ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም
ይጫኑ

1

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም



2

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም



3



4

አድራሻ፦ አራዳ ክፍለ ከተማ

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ስልክ ቁጥር +251-11-55-00-11

+251-11-56-39-31

+251-11-56-52-21

ፋክስ ቁጥር +251-11-55-16-09

enanegari@gmail.com

በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በየሁለት ወሩ የምትታተም መጽሔት



5

ድረ-ገፅ www.ena.et/web/negari

አስታራቂው ችሎት

06

አሻጋሪው ድልድይ. . .

22

አፍሪካ ለምን ትጠማለች? የመሪዎቿ ጉባዔ አንድምታ

40

የምታሸንፈው ኢትዮጵያ ናት

58

የተገለጠ ውበት

80

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ለኢትዮጵያ

92

ያልተነገረለት ሙያ

110

ድንበር ያልገደበው ማዕከል

120

በዲጂታል 2030- ወደ ላቀ ብልጽግና

142

መልዕክት

ውድ አንባቢያን ሠላም በያላችሁበት ይሁን! ነጋሪ መፅሔት እንደ ወትሮው ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ይዛ መጥታለች።

ኢትዮጵያዊያን ከቀደሙት ስህተቶች ተምረን፣ የዛሬን ተግዳሮቶች ተሻግረን፣ የነገዋን የበለጸገችና የተረጋጋች አገር የምንገነባበት፤ በካርዳችን የላቀ ጥቅማችንን ለማስጠበቅና ውሳኔያችንን ለማሳለፍ፤ ምርጫ ልናካሂድ ቀን ቆርጠናል፤ ኢትዮጵያም በወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች . . . - ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ዐቢይ ጉዳይዋ ያደረገችው ነጋሪ፤ የኢትዮጵያን የምርጫ ጉዞ በታሪክ መስታወት ታስቃኛለች።

ዓለማችን በሰው ልጅ ምጡቅ ዕውቀት ታግዛ ቀጣዩንና አስደናቂውን የቴክኖሎጂ ክህሎት እውን ለማድረግ በዋዜማው ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያም ቀደም ብላ የጀመረችውና በስፋት እየተተገበረ የሚገኘው ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ብሔራዊ የልማት አጀንዳዎች ጋር የጠበቀ ቁርኝት ያለው ነው። ዲጂታል 2025ን በስኬት አጠናቃ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ዲጂታል 2030 ተሸጋግራለች - ነጋሪ ዳሳዋለች።

“የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ የውሃ አቅርቦት እና አስተማማኝ የንፅህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ” የሚለውን የ39ኛውን የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ መሪ ሃሳብ የሚያስታውሰውና የጉባዔው አንኳር ማጠንጠኛ የሆነውን የውሃ ደህንነት ጉዳይ እንዲሁም የጉባዔውን ክዋኔና የመልዕክቶች አንድምታ የሚቃኘው የነጋሪ ጽሁፍ “አፍሪካ ለምን ትጠማለች” ይላል።

የንግድና የኢኮኖሚ ግኑኝነት አንዱ አካል የሆነውን ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ቀድመው የፈጸሙ ሀገራት ኢኮኖሚያቸውን በማጠናከር፣ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር፣ የሕዝብ የኑሮ ደረጃን በማሻሻል እንዲሁም የማኅበራዊ ግንኙነትን በማጎልበት አገራዊ ዕድገት ማስመዝገብ ችለዋል። የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣናስ? ይህ ስምምነት ዓላማው ምንድን ነው? ለኢትዮጵያስ ምን ማለት ነው? ትግበራውስ ምን ይመስላል . . . ነጋሪ ምላሽ አላት።

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ሀገር በቀል ዕውቀቶች አንዱ የሆነው ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ እንደየ አካባቢው ባህል እና ወግ የተለያየ መልክ ቢኖረውም የመጨረሻ ግቡ የተጣላን ማስታረቅ፣ ያጠፋውን መቅጣት፣ የበደለን መካስ ነው። ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎችንና ዕውቀትን ከዘመናዊው የምክክር መንገድ ጋር አጣምሮ መጠቀም በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያስችል ይታመናል . . . ስለዚህም ነጋሪ የምትለው አላት።

የህዋ ሣይንስ እና ጂኦስፓሻል መስክ እንቅስቃሴዎች የሰው ልጆችን ሕይወት ከማቅለል አልፈው የኢኮኖሚ ዕድገት መለኪያና ማሳያ እየሆኑ ነው። የዓለም መንግሥታት መስኩን አቅማቸውን ለማሳየት ብሎም በፖለቲካ መስክ የበላይነታቸውን ለማስቀጠል እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። ኢትዮጵያም በመስኩ የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀትና ሥራውን የሚመራ ተቋም በመመስረት ወደ ሥራ ገብታለች። ጉዳዩን የተመለከተው የነጋሪ ፅሁፍ በመስኩ የኢትዮጵያን ከየት ወዴት ይቃኛል።

የኢትዮጵያ የቱሪዝም ልማት ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም ባህላዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን በተገቢው መንገድ ለይቶ ማልማት፣ ማስተዋወቅና ተወዳዳሪ መዳረሻዎችን መፍጠር ላይ በልኩ ባለመሠራቱ ከዘርፉ ተገቢው ጥቅም አልተገኘበትም፡፡ ይሁንና የለውጡ መንግሥት በቀየሰው አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከለያቸው አምስት የዕድገትና የብልጽግና ምሰሶዎች ቱሪዝም አንዱ ሆኗል - በአግባቡ ያልታየው የኢትዮጵያ ውበትም ተገልጧል፤ የነጋሪ ሌላው ጉዳይ ነው።

ነጋሪ የህክምና ልህቀት ለደረሰበት ደረጃ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተውንና በዘርፉ ቁልፍ ከሚባሉ የሙያ መስኮች አንዱ የሆነውን ፓቶሎጂ (Pathology) እንዲሁም ድንበር ያልገደበውን የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሥልጠና ማዕከል የተመለከቱ ፅሁፎችም ይዛለች።

መልካም ንባብ!

ዋና አዘጋጅ ተስፋዬ ቦካ

ም/ ዋና አዘጋጅ የሺመቤት ደመቀ

ከፍተኛ አዘጋጅ ፍቅርተ ባልቻ ሰለሞን ተሰራ

አዘጋጅ መንገሻ ገ/ሚካኤል

አርት ዳይሬክተር ነብዩ መስፍን nebiyou1st@gmail.com



6

ማኅበራዊ

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

አስታራቂው ችሎት



7

በሰለሞን ተሰራ

ከሰው ልጅ ዕድሜ ጋር እኩል እንደሆነ የሚታመን ማኅበራዊ ክስተት ነው። ሰው አብሮ እስከኖረ ድረስ የማይቀየርና የማይታለፍ የሕይወት ተሞክሮ ስለመሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ። በዓለም ላይ በሁሉም የሰው ልጆች የሕይወት ዘርፎች ውስጥ አብሮ መጓዙንም ምሁራን ያስረዳሉ። ሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች መካከል በሚከሰት የሀሳብ፣ የፍላጎት ወይም የግብ አለመጣጣም ሊወለድ ይችላል። በጥቅሉ በግለሰቦች፣ በቡድኖች ወይም በሀገራት መካከል የሚፈጠር አለመግባባት፣ የሐሳብ ልዩነት ወይም የጥቅም ፉክክር ውጤት ነው - ግጭት። ግጭት በሰው ልጆች የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ የሚያጋጥምና ከተፈጥሯዊ ማንነታቸው ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑ በበርካታ ጥናት እና ምርምሮች ተመላክቷል።



8

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

“Traditional Conflict Resolution Mechanism in Ethiopia” በሚል ርዕስ Lakhomi Journal: Scientific Journal of Culture እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም የታተመው ጥናት በሰዎች ልጆች ታሪክ እና ሕይወት ውስጥ ግጭት አዲስ ክስተት እንዳልሆነ ጠቅሶ ሰዎች አብረው እስካሉ እና መስተጋብር እስከፈጠሩ ድረስ የሚኖር ስለመሆኑ ያትታል። የሰው ልጆች ግጭት የሕይወታቸው አንዱ ገጽታ እንደሆነም ይጠቅሳል። “የማይጋጭ ሰው ወይም ከግጭት ውጪ የሆነ ሰው ቢኖር በሕይወት የሌለ ብቻ ነው” ሲል ነው ጽሑፉ የግጭትን አይቀሬነት አጽንኦት በመስጠት ያስነበበው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ፣ ሥነ- ጽሑፍና ፎክሎር ትምህርት ክፍል በባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት ላይ በ2006 ዓ.ም የተሠራው ጥናት ግጭትን “ትግል፣ ልዩነት፣ አለመስማማት፣ ጠብ፣ ውጊያ፣ አለመግባባት” ነው ብሎታል። ይኸው ጥናት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ቡድኖች መካከል በሚኖር የዓላማ ልዩነት አንዱ የሌላኛው የበላይ ለመሆን ሲሻ የሚፈጠር ተቃርኗዊ ስሜት እንደሆነም አብራርቷል። በሰዎች መካከል ሊኖሩ የሚችሉ ልዩነቶች ሰፊ በመሆናቸው፣ የግጭት አለመኖር ብዙውን ጊዜ ትርጉም ያለው ማኅበራዊ መስተጋብር አለመኖሩን ያሳያል። ግጭት በራሱ ጥሩም መጥፎም አይደለም፤ ይሁን እንጂ ግጭቱ የሚስተናገድበት መንገድ ውጤቱን ገንቢ ወይም አጥፊ ያደርገዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ይህን ሀሳብ በመደገፍ “ግጭቱን የምንቆጣጠርበት ወይንም የምንፈታበት መንገድ ውጤቱን ገንቢ ወይንም አፍራሽ እንዲሆን ያደርጋል” ይላል። ግጭት የከፋ መልክ እንዳለው ሁሉ በሳል አመራርና ባህላዊ እሴቶችን በመጠቀም መፍትሔ የሚሰጥ አካል ከተገኘ ማኅበራዊ ትስስርን የተሻለ በማድረግ በዳይና ተበዳይን ወደ ሌላ የሕይወት ምዕራፍ ማሸጋገርም ያስችላል። መንስኤዎቹ እና ዓይነቶቹ ግጭት የሚነሳው የማይጣጣሙ ግቦች ባላቸው



9

ግለሰቦች ወይም ሌሎች አካላት መስተጋብር ነው። በዚህ ወቅት የአንዱ ወገን ዓላማ የመሳካት ዕድል በሌላኛው ወገን ምርጫ ወይም ውሳኔ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው። ብዙ ጊዜ ግጭቶች በአንድ ጊዜ በሚፈጠር ሁነት ብቻ የሚመጡ ሳይሆኑ የበርካታ ችግሮች ድምር ውጤት ናቸው። ቀደም ሲል የተጠቀሰው ጥናት የግጭትን መንስኤዎች በሦስት ከፍሎ አብራርቷቸዋል። ቡድኖች ወይም ግለሰቦች የተፈጥሮ ሀብት ውስንነት ሲያጋጥማቸው አንዳቸው ከአንዳቸው የተሻለ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያደርጉት ጥረት ወደ ግጭት እንዲገቡ ምክንያት ይሆናቸዋል። ይህም ለኢኮኖሚያዊ ግጭት አንዱ እና ትልቁ መንስኤ ነው።

ሌላው ከዕሴቶች ጋር የተያያዘው ሲሆን፤ በሰው ልጆች የአኗኗር ዘይቤ፣ የፍላጐት መቃረን እና የመሳሰሉት ልዩነቶች ከግጭት መነሻዎች መካከል ናቸው። አንዱ ወገን በሌላኛው ላይ የበላይ ለመሆን የሚያደርገው ጥረት በሦስተኛነት የተጠቀሰ የግጭት መንስኤ ነው። ይህ ዓይነቱ ግጭት በግለሰቦች፣ በቡድኖች ወይም በሀገር ደረጃ ሊከሰት የሚችል ነው። እነዚህ የግጭት ምክንያቶች በተናጠል ለአንድ ግጭት መንስኤ የሚሆኑበት አጋጣሚ ይኖራል። በተጨማሪም ሰው አንድን ነገር በራሱ አመለካከት ብቻ አጥሮ ሲተረጉም ተግባቦት ስለሚቀንስ ለግጭት ምክንያት ሊሆን ይችላል። በግጭቶቹ ከሚሳተፉ አካላት አንጻር ግለሰባዊ፣ ቡድናዊ እና ዓለም አቀፋዊ በሚል መግለጽ ይቻላል።

ግለሰባዊ ግጭት (Interpersonal conflict) የሚፈጠረው ሁለት ሰዎች በፍላጎት፣ በዓላማ፣ በአቀራረብ በተግባቦት ልዩነት ሲኖር ነው። እነዚህ ሰዎች ልዩነቶቻቸውን ለማጥበብና የዓላማ ልዩነታቸውን አቻችለው ማስኬድ ከቻሉ በመካከላቸው ያለው ተቃርኖ ይቀንሳል። የተግባቦት አቅምን በትምህርት ማበልፀግ እንዲህ ዓይነቱን ግጭት ለማስቀረት መፍትሄ እንደሆነም ይጠቀሳል። ቡድናዊ ግጭት (Intergroup conflict) ተመሳሳይ አመለካከትና ባህል ባላቸው ሰዎች የተፈጠረ ቡድን በተመሳሳይ ከተፈጠረ ሌላ ቡድን ጋር የሚያደርጉትን ግጭት ያጠቃልላል። ይህ አንድ ቡድን በሌላኛው ላይ የበላይ ለመሆን ሲፈልግ ይከሰታል። ዓለም አቀፋዊ ግጭት (International conflict) ግጭቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታዩ እና

በሀገራት መካከል የሚከሰቱ ናቸው። ምክንያታቸው እንደየሁኔታው የተለያዩ ቢሆም አንድ ሀገር በሌላኛው ሀገር ላይ የሚከፍተው ጦርነትና ኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ ዋነኛ መገለጫዎቹ ናቸው። የመፍትሔ መንገዶች ሰዎች በማኅበረሰብ ወይም በቡድን አብረው



10

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

እስከኖሩ ድረስ ከጥቅም ግጭት፣ ከፍላጎትና ከምኞት ልዩነት የሚነሱ ግጭቶች መኖራቸው የማይቀር ነው። በመሆኑም እንዲህ ያሉ የፍላጎት ልዩነቶችን ለመከላከል ወይም ለመፍታት የሚወሰዱ እርምጃዎች የግጭቱን አፈታት ይወስኑታል። በሌላ አነጋገር ግጭት በሚከሰትበት ጊዜ ወሳኙ ነጥብ አስፈላጊ የሆነውን የመፍትሔ መርህ ውጤታማ በሆነ መንገድ መተግበሩ ላይ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ጉዳዮች መምሪያ (2001) እንደገለጸው፤ ግጭት ሊፈታ የሚችለው ዋና መንስኤዎቹ ታውቀው ምላሽ ሲያገኙ ብቻ ነው። ግጭቱ በተሳካ ሁኔታ ሲፈታ በግለሰቦች፣ በግንኙነቶችና በመዋቅሮች ላይ ሥር የሰደደ አዎንታዊ ለውጥ እንዲመጣ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ስለዚህ ግጭትን በአግባቡ መፍታት በሰዎች መካከል የተሻለ ደህንነትና መልካም ግንኙነት እንዲሰፍን በማድረግ ለሰው ልጅ ዕድገትና ለአጠቃላይ ልማት መሠረት የሚሆን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ይቻላል። ግጭቶችን ስር ሳይሰዱና የከፋ ጉዳት ሳያስከትሉ አስቀድሞ ወደ መግባባት እንዲያመሩ መሥራቱ አጠያያቂ አይደለም። ግጭቶችን ለመፍታት የተለያዩ አማራጮች በተለያዩ ምሁራን ይቀርባሉ። ከእነዚህ መካከል ድርድር፣ ሽምግልና እና ዳኝነት ጎልተው የሚጠቀሱ ናቸው። ግጭቶችን ለመፍታት ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉትን ዘዴዎች በሁለት መንገድ መግለጽ ይቻላል፤ ዘመናዊ እና ባህላዊ ወይም (መደበኛ እና መደበኛ ያልሆኑ) በሚል። እነዚህን ስልቶች ሁሉም አገራት እንደራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ተግባር ላይ በማዋል ለችግሮቻቸው መፍትሔ ለመስጠት እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ።

Lakhomi Journal: Scientific Journal of Culture ላይ የታተመው የጥናት ሰነድ መደበኛ እና መደበኛ ያልሆኑ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መኖራቸውን ይጠቅሳል። መደበኛ/ዘመናዊ የሚሰኙት በመንግሥት ዕውቅና የተሰጣቸው በህገ-መንግሥት እና ከህገ-መንግሥት ድንጋጌዎች በመነሳት በሚዘጋጁ ሌሎች የህግ ማዕቀፎች እና አስፈጻሚ አካላት አማካኝነት ተግባራዊ የሚደረጉት ናቸው። በየደረጃው ባለው የመንግሥት መዋቅር ተፈጻሚ የሚሆኑት የግጭት መፍቻ ስልቶች እንደሆኑ ጥናቱ አብራርቷል። በአንጻሩ መደበኛ ያልሆኑት አንዳንዴ ’አገር በቀል የግጭት መፍቻ ስልቶች’ (indigenous conflict resolution method) የሚባሉት እንደሆኑ ጽሑፉ ገልጾ፤ እነዚህ በተለይ ብዝሃ ባህል ባላቸው ሕዝቦች ዘንድ በስፋት ተግባራዊ የሚደረጉ ስለመሆኑ አስፍሯል። ማኅበረሰቡ አገር በቀል ዕውቀቱን በመጠቀም (እንደራሱ ነባራዊ ሁኔታ) ችግሮቹን እና የሚጋጥሙትን ግጭቶች የሚፈታበትን ስልት በዘመናት ቆይታው የሚያዳብር መሆኑን ጥናቱ አመላክቷል።

ዘመናዊ የግጭት አፈታት (Modern Conflict Resolution) ከመደበኛው የሕግ ሥርዓት በተጓዳኝ እንደ አንድ ራሱን የቻለ የጥናትና የሥራ መስክ በይፋ መልክ መያዝ የጀመረው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ባሉት ዓመታት በተለይም በ1950ዎቹ እና 1960ዎቹ አጋማሽ ላይ መሆኑን በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የመንግሥት አስተዳደርና የልማት ጥናት ትምህርት ክፍል ከፍተኛ መምህር ኃይሌ ቹሉኬ ዲግሌ እና የታሪክና የቅርጽ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ከፍተኛ መምህር መንገሻ ሮብሰ ወዳጆ በጋራ ባሳተሙት (The Role of Indigenous Institutions



11

በወቅቱ የነበረው የቀዝቃዛው ጦርነት ሥጋት ምሁራን ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችሉ ስልታዊ ጥናቶችን እንዲያደርጉ እንደገፋፋቸውም ምሁራኑ ያስረዳሉ።

በ1957 “The Journal of Conflict Resolution” የተሰኘው የምርምር መጽሔት መታተም መጀመሩ እና በ1959 በኖርዌይ የሰላም ምርምር ተቋም (Peace Research Institute Oslo - PRIO) መመሥረት ለዘርፉ ዕድገት ወሳኝ ነበሩ።

ከ1970ዎቹ እስከ 1980ዎቹ ባለው ጊዜ የግጭት አፈታት ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለፈ በሀገር ውስጥ የህግ ሥርዓቶች (ለምሣሌ እንደ አማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴ) እና በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት መተግበር ጀመረ። ከ1990ዎቹ ጀምሮ የቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃትን ተከትሎ ትኩረቱ ከታላላቅ መንግሥታት ግጭት ወደ ማኅበረሰባዊ እና የብሔር ግጭቶች አፈታት መሸጋገሩን ሉዊስ ክሪስበርግ (Louis Kriesberg) The Evolution of Conflict

in Conflict Resolution: Abbagar in Focus, Wollo, ) በሚል ጥናታቸው ላይ አስፍረውታል።

Resolution በተሰኘው ታዋቂ የምርምር ጽሑፉ ጠቅሶታል። ይህ ሥርዓት በምዕራባዊያን ዕሴቶችና ልማዶች ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ መደበኛ/ዘመናዊ (Formal) የሚለው ቃልም በዋናነት የቅኝ ግዛት ውርስ የሆነውን ዘመናዊ የህግ አወቃቀር ያመለክታል። ሥርዓቱም በወጡ ህጎችና በሀገራት ሕገ-መንግሥት ይመራል። በዚህ ሥርዓት ውስጥ ፍትህ የሚሰጠው በሠለጠኑ ባለሙያዎችና ጠበቆች ሲሆን፣ አሠራሩም በጣም በተራቀቁና ተዋረድ ባላቸው ተቋማት (ፍርድ ቤቶች) የታጀበ ነው።

መደበኛ የግጭት አፈታት ከጥቂት የሀገር ውስጥ ህጎች በስተቀር፣ በሁሉም ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ዓለም አቀፋዊ ወይም ሁለንተናዊ ይዘት አለው። ፍርዱ በቅጣት ፍትህ መርህ ላይ የተመሠረተ አሠራር የሚከተል



12

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ሲሆን ሙያዊ ሥልጠናና ገለልተኝነት የህጋዊነት ምንጮች ተደርገው ይወሰዳሉ። ስለሆነም ዘመናዊ የግጭት አፈታት ስልቶች በመንግሥታዊ የፍትህ ተቋማት (ፍርድ ቤቶችና ፖሊስ) አማካኝነት በህግና በደንብ ላይ ተመሥርተው የሚከናወኑ ናቸው።

ሌላው እና በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው የግጭት መፍቻ ስልት መደበኛ ያልሆነው እና አገር በቀል ዕውቀትን የሚጠቀመው ነው። ባህላዊ (መደበኛ ያልሆኑ) የግጭት አፈታት ሂደቶች ለማስታረቅ፣ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ለመጠገንና ለማሻሻል የታለሙ፤ በሚገባ የተዋቀሩና በጊዜ የተፈተኑ የተግባራዊ ልምምድ ውጤቶች ናቸው።

ባህላዊ የግጭት አፈታት ስልቶች በማኅበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ዕምነት የሚጣልባቸውና ዘመናትን ያስቆጠሩ የመፍትሔ መንገዶች ናቸው። ዓላማቸው ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታትና ተበላሽቶ የነበረውን ግንኙነት መልሶ መጠገን ነው። ጥፋተኛውን ለመቅጣት ብቻ ሳይሆን፣ በተጣሉ ወገኖች መካከል የነበረውን ማኅበራዊ ትስስር መልሶ ለማደስም ይሠራሉ። ባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴ አንድ ማኅበረሰብ ከመደበኛው ፍርድ ቤት ውጭ ወይም ጎን ለጎን ግጭቶችን ለመፍታት የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች ስብስብ ነው። በግጭት ውስጥ ባሉ ወገኖች ስምምነት ላይ የተመሠረቱ በመሆናቸው የሁሉንም ፍላጎት እና



13

ጥቅም ያስከብራሉ። አነስተኛ ወጪ የሚጠይቁና በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሄ መስጠት መቻላቸውም ከጥቅሞቻቸው መካከል የሚጠቀስ ነው። ወደ ማኅበረሰቡ የቀረቡና በየአካባቢው በቀላሉ መገኘታቸው ተመራጭ ያደርጋቸዋል።

ባህላዊ የግጭት አፈታት ስልቶች ግጭቶችን ለመፍታት አማራጭ መንገድ ከመሆን አልፎ ሰዎች እርስ በእርሳቸው መተማመን እንዲኖራቸው ያደርጋሉ። ባህላዊ የግጭት አፈታት ዕሴቶችና መርሆዎች ለሰላማዊ ሕይወት ያላቸው ፋይዳ እጅግ የላቀ ነው። እነዚህ ሥርዓቶች ከቅጣት ይልቅ እርቅን፣ ከጥል ይልቅ ፍቅርን በማስቀደም የሚታወቁ የማኅበረሰብ የጥበብ መገለጫዎች ናቸው። የእነዚህ ዕሴቶች ዋነኛ ጠቀሜታ የተበላሸን ግንኙነት መልሶ በመገንባት ላይ ማተኮራቸው ነው።

በባህላዊ የግጭት አፈታት ሂደት ውስጥ ግቡ ጥፋተኛውን ለይቶ ማግለል ሳይሆን የበደለ እና የተበደለ በይቅርታ ታርቀው ዳግም በማኅበረሰቡ ውስጥ በሰላም እንዲኖሩ ማድረግ ነው። ይህ “ሁለቱም አሸናፊ” የሚሆኑበት መርህ ማኅበራዊ ትስስሩ እንዳይላላ እና በቀል እንዳይስፋፋ እንደ አጥር ሆኖ ያገለግላል።

በዚህ ሥርዓት ውስጥ ግንኙነቶችን ወደነበሩበት ቦታ ለመመለስና ቡድኖችን ለማስታረቅ ትኩረት ስለሚሰጥ፣ የቡድን ግንኙነቶችና መብቶች እንደ ግለሰብ መብቶች ሁሉ አስፈላጊ ተደርገው ይታያሉ። ዋናው መርህ ግጭቱን ለመፍታት የሚወሰዱ እርምጃዎች ከግጭቱ ተፈጥሮ፣ ፋይዳ፣ ውስብስብነት እና ለተጋጩት ወገኖች ካለው አስፈላጊነት ጋር ተመጣጣኝ መሆን አለባቸው የሚል ነው። እነዚህ ሥርዓቶች በእውነትና በፍትህ ላይ የተመሠረቱ ናቸው። ግጭቶቹ የሚዳኙት የማኅበረሰቡን የሞራል ዕሴቶች መሠረት በማድረግ በመሆኑ ውሳኔው በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነትን ያገኛል። ይህም በሕዝቡ ዘንድ የባለቤትነት ስሜትን ይፈጥራል፤ ግጭቶችም በራሱ በሕዝቡ ፍላጎትና ባህል ስለሚፈቱ ሰላሙ አስተማማኝና ዘላቂ እንዲሆን ያደርገዋል።

በአጠቃላይ አገር በቀል የግጭት አፈታት ስልቶች ሰላምን ከልብ የሚመነጭና በይቅርታ የታጀበ እንዲሆን በማድረግ፣ የማኅበረሰቡን አንድነትና ደህንነት በመጠበቅ ረገድ የማይተካ ሚና ይጫወታሉ።

አገር በቀል የግጭት መፍቻ ስልቶች - በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ፤ የጥንታዊና ቀደምት ሥልጣኔ ባለቤት መሆኗ ከተመሰከረላቸው ጥቂት የዓለማችን ሀገራት አንዷ ነች። ለዘመናት ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፉ የመጡ ባህላዊ እሴቶቿ የሕዝቦቿ የግልና የጋራ ማንነት መገለጫ ከመሆናቸውም በላይ ነፃነቷ ለዘመናት ጸንቶ እንዲዘልቅ ታላቅ ድርሻ እንዳላቸው የሚጠቅሰው የኢትዮጵያ የባህል ፖሊሲ ነው።

የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች መገኛና በጥንታዊቷ ሀገር ኢትዮጵያ ሁሉም አካባቢዎች እና ባህሎች ውስጥ አገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መኖራቸውን በጉዳዩ ላይ የተከናወኑ ጥናት እና ምርምሮች ያሳያሉ።

Africa Review (2024) “Conflict Resolution through Indigenous Knowledge Systems” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ጥናት በኦሮሞ፣ በአፋር፣ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሀረሪ፣ በሶማሌ፣ በሲዳማ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በትግራይ እንዲሁም በሌሎች ብሔረሰቦች እና ጎሳዎች የራሳቸው ሀገር በቀል የሆኑ የችግር



14

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

መፍቻ ዘዴዎች እንዳሏቸው ጠቅሷል። አያይዞም እነዚህ ዘዴዎች ከየአካባቢው እና ከማኅበረሰቡ ባህል፣ ወግ፣ ልማድ፣ አንጻር የተቃኙና የሚስማማ ባህሪይ የሚንጸባረቅባቸው ስለመሆኑም አብራርቷል።

ከትውልድ ወደ ትውልድ በተላለፈ ሀገር በቀል ዕውቀት፣ ዕሴት እና ልማድ በመጠቀም በማኅበረሰቡ ወይም በግለሰቦች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች የሚፈቱበት ይህ ጥበብ በብዙ መልኩ ሀገሪቷ ያላትን ቱባ ባህል በደማቁ ያሳያል። ችግር በራስ ባህል፣ ወግ እና ዕውቀት የመፍታት ልምምዶች በሀገራችን ከመደበኛው/ ዘመናዊው የህግ ሥርዓት ቀድመው የነበሩ እና ዛሬም ድረስ በስፋት በማገልገል ላይ የሚገኙ የፍትህ ምሰሶዎች ናቸው።

በሽማግሌዎች፣ በሃይማኖት አባቶች ወይም በጎሳ መሪዎች የሚመራው ይህ የችግር መፍቻ ስልት ጥፋተኛን ከመቅጣት ባለፈ ዕርቅ ለማውረድ፣ የተበላሸውን ማኅበራዊ ግንኙነት ለማደስ እና የተቋረጠውን ማኅበራዊ ግንኙነት መልሶ ለማስቀጠል ይረዳል። ማኅበረሰቡም ባህሉን ስለሚቀበለው የሚሰጡ ውሳኔዎች በፈቃደኝነት የመከበርና የመተግበር ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።

ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎች በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ዘንድ ለዘመናት የዘለቁ፣ የማኅበረሰቡን ሰላምና አንድነት ጠብቀው ያቆዩ ዕሴቶች ናቸው። እነዚህ ዕሴቶች እንደየአካባቢው ባህል እና ወግ የተለያየ መልክ ቢኖራቸውም የመጨረሻ ግባቸው የተጣላን ማስታረቅ፣ ያጠፋውን መቅጣት፣ የበደለን መካስ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች እንደየአካባቢው ባህል፣ ወግና እምነት የሚለያዩ ቢሆኑም፣ በዋናነት ዕርቅን፣ ሰላምንና ማኅበራዊ አንድነትን ለማምጣት ያገለግላሉ።

በባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ላይ በርካታ ጥናቶችን ያደረጉትና በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ታገል ወንድሙ የግጭት መፍቻ ሥነ-ዘዴዎቹ በርካታ ስያሜዎች እንዳሏቸው ጠቅሰው፤ ከእነዚህም መካከል ሀገር በቀል ወይም ባህላዊ የግጭት አፈታት፣ መልሶ አስታራቂው የፍትህ ሥርዓት እና ኢ-መደበኛ የግጭት አፈታት የሚሉትን ለአብነት ጠቅሰዋል።

በበርካታ የሀገሪቷ አካባቢዎች የሚደረጉ ማኅበራዊ መስተጋብሮች ለምሣሌ ግብይት፣ ብድር፣ ውሰት እና ሌሎች ግንኙነቶች የሚከናወኑት ከመረጃ ይልቅ በዕምነት ላይ ተመሥርተው በመሆኑ አለመግባባቶች ሲከሰቱ ማስረጃ ማቅረብን አዳጋች ያደርገዋል። ባህላዊ የግጭት መፍቻ ማስረጃ ከመፈለግ ይልቅ እውነት ፍለጋ ላይ ስለሚያተኩር ለሁለቱም ወገን ትክክለኛ ፍትህን ያስገኛል። ባህላዊውን መንገድ የተከተለ የዕርቅ ሥርዓት በማከናወን ከቂም በቀል የፀዳና ወደ ቀደመው ወዳጅነት የሚመልስ ማስማማት እንደሚከናወንበት ነው የገለጹት።

በሀገር በቀል ዕውቀት በሚከናወነው ግጭት የመፍታት ሂደት የሚሰጡ ውሳኔዎች የአካባቢው ማኅበረሰብ ከታዋቂ ሽማግሌዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና የሃይማኖት አባቶች ጋር ቁጭ ብሎ የሚወስናቸው በመሆናቸው “አሸናፊና ተሸናፊ” የሌለባቸው፣ ሁለቱም እኩል ተደስተው የሚወጡበት ነው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንደሚገልጸው፤ ሂደቶቹ ተደራሽ እና በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ታማኝነት ያላቸው፤ በሁለት ወገኖች መካከል “አሸናፊና ተሸናፊ” ከመፍጠር ይልቅ



15

“ሁለቱም አሸናፊ” የሚሆኑበትን የዕርቅ መንገድ የሚከተሉ ናቸው። በዚህ ረገድ በሀገራችን የተለያዩ ማኅበረሰቦች የሚገለገሉባቸው ከ75 በላይ ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶች መኖራቸውን የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የቋንቋና ባህል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልመሃዲ የተሻለች ሀገር፣ ትውልድና ኢኮኖሚ ለመገንባት ሀገር በቀል ዕውቀት የማይተካ ሚና እንዳለው ይገልጻሉ። “ሀገር በቀል ዕውቀት ከሌላ ያልተቀዳ ኢትዮጵያዊያን አኗኗራችንን መሠረት አድርገን የፈጠርነውና እስከ ዛሬ አፅንተን ያቆየነው የራሳችን የሆነ መገለጫ ነው” ይላሉ። መንግሥት ለሀገር በቀል ዕውቀትና ለባህል ልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት ተረስተው የቆዩ ዕሴቶችና ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ወደፊት በማምጣት ለሀገር ልማት የራሳቸው አበርክቶ እንዲኖራቸው እየተሠራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ብዙ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን የያዘች ትልቅ ሀገር ናት፤ ሁሉም አካባቢዎች ሀገር በቀል ዕውቀቶች አሏቸው። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በአገሪቷ የሚገኙ አሥር አገር በቀል ዕውቀቶችን በመለየትና ጥናት በማካሄድ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየሠራ ይገኛል። ከተለዩት ጉዳዮች ውስጥ ሽምግልና ወይም ሀገር በቀል የግጭት አፈታት፣ ባህላዊ ዳኝነት፣ የባህል መድሃኒት፣ የአመጋገብ ሥርዓት፣ ክብረ በዓላት ይገኙበታል።

ተከሳሽ፣ ሽማግሌዎች ፊት ሲቀርብ የሚገባው ቃለ መሃላ ጠንካራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ ገና ከጅምሩ ተከሳሹ ጥፋቱን መፈጸሙን በማመን የሚሰጠው ቃል ፍጹም ለእውነት የቀረበና ለፍርድ ሂደቱም አጋዥ መሆኑን ይገልጻሉ። ፍርዱ በዳይና ተበዳይ ባሉበት በመጀመሪያው ሸንጎ ይሰጣል ዕርቅም ይወርዳል። ሁለቱም ወገኖች ሁለተኛ ጠብ ላለመግጠም መሃላ በመግባት ቂማቸውን አራግፈው ይሄዳሉ። ይህንን መሃላ አፍርሶ በድጋሚ ወደ ግጭት የሚገባ አካል በገባው ቃልና በአካባቢው ባህላዊ ዕሴት መሠረት ከማንኛውም ማኅበራዊ ግንኙነት እንዲገለል የሚደረግ በመሆኑ ሁሉም የሽማግሌዎችን ቃል አክብሮ ለሚሰጠው ፍትህ ተገዥ ይሆናል።

ባህላዊ የግጭት አፈታት የፋይል ምርመራ የሌለበት፣ ቀጠሮ የማይሰጥበት፣ በአካባቢው



16

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በቅርበት የሚገኝና ምልልስ የሌለበት በመሆኑ ጊዜን ይቆጥባል። ምንም አይነት ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑ ደግሞ ማኅበረሰቡ ያለምንም ስጋት የሚሳተፍበትና ርትዕ የሆነ ፍትህ የሚያገኝበት ሥርዓት መሆኑን ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ የጠቀሱት።

ሰዎች ወደፀብ የሚገቡት መከባበር ሲጠፋና ክብራቸው ሲናቅ እንዲሁም ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት ሳይቻል ሲቀር መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ ታናሽ ታላቁን ካከበረ፣ አንዱ የሌላውን መብት ካልጣሰ፣ ግጭት አይፈጠርም። በመከባበር ባህል ላይ አበክረን ከሠራን አገራችንን ወደምንመኝላት ደረጃ እናሸጋግራታለን ለዚህ ደግሞ ሁላችንም ሰላምን ማቀንቀን፣ ማጽናትና ለሰላም መዘመር አለብን ብለዋል።

የኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ተቋም (IES) መጻሕፍት እና የኢትዮጵያ የፍትህና ህግ ምርምር ኢንስቲትዩት ያሳተማቸው “Customary Dispute Resolution Mechanisms in Ethiopia” ከተሰኙ ጥናታዊ ሰነዶች የተወሰዱና የቱባው ባህላችን ነጸብራቅ ከሆኑ ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎቻችን እና ከማይዳሰሱት ቅርሶቻችን መካከል ጥቂት ማሳያዎችን ስናነሳ፤ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ለዘመናት የቆየ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት ሲሆን፣ ግጭቶችን ለመፍታት እንደ ጃርሱማ (Jaarsummaa)፣ ሲንቄ



17

(Siinqee) እና ጉማ (Gumaa) ያሉ ውጤታማ ዘዴዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ። በአማራ ሕዘቦች ዘንድ በሽማግሌዎች በሚመሩና “የአባት አገር ህግ” በሚባሉ ባህላዊ ደንቦች ላይ ተመሥርቶ ግጭቶች የሚፈቱበት አንዱ ዘዴ ነው። የጉራጌ ማኅበረሰብ እንደ ሴራ እና ጎርደና ያሉ ባህላዊ መተዳደሪያ ደንቦች ከፍተኛው የፍትህና የግጭት መፍቻ ተቋም አድርጎ ይጠቀማል። የሲዳማ ሕዝቦች ከቀላል የቤተሰብ ግጭት እስከ ነፍስ ግድያ ያሉ ጉዳዮችን በሸንጎ የሚፈታበት ጥንታዊ ሥርዓት አፍኒን ይሰኛል።

ሌላው ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ በጋሞ ብሔረሰብ ዘንድ አባቶች እርጥብ ሣር ይዘው የሚሰየሙበትና ማንኛውም አይነት ችግር የሚፈታበት ታላቅ የዕርቅ

ሥነ-ሥርዓት ድቡሻ ነው። የሀላባ ብሔረሰብ ጉዳዮችን እንደየክብደታቸው የሚያይበትና በመተዳደሪያ ደንቡ (ሴራ) መሠረት የሚፈታበት ዘዴ ኦገት ይባላል። ዊርኩር-የአኙዋክ ብሔረሰብ ለዘመናት ሲሰራበት የቆየ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ ነው። ኢናሽማ በቦሮ-ሺናሻ ማኅበረሰብ ዘንድ በሽማግሌዎች የሚመራና ቤተሰባዊም ሆነ ግላዊ ግጭቶች በሽምግልና የሚፈታበት መንገድ ነው።

በጉራጌ እና በሲዳማ ማኅበረሰቦች ዘንድ “ሴራ” ወይም “የጎርደና ሴራ” እና “ዋሽ ዚግባ ሴራ” በመባል የሚታወቁ የባህል ህጎች እና የሽምግልና ምክር ቤቶች አሉ። እነዚህ ምክር ቤቶች እንደ መሬትና የድንበር ጉዳዮች ያሉ ግጭቶችን በሽማግሌዎች አማካይነት ይፈታሉ። ይህ በከምባታና በሌሎች የደቡብ ክልል አካባቢዎች የሚገኝ ባህላዊ ሥርዓት ማኅበራዊ ትስስርን ከማጠናከር ባሻገር ግጭቶችን የመፍታት አቅም አለው።

እነዚህን እንደ ማሳያ አነሳን እንጂ በመላ ሀገሪቷ በሁሉም አቅጣጫዎች ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ለሚከሰቱ ግጭቶች እልባት በመስጠት አንድነትን ለማጽናት ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ። ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ ለማኅበራዊ አንድነት እና ለፍትህ ተደራሽነት ያላቸው ሚና ከፍተኛ ስለመሆኑም ቀደም ሲል ከተጠቀሱት ምሣሌዎች መረዳት ይቻላል።

ዘመነኛውን ከቀደመው ለማጣመር

ዘመናዊው የግጭት መፍቻ ዘዴ በተጻፉ ህጎች የሚመራ እና በመደበኛው የመንግሥት መዋቅር ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ሀገር በቀሎቹ በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ እና ከትውልድ ወደ



18

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ትውልድ ሲተላላፉ የቆዩ መሠረታቸውም ያልተጻፉ ህጎች፣ ባህሎች እና ዕሴቶች ናቸው። በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙት ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎች የፍትህ ሥርዓቱን በእጅጉ እያገዙ ይገኛሉ።

በርካታ ጥናቶች እንዳመላከቱት የሁለቱን ስልቶች ጠንካራ ጎኖች በማቀናጀት መጠቀም ይመከራል። የዚህ መነሻው ዘመናዊው ሥርዓት ህጋዊ ዕውቅና ሲሰጥ፣ ባህላዊው ሥርዓት ደግሞ ዘላቂ ሰላምና ማኅበራዊ ዕርቅን በማውረድ ረገድ ትልቅ ድርሻ ያለው መሆኑ ነው። በሀገራችን ከ43 በመቶ በላይ የሚሆኑት አለመግባባቶች በባህላዊ መንገዶች እንደሚፈቱ ፍትህ ሚኒስቴር The Hague Institute for Innovation of Law-HIIL ከተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም ጋር ባካሄደው የፍትህ ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት አስታውቋል፡፡ ይህ የዘመናዊውን የህግ የበላይነት ከባህላዊው ዕርቅ ጋር ማቀናጀት ለዘላቂ ሰላም ያለውን ፋይዳ ያሳያል።

ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎችንና ዕውቀት ከዘመናዊው የምክክር መንገድ ጋር አጣምሮ መጠቀም በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ሁነኛ አማራጭ እንዲሁም መፍትሔ በመሆኑ ሰላም ሚኒስቴር እና ፍትህ ሚኒስቴር ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ከዘመናዊው የፍትህ ሥርዓት ጋር ለማቀናጀትና በህግ ዕውቅና እንዲያገኙ ለማድረግ በጋራ እየሠሩ ነው።

ሰላም ሚኒስቴር ኢትዮጵያዊያን ግጭቶችን በሀገር በቀል ዕውቀታቸው እንዲፈቱ የሚያስችል አጠቃላይ የሰላም ፖሊሲ ማዕቀፍ እያዘጋጀ ሲሀን፤ ፍትህ ሚኒስቴር በበኩሉ ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ከመደበኛው የህግ ሥርዓት ጋር ተደጋጋፊ ሆነው እንዲሠሩ ህጋዊ ዕውቅና ለመስጠት የሚያስችሉ ጥናቶችና የምክክር መድረኮችን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ከመደበኛው የፍትህ ሥርዓት ጋር ለማቀናጀትና ዕውቅና ለመስጠት በፍትህ ሚኒስቴር በኩል እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት ተደራሽነትን ለማስፋት፣ ወጪና ጊዜን ለመቆጠብ እንዲሁም የማኅበረሰቡን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ያለሙ ናቸው። የፍትህ ሚኒስትሯ ሃና ዓርአያሥላሴ እንደሚናገሩት፤ ኢትዮጵያ በባህላዊ ግጭት አፈታት ሥርዓት ዘመናትን የተሻገረ ታሪክ ባለቤት ብትሆንም እነዚህ የፍትህ ሥርዓቶች ተገቢውን የህግ ዕውቅና ሳያገኙ በመቆየታቸው ለመደበኛው ሥርዓት አጋዥ መሆን በሚገባቸው ልክ ሳይሠራባቸው ቆይተዋል።

ሚኒስትሯ አሁን መተግበር የጀመሩት ባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ትክክለኛውን ሥርዓትና መሠረታዊ መርሆዎችን ተከትለው ሊሠራባቸው እንደሚገባ፤ ተጋላጭ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ትኩረት በመስጠት ዕሴትን በማይሸረሽር መልኩ በቅንጅት ሊተገበሩ እነደሚገባ አስገንዝበዋል።

በቅርቡ በአድዋ ድል መታሰቢያ “የፍትሕ ተደራሽነት በአፍሪካ-2026” በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀ መድረክ የኢትዮጵያ የግጭት መፍቻ ባህላዊ ዕሴቶች መደበኛ የፍትህ ሥርዓቱን በማገዝ ለህግ የበላይነት መከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ያወሱትሚኒስትሯ፤ በኦሮሚያ ክልል ተግባራዊ የተደረገው ባህላዊ ፍርድ ቤት በሌሎች ክልሎችም እንደየማኅበረሰቡ ዕሴትና ሥርዓት ዕውቅና አግኝቶ ወደ ሥራ እየገባ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎች የዳኝነት ዕሴቶችን በጠበቀ መልኩ በሁሉም ክልሎች



19

ተግባራዊ እንዲሆኑና የማኅበረሰቡ አብሮነትና አንድነት እንዲጎለብት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው በትኩረት እየሠራ መሆኑን ያስታወቁት ሚኒስትሯ የክልሎችን ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት ለማስፋት በሚደረገው ጥረት ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግና በማኅበረሰቡ ዘንድ ቅቡልነት ያላቸው ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች ለዜጎች አፋጣኝ የፍትህ ምላሽ በመስጠት ለዘላቂ ሰላምና ዕርቅ ገንቢ ሚና እየተወጡ እንደሆነ አንስተዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ዕውቅና በተሰጣቸው የግጭት መፍቻ የማኅበረሰብ ዕሴቶች ከሶስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ጉዳዮች መስተናገዳቸውንም አክለዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በበኩሉ ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ከመደበኛው የፍትህ ሥርዓት ጋር ለማቀናጀትና ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነ ነው። ይህ ጥረት ፍትህን ተደራሽ ለማድረግና በፍርድ ቤቶች ላይ የሚታየውን የጉዳዮች ክምችት ለመቀነስ ያለመ ሲሆን፤ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሀገር በቀል ዘዴዎች ህጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖራቸውና ከመደበኛው የዳኝነት ሥርዓት ጋር እንዲጣጣሙ እየሠራ ይገኛል። የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ (ቁጥር 1234/2013) ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ መዋሉ ፍርድ ቤት መር ዕርቅን (Court-Annexed Mediation) በማካተት ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ከዘመናዊው የፍርድ ቤት ሥርዓት ጋር እንዲጣመር መሠረት ጥሏል።

ይህም በክልል ደረጃ ያሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን በማቋቋም ቀዳሚ ሚና እንዲጫወቱ እያገዘ ነው። ለአብነትም በኦሮሚያ ክልል ሰባት ሺህ የሚጠጉ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ተቋቁመው ከአንድ ሚሊዮን የበለጡ ጉዳዮችን በመፍታት የመደበኛ ፍርድ ቤቶችን ጫና እያቃለሉ ይገኛሉ። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለሆኑ 15 ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ህጋዊ ዕውቅና ሰጥቷል። ቀድሞ በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚታወቁትና ህጋዊ ዕውቅና የተሰጣቸው የግጭት መፍቻ ሥርዓቶች ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ በሚገኙ ከአራት ሺህ በላይ ቀበሌዎች ተግባራዊ ሆነዋል።

ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎችን ከዘመናዊው የፍትህ ሥርዓት ጋር ለማጠመር በሁለቱ ክልሎች የተጀመረው ሥራ አበረታች ነው። ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተደረገ እንቅስቃሴ የተገኘው ስኬት ለሌሎችም ተሞክሮ የሚሆን ነው። በአማራ ክልልም ጥሩ ጅማሮዎች አሉ፤ ሲዳማ እና ሌሎች ክልሎች ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን በህግ በማዋቀር ረገድ በዓርአያት ይጠቀሳሉ።

እነዚህ እንቅስቃሴዎችና ጥረቶች ቀላል የፍትሀ ብሔር ክርክሮችና ወንጀሎች በባህላዊ ሥርዓቱ እንዲታዩ በማድረግ መደበኛ ፍርድ ቤቶች ትኩረታቸውን ውስብስብና ከባድ ወንጀሎች ላይ እንዲያደርጉ ያስችላሉ። ተሞክሮዎቹን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ትልቁ የቤት ሥራቸው አድርገው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል።

ከፍሬው ለመቋደስ

ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ለዘመናት ሰላምን ለማስፈን እና ዕርቅ ለማውረድ ሲያገለግሉ የቆዩ የኢትዮጵያዊያን የጥበብ ምንጮች ናቸው። እነዚህን ዘዴዎች በመጠቀም አለመግባባቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የተለያዩ ተግዳሮቶች ማጋጠማቸው አልቀረም። እንደ



20

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

“ሽምግልና”፣ “እርቅ”፣ “ጉማ” እና የመሳሰሉት ሥርዓቶች ማኅበራዊ ትስስር እንዳይላላ በማድረግ ረገድ ትልቅ አበርክቶ ቢኖራቸውም እነዚህ ጠቃሚ ዕሴቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸሩና እንደ ኋላቀር የፍትህ ሥርዓት እየታዩ ነው።

የከተሞች መስፋፋት ይዞት የሚመጣው ከተሜነትና የምዕራባዊያን ባህል ተጽዕኖ የማኅበረሰቡን ጥብቅ ትስስር እያላላው ነው። በተለይ ወጣቱ ትውልድ ለባህላዊ ዕሴቶች ያለው ክብር እየቀነሰ በመምጣቱ የሽማግሌዎችን ምክርና ተግሳጽ የመቀበል ዝንባሌው ዝቅተኛ ሆኗል። ይህም በትውልድ ቅብብሎሽ የመጡና የኅብረተሰቡን ማኅበራዊ ትስስር ሲያጠብቁ የኖሩት የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ተቀባይነት እንዳያገኙ ምክንያት ሆኗል።

በሀገሪቷ መደበኛ የህግ ሥርዓት እና የፍትህ አካላት መስፋፋት ለችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ወሳኝ ቢሆንም መደበኛው ህግ ከባህላዊው አሠራር ጋር የማይጣጣምባቸው ሁኔታዎች መኖራቸው ነው። ይህ ሁኔታ ሰዎች በባህላዊው ሥርዓት የሽማግሌዎች ውሳኔ ላይ ዕምነት እንዲያጡ ያደርጋል።

አብዛኞቹ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች በወንዶችና በዕድሜ በገፉ የሀገር ሽማግሌዎች ላይ ብቻ የተመሠረቱ በመሆናቸው ምክንያት የሴቶችና የወጣቶችን ድምጽ በበቂ ሁኔታ ማስተናገድ አለመቻሉ፣ ሂደቱን አካታችነት የጎደለው አድርጎታል። ይህም በዘመናዊው ማኅበረሰብ ዘንድ የፍትሃዊነት ጥያቄ እንዲነሳበት ምክንያት ሆኗል። የባህላዊ ግጭት አፈታት ዘዴዎች ውጤታማ እንዳይሆኑ ካደረጓቸው ምክንያቶች አንዱ ከመንግሥት የሚሰጣቸው መደበኛ ዕውቅና እና ድጋፍ አነስተኛ መሆን ነው። የሚሰጡ ውሳኔዎች በመንግሥት የጸጥታ እና የህግ አካላት ካልታገዙ አስገዳጅነታቸው ደካማ ይሆናል። ለሽምግልና ሂደቶች የሚያስፈልጉ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፎች ስለማይመደቡ ሥራው በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዲሆን ያደርገዋል። በባህላዊው ዘዴ ሽማግሌዎች የሚሰጧቸው ውሳኔዎች በህግ ፊት ጥበቃ ካልተደረገላቸው ግጭቱ ዳግም ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት እንዲያመራና ስምምነቱ እንዲፈርስ በር ይከፍታል።

ባህላዊ ዕውቀቶች በአብዛኛው በቃል የሚተላለፉ መሆናቸውና እንደ ዘመናዊው ህግ በጽሁፍ ተመዝግበው አለመቀመጣቸውም ወጥ የሆነ አሠራር እንዳይኖር በማድረግ ለትውልድ ለማስተላለፍ አስቸጋሪ ሁኔታን ይፈጥራል። ስለሆነም በዘመናዊ እና በሀገር በቀል ዕውቀቶች በአንድነት በመገልገል ከሚገኘው ፍሬ ለመቋደስ እነዚህ ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል።

ሲጠቃለል

ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ከዘመናዊው የፍትህ ሥርዓት ጋር በማስማማትና አካታች በማድረግ ለዘላቂ ሰላም መጠቀም በራሱ የኅብረተሰቡን ችግር በቅርበትና በፍጥነት ለመፍታት ዓይነተኛ ሚና አለው። ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ያላቸውን ጥልቅ ማ`በራዊ ዕሴት ከዘመናዊው የህግ ሥርዓት ጋር አሰናስሎ መጠቀም አማራጭ የሌለው የመፍትሔ አቅጣጫ ነው። የዘመናዊው ህግ ዋነኛ ትኩረት ጥፋተኛን መለየትና ተመጣጣኝ ቅጣት መስጠት (Retributive Justice) ሲሆን ይህም ግጭቱን በህግ ቢቋጨውም በባላንጣዎች መካከል ያለውን የጠብ ስሜት



21

ግን ላያስወግደው ይችላል። ባህላዊ ሥርዓቶች ትኩረታቸው የተበላሸ ግንኙነትን በመጠገን፣ ይቅርታን በማውረድና ማ`በራዊ ትስስርን ማጠናከር (Restorative Justice) ላይ ነው።

ሀገር በቀሉን ከዘመናዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ጋር ማቀናጀት በራሱ የተሟላ ፍትህን ለማረጋገጥ ያግዛል። መደበኛው ህግ ወንጀለኛው በህግ ፊት ተጠያቂ የሚሆንበትን ሂደት ሲያመቻች፤ ባህላዊው ዕርቅ ደግሞ ተጎጂ ተክሶ ከበዳዩ ጋር በሰላም እንዲኖር ያግዛል። የሁለቱ ሥርዓቶች መቀናጀት ግጭቱ ለቀጣይ ትውልድ እንዳይተላለፍና የቂም በቀል ስሜት እንዳይቀጥል ያደርጋል።

የግጭት መፍቻ ዘዴዎቹ ተሰናስሎ መሄድ ፍትህን ተደራሽና ቀልጣፋ ያደርገዋል። መደበኛ ፍርድ ቤቶች ባሉባቸው የሰው ኃይል እና የበጀት እጥረት ምክንያት ጉዳዮች ለዓመታት ሊጓተቱ ይችላሉ። በዚህ ረገድ ባህላዊ ዘዴዎችን እንደ መጀመሪያ የፍትህ እርከን መጠቀም የፍርድ ቤቶችን የሥራ ጫና ከመቀነሱም በላይ ሕዝቡ በራሱ ቋንቋ፣ ባህልና አካባቢ በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሄ እንዲያገኝ ይረዳል፤ የውሳኔዎችንም ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ ያስችላል። ባህላዊ ሽምግልናዎች በመንግሥት ዕውቅና እና የህግ ድጋፍ ሲታጀቡ የሚያሳልፏቸው ውሳኔዎች ይከበራሉ፤ ግለሰቦችም ባህላዊ ብቻ ሳይሆን ህጋዊ ግዴታም ስለሚኖርባቸው ለስምምነቱ ተገዢ ይሆናሉ።

የዘመናዊው ህግ “አስገዳጅነት” እና የባህላዊው ሥርዓት “ርህራሄና ዕርቅ” ሲሰናሰሉ ግጭቶች ከመሠረታቸው እንዲፈቱ ያደርጋሉ፤ ይህ ውህደት ለሀገር ሰላም፣ ለፍትህ መከበር እና ለማኅበራዊ ዕድገት ወሳኝ መሰረት ነው። ስለሆነም መንግሥት ባህላዊ ዘዴዎችን በህግ ማዕቀፍ ውስጥ በማካተት፣ በቂ ድጋፍ በመስጠት እና ለሴቶችና ለወጣቶች ተሳትፎ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የሁለቱን ዘዴዎች ቅንጅት ማጠናከር ይጠበቅበታል።

የአንድ ሀገር ሕዝቦች ብዝሃ ባህል የማንነት መገለጫዎች ለዜጎች ታላቅ ሀብትና የማ`ራዊ ስብዕና መሠረቶች ናቸው። ባህል የቀድሞውን ሥልጣኔ እንደፈጠረ ሁሉ የዛሬውን የልማት ጥረትም ማገልገል ይጠበቅበታል፤ የነገውን ትውልድ የመቅረጽ ሚናም ይኖረዋል። እነዚህን ከጥፋት ለመታደግ ማጎልበትና ለዘለቄታዊ ልማት መጠቀም አስፈላጊ ነው። ሀገራዊ ዕሴቶች ያላቸውን እምቅ አቅም ድህነትን ለማሸነፍ ለተጀመረው ትግል እንዲውል ማድረግም ይገባል።

ኢትዮጵያ በርካታ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶቿን ለዓለም በማስተዋወቅ በዓለም ቅርስነት አስመዝግባለች። ባለፉት ዓመታትም ሀገር በቀል ዕውቀቶቿን የሚያጸባርቁ ባህላዊ ክንዋኔዎችን በማስመዝገብ ዓለም እንደ ሀብቱ እንዲጠብቃቸው፣ እንዲከታተላቸው በር ከፍታለች። እንደ የጥምቀት እና የመስቀል በዓላት፣ የገዳ ሥርዓት፣ የኮንሶ የእርሻ ሥራ እና ሌሎችም ሁሉ ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ከአንድ አካባቢ ሀብትነት ተሻግረው ለዓለም እንዲተዋወቁ መሥራት የግድ ይላል።

አበው “በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ” እንዲሉ፤ በአንድ በኩል እነዚህ ባህሎችና ሀገር በቀል ዕውቀቶች ተጠብቀው እንዲዘልቁ መልካም አጋጣሚን ይፈጥራል፤ በሌላ በኩል የዓለምን ትኩረት በመያዝ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ጎብኚዎች የሚገኘውን ገቢ በማሳደግ ለኢኮኖሚው የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት ያስችላል። እነዚህን የማይዳሰሱ ቅርሶች መንከባከብ፣ ማስተዋወቅ እና ማስቀጠል የኢትዮጵያዊያን የቤት ሥራ ነው።



22

ቴክኖሎጂ

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

አሻጋሪው ድልድይ …



23

በፍቅርተ ባልቻ

የሰው ልጅ ጠያቂ እና ለጥያቄዎቹ መልስ ፈላጊ ፍጥረት ነው፤ ይህ ባህሪው ከሌሎች በተለየ ተፈጥሮውን እና አካባቢውን መረዳት አስችሎታል። ከመረዳት ባሻገርም ተፈጥሮ ያላትን ኃብት ለእርሱ በሚያስፈልገው መልኩ ቀይሮ እየተጠቀመበት ይገኛል። ተፈጥሮን ለማወቅና ለመጠቀም በሚያደርገው ጥረትም ከምድር አልፎ እስከ ህዋ ዘልቋል። በተለይ በሠለጠነው ክፍለ ዓለም የሰው ልጅ እውቀቱም፣ ፍላጎቱም ከማደጉ ባሻገር የምርምር አድማሱ እጅጉን ሰፍቷል። ይህ ጠባዩ ኑሮውን ለማሻሻል እና ለማቅለል በእጅጉ ጠቅሞታል።

ይህን የሰው ልጅ ባህሪይ እና ጠባይ የተረዱት የዓለም አገራት



24

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ችሎታውን ወደ ውጤት እየቀሩት ነው፤ አገራቱ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮችን በመሥራት አዳዲስ ግኝቶችን እነሆ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። አገራቱ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ግኝቶችን በማፍለቅና በመጠቀም ኑሮን ቀላል ከማድረግ ባለፈ በዘርፉ ተወዳዳሪና የዘመነ አሠራር በመዘርጋት ዜጎቻቸውን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው።

በተለይ በህዋ (space) ሣይንስ እና ጂኦስፓሻል (Geospatial) መስክ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የሰው ልጆችን ሕይወት ከማቅለል አልፈው የኢኮኖሚያዊ ዕድገት መለኪያና ማሳያ እየሆኑ ነው። የዓለም መንግሥታት መስኩን አቅማቸውን ለማሳየት ብሎም በፖለቲካ መስክ ያላቸውን የበላይነት ለማስቀጠልና የዓለምን ፖለቲካ የሚዘውሩ አገራትን ለመቀላቀል እንደ አንድ ስልት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ዘግይታም ቢሆን በመስኩ በሚሠሩ ሥራዎች የምታገኘውን ጥቅም በመገንዘብ የህግ ማዕቀፎችን አዘጋጅታለች፤ ሥራውን የሚመራ ተቋምም መሥርታለች፤ ይህን ተከትሎ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው። በዚህ ጽሑፍ ኢትዮጵያ በመስኩ ከዓለም አገራት ተርታ ለመሰለፍ



25

ምን ጉዳዮች ላይ መሥራት ይጠበቅባታል የሚለውን የምንቃኝ ይሆናል። ዝለቁ!

ስፔስ ሣይንስ እና ጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ

የህዋን፣ የምድርንና አየር ላይም ፎቶግራፎችን በማንሳት፤ በምድር ላይ የቅየሳ መሣሪያዎች አማካኝነት እንዲሁም በህዋ ላይ የስፔስ ቴክኖሎጂን (ሳተላይትን) በመጠቀም መረጃዎች የሚሰበሰቡትና ለውሳኔ የሚረዱ መረጃዎች የሚገኙት በስፔስ ሣይንስ በሚከናወኑ ተግባራት አማካኝነት ነው። ስፔስ ሣይንስ በጥቅሉ በህዋ ላይ ያሉ ነገሮችን ያጠናል።

የስፔስ ሣይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባርን ለመወሰን በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀው ደንብ ቁጥር 511/2014 ‘ስፔስ‘ን “ከመሬት ከባቢያዊ አየር ውጪ ባሉት የተፈጥሮ አካላት እና ክስተቶች ላይ ትኩረት የሚያደርግ የሣይንስ እና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ነው” ሲል ተርጉሞታል።

ደንቡ ስለ ‘ጂኦስፓሻል‘ ምንነት ሲያብራራ “መሬት እና በመሬት ላይ ያሉ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አካላት መገኛ ጋር የተያያዘ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊና ፖለቲካዊ ሁነቶችን የሚተነትን እና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያስችል የሣይንስ፣ የቴክኖሎጂና የመረጃ ዘርፍ ነው” በማለት ገልጾታል።

የስፔስ እና ጂኦስፓሻል መስክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለተለያዩ ጥቅሞች እና ዓላማዎች እየዋለ ነው። በዓለም ላይ ያሉ አገራት “ህዋ እንዴት ተፈጠረ? በውስጡስ ምን አለ?” ከሚሉ ጥያቄዎች በመነሳት ሌሎችንም በማስከተል ምላሽ የሚሰጡ ጥናትና ምርምሮችን በመሥራት፣ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማመንጨት ለሰው ልጅ ጥቅም እንዲውል ሰፊ እና ሁለገብ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው።

የስፔስ ሣይንስና ቴክኖሎጂ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማኅበራዊና ምጣኔ ኃብት ዕድገት፣ ለአካባቢ ሀብት ጥበቃና አስተዳደር፣ ለአደጋ መከላከል ሥርዓት፣ ለሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ፣ ለስፔስ ምርምርና ግኝት አልፎ ተርፎም በስፔስ ዘርፍ ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ጥቅም ላይ ውሏል። ፈጣን የምጣኔ ሀብት ዕድገት በማስመዝገብ ላይ ያሉትን ጨምሮ በማደግ ላይ ባሉ በርካታ አገራትም ስፔስ ወሳኝ እየሆነ ስለመምጣቱ የኢትዮጵያ ስፔስ ፖሊሲ ሰነድ ይጠቁማል።

የኢትዮጵያ ስፔስ ሣይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ፀሀይ እንደሚገልጹት፤ ዘርፉ እጅግ በርካታ እና ሁለገብ ተግባራት የሚከናወኑበት ነው። ከእነዚህ መካከል በግንኙነት ሳተላይት (communication satellite) አማካኝነት እየተሠራ ያለው አንዱ ነው። ሳተላይቶቹ በምድር ላይ ያለ ሰው ከህዋ ጋር ግንኙነት እንዲኖረው የሚያገለግሉ ናቸው። የቴሌቪዥን እና ሬድዮ ስርጭቶች የሚሠሩት እነዚህን ሳተላይቶች በመጠቀም ነው።

ኃላፊው ያነሱት ሌላው አገልግሎት ምድር ላይ ያለን መገኛ ቦታ (exact location) ለማወቅ ማስቻላቸውን ነው። ካርታዎችን የማዘጋጀት እንዲሁም የቅየሳ ሥራዎችን መሥራት የተቻለው ህዋ ላይ ያሉ ሳተላይቶችን በመጠቀም ነው። “በዓለም ላይ ያሉ አገራት የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው



26

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በእነዚህ ቴክኖሎጂዎች ላይ የተመሰረተ ሆኗል” ያሉት ኃላፊው “ተጨማሪ ግኝቶች ላይ ለመድረስ ሳተላይቶችን እያስወነጨፉ ይገኛሉ” በማለት የዓለም አገራትን እንቅስቃሴ ገልጸውታል።

ሳተላይቶችን መገኛን ከማወቅ ባለፈ የአየር ንብረት ትንበያ በመሥራት እየተጠቀሙባቸው ነው። የአየር ጠባዩ በሚቀጥለው ሣምንት፣ ወር፣ ዓመት ምን ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ መተንበይ ተችሏል። የልማት ዕቅዶችን ለማዘጋጀት፣ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋን ለመከላከልም ሥራ ላይ እየዋለ ነው። ይህ ቴክኖሎጂ በሰው ልጅ ሕይወት እና በንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው።

አቶ በላቸው በዓለም አገራት ሥራ ላይ የዋሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንም አብራርተዋል። እንደ ማሳያም በአሜሪካዊያን የተመረተውን የጂፒኤስ (Global Positioning System - GPS) ቴክኖሎጂ ያነሱ ሲሆን፤ ይህ ቴክኖሎጂ የሰው፣ የዕቃ፣ የቦታ፣ ወዘተ … ትክክለኛ መገኛ የሚያመለክት እንደሆነ ጠቁመዋል። ከዚህ ቴክኖሎጂ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ግልጋሎት የሚሰጡና የተለያየ መጠሪያ ያላቸው ቴክኖሎጂዎች በሩሲያ፣ በቻይና እና በአውሮፓ ተመርተው ሥራ ላይ ውለዋል።

እነዚህን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ግንባታዎችን በመደገፍ፤ የመርከቦችን፣ የአውሮፕላኖችን፣ የሰዎችን ጉዞ በማስተካከል፣ ካርታዎችን በማምረት አካባቢዎችን የሚያመላክቱ መረጃዎች ለማግኘት አስችለዋል። ይህ ቴክኖሎጂ በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ሥራ ላይ ውሏል።

በርካታ አገራት ዘርፉን ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በተለይም ለወታደራዊ ሥራዎች እያዋሉት እንደሆነ ይታወቃል። መስኩ ከወታደራዊ እንቅስቃሴ እና የአገር ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ አንጻር ያለውን ጥቅም አያሌ መሆኑ ወታደራዊ እንቅስቃሴን ለመምራት በእጅጉ የሚጠቅም ቴክኖሎጂ ስለመሆኑ አስረጂ ነው።

በኢትዮጵያ - ከየት ወዴት?

የታሪክ መጻሕፍትና ተመራማሪዎች እንደሚመሰክሩት በምንኖርበት መሬት ጥንት ገናና ሥርወ መንግሥት ከነበራቸውን በሥልጣኔ እጅግ መጥቀው ከነበሩት ጥቂት የዓለማችን አገራት ኢትዮጵያ አንዷ ነች። “አገሪቷ ለብዙ ሺህ ዓመታት የዘለቁ የሥልጣኔዋ ማሳያ የሚሆኑ የራሷ ፊደል፣ የዜማ ሥልት፣ የዘመን አቆጣጠር፣ የኪነ- ህንጻ አሠራር፣ የሥዕል አሳሳል ጥበብ፣ ወዘተ… ያላት ስትሆን በተጨማሪም በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ጥንታዊ የብራና መጽሐፍትን ይዛ የኖረች አገር ናት” ሲል በመጋቢ ሀዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ እና በዶ/ር ጌትነት ፈለቀ ተዘጋጅቶ በ2011 ዓ.ም ለንባብ የበቃው አንድሮሜዳ መጽሐፍ ኢትዮጵያ በመስኩ የነበራትን የመጠቀ ዕውቀት ወደኋላ መለስ ብሎ በመመርመር ከትቦታል።

በጥንት ጊዜ ኢትዮጵያዊያን የከዋክብት ጥናት ያደርጉ እንደነበር፤ ህዋ እና ከዋክብትን በተለይም ሥርዓተ ፀሐይን መረዳት ባይቻል ኖሮ የዓመቱን የወቅቶች መፈራረቅ እና የቀን መቁጠሪያ ቀመር መሥራት አይቻልም ነበር። እነዚህ እንደ ሥልጣኔ ማሳያ የተጠቀሱ ነጥቦች የምርምር ውጤት ቢሆኑም የቀደመውን ትውልድ የዕውቀት እና የምርምር አካሄድ አስጠብቆ መጓዝ አልተቻለም። ስለሆነም ከአጀማመሩ አንጻር በአግባቡ አልተጠቀምንበትም ቢባል ማጋነን አይሆንም።



27

ከቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴ አንጻር ስናየው በተቋም ደረጃ ሥራው መመራት ስለመጀመሩ የሚጠቀሱ የተለያዩ መነሻዎች አሉ። በ1946 ዓ.ም “ኢትዮ-አሜሪካ ማፒንግ ሚሽን” የተሰኘ ቡድን ተቋቁሞ በጋራ ለመሥራትና ጉዳዩን ለመረዳት እንቅስቃሴዎች መደረጋቸው በቀዳሚነት ይነሳል። ይህን ተከትሎ የካርታ አነሳስ እና የጂኦግራፊ ኢንስቲትዩት ተመስርቶ ከ1946 ዓ.ም እስከ 1965 ዓ.ም ድረስ ዘልቋል።

“ይኸው ተቋም በ1966 ዓ.ም የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ባለሥልጣን፤



28

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በ1998 ዓ.ም የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲ ተባለ። በ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጂኦስፓሻል ኤጀንሲ ተብሎ እንደገና ተቋቋመ። በ2011 ዓ.ም የጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የሚል ስያሜ ተሰጠው” ሲሉ አቶ በላቸው ታሪኩን ወደኋላ መለስ ብለው ያብራራሉ።

ኢትዮጵያ ውስጥ በስፔስ ዙሪያ እንቅስቃሴ ማድረግ የተጀመረው በ1950ዎቹ (እ.አ.አ) ሲሆን፤ እንደ የሥነ ፈለክ ቅኝት፣ ሳተላይት መከታተልና ፎቶግራፍ ማንሳት እንዲሁም የስፔስ መረጃ ልውውጥን



29

የመሳሰሉ ተግባራት ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር በጅምር ደረጃ ይከናወኑ ነበር። በ1960ዎቹ እና በ1970ዎቹ (እ.አ.አ) መጀመሪያ ላይ ካሳየው መሻሻል አንጻር ሲታይ እስከ 2004 (እ.አ.አ) ድረስ የጎላ ዕድገት ሳያሳይ መቆየቱን የስፔስ ፖሊሲው ጠቁሟል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና መምህራን በአንድነት የስፔስ ሣይንስ ማህበር (Ethiopian space science society) መሥርተዋል፤ ይህም በቀጣይ ለተወሰዱ የለውጥ እርምጃዎች እንደ እርሾ ያገለገለ ነው። የማኅበሩ መቋቋም በአገሪቷ የስፔስ ዘርፉን ዕድገት አነቃቅቷል።

የኢትዮጵያ ስፔስ ሣይንስ ማኅበርን እንቅስቃሴ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሸጋገር በ2013 (እ.አ.አ) 32 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች፣ አንድ የግል ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሣይንስ ማኅበር ቦርድን ባካተተ ስብስብ የሚተዳደርና የስፔስ ፕሮግራም መንደፍ፣ ከስፔስ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ አተገባበር ጋር በተያያዘ ሙያዊ ክህሎትና አቅም መገንባትን ዓላማው ያደረገ የመጀመሪያው የምርምር ተቋም (የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማዕከል) ተቋቁሟል።

መስኩ ለአገሪቷ ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑ ግንዛቤ በመያዙ በ2008 ዓ.ም የኢትዮጵያ ስፔስ ሣይንስ እና የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተቋቋመ። በ2014 ዓ.ም የመንግሥት ተቋማት እንደገና ሲደራጁ የጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት እና የስፔስ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተዋህደው የስፔስ ሣይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ተመሰረተ። ይህም ሁለቱ ተቋማት ወደ አንድ የመጡት ያላቸውን ሰፊ የሰው ኃይል እና ኃብት በመጠቀም የአገሪቷን ልማት መደገፍ የሚያስችል አደረጃጀት መሆኑ ታምኖበት ነው።

በዚህ ሂደት እና ጉዞ የተለያዩ ሥራዎች ሲሠሩ መቆየታቸውን ያስታወሱት አቶ በላቸው መረጃዎችን መሰብሰብ፣ ካርታዎችን ማዘጋጀት እና የሳተላይት መረጃዎችን ለመጠቀም የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየቱን አንስተዋል። ሁለቱ ተቋማት ከተዋሀዱ በኋላ ባከናወኗቸው የተለያዩ ተግባራት ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በመስኩ የሚከናወነው ተግባር አዲስ በመሆኑ ዓለም ከደረሰበት ደረጃ ላይ ለመድረስ፣ መዘግየታችንን ለማካካስ ሊያሠራ የሚችል ከባቢ ለመፍጠር፣ መንገድ በማመላከት ረገድ የህግ ማዕቀፎች አይተኬ ሚና እንዳላቸው አጽንኦት በመስጠት አስተያየታውን ሰንዝረዋል አቶ በላቸው ናቸው። ኢትዮጵያ ከየት ተነስታ ወዴት እየተጓዘች እንደሆነና በምን መልኩ ብትሠራ ውጤታማ እንደምትሆን የሚያሳይ የስፔስ ፖሊሲ ሰነድ ተዘጋጅቶ በ2011 ዓ.ም ሥራ ላይ መዋሉም በዚህ ረገድ እንደ ትልቅ ውጤት የሚወሰድ ነው። በተጨማሪም ሊያሠሩ የሚችሉ አዋጆችና ደንቦች ተዘጋጅተው ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱ ለተገኙት ስኬቶች መንገድ አበጅተዋል።

የፖሊሲው ማጠንጠኛዎች

የስፔስ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ግስጋሴ ለየትኛውም አገር ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገትና ብልጽግና አስተዋጽኦ ያበረክታል። ከምንም በላይ ዓለም አቀፉ የስፔስ ፕሮግራም የሰው ልጆች ያላቸው ዕውቀት ጉልህ ዕድገት እንዲያሳይ ያስቻለ ከመሆኑም በተጨማሪ መላውን ዓለም ተጠቃሚ ያደረጉ አንኳር የቴክኖሎጂ ዕድገቶች የተገኙበት ነው።



30

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ይህም በዚህ ዘመን የሚገኘው መላው ኅብረተሰብ ምጣኔ ሀብታዊና ማኅበራዊ መሻሻሎች እንዲያገኝ በማስቻል ለመላው ዓለም ጠቀሜታውን አበርክቷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ውጤታማ የስፔስ ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግ እንዲቻል የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። የስፔስ ፖሊሲ በማዘጋጀት ሂደት ዐቢይ ተግዳሮቶችንና ችግሮችን ለይቶ ማወቅ የሚያስችል ጥናት በአገር አቀፍ ደረጃ ተካሂዷል። የዳሰሳ ጥናቱን መነሻ በማድረግ የስፔስ ፕሮግራምን በማጎልበት በሚገባ ጥቅም ላይ ለማዋል መሣሪያ ሆኖ ያገለግል ዘንድ የኢትዮጵያ የስፔስ ፖሊሲ ተቀርጿል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ያሉም ሆኑ ያደጉ አገራት ብሔራዊ የስፔስ ፕሮግራም መንደፍ አገራዊ የዕድገት ዕቅዶችን ለማሳካትና የሰውን ልጅ ደህንነት ለማሻሻል ወሳኝ ስልት እንደሆነ ይገነዘባሉ። የኢትዮጵያን ጂኦ-ፖለቲካዊ፣ ማኅበረሰባዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ፤ የስፔስ ልማት አገራዊ ዕድገትን ለማስቀጠልም ሆነ ብሔራዊ ሉዓላዊነትን ለማስከበር የሚሰጠው ጥቅም የላቀ ግምት የሚሰጠው ስለመሆኑ በፖሊሲው ተመላክቷል።

ፖሊሲው አገሪቷ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂና በምጣኔ ሀብት መስክ ቀጣይነት ያለው ዕድገት እንድታስመዘግብ፣ ብሔራዊ የስፔስ ጉዳዮች ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግባቸውን መዋቅሮች ለማዘጋጀት እንዲሁም የአገርን ብሔራዊ ጥቅሞችና ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ የሚኖረውን ሚና ለመተለም፣ የስፔስ ፕሮግራም የራሱን አስተዋጽኦ የሚያደርግበት አመራር መስጠትን ዓላማው አድርጎ የተቀረጸ ነው።

ፖሊሲው የተዘጋጀው ምድርን ከስፔስ ላይ ሆኖ ለማጥናት እና ስፔስን ከምድር ላይ ሆኖ ለመመርመርና ለልማት ለማዋል በሚያስችሉ ዕይታዎች ነው። የመጀመሪያው ዕይታ ለተለያዩ ልማት ዓላማዎች ሊውሉ የሚችሉ የሳተላይት ምስሎች ማግኘትን እንዲሁም የተለያዩ ሳተላይቶችን አቀናጅቶ በመጠቀም የመረጃ ልውውጥና የስርጭት አገልግሎቶች ምቹ እንዲሆኑ ማድረግን ያካትታል። የፖሊሲው እና ሌሎች የህግ ማዕቀፎች በመስኩ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለማሳለጥ ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል፤ የተገኙ ስኬቶችም አበረታች ናቸው።

ፖሊሲውን ለማሻሻል የታሰበ ነገር ይኖር ይሆን? በሚል ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ “እስከ አሁን ተከትለን እየሄድን ያለነው ቀደም ሲል የተዘጋጀውን ፖሊሲ ነው። የስፔስ ፖሊሲ ለብቻው ጂኦስፓሻል ላይ ስፓሻል ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ለየብቻ ነበሩ፤ እነዚህን ወደ አንድ በማምጣት ማሻሻያ እየተሠራ ነው” ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩት ፖሊሲዎች ዓለም አቀፋዊ እና ሀገራዊ ሁኔታውን በማጤን የተዘጋጁ ስለሆኑ ማሻሻያዎቹ መጪውን ጊዜ ታሳቢ ያደረጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል። የፖሊሲው ማሻሻያ ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጅቶ በባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጥበት እየተሠራ ሲሆን በዚህ ዓመት ይጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

ውጥን በተግባር ሲገለጥ

በስፔስ ሣይንስ እና ጂኦስፓሻል መስኮች



31

ምርምር ማካሄድ፣ ሥልጠና መስጠት፣ የሰው ኃይል ልማት፣ መረጃዎችን በመተንተን ለውሳኔ ሰጪዎች እና ለፖሊሲ አውጪዎች ማቅረብ፣ የቴክኒክ ድጋፍ ማድረግ፣ ማማከር፣ የሳተላይት ልማት፣ ሳተላይትን የማምጠቅ እና ከሚገኘው መረጃ መጠቀም የመሳሰሉ ሰፊ ኃላፊነትና ተግባራትን ይዞ የተቋቋመው የስፔስ ሣይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት፤ የስፔስ እና ጂኦስፓሻል ሣይንስና ቴክኖሎጂ የሚሰጠውን ፈርጀ ብዙ ጥቅም አሟጦ መጠቀም የሚያስችል የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ማከናወንና ለዚሁ ተግባር ቴክኖሎጂዎችና መሠረተ ልማቶች እንዲለሙ ማድረግ አንዱ እና የመጀመሪያው ነው። ሌላው ለልማት አስፈጻሚ፣ ለአገልግሎት ሰጪ እና ለደህንነት ተቋማት ዕቅድ ስኬትና ውሳኔ አሰጣጥ የሚያግዙ ስፔስ እና ጂኦስፓሻልን መሠረት ያደረጉ የማማከር አገልግሎቶችን መስጠት ነው።

በስፔስ እና ጂኦስፓሻል ምርትና አገልግሎቶችን ለመጠቀም፣ ለማላመድ፣ ለማሻሻል እና ለማምረት የሚያበቃ የሥልጠና አገልግሎት መስጠት ሦስተኛው ዓላማ ሲሆን አራተኛው የስፔስ እና ጂኦስፓሻል መረጃዎችን በመሰብሰብ፣ በማምረት እና ተደራሽ በማድረግ አገራዊ የልማት ሥራዎችን መደገፍ ነው። ከዚህ አንጻር ኢንስቲትዩቱ ምን አሳካ? ምንስ ይቀረዋል? የሚለውን መፈተሹ መስኩ በአገራችን በምን ደረጃ እና ቁመና ላይ እንዳለ ለመረዳት ያስችላል።

ከተገኙ ውጤቶች አንጻር በቀዳሚነት የሚጠቀሰው መስኩ በከፍተኛ ደረጃ የሠለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ያለበት በመሆኑ ከሰው ኃይል ልማት ጋር ተያይዞ የመጣው ለውጥ ነው። የስፔስ ሣይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ በመስኩ የተማረ እና ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት በሦስት መንገድ



32

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። የመጀመሪያው ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር የሚሰጡት የድህረ ምረቃ ትምህርቶች ናቸው። ዋና ዳይሬክተሩ “ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በቅንጅት በመሠራቱ እስከ አሁን 82 ተማሪዎችን ማስመረቅ ተችሏል። ከእነዚህ ውስጥ 31 በፒኤችዲ፣ 51 ደግሞ በማስተርስ ዲግሪ ተመርቀዋል። ይህ በተቋም ደረጃ ብቻ ሳይሆን እንደ አገር ያለውን የሰው ኃይል እጥረት ከማቃለል አኳያ ትልቅ እመርታ ነው” ብለዋል።

ከአዲስ አበባ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር መስጠት በተጀመረው ትምህርት 34 ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ናቸው። እስከ አሁን ስምንት ተማሪዎች በስፔስ እና በኤሮኖቲክ ኢንጂነሪንግ በማስተርስ ዲግሪ ተመርቀዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ ግማሹ በኢንስቲትዩት ተቀጥረው እየሠሩ ይገኛሉ።

በመስኩ የሠለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራት አንጻር እየተከናወነ ያለው ሁለተኛው ተግባር በስፔስና በስፓሻል ዘርፍ ልዩ ፍላጎትና ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊዎች በልዩ ሁኔታ መደገፍ ነው። ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደሚገልጹት፤ ላለፉት አምስት ዓመታት በዓለም አቀፍ መድረኮች፣ በተቋሙ እንዲሁም በክልሎች አማካኝነት የተለያዩ ሥልጠናዎች ተሰጥተዋል። ይህም ቀጣዩን ትውልድ ከማዘጋጀት እና ከማብቃት አኳያ የሚኖረው ፋይዳ ላቅ ያለ ነው።

የሰው ኃይል ለማልማት እየተደረገ ካለው ጥረት በሦስተኛነት የሚጠቀሰው ለተቋማት የሚሰጡት አጫጭር ሥልጠናዎች ናቸው። ሥልጠናዎቹም በተቋማት ፍላጎት ላይ በመመስረት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚሰጡ ናቸው። ከእነዚህም መካከል ጂአይኤስ፣ ሪሞት ሴንሲንግ፣ ካርቶግራፊ፣ ጂኤንኤስኤስ የመሰሉ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች ይገኙበታል።

ከተገኙት ውጤቶች አንዱ እና በቀደምትነት የሚጠቀሰው ሳተላይት የማምጠቅ ውጥን እና ጅማሮ ነው። ኢትረስ አንድ (Ethiopian Remote Sensing Satellite (ETRSS-1) እና ኢትስማርት የተሰኙ ሁለት ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ልካለች፤ አሁን ደግሞ (ETRSS-2)



33

የተሰኘች ሦስተኛ ሳተላይት እየተሠራች ነው።

እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ዋና ዳይሬክተሩ “ከተልዕኮ አንጻር ካየናቸው ከዚህ ቀደም የነበሩት ሁለቱ እና አሁን በመልማት ላይ ያለችውም የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች ናቸው። በመሬት ዙሪያ እየተሽከረከሩ ምስል በማንሳት ወደ መሬት የሚልኩ ሲሆን መሬት ባለው መረጃ መቀበያ አማካኝነት መረጃውን ተንትነን እና እሴት አክለንበት የተለያዩ ዘርፎችን ለመደገፍ እየተጠቀምንበት ነው” በማለት ነው ያብራሩት።

ሳተላይቶቹ ተልዕኳቸው ተመሳሳይ ቢሆንም አንደኛ ክብደታቸው፣ ሁለተኛ የሚይዙት ምስል ጥራት እንዲሁም በህዋ ላይ የሚኖራቸው የቆይታ ጊዜ የተለያየ እንደሆነ ጠቅሰዋል። አሁን እየተሰራች ያለችው ሦስተኛዋ ሳተላይት አምስት ዓመት በህዋ ላይ እንድትቆይ መታቀዱን እና በተያዘው መርኃ ግብር መሰረት ከተጓዙ በቀጣዩ ዓመት ወደ ህዋ እንደምትላክ ገልጸዋል። በዚህ ሥራ ላይ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች እየተሳተፉ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸው “በቀጣይ በራሳችን አቅም ሳተላይት ማምረት የምንችልበትን ሁኔታ እያየን ነው” ብለዋል።

የዲዛይን አቅም ከማሳደግ ጎን ለጎን ሳተላይቷ በምትገጣጠምበት ምዕራፍ ለ65 ቀናት በመገጣጠሚያ ጣቢያ ውስጥ ኢትዮጵያዊያኑ አብረው እንዲሠሩ መታቀዱንም ጠቁመዋል። ይህም ኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎች እና የመስኩ ባለሙያዎች ሳተላይቶችን ማምረት እና ማምጠቅ የሚችሉበት ዕውቀት፣ ክህሎት እና ልምድ እንዲያገኙ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ስለመሆኑ ተመላክቷል።

የእንጦጦ ላይ የሳተላይት ምስል መቀበያ፣ መመልከቻ እና የምርምር ማዕከል አለ። በውስጡም ህዋን የምንመለከትበት ቴሌስኮፓች፣ የአየር እና የምድር ጂኦስፓሻል መረጃ ለመቀበል የሚያገለግሉ የአየር ካሜራዎች እና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች አሉት።

የሳተላይት እና የመሬት መረጃ መቀበያ ጣቢያዎችን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለማሻሻል መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ለማሟላት መሠራቱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። መረጃን ለማደራጀት የክላውድ አገልግሎት (እንደ ስቶሬጅ) መጠቀም መጀመሩን አንስተዋል። መረጃን ለመተንተን ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ዋነኛ አካል የሚሆኑትን እንደ ማሽን ለርኒንግ፣ ዲፕለርኒንግ የመሳሰሉትን እየተጠቀሙ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ከ20 በላይ ሲስተሞችን (ፓርታሎችን) በራሳችን አቅም አልምተናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በተለይ የብሔራዊ የስፓሻል የመረጃ መሠረተ ልማት በዋነኝነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል። ይህም የስፓሻል መረጃን እኛ ብቻ ሳንሆን ሌሎችም የሚያጋሩበት ሲሆን መረጃውን የሚጠቀሙ አካላትም በቀላሉ ከፖርታሎቹ ማግኘት ችለዋል።

ኢንስቲትዩቱ ከመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለፍትህ ተቋማት ይሰጣል። እነዚህ መረጃዎች የመጀመሪያ ደረጃ የቴክኒክ ሰነድ ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው። እነዚህ እና ሌሎች የመስኩ መረጃዎች ሙስናን እና ህገወጥነትን በመከላከል ረገድ ትልቅ እገዛ እያደረጉ ነው።

በ2030 ዲጂታል ስትራቴጂ ላይ የተቀመጡት የኢ-ገቨርንመንት እና የኢ-ኮሜርስ ሥራዎችን



34

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ማሳካት የሚቻለው የዲጂታል የአድራሻ ሥርዓት ሲዘረጋ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ አብዲሳ ይልማ አንድ ሰው በፋይዳ መታወቂያ እንደሚለየው ሁሉ ቦታዎቹም መለያ እንዲኖራቸው እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል። በዚህ መሰረት እያንዳንዱን ቦታ፣ መኖሪያ እና ተቋም ለይቶ ልዩ የዲጂታል ኮድ ሰጥቶ በመመዝገብ ከአድራሻ ሥርዓት ጋር የማገናኘት ተግባር እየተከናወነ ነው።

የስፓሻል መረጃ እና ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዘርፎችን ከማገዝ አኳያ ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ “እ.አ.አ ከ2003 እስከ 2022 ድረስ በየአምሥት ዓመቱ የመሬት ሽፋን፣ የመሬት አጠቃቀም ዲጂታል ካርታ አዘጋጅተን ለግብርና ሚኒስቴር ሰጥተናል። የትኛው መሬት ለየትኛው ሰብል ተሰማሚ እንደሆነም በጥናት ተለይቷል” ሲሉ አብራርተዋል።

የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ፣ ለአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመተንበይ የሚያስችሉ እና ለመሠረተ ልማት ግንባታዎች ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎች በተቋሙ እየተመረቱ ለአገልግሎት እየዋሉ ነው። የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን ለመከታተል የሚረዳ ፓርታል በማልማት በየዓመቱ የሚተከለውን የችግኝ መረጃ አደራጅቶ መያዝ መቻሉን ኢንስቲትዩቱ ጠቅሷል።

በቱሪዝም ዘርፍ ከተሠሩት ውስጥ “ኢትዮጵያን ይጎብኙ” የተሰኘው መተግበሪያ አንዱ እና በኢንስቲትዩቱ አማካኝነት የተሠራ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመው የናሽናል ፓርክ ፓርታል በመልማት ላይ እንደሚገኝ አሳውቀዋል።

የጤና ተቋማት በአገር አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ስርጭት በማሳየት ትንተናዎችን በመሥራት፤ የት አካባቢ አዲስ ጤና ጣቢያ፣ አዲስ ትምህርት ቤት ያስፈልጋል የሚለውን በመለየት ለመወሰን የሚያስችል መረጃ በዘርፉ እየተመረተ ነው። ኢንስቲትዩቱ የመንገድ ሥራ ከመከናወኑ በፊት ለሚደረገው ቅየሳ እና የዲዛይን ዝግጅት ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎች እየተሰጡ ነው። በጥቅሉ የስፓሻል መረጃን ከዲጂታል ቴክኖሎጂው ጋር በማጣመር ዘርፎችን መደገፍ መቻሉን ቀደም ሲል ከተጠቀሱት ማሳያዎች መረዳት ይቻላል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወርሃ ግንቦት 2017 ዓ.ም ኢንስቲትዩቱን በጎበኙ ጊዜ “ኢንስቲትዩቱ ከከርሰ ምድር እስከ ህዋ ለልማት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በመለየትና በመተንተን ያከናወናቸው ሥራዎች መሠረት የጣሉ ናቸው። በአገር ውስጥ ሳይገደቡ ከዓለም አቀፍ መሰል ተቋማት ጋር በትብብር መሥራት የሚያስችል አቅም ገንብተዋል። ይህን በጥቂት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ማየት በጣም ደስታ የሚሰጥ ነው። ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ ለነገ አስባ እየሠራች ስለመሆኑም ማሳያ ነው” ብለዋል።

አፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ትስስሮች

የቀጣዩ ትውልድ የሀብት ምንጭ፣ የኃያልነት ማሳያ እና መወዳደሪያ ሜዳ እየሆነ በመምጣቱ ትልልቅ ኩባንያዎች ጭምር የህዋ ሣይንስ የምርምር ቴክኖሎጂን ጀምረዋል። የዓለማችን ግዙፍ ኩባንያዎች የህዋ ሣይንስ ምርምር ፕሮጀክቶችን በመጀመር ዘርፉን በስፋት እየተቀላቀሉ ነው።

በአንጻሩ አፍሪካ በስፔስ ሣይንስ እዚህ ግባ የሚባል ጥቅም እያገኘች አይደለም። አፍሪካዊያን በተናጠል ግዙፉን የአሰሳ ሥርዓት (Navigation system)



35

ለመገንባት መቸገራቸው አይቀርም። ስለሆነም በመተባበር አህጉራዊ የሆነ የአሰሳ ሥርዓት መገንባቱን እንደ አንድ አማራጭ መውሰድ ይጠይቃቸዋል።

ሉዓላዊነታችንን፣ አንድነታችንን ጠብቀን ማስቀጠል ካለብን አንዱ የምናረጋግጠው በስፔስ አማካኝነት ስለመሆኑ የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ሁሉም ጋር ያለው አቅም በአንድ ላይ ቢተባበር አፍሪካ የራሷ አህጉራዊ የአሰሳ ሥርዓት መፍጠር እንደምትችል የሚጠቁም ምክረ ሀሳብ ቅርበዋል። አፍሪካዊያን የሚጠቀሙባቸው (ጂፒኤስ እና ግሉናሲ የተባሉ) የህዋ ሣይንስ የአሰሳ ሥርዓት በሌሎች አገራት የለሙ ናቸው።

አፍሪካዊያን በቀጣይ የሉዓላዊነት እና የሀብት ምንጭ እየሆነ ያለውን የህዋ ሣይንስ ቴክኖሎጂ በጋራ በማልማት ለትውልድ ለማሻገር መንቀሳቀስ አለባቸው። በጋራ በመቆም በዓለም አቀፍ መድረኮች ፍትሃዊ ክፍፍሎች እንዲኖሩ ድምጽ ማሰማት፤ በዚህም ብቻ ሳይገደቡ ቀጣዩ ትውልድ በመስኩ ከሚገኘው ጥቅም ተቋዳሽ እንዲሆን ለማስቻል መሥራትን ዋነኛ ሥራቸው ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። በጋራ በመቆምና በመተባበር ግዙፍ የህዋ ሣይንስ ቴክኖሎጂ ማዕከል በመገንባት አህጉራዊ ጥቅማቸውን ማስከበር አለባቸው።

ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውጤታማ መሆን የሚችሉት በአህጉሪቷ ያለውን ትስስር እና አጋርነት በማጠናከር፣ ያለውንም ሀብት በፍትሃዊነት በመጠቀም፣ ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማምጣት ሲሠራ እንደሆነ ’Benefits of SPACE Science and Technology’ በሚል ርዕስ በአፍሪካ ኅብረት የተዘጋጀው የፖሊሲ ሰነድ አመላክቷል። ሰነዱ ሁለት አበይት ግቦችንም አስቀምጧል።

የመጀመሪያው በፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ አፍሪካ ላሏት ፍላጎቶች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆነ፣ የተቀናጀ እና የተደራጀ የስፔስ ፕሮግራም እውን ማድረግ ነው። ሁለተኛው ግብ የአፍሪካ ስፔስ ፕሮግራምን የሚደግፍ፣ የሚከታተል



36

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

አሠራር እና ማዕቀፍ ማበጀት ነው። በዚህም መነሻነት ሥራውን እንዲመራ የአፍሪካ ስፔስ ኤጀንሲ ተቋቁሞ ወደ እንቅስቃሴ የተገባ ሲሆን በቀጣይ በአህጉሪቷ በሚሠሩ ሥራዎች ውጤት እንደሚመጣ ተስፋ ተሰንቋል።

ወደ አገራችን ስንመለስ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ እና ከዓለም አገራት ጋር ትስስር በመፍጠር ተጠቃሚነቷን በማረጋገጥ ላይ ነች። በዓለም አቀፍ ደረጃ የምንፈጥራቸው ትብብሮች ብዙ ጥቅም እያስገኙልን ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ “በተለይ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ ባለው ጊዜ በአጠቃላይ የኢትዮጵያን የቆዳ ስፋት የሚሸፍን የሳተላይት መረጃ እያገኘን ነው። ይህ ትልቅ ዕድል ነው” ሲሉ በመስኩ የተገኘውን ውጤት ጠቅሰዋል።

ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት አንዱ መገለጫው የምርምር ውጤቶችን ማሳተም በመሆኑ እስከ አሁን 250 የምርምር ውጤቶች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባላቸው ጆርናሎች ታትመዋል።

በዓለም ላይ ለኢትዮጵያ ዓርአያ የሚሆኑና ልንከተላቸው የምንችላቸው አገራት መኖራቸውን የሚገልጹት የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ፀሀይ አሜሪካ፣ ሩስያ፣ ቻይና፣ ህንድ እና ሌሎች የአውሮፓ አገራት ካስመዘገቡት ስኬት አንጻር የሚታወቁ መሆናቸውን አንስተዋል። እነዚህ የሠለጠኑ አገራት የተጓዙበትን መንገድ ለመከተል ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አመላክተዋል። ከቻይና ጋር በመጣመር እየተሠራ ስላለው ሥራ፣ በሩሲያ ከሚገኙ ተቋማት ጋር ስለተጀመሩ ትስስሮች ገልጸዋል።

“የእነዚህን አገራት ልምድና ተሞክሮ እየተጠቀምን ለማደግ እየሠራን ነው። ይህም አርቀን እንድናይ ያደርገናል። ከሁሉም የሚጠቅሙንን ተሞክሮዎች ወደ አገራችን እያመጣን ተግባራዊ የምናደርግ ይሆናል” ሲሉም ቀጣዩን አቅጣጫ ጠቁመዋል። በጥቅሉ ኢትዮጵያ ከመስኩ ማግኘት ያለባትን ጥቅም ለማስጠበቅ ከአፍሪካ እና ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላትን ትስስር ይበልጥ ማጠናከሩን እንደ ትልቅ የቤት ሥራ ወስዳ መንቀሳቀስ ይጠበቅባታል።

ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

በአገራችን በመስኩ የተለየ እንቅስቃሴ የተጀመረው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ነው፤ በእነዚህ ዓመታት የዘርፉን ሥራዎች ለማሳካት በተደረገው ጥረት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል። በሂደቱም ተግዳሮቶችና ውጣ ውረዶች ነበሩ እስከ አሁንም የዘለቁ መኖራቸው ተጠቁሟል።

ከተግዳሮቶቹ መካከል አንደኛው ከቴክኖሎጂ ልማት ጋር በተያያዘ እያጋጠመ ያለው ችግር ስለመሆኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። የዩሮስፔስ ቴክኖሎጂዎችን ለመግዛት የሚጠይቀውን የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ከባድ መሆኑ ለሥራዎች መስተጓጎል መንስኤ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

“ጨረታ እያወጣን የአገር ውስጥ ነጋዴዎች ዕቃዎቹን እንዲያስገቧቸው ጥረት እያደረግን ነው። ይህን እንደ አንድ መፍትሔ ወስደን እየሠራን ቢሆንም ተግዳሮቶቹ በምንፈልገው ደረጃ እንዳንሄድ እያደረጉን ነው” በማለት ነው ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የችግሩን አሳሳቢነት የገለጹት።

ሌላው ከሰው ኃይል ፍልሰት ጋር የተያያዘው ችግር ነው። የምናሠለጥናቸው ሰዎች ወደ ሥራ ከገቡ በኋላ ሌላ አማራጭ ሲያገኙ ትተው ይሄዳሉ፤ ባለሙያዎች ሲለቁ በቅጥር ማሟላት እንዲሁም



37

በውስጥ ያለን አቅም ለመጠቀም ጥረት ማድረግ እንደመፍትሔ ተወስደዋል።

የግሉ ዘርፍ በመስኩ አለመሳተፍ እንደውስነነት የተነሳ ሌላው ጉዳይ ነው። በዓለም ላይ ስፔስ እና ጂኦስፓሻል እንደ ኢንደስትሪ ይቆጠራሉ የሚሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጠርበትና ገቢም የሚያነጭ ዘርፍ እንደሆነ ነው የጠቆሙት። በአገራችን ገና በደንብ ያልተሠራበት መስክ ስለሆነ የግሉ ዘርፍ እንዲጠናከርና እንዲስፋፋ ብዙ መሥራት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል።

“ሀሳብ ያላቸው እንዲወዳደሩ በመጋበዝ፣ የሚሠሩበት ቦታ በመስጠት፣ በቴክኒክ፣ በፋይናንስ፣ በመረጃ፣ በቢዝነስ ዕቅድ ዝግጅትና በመሳሰሉት ድጋፍ እያደረግን ነው። ይህነኑ ይበልጥ በማጠናከር በቀጣይ ሰፊ ሥራ መሥራት እንዳለብን እንገነዘባለን” ሲሉ መፍትሔ እና በቀጣይ በትኩረት የሚከናወኑ ተግባራትን አመላክተዋል።

እንደ አቶ በላቸው ገለጻ፤ በተለይ መረጃዎችን በስፋት ከሚጠቀሙ ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሠራ ነው። ሆኖም ሥነምህዳሩን (ecosystem) ተስማሚ እና ምቹ ከማድረግ አንጻር ብዙ ሥራ ይቀራል። ስለሆነም ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን በመለየትና ከእነርሱ ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ ይጠይቃል፤ ይህም እውን እንዲሆን የሚመለከታቸውን አካላት ትኩረት ይሻል።

ወደ ከፍታው ለመጓዝ - ድልድዩን መጠቀም

“በተለያዩ አገራት ቴክኖሎጂዎች እየተመረቱ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው፤ ለምሣሌ እኛ የሌሎች አገራትን የመገናኛ ሳተላይቶች (ወይም ጂአይኤስ - GIS) ነው የምንጠቀመው ቢከለክሉን ምንም ማድረግ አንችልም። ይህ አገራችንን በሌሎች ላይ ጥገኛ እንድትሆን ያደርጋታል” ሲሉ አስተያየታቸውን የሰነዘሩት የኢትዮጵያ ስፔስ ሣይንስ እና ጂኦስፓሻል



38

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ፀሀይ ናቸው።

በቻይና፣ በራሺያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የፖለቲካ አሰላለፍ ስንመለከት አንዱ የሌላውን የቴክኖሎጂ ውጤት የሚጠቀሙበት ቁመና ላይ አይደሉም። እነዚህ አገራት የየራሳቸውን የመገኛ ሳተላይት አምርተው ይገለገላሉ። በዘርፉ የሚፈጠረው አቅም በአገራት ፖለቲካ ላይ የሚያሳድረውን አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ከዚህ ማሳያ በመነሳት ሰፋ አድርጎ ማየት ይቻላል።

ተግተን ከሠራን አገራችንን በተለየ ሁኔታ ከፍ ሊያደርግ ብሎም ገጽታችንን ለመገንባት የሚያስችል መስክ ነው። ከኢኮኖሚያዊ፣ ከማኅበራዊ፣ ከተፈጥሮ አደጋዎች፣ ከአካባቢያዊ ጉዳዮች እና ሌሎች ሥራዎችን ከመደገፍ አንጻር ያለውን አበርክቶ ለመግለፅ ተሞክሯል። ነገር ግን መስኩ ከዚያ ያለፈ ጥቅም ያለው ስለመሆኑ ማንሳቱ ተገቢ ነው።

ኢትዮጵያ ሳተላይቶችን እያመረተች ሥራ ላይ የምታውልና ይፋ የምታደርግ ከሆነ ለአፍሪካ አገራት ጭምር መረጃ መሸጥ ትችላለች። ሳተላይቶቹ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይወሰኑ በሌሎች አገራትም ያለውን መረጃ የመሰብሰብ አቅም አላቸው። ስለሆነም የቴክኖሎጂ አቅምን መገንባት ለራስ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ለማገዝ ይረዳል። ይህም ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ትርፍ ያስገኛል፤ የገቢ ምንጭም ይሆናል።

በመስኩ እየተሠሩ ያሉ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ወደዚያው ማምራትን ታሳቢ ያደረጉ ስለመሆናቸው የኢንስቲትዩቱ መረጃዎች ያመላክታሉ። የሚከናወነው ተግባር ኢትዮጵያ ከተለያዩ አገራት ጋር ያላትን ጥምረት ይበልጥ የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ አቅምና ብቃቷን አጉልቶ ለማሳየት ብሎም ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግ ጠቃሚ ነው።

በአገራችን የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ስልክን ጨምሮ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተጠቃሚዎች (ግለሰቦች እና ተቋማት) ቁጥርም እያደገ ነው። እነዚህ ሁሉ አገልግሎቶች የሚሰጡት በሳተላይት መረጃዎች አማካኝነት ነው። እኛ ብቻ ሳንሆን ጎረቤት አገራትም ጭምር የኮሙኒኬሽን ሳተላይት



39

በመግዛት የቴሌኮም አገልግሎት ይሰጣሉ። ስለዚህ ሳተላይት መገንባት ይህን የገበያ ፍላጎት በማሟላት ገቢ ማመንጨት ያስችላል።

ኢትዮጵያ ያለችበት ጂኦግራፊያዊ መገኛ በፈጠረው መልካም አጋጣሚ ከምድር ወገብ በቅርበት መገኘታችን እና የመሬቱ አቀማመጥ ተዳምሮ የሰጠን ዕድል አለ። የሳተላይት መረጃ መቀበያ ጣቢያ መገንባት የሚያስችሉ ምቹ ቦታዎች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፤ እነዚህን በመለየት ለአገልግሎት ማዋል ያስፈልጋል።

የስፔስ ሀብት በጣም ውድ ስለሆነ ሁሉም አገራት ርብርብ ላይ ናቸው። ስለዚህ ሩጫው መሆን ያለበት ዓለም እንዴት እየሄደች እንደሆነ በማየት ለመድረስ መሥራት ላይ ነው። መሬት ላይ ብቻ ሳይሆን ህዋ ላይ የራስን ድርሻ መያዝና ይህን ማስጠበቅን የመጪው ጊዜ ትልም ማድረግ ያስፈልጋል።

የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢትዮጵያ ከስፔስ ሣይንስ እና ከጂኦስፓሻል ሥራዎች አንጻር ልትደርስበት የያዘችውን ውጥን ሲያብራሩ፤ የመጀመሪያው ዕቅድ የተጀመረውን የሳተላይት ፕሮጀክት ለሁሉም ሴክተር በሚያገለግል መልኩ ማጠናቀቅ ነው። ይህም አቅምን በማሳደግ አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት፣ ሦስት፣ እና ከዚያም በላይ ሳተላይቶችን ለማምረት እንቅስቃሴ የሚደረግበት ነው። በቅርቡ ተጠናቆ ሥራውን የሚጀምር የዩሮስፔስ ማዕከል እየተገነባ ነው። ማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ አነስተኛ ሳተላይቶችን ለመገጣጠምና ለመፈተሽ እንደሚያገለግል አመላክተዋል።

የሳተላይት መገጣጠሚያ እና ፍተሻ ማዕከል ፕሮጀክት ተጠናቆ ወደ ስራ ቢገባ የራሳችንን የሳተላይት መረጃዎች ማግኘት ያስችለናል፤ ሌሎች የአፍሪካ አገራት እኛ ጋር መጥተው ሳተላይታቸውን እንዲገነቡ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። ይህ ማዕከል ሲጠናቀቅ ሳተላይት ማምጠቅ ብቻ ሳይሆን የፍተሻ አገልግሎቶችንም ለመስጠት ያገለግላል። በአገር ውስጥ እና በሌሎች አገራት የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችም ይህንን የፍተሻ አገልግሎት መጠቀም ይችላሉ።

ሦስተኛዋ ሳተላይት እየተገነባች ትገኛለች፤ በህዋ ላይ ከቀደሙት ሁለት ሳተላይቶች የተሻለ ቆይታ እንደሚኖራትና የተሻለ ጥራት ያለው መረጃ እንድታመነጭ ታሳቢ ተደርጓል። ሳተላይት የማልማቱን ሥራ በማጠናቀቅ ወደ ህዋ ማምጠቅ ሌላው ትኩረት የተሰጠው የመስኩ ዕቅድ ነው።

በኢትዮጵያ ፈጣንና ትክክለኛ የጂኦስፓሻል መረጃዎችን ለማመንጨት የሚረዱ ማዕከላት መቋቋማቸው ይበል የሚያሰኝ ነው፤ ማዕከላቱ ለማኅበረሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ የህግ ማዕቀፎችን እያዘጋጁ ሥራ ላይ ማዋል ይጠይቃል። የስፔስ ሣይንስ እና ጂኦስፓሻል ሥነምህዳርን መፍጠር ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት መካከል ናቸው።

በጥቅሉ እነዚህ እንቅስቃሴዎች ተደማምረው የዓለም አገራት ወደደረሱበት ደረጃ የሚያሻግር ውጤት እንደሚገኝ ከወዲሁ በልበ ሙሉነት መግለጽ ይቻላል። በቀጣይ የሚኖረው ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን ማገዝ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ ከመንግሥት፣ ከምሁራን እንዲሁም ከአጠቃላዩ ማኅበረሰብ የሚጠበቅ የቤት ሥራ ነው።



40

ፖለቲካ

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

አፍሪካ ለምን ትጠማለች?



41

የመሪዎቿ ጉባዔ አንድምታ

በአየለ ያረጋል

መንደርደርያ

ጥንታዊቷና ምድረ ቀደምቷ ሀገር ኢትዮጵያ በዕልፍ ዘመን ታሪኳ ነጻነቷን ጠብቃ መኖሯ ለአፍሪካዊያን ኩራት ብቻ ሳይሆን የመሰባሰቢያ ማዕከል ትሆን ዘንድ ታሪክ የዕድል በር ከፍቶላታል። በዚህም አዲስ አበባ የዲፕሎማቲክ ማዕከል እና የማይስ ቱሪዝም (MICE Tourism) መናኸሪያ ሆና ቀጥላለች። አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን ሰርክ ታስተናግዳለች። ባሳለፍነው ወርሃ የካቲት



42

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ካስተናገደቻቸው ዓበይት ዓመታዊ ሁነቶች መካከል የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ አንዱ ነው።

39ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል። “የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ የውሃ አቅርቦት እና አስተማማኝ የንፅህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ” የሚለው የዓመቱ የሕብረቱ መሪ ቃል ነበር። በዚህም የጉባዔው አንኳር ማጠንጠኛ የውሃ ደህንነት የስትራቴጂ፣ የልማት፣ የሰላም እና የአየር ንብረት ጉዳይ ሆኗል። ይህ ፅሁፍ የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ጉባዔ ክዋኔና የመልዕክቶችን አንድምታ በወፍ በረር ይቃኛል።

አፍሪካ፡- መሻቷ፣ የውሃ ሀብቷና ተግዳሮቷ

አፍሪካ የውሃ ሀብት ተችሯታል። ቅሉ በአይነተ ብዙ መንስኤዎች ሳቢያ ትጠማለች። በአፍሪካ አህጉር 400 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለዕለት ተዕለት ኑሯቸው የሚሆን የውሃ አቅርቦት፤ ከ800 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ መሰረታዊ የንፅህና መጠበቂያ አገልግሎቶች እንደማያገኙ ዓለም አቀፍ መረጃዎች ዋቢ ናቸው። በዚህም ውሃና ንፅህና አጠባበቅ የዓመቱ መሪ ሃሳብ ሆኖ መመረጡ የጉዳዩን አንገብጋቢነት በቅጡ ያመላክታል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚያሳየው የአፍሪካ ታዳሽ የውኃ ሀብት በአማካይ 3 ሺህ 930 ኪዩቢክ ኪሎ ሜትር ነው። ይህም ከዓለም አቀፉ አጠቃላይ የውኃ መጠን ዘጠኝ በመቶ ገደማ ነው። በአንዳንድ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አካባቢዎች የተፈጥሮ ረግረጋማ ቦታዎች ብቸኛ ተደራሽ የውኃ ሀብቶች በመሆናቸው ለመኖሪያነት አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ውኃን፣ የግብርና አቅምን እና



43

የኑሮ መሠረትን ስለሚፈጥሩ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

ውሃ ተኮሩ የሕብረቱ የ2026 መሪ ሃሳብ ከአጀንዳ 2063ቱ የሕብረቱ የግማሽ ምዐተ ዓመት የልማት ማዕቀፍ ጋር የተሰናሰለ ነው። የምንሻትን አፍሪካ ዕውን ለማድረግ እና የአፍሪካን መጻዒ ዕድል ለመወሰን የተወጠነው የ‘አጀንዳ 2063’ አህጉራዊ ግብ ነው። በአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬት ደግሞ ውሃ ቀጥተኛም ሆነ ኢ-ቀጥተኛ አይተኬ ሚና ይጫወታል።

የአፍሪካ የውሃ ሀብት አጠቃቀም፣ የውሃ ደህንነትና የወደፊት ዕቅዶች ለአህጉሪቱ ዕድገት ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው። በተለይም የሕዝብ ቁጥር መጨመር እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ በታየበት በዚህ ወቅት፣ የውሃ ጉዳይ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚያዊ ውይይቶች ላይ ቀዳሚ ቦታ ይይዛል።

የውሃ ጉዳይ ከአፍሪካ ሕብረት የአጀንዳ 2063 ወሳኝ ግቦች አንዱ መሆኑ እሙን ነው። በአጀንዳ 2063 አፍሪካ የውሃ ሀብቷን በቅጡ በመጠቀም ለልማት፣ ለምግብ ዋስትና ለኃይል ግልጋሎት ማዋል የሚል ርዕይ ተነብሯል። በዚህ ግብ አፍሪካ ከመጠማት ተላቃ ለዜጎቿ ንጹህ መጠጥ ውሃና የንጽህና አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ፣ በድንበር ተሻጋሪ ወንዞቿ ትብብርን ማጠናከር እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥሉ የመስኖና ኢንዱስትሪ ልማት ማዋል ግድ ይላታል።

ምሁራን ስለ አፍሪካ የንጹህ መጠጥ ውሃ መጠማት እና ለንጽህና ሥርዓቷ መጓደል አይነተ ብዙ መንስኤዎች ያስቀምጣሉ። ከእነዚህም መካከል አንዱ የውሃ መሰረተ ልማት አለመኖር ነው። ይኸውም የውሃ ሀብት አለመኖር ሳይሆን ውሃውን በአግባቡ መጠቀም የሚያስችል መሰረተ ልማት አለመኖር ነው። ይህ ደግሞ ከፋይናንስ እጥረት እና ከጥገና ጉድለት የሚከሰት ጉዳይ ነው።

ሁለተኛው ዓለም አቀፋዊ መንስኤ የሆነው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የወለደው ችግር ነው። ምንም እንኳን ለከባቢ አየር መበከል አበርክቶዋ አነስተኛ ቢሆንም በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በሚከሰቱ ችግሮች ግን ቀዳሚዋ ሰለባ አፍሪካ ናት። የዝናብ ወቅት መዛባት፣ ጎርፍ፣ ድርቅ፣ የከርሰ ምድር ውሃ መጠን መቀነስና የምርት አለመኖር ችግሮች ዳርጓታል። የበረሃማነት መስፋፋት በተለይም በሳህል ቀጣና እና ኢትዮጵያ በምትገኝበት የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ለውሃ ምንጮች መድረቅ መንስኤ ሆኗል።

በሌላ በኩል አፍሪካ ያላት ፈጣን የሕዝብ ቁጥር ጭማሮ እና የአፍሪካ ፈጣን የክትመት ምጣኔ የውሃ ፍላጎትና አቅርቦት አለመመጣጠን እንዲከሰት መንስኤ ነው። ምክንያቱም በአፍሪካ የክትመት ምጣኔ በከፍተኛ ደረጃ ሲጨምር በአንጻሩ የውሃ መሰረተ ልማቶች በዚያው ልክ አልተዘረጉምና።

የውሃ አስተዳደር እና ፖለቲካዊ ችግሮችም አፍሪካን ለከፍተኛ የውሃ አለመኖር ችግር ዳርገዋል። ለአብነትም የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ውዝግቦች ውሃን በፍትሃዊ መንገድ ከመጠቀም ይልቅ ፖለቲካዊ መልክ እየተሰጣቸው ለአለመግባባት መንስኤ ዳርገዋል። ለዚህ ሁነኛ አብዮት የናይል ተፋሰስ ሀገራት ተጠቃሽ ናቸው። ይኸውም ግብጽና መሰሎቹ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በቅኝ ግዛት ስሁት እሳቤ በመመራት የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ውሃን ለዘላቂ ሀገራዊ ልማት እንዳይጠቀሙ ሁሉን አቀፍ ጫና ሲያደርጉ ይስተዋላል።



44

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

የውሃ ብክለት ሌላው ቁልፍ ተግዳሮት ነው። በአፍሪካ የኢንዱስትሪዎች መስፋፋትና የኢንዱስትሪዎች ቆሻሻዎች፣ የማዕድን ቁፋሮ ውጤቶች እና የፍሳሽ ዝቃጮች ውሃማ አካላት እንዲበከሉ መንስኤ ሆነዋል። ይህም ውሃ እያላት ውሃ እንድትጠማ ፈተና ጋርጦባታል። ‘የዓባይን ልጅ ውሀ ጠማው’ እንዲሉ።

በጥቅሉ አፍሪካ ለምን ትጠማለች? ስንል በውሃ ሀብት እጥረት ሳይሆን በውሃ ሀብቷ አስተዳደር፣ አጠቃቀም እና ሥርዓት የማበጀት ችግር ስለመሆኑ እንረዳለን። የውሃ ሀብቷን ወደ ጥቅም የሚቀይር የኢኮኖሚ አቅም እና ቀልጣፋ የአመራር ሥርዓት አልተሟላላትም።

አፍሪካ ወደ 60 የሚጠጉ ድንበር ተሻጋሪ የወንዝ ተፋሰሶች አሏት። የአፍሪካ ወንዞች በጋራ በማልማት ለአፍሪካ ሰላም እና ትብብር ቁልፍ ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል ይገባል። በውሃ ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶች ለአብነትም የመሠረተ ልማት እጥረት ሟሟላትና በቴክኖሎጂ ማዘመን እንዲሁም ከከፍተኛ የሕዝብ ቁጥሯ ጋር አብሮ የሚራመድ የውሃ አቅርቦት ማሟላት ትፈልጋለች። በአፍሪካ “ሰማያዊ ኢኮኖሚ” (Blue Economy) በሚሰኘው ጽንሰ ሀሳብ መሰረት በውሃ ሀብት፣ በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ በዓሣ ሀብት ልማትና በትራንስፖርት በቅጡ ለመጠቀም ሰፋ ያሉ ሥራዎች መከወን እንዳለባቸው በመስኩ የተደረጉ ጥናቶች ምክረ ሃሳቦች ሲሰነዘሩ ይስተዋላል።

የዓመቱ መሪ ሃሳብ በመሪዎች አንደበት

ውሃ እና የንጽህና ሥርዓት የአፍሪካ የዓመቱ መሪ ሃሳብ መሆኑ ከላይ ተጠቅሷል። ውሃ ለአፍሪካ ቁልፍ ዘርፍ ከመሆን የዘለለ አንድምታ አለው።

ውሃ ለምጣኔ ሀብታዊና ለሕይወት መሰረታዊ ግብዓት ነውና። ውሃ የልማት፣ የሰላም፣ የአየር ንብረት ጉዳይ፣ የምግብ ዋስትና፣ የትብብርና ኢንቨስትመንት፣ የጤናና ሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች አንኳር ጉዳይ ነው። በሌላ አገላለጽ ውሃ ሌሎች የ2063 አህጉራዊ አጀንዳዎችን ዕውን ለማድረግም የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ ዓሊ ዩሱፍ በኅብረቱ የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መክፈቻ ላይ በውሃ ኑረት እና ንፅህና አጠባበቅ ሥርዓት ላይ ያተኮረው የዓመቱ መሪ ሃሳብ ወሳኝ አህጉራዊ ጭብጭ ስለመሆኑ አውስተዋል። ቁጠባ ተኮር የውሃ ሀብት አጠቃቀም መርህ መከተል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

“ውሃ በምንም አይነት ዋጋ መጠበቅ ያለበት የጋራ ፀጋ በመሆኑ ከአየር ንብረት ለውጥና የዕለት ከዕለት ሕይወታቸን ውስጥ በቁጠባ መጠቀም አለብን። ውሃ የመንግሥታት አቀራራቢና የሰላም ማነቃቂያ መሳሪያ ሆኖ ማገልገል አለበት” ብለዋል። በተመሳሳይ በ39ኛው የመሪዎች ጉባዔ መክፈቻ ንግግራቸው “የውኃ አቅርቦት ለልማትና ለሰላም መጠናከር ወሳኝ ሚና መጫወት ያለበት የጋራ ሀብት” ብለውታል።

የአንጎላ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት እና ተሰናባቹ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ጆአዎ ማኑኤል ሎሬንዞ፤ የውሃ አቅርቦትን ማረጋገጥ ለአፍሪካ ልማት፣ ለሕዝብ ጤና፣ ለምግብ ዋስትና እና ለመረጋጋት ወሳኝ የሆነ ፖለቲካዊ፣ ሞራላዊ እና ስትራቴጂካዊ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ስለመሆኑ አውስተዋል።

ውሃ የሰላምና የትብብር መሳሪያ፤ የግጭት መንስኤ ሳይሆን የጋራ ልማት እና የሰላም ድልድይ



45

መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በተለይም ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብቶች በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ አህጉራዊ ስምምነቶች መጠናከር እንዳለባቸው ገልጸዋል።

አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለድርቅና ለውሃ እጥረት እየተጋለጠች በመሆኑ ውሃን በዘላቂነት ማስተዳደር የአፍሪካ ሕልውና ጉዳይ መሆኑንም አሳስበዋል። ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለሁሉም አፍሪካዊያን ተደራሽ ለማድረግ በትልልቅ የውሃ መሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚገባ እንዲሁም የአፍሪካ የውሃ ራዕይ 2063 (Africa Water Vision 2063) እንዲሳካና አፍሪካ በምግብ ራሷን እንድትችል የውሃ ሀብትን ለግብርና ሥራዎች በቅጡ ማዋል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ፕሬዚዳንቱ እንደ ተሰናባች ሊቀመንበርነታቸው፤ አህጉሪቱ በውሃ ሀብት አጠቃቀም ዙሪያ ያሏትን አለመግባባቶች በውይይትና በ”አፍሪካዊ መፍትሄ ለአፍሪካዊ ችግሮች” መርህ እንድትፈታም ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባዔው መክፈቻ ንግግራቸው፤ በአፍሪካ ስትራቴጂካዊ ሉዓላዊነት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና



46

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በአጀንዳ 2063 ጭብጦች ላይ ያተኮሩ አንኳር መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። የአፍሪካን ታሪካዊ ዐሻራ እና ፅኑ ርዕይ በማውሳት ቁልፍ ሃሳብ አስተጋብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፍሪካ ያላትን እጅግ ሰፊ የውሃ ሀብት ለአህጉራዊ ትስስርና ለጋራ ዕድገት መጠቀም እንደሚገባና በድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና በውሃ ሀብት አጠቃቀም ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶች፣ በባዕዳን ጣልቃ ገብነት ሳይሆን በራሳቸው በአፍሪካዊያን የውይይት መድረክና በኅብረቱ ማዕቀፍ ሊፈቱ እንደሚገባ አሳስበዋል። ይህም ኢትዮጵያ ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ ከምትከተለው የፍትሐዊ የውሃ አጠቃቀም መርህ ጋር የተጣጣመ መልዕክት ነበር። የውሃ፣ የምግብ እና የኢነርጂ ትስስርን በማውሳትም አፍሪካ የውሃ ፀጋዋን ማልማትና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንዳለባት አውስተዋል።

በሌላ በኩል አፍሪካ የውሃ ሀብቷን በዘላቂነት ለመጠበቅ የተፈጥሮ ሀብትና የአካባቢ ጥበቃ ያላውን ወሳኝ ፋይዳ በመጥቀስ የኢትዮጵያን የ’አረንጓዴ አሻራ’ ተሞክሮ ለአብነት አንስተዋል። አፍሪካ የተፈጥሮ ፀጋ የተቸራት መሆኑን በማውሳት ይህን ጸጋ አሟጦ ለመጠቀም በየቋማት ግንባታ፣ ፈጠራ እና ዘላቂ ልማትን ያማከለ አስተዳደራዊ



47

ችሎታ እንደሚያሻ ጠቁመዋል።

ውኃ ልማት፣ ኢነርጂ፣ የምግብ ዋስትና እና የኢንዱስትሪ ልማት ጅምሮችን ማሳደግ እንደሚገባና በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የስንዴ ምርት እና የኢንዱስትሪ ልማት ዕውን በማድረግ ለአፍሪካ ብልጽግና ተምሣሌት ለመሆን እየተጋች ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።

የአፍሪካን የሰው ኃይል ዕምቅ አቅም በተለይም ወጣቶችን ያማከለ ኢንቨስትመንት እንደሚያሻ፣ አረንጓዴ አሻራን መሰል የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን መቋቋሚያ ኢኒሼቲቮችን መተግበር፣ ዲጂታላይዜሸን እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለአፍሪካ መጻዒ ዘላቂ ልማትና ሁለንተናዊ ብልጽግና አይተኬ ሚና እንዳላቸው አጽንኦት ሰጥተው፤ ዓለም አቀፍ አጀንዳ የምትቀርጽ፣ ለሁሉም ዜጎች ልማትና ክብር ዋስትና የሆነች አፍሪካን ዕውን ማድረግ ይገባናል ብለዋል።

በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የአዝርዕት፣ የገጠር ልማት፣ የሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ጥበቃ ኮሚሽነር ሙሴ ቪላካቲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የዘንድሮው መሪ ቃል አፍሪካ በውሃ እና በንፅህና አጠባበቅ አገልግሎት ዙሪያ ለሰው ልጅ ደህንነት፣ ማኅበራዊ መረጋጋትና ኢኮኖሚያዊ ሽግግር መሳለጥ ትልቅ ትኩረትና ዕውቅና መስጠቷን አመላካች ስለመሆኑ አንስተዋል። የአፍሪካ ሕብረት በውሃ እና በንፅህና አጠባበቅ ረገድ አስፈላጊ የሆኑ የለውጥ እርምጃዎችን ለማፋጠን፤ የሕብረቱ ኮሚሽን የትግበራ ፍኖተ ካርታ መቅረጹን ገልጸዋል። ፍኖተ-ካርታው በአስተዳደርና ፖሊሲ፣ በፖለቲካ ቁርጠኝነት፣ በፋይናንስና ኢንቨስትመንት፣ አጋርነትን መገንባት፣ እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስለመሆናቸውም እንዲሁ።

የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ውሃ ከማኅበራዊ ግልጋሎት ባሻገር ለኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማቶች ግብዓትና ለአንድ ሀገር ምርታማነት ምሰሶ ስለመሆኑ አንስተዋል። በውሃ ወለድ በሽታዎች በአፍሪካ በየሠዓቱ 115 ሰዎች ለሕልፈት እንደሚዳረጉ በማውሳት የንጹህ ውሃ አጠባበቅን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል። በሌላ በኩል ለአፍሪካ ኢንቨስትመንት መጎልበት የውሃ መሰረተ ልማት አቅርቦት ያለውን አይተኬ ሚና አንስተዋል።

ከውሃ ባሻገር. . .

የአፍሪካ ያልተቋጩ የቤት ሥራዎች

የአፍሪካ ሕብረት የዓመቱ መሪ ሃሳብ ውሃ ላይ ቢያጠነጥንም ቅሉ አፍሪካ ግን ውሃ ብቻ አይደለም የተጠማችው። አፍሪካ ከሰላም፣ ከልማትና ብልጽግናም ጥሟንና ርሀቧን ገና አልቆረጠችም። በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ መንስኤዎች ሳቢያ ሁሉን አቀፍ ፈተናዎችን እየተጋፈጠች ትገኛለች። የሕብረቱ ጉባዔ መድረክ መልዕክቶች አንድምታ የአፍሪካን ያልተቋጩ የቤት ሥራዎች እንዴት እንሥራቸው? እንዴትስ በአንድ ልሳን እንናገር? የአፍሪካን ነገ ዛሬ ላይ እንዴት እንቀይሰው? በሚሉ ሀቲቶች ላይ ያተኮረ ነበር።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ዓለም አቀፋዊ ጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረት የነገሰበት፣ ግጭቶች የበረቱበት፣ ተቋማዊ ድክመቶች የታዩበትና በአንዳንድ የአህጉሪቱ



48

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ክፍሎች ሕገ-መንግሥታዊ ያልሆኑ የመንግሥት ለውጦች ዳግም ያገረሹበት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመድብለ-ወገን ግንኙነት የተዳከመበት፣ የጎራ ክፍፍል የናረበት ወቅት መሆኑን ጠቅሰዋል።

በአፍሪካ ተቋማዊ ተሃድሶ እና ራስ በቅ የፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋት አይቀሬ የቤት ሥራዎች እንደሆኑ አንስተዋል። አፍሪካ በኢንዱስትሪ፣ በግብርና ሽግግር፣ በኃይልና መሠረተ ልማት ዝርጋታዎችና ሌሎች አህጉራዊ ፋና ወጊ መርሃ ግብሮች ትሻለች ብለዋል። አፍሪካ ከውጭ ድጋፍ ጥገኝነት ወደ ራስን መቻል መሸጋገር እንዳለባት ጠቅሰው፤ የአጀንዳ 2063 ግቦች ተጨባጭ ውጤት ያመጡ ዘንድ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ሊቀመንበሩ ከሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ በተጓዳኝ በአፍሪካ የግል ዘርፍ ላይ በመከረ መድረክ ላይ “አፍሪካ ጥሬ ዕቃዎችን ወደ ውጭ የመላክ እና እሴት የተጨመረባቸውን ምርቶች ወደ ውስጥ የማስገባት ዘመኗ ማብቃት አለበት። አህጉሪቱ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ሕዝብ፣ 30 በመቶ የሚሆነውን የዓለም ወሳኝ ማዕድናት እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን (AfCFTA) እንደ መሰረት በመያዝ፤ ኢንዱስትሪዎቿን ለማሳደግ፣ ትስስር ለመፍጠር እና ለመምራት የሚያስችሏት ሀብቶች አሏት። የመንግሥት ፖሊሲ ብቻውን በቂ አይደለም። ኢንዱስትሪን ማስፋፋት፣ የኃይል ሽግግር፣ የዲጂታል ፈጠራ እና የምርት እሴት ሰንሰለት ልማት የሙሉ የግል ዘርፍ አጋርነትን ይጠይቃሉ” ሲሉ ተደምጠዋል።

በሱዳን፣ በሳህል፣ በምስራቅ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና በሶማሊያ ባሉ ቀውሶች እየደረሰ ባለው የሕዝብ ስቃይ አጋርነታቸውን በማውሳት፤ ጠንካራ፣ ራስ በቅና ብልጹግ አፍሪካን ለመገንባት ቁርጠኝነትና የጋራ ጥረት እንደሚጠይቅም አሳስበዋል።

የአንጎላ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት እና ተሰናባቹ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ጆአዎ ማኑኤል ሎሬንዞ፤ በአንድ ዓመት የሕብረቱ ፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት የሚበጁ ሥራዎች በመሰረተ ልማት፣ በኢንቨስትመንት፣ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) እና የሕብረቱ ሪፎርም ሥራዎች ስለመከናወናቸው አስታውሰዋል።

ፕሬዚዳንት ሎሬንዞ ከአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ አኳያ “የአፈሙዝ ዳና የማይሰማባት” የሚለውን አህጉራዊ መፈክር አጽንኦት በአፍሪካ ክፍላተ አህጉራት የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች በአፍሪካዊ መፍትሄ መፍታት እንደሚያሻ ገልጸዋል። ኢ-ህገመንግሥታዊ የመንግሥት ፍንቀላ ልምምዶች በአፍሪካ ሀገራት አሁንም መቀጠላቸውን በማውሳት ድርጊቱን ክፉኛ ኮንነዋል። በሌላ በኩል የአፍሪካ መሪዎች ለዜጎች ተጨባጭና ተለኪ ውጤት የሚያመጡ ከአጀንዳ 2063 ጋር የተጣጣሙ የቤት ሥራዎችን በመከወን፣ የጸናች፣ የተቀናጀችና የበለጸገች አፍሪካን ዕውን ለማድረግ በትጋት እንዲመሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንዳይሺሚዬ የአንጎላውን ጆአዎ ሎሬንዞን በመተካት የ2026 የዓመቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ሆነው በይፋ ተመርጠዋል። አዲሱ ፕሬዚዳንት በጉባዔው ላይ የቀጣናው ሰላምና ደህንነት፣ ኢኮኖሚያዊ ትስስር፣ የወጣቶችና ፈጠራ እንዲሁም ተቋማዊ ሪፎርምን



49

የተመለከቱ ጭብጦች ላይ ያተኮሩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

በፕሬዚዳንቱ ማሳሰቢያ መሰረትም ከሰላምና ደህንነት አኳያ በተለይም በመካከለኛው አፍሪካ፣ በታላላቅ ሐይቆች እና በሳህል ቀጣና ያላባሩ ግጭቶችን ‘የአፈሙዝ ዳና የማይሰማባት አፍሪካ’ የሚለውን የአፍሪካን መሻት ባማከለ አሠራር እልባት ማግኘት እንዳለበት ጠቁመዋል። ለዚህም በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ከኢኮኖሚያዊ ትስስር አኳያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) በማፋጠን ገቢር ነበብ ውጤት ማመጣት፣ በቴክኖሎጂና ግብርና ዘርፍ ኢንቨስትመነትን በማጎልበት ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር እንዲሁም የተጀመሩ የአፍሪካ ሕብረት ተቋማዊ ለውጦችን አጠናክሮ በማስቀጠል በኃላፊነት ዘመናቸው የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

“የአፍሪካ ጥንካሬ በተፈጥሮ ሀብቷ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በዓለም አቀፍ መድረክ በአንድ ድምፅ የመናገር አቅማችን ላይም ጭምር ነው። የ2026ቱን የመሪነት ሚና ስንረከብ፣ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ የተረጋጋች፣ ራሷን የቻለች እና የተሳሰረች አህጉርን መገንባት ይሆናል” ብለዋል።

አፍሪካ ተግዳሮቶቿን ወደ ዕድል ለመቀየር ያላትን ጠንካራ ሀብት፣ እውቀትና ፖለቲካዊ አቅም ያንጸባረቁት የአንጎላ ፕሬዚዳንት ዦአዎ ሎሬንዞ፤ በዳግም አወቃቀር ሂደት ውስጥ ባለው በዘመኑ የዓለም አቀፍ የጂኦፖለቲካዊ መልክ አፍሪካ



50

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በሁሉም መስክ ጥቅምና ፍላጎቷን ለማሳካት የጋራ አቋም መያዝ ያስገድዳታል ነው ያሉት። በተለይም በዓለም አቀፍ ተቋማት መዳከም አፍሪካ ለሕልውናዋና ለሕዝቧ ዘላቂ ደህንነት ተዕጽኖ ውስጥ ላለመውደቅ አባል ሀገራት በጋራ መቆምና ድምጻቸውን ማሰማት ጊዜ የማይሰጠው አጀንዳ ስለመሆኑ አንስተዋል።

የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ በበኩላቸው “የአፍሪካ ብልጽግናና ልዕልና ዋና መዳረሻ ግባችን ነው” ብለዋል። እ.ኤ.አ. በ1963 አዲስ አበባ ላይ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራች አባቶች የፓን-አፍሪካን ርዕይ ለአህጉሪቷ አንድነት፣ ትብብርና ሉዓላዊነት ምሰሶ ወደሚሆን ተጨባጭ ፕሮጀክት መቀየራቸውን አውስተዋል።

የቀደምት መሪዎች ርዕይ ‘ዛሬም ድረስ መነሳሳትን የሚፈጥርልን ውድ ውርስ ነው’ ያሉት ፕሬዚዳንቱ ቡሩንዲ ሪፐብሊክ በአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበርነት ኃላፊነቷን የፓን አፍሪካ ራዕዮች እንዲሳኩ የተቻላትን ሁሉ ጥረት እንደምታደርግ አረጋግጠዋል። በኃላፊነት ዘመናቸው የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም፣ ብዝኃነትን መጠበቅና ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር፣ የአፍሪካ ድምፅ በዓለም አቀፍ መድረክ ጎልቶ እንዲሰማና የአጀንዳ 2063 ውጥኖች እንዲሳኩ እንደሚሠሩ



51

ገልጸዋል። በተለይም በአፍሪካ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት እና የንጽህና ሥርዓት ለማሻሻል አበክረው እንደሚሠሩ ነው የተናገሩት።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀመድ ዓሊ ዩሱፍ የአፍሪካን ወቅታዊ ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫ በተመለከተ በርካታ አገራት ፖለቲካዊ እና ተቋማዊ ድክመት መጨመር፣ ግልጽና ድብቅ የሆኑ ግጭቶች ሥር መስደድ፣ መፈንቅለ መንግሥታት እያገረሹ ስለመሆኑ አንስተዋል። የዓለም አቀፉ ሥርዓት ቀውስ በአፍሪካ ላይ ጉልህ ተጽዕኖ እያሳደረና የባለብዙ-ወገን ግንኙነት እየተፈተነ መሆኑንም እንዲሁ።

አፍሪካ የአንድ ወገን(ተናጠላዊ) ውሳኔዎች እና ፖሊሲዎች እየተስፋፉ በመጡበት ዓለም ፓን- አፍሪካዊ ተቋማትን ማጠናከር እንዳለባት አሳስበዋል። በአጀንዳ 2063 ግቦች ‘የምንመኛት ጠንካራ፣ ራሷን የቻለችና የበለጸገች’ አፍሪካን ዕውን ለማድረግ በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ብለዋል።

የግል ዘርፍ ባለሀብቶች በአፍሪካ ይበልጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ሃሳቦች ተንሸራሽረዋል። ለአብነትም አፍሪካዊያን በኃይል፣ መድኃኒትን ጨምሮ የሕክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እጥረት ፈተናን ለመፍታተ የግሉ ዘርፍ የመሪነት ሚና እንዲወጣም በጉባዔው ተነስቷል።

በዘንድሮው የመሪዎች ጉባዔ የተለያዩ ውሳኔዎችና ስምምነቶች ተደርገዋል። ለአብነትም አጀንዳ 2063ን በፋይናንስ ለመደገፍና የአፍሪካን የፋይናንስ መዋቅር ለማጠናከር የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማት የትብብር ስምምነት ተደርጓል። የስምምነት ሥነ ሥርዓቱን የመሩት የጋናው ፕሬዚዳንት ጆን ማሃማ የአፍሪካ የፋይናንስ ሉዓላዊነት ከነቢብ ወደ ገቢር የተሻገረ ሥራ ይሻል ብለዋል። በዚህም የአፍሪካ የገንዘብ ተቋምን (AMI) እስከ መስከረም 2026 ዓ.ም ድረስ ወደ ሥራ ለማስገባት አባል ሀገራት ረቂቅ ሕጉን እንዲያጸድቁ ጠይቀዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽንም ለስምምነቱ ገቢራዊ መሆን ሚናውን መወጣት እንዳለበት አመልክተዋል። በተመሳሳይ የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ባንክን (AIB) ወደ ሥራ ለማስገባት ከ17 ዓመታት በፊት የቀረበው ምክረ ሃሳብ ተፈጻሚነት ጥሪ አቅርበዋል። አፍሪካ የፋይናንስ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ከዓለም አቀፍ ሥርዓቱ እንዲሻሻል ከመጠየቅ በተጨማሪ የራሷን ውስጣዊ ተቋማትም ማጠናከር ይገባታል ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሉዓላዊነት ከመልክዓ ምድራዊ ድንበር ባሻገር አፍሪካ ራሷን የመተረክ አቅሟን እና መጻዒ ዕድሏን የመወሰን አቅሟን ማሳደግን ታሳቢ ያደረገ ስለመሆኑ አንስተዋል። አፍሪካ ከአጀንዳ ተቀባይነት ወደ አጀንዳ ቀራጺነት መሸጋገር ይገባታል ብለዋል። የአፍሪካ ሕብረት ሩብ ምዕተ ዓመት ምስረታ በዓሉን በሚያከብርበት ዋዜማ ለአህጉራዊ አንድነትና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ወደ ላቀ ተጽዕኖ ፈጣሪ ተቋምነት መሸጋገር እንደሚገባው አንስተዋል። ሕብረቱ ነገ “የምንሻት አፍሪካ” ላይ አበክሮ መሥራት እንደሚገባውም እንዲሁ። በአህጉሪቱ ላይ የሚጫኑ የውጭ ተፅዕኖዎችን ለመቋቋም “የአፍሪካዊያን መፍትሔ ለአፍሪካ ችግሮች” የሚለውን መርህ ከማጠናከር ጋር በማያያዝ አብራርተዋል።



52

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

የአፍሪካ ሉዓላዊነት በአፍሪካ ሐቀኛ ትርክት እና የመጪውን ዘመን ቴክኖሎጂ ዕጣ ፈንታ መወሰንን ያማከለ መሆኑን በመጥቅስ አፍሪካ በዲጂታል አብዮት ውስጥ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ፈጣሪና ቁልፍ ተዋናይ መሆን እንደሚያሻት ነው ያነሱት። የቴክኖሎጂ ራስ በቅነት ለኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ነፃነት ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ዝግጅት ማጠናቀቋን እና ከአጀንዳ 2063 ጋር የተጣጣመ ርዕስ መሰነቋን ጠቅሰዋል። የአፍሪካን ዕውነተኛ ትርክት ለመተረክም የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያን ማቋቋሟን ለአብነት ጠቅሰዋል። የአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን (Af- CFTA) ማጠናከርን፣ የውኃ ደህንነትን ማረጋገጥን እና በዓለም አቀፍ የፀጥታው ምክር ቤት የአፍሪካን ድምፅ በማጉላት ረገድ አንኳር ሃሳብ ሰንዝረዋል።

የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳማይላ ዙባይሩ አፍሪካ ሀብቷን በቅጡ መጠቀም የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ነድፋ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልጋት አንስተዋል። ለአብነትም የጡረታ ፈንድን ለሥራ ፈጣሪ ኢንዱስትሪዎች ማዋል፣ የወርቅ ክምችቷን ለብድር ዋስትና መጠቀም፣ የማዕድን ሀብትን እሴት በመጨመር መጠቀም እንደሚገባት ተነስቷል። የአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ጥምረት (AMFI) አህጉራዊ የፋይናንስ ሥርዓት ወደ አንድ በማምጣት ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባው ተመላክቷል።

ተጋባዥ እንግዶች ምን አሉ?

በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ከሕብረቱ አባል ሀገራት ባሻገር የሌሎች ክፍለ አህጉራት ሀገራትና ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ተወካዮችም ታድመዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የክብር እንግዳ ሆነዋል። አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ስለሚኖራት ተሳትፎ ሲገልጹ “ዛሬ 2026 እንጂ 1946 አይደለም፤ አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል” ሲሉ ተደምጠዋል። በኃላፊነት ዘመናቸውም ሆነ ሥልጣን ከለቀቁ በኋላ አፍሪካ በተመድ ውስጥ ያላት ሚና ከቀዳሚዎቹ ተርታ እንድትሰለፍ ሁልጊዜም ከአፍሪካ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።

“ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” የሚለው ለአፍሪካ ወሳኝ መርህ መሆኑን በማውሳት በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የሚታዩ የጸጥታና አለመረጋጋት ችግሮች በሕብረቱ ማዕቀፍ መፈታት እንዳለባቸው አንስተዋል።

አፍሪካ ተለዋዋጭ ፈተናዎችን በቆራጥነት፣ በፈጠራና በጽናት እየተወጣች መሆኑንም ዕውቅና ሰጥተዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ሀገራት የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በዘላቂነት ገቢራዊ ማድረግ እንደሚያሻቸውም ጠቁመዋል።

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከጉባዔው ጎን ለጎን በሰጡት መግለጫም አፍሪካ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ቢያንስ ሁለት ቋሚ መቀመጫዎች ማግኘት እንዳለባት አጽንኦት ሰጥተዋል። አፍሪካ ከዓለም አቀፍ ውሳኔዎች ተቀባይነት ወደ ውሳኔ ሰጪነት፣ አንጡራ ሀብቶቿን ከብዝበዛ ወደ እሴት ጭመራ ለውጣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ወደሚያረጋግጥ ሥራ መሸጋገር እንዳለባት ጠቁመዋል።



53

አድሏዊና ኢ-ፍትሐዊ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት መለወጥ እንዳለበት በተለይም የአፍሪካ የዕዳ ጫና መቃለልና የብድር አቅርቦትም ሊመቻች እንደሚገባ አንስተው፤ አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ እየቀመሰች ላላው ገፈት የማካካሻ የፋይናነስ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል።

አፍሪካ ሕብረትና ተመድ በሰላም፣ በዘላቂ ልማትና በሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ላይ ያላቸው ስትራቴጂካዊ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋገጡት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ በተባበሩት መንግሥታት እና በአፍሪካ ሕብረት መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር አስፈላጊ ስለመሆኑ በተለይም ለሰላም፣ ለደኅንነት እና ለዘላቂ ልማት ሁለገብ ትብብር ወሳኝ እንደሆነ ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎዋና ፍላጎቷ እያደገ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ለውጥ (የአፍሪካን ውክልና ማጠናከርን ጨምሮ) አስፈላጊ መሆኑን ያረጋገጡበት ንግግር ነበር ያደረጉት። አፍሪካ ሕብረት እና ተመድ ለዓለም ሰላም፣ ጽናትና ብልጽግና በጋራ የመሥራት ቁርጠኝነታቸውን ማጠናከር እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።

ሌላዋ የጉባዔው ተሳታፊ እንግዳ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ነበሩ። ከሁለተኛው የጣሊያን- አፍሪካ ጉባዔ በተጨማሪ በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በጉባዔው የነበራቸውን ተሳትፎ ታሪካዊ ዕድል ብለውታል።

ጣልያን በእኩልነት ላይ የተመሰረተ እውነተኛ ትብብርን እንደምትሻ ገልፀው፤ በአዲስ አበባ በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የጣልያን-አፍሪካ ጉባዔ የዚህ ቁርጠኝነት ማሳያ ስለመሆኑ ተናግረዋል። በማቴ ዕቅድ (Mattei Plan) እና በሌሎች የትብብር መርሀ ግብራት ከአፍሪካ ጋር ስትራቴጂካዊ ትብብራቸው



54

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። የማቴ ዕቅድ የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት በዕውቀት፣ በቴክኖሎጂ እና በኢንቨስትመንት ሁነኛ ትብብር የሚገለጥበት ዕድል እንደሆነ ጠቅሰዋል። ጣልያን አፍሪካዊያን ወጣቶች ከስደት ይልቅ በሀገራቸው ሠርተው እንዲለወጡ በሰው ኃይል እና ክህሎት ልማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንደምትሻ ገልጸዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ መልዕክቶች በእውነተኛ ትብብር፣ በማቴ ዕቅድ፣ የዕዳ ክፍያን ወደ ኢንቨስትመንት ስለመቀየር፣ በአፍሪካ ተስፋና ዕድል ላይ ያተኮረ ነበር። “አፍሪካ ዛሬ ከተመልካችነት ወደ ቁልፍ ተዋናይነት የምትሸጋገርበትን ታሪክ እየተጻፈች ነው” ብለዋል።

የአውሮፓ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በአፍሪካ ላይ የተመሰረተ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ፤ ጣሊያንም ሆነች አውሮፓ ያለ አፍሪካ ንቁ ተሳትፎ የወደፊት ብሩህ ተስፋ ሊኖራቸው እንደማይችል ነው የተናገሩት። ለዚህ ደግሞ የአፍሪካን ሰፊ የተፈጥሮ ጸጋና የሰው ኃይል በቅጡ መጠቀም እንደሚገባ አመልክተዋል። ጣሊያን በአውሮፓና አፍሪካ መካከል እንደ ድልድይ በመሆን ወጣቶች በቴክኖሎጂና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ክህሎት እንዲጎናጸፉ የበኩሏን ሚና እንደምትወጣ አረጋግጠዋል።

ሌላው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ታዳሚ የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሙስጠፋ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፍሪካ ሁልጊዜም ለፍልስጤም ሕዝቦች ነፃነትና ሉዓላዊነት የምታሳየውን የቆየ አጋርነት አድንቀዋል። በቀጣይም በልማት፣ በልምድ ልውውጥና በኢኮኖሚ ውህደት ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነትም አረጋግጠዋል። ወቅታዊ የሀገሪቷን ሁኔታ አሳሳቢነት በማንሳት ግጭቱ በአስቸኳይ ቆሞ ሰላም እንዲሰፍንና ሰብዓዊ ድጋፎች ያለምንም መስተጓጎል እንዲደርሱ ጥሪ አቅርበዋል። አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላትን ሚና እንድታጠናክር ድጋፋቸውን በመግለጽ፣ ለአህጉሪቱ ሕዝቦች ሰላምና ብልጽግናን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ አቅምና ማንነት የተገለጠበት ጉባዔ



55

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔን በስኬት የማስተናገድ አቅሟ በየጊዜው እየጎለበተ መምጣቱ እሙን ነው። የዘንድሮው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔም አዲስ አበባ አዲስ ገጽታ በተላበሰችበት ወቅት መደረጉ ልዩ ያደረገው አጋጣሚ ሆኗል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ከጉባዔው ቀደም ብሎ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ዝግጅት በማድረግና አህጉራዊ አጀንዳዎችን በማንገብ በብቃት አስተናግዳለች።

ለጉባዔው ተሳታፊ እንግዶች ማለትም የአፍሪካ መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ምቹ መስተንግዶ ተደርጎላቸዋል። ይህም ኢትዮጵያ ለፓን- አፍሪካኒዊነት እሳቤ ያላትን የማይለወጥ ጽኑ አቋሟን ያጸና ነው።

ኢትዮጵያ ጉባዔውን ከማስተናገድ ባሻገርም ውሃና የንፅህና አጠባበቅን ጨምሮ በጉባዔው ቁልፍ አጀንዳዎችን በማስተጋባት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውታለች። በዘላቂ የልማት ግቦች፣ ከአጀንዳ 2063 ጋር የተጣጣሙ ተሞክሮዎቿን አካፍላለች። 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ የአዲስ አበባን የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ መዲናነት ያጠናከረ እና ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ትብብርን በማቀናጀት ረገድ ያላትን ብቃት በገሀድ የገለጠ ሆኗል።

የ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እና ሁለተኛው የጣሊያን-አፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ብሔራዊ የዝግጅት ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ጉባዔው “የኢትዮጵያን አዳዲስ ገጽታዎች ያስተዋወቀ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል” ብለዋል።

በጉባዔው 41 የአገራት መሪዎች፣ 48 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ 12 ቀዳማዊት እመቤቶች እና በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃ ሆነው የአገራቸውን ልዑክ የመሩ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። ከውጭና ከአገር ውስጥ ከ20 ሺህ ሰው በላይ ተካፍሏል። ኢትዮጵያ ጉባዔውን በስኬትና በላቀ ደረጃ በማስተናገድ እንግዶቿን በክብር ሸኝታለች። ለእንግዶቿ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማረፊያቸውና መመለሻቸው ባለው ዑደት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ የክብር አቀባበልና አሸኛኘት ሥርዓት አከናውናለች።

ኢትዮጵያ ከጉባዔው በተጓዳኝ የባለብዙ ወገንና የሁለትዮሽ መድረኮችን በመጠቀም ፍላጎቶቿን ያንፀባረቀችበትና ጥቅሞቿን ያስጠበቀችበት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሀገራት መሪዎች ጋር የኢትዮጵያን ጥቅሞች የሚያስጠብቁና ትብብሮችን የሚያጠናክሩ ቁልፍ የሁለትዮሽ ውይይቶችን አካሂደዋል። በተመሳሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ጌዲዎን ጢሞቲዎስ ከሀገራት አቻዎቻቸው ጋር ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረጉ ስኬታማ ውይይቶች አድርገዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አምባሳደር ብርሀኑ ለጉባዔው ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ የፀጥታ አካላት፣ ለሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ባለሙያዎች እንዲሁም የመዲናዋ ነዋሪዎች ለተጫወቱት ሚና አመስግነው፤ ዝግጅቱ ኢትዮጵያ ለቀጣይ ዓለም አቀፍ መድረኮች ያላትን ዝግጁነት ያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል።



56

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ታላላቅ ጉባዔዎችን ማስተናገድ የሚያስችል ሁለንተናዊ አቅም ገንብታለች። ከ1 ሺህ 225 በላይ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ተሳትፈዋል። ይህም የሀገርን ገጽታ የማስተዋወቅ መልካም ዕድል የፈጠረበት አጋጣሚ ነው።

በአዲስ አበባ የተገኙ ግለሰቦችና መሪዎች የአዲስ አበባን ኮሪደር ልማት በማየት ብቻ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የመቻል ተምሣሌት ስለመሆኗ በግልጽ ሲያሞካሹ ተደምጠዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበርና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት አቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ኢትዮጵያ የአፍሪካዊያን የአንድነት ምድርና የመመካከሪያቸው ማዕከል ናት ብለዋል። ኢትዮጵያ ለጉባዔው ስኬት ላደረገችው ድንቅ ዝግጅት ምስጋና አቅርበው፤ አዲስ አበባ የፓን አፍሪካኒዝም ጽኑ መሠረትና የኅብረቱ መገኛ መሆኗን ዳግመኛ ማስመስከሯን ገልጸዋል። በኢትዮጵያዊያን እንግዳ ተቀባይነት እሴት መደነቃቸውንም አውስተዋል።

ኢዜአ ያነጋገራቸው የጉባዔው ታዳሚ እንግዶች ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛነቷ፣ የአፍሪካ መዲናነቷና የአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ትዕምርት ስለመሆኗ በአንድ ድምጽ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ዛሬም የምንሻትን አፍሪካ ለማየት የተወጠነውን አህጉራዊ ርዕይ ዕውን ለማድረግ የጀመረችው ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ ለውጥ ዛሬም ተምሣሌትነቷን ይመሰክራሉ። ለአብነትም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በራሷ ዕውን ማድረጓ፣ በስንዴ ራስን የመቻል ስኬቷና ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች ለሌሎች ሀገራት ተምሣሌታዊ እንደሆኑ ነው ያነሱት።

ሌላው እንግዶቹን ያስደነቀው በኮሪደርና በወንዝ ዳርቻ ልማት አዲስ ገጽታ የተጎናጸፈችው የአዲስ አበባ ከተማ መልክ ነው። በርካታ አስተያየት ሰጪዎች አፍሪካ ውስጥ እንዲህ አይነት ከተማ አለ እንዴ? በሚል እጃቸውን በአፋቸው ጭነዋል። በአጠቃላይ የጉባዔው ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ ምልከታና አድናቆት ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድልን ያበሰረ ነው ማለት ይቻላል።

ጤና ይስጥልን!



57



58

ፖለቲካ

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

የምታሸንፈው ኢትዮጵያ ናት!



59

በምሕረት አንዷለም

መቅድም - የኢትዮጵያ የዴሞክራሲና የልዕልና ጉዞ መሠረት

ታሪክ ራሱን የሚፅፍበት ብዕር የለውም፤ ታሪክ የሚፃፈው በዜጎች የጋራ ትጋት እና በተቋማዊ ብቃትና ቁርጠኝነት ነው። ታሪክ ለነገው ትውልድ ብሩህ ተስፋ መሠረቱ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ በወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። ልክ እንደ ንጋት ጀምበር ስትናፍቀው የኖረችው የዴሞክራሲ ብርሃን በሀገራዊ ለውጡ እውን ወደ መሆን ተሸጋግሯል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገራችን ከምርጫ ሂደት ባለፈ፣ ከቀደሙት ስህተቶች ተምረን፣ የዛሬን ተግዳሮቶች ተሻግረን፣ የነገዋን የበለጸገችና የተረጋጋች ኢትዮጵያ የምንገነባበት፤ በካርዳችን የላቀ ጥቅማችንን ለማስጠበቅና ውሳኔያችንን ለማሳለፍ የምንከታተለው የፉክክርም የትብብርም አውድማ ነው።



60

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ይህ ጉዞ ልክ እንደ አንድ ውብ የቤት ወይም የሕንፃ ግንባታ ነው፤ ቤቱ ጸንቶ እንዲቆም፣ ንፋስና ማዕበል እንዳያናውጠው የማገሩ ጥንካሬ፣ የመሠረቱ ጥልቀትና የግንባታው ጥራት ወሳኝ ናቸው። ምርጫው ሂደቱ የተሳካ፣ ለመራጩ ሕዝብ በቂ ግንዛቤ የሰጠ ጠንካራውን ከደካማ መለየት ያስቻለ ሲሆን መሠረቱ ይጠነክራል። በተጨማሪም ምርጫ ሰላማዊና ስኬታማ የሚሆነው እያንዳንዱ ዜጋ፣ ፓርቲና አስፈጻሚ የድርሻውን ሲወጣ ነው። “ድር ቢያብር. . .” እንዲሉ ለሀገራችን የዴሞክራሲ ባህል መጎልበት፣ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ መሠረት፣ ለልዕልና ጉዟችን አቅም፣ ድህነትን በማሸነፍ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጉዞ ትልቁ ጉልበት ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በመጀመሪያ የፓርላማ ንግግራቸው፤ “የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መደማመጥን ይጠይቃል። ሕዝቡ አገልጋዩን የመተቸት፣ የመምረጥ፣ የመጠየቅ ሙሉ መብት አለው። . . . በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ውስጥ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም መርህ በመደማመጥ የሀሳብ ልዩነትን ማስተናገድ መሆን አለበት። ኢትዮጵያ የጋራችን የእኛ የሁላችን መሆኗን ተገንዝበን የሁሉም ድምፅ የሚሰማበት፣ ሁላችንንም የሚያሳትፍ፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመገንባቱን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን” በማለት የገለጹት ዴሞክራሲ በመደማመጥ፣ በሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት ላይ የሚገነባ መሆኑን ያሳያል።



61

በተጨማሪም መንግሥት በሁሉም ተሳትፎ ለሚገነባ ዴሞክራሲ ያለውን የጸና አቋም የሚያረጋግጥ ነው። የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሀሁ የሚጀምረው ከመንግሥት የፖለቲካ ቁርጠኝነት ነው፤ ይሁንና ሕይወት የሚዘራውና ፍጹም የሚሆነው በዜጎች ንቁ ተሳትፎና በገለልተኛ ተቋማት ጥብቅ ቁጥጥር መሆኑን ልብ ይሏል። የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ በባህሪው ለብቻ የሚሮጥበት ሜዳ አይደለም። ይልቁንም አንዱ ለሌላው ጉልበት የሚሆንበት፣ የሀሳብ ልዩነቶች እንደ ጌጥ የሚታዩበትና የሕዝብ ድምፅ የሚከበርበት የብዙ ባለድርሻዎች ሚና የሚገለጥበት መድረክ ነው።

በዚህ ታላቅ ሀገረ መንግሥት የመገንባት ሂደት ውስጥ መንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፍትሕ ተቋማት፣ የሲቪል ማኅበራት፣ መገናኛ ብዙኃንና እያንዳንዱ ዜጋ የየራሳቸው ሚና አላቸው። እነዚህ አካላት ልክ እንደ አንድ አካል ተሳስረው፣ እንደ ሠዓት መዘውሮች ተናበው ሲሠሩ ብቻ ነው የዴሞክራሲ እግሮች በትክክል የሚራመዱት።

የ2010 ዓ.ም ሀገራዊ ለውጥ ከሌሎች የሥልጣን ሽግግሮች የሚለየው የትውልድ የዴሞክራሲ፣ የፍትሐዊነት እና የወንድማማችነት ጥያቄዎች ተደማምረው በአንድ መድረክ ላይ በመምጣታቸው ነው። ይህ መንገድ ነባር ስብራትን በመጠገንና ለአዲስ ትውልድ የምትሆን ሀገረ መንግሥት በመገንባት ላይ የቆመ ነው።

ጄፍሪ ጆዌል (Jeffrey Jowell) The Rule of Law በሚለው መጽሐፉ የገለጸው ሀሳብ “ምርጫ ዜጎች በሀገራቸው ድርሻ እንዳላቸው የሚያሳዩበት ሂደት ነው። ድምፅ መስጠት ማለት ‘እኔ የዚህች ሀገር ባለቤት ነኝ፣ ነገዬም በእጄ ነው’ ብሎ ማወጅ ነው” በማለት ምርጫ የሥልጣን ሽግግር ማድረጊያ መንገድ ብቻ አለመሆኑን ያንፀባርቃል።

ስለሆነም ምርጫ ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ያላቸውን ባለቤትነት የሚያረጋግጡበት፣ በሀሳብ ልዕልና የሚያምኑበትና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን በራሳቸው ብዕር የሚጽፉበት የሉዓላዊነት ማረጋገጫ ማህተም ነው። ለዚህ ሀሳብ ማጠናከሪያ ዣን ዣክ ሩሶ “The Social Contract” በሚለው መጽሐፉ “ሉዓላዊነት ሊወከል አይችልም፣ ምክንያቱም ተለይቶ ሊሰጥ ስለማይችል... ሉዓላዊነት በዋናነት በጠቅላላ ፈቃድ (የሕዝብ ፍላጎትና ይሁንታ) ላይ የተመሠረተ ነው” ያለውን በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል።

በታሪክ መስታወት - የኢትዮጵያ የምርጫ ጉዞ

ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን የሀገረ መንግሥት ታሪክ ባለቤት ናት፤ ለዴሞክራሲም ባዕድ አይደለችም። ሆኖም ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በመንግሥታዊ መዋቅሯ ውስጥ ለመትከል ዘርፈ ብዙ ተጋድሎዎችን አልፋለች። እንደ ቅጽበት ውልብ ብለው ያለፉት እነዚህ አሥርት ዓመታት ለዘመናት ያህል የሚከብዱ የለውጥ ማዕበሎች የታዩባቸው ናቸው። ኢትዮጵያም ተስፋና ሥጋት፣ ዕድልና ፈተና እየተፈራረቁባት አያሌ ውጣ ውረዶችን ተሻግራ ዛሬ ላይ ደርሳለች። ባለፉት ዘመናትም ዴሞክራሲን ለመትከል በርካታ የምርጫ መድረኮችን አስተናግዳለች፤ ከንጉሡ ዘመን የሚጀምር የምርጫ ታሪክም አላት።

የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ “የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1847 እስከ 1983” በሚለው መፅሐፋቸው



62

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

እንደጠቀሱት፤ የኢትዮጵያ የፓርላማ ታሪክ የጀመረው በ1923 ዓ.ም በመጀመሪያው የተጻፈ ሕገ - መንግሥት ቢሆንም እስከ 1948 ዓ.ም ድረስ የነበሩት እንደራሴዎች በሕዝብ ሳይሆን በንጉሡና በባላባቶች ይመረጡ ነበር። ይህ የሚያሳየው በወቅቱ የምርጫው ሂደት ፍጹም አግላይና በታማኝነት ላይ የተመሠረተ እንደነበር ነው። በ1948 ዓ.ም የተሻሻለው ሕገ-መንግሥት ሕዝቡ በቀጥታ እንዲመርጥ ቢፈቅድም፣ ለተመራጭነት የተቀመጠው የሀብት፣ የንብረትና የማኅበራዊ መደብ መስፈርት አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል ያገለለና አካታችነት የጎደለው ነበር። የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላትም የሚመረጡት በባላባቶችና በመኳንንት ነበር።

በደርግ ዘመነ መንግሥት የምርጫ ተሳትፎ የታየበት የ1979 ዓ.ም የሸንጎ ምርጫ ላይ ነው። ኢትዮጵያ ከረጅም ወታደራዊ አገዛዝ ወደ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ለመሸጋገር የሞከረችበት አዲስ ምዕራፍ ነበር። በዚህ ወቅት 835 አባላት ያሉት የሥራ ዘመኑ አምስት ዓመት የሆነ “ባለ አንድ ሸንጎ ምክር ቤት” በምርጫ የተሰየመ ሲሆን፤ የመራጭነት ዕድሜ ከ18 ዓመት መጀመሩ በቁጥር ደረጃ ከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ እንዲታይ አድርጓል። ይሁን እንጂ ሂደቱ ዴሞክራሲያዊነት ያልታየበት በሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም የተወሰነው የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ለብቻው የቀረበበት ዕጩ የሚጠቁመው፣ የሚያስመርጠውና ተመራጩም ራሱ ፓርቲው ወይም በፓርቲው መታመን ያገኘ ሰው ብቻ የነበረበትና በተግባር “ጠቋሚውም፣ አስመራጩም፣ ተመራጩም ራሱ ፓርቲው” የሆነበት አግላይ የፖለቲካ ክስተት ነበር።

የደርግ ሥርዓት በ1983 ዓ.ም መክሰሙን ተከትሎ ኢሕአዴግ እና ልዩ ልዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የሽግግር መንግሥት መሥርተዋል። በዚህ ወቅት የጸደቀው ቻርተር 86 አባላት ያሉት የሽግግር መንግሥት ምክር ቤት እንዲመሠረት ያስቻለ ነው። በ1984 ዓ.ም በወጣው አዋጅ መሠረትም የመጀመሪያው የምርጫ ኮሚሽን ተቋቁሟል። በዚያው ዓመት በየካቲት የወረዳና የቀበሌ ጊዜያዊ አስተዳደር ምርጫዎች ተከናውነዋል። በግንቦት ደግሞ ብሔራዊ፣ ክልላዊ፣ የዞንና የወረዳ ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ተካሂዷል። ይህም ሀገሪቷ ከወታደራዊ አገዛዝ ወደ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ የተሻገረችበት የመጀመሪያው የምርጫ እንቅስቃሴ ተደርጎ ይወሰዳል፤ ይሁን እንጂ በዴሞክራሲያዊነቱ ጥሩ ስም አልተከለም።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና የአምስቱ ምርጫዎች ዳሰሳ (1987-2007)

የሽግግር መንግሥቱ የምርጫ ኮሚሽን ሥራውን አጠናቆ ሲጨርስ በምትኩ በአዋጅ ቁጥር 64/1985 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ተቋቋመ። ከዚያም በ1987 ዓ.ም የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መጽደቁን ተከትሎ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማቋቋሚያ አዋጁን በማሻሻል ሕገ መንግሥቱን የተገበረ ምርጫ ተካሄደ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ እንደሚያሳየው ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ስድስት ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ፤ አራት የአካባቢ ምርጫ፣ እና ሥምንት ሕዝበ ውሳኔዎችን አካሂዷል። እንዲሁም የተለያዩ የማሟያ እና ድጋሚ ምርጫዎችን በተለያዩ ዓመታት አከናውኗል፡: በአጠቃላይ 18 ምርጫዎችን አስፈጽሟል፡፡ እስከ አሁን በተከናወኑት ስድስት ሀገር አቀፍ ጠቅላላ



63

ምርጫዎች ለ547 የፌዴራል መቀመጫዎች እና ለ654) የክልል መቀመጫዎች ዕጩዎች ቀርበው የተወዳደሩ ሲሆን፤ የሕዝብ ይሁንታ ያገኙት መንግሥት መመሥረት ችለዋል።

ከ1987 ዓ.ም እስከ 2013 ዓ.ም የተካሄዱትን ስድስት ምርጫዎች ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ዋቢ በማድረግ ስንቃኛቸው በ1987 ዓ.ም የተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ጠቅላላ ምርጫ 43 የፖለቲካ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ 21 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች ተመዝግበው 20 ሚሊዮን የሚሆኑት ድምፅ ሰጥተዋል። በውጤቱም ኢሕአዴግ እና አጋር ድርጅቶቹ አብላጫውን ወንበር ሲያሸንፉ፤ 10 የግል ተወዳዳሪዎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ አግኝተዋል። በወቅቱ የሴቶች ተሳትፎ ዝቅተኛ ነበር።

ቀጣዩ ሁለተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በ1992 ዓ.ም ሲካሄድ የመራጮች ቁጥር ጥቂት ጨምሮ 21 ነጥብ 6 ሚሊዮን ደረሰ ከዚህም 19 ነጥብ 6 ሚሊዮን መራጮች ድምፅ ሰጡ። ኢሕአዴግ የፓርላማውን አብላጫ መቀመጫ ሲቆጣጠር፤ በፌዴራል የግል ተወዳዳሪዎች 13፣ በክልል ደግሞ 27 መቀመጫዎችን በማሸነፍ የሕዝብ ተወካይ መሆን ቻሉ።

በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ከፍተኛ መነቃቃት የተስተናገደበት የ1997 ዓ.ም ሦስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነው። በወቅቱ የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍቶ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በከፍተኛ መነቃቃትና በኃይል ብቅ ያሉበት ነበር። ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ እና ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ እንዲሁም ሌሎች ፓርቲዎች ሲያደርጉት የነበረው ጠንካራ ፉክክር አይዘነጋም። በወቅቱ 27 ነጥብ 3 ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበው 22 ነጥብ 6 ሚሊዮን ያህሉ ድምፃቸውን ሰጥተዋል። በዚህ ምርጫ ኢሕአዴግ 327 መቀመጫዎችን ሲያገኝ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ታሪካዊ የሚባል ውጤት አስመዝግበዋል። ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ 109



64

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ወንበሮችን፣ ኢዴኃን 52 ወንበሮችን እንዲሁም ኦፌዴን 11 ወንበሮችን ማግኘት ችለዋል።

አራተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በ2002 ዓ.ም የተካሄደው ነው። በወቅቱ የመራጮች ቁጥር ወደ 31 ነጥብ 9 ሚሊዮን አደገ፤ ከዚህም 93 ነጥብ 4 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ድምፅ ሰጥቷል። በምርጫው 63 የፖለቲካ ድርጅቶች የተሳተፉ ቢሆንም ኢሕአዴግ እና አጋሮቹ 99 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆነውን የፓርላማ መቀመጫ አግኝተዋል።

የመራጮች ቁጥር 36 ነጥብ 8 ሚሊዮን የደረሰበትና እጅግ ከፍተኛ ተሳትፎ የታየበት፤ 58 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወዳደሩበት፤ በውጤቱም ኢሕአዴግ እና አጋር ድርጅቶች የፓርላማና የክልል ምክር ቤቶች ወንበሮችን ሙሉ በሙሉ የያዙበት የ2007 ዓ.ም አምስተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ነው። የምርጫ ሂደቱ ተፎካካሪዎች ጠንካራ እንዳይሆኑ የተደረገበትና ብዝሃ ሀሳብ የሌለበት በመሆኑ በኢ- ዴሞክራሲያዊነቱ የተተቸ ነው።

እነዚህ አምስት ተከታታይ ምርጫዎች የሕዝብን እውነተኛ ተሳታፊነት የገደቡ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የውድድር ሜዳ ያጠበቡና የፖለቲካ ምህዳሩን ዝግ ያደረጉ በመሆናቸው፤ በሂደት የዜጎችን ተስፋና እምነት እያሟጠጡ የመጡ ናቸው። ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ‘ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ በሚለው መፅሐፋቸው “ኢሕአዴግ ባለ ሕገ መንግሥት እንጂ በሕግ የሚመራ መንግሥት አልነበረም” ሲሉ በመግለጽ የኢሕአዴግን ኢ-ዴሞክራሲያዊነት ተችተዋል። በምርጫ ሂደቶቹ ላይ የታየው ተቋማዊ ድክመትና የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበብ፣ ሕዝቡ ለለውጥ እንዲነሳሳ የሚያደርግ ትልቅ ግፊት ሆኗል። በዚህም ምክንያት የቀደሙት ምርጫዎች የፈጠሩት የዴሞክራሲያዊነት ክፍተት በ2010 ዓ.ም ሀገራዊ ለውጥ እንዲወለድ ገፊ ምክንያት ሆነዋል። ለስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ እንደ መንደርደሪያ በማገልገል ሀገሪቷ ወደ አዲስ የለውጥ ምዕራፍ እንድትሻገርም ምክንያት ሆኗል።

አዲስ ምዕራፍ

በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተው በ2013 ዓ.ም የተካሄደው ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ፤ ወቅቱ ተቋማዊ ሪፎርም የተደረገበትና ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ አመራር የተሰየመበት ነበር። 37 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች ለምርጫው ሲመዘገቡ፤ 40 የሚጠጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፈውበታል።



65

ገዥው ብልፅግና ፓርቲ አብዛኛውን ወንበሮች ሲያሸንፍ፣ ቀሪዎቹ በኢዜማ፣ በአብን እና በጌዴኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እንዲሁም በግል ተወዳዳሪዎች ተይዘዋል።

ይህንን ምርጫ ያስፈጸሙት የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ “ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ሰላማዊ ምርጫ ማከናወን እንደሚቻል ትምህርት የሰጠ ነው” በማለት ነው የገለጹት። ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሕዝቡ ያለውን ቁርጠኝነት ያመላከተም ነው። “ምርጫው በኢትዮጵያ የሥልጣን ሽግግር የሚደረገው በምርጫ ካርድ ብቻ መሆኑን አሳይቷል” በማለት ሕዝቡ ፍላጎቱን በካርዱ መወሰኑንም አረጋግጠዋል።

በአጠቃላይ ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በጸጥታና በሌሎች ችግሮች ውስጥ ቢካሄድም የምርጫ ተቋማትን ገለልተኝነት ለማረጋገጥና ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምጹን እንዲሰጥ የተደረገው ጥረት ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ እንደ ትልቅ ሽግግር የሚወሰድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረጉት ንግግር “ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ከእንከኖች የጸዳና እጅግ የተሳካ ነበር ባይባልም የዘመናት ጥያቄ የነበረውን ዴሞክራሲን የመትከልና የማጽናት ህልም እውን ለማድረግ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል፤ አንድ እርምጃም ወደፊት አራምዶናል” ሲሉ የገለጹት የምርጫ ሂደቱ ለዴሞክራሲ ልምምድ ላቅ ያለ ዕሴት መጨመሩን ያረጋግጣል።

ኢትዮጵያ አሁን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅቷን አገባዳለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንኑ አስመልክቶ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ “ምርጫ መሆን ያለበት በሃሳብ ላይ ተመስርቶ ነው። ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ሲሆን ፋይዳው የጎላ ይሆናል። ለምርጫ ድምፅ የሚሰጡ ዜጎች እንደ ‘ጡብ’ ናቸው፤ በምርጫው የሚሳተፉ ፓርቲዎች ደግሞ እንደ ‘ማገር’ ይቆጠራሉ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጡቦችና ከ50 በሚልቁ ማገሮች (የፖለቲካ ፓርቲዎች) የሚገነባ ጠንካራ ቤት እንዲኖረን፣ በርካታ ዜጎች ድምፃቸውን ሊሰጡ ጡባቸውን ሊጥሉ፣ ተፎካካሪዎችም ሃሳባቸውን (ማገራቸውን) ሊያኖሩ ይገባል። ያለበለዚያ ጠንካራ ቤት መገንባት አንችልም” ሲሉ አፅንኦት ሰጥዋል።

የዘንድሮው ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና አካታች እንዲሆን፤ ባለፈው ካየነው ምርጫ በሁሉም መስፈርት የተሻለ እንዲሆን አበክረን እየሠራን እንገኛለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “በዚህ ፓርላማ አሁን ካለው ቁጥር በአምስትና በአሥር እጥፍ የላቁ ልዩ ልዩ ድምፆች ይሰማሉ ብዬ አምናለሁ፤ ያንንም እፈልጋለሁ። የአንድ ፓርቲ ድምፅ ብቻ መሆን ለኢትዮጵያ አይጠቅማትም” ብለዋል። መንግሥት ይህንን አውድ ለማስፋት ብቻ ሳይሆን፣ ‘ይሁነኝ’ ብሎ በትኩረት እንደሚሠራበት ሲገልፁም፤ “በጣም ጠቃሚ የሚባሉ ግብዓቶችን የምናገኘው ከተፎካካሪዎች ነው፤ ተፎካካሪዎች መኖራቸው በተለይ ለኢትዮጵያ ትልቅ ፋይዳ እንጂ ጉዳት የለውም” ብለዋል።

የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ

ከሀገራዊ ለውጡ በፊት የኢትዮጵያ ምርጫ ታሪክ የሚያረጋግጠው አብዛኛዎቹ በአግላይነትና በአንድ



66

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ወገን የበላይነት የተሞሉ እንደነበሩ ነው። እንደሚታወቀው የ2010 ዓ.ም ሀገራዊ ለውጥ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አዲስና ምቹ መሠረት ጥሏል። ለውጡ ምርጫን የይስሙላ የሥልጣን ማራዘሚያ ከመሆን አውጥቶ፣ እውነተኛ የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባላቤትነት የሚንጸባረቅበት ተቋማዊ አሠራር አድርጎታል። ለአብነትም በለውጡ በሕግ ረገድ የተከናወኑት ማሻሻያዎች ለስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት ዋነኛ ምሰሶዎች ነበሩ። ከእነዚህም መካከል ቀደም ሲል የነበሩ አፋኝና ገዳቢ ሕጎችን በመለወጥ ረገድ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፦

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ (ቁጥር 1133/2011) ይህ አዋጅ ቦርዱ ከአስፈፃሚው አካል “ምርጫ መሆን ያለበት በሃሳብ ላይ ተመስርቶ ነው። ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ሲሆን ፋይዳው የጎላ ይሆናል። ለምርጫ ድምፅ የሚሰጡ ዜጎች እንደ ‘ጡብ’ ናቸው፤ በምርጫው የሚሳተፉ ፓርቲዎች ደግሞ እንደ ‘ማገር’ ይቆጠራሉ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጡቦችና ከ50 በሚልቁ ማገሮች (የፖለቲካ ፓርቲዎች) የሚገነባ ጠንካራ ቤት እንዲኖረን፣ በርካታ ዜጎች ድምፃቸውን ሊሰጡ ጡባቸውን ሊጥሉ፣ ተፎካካሪዎችም ሃሳባቸውን (ማገራቸውን) ሊያኖሩ ይገባል። ያለበለዚያ ጠንካራ ቤት መገንባት አንችልም’’

ተፅዕኖ ነፃ ሆኖ በገለልተኝነት እንዲመራና የራሱ በጀትና የሰው ኃይል አስተዳደር እንዲኖረው በማድረግ ተቋማዊ ነፃነቱን አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ (ቁጥር 1162/2011) አዋጁ ቀደም ሲል የነበሩትን በርካታ የተበታተኑ የምርጫ ሕጎች በአንድ ላይ በማቀናጀትና ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በማካተት



67

የተሻሻለ ነው። አዋጁ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓትን የሚያበረታቱ፣ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ምቹ የውድድር ሜዳ የሚፈጥሩና የሴቶችን ተሳትፎ የሚያሳድጉ ድንጋጌዎችን ይዟል።

የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች አዋጅ (ቁጥር 1113/2011) ቀደም ሲል የነበረውን አፋኝ ሕግ በመቀየር፣ የመደራጀት መብትን በማፅናት ሲቪል ማኅበራት በዴሞክራሲ ግንባታና በዜጎች የፖለቲካ ንቃት ላይ በነፃነት እንዲሳተፉ በር ከፍቷል።

የመድበለ ፓርቲ ሥርዓትና አካታችነት

ይህ የሪፎርሙ ሌላኛው ገጽታ ነው። ቀደም ሲል በጠባብ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ታጥረው የቆዩና በሰላማዊ መንገድ መታገል ያልቻሉ የፖለቲካ ኃይሎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ መደረጉ በስድስተኛው ምርጫም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የፓርላማ ወንበር ማግኘታቸው የለውጡን ጉዞ ተጨባጭነት ያሳያሉ። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ “የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ስኬታማ የሚሆነው ልዩነቶችን በማክበርና አሳታፊ የፖለቲካ ባህልን በማዳበር ነው። ሪፎርሙ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ ፓርቲዎች በነፃነት አማራጭ ሀሳብ ይዘው እንዲቀርቡና ሕዝቡም በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲሰጥ አስችሏል” በማለት የገለጹት ሪፎርሙ ውጤታማ መሆኑን ያሳያል።

ኢትዮጵያ በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ወደ ዴሞክራሲ የተደረገ ሽግግርን በተግባር አሳይታለች። ተግዳሮቶች ቢታዩም፣ ምርጫው የሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር መሠረት እንዲሆን መደረጉ፣ ሀገሪቷ ከውድቀትና ከአግላይነት ታሪክ ወጥታ ወደ ተቋማዊ ዴሞክራሲ እያመራች መሆኗን አብስሯል፤ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም ትልቅ መሠረት ጥሏል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ

አሁን ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ደርሰናል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያዊያን በድምጻቸው መንግሥት መመስረት ይችላል ለሚሉት ፓርቲ ይሁንታቸውን ይሰጣሉ። የዘንድሮው ምርጫ ከቀደሙት የሚለየው በተቋማዊ ግንባታው ጥልቀትና በባለድርሻ አካላት መካከል በተፈጠረው አዲስ የመከባበር መንፈስ ነው። የሲቪል ማኅበራት በመንግሥት እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር መታየት ጀምረዋል። ይህ አዲስ ምዕራፍ ዜጎች በነጻነት የመደራጀትና ሀሳባቸውን የመግለጽ መብታቸው በሕግ ብቻ ሳይሆን በተግባር መከበሩን የሚያሳይ ተጨባጭ ምስክር ነው። የሕግ የበላይነትና የፍትሕ ተቋማቱ ራሳቸውን ከፖለቲካ ተጽዕኖ አላቀው ለሕዝብ አገልግሎት መዘጋጀታቸው ለዴሞክራሲ ግንባታ ትልቁን ዋስትና ሰጥቷል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ተቋማዊ ሪፎርም የምታጸናበት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂንና ዘመናዊ አሠራርን በማቀናጀት የምርጫ ስርቆትንና የመራጭ ዜጎቿን እንግልት የታሪክ ትዝታ የምታደርግበት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው። የምርጫው ሂደት ትልቅ ትምህርት ቤት ነው፤ ለፖለቲከኞች የሠለጠነ ፉክክርን፣ ለተቋማት ገለልተኝነትን፣ ለዜጎች ደግሞ ኃላፊነትንና ባለቤትነትን ይበልጥ እንደሚያስተምር ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥር 26



68

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ቀን 2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ “ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ አለብን፤ አማራጭ ድምፆችን ለመስማት ዝግጁ መሆን አለብን። እንደ መንግሥትም እንደ ፓርቲም አማራጭ ድምጾች የሌሉበት ምክር ቤት አይፈይድም፣ አይጠቅመንም” በማለት የገለጹት ሀሳብ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከመቼውም ጊዜ የተሻለ እንደሚሆን የመንግሥት ፅኑ እምነት መሆኑን ያንፀባርቃል።

ዮሴፍ ሹምፒተር Capitalism, Socialism, and Democracy (1942) በተሰኘው መጽሐፉ “ዴሞክራሲ በአንድ ወቅት ተሰርቶ የሚያልቅ ሳይሆን፣ በየጊዜው በሚደረጉ ምርጫዎችና በሀሳብ ፉክክሮች ውስጥ የሚዳብር ሂደት ነው” ሲል እንደገለጸው፤ ዴሞክራሲ የአንድ ጀምበር ውጤት ባለመሆኑ በትዕግሥትና በጽናት መገንባት የሁላችንም ኃላፊነት ነው። እያንዳንዱ ዜጋ፣ ፓርቲ፣ ታዛቢና ባለድርሻ አካል የሚወጣው ሚና ለሀገር ግንባታ ወሳኝ ጡብ ነው። የጋራ ራዕያችን የበለጸገች፤ ሰላም፣ ፍትሕና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ማየት እስከሆነ ድረስ ጥረታችን ሁሉ ለዚህ ክቡር ዓላማ መዋል አለበት። በታሪካዊው የምርጫ ቀን እያንዳንዳችን የምንሰጠው ድምፅ እንደ ግል፣ ቡድንና ሀገር የነጻነታችን ዜማና የሉዓላዊነታችን ምስክር ሆኖ ያገለግላል።

የምርጫ ሂደቱ አሳታፊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ መሆን በራሱ ትልቅ ድል ነው። በሰላማዊ መንገድ ተወዳድሮ፣ በሀሳብ ልዕልና አምኖና የሕዝብን ውሳኔ በጸጋ ተቀብሎ ለሀገር ልማት በጋራ መቆም የሥልጣኔ መለኪያ ነው። ኢትዮጵያ ከምንም እና



69

ከማንም በላይ መሆኗን በተግባር የምናሳይበት ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ በታላቁ የዴሞክራሲ አደባባይ ላይ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ ለነጻነት፣ ለፍትሕና ለሰላም ሲቆም የታሪክ መዝገብ በትልቅ ኩራት ይከፈታል፤ በዚያም ላይ በደመቀ ቀለም የሚሰፍረው ሐቅ አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም የምታሸንፈው ኢትዮጵያና ኩሩው ሕዝቧ መሆናቸው ነው።

ኢትዮጵያን ወደ ዳበረ የዴሞክራሲ ባህል ከፍ ለማድረግ መሠረቱ እንጂ ግንባታው ገና አልተጠናቀቀም። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት የዛሬው ትውልድ ለነገው ትውልድ የሚያወርሰው የዴሞክራሲ ቅርስ፣ የኢትዮጵያ የትንሣኤ ብርሃንና የሕዝባችን የጽናት መግለጫ ሆኖ በታሪክ መዝገብ ላይ በደመቀ ቀለም መጻፍ አለበት።

የምርጫ ቦርድ ተቋማዊ ትንሣኤ እና የቴክኖሎጂ ምዕራፍ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ ለማድረግ ሰፊ ተቋማዊ ሪፎርሞችን እና የዲጂታላይዜሽን ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 መሠረት ራሱን በአዲስ መልክ ያዋቀረው ቦርዱ፤ ለተቋማዊ ገለልተኝነት ከአመራር ጀምሮ እስከ አሠራር ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል። ይህም ቦርዱ የሚሰጣቸው ውሳኔዎች በሕግና በዕውቀት ላይ የተመሠረቱ እንዲሆኑ ማስቻሉ ነው የሚገለጸው። “ተቋማዊ ሽግግሩ ቦርዱን ከፖለቲካ ተፅዕኖ በማላቀቅ ወደ ሙያዊና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋምነት ለውጦታል” በማለት ነው የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የሚናገሩት። ይህንንም ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተዓማኒነት እንደ ዋና ምሰሶ የሚታይ ስኬት አድርጎ መውሰድ ይቻላል።

የምርጫ ጣቢያዎች ገለልተኝነት - ቦርዱ ካደረጋቸው ትልልቅ ማሻሻያዎች አንዱ የምርጫ ጣቢያዎችን አመዳደብና አደረጃጀት መለወጥ ነው። ቀደም ሲል የምርጫ ጣቢያዎች በቀበሌና በወረዳ ቢሮዎች ውስጥም ይቋቋሙ የነበረ ሲሆን፤ ይህም መራጮች ላይ ፖለቲካዊ የሥነ-ልቦና ጫና ይፈጥር ነበር። እንደ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ገለጻ በአሁኑ ወቅት ከ52 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች በገለልተኛ ስፍራዎች እንዲደራጁ ተደርጓል። ይህ አሠራር መራጩ ዜጋ ያለምንም ስጋትና ፍርሃት ድምፁን ለፈለገው ዕጩ እንዲሰጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።



70

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በተጨማሪም የምርጫ ጣቢያዎቹ ተደራሽነት ለአካል ጉዳተኞችና ለሴቶች አመቺ እንዲሆኑ ልዩ ጥንቃቄ ተደርጓል። ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ለሀገር መከላከያ ሠራዊትና ለተፈናቃዮችም ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች ተቋቁመዋል። ጣቢያዎቹ ከፖለቲካዊ ተጽዕኖ ነፃ መሆናቸው የምርጫውን ውጤት ታማኝነት ከመገንባቱም በላይ ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ያስችላል።

ዲጂታላይዜሽን - የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አዲስ ገጽታ ነው። በዚህ ምርጫ የታየው ትልቁ የቴክኖሎጂ ስኬት የዕጩዎች ምዝገባ ሂደት ዲጂታላይዝ መደረጉ ነው። ቀደም ሲል ዕጩዎች ለመመዝገብ ረጅም ርቀት መጓዝና የቢሮክራሲ መጉላላት ያጋጥማቸው ነበር። አሁን ግን 47 የፖለቲካ ፓርቲዎችና 10 ሺህ 934 ዕጩዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በኢንተርኔት አማካኝነት ራሳቸው መመዝገብ ችለዋል።

አሠራሩ “ቢሮ ተዘጋብኝ ወይም ሰነድ አልተቀበሉኝም” የሚሉ ቅሬታዎችን ሙሉ በሙሉ አስቀርቷል። ቴክኖሎጂው ግልፅነትን ከማስፈኑም በላይ ቦርዱ የዕጩዎችን መረጃ በፍጥነት እንዲያጣራና ይፋ እንዲያደርግ ረድቶታል” በማለት የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ የተናገሩት የቦርዱን የስኬት ድምር ያሳያል። ዲጂታል ምዝገባው ለሴት ዕጩዎችና ከርቀት ለሚመጡ የግል ዕጩዎች ትልቅ እፎይታን ሰጥቷል። ይህም ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምርጫን እንዴት ዘመናዊና ፍትሐዊ ማድረግ እንደሚቻል ትልቅ ትምህርት የሰጠ ነው።

የመራጮች ዲጂታል መለያና ምዝገባ - ከየካቲት 28 እስከ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የመራጮች ምዝገባን ከመዝገብ ላይ በተጨማሪ በዲጂታል ሥርዓት በስማርት ስልክና በታብሌት ተከናውኗል። ይህ ለኢትዮጵያ ምርጫ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ነው። ስማርት ስልክ ያላቸው ዜጎች ደግሞ በ“ምርጫዬ” መተግበሪያ አማካኝነት ራሳቸውን መመዝገብ መቻላቸው የምዝገባ ሂደቱን



71

እጅግ ዘመናዊ አድርጎታል። ዲጂታል ምዝገባው ከአጠቃላይ ምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ17 ሺህ ጣቢያዎች ላይ ነው የተጀመረው። በዲጂታል የተመዘገቡ መራጮች መረጃቸው ለዘንድሮው ምርጫ ብቻ ሳይሆን ለቀጣይ ምርጫዎችም በመረጃ ቋት ውስጥ ይቀመጣል። ቴክኖሎጂው በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች መበልፀጉ ደግሞ ለሀገራዊ ኩራትና ለደህንነት ዋስትና ነው። ይህ የዲጂታላይዜሽን ጉዞ በሂደት መላ ሀገሪቷን በማካተት ወደፊት በኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ድምፅ መስጠት (E-voting) ለመሸጋገር እንደ መሠረት የሚወሰድ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው።

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማስፈጸሚያ የሚሆን በመንግሥት 10 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ተመድቧል፤ ይህም ከቀደሙት ምርጫዎች ጋር ሲነፃፀር በሀገር ውስጥ አቅም ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። በምርጫ ቁሳቁስና በሎጂስቲክስ ረገድም ከዚህ ቀደም ከነበሩት ምርጫዎች ሁሉ ደህንነቱ የተጠበቀና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ትልቅ ሥራ የተሠራበት ነው።

የሲቪል ማኅበራት ስትራቴጂካዊ የምርጫ አጋርነት

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ያከናወነችው ሀገራዊ ሪፎርም አንዱ ዋነኛ ትኩረት የዴሞክራሲ ተቋማትን ነፃ፣ ገለልተኛ እና ተዓማኒ ማድረግ ላይ የተመሠረተ ነው። ይህ የሪፎርም ሂደት በተለይም ቀደም ሲል የነበሩ ገዳቢ ሕጎችን በማሻሻል ምህዳሩ እንዲሰፋና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በሀገር ግንባታ ውስጥ ያላቸው ድርሻ እንዲጎለብት ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። ይህ ለውጥ መንግሥት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ማሳያ ከመሆኑም ባለፈ በዜጎችና በገዥው አካል መካከል አዲስ የመተማመን ድልድይ ለመገንባት መሠረት ጥሏል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ “መንግሥት ከሪፎርሙ ማግሥት ጀምሮ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር መመልከት ጀምሯል” በማለት ነው የመንግሥትን አተያይ የገለጹት። ይህ አጋርነት ቀደም ሲል የነበረውን የጥርጣሬ ግንኙነት በማስወገድ ድርጅቶቹ በፖሊሲዎች ላይ ሂሳዊ አስተያየትና ግብዓት እንዲሰጡ መንገድ የከፈተ ነው። ድርጅቶቹ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ተሞክሮ በማካፈል የዴሞክራሲ ግንባታው በሳይንሳዊ መንገድ እንዲመራና ዜጎች በየዕለቱ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በባለቤትነት እንዲሳተፉ በማስተማርና ግንዛቤ በመፍጠር የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ ነው።

የፍትህ ሚኒስትሯ ሀና አርዓያሥላሴ እንደገለጹት፤ የሲቪል ማኀበራት ድርጅቶችን የተመለከተው አዋጅ ቁጥር 1113/2011 በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ያመጣ የሕግ ማዕቀፍ ነው። አዋጁ ቀደም ሲል የሲቪል ማኅበራትን እጅና እግር አስረው የነበሩ አፋኝ ድንጋጌዎችን ሙሉ በሙሉ የለወጠ ነው። አዋጁ ድርጅቶቹ በምርጫ ሂደት ውስጥ እንደ ታዛቢና እንደ መራጮች ትምህርት ሰጭ ሆነው እንዲሳተፉ ሕጋዊ ጥበቃ የሚሰጥ በመሆኑ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት ሌላው መሠረት ነው።

ይህንን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በተግባር ለማዋል ደግሞ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ሚና ወሳኝ ሆኗል። የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን



72

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ቢራቱ እንደገለጹት፤ በተፈጠረው ምቹ ምህዳር የድርጅቶቹ ቁጥር 8 ሺህ 410 ደርሷል።

ባለሥልጣኑ “ራሱን ከቁጥጥር ባለፈ ወደ ድጋፍ ሰጪነት በመለወጡ ድርጅቶቹ ለሀገር ግንባታ እንዲተጉ የሕግና የሞራል ዋስትና ሰጥቷቸዋል” ይላሉ ዋና ዳይሬክተሩ። ከፌዴራል እስከ ወረዳ የተዘረጋው የትብብር ማዕቀፍም ድርጅቶቹ በመስክ ላይ ለሚገጥሟቸው የአስተዳደርና የጸጥታ ችግሮች ፈጣን መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፤ ከምርጫ በኋላ የሚካሄዱ ጥናቶችም ለቀጣይ ምርጫዎች እንደ ግብዓት በማገልገል የዴሞክራሲ ሥርዓቱን ለማጠናከር ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።

በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ ውስጥ የሲቪል ማኅበራት ሚና ከታዛቢነት አልፎ ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሸጋገሩ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ልዩ መገለጫ ነው። ሲቪል ማኅበራት በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል እንደ ድልድይ በማገልገል፣ ምርጫው ነጻ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ እንዲሆን የማዕዘን ድንጋይ ሆነው ያገለግላሉ። ይህ ሚናቸው በተለይም በሦስት ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ያተኩራል። እነዚህም ገለልተኛ ታዛቢነትን በማረጋገጥ የምርጫውን ተቀባይነት መገንባት፣ የዜጎችን ንቃተ ሕሊና ማሳደግ እና ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የግጭት መከላከል ሥራዎችን መሥራት ናቸው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ነዋይ፣ ሲቪል ማኅበራትን የምርጫው ስትራቴጂካዊ አጋር ናቸው ይሏቸዋል። ይህ ማለት ቦርዱ ምርጫውን ለብቻው ማስፈጸም ብቻ ሳይሆን፣ ሂደቱ በገለልተኛ ወገን እንዲመዘን ያለውን ሙሉ ዝግጁነትና ቁርጠኝነት እንዲሁም የማኅበራቱን ሚና ያሳያል። ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶቹ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያስመዘገቧቸው የታዛቢዎች ቁጥር ከስድስተኛው ምርጫ አንጻር በ15 ሺህ 771 ጭማሪ አሳይቶ 52 ሺህ 487 ደርሷል። ይህም በምርጫ ሂደቱ ላይ ያለውን የገለልተኛ ታዛቢነት ሚና በከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል። የታዛቢዎች ምልመላ የተካሄደው በዲጂታል መተግበሪያ አማካኝነት ሲሆን፤ ይህም ብቃትና ገለልተኝነት ያላቸውን ታዛቢዎች ለመምረጥ አስችሏል። ታዛቢዎቹ በመስክ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያሳይ ደረጃውን የጠበቀ ሲሙሌሽን (Simulation) የታከለበት ሥልጠና ወስደዋል። ይህ ሥልጠና ታዛቢዎች በጣቢያዎች ላይ የሚፈጠሩ ስህተቶችን በሠለጠነ መንገድ እንዲይዙና መረጃ እንዲያስተላልፉ ይረዳቸዋል። የሲቪል ማኅበራት ታዛቢዎች መኖራቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎችና ዜጎች በምርጫው ሂደት ላይ ሙሉ እምነት እንዲኖራቸው ያደርጋል።

ታዋቂው የፖለቲካ ምሁር ሮበርት ኤ. ዳህል ‘Polyarchy: Participation and Opposition’ በተሰኘው መጽሐፉ ላይ ስለ ዴሞክራሲያዊ ሂደቶች ሲገልፅ፤ “ዴሞክራሲያዊ አሠራር እንዲኖር፣ ዜጎች መረጃን ከገለልተኛና ከተለያዩ ምንጮች የማግኘት መብት ሊኖራቸው ይገባል፤ እነዚህ የመረጃ ምንጮች በመንግሥት ቁጥጥር ስር መሆን የለባቸውም” ይላል።

የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ሕብረት ለምርጫ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አበራ ኃይለማርያም፤ ከስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ትምህርት በመቅሰም የታዛቢዎችን ጥራት ለማረጋገጥ ሂደቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ተሠርቷል ብለዋል።



73

የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አህመድ ሁሴን፤ ለዘንድሮው ምርጫ ሲቪል ማኅበራት ከመቼውም ጊዜ በላይ መደራጀታቸውን ነው ያረጋገጡት፤ ድርጅቶቹ በመላ ሀገሪቷ በሚገኙ ከ52 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ሂደት እየታዘቡ ነው። በአሁኑ ወቅት 169 ድርጅቶች ለመራጮች ትምህርት እውቅና አግኝተው ወደ ሥራ ገብተዋል። ዜጎች በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ወደ ምርጫ ጣቢያ እንዲሄዱ ማድረግ ወሳኝ ነው። የመራጮች ትምህርት ዜጎች እንዴት ድምፅ መስጠት እንዳለባቸው ብቻ ሳይሆን፣ ድምፃቸው ለሀገር ግንባታ ያለውን ዋጋ እንዲረዱ የሚያደርግ ነው። ድርጅቶቹ ትምህርቱን በተለያዩ ቋንቋዎች ለሕዝብ እያደረሱ ይገኛሉ። ይህም በተለይ በመረጃ ተደራሽነት ዝቅተኛ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች የምርጫ መብታቸውን ተረድተው እንዲሳተፉ ያግዛል። የመራጮች ትምህርት የምርጫውን የድምፅ ብክነት (Invalid ballots) ከመቀነሱም በላይ ዜጎች በሠለጠነ መንገድ በሀሳብ ተከራክረው እንዲመርጡ ያደርጋል።

ዶክተር ተስፋዬ በልጅጌ ‘ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ’ በሚለው መጽሐፋቸው፤ “የሲቪክ ማኅበረሰብ ተቋማት በፖለቲካዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ሕዝብ በነቂስ እንዲሳተፍ ዕድል ከመፍጠራቸውም በላይ ስለ ዴሞክራሲ ዕሴቶች፣ ስለ ምክንያታዊነት እና ስለ ሥነ ምግባር ትምህርቶችን ይሰጣሉ። በዚህም የሀሳብ የበላይነት ላይ የተመሠረተ የተረጋጋ የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲኖር መደላድልን ይፈጥራሉ” ይላሉ። ከዚህ የምንረዳው ሲቪል ማኅበራት የዴሞክራሲ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን ነው። መንግሥት ሕግ ያወጣል፣ ምርጫ ቦርድ ምርጫ ያስፈጽማል፤ ሲቪክ ተቋማት ግን ዴሞክራሲን የሚገነዘብ የሠለጠነ ዜጋ ይቀርፃሉ። ዴሞክራሲ ሥር የሰደደና ጸንቶ የሚቆም ሥርዓት እንዲሆን ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል።



74

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በምርጫው ሂደት ላይ የሚደረጉ ታዛቢነቶችና የሚቀርቡ ምክረ ሐሳቦች ለቀጣይ ምርጫዎች እንደ ግብዓት እንዲያገለግሉ ድርጅቶቹ የድህረ ምርጫ ዳሰሳዎችን ማካሄድ ይገባቸዋል። ይህም ኢትዮጵያ በየጊዜው የምታካሂዳቸው ምርጫዎች ካለፈው ስህተት በመማር የተሻለ ምህዳር እንዲኖር ለማድረግ የታለመ አካሄድ ነው። ይህ የትብብር መንፈስ በሲቪክ ምህዳሩ ውስጥ አዲስ ተስፋ የፈጠረ ሲሆን፤ መንግሥት ለዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ያለውን ጽኑ አቋም በተግባር የሚያሳይ ነው። ጆን ስቱዋርት ሚል (Considerations on Representative Government) በተባለው ታዋቂ ሥራው ላይ “የአንድ መንግሥት ጥራት የሚለካው፣ ዜጎች በንቃት በሚያደርጉት ተሳትፎና በሚያሳዩት የንቃት ደረጃ ነው” ከሚለው ሀሳብም ጋር የሚስማማ ነው።

ሲቪል ማኅበራት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ከታዛቢነት እስከ መራጮች ትምህርት ድረስ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ወደተሟላ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለምታደርገው ጉዞ እንደ ትልቅ ስኬት የሚቆጠር ነው። ሂደቱ በቴክኖሎጂ መታገዙ፣ የታዛቢዎች ቁጥር ማደጉ እና የሕግ ከለላ መኖሩ ሲቪል ማኅበራት ለምርጫው ስኬት የቴክኒክ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲ ሥርዓቱ



75

በጠንካራ መሠረት ላይ እንዲቆም ለማድረግ የሚያስችሉ ዋስትናዎች መሆናቸውን ያረጋግጣል።

የፍትሕ ተቋማትና ፍርድ ቤቶች የምርጫ ቅሬታ አፈታት ሚና

ምርጫ በባህሪው የፉክክር መድረክ ነው። በሂደቱ ላይ ቅሬታዎችና ክርክሮች መነሳታቸው አይቀሬ ይሆናል። እነዚህን ቅሬታዎች በሠለጠነ፣ በገለልተኛና በሕጋዊ መንገድ የሚዳኝ የፍትሕ ሥርዓት መኖሩ ደግሞ የዴሞክራሲው ዋነኛ ዋስትና ነው። ታዋቂው የዴሞክራሲ ተንታኝ ሮበርት ኤ. ዳህል እንደሚለው “ዴሞክራሲ የሰላማዊ የፖለቲካ ውድድር ሥርዓት ነው፤ ይህ ውድድር ደግሞ ፍትሐዊ የሚሆነው ተሳታፊዎቹ በሕግ ፊት እኩል ሲታዩና ቅሬታዎቻቸውን የሚሰማ ገለልተኛ ዳኛ ሲኖር ብቻ ነው” ይህ የምሁሩ ሀሳብ እንደሚያሳየው ቅሬታዎችን በሠለጠነና በሕጋዊ መንገድ የሚዳኝ የፍትሕ ሥርዓት መኖሩ የዴሞክራሲው ልብ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አለመግባባትና ቅሬታዎች ቢፈጠሩ በምርጫ ጣቢያ፣ በምርጫ ክልል እና በማዕከል ደረጃ በፍጥነት መፍታት የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱን የቦርዱ ሰበሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ አረጋግጠዋል። ከዚህም ካለፈ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እልባት እንዲያገኝ ቦርዱ ከፍርድ ቤቶችና ከፍትሕ አካላት ጋር መሥራት የሚያስችለውን ዝግጅት አድርጓል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፤ “ፍርድ ቤቶች የምርጫ ክርክሮችን በሕግ በመዳኘት የመራጮችንና የዕጩዎችን መብት ለማስከበር ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሙሉ ዝግጅት አድርገዋል” በማለት ሊነሱ ለሚችሉ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ተገቢውን ፍትህ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት መኖሩን በአጽንኦት ገልጸዋል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የምርጫ ነክ ጉዳዮችን ብቻ የሚመለከቱ ልዩ ችሎቶች ተደራጅተዋል። ይህም ክርክሮች ሳይጓተቱ በፍጥነት ውሳኔ እንዲያገኙ ያስችላል። ምርጫ የሥልጣን ምንጭ ሕዝብ መሆኑን ማረጋገጫ ሥርዓት ነው። ይህ ሂደት በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ መመራቱ ለሀገር መረጋጋትና ለዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ወሳኝ ነው። ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት ፍትሐዊና ትክክልኛ ውሳኔ ዜጎች በሥርዓቱ ላይ ያላቸውን እምነት የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ ማንኛውም አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ በር ይከፍታል።

ፍርድ ቤቶች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚሰጣቸው ውሳኔዎች ከሕግ ጋር መጣጣማቸውን የማረጋገጥ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ይህም በሀገሪቷ ውስጥ ተቋማዊ ቁጥጥርና ሚዛን መኖሩን በተግባር የሚያሳይ ይሆናል። ተቋማዊ ሚዛን በሥራ ላይ እንዲውል የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ- ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ለዳኝነት አካሉ ግልጽ ሥልጣን ሰጥቷል። በአዋጁ አንቀጽ 154 መሠረት፣ በቦርዱ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ወገን ለፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት አለው። ይህ ድንጋጌ የአስፈጻሚ አካላት ውሳኔ በገለልተኛ ዳኛ መፈተሽ እንዳለበት የሚያረጋግጥ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቶች ከአስፈጻሚውና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተጽዕኖ ነፃ ሆነው ህጉን ማስጠበቅ አለባቸው።

የምርጫ ጉዳዮች በቅድሚያና በአስቸኳይ እንዲታዩ መደረጉ ለምርጫው ሰላማዊነትና ለውጤቱ ተቀባይነት ወሳኝ መሆኑን የፍትሕ ተቋማቱ



76

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

አረጋግጠዋል። በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 በተቀመጠው አስገዳጅ የጊዜ ገደብ መሠረት የምርጫ ክርክሮች በታወቀ አጭር ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ማግኘት ይኖርባቸዋል። በመሆኑም የዳኝነት ተቋማት በሕግ የተሰጣቸውን ነፃነትና ገለልተኛነት ተጠቅመው የሚሰጡት ብይን፣ ኢትዮጵያ ለጀመረችው የዴሞክራሲ ጉዞ መሳካት ትልቅ መሠረት ይሆናል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ስኬት

በማንኛውም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ ምርጫ የሕዝብ ሉዓላዊ ሥልጣን እውን የሚሆንበት እና የሀገር የፖለቲካ ዕጣ ፈንታ የሚወሰንበት ታላቅ የታሪክ መድረክ ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች የዴሞክራሲ ዋነኛ ተዋናዮች እና የሕዝብ አማራጭ ሐሳቦች መሸከሚያ ድልድዮች በመሆናቸው ሚናቸው ከመወዳደር ባለፈ የምርጫውን ተዓማኒነት እና ሰላማዊነት የማረጋገጥ ከፍተኛ ኃላፊነትን ያካትታል። ምርጫ ሂደቱ ብቻ ሳይሆን ውጤቱም ፍትሐዊና በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕግና በሥነ-ምግባር የታነፀ ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸው አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እንዲሆን ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያላቸው የቅድመ-ዝግጅት ጥራት እና የሀሳብ የበላይነትን የማንገስ ቁርጠኝነት ለሂደቱ ስኬት እንደ ወሳኝ ሞተር ይታያል። ታዋቂው የፖለቲካ ሳይንቲስት E.E. Schattschneider ‘The Semi sovereign People’ በተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ “የፖለቲካ ፓርቲዎች ዴሞክራሲን ፈጠሩ፤ ዘመናዊ ዴሞክራሲም ያለ ፓርቲዎች መኖር ሊታሰብ የማይችል ነው” ይላሉ። ይህ እሳቤ በኢትዮጵያ ካለው የምርጫ ፖለቲካ ጋር ይተሳሰራል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው የፖለቲካ ፓርቲዎች አሁን ላይ እያደረጉት ያለው ዝግጅት ነው።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመፎካከር በምርጫ ቦርድ የተመዘገቡና እውቅና ያገኙ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለኢትዮጵያ ዕድገት ይጠቅማል ያሉትን የፖለሲ አቅጣጫቸውን ይፋ እያደረጉ ይገኛሉ። መሪ ሀሳባቸውን፣ ማኒፌስቷቸውን በማስተዋወቅ መራጩ ሕዝብ ድምፅ እንዲሰጣቸው ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ እንደገለጹት፤ ፓርቲው ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲ፣ በማኅበራዊ እና በኢኮኖሚ ልማት ያላትን የመሪነት ሚና ለማጠናከር ያለመ ማኒፌስቶውን አስተዋውቋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም ምርጫው ያለውን ሀገራዊ ፋይዳ በማጉላት ሰፊ ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ። ከተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) መሪ ኢዮብ መሳፍንት፤ ፓርቲያቸው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እና ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ስለሚከፍት የፖሊሲ ሰነዶችና ማኒፌስቶ ይፋ ማድረጉን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ አበራ በቀለ፤ የዘንድሮው ምርጫ ለኢትዮጵያ የተረጋጋ ፖለቲካዊና ዴሞክራሲያዊ ጉዞ ጠንካራ መሠረት



77

የሚጣልበት ነው ብለዋል። ምርጫው ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ወሳኝ የታሪክ አጋጣሚ መሆኑንም አክለዋል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሽግግር በዴሞክራሲያዊ ምርጫና በሀሳብ የበላይነት ብቻ መሆን እንዳለበት ፓርቲያቸው በጽኑ እንደሚያምን የገለጹት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ የሱፍ ኢብራሂም፤ ከማኒፌስቶ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ አማራጭ ሀሳብ የማስተዋወቅ ሥራ በትኩረት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነቢሃ መሐመድ በበኩላቸው፤ ጠንካራ ሀገር እና መንግሥት የሚመሠረተው በዴሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት ብቻ ነው ብለዋል። ይህ የፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች ንግግር ፒፓ ኖሪስ “Critical Citizens” በተሰኘው ሥራቸው ላይ “የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕዝብን የመወከል ተግባር ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሕጋዊነት ወሳኝ ነው” በማለት የገለጹትን መርህ የሚያጠናክር ነው።

በዘንድሮው ምርጫ የፓርቲዎች ዝግጅት ሌላው ትኩረት የአካታችነትና የሥነ-ምግባር ደንብ ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ነዋይ እንዳነሱት፤ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ቦርዱ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት ዕጩ ተወዳዳሪዎች በምርጫ ቅስቀሳ፣ በክርክርና በምርጫ ሂደት ወቅት የሚገዙበት የሥነ ምግባር ሰነድ ተዘጋጅቷል፤ ዕጩዎችም ፈርመውታል። ሰነዱ የምርጫው ሂደት ሙሉ ለሙሉ ሰላማዊ እንዲሆን ማድረግ፣ ገዥ ፓርቲውና ተፎካካሪ ፓርቲዎች እኩልና ፍትሐዊ የመወዳደሪያ ሜዳ እንዲኖራቸው፣ መራጮች የሚፈልጉትን አካል በነጻነት የመምረጥ መብታቸውን ለማስከበር፣ ማናቸውም ውድድርና እንቅስቃሴዎች ሥነ ምግባርን የተከተሉ እንዲሆኑ በማድረግ የምርጫው ሂደትም ውጤቱም ተዓማኒ እንዲሆን ያለመ ነው። ከዚህ በመነሳት የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው



78

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ተዓማኒና ስኬታማ እንዲሆን የምርጫ ህጉን ማክበር፣ ማስከበርና መተግበር ይጠበቅባቸዋል።

ፖለቲካ ፓርቲዎች ዜጎች ከመራጭነት ባለፈ እንደ ባለቤት እንዲሳተፉ ማበረታታት፣ ስለ መብትና ግዴታቸው በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው በፓርቲዎች ፕሮግራም ላይ በቂ ግንዛቤ ይዘው ድምፃቸውን እንዲሰጡ ማድረግ ለሀገራዊ መግባባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል።

መገናኛ ብዙኃን እንደ ዴሞክራሲ ምሰሶና የሀሳብ መድረክ መገናኛ ብዙኃን በምርጫ ሂደት ውስጥ የዜጎችን የፖለቲካ ንቃተ-ሕሊና በማሳደግና የፖለቲካ ፓርቲዎች እሳቤዎቻቸውን በነፃነት እንዲያንሸራሽሩ ምቹ መድረክ በመፍጠር በዋና ምሰሶነት ያገለግላሉ። በተለይም በምርጫ ወቅት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እኩል የክርክርና የዘገባ ሽፋን እንዲያገኙ በማድረግ ሕዝቡ በቂ መረጃ ኖሮት በትክክለኛው ውሳኔ ድምፅ የሚሰጥበትን የማስተማር ኃላፊነት ይወጣሉ። የዘንድሮው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እንዲሆን የመገናኛ ብዙሃን የሀሳብ የበላይነትን የማንገስና የመድበለ ፓርቲ ሥርዓትን የማጎልበት ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ሰፊ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ ገብተዋል።

የፖለቲካ ኮሙኒኬሽን ምሁሩ በርናርድ ኮኸን፤ መገናኛ ብዙኃን ለዴሞክራሲ ያላቸውን ሚና ሲገልጹ “መገናኛ ብዙኃን ሰዎች ምን ማሰብ እንዳለባቸው በመንገር ረገድ ስኬታማ ላይሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን ስለምን ማሰብ እንዳለባቸው በመንገር ረገድ በሚያስገርም ሁኔታ ስኬታማ ናቸው” ይላሉ። ይህ የአጀንዳ ቀራጭነት ሚና በምርጫ ወቅት መገናኛ ብዙሃን የትኞቹን ፖሊሲዎችና አማራጭ ሀሳቦች ለሕዝብ ማቅረብ እንዳለባቸው በመወሰን ረገድ ያላቸውን ኃይል ያሳያል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ን ጨምሮ መገናኛ ብዙኃን ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት እያከናወኑት ያለው ተግባር ነው። የኢዜአ የዜና ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተፈራ በቀለ እንደገለጹት፤ መገናኛ ብዙኃን ለምርጫ ሂደት ገንቢ ሚና የሚወጡ የዴሞክራሲ ሥርዓት መገንቢያ መሣሪያዎች ናቸው። ኢዜአ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት ልዩ የምርጫ ዴስክ በማቋቋም የቅድመ ምርጫ፣ የምርጫ ወቅትና የድህረ ምርጫ ዕቅድ አውጥቶ በትኩረት እየሠራ ነው።

በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የምርጫ ዴስክ ሰብሳቢ አቶ በክሪ ናስር እንደሚሉት፤ ከስድስተኛው ምርጫ ከተገኘ ተሞክሮ በመነሳት ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የክርክር መድረክ በማዘጋጀትና የዘገባ ሥራዎችን በማከናወን ተደራሽ እያደረጉ ነው።

መገናኛ ብዙኃን ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚፈጥሯቸው መድረኮች ዜጎች አማራጭ የፖሊሲ ሀሳቦችን እንዲገነዘቡ በማድረግ በኩል ወሳኝ ሚና አላቸው። ይህም መረጃ ከመስጠት ባሻገር የፖለቲካ ፓርቲዎች የያዟቸውን አማራጭ ሀሳቦች በራሳቸው መንገድ እንዲተነትኑ ዕድል በመስጠት የሕዝቡን ግንዛቤ ለማሳደግ አቅም ይፈጥራል። የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳዊት መስፍን፤ እኩል የአየር ሠዓት ድልድል በመፍጠር ተፎካካሪ ፓርቲዎች የፖሊሲ



79

አማራጫቸውን በነፃነት ለሕዝብ የሚሸጡበት መድረክ በማመቻቸት ተፈፃሚ እያደረጉ ነው። ይህ ዓይነቱ አሠራር መራጩ ዜጋ “ይሆነኛል” ለሚለው ድምፅ እንዲሰጥ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም የነበረውን የመወቃቀስና የመካሰስ ፖለቲካ በሀሳብ ፉክክር የመተካት ተስፋ ሰጪ ጅምር ነው።

በአጠቃላይ በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን በሀሳብ የበላይነት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ባህል መገንባት የሚያስችል ምቹ የመገናኛ ብዙኃን ምኅዳር መፈጠሩን የመገነኛ ብዙሃን ኃላፊዎቹ አረጋግጠዋል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት የሚለካው እነዚህ ተቋማት በሚፈጥሩት ግልጽነትና ተዓማኒነት ነው።

የምታሸንፈው ኢትዮጵያ ናት

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ፤ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ ለጀመረችው ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ዴሞክራሲ በአንድ ወቅት ተሠርቶ የሚያልቅ ሳይሆን በትዕግሥትና በጽናት መገንባት ያለበት የሁላችንም ኃላፊነት ነው። በሰላማዊ መንገድ ተወዳድሮ፣ በሀሳብ ልዕልና አምኖና የሕዝብን ውሳኔ በጸጋ ተቀብሎ ለሀገር ልማት በጋራ መቆም የሥልጣኔያችን መለኪያ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ አሸናፊው የትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ቢሆን፣ ዋነኛዋ አሸናፊ ግን ሉዓላዊቷ ኢትዮጵያና ኩሩው ሕዝቧ ናቸው። ይህ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መሳካት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታችን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን ለዓለም የሚያበስርና ለቀጣዩ ትውልድ የምናወርሰው ኩሩ ተቋማዊ ቅርስ ሆኖ ይመዘገባል።

ምርጫው በጽኑ መሠረት ላይ የቆመና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት ለመገንባት ለምናደርገው የልዕልና ጉዞ ሁነኛ መሠረት ይጥላል። ምርጫ የመንግሥት ቅቡልነት ማረጋገጫ ብቻ ሳይሆን ዜጎች በፖለቲካው ሂደት ውስጥ እኩል ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚያደርግ መሣሪያ ነው። ይህ ሂደት ለኢትዮጵያ የመንግሥት ሕዝባዊ ቅቡልነትን በማምጣት የሀገረ መንግሥቱን መሠረት ያጸናል።

ይህንን ግዙፍ ሀገራዊ ግብ ለማሳካት የምርጫ ባለድርሻ አካላት ሚና የጎላ ነው። የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት፣ ምርጫ ቦርድ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የመገናኛ ብዙሃን ሚናቸው ከምርጫውም ባሻገር ዘላቂ የዴሞክራሲ ባህል የመገንባት ግዴታን ይጨምራል። ስለሆነም የምርጫ ባለድርሻ አካላት ገለልተኝነትና ጥንካሬ ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ልዕልና ጉዞ ዋስትና ነው።

አበው ነገርን በምሣሌ ሲጠቅሱ “ተቀመጥ በወንበሬ፣ ተናገር በከንፈሬ” ይላሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በካርዱ ሥልጣኑን ለተወካዮቹ ለማስተላለፍ ከመቼው ጊዜ በላይ እየተዘጋጀ ነው። ይህ ሂደት ስኬታማ እንዲሆን መራጩ ሕዝብ የፖለቲካ ፕሮግራሞችን በጥልቀት መርምሮ በነፃነትና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ሊሰጥ ይገባል። በአንጻሩ ተመራጮች የሕዝብ አደራ ጠባቂ መሆናቸውን ተረድተው ድምፅ የሰጣቸውን ማኅበረሰብ ፍላጎት በቅንነት ለማስተናገድ ራሳቸውን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል። በመሆኑም ምርጫው እውነተኛ የሕዝብ ድምፅ የሚከበርበትና የሀገር አንድነት የሚጸናበት መድረክ እንዲሆን ሁሉም ወገን በኃላፊነት ሊቆም ይገባል።



80

ኢኮኖሚ

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

የተገለጠው ውበት



81

በመንገሻ ገ/ሚካኤል

ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ልማት ለብዙ ሀገራት የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የባህል ልውውጥ እና የአካባቢ ጥበቃ ተግባራት ወሳኝ አንቀሳቃሽ በመሆን ብዙዎችን ተጠቃሚ አድርጓል። ቱሪዝም ሕዝቦችን በማስተሳሰር፣ የአገራትን የባህል ልውውጥ በማሳደግና የዲፕሎማሲ ትስስር በመፍጠር ረገድ የማይተካ ሚናም አለው፡፡

ቱሪዝም በግርድፉ ሲገለጽ ሰዎች ከለመዱት የመኖሪያ አካባቢ ወጥተው ለተለያዩ ዓላማዎች፤ ለዕረፍት፣ ለትምህርት ወይንም ለንግድ የሚያደርጉት ጉዞና በቆይታቸው የሚያገኟቸው አገልግሎቶች ስብስብ ነው። ይህ ዘርፍ በአገራችን “ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት” (Ethiopia: Land of Origins) በሚል ብሔራዊ መለያ (Brand)



82

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ይታወቃል። ቱሪዝም የአንድን ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት የሚያፋጥንና “ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ” በመባል የሚታወቅ ወሳኝ ዘርፍ ሲሆን በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በርካታ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ጸጋ ላላቸው ሀገራት የኢኮኖሚ ምሰሶ፣ የባህል መገናኛ እና የገጽታ ግንባታ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል።

ዘርፉ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጉድለት ያስተናገደ ቢሆንም አሁን ጠንካራ መነቃቃት ማሳየት ችሏል፡፡ የዚህ ማሳያ ደግሞ እ.አ.አ በ2025 ብቻ በተለያዩ ሀገራት ጉዞ ያደረጉ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ቁጥር 1 ነጥብ 52 ቢሊዮን መድረሱ ሲሆን ይህም ለአገራት የኢኮኖሚ ዕድገት የራሱን በጎ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ቱሪዝም ከዓለም ኢኮኖሚ ምጣኔ 10 ነጥብ 3 በመቶ ያህሉን የሚሸፍን ሲሆን፤ በ2025 ዓ.ም በዓለም ሀገራት አጠቃላይ የምርት ዕድገት ምጣኔ ላይ 11 ነጥብ 7 ትሪሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ አስገኝቷል። በሁሉም መስክ ከሚፈጠሩ አሥር የሥራ ዕድሎች አንዱ ከቱሪዝም ጋር የተያያዘ መሆኑ የዘርፉን አይተኬ ሚና ያሳያል። የቱሪዝም ልማት ለሚሊዮኖች የሥራ ዕድል በመፍጠርና የበርካታ ሀገራት ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ በመሆን በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የቱሪዝም ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በፈረንጆቹ 2025 ብቻ ሀገራት



83

ከቱሪዝም ዘርፍ 2 ነጥብ 2 ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ አግኝተዋል፡፡ የተገኘው ገቢ እስከ አሁን በዘርፉ ከተመዘገቡት ሁሉ የላቀ ሲሆን ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ የቱሪዝም ፍሰት እየጨመረ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከቱሪዝም ከፍተኛ ገቢ ከሚያገኙ አገራት አሜሪካ በቀዳሚነት የምትቀመጥ ሲሆን ከዘርፉ በዓመት ከሁለት መቶ ቢሊዮን ዶላር በላይ ታገኛለች። ስፔን፣ ፈረንሣይ እና ኢጣሊያ ከፍተኛ ጎብኚዎችን በማስተናገድ የሚታወቁ ሲሆን በተለይም በባህር ዳርቻዎች፣ በባህላዊ ቅርሶች፣ በጥንታዊ ከተሞች፣ በሙዚየሞች፣ በሥነ-ጥበብና ሥነ ሕንፃ እንዲሁም በባህላዊ መጠጦችና ምግቦች በመታገዝ ከፍተኛ ገቢ ያገኛሉ።

በባህል ብዝሃነቷ፣ ውብ በሆነው ተፈጥሯዊ አቀማመጧ እና በታሪካዊ ቅርሶቿ የሁሉንም ዓይን የምትስበው አፍሪካ በበኩሏ ከቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ ጥቅም እያገኘች ነው፡፡ አሁን ላይ ቱሪዝም ለብዙ የአፍሪካ ሀገራት የዕድገት መሠረት፣ የሥራ ዕድል ማስገኛ እና የገጽታ ግንባታ መደላድል ሆኖ ያገለግላል። ዘርፉ ለአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ ያለው ሲሆን በተለይም ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ፣ ታንዛኒያ እና ግብፅን የመሳሰሉ ሀገራት ጠንካራ የቱሪዝም ዘርፍ በመገንባት ኢኮኖሚያቸውን ማሳደግ ችለዋል፡ ፡ ኢትዮጵያም እንደ ሀገር በወጠነችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትኩረት ከሰጠቻቸው አምስት ብዝሃ ዘርፎች አንዱ የሆነው ቱሪዝም ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የተሻለ የጎብኚዎች ቁጥርና ገቢ በማስገኘት ላይ ይገኛል።

ቱሪዝም ከሌሎች ዘርፎች የሚለየው ብዝሃ ስብጥር ያለው መሆኑ ነው፡፡ ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠርና የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘት ባሻገር አገልግሎት ሰጪዎች ትራንስፖርት፣ ሆቴል፣ የግብርና ውጤቶች እንዲሁም የማምረቻውን ዘርፍ እና የመዝናኛ አገልግሎት አቅራቢዎችን በእጅጉ ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

ምድረ ቀደምት- ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በቱሪዝም ሀብታቸው ከሚታወቁ የዓለም ሀገራት አንዷ ስትሆን በአያሌ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ መስህቦቿ፣ በብሔራዊ ፓርኮቿ፣ በደማቅ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ሥርዓቶቿ በስፋት ትታወቃለች። ከባሌ ተራራ እስከ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን እና የአክሱም ሐውልት፤ ከጢያ ትክል ድንጋይ እስከ ጢስ አባይ ፏፏቴ፤ ከጀጎል ግንብ እስከ ሶፍ ኡመር ዋሻ ታይተው የማይጠገቡ የቱሪስት መስህቦችን የተቸራት ነች።

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የጎንደር አብያተ መንግሥት፣ የአክሱም ሐውልት፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የጢያ ትክል ድንጋይ፣ የጀጎል ግንብ፣ የመስቀል ደመራ እንዲሁም የጥምቀት በዓላት፣ የገዳ ሥርዓት፣ ፊቼ ጨምበላላ፣ የኮንሶ መልክዓ ምድር፣ የታችኛው አዋሽ ሸለቆና የታችኛው የኦሞ ሸለቆ፣ የጌዴኦ መልክዓ ምድር እና የባሌ ተራሮዎች ብሔራዊ ፓርክ እንዲሁም የሐረሪ ብሔረሰብ የሸዋሊድ በዓል የመሰሉ 18 የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን በዩኔስኮ በማስመዝገብ ከአፍሪካ ቀዳሚና በርካታ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ባለቤት ስትሆን፤ በጊዜያዊነት የተመዘገቡ 10 የሚጠጉ የቱሪዝም ሃብቶችን ይዛለች፡፡ የሕዝቦቿ ባህላዊና የራሳቸው መገለጫ የሆኑ የአመጋገብ ሥርዓቶችም አሁን



84

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

አሁን የብዙዎችን ቀልብ በመሳብ በርካታ የውጭ አገር ጎብኚዎች ወደ አገሪቷ እንዲመጡ እየጋበዙ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ የቱሪዝም ልማት ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም በአገሪቷ የሚገኙ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን ለይቶ ማልማት፣ ማስተዋወቅና ተወዳዳሪ መዳረሻዎችን መፍጠር ላይ በሚገባው ልክ ባለመሠራቱ ከዘርፉ ተገቢውን ጥቅም ማግኘት ሳይቻል ቀርቷል፡፡ በዘርፉ ከኢትዮጵያ በኋላ የተነሱ የአፍሪካ አገራት ከፍተኛ እመርታ ሲያሳዩ አገራችን በነበረችበት ቦታ መገኘቷ ሲያስቆጭ ቆይቷል፡፡ ይህን የተገነዘበው የለውጡ መንግሥት በቀየሰው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከለያቸው አምስት የዕድገትና የብልጽግና ምሰሶዎች ውስጥ ቱሪዝም አንዱ ሆኗል።

በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ፕሮሞሽን ዘርፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተሾመ ተክሉ ቱሪዝም ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ራሱን ችሎ በሚኒስቴር ደረጃ እንዲደራጅ በመደረጉ በዘርፉ ይታዩ የነበሩ መዋቅራዊ ችግሮችን መፍታት እንደተቻለ ይገልጻሉ። ከለውጡ በፊት ዘርፉ ብዙም ትኩረት ያልተሰጠው ሆኖ ቢቆይም አሁን በሀገሪቷ ቀዳሚ ከሆኑት ስትራቴጂካዊ የልማት አጀንዳዎች አንዱ እንዲሆን መደረጉ የተሰጠውን ልዩ ትኩረት ያሳያል ብለዋል።

ቱሪዝም በአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው የሀገሪቷን የብልጽግና ራዕይና ጉዞ ለማሳካት ከፍተኛ አበርክቶ እንዳላቸው ከታመነባቸው ዘርፎች አንዱ እና ልዩ የተሰጠው ሆኗል፡፡ በዘርፉ ያለውን እምቅ የመልማት አቅም በመጠቀም የሕዝቦችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትና ማኅበራዊ መስተጋብር ለማሳደግ እንዲሁም የሁሉንም አካባቢዎች ሥነ- ምድራዊና ሥነ-ምህዳራዊ ጸጋዎችና በረከቶች በማልማት ዜጎችን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ነው።

የተገለጠው ውበት

መንግሥት ኢትዮጵያን ተወዳዳሪ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በመላ ሀገሪቷ የሚገኙ ሀብቶቿን በመግለጥ በርካታ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻ ልማትና ነባሮቹም ላይ እሴት የመጨመር ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል አሁንም በማከናወን ላይ ይገኛል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመሩት የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ኢኒሼቲቮች የዘርፉን ዕድገት በማሳለጥ ሁነኛ ሚና መጫወታቸውን አቶ ተሾመ ይናገራሉ።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት ለቱሪስት መዳረሻ ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፤ በገበታ ለሸገር ፕሮጀክት በአዲስ አበባ የተገነቡት የአንድነት፣ የወዳጅነትና የእንጦጦ ፓርኮች የከተማዋና የሀገሪቷ የቱሪስት መስህብ መሆን ችለዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እና አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ለዘርፉ ዕድገት የራሳቸውን ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ።

ገበታ ለሸገር ወደ ገበታ ለሀገር ተሸጋግሮ በወንጪ፣ በጎርጎራ እና በኮይሻ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማት ዘርፉን አንድ እርምጃ ወደፊት አስፈንጥሮታል። የኮይሻ አካል የሆነው የሀላላ ኬላ ሪዞርት የዳውሮ ንጉሥ ያስጀመረውና ለ300 ዓመታት የዳውሮ ነገሥታት እየተቀባበሉ



85

እንደገነቡት የሚነገርለት ግንብ ሲሆን በኢኒሼቲቩ በመታገዝ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ሪዞርቱ ውብ የተፈጥሮ ገጽታን በተላበሰውና የጊቤ ሶስት የኃይል ማመንጫ ግድብ በሚገኝበት አካባቢ የተገነባ ነው።

በቅርቡ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ታሪካዊው የእስጢፋኖስ ሐይቅ (ሐይቅ ሎጎ) ዳርቻ የተገነባው የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት፣ በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን ከጅግጅጋ ከተማ 29 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተገነባው ዘመናዊና ግዙፉ የሸበሌ ሪዞርት እንዲሁም በአፋር ክልል የተገነባው ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡ የገበታ ለትውልድ አካል የሆኑት እነዚህ መዳረሻዎች ማኅበረሰብን ለማበልጸግና ሀገራዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የለውጡ ፍሬዎች ናቸው። በ“ገበታ ለትውልድ” ፕሮጀክት ተጨማሪ የቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎችን ለማልማት እየተሠራ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ በትግራይ ክልል “ገራ አልታ”፣ በኦሮሚያ “ጅማ”፣ በደቡብ “አርባ ምንጭ”፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሕዳሴ ግድብ አካባቢና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሚተገበሩ ናቸው።

በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የተሠሩት ፕሮጀክቶች እንዲሁም በብሔራዊ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ ኢኮ- ሎጆች የአካባቢ፣ የባህል ጥበቃ እና የማኅበረሰብ ተሳትፎን ያጣመረ አዲስ እሳቤን የሚያመላክቱና በተፈጥሮ ማራኪ የሆኑ ስፍራዎችን ወደ ሀብትነት በመቀየር ዘርፉ በከፍተኛ ደረጃ እንዲነቃቃ አስችለዋል።

የአዲስ አበባ - አዲስ መልክ

የአፍሪካ ኅብረት፣ የበርካታ ሀገራት ኤምባሲዎች እንዲሁም የዓለም አቀፍና አህጉራዊ ድርጅቶች መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ ስሟን የሚመጥን የቱሪዝም መዳረሻ እንዲኖራትና ዘላቂ የቱሪዝም ልማት ለማረጋገጥ በርካታ መዳረሻዎች ተገንብተዋል፡፡ የእንጦጦ፣ የወዳጅነት፣ የአንድነት እና የአራዳ ፓርኮች፤ እንዲሁም በከተማዋ መሃልና ዙሪያ የተገነቡና በግንባታ ላይ የሚገኙ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች፣ የኮሪደር መሠረተ ልማቶችና አረንጓዴ



86

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ስፍራዎች መዲናዋን ስሟን የሚመጥን ገጽታ አላብሰዋታል። ግንባታዎቹ የሀገሪቷን አጠቃላይ ባህል፣ ታሪክና ተፈጥሮ አጣምረው መያዛቸው አዲስ አበባን ልዩ የኢኮ ቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን አድርገዋታል።

አዲስ አበባን የኮንቬንሽን እና የኤግዚቢሽን ማዕከል ለማድረግ ሰፊ ሥራ በመከናወኑ ከተማዋ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶችን ለማስተናገድ ይበልጥ ተመራጭ አድርጓታል። የቱሪዝም መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የባህልና ኮንፈረንስ ቱሪዝምን በማስተዋወቅ ከተማዋን ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት እያገዙ ነወ። አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ አገሪቷ የተሠሩ የልማት ሥራዎች ኢትዮጵያ የአፍሪካና የዓለም የኮንፈረንስ መዲና እንድትሆን ማስቻላቸውን በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ፕሮሞሽን ዘርፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተሾመ ተክሉ ጠቅሰዋል፡፡ በቱሪዝም አገልግሎት ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የመሰብሰቢያ ማዕከላትና የቱሪዝም መዳረሻዎች መገንባታቸው ደግሞ ለተገኘው ስኬት መሠረት ናቸው፡፡

ፕሮጀክቶቹ የቱሪዝም ዘርፉን በማነቃቃት ለአገሪቷ ሁለንተናዊ ዕድገት ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ባሻገር መልካም ገጽታዋን ለመገንባት ያላቸው ፋይዳ የላቀ ነው። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላት መልካም ገጽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ሲሆን በተለይም በቱሪዝም ዘርፍ



87

በአፍሪካ ቀዳሚውን ተርታ ከሚይዙ ሀገራት ጎን ተሰልፋለች፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የቱሪዝም ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው ኢትዮጵያ በ2024 ከዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ፍሰት 40 በመቶ ጭማሪ በማስመዝገብ ከአፍሪካ ፈጣን የቱሪስት መዳረሻዎች አንዷ ሆናለች። ስኬቱ ከተሻሻለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቱሪዝም ፖሊሲ ጋር የተያያዘ ሲሆን ይህም ዘላቂ ዕድገትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ያለውን አበርክቶ አጎልቶታል።

ቱሪዝም በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ዘርፍ ያለው ድርሻ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ በኢትዮጵያም ለቱሪስቶች ምቹ የሆኑ መዳረሻዎች እየተገነቡ ነው። በፍጥነት እያደገ የመጣውን ኢትዮጵያን የሚጎበኙ የውጭ አገር ቱሪስቶች ቁጥር ምጣኔ ወደ ሁለት ሚሊዮን ለማሳደግ እየተሠራ ነው፡፡ በ2017 በጀት ዓመት አገሪቷን ከጎበኙ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ የውጭ አገር ጎብኚዎች 4 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት ተችሏል፡፡ በ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው ግማሽ በጀት ዓመት ብቻ ኢትዮጵያን ከጎበኙ ከ707 ሺህ ከሚልቁ የውጭ አገር ቱሪስቶች 2 ነጥብ 649 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደተገኘ ከቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መስመር መስፋት፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የቱሪስት መዳረሻዎች መገንባት፣ የዓለም አቀፍ ጉባዔዎች መጨመር፣ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ መሻሻል፣ ሰፊ የማስታወቂያ ሥራ መሠራት፣ አዎንታዊ ተቀባይነትን መገንባት፣ ማኅበረሰብን ማብቃት እና ደህንነትን ማረጋገጥ መቻሉ ለተገኘው ስኬት ጉልህ አበርክቶ አላቸው፡፡

የዘርፉ ሳቢነት

ቱሪዝም ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የሀገርን ሀብት በስፋት ለማንቀሳቀስ፣ ለገጽታ ግንባታና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው እምን ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ዘርፉ ለሌሎች የኢኮኖሚ መስኮች በተለይም ለምግብ ማቀነባበሪያ፣ ለችርቻሮ ንግድ፣ ለግንባታ፣ ለሎጂስቲክስ፣ ለታዳሽ ኃይል እና ለትራንስፖርት ዘርፍ ዕድገት በርካታ ዕድሎችን ይፈጥራል፡፡ በዚህም ቀጥተኛና ተያያዥ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማሳደግ የዜጎች ኑሮ እንዲሻሻል የራሱን ሚና ይጫወታል፡፡

የቱሪዝም ዘርፍ ከሌሎች የኢኮኖሚ አማራጮች በተለየ ክህሎት ያላቸውና የሌላቸውን ዜጎች በስፋት የሚያሳትፍ ነው፡፡ በዘርፉ የሚሰማሩ አልሚዎች በየአካባቢዎቹ ለሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች መሠረታዊ ሥልጠና መስጠት ከቻሉ፤ የቱሪዝም ሀብቶችን በመንከባከብ፣ ሥነ-ምህዳራቸውን በማስጠበቅ፣ አረንጓዴ ቱሪዝምን በማስፋፋት፣ ተፈጥሯዊና ባህላዊ ሀብቶችና ቅርሶች እንዲጠበቁ በማድረግ ከራሳቸው አልፈው ለማኅበረሰቡ ተጨማሪ ጥቅም ማስገኘት ይችላሉ፡፡

ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ቱሪስቶችን ለመሳብ የሚያስችሉ አስደማሚና ሁሉንም ዓይነት የተፈጥሮና ታሪካዊ ሀብት የያዙ መዳረሻዎች ያሏት መሆኑን ተከትሎ ዘርፉን ለማሳደግ ያሉት አማራጮች ያልተነኩና የኢኮኖሚ ጥቅማቸውም ከፍተኛ ነው፡፡ አስቸጋሪ ጉዞችን የሚወዱ ጎብኚዎች ወደ ኤርታሌ፣ የምግብ ዓይነት የሚዳስሱ ጎብኚዎች ወደ አዲስ አበባ፣ የእምነት ተጓዦች



88

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ወደ ቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ አዕዋፋትን የሚወዱ ወደ ሻላ እና አብያታ፣ ዋሻ አፍቃሪዎች ወደ ሐረር እና ሶፍ ዑመር ዋሻ ቢጓዙ የተመኙትን ተመልክተውና የማይረሳ ትዝታና ተሞክሮ አግኝተው መመለስ ይችላሉ፡፡ ኢትዮጵያ የታደለችው ዘርፈ ብዙና የተሰባጠረ የቱሪዝም ሀብት ጎብኚዎች ሁሉንም በጉጉት እንዲመለከቱና ተጨማሪ ወጪ እንዲያወጡ የሚቆሰቁሱ ናቸው፡፡

የሀገር ውስጥ ቱሪዝም

በቱሪዝም ዘርፉ ሁለት ዋና ዋና የቱሪዝም ገበያዎች አሉ፤ ዓለም አቀፍ እና የአገር ውስጥ ቱሪዝም ገበያ። ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ገበያ ከውጭ አገር የሚመጡ ጎብኚዎችን የሚያጠቃልል ነው። የአገር ውስጥ ቱሪዝም ደግሞ ዜጎች ለሥራ፣ ለትምህርት፣ ለሃይማኖታዊ ተልዕኮ ወይም ለጉብኝት ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሰው የአገራቸውን ተፈጥሯዊና ባህላዊ ቅርሶቸ እንዲያውቁ የሚደረግበት ነው። ሁለቱም የቱሪዝም ገበያዎች ጥቅማቸው የተለያየ ቢሆንም ለአገር ዕድገት እኩል ጠቀሜታ አላቸው የሚሉት አቶ ተሾመ ለሁለቱም ዘርፎች እኩል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የአገር ውስጥ ቱሪዝም ዋነኛው የኢኮኖሚ ሞተር በመሆን ከማገልገሉ ባሻገር ነባራዊ የኢኮኖሚ ፍሰቱ አንድ ቦታ እንዳይከማች ክልሎች ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑና ሁሉም ዜጋ ከዘርፉ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ ያስችላል፡፡ የአገር ውስጥ ቱሪዝም ኢትዮጵያ እየተጓዘችበት ላለችው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት ካለው የላቀ አስተዋጽኦ ባሻገር ክልሎች የተሻለ ሀብት እንዲፈጥሩና ዜጎች እርስ በእርስ በመቀራረብ ዘላቂ የኢኮኖሚ ጥቅም እንዲያገኙ ብሎም የጋራ ሰላም እንዲመሠርቱ ጉልህ ፋይዳ አለው። በተጨማሪም ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህል፣ ወግ፣ ልማድና የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መስህቦቻቸውን በማስተዋወቅና በማወቅ በልዩነት ውስጥ ያለውን ሕብረ ብሔራዊነት በማጉላት አንድነትን ማጽናት ያስችላል፡፡

ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት የኢትዮጵያን ገጽታ ከማስተዋወቅና ቱሪዝምን ከማነቃቃት ባሻገር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ያላቸው ሚና የማይተካ ነው። የአገር ውስጥ ቱሪዝም ለጋራ ትርክት ግንባታና ብሔራዊ ገጽታን ለማስረጽ ከፍተኛ ድርሻ ያለው መሆኑን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች የሚከበሩ ሕዝባዊና ሐይማኖታዊ በዓላትን በማስተዋወቅ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማሳደግ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን አቶ ተሾመ ይናገራሉ። በዚህም የውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች የተለያዩ ሃይማኖታዊ እና የብሔር ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላት ላይ እንዲታደሙ መረጃዎችን የማሰራጨትና የመቀስቀስ ሥራ ተሠርቷል።

የአገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማበረታታትና የቱሪዝም አማራጮችን በስፋት ለማስተዋወቅ “ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ፣ በሐዋሳ፣ በአርባ ምንጭ፣ በበቆጂ እና በጅማ ከተሞች በተከናወኑ የሩጫ ውድድሮች የቱሪስት መዳረሻዎችን ማስተዋወቅ ተችሏል፡፡ አገር ተረካቢው ወጣት ሀገሩን እንዲያውቅና የጉብኝት ባህሉን እንዲያሳድግ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች የጉብኝት መርኃ ግብሮችን ማካሄድ ጀምረዋል፡፡

ቱሪዝም እና መሰረተ ልማት



89

ለቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት የመንገድ፣ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መሰረተ ልማትና የትራንስፖርት አገልግሎት መሳለጥ የግድ ይላል፡፡ በተለይ ወደ መዳረሻ ቦታዎች የሚደረግን ጉዞ ቀላልና ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ ቱሪስቶችን ለመሳብ ተቀዳሚ መስፈርት በመሆኑ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ሰፋፊ የመሠረተ ልማት ግንባታ አከናውናለች፤ በማከናወን ላይም ትገኛለች፡፡

በትራንስፖርት መሰረተ ልማት ከአፍሪካ ቀዳሚና ተመራጭ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ለማስተሳሰር የላቀ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኝ የአህጉሪቷ አንጡራ ሀብት ሲሆን፤ አዲስ አበባም ይህንኑ ትስስር የምታሳልጥና በቱሪዝም ዘርፍ ያልተነካ እምቅ ሀብት ያላት ተመራጭ መዳረሻ ናት፡፡ ይህ በዘርፉ መሰማራት ለሚሹ ባለሀብቶች ትልቅ ዕድል መሆኑ አያጠያይቅም፡፡

መንግሥት የቱሪዝም ስትራቴጂ በመዘርጋት ሁሉንም የአገሪቷን ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህም ቀደም ብለው የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማደስና የማስፋፋት፣ አዳዲስ መዳረሻዎችን የመገንባት፣ ሰላምና ደህንነትን የማረጋገጥ ሥራዎችን አበክሮ በመሥራት ዘርፉን ይበልጥ ተደራሽ በማድረግ ኅብረተሰቡ ከሀብቱ ተቋዳሽ ሆኗል። መንግሥትና የግሉ ዘርፍ መዋዕለ ንዋያቸውን በማውጣት በጋራ የሚያከናውኗቸው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ለዘርፉ ዕድገት አይተኬ ሚና አላቸው፡፡ መንግሥት በጀመራቸው ኢኒሼቲቮች በመታገዝ የተሻለ የቱሪስት መስህብ የሆኑ፣ ከፍተኛ ገቢ የሚያመነጩ መዳረሻዎችን፣ ባህላዊና ታሪካዊ ሀብቶችን በመለየት ወጥነት ባለው መልኩ ሀብቶቹን የማስተዳደርና የመደገፍ አካሄድ ተፈጥሯል፡፡ የተቀናጀ የመዳረሻ አስተዳደር ወጥነት ያለው አቀራረብ ሲሆን መሰረተ ልማትን፣ ኢንቨስትመንትን፣ የአቅም ግንባታን፣ የግልና የመንግሥት ካፒታል ፍሰትን የሚጠይቅ ነው፡፡

አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ

የቱሪዝም ዘርፍ ለኢትዮጵያ የሚያበረክተውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ለማሳደግ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ የቱሪዝም ልማት ፖሊሲ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን በዚህም በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡ ፡ ይሁንና ሀገሪቷ ካላት እምቅ የቱሪዝም ሀብት አንፃር የተገኙት ውጤቶች እዚህ ግባ የሚባሉ ባለመሆናቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት



90

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

የቱሪዝም ተወዳዳሪነት ዝቅተኛ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ፖሊሲው የተቀናጀና ቀጣይነት ያለው የቱሪዝም ልማት ማረጋገጥ አለመቻሉ፣ አዳዲስ መዳረሻዎችን የማልማት ሥራ ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም የመስህቦች ተደራሽነት አለመጠናከር ከውስንነቶቹ መካከል ይጠቀሳሉ፡ ፡ በተጨማሪም ውጤታማ የግብይትና የማስተዋወቅ ሥራ በበቂ ሁኔታ አለመሠራቱ አዳዲስ ገበያዎችን መፍጠር ብሎም የገበያ ድርሻን ትርጉም ባለው ደረጃ ማሳደግ አልተቻለም፡፡ ምቹ የንግድ ሥነ ምህዳር ባለመፈጠሩ አነስተኛና መካከለኛ የቱሪዝም ንግድ ተቋማትን በማስፋፋትና በዘርፉ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ የነባሩ ፖሊሲ ጉድለቶች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡

ነባሩ የቱሪዝም ልማት ፖሊሲ ዘርፉ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ከማስቻል አኳያ ውስንነቶች የነበሩበት በመሆኑ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ እንደሚያስችል የታመነበትን አዲሱን የቱሪዝም ፖሊሲ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም አፅድቋል።

የተሻሻለው የቱሪዝም ልማት ፖሊሲ ዘርፉን ለዘመናት ተብትበው የያዙትን ማነቆዎች በመፍታት የሀገሪቷን ሰፊ የቱሪዝም ሀብት መሠረት በማድረግ የቱሪዝም መዳረሻዎችና ምርቶችን በማስፋት ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ ነው፡፡

የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ማስፋት፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ በዘርፉ የአገልግሎት ልህቀት ማረጋገጥ፣ ከጎብኚ አመንጪ ሀገራት ጋር ጠንካራ የገበያ ትስስር በመፍጠር የጎብኚዎችን ፍሰት እና የገበያ ድርሻ ማሳደግ እንዲሁም የታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ተፈጥሯዊ ሀብቶች



91

ጥበቃ እንዲጠናከርና የዜጎች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ከሌሎች ዘርፎች ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር በተሻሻለው ፖሊሲ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

ፖሊሲው ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘው ገቢ እንዲጨምርና ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት የሚያበረክተውን ድርሻ ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ነው፡፡ መንግሥት በዘርፉ የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረጉ ተቋማዊ ቅንጅት እንዲጠናከር ከማድረግ ባሻገር የመሰረተ ልማት መስፋፋት፣ የዲጂታል ሽግግር እና የሥራ ፈጠራን ጨምሮ ጠንካራ ሀገራዊ ስትራቴጂ እንዲዘጋጅ የሚያስችል፤ በዘርፉ መሠማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶችም ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው

ማጠቃለያ

መንግሥት ከቱሪዝም ዘርፍ ጋር ተያይዞ የኢኮኖሚ ዕድገቱን ለማስቀጠል፣ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እና የሀገሪቷን ዓለም አቀፋዊ ገጽታ ለማጎልበት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል በዚህም አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ለበርካታ ዓመታት ተዘንግቶ የቆየው የቱሪዝም ዘርፍ አሁን የሀገር ገጽታ መገንቢያ፣ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ እና የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት እየሆነ መጥቷል፡፡

የተመዘገቡ ስኬቶችን የመጨረሻ ግብ ባለማድረግ የኢትዮጵያን ገና ያልተነኩና መስህብ ሊሆኑ የሚችሉ ያልተገለጡ ሀብቶቿን ፈልጎ በማውጣት፣ በማልማት ከዘርፉ ይበልጥ ተጠቃሚ ለመሆን በቱሪዝም ባለድርሻ አካላት መካከል ጠንካራ ቅንጅት መፍጠር ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ በጋራ የሚከናወኑ የመዳረሻና የገበያ ልማት፣ የገጽታ ግንባታና የማስተዋወቅ ሥራዎችን ማጠናከር፤ መሠረተ ልማቶችና አገልግሎት መስጫዎችን ማስፋፋት፣ የመዳረሻዎችን ተወዳዳሪነት ማሳደግ እና በቱሪዝም ዕሴት ሰንሰለት ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጥራት ማረጋጋጥ ያስፈልጋል፡፡



92

ኢኮኖሚ

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

የአፍሪካ ነጻ የንግድ



93

ቀጣና ለኢትዮጵያ

በዳግም መርሻ እና በኤልያስ መሀመድ

የምንኖርበት ዓለም በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በፈጣን መረጃ ልውውጥ፣ በነፃ ንግድ እና በማኅበራዊ ሚዲያ የተሳሰረ፣ የሉላዊነት ወይም የግሎባላይዜሽን ዘመን ነው። ይህ ዓለም አቀፍ ሁኔታ የምጣኔ ሀብት ዕድገት እና የባህል ልውውጥን ቢያፋጥንም፤ የሀገራትን ፖለቲካዊ ሉዓላዊነት፣ ባህላዊ እሴቶች እንዲሁም በራስ የመመካት አቅምን በመፈታተን የኢኮኖሚ ጥገኝነትና ማኅበራዊ መመሰቃቀል እያስከተለ መሆኑን የየዕለቱ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች በቂ ማሳያዎች ናቸው።

አገራት ሉላዊነት (ግሎባላይዜሽን) ያመጣቸውን እነዚህን ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች ለመቋቋምና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከሚወስዷቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ በተለያዩ የንግድ እና



94

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

የኢኮኖሚ ግንኙነቶችና ድርድሮች በመሳተፍ አጋርነትን ማጠናከር ነው። እነዚህ እርምጃዎች ዘላቂ ዕድገት ለማምጣት፣ ሕዝባቸውን ከድህነት ለማላቀቅ፣ የንግድ ሚዛን ጉድለትን ለመቀነስ አንዲሁም ዓለም አቀፍ ተጽዕኖን ለመፍጠር ያስችላሉ። የጋራና ተመሳሳይ ፍላጎቶችንም ለማሟላት ተጨማሪ ጉልበትና አቅም መሆናቸውንም የበርካታ የዓለም ሀገራት ተሞክሮ ያሳያል።

ነጻ የንግድ ቀጣና (ስምምነት) የንግድና የኢኮኖሚ ግኑኝነት አንዱ አካል ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ይህን ስምምነት ቀድመው የፈጸሙ ሀገራት ኢኮኖሚያቸውን በማጠናከር፣ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር፣ የሕዝብ የኑሮ ደረጃን በማሻሻል እንዲሁም የማኅበራዊ ግንኙነትን በማጎልበት አገራዊ ዕድገት ማስመዝገብ ችለዋል። በተለያዩ ዓለማት በርካታ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች ቢኖሩም የአውሮፓ ሕብረት (EU) በጥሩ ተምሣሌትነት ይነሳል። 27 አባል ሀገራትን ያቀፈው የአውሮፓ ሕብረት አንድ የጋራ ገበያ ከመፍጠር ባሻገር፣ የጋራ መገበያያ ገንዘብ (ዩሮ) እና የጋራ ፖሊሲዎች አሉት። በዓለም ላይ ኃያል ከሚባሉት የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ጥምረቶች መካከልም አንዱና ዋነኛው ሆኖ ይጠቀሳል።

ወደ አፍሪካ ስንመጣ በኢኮኖሚ የተዋሀደች አፍሪካን እውን ማድረግ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት የያኔው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት መሥራች አባቶች ራዕይ ነበር። መነሻውም ሰፊ ገበያና ብዙ ሕዝብ፣ የመግዛት አቅም ያለው ጠንካራ ኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ግቦችን ማሳካት ዓላማ ያደረገ ነው።

እንደ አ.አ.አ 1963 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሲመሠረት የድርጅቱ መሥራች አባቶች የአፍሪካ ሀገራትን የፖለቲካ ነጻነት በኢኮኖሚ ነጻነት የማጠናከር ትልም ነበራቸው። ከዚህ አኳያ የአውሮፓ ነጻ የንግድ ማኅበርን (EFTA - European Free Trade Association) እንደ ሞዴል በመውሰድ በሂደት አንድ የጋራ ገበያ፣ የጋራ የጉምሩክ



95

ሥርዓት እና በመጨረሻም የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ማኅበረሰብ የመፍጠር ራዕይ እንደነበራቸው ታሪካዊ ሰነዶች ያመለክታሉ።

ከላይ የተጠቀሰውን ራዕይ ለማሳካት የአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና የትብብር ማዕቀፍ ከተጠነሰሰበት እ.አ.አ ከ1979 የሞንሮቪያ ስትራቴጂ ጀምሮ ጥረቶች ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን በተለይም በ1980 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአፍሪካ የተፋጠነ የኢኮኖሚ ልማት ለማረጋገጥ ይረዳ ዘንድ የአፍሪካ የጋራ ገበያ ምሥረታ እና የኢኮኖሚ ውህድትን ለማጠናከር እንደ መሪ ዕቅድ የሚታየውን የሌጎስ የድርጊት መርሃ ግብር (Lagos Plan of Action) አጽድቋል።

ይህ መርኃ ግብር የጋራ የጉምሩክ ሥርዓትና አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ በመፍጠር የአህጉሪቷን የንግድና የካፒታል ዝውውር ለማሳለጥ ያለመ ነው። በተጨማሪም እ.አ.አ በ1991 የድርጅቱ አባል ሀገራት የአፍሪካን ነጻ የኢኮኖሚ ውህደት፣ የጋራ ንግድ፣ አገልግሎት እና የካፒታል ዝውውር በማሳለጥ 55 ሀገራትን ለማስተሳሰር እንዲሁም አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ያለመውን የአቡጃ ስምምነት አጽድቀዋል። ይህ ስምምነት በተለይ ለአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና መመስረት ወሳኝ እርምጃ ተደርጎ ይወሰዳል።

ምንም እንኳን ሂደቱ ብዙ ጊዜ ቢወስድም እ.አ.አ በ2018 በሩዋንዳ ኪጋሊ 44 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ለመመስረት የተዘጋጀውን ሰነድ በመፈረም ዛሬ ላይ የአፍሪካ ሀገራትን በአንድ የጋራ ገበያና ኢኮኖሚ የሚያስተሳስረው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ተፈጥሯል።

በመቀጠልም የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ባካሄደው 25ኛው መደበኛ ስብሰባ አህጉራዊው ነጻ የንግድ ቀጣና ድርድር በይፋ እንዲጀምር ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወቅ ሲሆን፤ እ.አ.አ ከጃንዋሪ 2021 ጀምሮ ደግሞ ስምምነቱን የፈጸሙ ሀገራት የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ ጀምረዋል። በዚህም ኢትዮዽያን ጨምሮ 47 ሀገራት ስምምነቱን የሀገራቸው ህግ አድርገው በተለያየ ደረጃ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

አህጉራዊ አንደምታው

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና የአጀንዳ 2063 አካል ሲሆን ዓላማውም የተዋሀደች፣ የበለጸገችና ሰላማዊት አፍሪካን ከመፍጠር ባሻገር በፓን አፍሪካ ራዕይ የአፍሪካን የኢኮኖሚ መሰረት የሚያሰፋ፣ በሰዎች ነጻ እንቅስቃሴ የሚታገዝ፣ የንግድ ቀጣና ታሪፍን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በማስቀረት እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር በ2034 አፍሪካ ውስጥ 60 በመቶ ንግድን ለመፍጠር ያለመ ነው። ይህም 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ሕዝብ ያላትን አህጉር ድምር የሀገር ውስጥ ምርት 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር እንዲደርስ የሚያደርግ ነው።

ስምምነቱ ከአገልግሎትና ከዕቃዎች ንግድ አልፎ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የሴቶች እና የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና አለው። የንግድ ማዕቀፉ ደረጃ በደረጃ እየሰፋ የሚሄድ ሲሆን በተጨማሪም በአፍሪካዊያን መካከል ጠንካራ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ ግኑኝነቶችም እየተጠናከሩ የሚሄዱ መሆኑን የሚያሳዩ ድንጋጌዎች ስምምነቱ ውስጥ ተካተዋል።

የአፍሪካ ሕብረት መረጃ እንደሚያሳየው በአሁኑ



96

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ወቅት የአፍሪካ ሀገራት እርስ በእርሳቸው የሚያደርጉት የንግድ ልውውጥ ከጠቅላላ የንግድ ልውውጣቸው ከ15-18 በመቶ ብቻ ነው። ይህ የአውሮፓ እና የእስያ ሀገራት እርስ በርስ ከሚያደርጉት ንግድ ጋር ሲነጻጸር እጅግ ዝቅተኛ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። በመሆኑም የንግድ ሚዛኑን መዛባት ለማስተካከል አህጉራዊው ነፃ የንግድ ቀጣና አይነተኛ መፍትሔ ነው፡፡ በርግጥ አንዳንዴ የተለያዩ ሀገራት እንደ አጉዋ (AGOWA) ያሉ የገበያ ዕድሎችን ለአፍሪካ ሀገራት የሚያመቻቹ ቢሆንም እነዚህ ኢኒሼቲቮች ተልዕኳቸው ከአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና የተለየ ከመሆኑም በላይ አብዛኛውን ጊዜ ዘላቂነት የላቸውም። ከዚህ አንጻር ከራሳችን ጋር በዘላቂነት የሚቆየውና የአፍሪካን ችግር ይፈታል ተብሎ የታመነበት ከእኛው ለእኛው የሆነ ኢኒሼቲቭ ነው-የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና።

የዓለም ባንክ ሪፖርት እንደሚያሳየው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውጥን ተግባራዊ መሆን ከቻለ እ.አ.አ በ 2035 ዓ.ም 30 ሚሊዮን አፍሪካዊያንን ከከፋ ድህነት፣ እንዲሁም 70 ሚሊዮን የአህጉሪቷን ሕዝቦች ከመካከለኛ ድህነት ያወጣል። ሪፖርቱ እንዳስቀመጠው በዚሁ ዓመት የአፍሪካን ገቢ በ450 ቢሊዮን ዶላር (7 በመቶ) እንዲያድግ የሚያስችል ሲሆን የአፍሪካ የወጪ ምርት በ560 ቢሊዮን ዶላር ከፍ እንዲልም ያደርጋል።

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ተግባራዊ ሲሆን የአፍሪካ ኢኮኖሚ ከሌላው ዓለም ጋር ያለውን የንግድ ግንኙነት በተሻለ መልኩ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል። በሌላ በኩል አሁን ያለው 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን የአፍሪካ ሕዝብ እ.አ.አ በ2050 ወደ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን እንደሚያድግ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም ለአህጉራዊው ነፃ የንግድ ቀጣናው ግዙፍ ዕድሎችና ገበያዎችን ይዞ ይመጣል።

በርካታ የአፍሪካ ሀገራት እሴት የታከለባቸው ምርቶችን ቀለል ባለ መንገድ እርስ በእርስ ከመገበያየት ይልቅ ጥሬ ዕቃዎችን ወደ ውጭ



97

ልከው የተጠናቀቁ ምርቶችን በውድ ዋጋ መግዛት ለረጅም ጊዜ የተጓዙበት መንገድ ነው። ነጻ የንግድ ቀጣናው ይህን ሂደት (አዙሪት) በመቀየር አንድ የጋራ ገበያ በመፍጠር የጋራ ጥቅሞቻችንን (Net gain) እውን ምናደርገው እንዴት ነው? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስና በኢኮኖሚ እርስ በእርስ ለመተሳሰር ያላቸውን ቁርጠኝነት ስለሚያሳይ ትልቅ ፖለቲካዊ መልዕክት አለው።

በተጨማሪም የአፍሪካ ሀገራት ሰፊና የተረጋገጠ ገበያ ሲያገኙ በውድድር ሂደት ውስጥ ማለፍ ስለሚጠበቅባቸው ምርትና ምርታማነታቸውን ያሻሽላሉ። ከዚህም ባሻገር በአህጉር ደረጃ የሚወጡ ፖሊሲዎች ተገማችና የማይቀያየሩ በመሆናቸው ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለመሳብ የሚያስችል ሁኔታ ይፈጥራል። ይህም ሸማቾች በተሻለ ዋጋ ጥራት ያላቸውን እንዲሁም አማራጭ ምርቶችን እንዲያገኙ ያስችላል።

በተመሳሳይ አምራቾች ሰፊ ገበያ ስለሚያገኙ “በአፍሪካ የተመረተ” (Made in Africa) የሚሉ ምርቶችን በብዛት እንዲያመርቱ የሚያግዝ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። ከንግድ ልውውጥ ባለፈም በሀገራት መካከል ባህላዊና ማኅበራዊ ትስስርን ያጠናክራል፤ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግርንም ያሳድጋል፡፡

ሆኖም የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ዕድሎች እንዳሉት ሁሉ ስጋቶችም ይነሱበታል። ከዚህ አንጻር በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው የትራንስፖርት ትስስርና የሎጂስቲክስ ሥርዓት ደካማ መሆን፣ ወጥ የሆነ የጋራ መገበያያ ገንዘብ አለመኖር፣ ወጥነት የሌላቸው የጉምሩክ ህጎችና ድንበር ላይ ያሉ እንቅፋቶች፣ የአባል ሀገራቱ በተለያየ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ መገኘት እና ይህም ነጻ የንግድ ቀጣናውን በእኩል ደረጃ ለመቀበልና ለመተግበር ፈተና መሆኑ እንዲሁም አንዳንድ ሀገራት ነፃ የንግድ ቀጠናውን አለመቀላቀላቸው በትግበራ ሂደት እያጋጠሙ ያሉትን ፈተናዎች የሚያሳዩ ዋና ዋና ጉዳዮች ናቸው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው የመከራከሪያ ነጥብ ወይም ስጋት ጠንካራ የአምራች ዘርፍ ያላቸው ጠንካራ ያልሆነ የአምራች ዘርፍ የሌላቸውን ሀገራት ገበያ እንዲቆጣጠሩ ስለሚያደርግ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ያዳክማል፤ ሀገራት ከታክስ ያገኙ የነበረውን ከፍተኛ ገቢ እንዲቀንስ ያደርጋል የሚል ይገኝበታል። ይህ ስጋት በተወሰነ መልኩ እውነትነት ቢኖረውም ነፃ የንግድ ቀጣናው ምርታማነትን ለማሻሻልና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ካለው ትልቅ ፋይዳ አንጻር ስጋቱ የተጋነነ ነው በሚል ይተቻል።

ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው?

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ሰነዱን በፊርማቸው አፅድቀው ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ከሚገኙ 47 ሀገራት መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች።

በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የፈንድ እና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታገስ ሙሉጌታ እንደሚሉት አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ለኢትዮጵያ አዲስ ልምምድ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት አሁን ባለው ትልቁ የዓለም የንግድ ማዕቀፍ ለምሣሌ (የዓለም ንግድ ድርጅት) ውስጥ ኢትዮጵያ አባል አልነበረችም፤ ምንም እንኳን አሁን አባል ለመሆን ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገች ቢሆንም። በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ነፃ የንግድ ስምምነትም ቢሆን ከተሳትፎና



98

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

አባል ከመሆን ባለፈ ወደ መሬት የሚወርዱ ጉልህ እርምጃዎችን አልወሰድንም። በዚያ ልክ ኢኮኖሚያችን ላይ ያለውን አንደምታ መተንተን አስቸጋሪ ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ የነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ያደረገቸው እ.አ.አ በ2001 ከሱዳን ጋር ሲሆን ወደ መሬት ባይወርድም እ.አ.አ በ2017 ከደቡብ ሱዳን ጋርም እንደሆነ ያብራራሉ።

ኢትዮጵያ ከዚህ የተለየ ነፃ የንግድ ሰምምነት ታሪክ እንደሌላት የሚገልጹት አቶ ታገስ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት አዲስ ጅማሮ እንደሆነ ይገልጻሉ። የነፃ የንግድ ቀጣናው ስምምነት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ጥቅም ሲያብራሩ “ስምምነቱን በአግባቡ ከተገበርነው፣ ተቋማዊ አደረጃጀታችንን ካጠናከርን፣ የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓታችንን በአግባቡ ሥራ ላይ ካዋልን ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገራት ያገኙትን ጥቅም አገራችንም ልታገኝ ትችላለች” ሲሉ ይገልጻሉ።

ነፃ የንግድ ቀጣናው ለኢትዮጵያ ተገማች የሆነ የንግድ መዳረሻ የሚፈጥርላት መሆኑንና አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ እንደ እነዚህ አይነት ስምምነቶች ካልተደረጉ “ያሰብነው የገበያ መዳረሻ ቦታ ሊቋረጥብን ይችላል” ሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል። ይህ የሚያሳየው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ቁመና ላይ መሰረታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ነው።

ከዚህ የንግድ ስምምነት የሚገኘው ጥቅም እንደየሀገራቱ የኢኮኖሚ ዕድገት እና ተጨባጭ ሁኔታ ይለያያል። እንደ አቶ ታገስ ማብራያ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ጥቅም በሶስት ከፍሎ ማየት ይቻላል።

የመጀመሪያው ምጣኔ ሀብታዊ ጥቅሙ ሲሆን ይህ በመንግሥት ልዩ ከለላ እና ድጋፍ (Protectected industry) ስር ለቆየና ትኩረቱን በሀገር ውስጥ ብቻ አድርጐ ከነበረ የኢንዱስትሪ ስትራቴጂ ወደ ክልላዊ የኢኮኖሚ ውህደትና ውድድር ወዳለበት የገበያ አውድ የሚደረግ የኢኮኖሚ ሽግግርን ያመላክታል። በዚህ አውድ ውስጥ ለኢትዮጵያ ምርቶችና አገልግሎቶቸ ከ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ ያለውና ከ 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር አጠቃላይ አህጉራዊ ምርት ያለው የገበያ ዕድል ይፈጠራል። ይህ ከዚሀ ቀደም በተበታተነ መልኩ ሲካሄድ ከነበረው የንግድ ግንኙነት አንጻር እጅግ የላቀ ጠቀሜታ አለው።

ሁለተኛው ከፖለቲካ አንጻር ያለው ጥቅም ነው። የኢትዮዽያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አንደኛው የትኩረት አቅጣጫ አፍሪካ በፖለቲካ እና በምጣኔ ሀብት የተሳሰረች፣ የበለጸገች እንድትሆን እንዲሁም በአፍሪካ ሀገራት መካከል የንግድ እንቅስቃሴ እንዲጎለብት ማድረግ ላይ ያተኩራል። ይህ ኢትዮዽያ ከቀድሞ ጀምሮ ስታራምደው የቆየችው የፓን አፍሪካኒስት የውጭ ግኑኝነት ፖሊሲ አቅጣጫ ስለሆነ ስምምነቱን ዳር ማድረስ እንደ አንድ የውጭ ግንኙነት ስኬት ተደርጎ ይቆጠራል። በተጨማሪም ከብዙ ሀገራት ቀድመን ነፃ የንግድ ቀጣናውን ስምምነት በመፈረማችን ለአህጉራዊው አጀንዳ 2063 መሳካት እንዲሁም ለአፍሪካ አንድነት (ፓን አፍሪካኒዝም) እና ለአህጉራዊ ውህደትና አንድነት ያለንን ቁርጠኝነት ያጠናክረዋል።

ግንኙነታችንን ከቀላል ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነት



99

ወደ ዘርፈ ብዙና የጋራ ጥቅም ወደሚያረጋግጥ ኢኮኖሚያዊ አጋርነት ይለውጠዋል። ይህም ሀገራት በተስማሙበት የጋራ መርህና ፖሊሲ መሰረት የሚመራ በመሆኑ የጋራ መደጋገፍን ይፈጥራል፤ ለሰላምና መረጋጋትም ጠንካራ መሰረት ይጥላል።

በሌላ በኩል ማኅበራዊ ግኑኝነትን ከማጠናከር አኳያ ሲታይ ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ቁጥር መጨመር እና የገበያ መስፋፋት የሕዝብ ለሕዝብ ግኑኝነትን ያጠናክራል፤ ድንበር ተሻጋሪ ትብብርን እና የጋራ ማንነት ስሜትን ያጎለብታል። የንግድ መጠናከር ደግሞ የተለያዩ የኅብረተሰብ ከፍሎች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ ባለሙያዎች እንዲሁም ምሁራን ከሌሎች የአፍሪካ አቻዎቻቸው ጋር እንዲቀራረቡና ልምድ እንዲለዋወጡ የመገናኛ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል። ይህ ደግሞ የተዋሃደና አንድ አፍሪካዊ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ እንዲፈጠር ትልቅ አበርክቶ ይኖረዋል።

በአጠቃላይ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የአኮኖሚ ግንኙነት አሁን ካለበት ዝቅተኛ ደረጃ በተግባር ወደሚገለጥ፣ ወደ ተደራጀና የጋራ ጥቅም ወደሚያስገኝ የተሳትፎ ደረጃ ለመሸጋገር የሚያግዝ አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

የዝግጅት ሂደትና ትግበራው

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና መሥራችና ስምምነቱን ከፈረሙ ቀዳሚ ሀገራት አንዷ እንደ መሆኗ ስምምነቱን መሠረት ያደረገ ግብይት ለመጀመር አብዛኛውን ዝግጅት ጨርሳለች።

ከዝግጅቶቹ መካከል ግብይቱን ለመጀመር የታሪፍ የቀረጥ ምጣኔ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወስኖ ሀገራት እንዲያውቁት መደረጉ፣ የንግድ ዕቃዎች የውል ሰንጠረዥ እና የአገልግሎት ግዴታ ሰነዶች ተዘጋጅተው መጽደቃቸው፣ ስምምነቱን ለመተግበር የሚያስችል ዝርዝር ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መግባቱ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ከዚህ ጎን ለጎን ለአምራቾች፣ ለንግዱ ማኅበረሰብ እና ለባለድርሻ አካላት የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ለሀገራትና ለንግዱ ማኅበረሰብ ስለሚያስገኘው ጥቅም፣ ስለ ኢትዮጵያ



100

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

የዝግጅት ሂደት፣ የግሉ ዘርፍ ሊያከናውናቸው ስለሚገቡ ቅድመ ዝግጅቶች የጋራ ግንዛቤ የማስጨበጥና የማነቃቃት ተግባራትም ስትሠራ ቆይታ ግብይቱን መስከረም 2018 ዓ.ም በይፋ ማስጀመሯን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይገልጻል።

አቶ ታገስ ሙሉጌታ ከዝግጅት አንጻር ያለውን ሁኔታ ሲያስረዱ፤ ኢትዮጵያ የአህጉራዊው የነፃ ንግድ ቀጣና ዓላማዎችን ለማሳካት የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት ያካተተ ሰፊ ዝግጅት እያደረገች መሆኑንና ለዚህም የሚያስፈልጉ የህግ እና ተቋማዊ አደረጃጀቶች መዘርጋታቸውን ይገልጻሉ።

ከዚህ አንጻር በሀገር አቀፍ ደረጃ የስምምነቱን የትግበራ ሂደት የሚያስተባብርና ቁልፍ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን (ንግድና ቀጣናዊ ተስስር ሚኒስቴር፣ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ፕላን ኮሚሽን፣ ጉምሩክ ኮሚሽን) ያቀፈ ብሔራዊ የአፍሪካ አህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና ኮሚቴ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተቋቁሟል። ይህ ኮሚቴ የስምምነቱን ትግበራና አፈጻጸም እንዲሁም እንደ ሀገር እየተገኙ ያሉትን ጥቅሞችና የአፈጻጸም ክፍተቶች በመገምገም አተገባበሩ በአግባቡ እየተካሄደ መሆኑን ያረጋግጣል፤ የእርምት እርምጃዎች ይወስዳል እንዲሁም አፈጻጸሙን ይመራል።

በሌላ በኩል በብሔራዊ ኮሚቴው ስር የቴክኒክ ኮሚቴዎች ተቋቁመው ለብሔራዊ ኮሚቴው ቴክኒካዊ ድጋፎችን ይሰጣሉ። ከዚህ በተጨማሪም በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ስር በስምምነቱ ውስጥ በተቀመጡት ፕሮቶኮሎች ልክ የሥራ ክፍሎች የተደራጁ ሲሆን ሥራቸውም አስፈጻሚ አካላትን ማሳተፍ እና መደገፍ መሆኑን፤ ይህም የዝግጅቱ አንዱ አካል ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን ነው አቶ ታገስ የገለጹት።



101

ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ቁልፍ ተግባር በብሔራዊ ደረጃ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መግባቱ ነው። ስትራቴጂው ግብይት እንዴት ይፈጸማል፣ አሠራሩ በምን የህግ ማዕቀፍ ይመራል፣ በየትኛው ዘርፍ፣ በየትኛው ገበያ ላይ ጥቅም አናገኛለን፣ ግብይት እንዴት ይፈጸማል የሚሉ እና መሰል ጉዳዮችን በግልጽ የሚያሳይና ሁሉንም የስምምነት ማዕቀፍ የያዘ መሆኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ይገልጻሉ። በተጨማሪም የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ዕድልን በአግባቡ መጠቀም የሚያስችሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ማዘጋጀት፣ ላኪዎችን ማደራጀት ሌላው የዝግጅቱ አካል መሆኑን ገልጸዋል።

ከፖሊሲና የህግ ማሻሻያ ሥራዎች ጋር በተያያዘ የተከናወኑትን ሥራዎች አስመልክቶ አቶ ታገስ ሲያብራሩ እየተካሄዱ የሚገኙት ሰፋፊ የኢኮኖሚ ማሻሻያና የሪፎረም ሥራዎችን በተለይም እንደ ሎጂስቲክስና ቴሌኮሙኒኬሽን ባሉ ስትራቴጂክ ዘርፎች ላይ የተወሰደው ገበያን ክፍት የማድረግ እርምጃ (Market liberalization) ለአህጉራዊው ነፃ የንግድ ቀጣና ምቹ የውድድር አውድ ለመፍጠር ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ መሆኑን ገልጸዋል።

“የጉሙሩክ አሠራሮቻችንን እና የደረጃ ማረጋገጫ ሥርዓቶቻችንን ከአህጉራዊው አሠራሮችና የተለያዩ መመሪያዎች ጋር ለማጣጣም አየተሠራ ነው” ያሉት አቶ ታገስ፤ በተጨማሪም የመጀመሪያ ደረጃ የታሪፍ ቅናሽ የጊዜ መርኃ ግብር ተዘጋጅቶ መቅረቡንና የታሪፍ ትግበራው መርኃ ግብር ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ፍላጐት ጋር በተጣጣመ መልኩ በዝርዝር ተዘጋጅቶ መቅረቡን አክለዋል።

በሌላ በኩል በትግበራው ሂደት የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ለስኬታማነቱ ወሳኝ በመሆኑ የንግዱን



102

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ማኅበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በትኩረት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል ግዛው እንዳሉት የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ጽንሰ ሀሳብ ለኢትዮጵያ አዲስ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በግሉ ዘርፍ ዘንድ የነበረው ግንዛቤ በቂ አልነበረም። ይህንኑ መነሻ በማድረግ በተሠራው ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫና የአቅም ግንባታ ሥራ በንግዱ ማኀበረሰብ ዘንድ ያለው ንቃተ ህሊና ከቀን ወደ ቀን እየተሻሻለ መጥቷል።

አቶ ታገስ በበኩላቸው ምንም እንኳን በቂ ነው ባይባልም በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የንግድ ምክር ቤቶችንና አደረጃጀቶችን በመጠቀም የንግዱ ማኅበረሰብ ተከታታይ ግንዛቤ እንዲያገኝ መደረጉን ገልጸው፤ ለላኪዎች፣ ለጉሙሩክ ኮሚሽን እና ለደረጃ ማረጋገጫ ተቋማት ሠራተኞች የተሰጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የሥልጠና መርኃ ግብሮችን ለማሳያ አንስተዋል። ሆኖም በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ሆነ በሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተደረጉ የሚገኙት እነዚህ እንቅስቃሴዎች በቂ ባለመሆናቸው አሁንም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው በአጽንኦት ገልጸዋል።

የመሰረተ ልማት ዝግጅትን በተመለከተ አቶ ታገስ እንደሚሉት እንደ ኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር፣ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለይም የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና፣ የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫና በሂደት ላይ የሚገኙ ሌሎች የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች እንዲሁም ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያስተሳስሩ የመንገድ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ ስር ለሚደረጉ ግብይቶች የንግድ ወጪን ለመቀነስና ኢትዮጵያን ተወዳዳሪ የማኑፋክቸሪንግ እና የሎጂስቲክስ ማዕከል ለማድረግ ወሳኝ ነው።



103

በጥቅሉ ይህ የሚያሳየው ኢትዮጵያ ከቃል ባሻገር ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ተግባራዊነት ያላትን ቁርጠኝነት ነው።

የትግበራው ሂደት

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ከተፈረመ ወዲህ አንዳንዶቹ አባል ሀገራት በተመረቱ ምርቶች ላይ የንግድ ልውውጥ በማድረግ የስምምነቱን ተግባራዊነት እያሳዩ ሲሆን ሌሎች ደግሞ አሁንም ተቋማትን በመገንባት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርገዋል።

ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ሀገራት የተለያዩ ምርቶችን መላክ ከጀመሩ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ድርድሩን ካጠናቀቀች በኋላ ከመስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ግብይት መጀመሯን አስታውቃለች። በዚህ ረገድ ስጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ወደ ሶማሊያ፤ ነጭ እና ቀይ ቦሎቄ እንዲሁም ቡና ወደ ደቡብ አፍሪካ፤ የበቆሎና የቦሎቄ ምርቶችንም ወደ ኬንያ ማስገባቷ ቀረጥ ከሌለባቸው ግብይቶች መጀመሯን ያመላክታል። በአፍሪካ ከ60 በላይ መዳረሻዎች ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰዎችንና የሸቀጦችን ትራንስፖርት በማቀላጠፍ በነፃ ንግድ ቀጣናው ትግበራ ሂደት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል።

አቶ ታገስ ሙሉጌታ እንገለጹት ከሆነ ከስምምነቱ መተግበር በኋላ በጉሙሩክ ኮሚሽን አማካኝነት በነፃ የንግድ ማዕቀፍ ግብይት ማካሄድ የሚያስችል የዕቃዎች የስሪት ሀገር ምንጭ (Rules of or- igin) የምስክር ወረቀት (Certificate) ለ90 ኤክስፖርተሮች እና ባለሀብቶች ተሰጥቷል። የዕቃዎች የስሪት ሀገር ምንጭ ማለት አንድ ምርት በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ የት ሀገር እንደተመረተ ለመለየት የሚያገለግሉ መመሪያዎችና መስፈርቶች ናቸው። ይህ “የምርት ፓስፖርት” ተብሎ የሚጠራው አሠራር ዕቃው ዝቅተኛ የታሪፍ ተጠቃሚ መሆን አለመሆኑን፣ የንግድ ገደቦችን እና የምርቱን አመጣጥ ወይም ምንጭ የሚያረጋግጥ ነው።

እንደ አቶ ታገስ ገለጻ ከዚህ ቀድም ኤክስፖርት ሲደረግባቸው የነበሩ የገበያ መዳረሻዎች ሲላክ የነበረው የምርት መጠን ከስምምነቱ ትግበራ በኋላ በተወሰነ ደረጃ ጭማሪ አሳይቷል። በዚህ መሠረት ኬንያ ከፍተኛውን የገበያ ድርሻ በመያዝ የኢትዮጵያ ቁልፍ የወጪ ምርት መዳረሻ ሆና ቀጥላለች። ከዚህ ቀደም የወጪ ምርት መዳረሻ የነበሩት እንደ ሩዋንዳ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አልጄሪያ፣ ታንዛኒያ እንዲሁም ጋናን የመሳሰሉ ሀገራት በኢትዮያ የግብርና ምርቶች ላይ እያሳዩት ያለው ፍላጎት ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ ቢመጣም ወደ ኬንያ ከሚላከው የወጪ ምርት አንጻር በጣም አነስተኛ ነው። ይህም ኢትዮጵያ በአህጉራዊው ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ ያላትን የንግድ መዳረሻ በይበልጥ ማስፋትና የገበያ ድርሻውን የተመጣጠነ ማድረግ እንዳለባት የሚጠቁም ከመሆኑ በተጨማሪ ላኪዎች የገበያ ዕድሉን በተሸለ ሁኔታ መጠቀም እንደሚኖርባቸው ተገልጿል።

ከገቢ ምርት አንጻር ከስምምነቱ ትግበራ በኋላ በተመሳሳይ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን ኬንያ ከፍተኛውን ድርሻ በመያዝ ቀዳሚ የገቢ ምርት ምንጭ መሆኗ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ግብጽ እና ታንዛኒያ ደግሞ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ይህ የሚያሳየው ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት የንግድ ትስስር በተለይም ከኬንያ ጋር ያለው ግንኙነት



104

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በአህጉራዊው ነፃ የንግድ ቀጣና ውስጥ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ነው።

የሀገራችን አብዛኞቹ ነጋዴዎችና ባለሀብቶች በአብዛኛው ዕቃ የሚያስመጡት ከቻይና፣ ከዱባይ ከታይላንድ ወይንም ደግሞ ከሌሎች የመካከለኘው ምስራቅ ሀገራት መሆኑንና እዚሁ አህጉራችን ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ገበያ አፈላልጎ ዕቃ የማስመጣት ልምድ አለመኖሩን የገለፁት አቶ ታገስ፤ የወጪና ገቢ ንግዱን የተወሰነ ገበያዎች ላይ ብቻ ትኩረት ከማድረግ በምዕራብ፣ በሰሜንና በደቡብ አፍሪካ ሀገራት ላይም ትኩረት በማድረግ የገበያውን ዕድል መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

ለአምራቾችና ላኪዎች ያለው ፋይዳ

ኢትዮጵያ ከ120 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት፤ በዚህም በአፍሪካ ከናይጄሪያ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ መሆኗ ለአምራቾችና ለግል ባለሀብቶች ሰፊ የሀገር ውስጥ የገበያ ዕድል የሚፈጥር ትልቅ አቅም ነው። ይህ እንዳለ ሆኖ ግን የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ከዚህ በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ሰፊ የገበያ ዕድል የሚፈጥር ማዕቀፍ ነው።

አህጉራዊው ነፃ የንግድ ስምምነት 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ሕዝብ በሚኖርባት አህጉር ከ 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያለው ሰፊ ገበያ በመፍጠር አምራቾችና የግል ባለሀብቶች የንግድ ዕድል እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል ግዛው ይገልጻሉ፡፡

እንደ ኃላፊው ማብራሪያ የሀገር ውስጥ ገበያ የሚመረት ምርት እና የ54 የአፍሪካ ሀገራትን ገበያ ታሳቢ በማድረግ የሚመረት ምርት ብዛትና የሚያመጣው ጥቅም ይለያያል። ሰፊ የገበያ ዕድል ይፈጠራል ሲባል ይሄንን ሁኔታ ያመላክታል። የበርካታ ሀገራት ገበያን ታሳቢ በማድረግ የሚካሄድ የንግድ እንቅስቃሴ በስፋት በሚመረት ምርትና አቅርቦት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የሚያስገኘውም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍ ያለ ነው።

በመሆኑም አንድ አምራች ወይም የግል ባለሀብት የሚያመርተው ምርት የትም ሀገር ላይ ሄዶ ተወደዳሪ መሆን ከቻለ በሀገር ውስጥ ገበያ ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀርበት ምክንያት እንደማይኖር ይገልጻሉ። የተረጋገጠ ገበያም ከዚህ ጋር የሚያያዝ ሆኖ የሚመረቱት ምርቶች ከቀረጥ ነጻ በሆነ መልኩ ስለሚላኩ ገበያውን መገመት ወይም መተንበይ ይቻላል። በአጭሩ የገበያውን አዋጭነት አረጋግጦ መገበያየት እንዲሁም የገበያ መዋዠቅ የሌለበት የግብይት ሂደት ማለት እንደሆነ አቶ ሳሙኤል ያስረዳሉ።

“ኢትዮጵያ ከፍተኛ የግብርና ምርቶችን የማምረት አቅም ያላት ሀገር ነች። ምቹ እና የተለያዩ የአየር ንብረት ቀጣናዎች (ከደጋ እስከ ቆላ)፣ ለም መሬት፣ ሰፊ የውሃ ሀብት፣ ማምረት የሚችል ሰፊ የሰው ጉልበት፣ እንዲሁም ሀብታም የተፈጥሮ ፀጋዎችን በጉያዋ የታቀፈች በመሆኗ እነዚህን ጸጋዎች መጠቀም ላይ ትኩረት አድርጋ ማምረት ከቻለች ለውስጥ ገበያም ሆነ ለአፍሪካ ሀገራት ተደራሽ ማድረግ የምትችልበት አቅም አላት” ያሉት አቶ ሳሙኤል፤ ስምምነቱ አስተማማኝ እና የተረጋገጠ ገበያ የሚፈጥር በመሆኑ አምራች ኩባንያዎችና ነጋዴዎች የሚያመርቱትን ምርት “ምን እናድርግ”



105

የሚል ስጋት አይገጥማቸውም ሲሉ አክለዋል።

በተጨማሪም አህጉራዊው ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ለኢትዮዽያ እንደ ማንኛውም የንግድ ስምምነት የሚታይ ሳይሆን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ሽግግር ያመጣል ተብሎ የሚታሰብ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ሳሙኤል፤ ምርት በስፋት ተመርቶ ሰፊ እንዲሁም የተረጋገጠ ገበያ ከሌለ ውጤቱ አሉታዊ እንደሆነ ኬንያን በምሣሌነት ይጠቅሳሉ። እ.አ.አ በ2023 በኬንያ የወተት ምርት በስፋት ተመርቶ ገበያ ላይ ገዥ በማጣቱ በወቅቱ ከ290 ሚሊዮን ሊትር በላይ ወተት ከጥቅም ውጪ መሆኑን አስታውሰው፤ የአፍሪካ የንግድ ቀጣና ግን እንዲህ አይነቱ አሉታዊ የገበያ ሁኔታ እንዳይፈጠር ያደርጋል ሲሉ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የወጭ ንግድ መጠኗ እያደገና ከዘርፉ የምታስገባው የውጭ ምንዛሬ መጠን እየጨመረ መምጣቱ ይታወቃል። የወጭው ንግድ ቢያድግም እንደ ሀገር ከአፍሪካ ጋር ያለው የንግድ ትስስር ግን ዝቅተኛ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያ ከጠቅላላ የወጪ ንግዷ ወደ አፍሪካ የምትልከው ከ18 በመቶ አይበልጥም። አብዛኛው የውጭ ንግዷን የምታካሄደው ከአፍሪካ ውጪ ካሉ ሀገራት ጋር ነው። ሀገሪቷ ወደ አፍሪካ ከምትልካቸው ምርቶች ውስጥ አብዛኛውን በቅርባችን ላሉት ሶማሊያ፣ ጅቡቲ እና ኬንያ ወደመሳሰሉ ሀገራት ነው የምትልከው። ወደ ሀገር ውስጥ ከምታስገባው የገቢ ምርት ውስጥ ደግሞ ከአፍሪካ የምታስገባው ከ9 ነጥብ 6 በመቶ አይበልጥም ያሉት ኃላፊው፤ የኢንቨስትመንት ትስስሩም ዝቅተኛ መሆኑን በጥናት መረጋገጡን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ አብዛኛውን የወጪና የገቢ ንግዷን የምታካሄድባቸው የአውሮፓ፣ የሰሜን አሜሪካ፣ የእስያ እንዲሁም የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ለሀገራዊ ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገት ያላቸው አበርክቶ ከፍተኛ ቢሆንም ያላቸው ከፍተኛ ርቀት፣ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ካለው መጠነ ሰፊ ውድድር እና የዋጋ አለመረጋጋት አኳያ ሙሉ ለሙሉ አስተማማኝ ናቸው ብሎ መደምደም እንደማይቻል የመስኩ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ከዚህ አንጻር ስምምነቱ ይህንን ሀሳባዊ ግንብ በማፍረስ የንግድ ግንኙነቱን አቅጣጫ ይቀይረዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል። በተለይ ለኢትዮጵያ አምራቾችና ላኪዎች ሰፊና የተረጋገጠ የገበያ ዕድል እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። ይህ የሚያሳየው ስምምነቱ የሚያስገኘው ጥቅም ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ከገበያው ተገማችነት እና ገበያ ላይ የሚቀርበውን የምርት መጠን አዋጭነት ባለው መልኩ (Economies of scale) አቅዶ ከማምረት ጋር እንደሚያያዝ ነው።

በግብይቱ ሂደት በምርቶችና አገልግሎቶች ከድንገተኛ የታሪፍ ጭማሪና ከኮታ ገደብ ጋር ከተያያዙ ስጋቶች ነፃ በመሆናቸው አምራቾች፣ የግል ባለሀብቶች እና ላኪዎች ምርታማነታቸው እንዲጨምር፣ የምርታቸውን ጥራት እንዲያሻሽሉ እንዲሁም በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ብራንዳቸውን ለመገንባት እና የበለጠ እውቅና እንዲኖራቸው ያደርጋል። በሌላ መልኩ ስምምነቱ እሴት ያልታከለባቸውና ከተለመዱት መሰረታዊ ምርቶች ባሻገር እሴት የተጨመረባቸውን እንደ ቡና፣ ቆዳ፣ መድኃኒት እንዲሁም የተገጣጠሙ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን የተገልጋዮችን ፍላጎትና ምርጫ ባሟላ መልኩ አምርተው ለገበያ ማቅረብ እንዲችሉ ያግዛል።



106

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በተጨማሪም ኢትዮጵያ የንግድ ስምምነቱን በአግባቡ ከተጠቀችበት የግሉ ዘርፍ የገበያ ውድድር ውስጥ እንዲገባና የበለጠ አቅማቸውን አሳድገው እንዲሠሩ ጫና ይፈጥርባቸዋል። ይህ ደግሞ ምርታማነታቸውን እንዲጨምሩና በአፍሪካ ገበያዎች አዳዲስ ደንበኞችና የንግድ አጋሮችን እንዲያፈሩ ያስችላቸዋል። ለምሣሌ ኢትዮጵያ የምትታወቅበትን ባለልዩ ጣዕሙን የቡና ሀብቷን እሴት በመጨመር ወደ አፍሪካ ሀገራት በመላክ የአምራቾች፣ የላኪዎች እና የሀገርን ተጠቃሚነት ማሳደግ የምትችልበት ሰፊ ዕድል አላት።

በተለምዶ የኢትዮጵያ ቡና ዋነኛ መዳረሻዎች ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጀርመን፣ ቤልጂየም፣ ጃፓን፣ ቻይና እና ሳዑዲ ዓረቢያን የመሳሰሉ ሀገራት ናቸው። ይህ ስምምነት ከነዚህ የተለመዱ መዳረሻዎች ባሻገር ቡናን ወደ ናይጀሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽ፣ አልጄሪያ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ እና ማዳጋስካር ያሉ ሰፊ የኢትዮጵያ የቡና ፍላጎት ወዳለባቸው ሀገራት በመላክ የላቀ ጥቅም ለማግኘት ያስችላል። በተለይም ግብይቱ የታሪፍ ቅናሽን ያካተተ በመሆኑ የኢትዮጵያ ቡና በእነዚህ የአፍሪካ ገበያዎች ተወዳዳሪነቱ እንዲጨምር ይረዳል።

ይህ ስምምነት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ንግድ ለማሳደግ ብቻ ሳይሆን በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን የፈለጉትን ምርት በስፋት በማምረት (High Scale Production) ለገበያ ማቅረብን ለማሳደግ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ሰፊ ዕድል ይፈጥራል። በመሆኑም አምራቾች የተለያዩ ምርቶችን በህጋዊ ውድድር ሂደት አልፈው ሲያመርቱ ከኢትዮጵያ ባለፈ የሌሎች የአፍሪካ ገበያዎችን አስበው እንዲያመርቱ፣ አዳዲስ አሠራሮችን እንዲከተሉና ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችላል። የገበያውን ክፍት መሆን ተከትሎም ከሌሎች አፍሪካዊያን ነጋዴዎች ጋር አዲስ የንግድ አሠራሮችን ለመቅሰም ትልቅ አጋጣሚ የሚፈጠርላቸው መሆኑንና ሰፊ የገበያ ዕድል ሲወራ እነዚህን ሁኔታዎች የሚያካትት መሆኑን አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል።

በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የፈንድ እና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታገስ ሙሉጌታ በበኩላቸው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና በአፍሪካ ያለውን የንግድ ሥርዓትና ከባቢ ሙሉ በሙሉ እንደሚለውጠው ይገልጻሉ። በዚህም አምራቾችና በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ የተሰማሩ የግል ባለሀብቶች 120 ሚሊዮን ሕዝብ በሚያቅፈው የሀገር ውስጥ ገበያ ላይ ብቻ ትኩረት ከማድረግ ወጣ ብለው 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ሕዝብ ያለውን አህጉራዊ ገበያ አስበው እንዲያመርቱ ያስችላል።

ለምሣሌ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ አንድ የጨርቃጨር እና አልባሳት አምራች ድርጅት ከዚህ ቀደም ወደ ናይጄሪያ ወይም ኬንያ ምርቱን ሲልክ ይገጥመው ከነበረው ታሪፍ ነጻ ስለሚሆን ምርቱን ያዋጣኛል ወደሚለው የአፍሪካ ገበያ ላይ ብዙ ውጣውረድና ጫና ሳያጋጥመው መላክ የሚችል ሲሆን ይህ የውድድር አቅማቸውን አንዲያጎለብቱ፣ አዳዲስ ደንበኞችን እንዲያፈሩና ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ ያበረታታል ሲሉ የንግድ ቀጣናው ለአምራቾ ኢንዱስትሪው ይዞ የሚመጣውን ሰፊ ዕድል አብራርተዋል።

በተመሳሳይ በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ የተሰማሩ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በግብርና ምርቶች



107

ላይ እሴት በመጨመር በፋብሪካ የተቀነባበረና የታሸገ ቡና፣ ማር እንዲሁም የፍራፍሬ ውጤቶችን በማምረት ፍላጎቱ ወዳላቸው ሀገራት በብዛትና በጥራት በማቅረብ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ የሚያስችል መሆኑን አመልክተው፤ ይህም ምርት የሚልኩባቸውን ገበያዎች ለማረጋጋት፣ አንዲሁም የቡና እና ፍራፍሬ አምራች አርሶ አደሮችን ጨምሮ በግብይቱ ሂደት ውስጥ በተለያየ ደረጃ ተሳታፊ የሚሆኑ አካላትን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

አቶ ታገስ ነፃ የንግድ ቀጣናውን ስምምነት ስለፈረምን ብቻ የሚመጣ ለውጥ እንደማይኖር ገልጸው፤ ቁልፉ ነገር ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ገበያ ላይ ማቅረብ ሲቻል በመሆኑ አምራቹንና የግል ባለሀብቱ የማምረት አቅሙን እንዲያሳድግ ከአሁኑ በበለጠ ማብቃትና መደገፍ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

ከኢንቨስትመንት አኳያ

የምጣኔ ሀብት ምሁራን እንደሚያስረዱትም ሆነ ዓለም አቀፍ የንግድ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት ነፃ የንግድ ቀጣና ካሉት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች አንዱና ዋነኛው የኢንቨስትመንት ፍሰትንና የኢንቬስተሮችን የንግድ ትስስር የሚያጠናክር መሆኑ ነው። በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና የትብብር ማዕቀፍ ሰነድ ውስጥ ከተቀመጡ ቁልፍ ግቦች አንዱ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት ግንኙነትና ትስስር ማጠናከር ነው።

በዚህ አውድ መሠረት የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ከያዛቸው አንኳር ድንጋጌዎች አንዱ የኢንቨስትመንት ፕሮቶኮል ነው። ይህ ፕሮቶኮል ዘርፉን ከማሳደግ ባለፈ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት፣ ባለሀብቶች ለሚያጋጥማቸው ችግር ጥበቃና ከለላ ለመስጠት፣ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት ትስስር ለማሳደግ እንዲሁም የጋራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ታስቦ የተነደፈ ነው።

እንደ አቶ ታገስ ማብረሪያ ፕሮቶኮሉ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በተቀባይ ሀገር የሚቀርቡ ጥቅማጥቅሞች እና ማበረታቻዎች (Incentives)



108

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በህግ እና መመሪያ እንዲመራ ያደርጋል። በባለሀብቱ እና በተቀባዩ ሀገር መካከል አለመግባባት ቢፈጠር እንዴት መፈታት እንዳለበት በፕሮቶኮሉ በግልጽ ተቀምጧል። ይህ ለኢትዮጵያም ተመሳሳይ ዕድል ይፈጥራል። አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት ወደ ሌላ የአፍሪካ ሀገር ተጉዞ ኢንቨስት ቢያደርግ ሰምምነቱ የህግ ጥበቃና ተገቢውን ድጋፍ የሚሰጥ በመሆኑ ለኢንቨስትመንት መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

በሌላ በኩል አቶ ሳሙኤል እንደሚሉት የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ፕሮቶኮል የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለማሻሻልና የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን በዝርዝር መያዙ የዕቃዎች፣ የካፒታልና የሰዎችን እንቅስቃሴ የቀለለ በማድረግ አንድ የውጭ ባለሀብት ለኢንቨስትመንት የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ግብዓቶችን ከአንድ ከሀገር ያለገደብ በማንቀሳቀስ እንዲሠራና በመረጠው ዘርፍ ውስጥ መዋዕለ ነዋዩን እንዲያፈስ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

በተመሳሳይ ስምምነቱ ኢንቨስትመንትን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ ያግዛል። የዚህ መሠረታዊ ምክንያት ኢንቬስተሮች ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡበት ጊዜ ትኩረት የሚሰጡት ለኢትዮጵያ ገበያ ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ የዚህ ስምምነት አካል በመሆኗ ዕቃ አምርተን ወደ ሌሎች በርካታ የአፍሪካ አገራት መላክ እንችላለን፤ እንዲሁም ላመረትነው ምርት ሰፊ የገበያ ዕድል እናገኛለን ብለው ስለሚያስቡ ወደ ሀገር ውስጥ የሚደረገውን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) ፍሰት እንዲጨምር ምቹ መደላድል ይፈጥራል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ነጥብ ስምምነቱ ወደ ትግበራ ሲገባ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ሰፊና የተረጋገጠ ገበያ እንዳላቸው ሲረዱ አቅማቸውን ለማጠናከር፣ የሚጠቀሙበትን ቴክኖሎጂ ለማዘመን፣ ካፒታላቸውን በማሳደግ ወደ አዳዲስ ዘርፎች ገብተው ሥራቸውን ለማስፋፋት እንዲሁም የአስተዳደር (Manegment) ክህሎትን በማሳደግ ;aለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ለማጎልበት ሊያነሳሳቸው የሚችል መሆኑ ነው። ይህ ኢንቨስትመንትን፣ ምርት እና ምርታማነትን እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራን የሚያጠናክር አመቺ ሁኔታ እንደሚፈጥር አቶ ታገስ ይገልጻሉ።

ነፃ የንግድ ቀጣናውን በመጠቀም በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያለንን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የታቀዱ ቁልፍ ተግባራትን የዘረዘሩት አቶ ታገስ፤ እነርሱም የንግድ ሥራ አውድ አመቺነትን (Esae of Doing Business) ማሻሻል፣ የፋይናንስ አቅርቦትን ማሳደግ፣ ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማት (NQI) ማጠናከር እንዲሁም የመንግሥት እና የግሉን ዘርፍ የምክክር መድረክ አጠናክሮ ማስቀጠል ናቸው።

በጥቅሉ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የግብርና፣ የማኑፋክቸሪንግ፣ የኮንስትራክሽን እንዲሁም በተወሰነ መልኩ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ውስጥ ያለውን ያልተነካ እና አጓጊ ዕድል ለመቋደስ ኢትዮጵያን ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻቸው ለማድረግ ብሎም ከሌሎች ሀገራት ጋር ለሚያደርጉት የንግድ ግኑኝነት እንደ መሸጋገሪያ ድልድይ (Gateway) ለመጠቀም ትልቅ ዕድል የሚፈጥርላቸው ይሆናል።



109

ለሸማቾች የሚያመጣው ትሩፋት

የነፃ የንግድ ቀጣና አንዱና ትልቁ ጥቅም ለሸማቹ ማኀበረሰብ የተለያዩ ምርቶችና ሸቀጦችን እንዲሁም አገልግሎቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በጥራት እና በበቂ ሁኔታ ማግኘት የሚያስችል ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ነው።

ከዚህ አንጻር ነፃ የንግድ ቀጣናው በተለይ በንግድ ሰንሰለቱ ጤናማ አለመሆን፣ በምርት እጥረት፣ በጥራት ችግር፣ እንዲሁም በዋጋ መናር እየተቸገረ ያለውን ሸማች ችግር በዘላቂነት የሚያቃልል ይሆናል። ስለዚህ ኢትዮጵያ የነፃ ንግድ ስምምነቱን መፈረሟ ከሸማቾች መብት አኳያ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ የተለያዩ ምርቶችና አገልግሎቶችን በተፈለገው መጠን ለማግኘትም የሚያስችል ነው።

ከነባሩ የገበያ ሥርዓት ውጪ አዳዲስና በርካታ አቅራቢዎችና ሻጮች ገበያውን ሲቀላቀሉ ከፍተኛ ውድድር ይኖራል። ይህ ደግሞ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለሸማቹ ዕድል ይዞ የሚመጣ ነው። ከሁሉም አስቀድሞ ግን ለዚህ ምቹ የመወዳደሪያ ምህዳር መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ስምምነቱ የንግድ ውድድር ፖሊሲ ፕሮቶኮል በውስጡ እንዲያካትት ተደርጓል። ፕሮቶኮሉ በአባል ሀገራቱ መካከል በሚደረጉ የንግድ ግብይቶች የሸማቾችን መብት ለማስጠበቅ፣ የምርቶችን ጥራትና ስታንዳርድ ለማሻሻል፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁ፣ ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ምርቶች እና አሳሳች ማስታወቂያዎችን ለመከላከል እንዲሁም ፍትሃዊ ካልሆነ የንግድ ውድድር እንዲጠበቁ ያደርጋል። በጥቅሉ ፕሮቶኮሉ የሸማቾችን ደህንነት፣ ጤንነት እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ ነው።

ስለዚህ በዚህ የውድድር ሂደት ሸማቹ በጥራት፣ በአይነትና በዋጋ ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታ ይፈጠራል ይላሉ አቶ ሳሙኤል።

ስምምነቱ አባል አገራት በነፃ ገበያው ምርታቸውን ቀረጥ ሳይከፍሉ ልክ እንደ ሀገራቸው ገበያ የሌላውንም ሀገር ገበያ ስለሚጠቀሙበትና ግብይት የሚፈጽሙበት በመሆኑ የሚፈጠረው የንግድ ምህዳር ሸማቹን ማኅበረሰብ በእጅጉ ተጠቃሚ ያደርጋል።

በዚህ አውድ ውስጥ አህጉራዊው ነፃ የንግድ ቀጣና ለደንበኞች የተሻለ አማራጭ፣ የተሻለ የዕቃዎችና የአገልግሎት ጥራት፣ እንዲሁም ተወዳዳሪ ዋጋ እንዲኖር ደርጋል። ነፃ የንግድ እንቅስቃሴ ሲፈጠር ምርት አቅራቢዎችና ሻጮች ደንበኞችን ይዞ ለመዝለቅ፣ ለገበያ ለሚያቀርቡት የምርት ጥራት ቅድሚያ እንዲሰጡ እና ብቃታቸውን እንዲያሻሽሉ ተጽዕኖ ይፈጥርባቸዋል፤ ይህ ደግሞ ለሀገር ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገት አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ይሁንና እንደ ሀገር የሙከራ ንግድ ( guided trade initia- tive) ምዕራፍ ላይ እንደመሆናችን መጠን ሸማቹ የገበያው እውነተኛ ተጽዕኖ የሚሰማው ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ሲተገበር መሆኑን በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የፈንድ እና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ታገስ ሙሉጌታ አብራርተዋል።

የአፍሪካ ቀደምት አባቶች ህልም እውን እንዲሆን የፖለቲካ ቁርጠኝነት የግሉ ዘርፍ ተሳትፎና የመሰረተ ልማት ግንባታ ተቀናጅተው መቀጠል ይኖርባቸዋል። ይህ ደግሞ አፍሪካ በራሷ ሀብትና ሕዝብ የኢኮኖሚ ብልጽግናዋ የምታረጋግጥበት ጊዜ ሩቅ እንዳይሆን የሚያደርግ ነው።



110

ማኅበራዊ

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ

ያልተነገረለት ሙያ



111

ያልተነገረለት ሙያ

በፍቅርተ ባልቻ

የህክምና ልህቀት ለደረሰበት ደረጃ ትልቁን አስተዋጽኦ ያበረከተ የህክምና ሣይንስ መሰረትና ግዙፍ አገልግሎት የሚሰጥበት፤ የህክምና ዘርፍ ‘ግንድ’ እና ‘ድልድይ’ ተደርጎ የሚወሰድ፤ በዘርፉ ቁልፍ ከሚባሉ የሙያ መስኮች አንዱ ሲሆን፤ የሕሙማንን በሽታ በቤተ¬-ሙከራ (Laboratory) እና በክሊኒካል መንገዶች መለየትና ማረጋገጥ ላይ የሚሠራ የሙያ መስክ ነው - ፓቶሎጂ (Patholo- gy)።

“ፓቶሎጂ” (Pathology) የሚለው ቃል ‘ፓቶ’ በሽታዎች፣ ‘ሎጂ’ ጥናት ከሚሉት ቃላት የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “የበሽታዎች



112

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ምንነት ጥናት” ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። ፓቶሎጂ ‘ሥነ ደዌ’ በሚል ተተርጉሞ ሊገኝም ይችላል። በዘርፉ የተሰማሩ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ደግሞ ፓቶሎጂስት በመባል ይጠራሉ።

‘Pathology’ የሚለው የሙያው ስያሜ በአማርኛ ቋንቋም ‘ፓቶሎጂ’ ሆኖ እንዲቀጥል በመስኩ እየሠሩ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎችን ይሁንታ አግኝቷል። ‘ፓቶሎጂ’ን ፓቶሎጂ በሚለው ስያሜ ማስተዋወቅ ሰዎች ስለ ትርጉሙና ምንነቱ ለማወቅ በሚያደርጉት ጥረት የተሻለ መረዳት እንዲኖራቸው ያግዛል በሚል ታምኖበት የተመረጠ ስለመሆኑ መረጃዎች ያመላክታሉ። በሥራው ላይ ያሉ ባለሙያዎች ፓቶሎጂ በነበረው ከፍተኛ የባለሙያ እጥረት ምክንያት በህክምና ዘርፍ ካለው አበርክቶ በተቃራኒ ብዙም ያልታወቀና ወደፊት ያልመጣ ሙያ ሆኖ ስለመቆየቱ ይናገራሉ።

ረጅምና አድካሚ ሥልጠና በወሰዱ ሀኪሞች በስፔሻሊቲ እና ሰብ ስፔሻሊቲ ደረጃ ተደራጅቶ በበሽታ ከተያዙ የታካሚዎች የሰውነት ክፍሎች ላይ ከሚወሰዱ ልዩ ናሙናዎች (ቲሹ እና ህዋሳት) እና የታካሚውን መረጃዎች አካተው በሚደረጉ ውስብስብ ሣይንሳዊ ዘዴዎች በሽታ ልየታና ማረጋገጥ ላይ በትኩረት መስራቱ ከሌሎች የሜዲካል ላቦራቶሪ ዘርፎች የተለየ ያደርገዋል። በፓቶሎጂ ምርመራ የሚገኘው ውጤትም በፓቶሎጂስት ሀኪሙ በቂ ሥልጠና፤ የክሊኒካል እውቀትና ልምድ ላይ ተመርኩዞ የሚደረግ ነው። የሚወሰዱት ናሙናዎች በማሽኖችና በፓቶሎጂ ቴክኖሎጂስቶች እገዛ ለንባብ ተዘጋጅተው በፓቶሎጂስቱ (ዓይን ፊት በማይክሮስኮፕ ቀርበው) ይጠናሉ።

የምርመራ ውጤቶቹም በሽታው እንዲህ ነው ወይም አይደለም፤ እዚህ ደረጃ ላይ ነው አይደለም የሚለውንና የመሳሰሉትን የሚያመለክቱ እንጂ



113

እንደ አብዛኛው ላቦራቶሪ ምርመራ ውጤቶች በማሽኖች ተሠርቶ በቁጥር የሚለካ ወይም ፖዘቲቭ፣ ኔጋቲቭ በሚል የሚገለጽ ዓይነት አይደለም። ይህም የፓቶሎጂ ውጤትን በቁጥር ተመዛኝ እንዳይሆን አድርጎታል።

ከጥቅሞቹ በጥቂቱ …

የፓቶሎጂ ምርመራ ካንሰር ብቻ ሳይሆን ሌሎች በሽታዎችም የሚደረግ የህክምና ምርመራ አገልግሎት ነው። ኩላሊት እና ጉበት፣ አንጀት፣ የሳምባ ውስጥ ችግሮች፣ የጡት በሽታዎች፣ የጭንቅላት ውስጥ ካንሰሮች፣ እንቅርትና የአንገት አካባቢ በሽታዎች፣ የአጥንትና ተያያዥ ክፍሎች በሽታዎች፣ የቆዳና ተያያዥ ክፍል በሽታዎች፣ የደም እና ተያያዥ ክፍል በሽታዎች (አኒሚያ፣ ሉኪሚያ፣ ሊምፎማ፣ ወዘተ … ) የፓቶሎጂ ምርመራ ይደረግባቸዋል።

በተጨማሪም የፓቶሎጂ ምርመራዎች የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚነሱ የካንሰር ዓይነቶች፣ የአካል መከላከያ ችግሮች (Autoimmune diseas- es)፣ የማህጸን ችግሮች እና የልጅ መውለድ ጋር የተያያዙ ምርመራዎች፣ እንዲሁም የቁስል እና የአካል እብጠት ምክንያቶችን ለመለየት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

የፓቶሎጂ ምርመራ የካንሰርና ካንሰር ባልሆኑ በሺዎች በሚቆጠሩ በሽታዎች ላይ ቢደረግም ወቅቱን ተከትሎ አሳሳቢ እየሆነ በመጣው የካንሰር በሽታ ምርመራ ላይ እያደረገ ያለው እገዛ በጉልህ የሚጠቀስ ነው።

የካንሰር በሽታ እንደያዘው የተጠረጠረ ታማሚ ካንሰር ሊሆን ይችላል ተብሎ ከተጠረጠረው የሰውነቱ ክፍል ላይ ናሙና በመውሰድ የበሽታው ምንነት በፓቶሎጂ የምርመራ መንገዶች ይረጋገጣል። ካንሰር ሆኖ ከተገኘ በቀጣይነት ምን ዓይነት ካንሰር እንደሆነ፣ ያለበት ደረጃ፣ ምን ዓይነት ህክምና ሊረዳው እንደሚችል፣ ከጸባዩ አንጻር ለህክምናው ሊኖረው ስለሚችለው ግብረ መልስ ለማወቅ የሚረዱ መረጃዎች በፓቶሎጂ ምርመራ ውጤቶች ውስጥ በብዛት ተጠቃለው ይገኛሉ።

በዚህም ቀዶ ህክምናና የካንሰር ህክምና እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ተቀዳሚ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ። አሁን አሁን በተለይ የካንሰር ህክምና እየላቀ በመምጣቱ አንድ ዓይነት ካንሰር ያላቸው ሁለት ታካሚዎች በተለያዩ ህብለዘራዊና ቅንጣቶች መለያየት ምክንያት ለየግላቸው የተለካ የተለያየ ህክምና (Personalized Medicine) የሚያገኙበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ፓቶሎጂም በሽታዎችን በዘረመልና ከዛም ባነሱ ቅንጣቶች ደረጃ መርምሮ



114

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

የመለየትና የማረጋገጥ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ትልቅ እገዛ እያደረገ ነው።

የበሽታዎችን መንስኤ፣ ሂደት፣ በታካሚው ሰውነት ላይ የሚያመጣውን ለውጥና በዚህም ምክንያት ታካሚው የሚያሳያቸውን ምልክቶች በጠቅላላ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የታካሚውን በሽታ ለይቶና አረጋግጦ ለቀጣይ ህክምና የሚያመቻች በመሆኑ ፓቶሎጂን ከሌሎች የህክምና ሙያዎች ለየት ያደርገዋል።

የፓቶሎጂ ምርመራ በርካታ ጥቅሞች አሉት። ከእነዚህም ውስጥ የመጀመሪያው ትክክለኛ የበሽታ ምርመራ (Definitive diagnosis) መስጠቱ ነው። በተጨማሪም አንዱን በሽታ ከሌላው በሽታ በትክክል ለመለየት ይረዳል። የህክምና ውሳኔን ትክክለኛ እንዲሆን ማስቻሉም ሌላው ጥቅሙ ነው። በአንድ በኩል ለሀኪሞች ትክክለኛ የህክምና ዕቅድ እንዲያዘጋጁ በሌላ በኩል ታካሚዎች በሽታቸውን በግልጽ እንዲያውቁ ከማስቻሉ ባሻገር ከአላስፈላጊ ወጪ እና በውጣ ውረድ ውስጥ ከማለፍ ይታደጋቸዋል። ስለሆነም “ምርመራ ትክክል ካልሆነ ህክምና ትክክል አይሆንም” የሚለው አባባል የፓቶሎጂ ትክክለኛው መገለጫው ነው ማለት ይቻላል።

መነሻ እና ጉዞው …

ፓቶሎጂ በዓለም ላይ በፍጥነት እየተሻሻለና እያደገ ያለ ሙያ ነው።

ፓቶሎጂ የሞሎኪውላር ምርመራ (Molecular diagnostics)፣ ኢሚዩኖሂስቶኬሚስትሪ (Immu- nohistochemistry/IHC)፣ ዲጂታል ፓቶሎጂ እና ሰው ሰራሽ አስተውህሎትን በመጠቀም ወደ ትክክለኛ እና ፈጣን ምርመራ እየተጓዘ ነው።

በአገራችንም በተለያዩ የጤና ማዕከላት እና ሆስፒታሎች በፓቶሎጂ የታገዘ የህክምና አገልግሎት መስጠት ከተጀመረ ሰነባብቷል። በዚህ ረገድ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በቀደምትነቱ ይጠቀሳል።

የፓቶሎጂ ህክምናና ትምህርት ክፍል የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ሣይንስ ኢንስቲትዩት ጋር በፈጠረው የሁለትዮሽ ትብብር የተመሰረተ ነው። ሜዲካል ኮሌጁ እንደ ኮሌጅ ሥራውን ከጀመረበት ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በውስጡ የሚሰጡ የስፔሻሊቲ አገልግሎቶች በተለይም ከቀዶ ህክምና አገልግሎቶች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የፓቶሎጂ ምርመራ አገልግሎት ቁልፍ ሆኖ ተገኝቷል።

ክፍሉን በግብዓትና በሰው ኃይል በማጠናከር ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ሁለቱ ተቋማት በጋራ እንዲያስተዳድሩት ተደርጓል። ይህም በኮሌጁ ለፓቶሎጂ ህክምና ምርመራ አገልግሎትና ትምህርት



115

ክፍል ምስረታ መሰረት ጥሏል። በወቅቱ የነበሩት የሁለቱ ማዕከላት ኃላፊዎች ዶ/ር ዘሪሁን አበበ እና ዶ/ር አምሃ ከበደ (ፒኤችዲ) ለክፍሉ መመስረት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል። በ2008 ዓ.ም ክፍሉን በሰው ኃይል በማጠናከርና ለፓቶሎጂ ማስተማሪያነት የሚያገለግል ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ በኢትዮጵያ ሁለተኛው የፓቶሎጂ ስፔሻሊቲ ማሠልጠኛ ማዕከል በመሆን አገልግሎቱን ማጠናከር ተችሏል።

ከዚህ ጎን ለጎን በ2009 ዓ.ም በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ባለ አራት ወለል የፓቶሎጂና ፎረንሲክ ሜዲስን ህንጻ ግንባታ ተጠናቆ፤ የፓቶሎጂ አገልግሎት እና ትምህርት ክፍል ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በዚሁ ህንጻ ላይ በዘመናዊ መልኩ ተደራጅቶና ራሱን ችሎ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል።

አሁናዊ ሁኔታው

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የፓቶሎጂ ህክምና ምርመራ አገልግሎት እና ትምህርት ክፍል የበሽታ ልየታና ማረጋገጥ አገልግሎት (Clinical Ser- vices)፣ የህክምናና የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን ማስተማር፣ ማሠልጠንና ማብቃት እና በበሽታዎችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር ማድረግ ላይ አተኩሮ ይሠራል።

ዶ/ር መስፍን አሰፋ ሲኒየር ኮንሰልታንት ፓቶሎጂስትና የደምና ተያያዥ በሽታዎች ልየታ ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም (He- matopathologist) ናቸው። የፓቶሎጂ ህክምና ምርመራ አገልግሎት እና ትምህርት ክፍል ኃላፊም ናቸው። የትምህርት ክፍሉን ከመምራት ጎን ለጎን በደምና ተያያዥ በሽታዎች የሚጠረጠሩ ታካሚዎች ከደምና መቅኔ እንዲሁም ከተለያየ የሰውነት ክፍላቸው (ሊምፎማ ለሚባሉ በሽታዎች ምርመራ) በሚወሰዱ ናሙናዎች ላይ በልዩነት የበሽታ ልየታና ማረጋገጥ ህክምና ምርመራ



116

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

አገልግሎት ይሰጣሉ።

ከህክምና ምርመራ አገልግሎት በተጨማሪ ለህክምና ተማሪዎች መደበኛ የፓቶሎጂ ትምህርት ማስተማር፣ የፓቶሎጂ ስፔሻሊቲ ድህረ ምረቃና የሌሎች ክፍሎችን የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ማሠልጠን እንዲሁም በትምህርት ክፍሉ በጥናትና ምርምር ዘርፎች ላይ በተባባሪ ፕሮፌሰርነት እየሠሩ ይገኛሉ።

ዶ/ር መስፍን በትምህርት ክፍሉ 12 ፓቶሎጂስት ሀኪሞች ማለትም በደምና ተያያዥ በሽታዎች ሰብ ስፔሻሊስት (ሄማቶፓቶሎጂስት) ጨምሮ፣ በኩላሊትና በአንጀት በሽታዎች፣ በማህጸንና ጡት፣ በዓይንና ህጻናት በሽታዎች ፓቶሎጂ ዙሪያ ሥልጠና የወሰዱ ባለሙያዎች መኖራቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም 10 የላቦራቶሪ ባለሙያዎች (3 ማስተርስ ሂስቶ ቴክኖሎጂስቶች) እና ሌሎች አጋዥ ባለሙያዎች በጋራ አገልግሎት ይሰጣሉ።



117

መሠረታዊ የፓቶሎጂ ምርመራን የሚያሳልጡ ማሽኖች፣ የላቀ የፓቶሎጂ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የፍሮዝን ሴክሽን (Cryostat) እና ኢሚዩኖሂስቶኬሚስትሪ (Immunohisto- chemistry) ማሽኖች፤ ዲጂታል ስላይድ ስካነር ለታካሚ ውጤት ለማውጣትና ለማስተማሪያነት የሚያገለግሉ ማይክሮስኮፖች ክፍሉ ካሉት መሣሪያዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው።

የታካሚዎች አገልግሎትን በተመለከተ በስሩ ከአስር የሚልቁ የበሽታ ልየታና ማረጋገጥ አገልግሎት ዘርፎች ሲኖሩ፤ ታካሚዎች በሽታቸው በፓቶሎጂ የምርመራ ዘዴዎችና ጥበቦች ከተረጋገጠላችው በኋላ ወደ ቀጣይ የህክምና ውሳኔዎችና አገልግሎቶች ይሸጋገራሉ። በተጨማሪም በሽታን የመከላከል ምርመራ አገልግሎቶች ይሰጣሉ።

በዘርፉ በሽታዎች ከታካሚው የታመመ የሰውነት ክፍል በተለያዩ ዘዴዎች በሚወሰዱ ናሙናዎች በፓቶሎጂ ላቦራቶሪ ውስብስብና ሣይንሳዊ መንገድ የተለያዩ የህክምና መሣሪያዎችን በመጠቀም የልየታና የማረጋገጥ ሥራዎች ይሰራሉ።

በክፍሉ በተለያዩ የፓቶሎጂ ዘርፎች በዓመት በአማካኝ 15 ሺህ ታካሚዎች የፓቶሎጂ ምርመራ አገልግሎቶችን ያገኛሉ፤ በቀጣይ ዓመታት ቁጥሩ እንደሚጨምር ይጠበቃል ያሉት ኃላፊው፤ የፓቶሎጂ ስፔሻሊቲ አገልግሎቶችን በመደበኛነት የቲሹ (Conventional histopa- thology)፣ የህዋሳት (Conventional cytopa- thology) የመሳሰሉ ምርመራዎችና በልህቀት (Frozen section፤ immunohistochemis- try) የሚባሉ ምርመራዎች እንዲሁም የደምና ተያያዥ በሽታዎችን በሰብ ስፔሻሊቲ ደረጃ እየሰጠ መሆኑንና በቅርቡም የተቋረጠውን የኩላሊት ፓቶሎጂ ምርመራ እንደገና ለመጀመር ጥረቶች እየተደረጉ ስለመሆኑ አክለዋል። ክፍሉ ከ2008 ዓ.ም አንስቶ በየሦስት ዓመቱ በአምስት ዙር ከ20 በላይ ፓቶሎጂስቶችን በማሠልጠንና በማስመረቅ ለአገሪቷ የፓቶሎጂ ሙያ ዕድገት እንዲሁም ለአገልግሎቱ መስፋፋትና ተደራሽነት ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

የፓቶሎጂ ህክምና ምርመራ አገልግሎት እና ትምህርት ክፍሉ በወጣት የፓቶሎጂ ሀኪሞች መዋቀሩ፣ አዳዲስ የላቁ የፓቶሎጂ አገልግሎቶችን ማስጀመሩ፣ የኢትዮጵያን የፓቶሎጂ መስፈርት ማሟላቱ እና በፓቶሎጂ ሰብስፔሻሊቲ አገልግሎት ዘርፍ ቀዳሚና ብቸኛ መሆኑ ከሌሎች የፓቶሎጂ የምርመራ ማዕከላት የተለየ ያደርገዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ፓቶሎጂን ለማስፋፋት ባለሙያዎችን አሠልጥኖ ወደ ሥራ በማስገባትና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ከማስፋፋት አንጻር እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ ቢሆንም የሚስተዋሉ ውስንነቶች አሉ። እነዚህ ችግሮች ሙያው እና አገልግሎቱን ለማስፋት ማነቆ ሆነውበታል፡፡

ዶ/ር መስፍን በሥራቸው ላይ የማሽኖች እጥረት፣ የአላቂ ዕቃ እና የሪኤጀንት ግዢ ችግሮች፣ የጥራት ሥርዓት አለመጠናከር እና የተሻለ ቴክኖሎጂ አቅርቦት ላይ ውስንነቶች መኖራቸውን ገልጸዋል። የመሣሪያዎች ብልሽት፣ የጥራት መጠበቂያ ሥርዓት እጥረት፣ የሪኤጀንት አቅርቦት መቋረጥ፣ የባለሙያ እጥረት እና የባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ



118

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ድጋፍ ደካማ መሆን የዘርፉ ፈታኝ ማነቆዎች እንደሆኑም ጠቅሰዋል።

ዘመኑን የዋጁ አዳዲስ ማሽኖችን ማቅረብ፣ የማሽኖች የጥገና ስምምነቶች እና ዕቅዶችን ማጠናከር፣ ሥልጠናዎችን በስፋት መስጠት፣ የሪኤጀንት አቅርቦት ሥርዓትን ማሻሻል፣ የጥራት ማረጋጋገጫ እና የቁጥጥር ሥርዓትን ማጠናከር፣ ከሌሎች ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግ ለችግሮቹ እንደመፍትሔ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ሊሆኑ እንደሚገባም አመላክተዋል። በዚህ ረገድ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ከወዲሁ እልባት እንዲያገኙ መሥራት ይጠይቃል ነው ያሉት።

ዕቅድ እና መዳረሻው

ፓቶሎጂ በአይነት እየጨመሩ ካሉት የማይተላለፉ በሽታዎች (በተለይም ከካንሰር) አንጻር በሚቀጥሉት ዓመታት በአገልግሎት ተፈላጊነት ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዝ ይታሰባል። ሙያው እነዚህን በሽታዎች በመከላከልም ይሁን መርምሮ ለህክምና በማመቻቸት ረገድ ትልቅ ተግባር እያከናወነ ይገኛል። በመሆኑም መንግሥት እና የህክምና ተቋማት መጪውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ከወዲሁ መሥራት ይጠበቅባቸዋል። ይህም የሚመጣውን ጫና ለመቋቋም ይረዳል።

ሀኪሞች ስለ ዘርፉ ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ ታካሚዎቻቸውን በተሻለ መልኩ ለማገልገል የሚችሉበትን ሁኔታ ከወዲሁ ማየት ይጠበቅባቸዋል። በትምህርት ክፍሉ እየተከሰቱ ስላሉ በሽታዎች በርካታ መረጃዎች ያሉ በመሆኑ የኅብረተሰብ ጥናት ባለሙያዎች ቢጠቀሙበት መልካም እንደሆነ ዶ/ር መስፍን ይመክራሉ።

“እንደ ፓቶሎጂ ያሉ ቁልፍ የህክምና ሙያዎችን በማስተዋወቅ፣ ስለ በሽታዎች መንስኤዎች፣ ሂደቶች፣ የሰውነት ላይ ለውጦች እና ምልክቶች እንዲሁም የህክምና አማራጮች መረጃዎችን ከባለሙያዎች የሚያገኙበት መንገድ በመፍጠር የኅብረተሰቡ የጤና ንቃት እና ግንዛቤ እንዲጎለብት ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል” ሲሉም አሳስበዋል።

ኮሌጁ በመደበኛነት የህክምና ተማሪዎችን፣ የድህረ ምረቃ የፓቶሎጂ ስፔሻሊቲ ተማሪዎችን እና የሌሎች ስፔሻሊቲ ዘርፎች ድህረ ምረቃ ተማሪዎችን ያስተምራል። በቀጣይም ፍኖተ ካርታ ቀርጾ በኩላሊት፣ በደም እና ተያያዥ በሽታዎች እንዲሁም በአንጀት ፓቶሎጂ በሰብ ስፔሻሊቲ ደረጃ ትምህርት ለመጀመር እንቅስቃሴ ላይ ነው።

በደም እና ተያያዥ በሽታዎች ዙሪያ ለሚጠረጠሩ ታካሚዎች ከደምና መቅኔ እንዲሁም ከተለያየ የሰውነት ክፍላቸው (ሊምፎማ ለሚባሉ በሽታዎች ምርመራ) በሚወሰዱ ናሙናዎች ላይ በልዩነት የበሽታ ልየታና ማረጋገጥ ህክምና ምርመራ አገልግሎት በኮሌጁ ይሰጣል። ይህ ምርመራ በፓቶሎጂ በሰብ ስፔሻሊቲ ደረጃ ተዋቅሮ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ብቻ የሚሰጥ አገልግሎት ሲሆን በቀጣይነትና በቀዳሚነት በዘርፉ ሰብ ስፔሻሊቲ ፕሮግራም ለመጀመር ዕቅድ መኖሩን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ኮሌጁ ያሉትን የላቁ የፓቶሎጂ ምርመራ ግብዓቶች ለማሳደግ (ወረቀት አልባ - ዲጂታል ማድረግ)፣ ቴሌ ፓቶሎጂ (የርቀት የፓቶሎጂ ምርመራዎች



119

ማማከር) አገልግሎትን ለማጠናከር አቅዶ እየሠራ ነው። የብቃትና የጥራት ደረጃዎችን ለመተግበር፣ የሰብ ስፔሻሊቲ ሥልጠናዎችን ለመጀመር፣ የበሽታዎችን ምርመራ በዲጂታል ፓቶሎጂ እና ሰው ሰራሽ አስተውህሎት የታገዘ ለማድረግ እየተሠሩ ያሉ ጥናቶችን በማጠናከር በትኩረት እየሠራ ይገኛል።

ሜዲካል ኮሌጁ ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር የሥራና የጥናት አጋሮች ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚንቀሳቀስ አሳውቋል። የአገልግሎት እና የትምህርት ክፍሉን በአገሪቷ ወደ ቀዳሚ የፓቶሎጂ ምርመራ ማዕከልነት (National Pathology Refer- ence Center) ለማሸጋገር ዕቅድ ይዞ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።



120

ኢኮኖሚ

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በዲጂታል 2030 -



121

ወደ ላቀ ብልጽግና

በሰለሞን ተሰራ

የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማኅበራዊ ዕድገት፣ ምርታማነትን ለማሻሻል እና ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ ሚና እንዳለው እሙን ነው። ዓለማችን በሰው ልጅ ምጡቅ ዕውቀት ታግዛ ቀጣዩንና አስደናቂውን የቴክኖሎጂ ክህሎት እውን ለማድረግ በዋዜማው ላይ ትገኛለች። ይህ ለውጥ በተለያየ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሀገራት ምቹ አጋጣሚ እንደሚፈጥር ታምኖበት በስፋት እየተሠራበት የሚገኝ ሲሆን በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ቀደም ብላ የጀመረችውና በስፋት እየተተገበረ የሚገኘው ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በዋናነት ከሀገራዊ ርዕይ እና ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ብሔራዊ የልማት አጀንዳዎች ጋር



122

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

የጠበቀ ቁርኝት አለው።

ዲጂታል ኢትዮጵያ ፈጠራና ፍጥነትን ያዘለ፣ ዓለም ከደረሰችበት ደረጃ ለመድረስ መሰላል በመሆን የሚያገለግል፣ የአገር ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽና የብልጽግና ግብ መዳረሻ ዋነኛ መንገድ ነው፡ ፡ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 መተግበር ሲጀምር ቀዳሚ እሳቤው የዲጃታል መሰረት በመጣል ለቀጣይ መዳረሻ መደላድል መፍጠር ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ይፋ በተደረገበት ሰነድ መግቢያ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት “ስትራቴጂው የመጀመሪያ ርምጃ እና የድርጊት ጥሪ ነው፣ ድርጊት ሕይወት ይዘራል፤ ዜጎች የሚገባቸውን የብልጽግና ሕይወት በማሳካት ሂደት ትርጉም ያለው ውጤትም ይሰጣል። ይህ ስትራቴጂ የመጀመሪያው ርምጃ እና በመሠረታዊነት ወደ ድርጊት የሚያመራ ጥሪ ነው። ለኢትዮጵያ የብልጽግና ተስፋ መሳካት ቃል የገቡት ሁሉ በመተጋገዝ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ እንዲያበረክቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ። አብረን እንደምናሳካውም ሙሉ እምነት አለኝ” ነበር ያሉት።

እናም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ይፋ በተደረገበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቃላቸው ሰምሮ፣ ተስፋቸው እውን ሆኖ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በሙሉ ስኬት ተጠናቆ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ መሸጋገሩን አብስረዋል፡፡ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ደግሞ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሠረት በማድረግ መዘጋጀቱንና



123

ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና አስተማማኝ የዲጂታል ምህዳር መፍጠር ላይ ትኩረት ማድረጉን አስታውቀዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተደራሽነትን ማስፋት፤ እኩል ዕድል ማመቻቸትና በተቋማትና በሕዝብ መካከል መተማመንን መፍጠር የሚሉ ሦስት ቁልፍ ትልሞችን ይዟል።

እነዚህን ትልሞች ለማሳካት ደግሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሪክና የቴሌኮም ትስስር ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ ማድረግ፣ ለሕዝብ መገልገያ ዲጂታል መሰረተ ልማት መስፋፋት ልዩ ትኩረት መስጠት፣ በጠንካራ የሳይበር ደህንነት መታገዝ፣ የሳይበር ደህንነት ሥራውም የዲጂታል ሥርዓት፣ የዲጂታል መረጃንና ትውልዱን መጠበቅ እንዳለበት ማስገንዘባቸው ይታወሳል። የትውልዱ የዲጂታል አጠቃቀም ከኢትዮጵያ ባህል፣ እሴትና ሉዓላዊነት ጋር መናበብ እንዳለበትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስገንዝበዋል።

በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ እየተገነቡ ያሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ትኩረት የዜጎችን ደኅንነትና ብሔራዊ ሉዓላዊነት መጠበቅ እንዲሁም በዲጂታል ሥርዓት ውስጥ ማንም ወደኋላ እንደማይቀር ማረጋገጥን ታሳቢ ያደረጉ ናቸው። በዋናነት በሰው ኃይል ግንባታ ላይ መዋዕለ ንዋይን ማውጣት፣ ከተሞችንና ገጠራማ አካባቢዎችን ወደተሻለ ደረጃ ማሳደግ፣ ዲጂታል አስተሳሰብና የፈጠራ ባህልን በማጎልበት ኢትዮጵያን ወደ ሁሉን አቀፍ ዕድገትና ብልጽግና ማሸጋገርን ያካትታል። “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ብሔራዊ ስትራቴጂ፣ ልማትና ሉዓላዊነትን በማጎልበት የኢትዮጵያን የልማት ጎዳና በራስ አቅም ለመቅረጽ ቁርጠኝነት የተያዘበት ነው።

“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂ፣ በዓላማ፣ በቁርጠኝነትና በችሎታ ላይ የተመሠረተ ብሔራዊ ምላሽ መስጠት ላይ ያተኮረ ሲሆን ስትራቴጂው ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2030 ታላቅ ልማትን ለማስመዝገብ ያላትን ከፍተኛ ምኞት የሚያሳይ፣ በኢኮኖሚ፣ በመንግሥታዊ አስተዳደርና በማኅበራዊ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት ያለመ ነው።

ይህ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትልም እና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስኬት ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በዲጂታላይዜሽን እና በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፎች ላስመዘገበችው ዕድገትና ከፍተኛ አፈጻጸም ከወዲሁ ከሀገር የተሻገረ ምስክርነትን ያስገኘ ሆኗል። የአፍሪካ ኅብረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) አድርጎ ሾሟል። ሹመቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘርፉ ላሳዩት አመራር እና ኢትዮጵያ በአህጉሩ የሰው ሰራሽ አስተውሎትና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች ለምትገኘው የላቀ ሚና እውቅና የሰጠ፤ ኃላፊነቱም ኢትዮጵያ በዘርፉ በአፍሪካ የያዘችውን መሪነት በጉልህ ያሳየ ነው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ተመስገን ጥሩነህ የዲጂታል ኢትዮጵያ ማብቂያና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ጅማሮ ማብሰሪያ መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት በዲጂታል 2025 ትግበራ የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት ጊዜና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል፤ በዚህም አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል፡፡



124

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በተደረገው ጥረት ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሊያደርጋት የሚችለውን የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በማስጀመር ተቋማትን ከአላስፈላጊ አስተዳደራዊና የቁጥጥር ወጪ ማዳን መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ አሁን በማዕከሉ 23 የፌዴራል ተቋማት 180 አገልግሎቶችን በአንድ መስኮት እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዲጂታል 2025 የዲጂታል ሽግግር ውጥኖችን ለማገዝ የሚያስችሉና ልዩ ትኩረት የሚሹ የፋይናንስ፣ የሰው ሃብት ልማትና አስቻይ ፖሊሲዎች ተለይተው ሲሠራባቸው መቆየቱንና አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስረዱት፡፡

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የአገሪቷን የፋይናስ አሠራር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የሕዝብ ትስስርን፣ የንግድ ሥርዓቱን፣ የመንግሥት ተደራሽነትን፣ የፀጥታና ደህንነት አጠባበቅን እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃን አውድን በማሻሻል የአገሪቷን ሁለንተናዊ ጉዞ ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሮታል፡፡

የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ በዲጂታል ዘርፍ የተያዙ ውጥኖቸ በፍጥነት የሚስፋፉበት፣ ተናባቢ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር የሚገነባበት፣ ዘላቂ የዲጂታል እመርታ የሚመጣበት፣ በሥርዓት የተደገፈ አገራዊ ሽግግር የሚረጋገጥበት፣ ዜጎችን ማዕከል ያደረገ መንግሥታዊ ሥርዓት በእጅጉ የሚጎለብትበት፣ ሁሉን አቀፍ አካታች የዲጂታል አገልግሎቶች የሚቀርቡበት ሉዓላዊና ደህንነታቸው የተጠበቀ የዲጂታል ሥርዓቶች የሚበራከቱበትና የውስጥ ፈጠራ የሚበረታታበት መሆኑንንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አረጋግጠዋል፡፡

ስትራቴጂው በአጠቃላይ የአገሪቷን ኢኮኖሚና ትራንስፎርሜሽን በማሳለጥ ወደምንመኘው ሁለንተናዊ ብልጽግና የምንሸጋገርበት አውድ ሲሆን ይህንን የሚያሳልጥ ብሔራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት መቋቋሙንና ምክር ቤቱ ባለፈው አንድ ዓመት ባከናወናቸው ተግባራት አለአግባብ ሊወጣ የነበረን ከ68 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር ማዳን መቻሉንም አስታውቀዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ “በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” በተገኙ ስኬቶች ላይ ተመስርቶ አዳዲስ የዲጂታል ዕድገቶች ላይ ማተኮሩንና ስትራቴጂው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ፣ ስማርት ከተሞችን፣ ድንበር ተሻጋሪ ኢ-ኮሜርስ፣ ዲጂታል ሉዓላዊነትን የመሳሰሉ ጽንሰ ሃሳቦችን በማካተት መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስና ሮቦቲክ የልህቀት ማዕከል ኃላፊ ዶክተር ዐቢይ መሀመድ ሁሴን ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ዲጂታል መሰረተ ልማቶችን፣ የዲጂታል ተደራሽነትንና የግንኙነት አድማሱን ፈጣን ማድረጉንና የሞባይል ተጠቃሚዎችን ቁጥርና የ4G (አራተኛው ትውልድ) አገልግሎትን በእጅጉ ማሳደጉን በአዎንታዊ ጎኑ አንስተዋል፡፡

በስትራቴጂው በመታገዝ የዲጂታል አገልግሎቶች መስፋፋታቸው፣ ለኅብረተሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶች ፈጣን በሆነ ሁኔታ ተደራሽ መደረጋቸው፣ የፋይዳ መታወቂያ በስፋት መዳረሱ፣



125

ዲጂታል ኢኮኖሚን በመገንባት አዳዲስ ሥራ ፈጣሪዎችን ወደፊት ማምጣትና ተጠቃሚ ማድረግ ላይ እንደሚያተኩር፣ ከተማውንና የገጠሩን ክፍል በስፋት የሚያገናኝ አካታችና ደህንነቱ የተጠበቀ መሰረተ ልማት ማስፋፋት ላይ ማተኮሩን ዶክተር ዐቢይ ጠቅሰዋል፡፡

ስትራቴጂው የሰውና የማሽን ትብብርን በማጎልበት በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና፣ በፋይናንስ፣ በቱሪዝም፣ በከተማ ልማት፣ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ዘርፍ ዘመኑን የዋጀ ለውጥ ለማምጣት የሚሠራበት ነው፡፡ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለሚፈጠሩ የ”ራ ዕድሎች፣ አካታች እና ፍትሃዊ ልማትን እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ፣ የዲጂታል እውቀትን በማስፋፋት እና የተቋም አቅምን በመገንባት የግለሰቦችን እንዲሁም የተቋማትን የመፈጸም የዲጂታል ክህሎትና አካታችነትን ማሳደግ መቻሉን፣ የአምስት ሚሊዮን ኮደርሶች ሥልጠና ዲጂታል ክፍተቱን ለመሙላት በእጅጉ ማገዙን፣ አካታች የፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋቱን፣ የዲጂታል ሽግግሩ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱን፣ መደበኛው ኢኮኖሚ እንዲነቃቃና ከዘርፉ የሚገኘው ገቢ እንዲያድግ ማስቻሉን እንዲሁም የግሉን ዘርፍ ተወዳዳሪነት ማሳደጉን ሳፋሪኮምን በመጥቀስ አነጻጽረውታል፡፡

የዲጂታል መሰረተ ልማትን ለማሳደግ ግዙፍ የዳታ ማዕከላትና፣ የአይሲቲ ፓርክ መገንባቱ የሳይበር ደህንነትን ማጠናከር መቻሉንና በዲጂታል 2025 አገሪቷን ወደፊት ሊያሻግሩ የሚችሉ መደላድሎች በመፍጠር የታቀዱ ግቦችን ሙሉ በሙሉ ማሳካት መቻሉን አስረድተዋል፡

ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የኢትዮጵያን ሽግግር የሚያፋጥኑ የዲጂታል መሰረተ ልማቶችንና ሀገር በቀል የዲጂታል ዕውቀትን የሚጠቀም፣ ፈጠራን የሚያጎለብት፣ የሰዎችን ሕይወት የሚያሻሻል ቴክኖሎጂን እውን የሚያደርግ ነው፡፡ አካታች



126

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

አቅም ማጎልበት ላይም ትኩረቱን አድርጓል።

አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ዕድገትን ማፋጠን፣ ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ተደራሽነትን ማሳደግ እና ኢትዮጵያን ለዲጂታል የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ተመራጭ መዳረሻ ማድረግ ከስትራቴጂው ዓላማዎች መካከል ይካተታሉ። አገራዊ ዳታዎችንና ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አዝማሚያዎች እና አገራዊ የልማት ፍላጎቶችን መሰረት ያደረጉ መረጃዎችን በማሰባሰብና በመተንተን የዲጂታል ልማት ምሰሶዎችንና የትኩረት አቅጣጫዎችንም የለየ ነው።

የዲጂታል ለውጡ በኢትዮጵያ ማንነትና እሴቶች የተደገፈ ሲሆን፤ ለሁሉም ዜጎች አካታች፣ ፍትሃዊ እና ትርጉም ያለው እንዲሁም ኢትዮጵያ የራሷን የዲጂታል ልማት ጎዳና ስትቀይስ፤ ጥንካሬ ያላት፣ ሉዓላዊት እና ለወደፊት ዕድሎች ዝግጁ የሆነች ዲጂታል ኢትዮጵያ ለመገንባት ያለመ ነው።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ስታርት አፖችን የኢኮኖሚው ዋነኛ ሞተር በማድረግ የፈጠራ ሥራዎች ወደ ስኬታማ ቢዝነስ እንዲለወጡና ወጣቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል ሲሆን ዜጋ ተኮርና ሁሉን አቀፍ የዲጂታል አሠራር እንዲሰፍን እንዲሁም የፈጠራ ሥራዎች እንዲበረታቱ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው።

የስታርት አፖችን አቅም ይበልጥ በማሳደግ ለአዳዲስ እና በቴክኖሎጂ ላይ ለተመሠረቱ የፈጠራ ሥራዎች ስኬታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ በማድረግ በዘርፉ ከአንድ ሚሊየን በላይ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ታሳቢ አድርጓል፡፡ ስትራቴጂው በፈጠራ የታጀበ ፈጣን የዲጂታል ሽግግር ለማድረግ የሚያስችል ሲሆን ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተገኙ ተሞክሮዎችን መነሻ በማድረግ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ወጣቶች



127

የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ወደ ተግባራዊ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲለውጡና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን እንዲያሳድጉ ትልቅ ተስፋ ሰንቋል።

ስትራቴጂው ወጣቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲያገኙ መንገድ ከመክፈቱም ባለፈ፤ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ መሠረት በቴክኖሎጂ የሚደገፉ የፈጠራ ሥራዎች ወደ ንግድ ተለውጠው ለኢኮኖሚው ዕድገት የላቀ ድርሻ እንዲያበረክቱ የሚያስችል እንዲሁም በኮምፒውተር እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ግልጽነትን በማስፈን፣ ብክነትን፣ ድካም እና ጊዜን በመቆጠብ የምጣኔ ሀብት ዕድገትን ያፋጥናል፤ የዜጎችንም ሕይወት ቀላል ያደርጋል፡፡

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ኢትዮጵያን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ወደፊት ለማስፈንጠርና የሕዝቦቿን ሕይወት ቀላል፣ ቀልጣፋ እና ከብክነት የሚጠብቅ ለማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን በዚህም በሀገሪቷ ምጣኔ ሀብት ትልቅ ድርሻ ያላቸውን ግብርና፣ ማኑፋክቼሪንግ፣ ቱሪዝም እና የመረጃ ቴክኖሎጂን ያቀፈ ነው፡፡

ዲጂታል ሥርዓት መዘርጋት ብቻውን ግብ አይደለም፡፡ ነገር ግን ያንን በመጠቀም ሥራን የሚያሳልጥ በቴክኖሎጂ ክህሎቱን እና ዕውቀቱን ያዳበረ ዜጋ መገንባት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ ስትራቴጂው ስኬታማ እንዲሆን ኢትዮጵያ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ጋር በመተባበር ለአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከክፍያ ነፃ ዓለም አቀፍ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሥልጠና መርኃ ግብር በመዘርጋት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት እና ዕውቀት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው፡፡ በመርኃ ግብሩ በመታገዝ የዲጂታል ምህዳሩን ሰው ተኮር ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት ዘርፉን ሊመሩ የሚችሉ ከሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ሠልጣኞችን በማቀፍ ከነዚህ ውስጥ አንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ወጣቶች ሥልጠናቸውን አጠናቀው ሰርትፊኬት መውሰዳቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

የዲጂታል ሥነ-ምኅዳሩ ለመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ የሚያግዙ መደላድሎች (ፕላትፎርም) እና አስቻይ ሥርዓት ለመፍጠር በማስቻሉ በሀገሪቷ እስከ አሁን ከ900 በላይ የመንግሥት ተቋማት አገልግሎቶቻቸውን ኦንላይን ማድረጋቸው የዜጎችን ሕይወት አቅልሏል። ከዚህ በፊት ጊዜ፣ ገንዘብ እና ጉልበት ያባክን የነበረው አገልግሎት አሰጣጥ ዲጂታላይዝ መደረጉ የአገሪቷን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወደፊት አስፈንጥሮታል። በዚህ ረገድ በርካታ ተቋማት አሠራራቸውን ዲጂታላይዝ በማድረግ የለውጡን ጉዞ የተቀላቀሉ ሲሆን በተፈጠረው ምቹ ምህዳር በመታገዝ ሁለንተናዊ የኦኮኖሚ ዕድገትና ሽግግር ማምጣት ተችሏል፡፡

ኢትዮ-ቴሌኮም

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ሲሆን ለአብነትም የሞባይል ደንበኞችን ቁጥር 97 ሚሊዮን፣ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን 57 ሚሊዮን እንዲሁም 1 ሺህ 030 ከተሞች የ4ጂ ኔትወርክ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞችን ቁጥር 128 ሚሊዮን፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋን ወደ 100 ከተሞች ለማድረስ ግብ ተቀምጧል። በ2030 የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ



128

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከሰባት እጥፍ በላይ እንዲያድግ በልዩ ትኩረት እንደሚሠራበት አቅጣጫ መቀመጡን የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።

ኢትዮ-ቴሌኮም ደንበኞቹ በዲጂታል አማራጭ የመረጃና የመዝናኛ ይዘት ያላቸው ቪዲዮችን መመልከት የሚያስችላቸው የቴሌስትሪም / TeleStream/ አገልግሎት በቅርቡ አስተዋውቋል። ቴሌስትሪም ከማዝናናት ባሻገር በትምህርት፣ በጤናና በተለያዩ ዘርፎች ይዘት ማዘጋጀትና ለሚሊዮኖች ተደራሽ ማድረግ ያስችላል። ቴሌስትሪም “ብሔራዊ የዲጂታል ይዘት መድረክ” በመሆኑ ሀሳብ ያላቸው አካላት ይዘት በመፍጠር የሚያስተላልፉበት መድረክ ነው።

በኢትዮጵያ 98 በመቶ መረጃ የሚተላለፈው በሳተላይት መሆኑን ተከትሎ ቴሌስትሪም የሚያድግና የሚሰፋ የቴሌኮም አገልግሎት ሲሆን፤ ምስሎችንና ቪዲዮዎችን በ4k፣ 8k እና በHD ጥራት ማሳየት ያስችላል። መተግበሪያው ሁሉንም ዜጎች ከዲጂታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርግ እንዲሁም ቴሌስትሪም ክፍያዎችን በቤት ውስጥ ሆኖ በቴሌ ብር ማከናወን የሚያስችል ነው። መተግበሪያው ኢትዮጵያ ለሳተላይት ክፍያ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ ከማዳን ባለፈ ያልተቆራረጠ አገልግሎት ለመስጠት እና የቴሌስትሪም ምርቶችን በዘመን ገበያ በማዘዝ በኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ማዕከላት ለማግኘት የሚያስችል ነው።

የቴሌብር ግብይት

የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 59 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን አገልግሎቱ ከተጀመረ አንስቶ በዲጂታል የክፍያ መንገድ ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ልውውጥ በማድረግ በኢኮኖሚው ውስጥ 18 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ብር በኤሌክትሮኒክ ማንቀሳቀስ ተችሏል፡፡ በዚህም በሀገሪቷ ታሪክ ከጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ይልቅ የዲጂታል ገንዘብ ዝውውሩ በልጦ ተገኝቷል፡፡ ይህ በሀገራችን የገንዘብ ዝውውርን ዲጂታላይዝ ከማድረግ ባሻገር የፋይናንስ አገልግሎቶችን በእጅጉ አካታችና ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ አስችሏል፡፡ በተጨማሪም አገልግሎቱን ከ30



129

ባንኮች ጋር የማስተሳሰር ሥራ ተጠናቆ ከባንክ ወደ ቴሌብር ከቴሌብር ወደ ባንክ በቀላሉ ገንዘብ ማዘዋወር ተችሏል፡፡

በ2030 ስትራቴጂ የሞባይል ኢኮኖሚ ከባቢን በመጠቀም አንድ ነጥብ 2 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ዕቅድ ተቀምጧል፡ ፡ ኢትዮ ቴሌኮም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን የያዙ መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት 98 በመቶ የሚሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን ኦንላይን የማድረግ ውጥን አስቀምጦ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

የዘመን ገበያ አፈጻጸም

የሀገራችንን የግብይት ሥርዓት በማዘመን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ዘመን ገበያ የተሰኘ የዲጂታል ግብይት ፐላትፎርም (ኢ-ኮሜርስ) በሥራ ላይ በማዋል በከፍተኛ ደረጃ የዘመን ገበያ ተጠቃሚዎችን እና የዲጂታል ግብይት ልምምድን በእጅጉ ማነቃቃት ተችሏል፡፡ ዘመን ገበያ በተለይም አብዛኛው ማኅበረሰብ የሚጠቀምባቸውን የፍጆታ እቃዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በተሳለጠ መንገድ ለማኅበረሰቡ ማድረስ እንደሚቻል እንዲሁም



130

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

አምራቾች ምርቶቻቸውን በተሻለ አማራጭ ማቅረብ እንደሚችሉ አመላካች ሆኗል።

ፋይዳ መታወቂያ

በኢትዮጵያ የተጀመረውን የዲጂታል ሽግግር እውን ለማድረግ ከተያዙት ግቦች ቀዳሚው የሆነው የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ተደራሽነት አራት መርሆች ያሉት ሲሆን አነዚህም አካታችነት፣ አስተማማኝነት፣ የተመጠነ መረጃ የሚወስድ እና ተናባቢ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የነበረው ተገማችና ከዘመናዊ አሠራር ወደኋላ የቀረ የማንነት ማረጋገጫ (መታወቂያ) አሰጣጥ እንደ ሀገር ካለው ሕዝብ 40 በመቶው ራሱን የሚገልጽበት ምንም አይነት መረጃ ወይም ማስረጃ /መታወቂያ/ እንዳይኖረው ማድረጉን የተቋሙ ሥራ አስፈጻሚ ዮዳሄ ዓርአያሥላሴ አስታውቀዋል፡፡

አገሪቷ ሁሉም ዜጎች ማንነታቸውን የሚገልጽ መለያ እንዲኖራቸው የዘረጋችው ዲጂታል አሠራር አሁን ላይ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች የሚታይ ውጤት አስገኝቷል፡፡ ይህንኑ ውጤት ወደተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ማስረጃ የሌላቸው የጐዳና ተዳዳሪዎች፣ በተለያዩ ማዕከላት የሚኖሩ አቅመ ደካሞች፣ ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ሕፃናት ፋይዳ መታወቂያ ያላቸውን ሰዎች ምስክር በማድረግ ወይም ባሉበት ተቋም ሆነው መታወቂያውን የሚያገኙበት ሥርዓት ተፈጥሯል፡፡

በኢትዮጵያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የበለፀገ፣ ዘርፍ ተሻጋሪ፣ መሠረታዊ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን ተከትሎ በተዘረጋው አሠራር አሁን ላይ 38 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ማድረግ የተቻለ ሲሆን እስከ ሰኔ 2018 ድረስ 70 ሚሊዮን ዜጎችን የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ባዮሜትሪክ እና ዲሞግራፊክ መረጃን ከነዋሪዎች በመሰብሰብ አንድን ሰው ልዩ በሆነ ሁኔታ መለየት የሚያስችል፣ ለሁሉም አገልግሎት ሰጪዎች ማንነትን በማረጋገጥ እና በኤሌክትሮኒክ መልኩ ደንበኞቻቸውን ማወቅ የሚያስችል ተዓማኒነት ያለው የዲጂታል ማንነት ምዝገባ ሥርዓት ነው።

የፋይዳ መታወቂያ ሥርዓት ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ መሳካት አንዱ ምስሶ ነው፡፡ መርኃ ግብሩ ሀገራዊ ልማትን በአግባቡ ለማቀድ፣ ምጣኔ ሃብታዊ ሽግግር ለመፍጠር፣ መልካም አስተዳደር ለማስፈን፣ የሀብት ብክነትን ለመቀነስ፣ ወንጀልን ለመከላከል፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ እና የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን ለማስቀረት እና አካታችነትን ለማጎልበት ይረዳል፡፡

የፋይዳ ሥርዓት ዲጂታል አሠራሮችን እውን የሚያደርግና የእያንዳንዱን ግለሰብ ማስረጃ በዘመናዊ መንገድ የሚሰንድ በመሆኑ ከገቢዎች፣ ከመሬት ካርታ፣ ፕላንና ከገንዘብ ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩ ማጭበርበሮችን ያስቀራል፡፡ አገልግሎቱ የግለሰቦችን ማንነት ከተቋማት ጋር በዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚያስተሳስር በመሆኑ ሰዎች የግል ስልካቸውን በመጠቀም የሚፈልጉትን አገልግሎት ባሉበት ቦታ ሆነው ለማግኘት ያስችላቸዋል፡፡

የግላዊ መረጃዎች ጥበቃ

ማንኛውም ተመዝጋቢ ፈቃዱን በግልጽ ሳይሰጥ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የተመዘገቡ የግል መረጃዎችን መውሰድ፣ ማሰራጨት፣ ማተም፣ መጠቀም፣ መረጃውን መስጠት ወይም ቅጂውን ለሦስተኛ ወገን ወይም አካላት መስጠት ወይም ይፋ



131

ማድረግ የተከለከለ ነው። የግል መረጃ እንዲሰጥ የሚፈቀደው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲመጣ ብቻ ነው። ስለሆነም የግለሰብ መረጃ ለሦስተኛ ወገን (ለግለሰብም ሆነ ለመንግሥት) ያለ ግለሰቡ ፈቃድ አይተላለፍም። በዚህ ሁኔታ በተገቢው ሁኔታ የተላለፈው መረጃ የሚያገለግለው ወይም ጥቅም ላይ የሚውለው ለተፈለገው አገልግሎት ብቻ ነው።

አገልግሎትን ከፋይዳ ጋር ማስተሳሰር

ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተጀመረው ጥረት አገልግሎታቸውን ከፋይዳ ጋር መታወቂያ ጋር ያስተሳሰሩ ተቋማት ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። ከእነዚህም መካከል ኢትዮ- ቴሌኮም ይጠቀሳል። ሌሎች ከ30 በላይ የሚሆኑ ተቋማትም አገልግሎታቸውን ከፋይዳ ጋር አስተሳስረዋል። በዚህም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ለማውጣት የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ቅድመ ሁኔታ ሆኗል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአዲስ አበባ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት ፋይዳ የዲጂታል



132

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

መታወቂያ በግዴታ እንዲቀርብ ያደረገ ሲሆን በመላ አገሪቷ የሚገኙ ደንበኞች የትኛውንም የባንክ አገልግሎት ለማግኘት የፋይዳ መታወቂያ እንዲይዙ ይጠየቃል።

በተጨማሪም በርካታ የፋይናንስ እና ቴሌኮም ተቋማት አገልግሎቶች፣ የተለያዩ የመንግሥት አገልግሎቶች፣ ሰነድ ማስመዝገብ እና ማረጋገጥ፣ የትራንስፖርትና መጓጓዣ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶች በፋይዳ መታወቂያ አማካኝነት እንዲሰጡ እየተደረገ ነው።

ገቢዎች

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የገቢ አሰባሰብን ለማዘመንና ውጤታማ ለማድረግ፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን በመተግበር አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል። ይህ ዲጂታል አሰራር ቀደም ሲል ቀናት ይወስድ የነበረውን የግብር ክፍያ ወደ ደቂቃዎች በመቀነስ፣ ግብር በወቅቱ ለመክፈልና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍ አስችሏል። በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታክስ ህግ ተገዥነትን በማረጋገጥና የገቢ አቅምን በማሳደግ ረገድም ገንቢ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የግብር አሰባሰብ ዲጂታይዜሽን፦ ግብር ከፋዮች ክፍያቸውን በዲጂታል መተግበሪያዎች (ኦንላይን) እንዲፈጽሙ በማድረግ፣ አገልግሎት አሰጣጡን ፈጣን እና ምቹ ማድረግ አስችሏል።

የውጤታማነት መጨመር፦ የዲጂታል አሠራሩ የገቢ አሰባሰብ አቅምን ማሳደግ ያስቻለ ሲሆን፣ ከገንዘብ ልውውጦች ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማከናወን ረድቷል።

የታክስ ህግ ተገዥነት፦ የታክስ ህግ ተገዥነትን ለማረጋገጥና በዲጂታል ሥርዓት ታክስን በወቅቱ ለማሳወቅና ለመሰብሰብ አስችሏል፣ በዚህም የገቢ አሰባሰቡ በአገሪቷ ታሪክ ታይቶ ወደማይታወቅ የላቀ ደረጃ ተሸጋግሯል።

በአጠቃላይ ዲጂታል ኢትዮጵያና የገቢዎች ሚኒስቴር የጋራ ሥራ የግብር አከፋፈልን ዘመናዊና



133

ግልጽ በማድረግ የሀገርን ገቢ ለማሳደግ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው። በዲጂታል 2030 ስማርት ከስተም አሠራሮችን በመዘርጋትና የዲጂታል ሥራዎችን በማቀላጠፍ የገቢ አሰባሰቡን ከ1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን በላይ ለማድረስ ዕቅድ ተይዟል ፡፡

የሳይበር ደህንነት

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነትን በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ቁልፍ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ በማከናወን ለኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት፣ ለፋይዳ መታወቂያና ለኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ የሚያገለግሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ መሰረተ ልማቶቸን ተደራሽ ማድረግ መቻሉ ከተገኙ ስኬቶች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ ለአገሪቷ ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጠውን የክላውድ አገልግሎት ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉ በዘርፉ የተገኘውን እመርታ የሚያመላክት ነው፡፡

የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል በተሠራ ሥራ ዲጂታል ፎረንሲክ ላብራቶሪ በማስመረቅ ወደ ሥራ ማስገባት የተቻለ ሲሆን ቁልፍ የሆኑ ተቋማትን መሰረተ ልማቶች 24/7 በመጠበቅ አስተማማኝ ደህንነትን ማረጋገጥ ተቸሏል፡፡

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በሳይበር ደህንነት አይበገሬ የሆነ ቁልፍ መሰረተ ልማት መገንባት፣ የመንግሥት መሰረተ ልማቶችን ተደራሽ ላልሆኑ አገልግሎቶች ተደራሽ ማድረግ፣ የዲጂታል ደህንነትን የሚያረጋግጥ የዲጂታል ፊርማ ወይም (ሲግኔቸር) ሥርዓት መዘርጋት ላይ በትኩረት ይሠራል፡፡ ዲጂታል ትስስሩ እየሰፋ ሲሄድ የገንዘብ ዝውውርና ግላዊ መረጃዎችን ለመጠበቅ የሚያስችል አስተማማኝ የአደጋ ምላሽ መስጫ ማዕከል ይዘጋጃል፡፡

አዲሱ ስትራቴጂ የግሉ ዘርፍ በሳይበር ደህንነት ሥራ ላይ በስፋት እንዲሳተፍ ዕድል የሚሰጥ መሆኑ ሂደቱን የተለየ ያደርገዋል፡፡ ስትራቴጂው ዜጎች ያለ ስጋት በፍጹም ደህንነት አገልግሎት የሚያገኙበት የዲጂታል መተማመኛ የሚፈጠርበትና የዲጂታል ሉዓላዊነት የሚረጋገጥበት ነው።

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ

በዲጂታል 2030 የተቀመጠው የቴክኖለጂ መዳረሻ ግብ ሰፊ በመሆኑ አሻጋሪ ቴክኖሎጂ መጠቀም ግድ ይላል። ዲጂታል ኢኮኖሚውን ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግሪት ቴክኖሎጂዎቹ የመንግሥትን አሠራር ዘመናዊ እያደረጉት ይገኛሉ፡፡ ቴክኖሎጂዎቹ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያሳልጡና ወደፊት የሚያስፈነጥሩ፣ ብሔራዊ ለዓላዊነትን የሚያረጋግጡ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ዕድገት እውን የሚያደርጉ ናቸው፡፡ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስና የሮቦቲክ ቴክኖሎጂን በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ፣ በአምራች ዘርፍ በመጠቀም አገሪቷን የሚያሻግሩ ስኬቶችን ለማስመዝገብ ያስችላል፡፡

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥራ ቁልፉ ተግባር ዳታን መቆጣጠር ሲሆን ዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ዘመናዊና በራስ አቅም የሚተገበር የዳታ አስተዳደር ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ ዳታዎችን በሥነ ምግባርና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መጠቀም፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዝግጁነትን ማሳደግ፣ ተአማኒነት ያለው ፖሊሲ ማስረፅ በዳታ ጥበቃና አጠቃቀም የሕዝብ አመኔታን ማግኘት ያስፈልጋል፡፡



134

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

የመንግሥት ኤሌክትሮኒክስ ሥራ አመራርና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎቶች የዜጎችን እርካታ ከፍ ያደረጉ ቢሆኑም ቀሪ ሥራዎች በመኖራቸው በዲጂታል 2030 በመታገዝ ዜጎች በቤታቸው ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትና ከወረቀት የፀዱ የመንግሥት አገልግሎቶችን መቶ በመቶ በመስጠት የሙስና ተጋላጭነትን በእጅጉ ለመቀነስ ታቅዷል፡፡

ስታርት አፕ

በሥራ ፈጠራና በተሸጋገሩ ስታርት አፖች በአገሪቷ የሚከናወኑ የፈጠራ ሥራዎች ነባራዊ አሴቶችን ያልለቀቁ፣ አካታችና በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሆኑ ይፈለጋል፡፡ የዲጂታል ክህሎት ልማት እየተለወጠ ባለው የሥራ ምህዳር ተወዳዳሪ የሆኑ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት፣ የዲጂታል ሽግግር ለማድረግ፣ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማጎልበት የወጣቶችን እምቅ አቅም ለመጠቀም ያስችላል፡፡

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ 70 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የዲጂታል ክህሎት እንዲኖረው ማስቻል፣ ከ80 በመቶ በላይ የሆነውን የመንግሥት ሠራተኛ የዲጂታል ክህሎት ማላበስ፣ 10 ሚሊዮን የሚጠጋውን ዜጋ እንደ ኮደርስ ባሉ የሥልጠና መርሃ ግብሮች በመታገዝ የዲጂታል ዕውቀት ባለቤት ማድረግና በርካታ ወጣቶችን በዲጂታል ክህሎት ከሁለተኛ ዲግሪ በላይ በማስተማር ብቁ ማድረግን አልሟል፡፡ በዚህ ሁሉ ጥረት በመታገዝ ከአንድ ሚሊዮን የላቀ የዲጂታል ሥራ በመፍጠር ከዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት የሚገኘውን ገቢ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማድረስ ዕቅድ ተይዟል፡፡

ንግድ

በዕድገት ጎዳና ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዲጂታል ንግድ ሥነ-ምህዳር እ.አ.አ በ2024 የኢ-ኮሜርስ ገቢ 465 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን፤ እ.አ.አ በ2030 ደግሞ 845 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ያመላክታል። ነገር ግን የተበታተነ የሎጂስቲክስ አሠራር፣ የተገደበ የዲጂታል ክፍያ እና የቁጥጥር ክፍተቶችን ማስተካከል ስኬቱን የበለጠ ለማሳደግ ያግዛል። ድንበር ተሻጋሪ መስተጋብርን ለማሳደግ፣ እንከን የለሽ ግብይቶችን ለማንቃት እና ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የንግድ ልውውጦችን ለማሳለጥ አጠቃላይ የዲጂታል ንግድ ስትራቴጂን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል። ዲጂታል ንግድን ማሳደግ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ብዝሃነት፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራን ያበረታታል። የሀገር ውስጥ እና ዓለምአቀፍ ገበያዎችን መክፈት ደግሞ ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማትን ያጠናክራል፣ ለገጠሩ ማኅበረሰብ ሰፊ ገቢ በማስገኘት ሁሉን አቀፍ ዕድገትን ያበረታታል። ስትራቴጂው በዲጂታል የንግድ አሠራር በመታገዝ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አተገባበርን አሁን ካለበት ደረጃ በማሳደግ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ምርቶች ወደ ውጭ ለመላክ ያስችላል።

ሎጂስቲክስ

የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፍ በከፍተኛ የለውጥ ጉዞ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን መንግሥት የሎጂስቲክስ መሠረተ ልማቶችን ለማዘመን እና የንግድ ኮሪደሮችን ለማሳደግ የ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ስትራቴጂክ ዕቅድ ይፋ አድርጓል። ይሁን እንጂ የሎጂስቲክስ ወጪዎች ከፍተኛ መሆናቸውን ተከትሎ የአፍሪካ አገራት የእርስ በእርስ የንግድ



135

ልውውጥ አሁን 9 ነጥብ 1 በመቶ ብቻ ነው። ይህንን ክፍተት ለመሙላት በዲጂታል የንግድ ሥርዓት በመታገዝ ቀልጣፋ የንግድ አሠራር፣ የንግድ ልውውጦችን መዳረሻ መከታተልእና ድንበር ተሻጋሪ ውህደትን እውን ማድረግ ለነገ የማይባል ሥራ ነው። የኢትዮጵያን የአቅርቦት ሰንሰለት ዲጂታላይዝ ማድረግ በራሱ የኢትዮጵያን የንግድ ተወዳዳሪነት ከማሳደግ ባሻገር የተቀናጀ የንግድ ማዕከል የመሆን ፍላጎቷን በቀጥታ ያሳድጋል። የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ስልታዊ በሆነ መንገድ መጠቀም የንግድ ቅልጥፍናን ያሳድጋል፣ ብክነትን ይቀንሳል፣ ግልጽነትን ይጨምራል፣ የገበያ ተደራሽነትን ያጠናክራል። በ2030 ዲጂታል ስትራቴጂ በመታገዝ እውን የሚደረጉት አሠራሮች የወጪ ንግድ አፈጻጸሙን በእጅጉ ለማሳደግ ያስችላሉ።

ትምህርት

ዲጂታል ቴክኖሎጂን በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ማካተት ተደራሽነትን፣ ጥራት እና ፍትሃዊነትን ለማሳደግ የማይተካ ሚና አለው። ኢትዮጵያ የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በጀመረችው ጥረት ውስጥ በተለይ በገጠር እና በቂ መሰረተ ልማት በሌላቸው አካባቢዎች ከፍተኛ ተግዳሮት ገጥሟታል። በእነዚህ አካባቢዎች ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ማድረግ ባለመቻሉ የትምህርት ተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት ለመስጠት አልቻሉም። እንደ ሀገር ዲጂታል ቴክኖሎጂን በማስፋፋት በዘርፉ ክህሎት የተላበሰ ትውልድ ለማፍራት መንግሥት በቁርጠኝነት እየሠራበት ይገኛል።

በዲጂታል ትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ይህም ዲጂታል ክህሎት የጨበጠ ትውልድ በማፍራት ዘላቂ እና ፍትሃዊ ልማት በማረጋገጥ የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ ዕድገት በቀጥታ መደገፍ ይቻላል። በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት የዲጂታል



136

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ክህሎትን በማሳደግ ዓለም እየሄደችበት ያለውን የዲጂታል እመርታ በአግባቡ በመተግበር ራሱንና አገሩን የሚጠቅም ትውልድ ለማፍራት ያግዛል። የኢትዮጵያን የ2030 ብሔራዊ ዲጂታል ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ የትምህርት ዘርፉ የማይተካ ሚና ያለው በመሆኑ የመንግሥትና የግል አጋርነትን ማጠናከር ለነገ የማይባል ዛሬ ላይ ሊጀመር የሚገባው ወሳኝ ሥራ ነው፡፡

ግብርና

ግብርና አሁንም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆኖ የቀጠለ ሲሆን ከአገሪቷ ሕዝብ ከ65 በመቶ በላይ የሚሆነውን እንዲሁም ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት አንድ ሶስተኛውን አስተዋፅኦ ያደርጋል። ምንም እንኳን ግብርናውን ለማዘመን ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ዘርፉ አሁንም በዝቅተኛ ምርታማነት፣ በቴክኖሎጂ ውህደት ውስንነት እና በአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮት እየተፈተነ ነው፡፡ አገሪቷ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የምታገኝባቸው እንደ ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና የእንስሳት ሀብት ያሉ ቁልፍ የእሴት ሰንሰለቶች በቀደሙ አሠራሮች የታሰሩ፣ በደካማ የገበያ ትስስርና በአነስተኛ የዲጂታል መሣሪያዎች አጠቃቀም የተገደቡ ናቸው። የግብርና ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ወደታገዘ አዲስ አሠራር ማሳደግ የገጠሩን ማኅበረሰብ ኑሮ ለማሻሻል፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና አርሶ አደሮችን ከዓለም አቀፍ ገበያዎች ጋር በማዋሃድ የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ ብልጽግና ማረጋገጥ ያስችላል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ በራሱ ምርትና ምርታማነትን ያሻሽላል፣ የእሴት ሰንሰለት ግልጽነትን ያሳድጋል፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ስብጥርም ያጠናክራል።

ማኑፋክቸሪንግ

ማኑፋክቸሪንግ ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት ሰባት በመቶ የሚጠጋ አስተዋፅኦ ያለው ሲሆን በአልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣ በቆዳና በቆዳ ውጤቶች፣ በግብርና ማቀነባበሪያ እና በግንባታ እቃዎች ምርት ዘርፍ በርካታ የሥራ ዕድል የመፍጠር እምቅ አቅም አለው። ኢትዮጵያ በዲጂታል ሽግግር አሠራሯ



137

በመታገዝ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ አፍስሳለች፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ በወጪ ንግድ ምርት ላይ የተሰማሩ የውጭ እና የአገር ወስጥ ባለሃብቶችን ትኩረት በስፋት መሳብ ችለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዋናነት በኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሰማሩ ቅድሚያ የምትሰጣቸው ባለሃብቶች ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱ ሲሆኑ፤ ባለሃብቶቹ በዕድሉ በመጠቀም ዘርፉን እያነቃቁት ይገኛሉ። ይሁን እንጂ ዘርፉ አሁንም ዝቅተኛ ምርታማነት፣ የቴክኖሎጂ ውስንነት እና ደካማ የአቅርቦት ሰንሰለት የሚታይበት ነው።

የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ኢትዮጵያ በዘርፉ በመታገዝ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ፣ ዘላቂ እና ፈጠራ ያለው የማምረቻ ማዕከል ለመሆን የያዘችውን ውጥን በቀጥታ ይደግፋል። ስትራቴጂው የዘርፉን ምርታማነትና የምርት ጥራትን ለማሳደግ እና ብክነትን ለመቀነስ ብሎም የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነት ለማጠናከር የማይተካ ሚና እንዳለው እሙን ነው።

ጤና

የኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት ያልተመጣጠነ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የሠለጠነ የሰው ኃይል እጥረት እና የዲጂታል ጤና መሣሪያዎች ውህደት ውስንነት አለበት። በኢትዮጵያ 16 ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መሰረታዊ የጤና አጠባበቅ አገልግሎት እንደሚያስፈልጋቸው በጥናት ቢረጋገጥም አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ከሚያስፈልገው ገንዘብ ወስጥ እስከአሁን የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ 30 በመቶ መሆኑ አፈጻጸሙን ፈታኝ አድርጎታል። ሀገሪቷ አሁንም ከኮሌራ ተጋላጭነት፣ የወባ እና የኩፍኝ ወረርሽኝን ጨምሮ ከበርካታ የሕዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ጋር እየታገለች ትገኛለች። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እነዚህን ተግዳሮቶችና ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ ምርምሮችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን አሁን ላይ በAI የሚመሩ የስኳር እና የካንሰር በሽታ መመርመሪያ መሣሪያዎችን አዘጋጅቷል። ነገር ግን ዘርፉ አሁንም በመረጃ አቅርቦት፣ በሰው አቅም እና በመሠረተ ልማት አቅርቦት ዙሪያ ያሉበት ተግዳሮቶች የለውጥን አስፈላጊነትን ያጎላሉ። ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ዲጂታል የጤና መፍትሄዎችን ለማቅረብ እንዲሁም ፍትሃዊ እና ተደራሽ የጤና አጠባበቅ ሥርዓትን እንደሚያረጋግጥ ታምኖበታል። ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች የጤና አጠባበቅ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የታካሚዎችን የእንክብካቤ ጥራት ለማሳደግና የአገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን ያስችላሉ።

ማዕድን

የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ከነበረበት አስቸጋሪ ሁኔታ በመውጣት ለውጥ እያሳየ የመጣ ሲሆን በተለይም ዘርፉ በስትራቴጂካዊ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትና በወርቅ ምርት መጨመር ተደግፎ ተጨባጭ እመርታ አስመዝግቧል። በዚህም እ.አ.አ በ2024/2025 የበጀት ዓመት ከወርቅ ሽያጭ 3 ነጥብ 46 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል። ዕድገቶች ቢኖሩም አሁንም የተገደበ የጂኦሎጂካል መረጃ እና ጊዜ ያለፈባቸው የማዕድን ማምረቻ ዘዴዎችን መጠቀም የዘርፉ ተግዳሮቶች ሆነው ቀጥለዋል። የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ



138

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በዲጂታል መንገድ መለወጥ ዘላቂ፣ ሁሉን አቀፍ እንዲሁም አካታች የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ ያግዛል። በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር የማዕድን ፍለጋ መረጃዎችንና ክምችቶችን ትክክለኛ አሃዝ ለማወቅ አይነተኛ መፍትሄ ነው፡ ፡ ዲጂታል አሠራሮች የአካባቢ ተፅእኖዎችን በመቀነስና የሰዎችን ደህንነት በመጠበቅ ከማዕድን ሀብት የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማይተካ ሚና አላቸው።

የከተማ ልማት

ከለውጡ በኋላ የኢትዮጵያ ከተሞች ገጽታና የከተሜነት እሳቤ በፍጥነት እየተቀየረ መጥቷል።

እ.አ.አ በ2025 የከተሜነት ምጣኔ 24 ነጥብ 2 በመቶ ሲደርስ ዓመታዊ የዕድገት መጠኑ ደግሞ 4 ነጥብ 77 በመቶ ሆኗል። በአገሪቷ የሚታየው የከተሞች መስፋፋት በበኩሉ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ፣ የአየር ብክለት ስጋትና እና የሕዝብ አገልግሎቶች ተደራሽነትን እየፈተነ መጥቷል። ተግዳሮቶቹ እንዳሉ ሆነው የከተሞች በፍጥነት መስፋፋትን ተከትሎ በተለያዩ ከተሞች የሚሠሩ የኮሪደር ልማቶች የትራንስፖርት መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፋት፣ አረንጓዴ ቦታዎችን እና የሕዝብ መገልገያዎችን በማሻሻል ከተሞችን ዘመናዊ ገጽታ ለማላበስ ከፍተኛ ዕድል ፈጥረዋል። በከተሞች የሚታየው የትራፊክ አስተዳደር፣ የደረቅ ቆሻሻ



139

አሰባሰብ፣ የሕዝብ ደህንነት እና የኃይል አጠቀቃቀም በዲጂታል የታገዘ መፍትሄ የሚፈልግ መሆኑን ተከትሎ በዲጂታል 2025 የተገኙ ውጤቶችን በመቀመርና በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በመታገዝ ከተሞችን ዘመናዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሊያደርጋቸው የሚቸል ወጥነት ያለው አሠራር ተግባራዊ ማድረግ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው። በዲጂታል አሠራር የታገዘ የስማርት ከተሞች ግንባታ ዘላቂ የከተማ ልማት፣ የተሻሻለ አኗኗር እና ቀልጣፋ የሀብት አስተዳደርን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና አለው። ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች የተሻሉ ከተሞችን ለመገንባት፣ የሕዝቦችን እንቅስቃሴና ደህንነት ለማሳለጥ፣ የኃይል አቅርቦትን ለመቆጠብና የአካባቢ ዘላቂነትን ለማረጋገጥም እንዲሁ ወሳኝ ናቸው፡፡

ቱሪዝም

ኢትዮጵያ በብዝኃነት የተሟሸች፣ በኅብረ ብሔራዊነት የደመቀች በታሪክ እና በተፈጥሮ ሀብቶች የተዋበች ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ ያሏት የበለፀጉ እና የተለያዩ ባህል፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ መስህቦች እንዲሁም የዱር አራዊት ሃብቶቿ የተለያየ ፍላጎት ያላቸውን የውጭና የሀገር ውስጥ አገር ጎብኚዎች ለመሳብ ልዩ ዕድል ፈጥረውላታል። ሀገሪቷ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ 18 የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶች ባለቤት መሆኗ ደግሞ ለቱሪስቶች ልዩና ተመራጭ መዳረሻ አደርጎታል። እነዚህ ሀብቶች የኢትዮጵያን ጥልቅ ታሪካዊ ጠቀሜታ እና የተለያዩ ባህላዊ ቅርሶች የሚያንፀባርቁ ናቸው። እ.አ.አ በ2024 ኢትዮጵያን የጎበኙ የውጭ አገር ቱሪስቶች ምጣኔ የ40 በመቶ ዕድገት ያስመዝገበ ሲሆን ይህም በዘርፉ ትልቅ እመርታ ካመጡ ጥቂት የዓለም አገራት አንዷ እንድትሆን አስችሏታል። ይህ ዕድገት ሀገሪቷ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን የሚያስችላት እምቅ አቅም እንዳላት ያረጋገጠ ነው። ስኬቶቹ እንዳሉ ሆነው አሁንም የቱሪዝም ዘርፉ የተገደበ የዲጂታል መሠረተ ልማት፣ የተበታተነ የጉብኝት ፕሮግራም ማረጋገጫ (fragmented booking systems) እና በበቂ ሁኔታ የዲጂታል መተግበሪያዎችን ያለመጠቀም ጉድለት ይታይበታል። እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ኢትዮጵያ በዘረጋቻቸው ዲጂታል ስትራቴጂዎች በመታገዝ የተራቀቁ



140

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ከዘርፉ ጋር ለማዋሃድ እየሠራች ትገኛለች።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ ያላትን ቦታ ለማሳደግ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የተደገፈ ጠንካራ የቱሪዝም ስትራቴጂ አውጥታ እየተንቀሳቀሰች ነው። ቱሪዝምን እና ቅርሶችን በዲጂታል መንገድ ማሳደግ በራሱ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገት እና የባህል ጥበቃን ለማረጋገጥ ያስችላል። ዘመናዊ ዲጂታል መደላድሎችና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ መዳረሻነት ለማሳደግ፣ የጎብኝዎችን ቆይታ ለማርዘም እና ዘርፈብዙ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን ለመፍጠር ያስችላሉ። የቱሪዝም ዘርፉ በአገሪቷ ከተመረጡ የዲጂታል ሽግግር አጀንዳዎች ውስጥ መካተቱ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶቿን ለመጠበቅና ለማስተዋወቅ እንዲሁም የተለያዩ አገራት ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን ለመሳብ ትልቅ አቅም ይሆናል፡፡

መውጫ

ብሔራዊ የለውጥ አጀንዳ የሆነው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030፤ በኢትዮጵያዊ ማንነትና እሴቶች ላይ የተመሰረተ፣ ከአህጉራዊ ማዕቀፎችና ከዓለም አቀፍ ምርጥ ልምዶች ጋር የተጣጣመ እንዲሁም ሁሉን ያካተተ፣ ጠንካራ እና ተወዳዳሪ የዲጂታል ኢኮኖሚ መሰረት ለመጣል በማሰብ እውን የተደረገ የነገ የብልጽግና መዳረሻ ነው። መንግሥት ዜጎችን እንዴት ማገልገል እንዳለበት፣ ንግዶች እንዴት እንደሚያድጉ እና ሰዎች በኢኮኖሚው ውስጥ እንዴት መሳተፍ እንዳለባቸው ግልጽ መዳረሻዎችን አስቀምጧል።

ኢትዮጵያ ለስኬቷ ስንቅ የሚሆኑ እርሾዎችን ቀደም ብላ ያዘጋጀች ሲሆን እነዚህም ለዲጂታል ቴክኖሎጂ ጉጉ የሆነ ወጣት ኃይል፣ በፈጠራ ክህሎት እየተካነ የመጣ አዲስ ትውልድ፣ በከፍተኛ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ የሚገኝ የመንግሥት የዲጂታል መሠረተ ልማት ግንባታ፣ ለለውጥና ለቴክኖሎጂ ቅበላ ዝግጁ የሆነ መንግሥት እና ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ክልላዊ እና ዓለም አቀፋዊ ውህደት ናቸው።

የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ዕድሎችን ወደ ዘላቂ፣ ሁሉን አቀፍ እና ማንንም ወደኋላ የማያስቀር ዕድገት ለመቀየር የሚያስፈልጉትን መሰረቶች፣ ግቡን የሚያሳኩ ባለድርሻዎች እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ዘርፎች ለይቶ ያስቀመጠ ነው። ነገሮችን በጥርጣሬ በማየትና ድፍረት በማጣት ከተግባራዊ እንቅስቃሴ መገደብ የሚያስከፍለው ዋጋ ከፍተኛ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም። በዚህ ረገድ ዲጂታል 2030ን በኅብረትና በሙሉ ፍላጎት ተግባራዊ ካደረግነው አገራችንን ካደጉት አገራት ተርታ የምናሰልፍበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ ይህንን ማድረግ ካልቻልን ግን በኢትዮጵያ እኩልነትን ማረጋገጥ፣ ተወዳዳሪነትና ማሳደግና የሥነ ሕዝብ አወቃቀር ጥረትን እውን ማድረግ አዳጋች ይሆናል። በተቀናጀ ጥረት፣ በቁርጠኝነትና በእኔነት ስሜት መሥራት ከቻልን ደግሞ በስትራቴጂው በመታገዝ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ማስፋፋት፣ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደርን ማሻሻል እንዲሁም ዓለም አቀፍ የዲጂታል አካታችነትን ማረጋገጥ ይቻላል።

ይህንን ምኞት ዕውን ለማድረግ ደግሞ ፖሊሲዎችን ከማውጣት ባለፈ ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ ይጠይቃል። ለአብነትም ዲጂታል 2030 ስትራቴጂን መሰረት ባደረገ የዳሽቦርድ



141

እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ካውንስል ባሉ ስልቶች ጠንካራ አስተዳደር፣ ግልጽ ክትትል እና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ይገባል። በተጨማሪም ሉዓላዊነትን፣ ደህንነትን እና ዘላቂነትን በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እምብርት ላይ በማካተት ማንም ወደኋላ እንዳይቀር ለማድረግ በተለይ በሴቶች፣ በወጣቶች፣ በስታርትአፖች እና በገጠር ማኅበረሰቦች ላይ ቀጣይነት ያለው ኢንቨስትመንት ማውጣት ያስፈልጋል።

ዲጂታል 2030ን እውን ማድረግ የመንግሥት፣ የግሉ ዘርፍ እና የኅብረተሰቡን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፤ ተጠያቂነትን፣ ትብብርን እና ቀጣይነት ያለው ፈጠራን ይፈልጋል። ለግቡ መሳካት ዋናው ሃብት አዲሱ ትውልድ በመሆኑ ትውልዱን በአግባቡ መያዝና መጠቀም ከተቻለ ሀገሪቷን ወደ አዲስ የብልጽግና፣ የፍትሃዊነት እና የጽናት ዘመን ማሻገር ይቻላል። ኢትዮጵያን የዲጂታል ኃይል ማስታጠቅ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ለአፍሪካ የዲጂታል ጉዞና የወደፊት ዕጣ ፈንታ መለኪያ ማድረግ ደግሞ የስትራቴጂው ግብ ነው። እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው አሁን ነው፤ የሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍና አካታች ዲጂታል ሀገር በመገንባት ረገድ ዓርአያ እንድትሆን ዕድል እንደሚፈጥርላት አያጠራጥርም።

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የአገሪቷን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወደፊት የሚያስፈነጥር መሠረት የተጣለ መሆኑ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ብልጽግናን በመላው ኢትዮጵያ ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። በዲጂታል 2030 ዲጂታል ኢኮኖሚውን በጥልቀት ማስፋፋት ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡ ስትራቴጂው ሰዎች እና ተቋማትን ማብቃት፣ ሁሉን አቀፍ ዲጂታል ተደራሽነትን ማረጋገጥ፣ አካታች የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገትን ማፋጠን እና ኢትዮጵያን ዋና የኢንቨስትመንት መዳረሻ ማድረግ ላይ አተኩሯል።

የዲጂታል ሽግግሩን ተግባራዊ ለማድረግ ሕጎች፣ መረጃ፣ ክህሎት እና ታማኝነት ወሳኝ ሲሆኑ ግብርናን፣ ጤናን፣ ትምህርትን፣ ኢንዱስትሪን ጨምሮ ከተሞችና ክልሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ደግሞ ቀዳሚው ግብ ነው። በሀገር አቀፍ ደረጃ የኃይል እና የኢንተርኔት ተደራሽነትን ማረጋገጥ፣ የተሻሻለ የሕዝብ አገልግሎት መዘርጋት፣ ዳታ ላይ የተመሠረቱ ውሳኔዎችን መስጠት፣ ለሳይበር መከላከል በቂ ዝግጁነትን ማሳካትና የኢትዮጵያን የዲጂታል መሪነት ማጎናፀፍ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተጠባቂ ውጤቶች ናቸው፡፡

ለዚህ ደግሞ ከፋይናንስ ጋር በተያያዘ የተሻሻለው የኢንቨስትመንት አዋጅ፣ የአዕምሯዊ ንብረትን እንደ ካፒታል እውቅና በመስጠት የዳያስፖራው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲያድግ የሚያደርግ መደላድል ተፈጥሯል፡፡ የቴሌኮምና የባንክ ዘርፍ ፈቃድ በውድድር ለመስጠት ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት በማድረግ የፋይናንስ ዘርፉን እንቀሰቃሴ ከተለመደው አካሄድ ማውጣትና በፋይናንስ ዘርፍ የካፒታል ገበያን በኢትዮጵያ ማስተዋወቅ ተችሏል። ይህም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል መደላድል መፍጠሩ የተያዙ ግቦችን ለማሳካት ወሳኝ እርምጃ ነው፡፡

ዲጂታል ኢትዮጵያ በመንግሥት ጥረት ብቻ ሳይሆን በሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል እና በአጋር አካላት ትብብር የሚተገበር በመሆኑ ለስኬቱ ሁሉም ዜጋ በግንባር ቀደምትነት መሰለፍ ይጠበቅበታል።



142

ማኅበራዊ

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

(በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ)



143

ድንበር ያልገደበው ማዕከል

ወቅቱ የስጋ ደዌ በሽታ በኢትዮጵያ ተስፋፍቶ የነበረበትና በማኅበረሰቡም ዘንድ ስለ በሽታው ትክክለኛ ግንዛቤ ያልተፈጠረበት ነበር - 1926 ዓ.ም፤ ይሁንና ይህንን ሁኔታ የሚቀይር አንድ ክስተት ተፈጠረ፤ የሥጋ ደዌ ህሙማንን ሕይወት ብቻ ሳይሆን በሽታውን አስመልክቶ የጤና ባለሙያዎችን አቅም በሥልጠና ማጎልበትን ታሳቢ ያደረገ ለኢትዮጵያም ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የዚያን ጊዜው የልዕልት ዘነበወርቅ መታሰቢያ ሆስፒታል ተቋቋመ።



144

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ሆስፒታሉ ሥራውን ለሥጋ ደዌ በሽታ አስቸኳይ ምላሽ በመስጠት ቢጀምርም በኋላ ግን በዘርፉ የሠለጠነ የጤና ባለሙያ ያለመኖር የበሽታውን ሥርጭት ከባድ ሊያደርገው እንደሚችል ግንዛቤ በመወሰዱ በ1958 ዓ.ም ‘የመላው አፍሪካ ሥጋ ደዌና ቲቢ ህክምና የማገገሚያ እና ሥልጠና ማዕከል (All Africa Lepro- sy, Tuberculosis and Rehabilitation Training Centre - ALERT) እንዲመሠረት ምክንያት ሆነ። ያ ማዕከል የዛሬው አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተብሎ የሚጠራው አንጋፋ ተቋም ነው።

የአለርት ሚና ከሀገር ውስጥ አልፎ ወደ ውጭ አገራት ተስፋፍቶ፤



145

በዚህ ሥራውም በአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት) እንዲሁም በዓለም ጤና ድርጅት የመላው አፍሪካ የሥልጠና ማዕከል ተደርጎ ዕውቅና ተሰጠው። በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችል የሥልጠና ማዕከል እና የሥልጠና መመሪያ (Manual) ተዘጋጅቶም ወደ ሥራ ተገባ፡፡

በዚህ ሁኔታ የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ማዕከልነት ተልዕኮ ተቀብሎ ሲሠራ የቆየው አለርት፤ አሁን በሥጋ ደዌ፣ ደርማቶሎጂ፣ ቲቢ እና ሌሎች ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን የሚያካትቱ በርካታ የሥልጠና አይነቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል።

የሥልጠና ማዕከሉ በተለያዩ ደረጃዎች ከሚሰጣቸው ሥልጠናዎች መካከል መሠረታዊ፣



146

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

የአሠልጣኞች ሥልጠና እንዲሁም በአድቫንስድ ደረጃ የሚሰጣቸው ይጠቀሳሉ። ከሦስት ቀናት እስከ 3 ሣምንት ለሚደርስ ጊዜ የሚሰጡት እነዚህ ሥልጠናዎች በፀደቀ የሥልጠና መመሪያና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ የሚቀርቡ ሲሆኑ ጥራትና ተገቢነትን የሚያረጋግጡ፤ የጤና ባለሙያውን ዕውቀትና ክህሎትም የሚያሻሽሉ ናቸው።

በሥልጠና ማዕከሉ ከተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች በየዓመቱ ከአምስት ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች ይሠለጥናሉ። እነዚህ ሠልጣኞች ወደ አካባቢያቸው ተመልሰው የተሻለ አገልግሎት በመስጠት በጤና ሥርዓቱ ላይ አዎንታዊ ለውጥ እየፈጠሩ ይገኛሉ። አብዛኞቹ ሠልጣኞች በህክምና ተቋማት በተለይ በጤና ሚኒስቴር እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በክልል ጤና ቢሮዎች በኩል ቢሆንም ሥልጠናውን በግላቸው መውሰድ ለሚሹ አስፈላጊው መስፈርት የጤና ባለሞያ ሆነው መገኘታቸው ብቻ ነው።

የአለርት ታሪክ በአገር ውስጥ ብቻ ተወስኖ የሚቆም አይደለም።



147

ማዕከሉ ዓለም አቀፍ የማሠልጣኛ መዳረሻ ሆኖ ከተለያዩ አገራት የጤና ባለሙያ ሠልጣኞችን ያስተናግዳል። ለአብነት ደቡብ ሱዳን፣ ሕንድ፣ ኔዘርላንድስ፣ ሞሮኮ፣ ኢራን፣ ቤልጂየም፣ ጀርመን፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ታንዛኒያ ፓኪስታን እና ናይጄሪያን መጥቀስ ይቻላል። ከፍተኛ (Ad- vanced) የሥጋደዌ እና ሌሽማኒያሲስ (Leish- maniasis) ሥልጠናዎች በየዓመቱ ከ100 በላይ ለሚሆኑ ዓለም አቀፍ ተሳታፊዎች ሥልጠና ይሰጣል፡፡

ማዕከሉ በከፍተኛ ትጋት ጥራትና ቁርጠኝነት በብዙ መልኩ ስኬቶችን አስመዝግቧል። እ.አ.አ ከ2021 ጀምሮ በኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር (EPHA) የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ አቅራቢ ፈቃድ የተሰጠው ሲሆን፤ ከጤና ሚኒስቴር እና

ከተለያዩ አጋሮች የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ እውቅናን አግኝቷል።

የአለርት ሆስፒታል የሥልጠና ማዕከል በዓመታት ጉዞው ጽናት፣ በጤናው መስክ ያስመዘገበው ስኬት ቀላል የሚባል አይደል። ከሥጋደዌ ህክምና ማዕከልነት ጀምሮ እስከ ዛሬ ዓለም አቀፍ የሥልጠና መሪ ተቋም በመሆን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በሆስፒታሉ ውስጥ ከሚከናወኑና እየተከናወኑ ካሉ ሥራዎች በተጨማሪ የሥልጠና ማዕከሉ በተለይ የጤና ባለሞያዎችን ዕውቀት ከማሻሻልና ከማጎልበት አኳያ ቁልፍ ሚና አለው፡ ፡ በዚህም የጤና አገልግሎትን ወደፊት እየመራ የሚገኝ አንጋፋ የሥልጠና ማዕከል ሆኗል፡፡

የሥልጠና ማዕከሉ ዳይሬክተር ሲስተር ማርታ ፍቃዱ፤ በማዕከሉ የሚሰጠው ሥልጠና



148

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም

በስፔሻሊስት ሐኪሞች፣ ልምድ ባላቸውና የአሠልጣኝነት ሥልጠና ወስደው በተከታታይ በሰጡት ሥልጠና ጥሩ ግብረ መልስ ባላቸው የጤና ባለሞያዎች የሚከናወን መሆኑን ነው የገለጹት።

በጤናው ዘርፍ የሚሠማራ አንድ ባለሞያ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተመርቆ ወደ ሥራ ዓለም ከተሠማራ በኋለ የተለያዩ የሞያ ማሻሻያ ኮርሶችንና ሥልጠናዎችን መውሰድ እንደሚጠበቅበት የገለጹት ሲስተር ማርታ፤ ይህም በሞያው ያለውን ዕውቀት በየጊዜው ከወቅቱ ጋር ለማሻሻልና ለማሳደግ ያግዘዋል፤ በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኘው የሥልጠና ማዕከል በዚህ ረገድ ጉልህ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

የሥልጠና ማዕከሉ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉትን ክፍሎች ሳይጨምር፤ አዳራሾች፣ የኮምፒዩተር ላቦራቶሪ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፤ ሠልጣኞች ለተግባር ልምምድ በሆስፒታሉ የተለያዩ የህክምና ክፍሎች ውስጥ ተመድበው ይሠራሉ፡ ፡ ለሥልጠና ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ ሠልጣኞችም የመመገቢያ እና የመኝታ አገልግሎቶችን የሚያገኙባቸው ክፍሎች አሉት። በአጠቃላይ የሥልጠና ማዕከሉ በአንድ ጊዜ እስከ 160 ሠልጣኞችን ተቀብሎ የማስተናገድ አቅም አለው፡፡

ከአገር አልፎ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያተረፈውና ድንበር ያልገደበው የሥልጠና ማዕከል ባለቤት የሆነው አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፤ በሕክምና አገልግሎቶች የቆዳና አባላዘር (Dermatology) የአጥንትና የነርቭ ቀዶ (Ortho- pedic & Neurosurgery)፣ የፕላስቲክ እና የመልሶ ማቋቋም ቀዶ፣ የዓይን (Ophthalmol- ogy)፤ በእናቶችና ህፃናት ጤና የማህፀንና ፅንስ እንዲሁም የህፃናት ህክምና፤ በተላላፊ በሽታዎችና ተሀድሶ የሥጋደዌ እና የሣምባ ነቀርሳ፣ የፊዚዮቴራፒ እና መልሶ ማቋቋም (Rehabil- itation) እንዲሁም 24 ሠዓት የሚሠራ የድንገተኛ ህክምና እና የፅኑ ህሙማን እንክብካቤ (ICU) የህክምና አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ የሚገኝ ሁሉን አቀፍ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው።



149



150

ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 33 ግንቦት 2018 ዓ.ም


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም