እንዲህ ይገልጿቸዋል። በኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ ውስጥ ትልቅ የለውጥ ምዕራፍ የከፈተው የአኩቴክ ዲያግኖስቲክስ ማዕከል (Ac- cu-Tech Diagnostics) በዘመናዊ የላቦራቶሪ ቴክኖሎጂና አውቶሜሽን የታገዘ አህጉራዊ አቅም በመፍጠር የዜጎችን እንግልት ያስቀረ ድንቅ ተቋም ነው። በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ (ሚሊኒየም ሄልዝ ኬር ኢንተርፕራይዝ) እና በሬቲና ፋርማሲዩቲካልስ አጋርነት የተመሰረተው ይህ ማዕከል ከዚህ ቀደም ለሣምንታት በጭንቀት የሚጠበቁና ለከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ ይዳርጉ የነበሩ ውስብስብ ምርመራዎችን በሀገር ውስጥ መፈጸም አስችሏል። ተቋሙ የዘረጋው አሠራር የታካሚዎችን የህክምና ሂደት ከመታደጉም በላይ የላቦራቶሪ አገልግሎትን ጥራት፣ ፍጥነትና ተደራሽነት በሀገራችን ከዚህ ቀደም ከነበረበት ወደ አዲስ ከፍታ ላይ አድርሶታል።

የአኩቴክ ዲያግኖስቲክስ የምርመራ አቅምና የጥራት ደረጃ የሚጀምረው 58 በመቶ የሚሆነውን የላቦራቶሪ ስህተት ሙሉ በሙሉ ከሚያስቀረው ከስህተት የጸዳ የቅድመ- ምርመራ (pre-analytical) አውቶሜሽን ነው። የሰው እጅ ንክኪን ባስቀረ መልኩ ናሙናዎችን በራሱ የሚለያይ፣ የሚከፋፍልና ባርኮድ የሚለጥፍ በመሆኑ በሰው ሰራሽ ስህተት የሚፈጠሩ ግድፈቶችን ከመሠረቱ ያስወግዳል። በተጨማሪም በሰው ሰራሽ አስተውህሎት (AI) የታገዙት የሂማቶሎጂና ኮአጉሌሽን የክሊኒካል ሄሚስተሬ ኤሌክትሮላይት እና የኢሚዩኖአሰይ አናላይዘሮች እንዲሁም የሞለኪውላር ምርመራዎችን መስራት የሚችለው Cobas 6800 በ8 ሠዓት ውስጥ እስከ 11 ሺህ 200 ናሙናዎችን በመቀበል በርካታ ምርመራዎችን ፍጹም ትክክለኛ በሆነ ጥራት የማከናወን አቅም አለው።

ማዕከሉን የልቀት ደረጃ ከፍታ ማሳያ የሚደርገው ደግሞ የጄኖሚክስ (NextSeq 2000 Next-Generation Sequencing) እና የትራንስፕላንት ኢሚዩኖሎጂ ቴክኖሎጂው ነው። ቀደም ሲል የዲ.ኤን.ኤ (DNA Sequenc- ing) የአባትነት እና እናትነት፣ የፅንስ የጄኔቲክ ምርመራዎች እንዲሁም የኩላሊትና የጉበት ንቅለ-ተከላ ተስማሚነትን የሚያረጋግጡ ውስብስብ የላቦራቶሪ ፍላጎቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ውጭ ሀገር ይላኩ የነበሩትን አኩቴክ በራሱ ደጃፍ አስተናግዶ ያስቀረዋል፤ ለዚህም የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎችን ከውጭ ሀገራት በማስመጣት ሒደት ላይ በመሆኑ በጥቂት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ የሚገቡ ይሆናል።

ይህንን የተደራሽነት አድማስ በዲጂታል ፓቶሎጂ እና በሞባይል መተግበሪያዎች በማስደገፍ ሐኪሞች ባሉበት ቦታ ሆነው የታካሚዎቻቸውን ውጤት የሚያገኙበትን ዘመናዊ ትስስር ይፈጥራል።

በአህጉረ አፍሪካ ከሚገኙት ታላላቅ የላቦራቶሪ ማዕከላት ጋር ሲነፃፀር፣ አኩቴክ ትልቁ ሙሉ በሙሉ የተቀናጀ የቶታል ላቦራቶሪ አውቶሜሽን (Cobas TLA) ባለቤት በመሆኑ በግንባር ቀደምትነት ይሰለፋል። በድህረ ምርመራ ክፍሉ (Post analytical unit) በውስጡ ባሉት የሮቦቲክ አርሞች (Robotic Arms) አማካኝነት 27 ሺህ ናሙናዎችን ለ29 ቀናት ጠብቆ የማቆየት፣ በድጋሚ ሲፈለጉ ራሱ ፈልጎ የመመለስ እና ጊዜያቸው ሲያልቅ በራሱ የማስወገድ ጥንቅቅ ያለ የሮቦቲክስ አሠራር የታደለ ነው። ይህ በቴክኖሎጂ ምጥቀት፣ በዲጂታል ዝግጁነትና በጽኑ ተቋማዊ መሠረት የተገነባው ማዕከል፤ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለመሆን የምታደርገውን ጉዞ በተግባር ያረጋገጠ ነው።



91

አሻግሮ የሚመለከት የላቦራቶሪ አብዮት

አኩቴክ ዲያግኖስቲክ ሴንተር (Accu-Tech Di- agnostics) ወደ ውጭ ሀገራት ይላኩ የነበሩ ውስብስብ የምርመራ ዓይነቶችን በሀገር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት በሚያደርገው ታሪካዊ ጉዞ፤ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸውን የመጨረሻ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ አውሏል። የማዕከሉ የገቢ ምንጭ እና የቢዝነስ ሞዴል መንግሥትንም ሆነ የግሉን ዘርፍ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ የማኅበረሰቡን የሕክምና ጥያቄ የመለሰ በመሆኑ እጅግ ልዩና ዓርአያነት ያለው ያደርገዋል። የላቦራቶሪ ባለሙያው አቶ አሸብር እንደሚያስረዱት እንደ አኩቴክ ዓይነት ዘመናዊና ሙሉ በሙሉ በአውቶሜሽን የተገነባ የላቦራቶሪ ማዕከል በአጠቃላይ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ከ1 በመቶ (1%) በታች ብቻ ነው የሚገኘው፡፡

ለሁሉም ዜጎች እኩል፣ ፈጣንና ጥራቱን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት መስጠት እንዲሁም እኩል ተጠቃሚነትን ማስፈን የማዕከሉ ዋና ዋና ዓላማዎች ናቸው። ይህንን አልሞ በመነሳት ተደራሽነትን እውን ለማድረግ ከተለያዩ የሀገሪቷ ክልሎችና ራቅ ካሉ አካባቢዎች ናሙናዎችን በድሮን (Drone) ቴክኖሎጂ ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች ተደርገዋል። የድሮን ቴክኖሎጂን ሕይወትን ለማዳን እንዲውል የማድረጉ አሠራር በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ውጤት ያመጣ መሆኑ ይታወቃል። ለአብነትም በሩዋንዳ በድሮን ቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን የሕክምና አቅርቦት አሠራር ለደም ባንክ የሚሰበሰቡ ደሞችን በድሮን በመታገዝ በማመላለስ፣ ከወሊድ በኋላ በሚከሰት ደም ማፍሰስ ምክንያት የሚመጣውን የእናቶች ሞት በ51 በመቶ መቀነስ የተቻለ ሲሆን፤ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ በራሳቸው በሚበሩ ድሮኖች የተደረጉ የሕክምና አቅርቦቶች በአጠቃላይ ከ100 ሚሊዮን ማይልስ በላይ በሰማይ ላይ በመብረር አንድም አደጋ ወይም የዕቃ መጥፋት ሳይገጥማቸው በስኬት ተከውነዋል። ቀደም ሲል በአስቸጋሪ የመሬት መንገድና የተራራ ውጣ ውረድ ምክንያት 4 ሠዓታትን ይወስድ የነበረው የተሸከርካሪ ጉዞ ዛሬ አየር ላይ፣ ምንም ዓይነት የበካይ ጋዝ ልቀት ሳይኖር ለደም ባንክ የሚሰበሰቡ ደሞችን በድሮን በመታገዝ በማመላለስ በ20 ደቂቃ ብቻ ይጠናቀቃል።

ረዳት ፕሮፌሰር ብርሃነመስቀል፤ የድሮን ቴክኖሎጂን ለላቦራቶሪ አገልግሎት ለማዋል ከሚመለከተው የመንግሥት ተቋም ጋር ስምምነት መደረሱን ይፋ አድርገዋል። ይህ አዲስ አሠራር ከሀገሪቷ የተለያዩ ክፍሎች ናሙናዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማምጣት ከማስቻሉ ባሻገር ናሙናው በተወሰደ አንድ ሠዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የምርመራ ውጤቱ ለሕክምና ባለሙያዎች በስልካቸው እንዲደርሳቸው ያደርጋል። ይህም ለሕመምተኛው ትልቅ እፎይታና ፈጣን የሕክምና ውሳኔን ይሰጣል።

የዚህ ማዕከል ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ መግባት ኢትዮጵያ የጀመረችውን የሜዲካል ቱሪዝም (Medical Tourism) ዕቅድ ለማሳካት በጉልህ የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ ወደ ውጭ ሀገር በሚላኩ ምርመራዎች ምክንያት ይፈስ የነበረውን አገራዊ የውጭ ምንዛሬ በመታደግ ለሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ ድጋፍ ያደርጋል። ከሁሉም በላይ ግን አዲስ የሕክምና መንገድ በማሳየት ዳይናሚክሱን ለመቀየር በር የሚከፍት ስለመሆኑ በልበ ሙሉነት መናገር ይቻላል።

መደምደሚያ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የሕብረትና የዲፕሎማሲ ማዕከል፣ አዲስ አበባ ደግሞ የኢትዮጵያ ካፒታል ነች። ስለሆነም በዓለም አቀፍ የላቦራቶሪ ቴክኖሎጂ፣ በሮቦቲክስ እና በድሮን ትራንስፖርት የበለፀገው አኩቴክ ዲያግኖስቲክስ (Accu-Tech Diagnostics) መሆን ያለበት አጠቃላይ የአፍሪካ ዋነኛ የዲያግኖስቲክስ ማዕከል ነው፤ ናሙናዎችን ወደ ውጭ ሀገራት ለምርመራ የሚልክ ሳይሆን፣ ከመላው አህጉርና ቀጣናው ናሙናዎችን ተቀብሎ በከፍተኛ ጥራት የሚመረምር የሕክምና ማዕከል! ከመንግሥት ጋር በጥምረት ለመሥራት የተቀረጸውን ይህን ዓርአያነት ያለው ተሞክሮ አብዝቶ ማስተዋወቅና ወደ ሌሎች ሀገራዊና አህጉራዊ ተቋማት ማስፋት የሁሉም ኃላፊነት ነው።

ይህ አዲስ አሠራር ከሀገሪቷ የተለያዩ ክፍሎች ናሙናዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማምጣት ከማስቻሉ ባሻገር ናሙናው በተወሰደ አንድ ሠዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የምርመራ ውጤቱ ለሕክምና ባለሙያዎች በስልካቸው እንዲደርሳቸው ያደርጋል።



92

ማኅበራዊ

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

(በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ)

አረንጓዴው ቴክኖሎጂ ኢኮስትሪል 250



93

በሰለሞን ተሰራ

በመላው ዓለም የሚገኙ የጤና ተቋማት የሚሰጧቸው አገልግሎቶች ውስብስብ፣ በቴክኖሎጂ የታገዙ እና ከፍተኛ የኬሚካልና የጨረር ይዘት ያላቸው ናቸው። ከእነዚህ ተቋማት የሚወጡ አደገኛ እና ተላላፊ ቆሻሻዎች አያያዝ የዓለማችን ትልቅ ስጋት እየሆነ መጥቷል። ለዘመናት ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩት ባህላዊ የቆሻሻ ማቃጠያ ማሽኖች (Incinerators) ቆሻሻውን ቢያጠፉትም፣ ወደ ከባቢ አየር የሚለቁት መርዛማ ጭስ (እንደ ዲኦክሲን እና ፉራን ያሉ ካንሰር አምጪ ጋዞች) ሌላ የጤና እና የአየር ንብረት ቀውስ ሲፈጥሩ ቆይተዋል።

ይህን ፈተና ለመቅረፍ የቤልጂየም ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አምራች ኩባንያ የሕክምና ቆሻሻ አወጋገድን ሙሉ በሙሉ የቀየረ ኢኮስትሪል 250 (Ecosteryl 250) የተሰኘ የሕክምና ቆሻሻ አወጋገድን ሙሉ በሙሉ የቀየረ አረንጓዴ ቴክኖሎጂ ለዓለም አበርክቷል።

ማሽኑ አደገኛ የሕክምና ቆሻሻዎችን ጭስ፣ ሽታ እና ብክለት ሳይፈጥር ያለምንም የአየር ብክለት ወደ ተራ ደረቅ ቆሻሻነት የሚቀይር ድንቅ የፈጠራ ውጤት መሆኑን በርካታ ዓለም አቀፍ የሕክምና ተቋማት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።



94

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በማደግ ላይ የሚገኙ እና የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂን በመተግበር ውጤታማ እየሆኑ ያሉ ሀገራት ደግሞ የኢኮስትሪል 250 ቴክኖሎጂን መጠቀም መጀመራቸው ችግሩን ለመፍታት ትልቅ እፎይታን አስገኝቶላቸዋል። ማሽኑን በከተሞች አካባቢ በሚገኙ ትልልቅ ሆስፒታሎች ወይም ማዕከላዊ የቆሻሻ ማከሚያ ቦታዎች ላይ በመትከል የማኅበረሰቡን ጤና ከበሽታ ሥርጭት መጠበቅ ይቻላል።

ኢኮስትሪል 250 በአለርት

አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሚሰጠው ሁሉን አቀፍ የሕክምና አገልግሎት ባሻገር፤ የተቋሙን ምድረ ግቢ የማስዋብና ለታካሚዎች ምቹ የማድረግ ሰፊ ሥራዎችን አከናውኗል። ከዚሁ ጎን ለጎን ጤናማና ንጹህ አካባቢን ለመፍጠር በቆሻሻ አወጋገድ ረገድ ከፍተኛ ስኬት አስመዝግቧል። ሆስፒታሉ በአሁኑ ወቅት ዘመናዊ የደረቅ እና የፈሳሽ ቆሻሻ ማቀነባበሪያ ግዙፍ ማሽን በመጠቀም በሕክምና አገልግሎት ወቅት የሚፈጠሩ ቆሻሻዎች በአግባቡ ተቀነባብረው መልሰው ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ሥርዓት በመዘርጋት የቆሻሻ አወጋገድ ዘዴውን ሙሉ በሙሉ አዘምኗል።

በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ከሆኑ ሆስፒታሎች አንዱ የሆነው አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ማሻሻያዎችና ዘመናዊ አሠራሮችን መተግበር ከመጀመሩ በፊት፤ የዘመናዊ ቆሻሻ ማቃጠያ (Incinera-



95

tor) እጥረት፣ የግንዛቤ ክፍተት እና የደህንነት መጠበቂያ አልባሳት እጥረት ያጋጥሙት የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ሥር ነቀል ለውጦችን በማድረግ ላይ ይገኛል።

ሆስፒታሉ የሕክምና ቆሻሻዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማከም እና የኢንፌክሽን ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችለውን እጅግ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና ቆሻሻ ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂ ኢኮስቴሪል 250 (Ecosteryl 250) አስተዋውቋል። ይህ ቴክኖሎጂ ጎጂ የሆኑ ተላላፊ ቆሻሻዎችን ያለምንም የአየር ብክለት ወደ ተራ ደረቅ ቆሻሻነት ለመቀየር ያስችላል።

ከኢኮስትሪል 250 ልዩ ባህሪያት አንዱ ኢ-ኬሚካላዊ እና ጭስ አልባ አሠራር ያለው መሆኑ ነው። ቆሻሻን ለማጥፋት እሳት ወይም ኬሚካል አይጠቀምም። ማሽኑ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠራ ሲሆን፤ ተላላፊ ቆሻሻዎችን ሙሉ በሙሉ ለማጽዳት የማይክሮዌቭ እና የደረቅ ሙቀትን (Dry Heat) ቴክኖሎጂን ይጠቀማል።

ከፍተኛ የማከም አቅም ያለው ኢኮስትሪል 250፤ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠራው እና በሠዓት 250 ኪሎ ግራም ቆሻሻ የማከም አቅም ያለው ሲሆን፤ በ24 ሠዓት ውስጥ በአጠቃላይ ከአምስት እስከ ስምንት ቶን የሚደርስ ቆሻሻን ያቀነባብራል። አሠራሩ የኤሌክትሪካል ዌቭ (የማይክሮዌቭ ሙቀት) ቴክኖሎጂን የሚጠቀም በመሆኑ ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት አያስከትልም። ማሽኑ ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት የሚታየውን የቆሻሻ አካል እስከ 80 ከመቶ ድረስ በመፍጨትም መጠኑን ያሳንሰዋል።

ይህ ሥርዓት ቆሻሻን የሚፈጩ ሁለት ማሽኖች እና ቆሻሻዎችን የሚለይ ሌላ አንድ ማሽንን ያካተተ ነው። ማሽኑ የተበከሉ የሕክምና ቆሻሻዎችን ሙሉ በሙሉ ካጸዳ በኋላ መልሰው ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉትን እንደየክብደታቸው ይለያቸዋል። በዚህ መንገድ ተለይተው የሚወጡትና መልሰው ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉት ደረቅ ቆሻሻዎች በአንድ በኩል ለኃይል ማመንጫ (ማገዶ) በሌላ በኩል ደግሞ ለፕላስቲክ ፋብሪካዎች በግብዓትነት እንዲያገለግሉ ይደረጋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቅርቡ ባደረገው የመስክ ምልከታ ሆስፒታሉ ከተለያዩ የሕክምና ክፍሎቹ የሚወጡ ደረቅ ቆሻሻዎች በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ በየፈርጁ ለይቶ የማስወገድ ሥርዓቱን በፍጥነት እያስተካከለ መሆኑን አረጋግጧል።

በሆስፒታሉ የሃይጂንና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ ወንድማገኝ ስንዴው እንደገለጹት፤ ማሽኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተስማሚ ከሆኑ ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል አንዱ ሲሆን ወደ ከባቢ አየር የሚለቀው ምንም ዓይነት መርዛማ ኬሚካልም ሆነ በካይ ጋዝ የለውም።

ማሽኑ ሥራውን ከጀመረ ከሁለት ወራት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፤ እስካሁን በሙከራ ደረጃ ላይ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት ሆስፒታሉ ወደ ሙሉ የሥራ ምዕራፍ ለመግባት የሚያስችለውን ፈቃድ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ሆኖም ፈቃዱ እስከሚገኝ ድረስ ሆስፒታሉ በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙና በሕክምና ሂደት ጥቅም ላይ ውለው የሚወገዱ ቆሻሻዎችን



96

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

በማሽኑ አማካኝነት በማከም ጥቅም ላይ ወደሚውሉ ንጹህ ቁሳቁሶች የመቀየር ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።

ከተለያዩ የሕክምና አገልግሎቶች በኋላ የሚፈጠሩ የተበከሉና በቆሻሻ ማስወገድ ሥርዓቱ ከብክለት ነጻ ወደሆነ ግብዓት የሚቀየሩት ቆሻሻዎች በአብዛኛው ሆስፒታሉ በሕክምና ሂደት ውስጥ በስፋትና በከፍተኛ መጠን የሚያመነጫቸው ናቸው። በሆስፒታሉ ውስጥ የሚፈጠሩት ቆሻሻዎች በሁለት ዓበይት ክፍሎች እንደሚመደቡ የገለጹት አስተባባሪው፤ እነሱም ለጤና ጉዳት የሚያመጡ (የተበከሉ) እና ጉዳት የማያመጡ (ያልተበከሉ) ቆሻሻዎች ናቸው። ኢኮስትሪል 250 ቴክኖሎጂም ልዩ ትኩረት አድርጎ የሚያክመው ለጤና አደገኛ የሆኑትን የተበከሉ ቆሻሻዎችን ብቻ ሲሆን እነዚህ የተበከሉ ቆሻሻዎች ወደ ማሽኑ በሚገቡበትና በሚታከሙበት ወቅት ጥብቅ የሆኑ፤ መደረግ ያለባቸውና መደረግ የሌለባቸው (Do’s and Don’ts) መመሪያዎች ይተገበራሉ።

የሚታከሙ እና የማይታከሙ ቆሻሻዎች (Do’s and Don’ts)

ይህ ማሽን የተበከሉ ቆሻሻዎችን ወደ ያልተበከሉ በመቀየር ቀጥታ ወደ መሬት (ወደ መጣያ ቦታ) መሄድ እንዲችሉ ቢያደርግም ወደ ማሽኑ የሚገቡት ቆሻሻዎች ግን ጥብቅ መስፈርት አላቸው።

• የሚታከሙ ቆሻሻዎች፦ በሕክምና ሂደት የተበከሉ መደበኛ ቁሳቁሶች እና እንደ ሹል መርፌ ያሉ ትናንሽ ብረቶች ቢቀላቀሉ ማሽኑ ያለምንም ችግር ያክማቸዋል።

• የማይታከሙ ቆሻሻዎች፦ ከመድኃኒት ቤት (Pharmacy) የሚወጡ ቆሻሻዎች፣ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች፣ እንዲሁም ከሲኤ (CA) ወይም ከካንሰር ሕክምና ጋር ግንኙነት ያላቸው (Cyto- toxic) ቆሻሻዎች ወደዚህ ማሽን አይመጡም። በተጨማሪም መጠናቸው ትልልቅ የሆኑ ብረቶች (የማሽኑን መፍጫ ጥርስ ስለሚጎዱ)፣ የሚፈነዱ ቁሳቁሶች እና ሜርኩሪ ያላቸው መሣሪያዎች ወደ ማሽኑ አይገቡም።



97

ኢኮስቴሪል 250 ቆሻሻን በሚያክምበት ወቅት ምንም ዓይነት የማቃጠል ሂደት ስለማይጠቀም የአየር ብክለትን ሙሉ በሙሉ ያስቀረና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ፍጹም የተስማማ ቴክኖሎጂ ነው። ይህም ሆስፒታሉ የአገልግሎት ጥራቱን ከማሳደግ ባለፈ ለታካሚዎቹና ለአካባቢው ማኅበረሰብ ጤናማና ንጹሕ ከባቢ ለመፍጠር የጀመረውን ጉዞ ስኬታማ አድርጎታል።

የህክምና ቆሻሻ አወጋገድ በጤናው ዘርፍ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠውና ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ ተግባር ነው። በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ ውስጥ በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ ትልቅ እመርታ ተደርጎ የሚወሰደውና በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኘው የቆሻሻ ማከሚያ ማሽን ደግሞ ለዚህ አንዱ ማረጋገጫ ነው። ሆኖም ይህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ካለው እምቅ አቅም አንጻር ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ እንዳይውል የገበያ ትስስር ተግዳሮቶች ማነቆ ሆነውበታል።

ማሽኑ የተበከሉ ቆሻሻዎችን በአግባቡ አክሞ እና አጽድቶ፤ መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለይቶ የማውጣት ከፍተኛ ብቃት ቢኖረውም እስከአሁን እነዚህን የተለዩ ቆሻሻዎች ተረክበው መልሰው ጥቅም ላይ የሚያውሉ ድርጅቶችን አላገኘም። ለዚህም ዋናው ምክንያት የአገሪቷ የፕላስቲክ ፋብሪካዎች ምን አይነት የፕላስቲክ ግብዓት መጠቀም እንደሚፈልጉ በቂ ጥናት አለመደረጉ መሆኑን አስተባባሪው ይገልጻሉ። በዚህ ምክንያት ሆስፒታሉ እስካሁን ድረስ ቆሻሻዎቹን በግብዓትነት የሚያስረክብበት ምንም አይነት የውል ስምምነት ከግልም ሆነ ከመንግሥት ድርጅቶች ጋር መመስረት አልቻለም።

ይህ ተግዳሮት ባለበት ሁኔታም ቢሆን ሆስፒታሉ የማሽኑን አቅም ለመጠቀምና የህክምና ቆሻሻን በአግባቡ ለማስወገድ ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ እየሠራ ይገኛል። አሁን ላይ የሌሎች ሆስፒታሎችን ቆሻሻዎች ተቀብሎ በማከም ላይ የሚገኝ ሲሆን በተለይም ከዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ጋር የሁለትዮሽ ውል በመፈጸም ወደ



98

ነጋሪ 9ኛ ዓመት ቁጥር 34 መስከረም 2019 ዓ.ም

ተግባራዊ ሥራ ገብቷል። ይህም የአዲስ አበባን የህክምና ቆሻሻ አወጋገድ ጫና በመቀነስ ረገድ የራሱን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ወንድምአገኝ እንደሚናገሩት፤ ይህ አይነቱ እጅግ ዘመናዊ ማሽን በአገር አቀፍ ደረጃ በሦስት ስፍራዎች ብቻ ነው የሚገኘው። ማሽኑ የሚገኝባቸው የጤና ተቋማትም ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ እና አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ናቸው።

በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኘው ማሽን በአፍሪካ ደረጃም ቢሆን ተወዳዳሪ የማይገኝለት መሆኑን የጠቆሙት አስተባባሪው፤ እንደ ታንዛኒያ እና ኬንያ ባሉ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ውስጥ ተመሳሳይ የቆሻሻ ማከሚያ ማሽኖች የሚገኙ ቢሆንም የህክምና ቆሻሻን አክሞ ዳግም ጥቅም ወደሚሰጥ ቆሻሻነት (Recyclable material) ለይቶ የሚያወጣው ብቸኛው ማሽን በአለርት ሆስፒታል የሚገኘው መሆኑ ተቋሙን በአህጉሪቱ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

የዚህ ማሽን ወደ ሥራ መግባት ሆስፒታል ወለድ በሽታዎችን (Nosocomial Infections) ከመከላከል አኳያ ጉልህ ሚና ይጫወታል። በሆስፒታሉ የሚመነጨው ቆሻሻ በአግባቡ ታክሞ ስለሚወጣ ለማኅበረሰቡ ምንም ዓይነት የአደጋ መንስኤ አይሆንም። ይህም ከጤና ተቋማት ቆሻሻ አወጋገድ ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ክፍተቶችንና ችግሮችን መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ የመፍታት አቅም አለው። ከዚህም በላይ ማሽኑ ቆሻሻዎችን ሙሉ በሙሉ የሚያክመው ከአካባቢ አየር ጋር በተጣጣመና ሥነ-ምህዳርን ባልበከለ መልኩ በመሆኑ ምንም ዓይነት የብክለት ስጋት አይፈጥርም።

ተቋሙ ጽዱ፣ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ለመፍጠር የጀመረው ተግባር በከተማ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው። ለምሣሌ በከተማዋ ውስጥ የቆሻሻ ማከሚያና ማቃጠያ ማሽን የሌላቸው ድርጅቶች ቢኖሩ የሚያመነጩትን ቆሻሻ ወደ አለርት ሆስፒታል በማምጣት በተመጣጣኝ ዋጋ ማቃጠልና ማስወገድ ይችላሉ። ይህ ሂደት ማሽኑ ከተቋሙ ባለፈ የከተማዋን የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ችግር በከፍተኛ ደረጃ የማቃለል አቅም እንዳለው ያሳያል።

ማሽኑ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር በቀን 24 ሠዓት መሥራት የሚችል ነው። ይሁን እንጂ ማሽኑ ለ24 ሠዓታት በሚሠራበት ወቅት በሠራተኞች ላይ ሊደርስ የሚችለውን የአደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስና የሥራ ጫናን ለማቃለል ሥራው በሦስት ፈረቃ እንዲከፋፈል ተደርጓል። ማሽኑን በበላይነት የሚቆጣጠሩትና የሚያንቀሳቅሱት ባለሙያዎች በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች የሚመደቡ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ የማሽን ኦፕሬተሮች ናቸው። በእነዚህ ኦፕሬተሮች ውስጥ ደግሞ የኤሌክትሪክ ባለሙያዎች፣ ሲኒየር ሜካኒኮችና የባዮሜዲካል ቴክኒሻኖች ይካተታሉ። በአጠቃላይ ማሽኑ ከሱፐርቫይዘሩ ውጭ 21 ቋሚ ሠራተኞችን ይፈልጋል።

በአጠቃላይ ይህ የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ወደ ሥራ ያስገባው የቆሻሻ ማስወገጃ ቴክኖሎጂ አገር በቀል ችግሮችን ለመፍታትና ቆሻሻን ወደ ሃብት ለመቀየር ያለውን አቅም በተሟላ ሁኔታ መጠቀም እንዲችል የፕላስቲክ ፋብሪካዎችን ፍላጎት ያማከለ ጥናት በአፋጣኝ መደረግና የገበያ ትስስር መፈጠር ይኖርበታል።



99



100




የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም