ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም - ኢዜአ ነጋሪ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
የደም
የላብ
የዕንባ
የውኃ ጠብታ. . .
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
“የኢትዮጵያ ማንሠራራት ጅማሮ፤
የደም ጠብታ
የላብ ጠብታ
የዕንባ ጠብታ
የውኃ ጠብታ
ድምር ውጤት መሆኑን፤ ይህ ግድብ ህያው ምልክት ሆኖ ለትውልድ ሲመሰክር ይኖራል”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
በተለያዩ እሴቶችና የታሪክ ዳራዎች የምትገለፀው አገር ሕዝቦች የሆንን እኛ የዓባይ ዘመን ትውልዶች ዓባይ ላይ አሻራችንን ልናኖር ጉዞ ከጀመርን እነሆ አስራ ሦስት ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ በጋራ ጥረታችን የመልማትና የማደግ ተስፋችን በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ፡፡ ሥራ በጋራ ተሰርቶ እንዴት ማጠናቀቅ እንደሚቻል መለያ ቀለማችን በሆነው በሕዳሴ ግድባችን በተግባር አይተናል፤ በኅብረት ሰርቶ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረስ የሚያስገኘውን ደስታም ማጣጣም ጀምረናል። የሕዳሴ ግድባችንን አጠናቀናል። ይህ ኢትዮጵያዊያን ስንተባበር ለችግሮቻችን ሁሉ መፍትሔ ማግኘት እንደምንችል ማሳያ ነው፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፤ የኤሌክትሪክ ብርሃን፤ የሥራ ዕድል መክፈቻ የኃይል ምንጭ፣ የትውልዱ ዘመን ተሻጋሪ አሻራ ነው። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድባችን ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ስንቆም ያሰብነውን ማሳካት እንደማይሳነን ለዓለም ያሳየንበት ታላቅ ፕሮጀክት ነው።
‘በግድባችን የመጣ በአገሬ የመጣ’ ያልን፤ እኛ በአገር ውስጥና በመላው ዓለም የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን የግንባታውን ሂደት የሚያስተጓጉሉ ክስተቶች በተፈጠሩ ጊዜ በዓለም አደባባይ ለአገራችን ተሟግተናል። ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ፍትህና ርትዕ እንደምትሻ፣ የታችኛውን የተፋሰስ አገራት የመጉዳት ሃሳብ እንደሌላት፣ ወንዙ ለሁላችንም እንደሚበቃ፣ የትብብርና የወዳጅነት መርህ ያለውን የኢትዮጵያ እና የሕዝቦቿን ፍላጎትና እውነት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አስረድተናል፡፡
በገንዘብ፣ በዕውቀት እና በጉልበታችን ብቻ ሳይሆን በተለያዩ መድረኮች፣ በመገናኛ ብዙኃን በተለያዩ አግባቦች በግድቡ ዙሪያ የሚሰራጩ
አሉታዊ መረጃዎችን በታላቅ ቁርጠኝነትና በትጋት መመከት ችለናል። በዚህ ዲፕሎማሲያዊ ተጋድሎ የተገኘውን ድልም ታሪክ መዝግቦታል።
“ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፤ ለሃምሳ ሰው ጌጡ” እንዲሉ፤ መላው አገር ወዳድ ዜጋ የፓለቲካ አመለካከት፣ የሃይማኖት ልዩነት፣ የመኖሪያ ቦታ ርቀት ሳይገድበው በአንድ ዓላማ የተሰለፈበት፤ ከዕለት ጉርሱና ከዓመት ልብሱ እየቀነሰ ገንዘቡን የለገሰበትና ቦንድ የገዛበት፤ አርሶ እና አርብቶ አደሩ በጉልበቱ ላቡን አፍስሶ በአካባቢ ጥበቃ ሥራ ላይ በመሰማራት ታላላቅ አገራዊ ስኬቶች ያስመዘገበበት ነው።
እናቶች መቀነታቸውን የፈቱለት፤ አባቶች መጦሪያቸውን ያወጡለት፤ የተማሪ ቦርሳ፣ የሠራተኞች ደመወዝ፣ የባለሀብቶች ጥሪት ሳይቀር ፈሰስ የተደረገበት፤ ኢትዮጵያዊያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ በአንድነት የቆሙለትና ለፍፃሜ ያደረሱት የሕዳሴ ግድባችን ግንባታ የመጨረሻ ምዕራፍ መጠናቀቅ የምሥራች እነሆ በአዲስ ዘመን ዋዜማ ተበስሯል! በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአዲስ ዘመን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ተከፍቷል። የኢትዮጵያ ብልፅግና በዓለም ይናኛል።
“ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ተባበርን፣ እንኳን ጨከንን፣ እንኳን አብረን ቆምን፣ እንኳን ለአገራችን ክብር እና ዕድገት የሚገባውን መስዋዕትነት ከፈልን። ምክንያቱም ፍሬው ጣፋጭ ነው። መስዋዕትነት ከፍለን፣ ገንዘብ አባክነን መጨረሻ ላይ ይሄንን ነገር ማየት ባንችል ኖሮ ኪሳራ ነበር። ነገር ግን ያ ሁሉ ጭቅጭቅ ያ ሁሉ መከራ መጨረሻ ላይ ለልጆቻችን ከ62 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ውሃ ለማኖር ነው። ያንን ዛሬ አሳካነው።”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ማውጫ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በየሁለት ወሩ የምትታተም መጽሔት መስከረም 2009 ዓ.ም ተመሰረተች
አድራሻ፦
አራዳ ክፍለ ከተማ
ስልክ ቁጥር
+251-11-55-00-11
+251-11-56-39-31
+251-11-56-52-21
ፋክስ ቁጥር
+251-11-55-16-09
enanegari@gmail.com
የታላቁ ህዳሴ ግድብ አገራዊና ቀጣናዊ ትሩፋቶች
12
መሶብ - አዲሱ የዲጂታል አብዮት
24
ኢትዮጵያን ማሳያ ሌላኛው መንገድ - ማይስ
48
ከዘመን ጋር ለመዘመን
56
መጪውን ትውልድ ለመታደግ…
70
የአገልግሎቶቹ የጀርባ አጥንት
78
ሉዓላዊነትን የማስጠበቅ አንዱ እርምጃ
88
አለርት - በፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና. . .
104
መልዕክት
ውድ አንባቢያን ሠላም በያላችሁበት ይሁን! ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የዳሰሰችው ነጋሪ መፅሔት ወደ እናንተ ደርሳለች።
ነጋሪ በዚህ ዕትሟ መታወቂያ ለማደስ፣ የንግድ ፈቃድ ለማውጣት፣ ግብር ለመክፈል፣ ፓስፖርት ለማውጣት፣ የትምህርት ማስረጃዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ሌላም ሌላም . . .መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደተለያዩ ተቋማት መኳተንና ማለቂያ የሌላቸው በሚመስሉ አታካች ወረፋዎች መጉላላትን ታሪክ ያደረገውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫን ታስቃኛለች።
የሰው ልጅ ዕለታዊ ተግባሩን ለማቅለል ብዙ ተመራምሮ ከፈጠራቸው ውጤቶቹ መካከል የዘመኑ የቴክኖሎጂ ልህቀት ደረጃ የሆነው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence - AI) ተጠቃሽ ነው። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት መስክ ለአፍሪካ የልህቀት ማዕከል እንድትሆን የተጀማመሩ ጥናትና ምርምሮች፣ ሮቦቶችን መሥራት ያሉ አበረታች ሥራዎች በነጋሪ ተዳሰዋል።
የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዳዲስ ውብ መልኮችን እየተላበሰች ትገኛለች። የኮሪደር ልማትን ጨምሮ እንደ እንጦጦ ፓርክ፣ አንድነት ፓርክ፣ የወዳጅነት አደባባይ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ያሉ ፕሮጀክቶች አዳዲስ ውበትን ጨምረውላታል፡፡
እነዚህ የልማት ፕሮጀክቶች አገሪቷ የነበራትን ገጽታ በመልካምነት አጉልተው ከማሳየት ባሻገር የላቀ ትርጉም አላቸው - የረጅም ጊዜ ዘለቄታዊ ጥቅሞችን የሚያስገኙ መሆናቸውንም ልብ ይሏል። ይበልጡን ደግሞ አዲስ አበባ የቱሪዝም ኮንፍረንስ ማዕከል እንድትሆን፣ ከዘርፉም የላቀ ገቢ እንዲገኝ ትልቅ አበርክቶ አላቸው . . . ማይስ ቱሪዝም የነጋሪ ሌላው ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ቀርቧል።
በአንድ አገር ፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገት ለማምጣትና ዘላቂ የልማት አቅም ለመገንባት ለዜጎች በማንኛውም ጊዜ የምግብ አቅርቦትና ተደራሽነትን ማረጋገጥ ይጠይቃል። ተደራሽ የሚሆነውም ምግብ ጥራቱ፣ ደህንነቱና የንጥረ ምግብ ይዘቱ የተሟላ ሲሆን ጤናማ፣ አምራች፣ ረዥም ዕድሜና አስተማማኝ የፈጠራ ብቃት ያለው ዜጋ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ ያግዛል።
ሉዓላዊነትን የማስጠበቅ አንዱ እርምጃ እንደሆነ የታመነበት፤ የኩታ ገጠም እርሻ እና የመስኖ (የበጋ) ስንዴ ምርት እና ምርታማነት፣ የሌማት ትሩፋት፣ ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘው የአረንጓዴ አሻራ ኢንሼቲቭ፣ የተማሪዎች ምገባ እና ሌሎችም ውጤት የተገኘባቸውን ሥራዎች በስፋት የዳሰሰው የኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ሽግግር ራዕይ ከዓለም አቀፍ ጉዳይነቱ ጋር ተጣምሮ በነጋሪ ተሰንዷል።
አለርት - በፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና፣ የአገልግሎቶቹ የጀርባ አጥንት እና መጪውን ትውልድ ለመታደግ በሚሉ ርዕሶች የተዘጋጁ ጤና ላይ ያተኮሩ ፅሁፎችም በነጋሪ ተካተዋል።
መልካም ንባብ!
ዋና አዘጋጅ
ፈለቀ ሽኩር
ም/ ዋና አዘጋጅ
የሺመቤት ደመቀ
ከፍተኛ አዘጋጅ
ፍቅርተ ባልቻ
አዘጋጅ
መንገሻ ገ/ሚካኤል
አርት ዳይሬክተር
ነብዩ መስፍን
nebiyou1st@gmail.com
ድረ-ገፅ
www.ena.et/web/negari
ፖለቲካ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
የታላቁ ህዳሴ ግድብ
አገራዊና ቀጣናዊ ትሩፋቶች
በለዓለም መ.
መግቢያ
ዝንተ ዓለም ከኢትዮጵያ ማህጸን እየፈለቀ፤ ጋራ ሸንተረሯን እየዞረ የሚሄድ አንጡራ ሀብት - ዓባይ! ኢትዮጵያዊያን ከመቆጨት፣ ከመቀኘትና ከመውቀስ ባሻገር ይህ ነው የሚባል ሥራ ሳይሰሩበት ዘመናት የተቆጠሩበት እምቅ ጉልበት።
በረጅሙ የመካከለኛው ዘመን እና የዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ከግብጽ ጋር በሚኖር ሃይማኖት ለበስ ፖለቲካዊ መካረሮች ወቅት ነገሥታት “ዓባይን እንገድባለን” እያሉ ለማስፈራራት ቢሞክሩም፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንዳሉት እንኳን ሊገድቡት በክረምት ሊሻገሩት እንኳን
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
አይሞክሩም። (ግርንቢጥ በሚበዛው ታሪካችን ውስጥ በውል ሊታዩ ከሚገባቸው ጉዳዮች አንዱ አክሱምን ያህል ሃውልት፣ ላሊበላን ያህል የተራቀቀ የአንድ አለት ውቅር አብያተ ቤተክርስቲያ ሠርተን ያሳየን፤ እንኳን ዓባይን ሌሎች ትናንሽ ወንዞቻችንንም የሚያሻግሩ ድልድዮች መሥራት ያለመቻላችን ነው። ይህኛው ርዕስ ጉዳይ ይቆየን!)
ለዘመናት ሀብታችንን መጠቀም ባለመቻላችን ምክንያት ገጣሚው በእውቀቱ ስዩም ቅልብጭ ባለ መልኩ እንዳስቀመጠው “ዓባይ ለግብጻዊያን ምሣ፣ ለኢትዮጵያዊያን ምሣሌ” ሆኖ ቆየ። እንደው የሩቁን እንኳ ብንተወው በቅርቡ ታሪካችን ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶቿን በማልማት ከድህነት ለመውጣት የምታደርገውን ጉዞ ለማሰናከል ከቅርብም ከሩቅም ያሉ ኃይሎች ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋላል። ከዓለም አቀፍ ተቋማት ምንም አይነት ድጋፍና ብድር እንዳታገኝ ከማሰናከል ጀምሮ እስከ የውስጥ የቤት ሥራዎችን በመፍጠር አቅም ፈጥራ ልማት ላይ እንዳታተኩር ማድረግን የመሳሰሉ መልከ ብዙ እንቅፋቶች ተፈጥረዋል። ሆኖም ጊዜው በደረሰ ጊዜ በመንግሥት ቁርጠኝነትና በሕዝብ የጋራ ርብርብ ዐብይ አገራዊ ፕሮጀክት ታልሞ ወደ ሥራ ተገባ።
ለፍፃሜ የደረሰው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለአገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ከሚኖረው ግዙፍ ፋይዳ ባሻገር ቀጣናዊ እና ተፋሰሳዊ አንድምታው የጎላ ነው። በዚህ ፅሁፍ የግድቡን አገራዊ እና ቀጣናቂ ፋይዳዎች ለመዳሰስ ይሞከራል።
የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅሙና አጠቃላይ ይዞታው
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአንድ ጊዜ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት፣ በዓመት በአማካይ 15 ሺህ 759 ጊጋዋት በሠዓት ኃይል በማመንጨት ለአገር አቀፍ
የኤሌክትሪክ ትስስር ሥርዓት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ይህም አቅም አገራችን ከግድቡ ኃይል ማመንጨት በፊት የነበራትን ኃይል በእጥፍ ያህል የሚያሳድግ ነው። በዚህ ይዞታው ግድቡ በአንድ ጊዜ የሚያመነጨው አቅሙ (5 ሺህ150 ሜጋ ዋት) ከዓለም 17ኛው ግዙፍ ግድብ ያደርገዋል። የሕዳሴ ግድብን የሚቀድሙት ግድቦች ሰባቱ በቻይና፣ ሁለቱ በብራዚል፣ አንዱ በብራዚልና ፓራጓይ፣ አንዱ በቬኔዙዌላ፣ ሁለቱ በአሜሪካ፣ ሁለቱ በሩሲያ፣ ሁለቱ በካናዳ ይገኛሉ። ይህም የሚያሳየው አገራችን በራሷ ውስጣዊ አቅም የገነባችው ግድብ በቻይና፣ በአሜሪካ፣ በሩሲያ፣ በካናዳ እና በብራዚል ከሚገኙ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ማመንጫዎች ቀጥሎ የሚጠቀስ ግዙፍ ግድብ መሆኑን ነው።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ሲሆን ቀጥሎ የሚመጣውን የአስዋን ግድብም 2 ነጥብ 5 እጥፍ ይበልጠዋል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በዓመት በአማካይ 15 ሺህ 759 ጊጋዋት በሠዓት ኢነርጂ በማመንጨት ኤሌክትሪክ ያልተዳረሰባቸው የገጠር መንደሮችና ከተሞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግና አቅርቦቱን አሁን ካለበት 54 በመቶ ወደ 65 በመቶ ከፍ ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የዚህ ኘሮጀክት ድርሻ ከፍተኛ ነው።
ግድቡ የሚያመነጨው ኃይል ታዳሽ ወይም ንጹህ ኢነርጂ በመሆኑ ከአካባቢ ብክለት የጸዳ፣ ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃችን ተጨማሪ እሴት የሚጨምር ነው። ኃይል (Energy) የቀጣዩ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ አንቀሳቃሽ ሞተር ነው። ንፁህና ታዳሽ ኃይል ነዳጅ ላይ ያለንን ጥገኝነት በመቀነስ፣ የመንግሥትን የዘላቂ ልማት ጥረቶች በመደገፍ፣ የኢንዱስትሪ ምርቶቻችን ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማድረግ፣ ኢነርጂ በብዛት ፈላጊ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
(Energy-intensive) የሆነውን የቀጣዩን ኢንዱስትሪያዊ (የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) አብዮት በማሳለጥ ድርብ ድርብርብ ሚና አለው።
ከኢነርጂ ባሻገር
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ለማቃለል ወሳኝ ነው። የሚመነጨው ከፍተኛ መጠን ያለው ኃይል ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለከተሞች መስፋፋትና ለገጠር የኤሌክትሪክ መስፋፋት በሚኖረው ጉልህ አበርክቶ የኢኮኖሚ ዕድገትን ያፋጥናል። የሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን እንደሚያስገኝ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ከእነዚህ መካከል ዋና ዋናዎቹን መጥቀስ ይቻላል።
የውጭ ምንዛሬ ገቢ
ኢትዮጵያ ከግድቡ ከምታመነጨው ኃይል የራሷን ፍጆታ ከመሸፈን ባሻገር ለጎረቤት አገራት በመሸጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ትችላለች። በዚህ ረገድ እስካሁን ለሱዳን፣ ለኬንያ እና ለጅቡቲ ኃይል በማቅረብ በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚገመት የውጭ ምንዛሬ ገቢ እያገኘች ሲሆን በቀጣይም ለእነዚህ አገራት የሚቀርበውን ኃይል በመጨመር፣ ለታንዛንያ እና ለሌሎችም አዳዲስ አገራት በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ገቢዋን የምታሳድግበት ዕድል ይፈጠራል።
የዕውቀት ሽግግር እና የሥራ ዕድል ፈጠራ
ታላቁ የሕዳሴ ግድባችን ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ይዞ የመጣ ፕሮጀክት መሆኑ እሙን ነው። ከከፍተኛ ባለሙያዎች ጀምሮ እስከ የቀን ሠራተኛ ድረስ በግንባታው ሥራ በመሳተፍ በአጠቃላይ ከ12 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ከ30 አገራት ለተውጣጡ ከ300 በላይ የውጭ አገር ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል። በፕሮጀክቱ የእስካሁን ሂደት በቀጥታ የሥራ ዕድል ከፈጠረላቸው ባሻገር እጅግ በርካታ ዜጎች ለግድቡ ግንባታ ሠራተኞች የተለያዩ አገልግሎቶችን በማቅረብ ጊዜያዊ የሥራ ዕድል አግኝተዋል። በቀጣይም በብዝሃ ዘርፍ የሥራ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ዕድል የሚፈጠርላቸው ዜጎች ይኖራሉ።
ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተሰባሰቡ ከ300 በላይ ባለሙያዎች በግድቡ ግንባታና የማማከር ሥራ ላይ ተሳትፈዋል። በዚህም ለዜጎቻችን በተግባር የተደገፈ ሰፊ የክህሎት እና የቴክኖሎጂ ልምድ የመቅሰም ዕድል ተፈጥሮላቸዋል። የአገር ልጆች የግድቡን ዲዛይን በማሻሻል እና የተርባይኖችን አቅም በማሳደግ የግድቡን ኃይል የማመንጨት አቅም ማሳደግ የመቻላቸው ምስጢርም ይኸው ነው። ከቴክኖሎጂ ሽግግርና ከክህሎት ማሳደግ አገራዊ ፋይዳው ባሻገር ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ብሎም ክህሎታቸውን ለማሳደግ ምክንያት ሆኗል።
ግድቡ የፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ
በግድቡ ግንባታ አማካኝነት የተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ በአገራችን ትልቁ የውሃ አካል ነው። የጣናን ሐይቅ በሁለት እጥፍ የሚበልጠው ይህ ሐይቅ ለአካባቢው የአየር ንብረት ከሚኖረው ጉልህ ፋይዳ በተጨማሪ ከሌሎች አገልግሎቶቹ
ጎን ለጎን ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ማልማት ያስችላል። ይህም የአገሪቷን ልማት ከማፋጠን አንጻር ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ነው። በተጨማሪም የግድቡ ሰው ሰራሽ ሐይቅ በዓመት ከ10 እሰከ 15 ሺህ ቶን የዓሣ ሀብት ማምረት ያስችላል። ግድቡ ለመስኖ ልማት የሚያገለግል የውሃ ማጠራቀሚያ ይፈጥራል። ይህ ደግሞ በዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነውን የግብርና አሰራራችን በማሻሻል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በእጅጉ ያግዛል።
የቁጠባ ባሕል ከማዳበር አንጻር
የሕዳሴው ግድብ ቦንድ ሽያጭ አገራዊ የቁጠባ ባሕል እንዲስፋፋ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ቁጠባ ለአንድ አገር ኢኮኖሚ ማደግ አንዱ አመላካች ሲሆን ዜጎች የመቆጠብ አቅማቸው እያደገ በመጣ ቁጥር የአገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ይስፋፋል፤ በዚህም የሥራ ዕድል ይፈጠራል። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ጊዜ የአገራችን የቁጠባ ባሕል ደካማ የነበረ ሲሆን አሁን አገራዊ ቁጠባችን ዕድገት አሳይቷል።
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
የቱሪዝም መዳረሻነት
በግድቡ አካባቢ የተፈጠረው ትልቅ የውሃ አካል ለቱሪዝም ልማት ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል። ይህ ደግሞ ተጨማሪ የሥራ ዕድሎች በመፍጠር አስተዋጽኦ ያደርጋል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማለት በሚቻልበት ሁኔታ ይህን የትውልድ አሻራ የሆነ ቅርስ ለማየት ይጓጓል። እስካሁን ባለው የግንባታ ሂደት ከ300 ሺህ በሚልቁ የአገር ውስጥ ጎብኝዎች ተጎብኝቷል። ሕዳሴ ግድብ የአገር ውስጥ ቱሪዝምን እጅግ አስፋፍቷል፣ በአካባቢው በሚገኙ ከተሞች ዘንድም መነቃቃትን ፈጥሯል። በቀጣይ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻ የሚያደርጉት በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ነው። በዚህ ላይ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ በሚኖሩት ከ70 በላይ ደሴቶች የሚፈጠሩ ተጨማሪ የቱሪስት መዳረሻዎች ቱሪዝምን የሚያነቃቃና ተጨማሪ ገቢ የሚያመነጭ ይሆናል።
ለአካባቢ ጥበቃ ሥራ ተነሳሽነት መፍጠሩ
ኅብረተሰቡ ግድቡ የታለመለትን ዓላማ ማሳካት የሚያስቸለውን ያህል ዕድሜ እንዲኖረው ለማስቻል፣ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን በተለይም በችግኝ ተከላ እና በአፈር ጥበቃ ሥራዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተረባረበ ይገኛል። ግድቡ በደለል እንዳይሞላ የአፈር ጥበቃ እና ችግኞችን የመትከል
ተግባር በአገራችን ሁሉም አካባቢዎች ባሕል ሆኖ ቀጥሏል። በተጨማሪ ግድቡ የዓባይን ወንዝ የውሃ ፍሰት በመቆጣጠር የታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ ሊከሰት የሚችልን የጎርፍ አደጋ ለመቀነስ ይረዳል።
ብሔራዊ ኩራት እና የአንድነታችን ዓርማ
የግድቡ ግንባታ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ጥረት ውጤት በመሆኑ፣ የብሔራዊ ኩራትና የአንድነት ምልክት ሆኗል። የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ መሰረት ከመጣል ባሻገር በቀጣናው የይቻላል መንፈስን በተግባር ያረጋገጠ ነው።
በኢትዮጵያዊያን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቀጣናው አገራትም የይቻላል መንፈስ ማሳያ ሆኗል። ኢትዮጵያዊያን በጋራ ጉዳዮቻችን ላይ ያለንን አቋም (ሕብረ ብሄራዊነት) ለቀጣናው እና ለዓለም አገራት ያሳየንበት ከመሆኑ ባሻገር በእኛም ውስጥ የ’ይቻላል’ መንፈስ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለመጪው ትውልድ የይቻላል መንፈስን ሲያንጸባርቅ የሚኖር ፕሮጀክት ነው። ያለምንም የውጭ አገራት ብድር እና ድጋፍ የተከናወነው ይህ አገራዊ ፕሮጀክት፤ ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ የሚጠይቅና በምንም ተዓምር በታዳጊ አገር አቅም የማይታሰብ ፕሮጀክት ቢሆንም፤ የሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች መካከል አገራዊ መግባባት እንዲጎለብት አድርጓል።
ፕሮጀክቱ ሁሉም አገር ወዳድ ዜጋ የፖለቲካ አመለካከት፣ የሃይማኖት ልዩነት፣ የመኖሪያ ቦታ (ከአገር ውስጥም ይሁን ከውጭ) ርቀት ሳይገድበው፣ የብሔር፣ የዕድሜ፣ የጾታ ልዩነት ሳይታይበት ሁሉም በአንድነት በመረባረቡና ግንባታው በመጠናቀቁ ለቀጣይ የአገራችን የብልጽግና ጉዞ መሰረት ጥሏል።
ቀጣናዊ ሲሳይ
ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የትኛውንም አገር የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት፤ በጋራ የማደግ መርህን የምትከተል መሆኗን እና ከግብፅ ጋር ለመወያየትና ለመነጋገር አሁንም ፍላጎት ያላት መሆኑን በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች። ኢትዮጵያ ይህንን አቋሟን ስትገልጽ እንደቆየችው ግድቡ በተፈጥሮ ሀብቷ የመጠቀም ፍላጎቷን ለማረጋገጥ እና የሕዝቦቿን የመልማት ፍላጎት እውን ለማድረግ ነው። ሌሎችን የመጉዳት ሀሳብ እንደሌላት በተደጋጋሚ አስታውቃለች። በዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ውስጥ ከተካተቱ መሰረታዊ መርሆዎች አንዱ የጋራ ተጠቃሚነትና ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርህ ነው። ኢትዮጵያ ህጋዊ በሆነ መንገድ በተፋሰሱ አገራት መካከል አሁንም ውይይት ቢካሄድ መተማመን ይፈጠራል የሚል እምነት አላት።
ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ
ኢትዮጵያዊያንን ብሎም የተፋሰሱን አገራት ሕዝቦች፤ በጋራ በማደግ ፍላጎት ጥላ ስር ያሰባሰበው የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት፤ በተፋሰሱ አገራት መንግሥታት መካከል የግንኙነት መንስኤ ከመሆን ባሻገር ለተፋሰሱ አገራት ሕዝቦች መልካም ግንኙነት መሰረት ጥሏል። በተጨማሪም በተፋሰሱ አገራት መካከል ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲነግሥ በማድረጉ ከአገራት ጋር የመተማመንና የመተባበር ዲፕሎማሲ እንዲፈጠር አስገድዷል።
የግድቡ መገንባት ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን ፍትሃዊ አመለካከታችንን ለዓለም ለማሳወቅ መልካም
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
አጋጣሚን ፈጥሮልናል። ኢትዮጵያ ምን ያህል ፍትሃዊ እንደሆነች የዓለም ሕዝቦች የተረዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል። የአገራችንን የመደራደር አቅምም አሳድጓል፤ ይህም የአገራችንን ገፅታ እጅጉን ቀይሮታል። የታችኛው ተፋሰስ አገራት በተለይ ግብፃዊያንን ለውይይት እና ምክክር በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲቀመጡ አድርጓቸዋል።
ለተፋሰሱ አገራት የሚያስገኘው ጥቅም
ድንበር ተሻጋሪው የዓባይ ወንዝ፤ ከኢትዮጵያ ተራራማ ቦታዎች ተነስቶ ወደ ሱዳን እና ግብፅ ይፈሳል። ሱዳን ድንበር ላይ የወንዙ ዓመታዊ አማካይ የፍሰት መጠን 50 ነጥብ 6 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ነው።
በሱዳን፡- የጎርፍን አደጋ መቀነሱ፣ ሁሌም የተመጣጠነ ውሃ እንዲኖር ማድረግ፣ ድርቅን መከላከል፣ የውሃ ትነትን እና የደለል መጠንን መቀነስ፣ ከግድቡ በታች ኃይል የማመንጨት አቅምን በማሳደግ ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል የማግኘት ዕድል መፍጠሩ ተጠቃሽ ነው።
በግብፅ፡- ውሃን በመቆጠብ የተሻለ የውሃ አጠቃቀም እንዲኖር ማድረጉ፣ ጎርፍ መከላከልና በሁሉም ወቅት የተመጣጠነ ውሃ ማግኘት ማስቻሉ፣ የውሃ ትነት እና የደለል መቀነስ፣ የመጓጓዣ እንዲሁም ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል የማግኘት ዕድል መፍጠሩም እንዲሁ።
የአየር ብክለትን በመቀነስ የአየር ንብረት ለውጥን መቀነስ፣ በአካባቢው አገራት የኃይል ትስስርን በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣት ከአካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጠቀሜታዎቹ መካከል ናቸው።
ሲጠቃለል
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በናይል ተፋሰስ አገራት የትብብር፣ የልማት፣ የተሻለ ውሃ አጠቃቀም እንዲሁም ለአካባቢው አየር ንብረት መሻሻል ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለው ይታመናል። ከእነዚህም መካከል አምስት ዋና ዋና ጠቀሜታዎችን ማንሳት ይቻላል።
የጎርፍ አደጋ ቅነሳ፡- ግድቡ በተለይም በሱዳን ላይ በየዓመቱ ይደርስ የነበረውን ከባድ የጎርፍ አደጋ ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
የውሃ አያያዝ ቁጥጥር፡- ሕዳሴ ግድብ በዓባይ ወንዝ ፍሰት ላይ የተሻለ ቁጥጥር እንዲኖር ያስችላል። ይህም የውሃ አቅርቦትን ለመቆጣጠር እና የውሃ አጠቃቀምን ለማቀድ ይጠቅማል።
የኃይል አቅርቦት ዕድል፡- የታችኛው ተፋሰስ አገራት በተለይም ሱዳን ከግድቡ የኤሌክትሪክ ኃይል የመግዛት ዕድል አላቸው፣ ይህም የኃይል ፍላጎታቸውን ለማሟላት ሁነኛ መላ ነው።
የደለል ቁጥጥር፡- ግድቡ ከፍተኛ መጠን ያለው ደለል በመያዝ ወደ ታችኛው የተፋሰሱ አገራት የሚሄደውን ደለል መጠን ይቀንሳል። ይህ ደግሞ የነባር ግድቦችን ዕድሜ ለማራዘም እና የመስኖ ቦዮችን የመደፈን ችግር ለመቀነስ ይረዳል።
የተሻለ የትብብር ዕድል፡- የግድቡ ግንባታ በጋራ የውሃ ሃብት አጠቃቀም ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብፅ መካከል ለተሻለ ትብብር በር ይከፍታል።
በአጠቃላይ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋን የሚሰጥ እና ለአካባቢውም በርካታ ጥቅሞችን የሚያስገኝ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውነታዎች
• የግንባታው የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠው፦ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም
• የግንባታው ስፍራ፦ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ጉባ ወረዳ
• ግድቡ የሚያመነጨው የኃይል መጠን፦ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት
• የዋናው ግድብ ርዝመት፦ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር
• የዋናው ግድብ ከፍታ፦ 145/ 155 ሜትር፣
• የዋናው ግድብ ውፍረት፦ የግድቡ ግርጌ 130 ሜትር፣ የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው ክፍል 11 ሜትር
• ግድቡ የሚሸፍነው የቦታ ስፋት፦ 1 ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር
• ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን፦ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
• ግድቡ ሲጠናቀቅ ውሃ የሚተኛበት መሬት ርዝመት፦ 246 ኪሎ ሜትር
• የኮርቻ ግድብ ርዝመት፦ 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር
• የኮርቻ ግድብ ከፍታ፦ 50 ሜትር
• የግድቡ የኃይል ማመንጫ ዩኒቶች፦13 የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች
• እያንዳንዱ ዩኒት የሚያመነጨው የኃይል መጠን፦ ከ375 እስከ 400 ሜጋ ዋት
• በመስኖ የማልማት አቅም፦ ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት
• ግድቡ ከ70 በላይ ደሴቶች ይኖሩታል፤
• ለግድቡ ግንባታ ከሕዝብ የተሰበሰበ ገቢ፦ ከ23 ቢሊየን ብር በላይ
ፖለቲካ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
መሶብ - አዲሱ የዲጂታል አብዮት
በሔኖክ ታደለ
በኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ከተጀመረ አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተበታተኑ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ሲሰጥ፤ ተገልጋዩ ሕብረተሰብም የተለያዩ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት በየአቅጣጫው በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት መሄድ ሲጠበቅበት ቆይቷል፡፡
ተቋማቱ ውስብስብና ኋላቀር የሆነ የወረቀት ማኅደር አያያዝ ሥርዓት ያላቸው በመሆኑ አስፈላጊ ሰነዶችን በፍጥነት ለማግኘት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ ለሰነድ መጥፋት ፣ ለስርቆት፣ በአይጥ ለመበላት እንዲሁም ከእርጥበት ጋር በተያያዘ የሰነድ መጎዳት የተጋለጡ ነበሩ፡፡ የሰነድ አያያዙ ፈልጎ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ለማግኘት አዳጋች በመሆኑ ጊዜ የሚወስድ፣ ቅልጥፍና የጎደለውና የተገልጋዩን ጊዜ፣ ጉልበት፣ ገንዘብ የሚበላና ለብልሹ አሠራር በር የሚከፍት ሆኖ ቆይቷል፡፡
የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ በበርካታ ቀበሌዎችና በመንግሥታዊ ተቋማት የሰነድ አያያዝ ላይ እስከመጥፋት የደረሰ ጉዳት ሲደርስ ተስተውሏል። ምክንያቱ ምን ይሁን ምን በሚደርሰው ጉዳት መተኪያ የሌላቸው የወረቀት ሰነዶች ላይገኙ ጠፍተው የሚቀሩበት አጋጣሚ የበዛ ነው። ይህም የሰነድ አያያዝ ክፍተት በአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የቱን ያህል ክፍተት እንደሚፈጥር ያሳያል፡፡ ለዚህም ነው በዲጂታል ሥርዓት የተደገፈ የሰነድ አያያዝን ማረጋገጥ ቅንጦት ሳይሆን አሰራርን ማዘመን ታሪክንም መሰነድ ነው የሚባለው።
አንድ ሰው መታወቂያ ለማደስ፣ የንግድ ፈቃድ ለማውጣት፣ ግብር ለመክፈል፣ ፓስፖርት ለማውጣትና የትምህርት ማስረጃዎቹን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በተራራቀ ስፍራ በሚገኙ አምስት መንግሥታዊ ተቋማት በአካል በመገኘት፣ ማለቂያ የሌላቸው በሚመስሉ አታካች ወረፋዎች ለማለፍ ይገደዳል፡፡ በዚያ ላይ
አገልግሎቱ ለዘመናት የተሰነዱ የወረቀት መዛግብቶችን ተመርኩዞ የሚሰጥ በመሆኑ ለእያንዳንዱ አገልግሎት በአማካኝ ከሁለት እስከ ሦስት ቀናት ሊፈጅበት ይችላል - ያውም ከፈጠነ፡፡
አድካሚው ሂደት አንድ አገልግሎት ለማግኘት ወደተለያዩ ማዕከላት መንከራተት የሚጠይቅ በመሆኑ ለግለሰቦችና ለንግድ ድርጅቶች ጠቃሚ ጊዜ እና ሀብትን የሚያባክን ነበር። መንግሥታዊ የአገልግሎት አሰጣጡ በተበታተኑና በተራራቁ ቦታዎች መሰጠቱ ተገልጋዩ ከመንግሥት የሚያገኘው አገልግሎት እጅግ ቅልጥፍና እንዲጎድለው ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህ አይነቱ የተበጣጠሰ ቦታ የሚሰጠው አገልግሎት ቅልጥፍና የጎደለው በመሆኑ ሕብረተሰቡ እንግልት ሳይገጥመው ጉዳዩን ለመጨረስ ካለው ጉጉት የተነሳ ለአገር ዕድገት ትልቅ እንቅፋት ለሆነው ብልሹ አሰራር በር መክፈቱ፤ ስር የሰደደው ቢሮክራሲም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ከማፈን ባለፈ የሕዝቡን አመኔታ በመሸርሸር ለሙስና የተመቸ አካባቢን በመፍጠሩ በመንግሥትና በዜጎች መካከል አጥር መስራቱ የአደባባይ ምስጢር ነው።
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተመራው የለውጥ ራዕይ ከሰነቃቸው ለውጦች መካከል በመንግሥት ተቋማት የሚሰጠውን የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻልና ማዘመን ይገኝበታል፡፡ መሶብ የአንድ ማዕከል ፕሮጀክትም የተወለደው ከዚህ እሳቤ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ለመገንባት ያለመ ነው። ይህ ማሻሻያ በየጊዜው ሲካሄድ የቆየ ሲሆን የተለያዩ ገጽታዎችም አሉት።
ታሪኩ በአጭሩ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዘመናዊ ሲቪል ሰርቪስ በ1900 ዓ.ም እንደተጀመረ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ። ከዚያ በኋላ በመጡት ለብዙ አሥርት ዓመታት የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደርን ለማዘመን የተለያዩ ተቋማዊ ለውጦች ተደርገዋል። ከ “ጠቅላይ መሥሪያ ቤት” እስከ “የመንግሥት ሠራተኞችና መሥሪያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን”፣ “የሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ”፣ “የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር” እና “የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ሚኒስቴር” ድረስ በተለያዩ ስያሜዎችና መዋቅሮች ሲሰራ ቆይቷል።
አሁን ያለው የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሲቪል ሰርቪስ ዘርፍን የሰው ኃብት ልማትና ሥራ አመራርን፣ የመንግሥት አስፈጻሚ ተቋማትን አቅም መገንባትን፣ የአገልግሎት አሰጣጥንና የቅሬታና አቤቱታ ሥርዓትን የመዘርጋት ሥራዎችን ያከናውናል።
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ የመንግሥትን አገልግሎት ውጤታማነትና ብቃት ለማሳደግ ያለመ ዘርፈ ብዙ ጥረት ነው። ሆኖም፤ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን በርካታ ፈተናዎችን መጋፈጥና መፍታት ይጠበቅበት ነበር።
ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ስትራቴጂዎችን ቀርፃ ወደ ትግበራ መግባቷ ይታወቃል። ከእነዚህ
ስትራቴጂዎች መካከል ዋነኛው ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ የምታደርገው ለውጥ የመንግሥት አገልግሎቶችን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ ትልቅ ቦታ ይሰጣል።
የ”ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስትራቴጂ እና በቀጣይ የሚመጣው “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂ ዋነኛ ትኩረታቸው አንዱ የመንግሥት አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ ማቅረብ ነው። ይህ ደግሞ የሲቪል ሰርቪስ ዘርፉን ለማዘመን ወሳኝ ነው።
የመንግሥት አገልግሎቶችን በዲጂታል መልክ ማቅረብ (e-Government)
የሲቪል ሰርቪሱ ዋነኛ ተግባር ለሕዝብ አገልግሎት መስጠት ነው። የዲጂታል ስትራቴጂው የመንግሥት አገልግሎቶችን (ለምሣሌ የንግድ ፈቃድ ማውጣት፣ የመሬት ምዝገባ፣ የግብር ክፍያ፣ የጤና አገልግሎት ቀጠሮ ማስያዝ) በኦንላይን እንዲቀርቡ ያስችላል። ይህ ወረፋ መቀነስ፣ ጊዜ መቆጠብ፣ ወጪን መቀነስ እና ተደራሽነትን ማሳደግ የሚያስችል የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ነው። ግልጽነትና ተጠያቂነትም የዲጂታል አሠራሮች የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶችን ግልጽ በማድረግ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት ስለሚቻል ሙስና እና ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመቀነስ ያግዛሉ። ሌላው “ፋይዳ” ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሲሆን ይህ ሥርዓት የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት መሠረታዊ መሠረተ ልማት ነው። የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ የተገልጋዩን ማንነት ለማረጋገጥና መረጃዎችን ለማጣራት እንዲችሉ ያግዛቸዋል።
የሲቪል ሰርቪስ ውስጣዊ አሰራሮችን ማዘመን (Digitalization of Civil Service)
የሰው ኃብት አስተዳደር (HRM) ዲጂታላይዜሽን የመንግሥት ሠራተኞች ቅጥር፣ ስምሪት፣ ሥልጠና፣ የደመወዝ ክፍያ፣ የእረፍት አስተዳደር እና የጡረታ አሠራሮችን በዲጂታል መልክ በመምራት አስተዳደራዊ ቅልጥፍናን ይጨምራል። ወረቀት አልባ አሠራር (Paperless Office) ደግሞ የወረቀት አጠቃቀምን በመቀነስ ሰነዶችን በዲጂታል መልክ ማደራጀትና ማስቀመጥ የአሠራር ሂደቶችን ያፋጥናል፡፡ የመረጃዎችን ደህንነት ከመጠበቅ ባለፈ ወጪን ይቀንሳል። ሌላው ዘመነኛ አሰራር የመረጃ ሥርዓቶች ውህደት (System Integration) ሲሆን፤ በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ የመረጃ ሥርዓቶችን ማቀናጀትና ማሰናሰል አስፈላጊ ነው። ለምሣሌ አንድ ዜጋ ለአንድ ተቋም የሰጠው መረጃ ሌላ አገልግሎት ሲፈልግ በሌላ ተቋም ውስጥ በቀላሉ የሚገኝበትን ሁኔታ መፍጠር ቢቻል የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ያደርገዋል።
የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች አመለካከት/አቅም ግንባታ
በዲጂታል ለውጡ ሂደት የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች አዳዲስ የሥራ መንገዶችንና ቴክኖሎጂዎችን እንዲቀበሉ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ወሳኝ ነው።
መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ (Data- driven Decision Making)
የዲጂታል ሥርዓቶች በርካታ መረጃዎችን ያመነጫሉ። እነዚህን መረጃዎች በመተንተን (Big
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
Data Analytics) የመንግሥት ፖሊሲዎችን እና የአገልግሎት አሰጣጥ ስልቶችን በማሻሻል የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ይረዳል። ለምሣሌ የአንድ ክልል የግብርና ምርታማነት መረጃን ተንትኖ ቀጣይ ድጋፎችን መወሰን በማሳያነት ሊጠቀስ ይችላል።
የሳይበር ደህንነት
የአገልግሎቶች መስፋፋት የሳይበር ጥቃቶች ስጋትም አብሮ ይጨምራል። የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓቶችንና የዜጎችን መረጃ ለመጠበቅ ጠንካራ የሳይበር ደህንነት መሠረተ ልማትና አሠራር መዘርጋት የስትራቴጂው አካል ነው።
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ዲጂታል ስትራቴጂ የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ ግልፅ እና ተደራሽ በማድረግ የሲቪል ሰርቪስ ዘርፉን ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር በማዋሃድ የዜጎችን እርካታ ለማሳደግ እና መልካም አስተዳደር ለማስፈን ቁልፍ ሚና ይጫወታል።
በትግበራ ላይ ከሚገኘው “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” በመቀጠል የሚተገበረው የ”ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂ በዝግጅት ላይ መሆኑ ደግሞ የመስኩን ስኬት የሚያፋጥን ይሆናል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ዋና ዋና ግቦች እና ምሰሶዎች
ይህ ስትራቴጂ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ኢትዮጵያን ወደ አካታችና የበለፀገች አገር ለመለወጥ ያለመ ነው። በዋና ዋና ግቦቹ እና ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎቹ የሚከተሉት ተካተዋል፡-
አካታች ብልጽግና:-
የዲጂታል ለውጥ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማፋጠን እና የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል ይረዳል ተብሎ ይታመናል።
የኢኮኖሚ ብዝሃነት:-
ከባሕላዊ የግብርና ኢኮኖሚ ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ወደሚያቅፍ፣ በማምረቻና በአገልግሎት ዘርፎች ላይ ወደተመሠረተ ኢኮኖሚ ሽግግር ለማድረግ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።
የሥራ ዕድል ፈጠራ:-
በተለይም በዲጂታል ዘርፍ አዳዲስ ሥራዎችን በመፍጠር ሥራ አጥነትን መቀነስ እና ወጣቶች ከዘመኑ ጋር እንዲራመዱ ያግዛል።
ከዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ጋር መዋሃድ:-
ኢትዮጵያን በዲጂታል ተወዳዳሪነት በዓለም አቀፍ የዕሴት ሰንሰለት ውስጥ ቁልፍ ተዋናይ እንድትሆን ማስቻልም ከግቦቹ መካከል ይገኙበታል።
የመንግሥት አገልግሎቶችን ማሻሻል (ኢ-መንግሥት):-
የመንግሥት አገልግሎቶችን በዲጂታል መተግበሪያዎች ማሻሻል፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ግልፅ እንዲሆኑ ለማድረግ ያስችላል። ይህም በኤሌክትሮኒክስ መንገድ የሚደረግን ንግድ ለማሳለጥ፣ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ለመፈጸም፣ የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት እና የንግድ ሥራ ከባቢን የተቀላጠፈ ለማድረግ የሚረዱ መተግበሪያዎችን ያካትታል።
የዲጂታል መሰረተ ልማት:-
ሰፊ የኢንተርኔት ተደራሽነትና ትስስርን ለማረጋገጥ የዲጂታል መሰረተ ልማትን ማስፋፋትና ማሻሻልን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ይህም ለዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ሁሉ መሠረት የሚጥል ነው።
የሰው ኃብት ልማት:-
የዲጂታል ኢኮኖሚን
ለመደገፍና ለማሳደግ የሚያስችል የሠለጠነ የሰው ኃይል ለመገንባት በትምህርት እና ሥልጠና ላይ ኢንቨስት ማድረግንም ይጨምራል። የ”አምሥት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደሮች” ን የመሰሉ ፕሮግራሞችን ያካትታል።
ለዲጂታል ንግዶች ምቹ ሥነ-ምህዳር:-
ዲጂታል ንግዶችን እና ኢንቨስትመንቶችን የሚያበረታታ ደጋፊ የሕግ ማዕቀፍ፣ ፖሊሲዎችና ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር።
የዘርፍ ለውጥ:-
በዋና ዋና ዘርፎች ማለትም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአገልግሎት እና በቱሪዝም ዘርፎች የዲጂታል መሣሪያዎችን በመጠቀም ምርታማነትንና ቅልጥፍናን ማሳደግ።
የተመዘገቡ ውጤቶች
ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ):-
ኢትዮጵያ በብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት “ፋይዳ” በአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑ አገራት አንዷ ነች። የኢትዮጵያ መንግሥት በ2018 ማብቂያ 90 ሚሊዮን ሰዎችን በመርኃ ግብሩ ለመመዝገብ አቅዷል። ይህ እንደ መሰረታዊ የዲጂታል ሕዝባዊ መሠረተ ልማት ይታያል።
የሞባይል ክፍያዎች:-
የዲጂታል የክፍያ ሥርዓቶች አጠቃቀም በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል፣ በተለይም የሞባይል ገንዘብ (ቴሌብር) የፋይናንስ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ተደራሽነትን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል።
የመሠረተ ልማት መስፋፋት:-
የዲጂታል መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት በርካታ መዋዕለ ነዋይ በማውጣት ኢንቨስት ተደርጓል። ይህም የ4ጂ ኔትወርክ ሽፋን ማስፋፋት እና በዋና ዋና ከተሞች የ5ጂ አገልግሎት ማስጀመርን ያካትታል።
የዲጂታል ዕውቀት እና ክህሎት:-
የ”አምሥት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች”ን የመሰሉ ፕሮግራሞች ወጣቶችን አስፈላጊ በሆኑ የዲጂታል ክህሎቶች ለማስታጠቅ የታለሙ ናቸው።
የሳይበር ደህንነት:-
የአገር ውስጥ መተግበሪያዎችን እና የሳይበር ደህንነት ተነሳሽነቶችን በማዳበር ደህንነቱ የተጠበቀና ዘላቂ የዲጂታል ኢንዱስትሪ ለመገንባት እየተሠራ ነው።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence):-
እንደ “መላ” ያሉ የአገር ውስጥ ቋንቋዎችን የሚጠቀሙ የAI ሥርዓቶች ልማት ከኢትዮጵያ ባለፈ አፍሪካን ያማከለ ሥራ የለመሥራት ጅምር አለ።
በግለሰብ-ለግለሰብ (P2P) ላይ የተመሠረተ ዲጂታል ኢኮኖሚ:-
ለንግድ ግብይቶች የግለሰብ- ለግለሰብ ዲጂታል ክፍያዎች መስፋፋት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለመከታተል አስቸጋሪ ሊያደርግ ይችላል፣ ለአነስተኛ ንግዶች መደበኛ የፋይናንስ ምርቶችን የማግኘት ዕድልን ይገድባል፤ እናም የደንበኞችን ጥበቃ ሊቀንስ ይችላል።
ኢትዮጵያ እነዚህን ፈተናዎች ለመቋቋም በስትራቴጂያዊ ሽርክናዎች፣ ቀጣይነት ባለው ኢንቨስትመንት እና ሁሉን አቀፍ ዕድገት ላይ በማተኮር ሙሉ ዲጂታል አቅሟን ለመጠቀም እየጣረች ነው። ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ወደ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የሚደረገው ሽግግር በዲጂታል ዘርፍ ለፈጠራ እና ለዕድገት ያለውን የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት ያሳያል።
የሲቪል ሰርቪስ አስተዳደርን የማዘመን ሃሳብ ከዲጂታል ኢትዮጵያ ጋር ሲተሳሰር ነው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የወለደው፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት
ሚያዚያ 2017 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃው መሶብ -የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ የተበታተኑና በየፈርጁ ያሉ መንግሥታዊ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል በመስጠት ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ ምቹ ሁኔታን ይዞ መጥቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመረቁት የአንድ ማዕከል የመንግሥት አገልግሎት መስጫ አገሪቷ ሕዝባዊ አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን ስታደርግ የቆየችው ጥረት ውጤታማ መሆኑንና በዘርፉም ጉልህ እመርታ መምጣቱን የሚያመለክት ነው፡፡ ከ12 የፌዴራል መንግሥት ተቋማት የተውጣጡ ከ40 በላይ አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል እና ከወረቀት ነጻ በሆነ መንገድ በመስጠት ወደ ሥራ የገባው ማዕከሉ በአጭር ጊዜ የተቋማቱንም የአገልግሎቶቹንም ቁጥር ኣሳድጓል።
የተቋሙ አገልግሎት መጀመር መንግሥት በሕዝባዊ አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ያመጣው የዲጂታል አብዮት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ በአዲሱ የዲጂታል አብዮትም ያረጀውንና በወረቀት ሰነድና መዛግብት ተንተርሶ የቆየውን መንግሥታዊ አገልግሎት ከመሰረቱ በመቀየር በመንግሥታዊ አገልግሎት ላይ ቅልጥፍና፣ ግልጽነት፣ የተሻለ የተገልጋይ እርካታና በሕዝብና በመንግሥት መካከል የተሻለ መተማመን ለመፍጠር መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው፡፡ የአገልግሎቱ መስፋፋትና ውጤታማነት መንግሥት የተሻለ ሕዝባዊ ቅቡልነት እንዲያገኝ እንደሚያግዝ ይታመናል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫን በመረቁበት ጊዜ የአገልግሎቱ መጀመር ለኢትዮጵያ ትልቅ የምስራች እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ አንድ ሰው የመንግሥት አገልግሎት ለማግኘት ወደተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ቦታዎች ሳይጓዝ በአንድ ማዕከል አገልግሎት ማግኘቱ ጥቂት የተሳካላቸው አገራት የሚኮሩበት ውጤት ነው ብለዋል፡፡
ከለውጡ ወዲህ በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ለአገር ልማትና ለዜጎች እርካታ ወሳኝ ማነቆ ሆኖ የቆየውን ጋሬጣ በመገንዘብ፤ ችግሩን ከስሩ ለመፍታት የመንግሥትን አገልግሎት ለማሻሻልና የዜጎችን እርካታ ከፍ ለማድረግ ቃል መግባቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ አስታውሰዋል።
የመሶብ ራዕይና ውልደት
በፈጣንና ሁለንተናዊ የለውጥ ጎዳና ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የአንድ ማዕከል መንግሥታዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው “መሶብ” የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ያለመ አዲስ እና ወሳኝ ፕሮጀክት ነው። “መሶብ” የሚለው ስያሜ፤ ባሕላዊው የኢትዮጵያ ምግብ ማቅረቢያ ልዩ ልዩ የምግብ ዓይነቶች በአንድ ላይ ለተመጋቢው የሚቀርቡበት በመሆኑ አዲሱን የአንድ ማዕከል መንግሥታዊ አገልግሎት በትክክል ይገልጻል። የላቁ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በአዲሱ ትውልድ ቁርጠኛ ባለሙያዎች አገልግሎት የሚሰጥበት፣ በርካታና አስፈላጊ የመንግሥት አገልግሎቶችን በተዋሃደ፣ በተጣጣመና በተቀናጀ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
መንገድ በአንድ ጣሪያ ስር የሚሰጥ መሶብ የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል፡፡
የ”መሶብ” ዋና ዓላማዎች
ቅልጥፍናን መጨመር:-
የመሶብ ዋነኛ ዓላማ ዜጎች እና የንግድ ተቋማት ተወካዮች ቀደም ሲል የተለያዩ ቢሮዎችን በመዞር፣ ማለቂያ በሌላቸው ወረፋዎች ጊዜ በማባከንና ባረጁ የወረቀት መዛግብት ላይ ተመስርቶ በሚሰጥ አገልግሎት የሚያባክኑትን ጊዜና ጉልበት ገንዘብ ማስቀረት ይገኝበታል። መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ከወረቀት መዛግብት ይልቅ በዲጂታል መተግበሪያዎችና መፍትሔዎች በአንድ ማዕከል መስጠት ዜጎች ከመንግሥት የሚፈልጉትን አገልግሎት ቅልጥፍና በከፍተኛ ደረጃ በመጨመር የአገልግሎት ሰንሰለትን ማሳጠር ነው፡፡
ተደራሽነትን ማስፋት:-
መሶብ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ለሁሉም ዜጎች በቀላሉ ተደራሽ ማድረግን ዓላማ ያደረገ ነው። ዲጂታል መንግሥታዊ አገልግሎቶች ሲስፋፉ፣ ዜጎች ከየትኛውም ቦታ ሆነው በቀላሉ መንግሥታዊ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ ያለመ ነው።
ግልጽነትን ማምጣት:-
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዓላማ አድርጎ ከያዛቸው መካከል በመንግሥታዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ግልጽነትን መፍጠር አንዱ ነው። በዲጂታል መንገድ አገልግሎት የመስጠት አሠራር አገልግሎትን ከማቀላጠፉም በላይ የመንግሥት ቢሮክራሲ ለሙስና እንዳይጋለጥ ያደርጋል ወይም ሙስናን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
ዜጋ-ተኮር አገልግሎት መስጠት:-
ማዕከሉ አገልግሎት ፈላጊዎችን ማዕከል ያደረገ ሥርዓት መዘርጋት ዋነኛ ዓላማው፤ የዜጎችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ፣ ምላሽ ሰጪ እና አጠቃላይ እርካታን የሚያስገኝ አገልግሎት መስጠት ነው።
ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ማዕከል ያደረገ አገልግሎት አሰጣጥ:-
የመንግሥት አገልግሎቶችን በዘመናዊ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች መደገፍ ኋላቀር አሠራርን በዘመናዊና ቀልጣፋ የአሠራር ሥርዓት ለመቀየር ያግዛል። ይህ የሰነድ ምዝገባን፣ ፈቃድ አሰጣጥን፣ የታክስ ክፍያን፣ የኢሚግሬሽን አገልግሎቶችን እና ሌሎችንም በዲጂታል ሥርዓት እንዲከናወኑ ያስችላል።
ተቋማዊ ትስስር ማጠናከር:-
መሶብ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት አገልግሎቶችን ለማቅረብ የሚያስችል የተቀናጀ ሥርዓት ለመፍጠር ያለመ ነው። በመረጃ ልውውጥና በጋራ አሠራር በመታገዝ የብዙ ተቋማትን አገልግሎቶች በአንድ ጣራ ስር እንዲሰጥ ማስቻል ከዋነኛ ግቦቹ መካከል አንዱ ነው፡፡
ኢንቨስትመንትን ማበረታታት:-
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ መጀመር ለንግድና ኢንቨስትመንት ተስማሚ የሆነ ከባቢ ለመፍጠር በእጅጉ ያግዛል። አሠራሩ ከወረቀት ሰነድና መዛግብት አያያዝ የተላቀቀ፤ ቀልጣፋ የዲጂታል አገልግሎት በመሆኑ ባለሀብቶች በቀላሉ የንግድ ፈቃድ እንዲያገኙ፣ ንግዳቸውን እንዲያስመዘግቡና ከሌሎች ተቋማት ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቀሉ ማድረግ ያስችላል።
በጥቅሉ “መሶብ” የኢትዮጵያን የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ከአሮጌው ወረቀት ተኮር
መዛግብት አያያዝ እና ቅልጥፍና ከጎደለው ቢሮክራሲያዊ አሠራር በማላቀቅ፤ ቀልጣፋ፣ ግልጽ፣ ተደራሽ እና በቴክኖሎጂ የላቀ የዲጂታል አገልግሎት ሥርዓት የመፍጠር ዓላማ ያነገበ ነው። ይህም የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት ለማቃለልና የአገሪቷን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለመደገፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይታሰባል።
ቀደም ሲል በብቃት ማነስና ማለቂያ የሌለው ከሚመስል የተገልጋይ ወረፋ ጋር ስሙ ሲነሳ የኖረው የኢትዮጵያ መንግሥታዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት አሁን በስኬታማ የዲጂታል አብዮት ለውጥ ላይ ይገኛል።
መሶብ አስፈላጊ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ጣራ ሥር በማሰባሰብ፣ በቀደሙት ዘመናት ሊታሰብ የማይችል ቀልጣፋ አገልግሎት ለዜጎች በመስጠት ላይ ይገኛል። መሶብ በመሀል አዲስ አበባ በሚገኘው ዘመናዊ ሕንፃው ውስጥ በመስጠት ላይ የሚገኘው ዘመነኛና ቀልጣፋ አገለግሎት አገሪቷ በመንግሥታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለውጥ ለማምጣት ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል፡፡
የመሶብ ሥራ መጀመር ኋላቀር ቢሮክራሲያዊ አሠራሮችን በማስቀረት፣ ዜጎችን ያስቀደመ፣ ለዜጎች ምቹ አቀራረብ ያለው ቀልጣፋ መንግሥታዊ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
አገልግሎት ለሕዝብ ለማድረስ በማገዝ ላይ ይገኛል፡ ፡ መሶብ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተጓተተ አገልግሎት አሰጣጥን በመቀነስ የአሠራር ሂደቶችን ለማቀላጠፍ ያለመ ነው፡፡ ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ አድርጓል። መሶብ ግልጽነት የተላበሰ አገልግሎትን የመከተል ቁርጠኝነት ያለው ነው፡፡ ምክንያቱም ዜጎችን በመረጃ በማብቃትና የአስተያየት መስጫ ዘዴዎችን በማመቻቸት የተጠያቂነት ባሕልን ያዳብራል።
ከዚህም በላይ፤ መሶብ ቁስ አካላዊ ቦታ ብቻ ሳይሆን ለአገሪቷ መንግሥታዊ አስተዳደር የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሰፊ ራዕይ ሰንቋል። አገሪቷ ዲጂታል መፍትሄዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ማድረጓ፣
ለሌሎች አገራት ሞዴል በመሆን፣ በመንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት የመንግሥትን ቁርጠኝነት ያሳያል። ይህ ዓርአያነት የዜጎችን የኑሮ ጥራት ለማሻሻል ያለመ ሲሆን፤ የመንግሥት አገልግሎቶች ተደራሽ ብቻ ሳይሆኑ ለኅብረተሰቡ ፍላጎት ምላሽ የሚሰጡ መሆናቸውን ያረጋግጣል።
በጥቅሉ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ መጀመር ኢትዮጵያ የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን በምታደርገው ሂደት ውስጥ ትልቅ እርምጃ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። ቅልጥፍናና የዜጎችን ተሳትፎ ቅድሚያ በመስጠት ዘመኑ የዋጀውን ቴክኖሎጂ ተከትሎ የሚለወጠውን የኅብረተሰብ የአገልግሎት ጥያቄና ምኞት የሚያንፀባርቅ አዲስ የሕዝባዊ አስተዳደር ዘመን ጅማሮን ያመለክታል። ኢትዮጵያ የዕድገት ጎዳናዋን ስትቀጥል፣ መሶብ ለተጨማሪ አካታችና በቴክኖሎጂ የላቀ የወደፊት አገልግሎት ተስፋን ማብሰሩን ይቀጥላል።
አዲሱ የአንድ ማዕከል መንግሥታዊ አገልግሎት መሶብ - ወጥነት ያለው፣ ተደራሽና ዜጋን ያማከለ የመንግሥት አገልግሎት መስጫ እንደመሆኑ ራዕዩ የተበታተኑ አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር በአካልም ሆነ በዲጂታላዊ መልኩ ማጠናከር በመሆኑ የተበታተኑ እና ኋላቀር የአሠራር ሂደቶችን ዘመኑ ባፈራው ቴክኖሎጂ ይተካል።
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በቅርቡ እንደተናገሩት 23 ተቋማት 124 አገልግሎቶችን በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመንና የመልካም አስተዳደር ቅሬታዎችን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችል ሪፎርም በማጠናከር ላይ እንደምትገኝ፤ በተለይም የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመጀመር ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በ2018 ዓ.ም ሁሉም ክልሎች ቢያንስ አንድ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል እንዲኖራቸው ይደረጋል፡፡
ኢትዮጵያ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመንና የመልካም አስተዳደር ቅሬታን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችለውን ሪፎርም በሦስት ምዕራፎች በማከናወን በመጀመሪያው ስምንት፣ በሁለተኛው ዘጠኝ እንዲሁም በሦስተኛው ሰባት
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ተቋማት ላይ ሪፎርሙ ተፈፃሚ ይሆናል ብለዋል ኮሚሽነሩ። በሁሉም ምዕራፎች የዝግጅት፣ የትግበራና የማጽናት ምዕራፎች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ በመጀመሪያው የሪፎርም ሙከራ ትግበራ ወደ ተግባር ምዕራፍ እየተገባ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርሙ ትኩረቱን የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን ላይ አድርጓል።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ መንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን ትልቅ እመርታ ካሳዩት መካከል አንዱ የሆነው የመሶብ የአንድ ማዕከል የመንግሥት አገልግሎት (Mesob - Ethiopia’s One Stop Government Service Center) በተገልጋዮች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን እያገኘ ሲሆን የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይታሰባል፡፡
አዲሱ የአገልግሎት አብዮት በተገልጋዮች አንደበት
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከዚህ ቀደም ያጋጥሙ የነበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመቅረፍ፣ ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበታቸውን በእጅጉ እንደቆጠቡ የገለፁ ተገልጋዮች ጥቂቶቹ እንዲህ ይላሉ።
ኩራ መኮንን ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከመጣ በኋላ በሰጠው አስተያየት
እንዲህ ብሏል። “ፓስፖርት ለማደስ ነው የመጣነው፡፡ መጀመሪያ የሄድነው እንደለመድነው የላይኛው ኢሚግሬሽን ነበር፡፡ እዚያ ውጣ ውረዶች ነበሩ፤ ወረፋና ብዙ ሰው ነበር፡፡ ሠራተኞቹ ናቸው ወደዚህ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንድንመጣ የጠቆሙን፡፡ ምክራቸውን ሰምተን ነው ወደዚህ የመጣነው፡፡ እዚህ ስንመጣ ያገኘነው መስተንግዶ በጣም ቀልጣፋና የሚያስደስት ነው” ኩራ ቀደም ሲል የነበረውን የቢሮክራሲ ችግር በጉልህ አንስቷል፡ ፡ ይህ በሌሎች ተገልጋዮችም ዘንድ የሚነሳ ችግር ሲሆን የመሶብ ማዕከል መፍትሄ ሆኖ መጥቷል፡፡
“በመጀመሪያ እንደ ድሮው መስሎኝ የሄድኩት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነበር፡፡ ከዚያ እዚህ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደሚሰጥ በሚዲያ ሰምቼ ነው የመጣሁት፡፡ እዚህ ስመጣ ሁሉንም መሠረታዊ መንግሥታዊ አገልግሎት በአንድ ቦታ ነው ያገኘሁት፡፡ በበፊቱ አሠራር ያልተሟላ ሰነድ ሲኖር ወይም የተሳሳተ ነገር ሲኖር ወደ ሌላ የአገልግሎት ተቋም ሄዶ ማስተካከል ያስፈልግ ነበር፡፡ ይህም በጣም አታካችና አድካሚ ነበር፡፡ እዚህ ግን ያ ሁሉ አያስፈልግም፡፡ ሁሉም አገልግሎት በአንድ ላይ ይሰጣል፡፡ ከግራውንድ ፍሎር አንስቶ ሁሉንም አይነት አገልግሎት በሁሉም ፎቆች ላይ ይሰጣል፡፡ እንደበፊቱ ክፍያ ለመክፈል ባንክ ድረስ ሄደህ ስሊፕ ማምጣት አይጠበቅብህም፡፡ በእጅ ስልክህ ትከፍላለህ፡፡ ለፎቶ ኮፒም አትንከራተትም፡ ፡ ስካን ለማስደረግም እዚያው ቆመህ በእጅ ስልክህ ስካን አድርገህ ከሰነድህ ጋር ማያያዝ ትችላለህ፡፡ አገልግሎቱ ይህንን በመሳሰሉ ዲጂታል አገልግሎቶች የሚደገፍ በመሆኑ ቅልጥፍናው ሲበዛ ተሻሽሏል፡ ፡ ይህንን የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመከፈቱ መንግሥትን ማመስገን እፈልጋለሁ” ያለው ደግሞ ዮናስ ታደሰ ነው።
አክሎም “ይህ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ በመከፈቱ በመንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በአንዳንድ አገልግሎት ሰጪዎች ይስተዋሉ ከነበሩ ብልሹ አሠራሮች የፀዳ አገልግሎት ማግኘት ችለናል። ዶክመንት ፎቶ ኮፒ አድርገህ አምጣ፣ ስካን አስደርገህ ና የሚሉ አሰልቺና አታካች፣ ጊዜ የሚወስዱና ልብ የሚያዝሉ አሠራሮች ተቀይረው በዲጂታልና በኮምፒውተር የተደገፈ አሠራር ሆኗል፡፡ ዛሬ ዶክመንት ስካን ማድረግ ካለብህ ስካን አድርገህ ራስህ ኦንላይን ገብተህ ማያያዝ ትችላለህ፡፡ ስህተት ካለም አገልግሎት ሰጪዎቹ እንድታስተካክለው ግብረመልስ ይሰጡሃል፡፡ ይህ አሠራር በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ብልሹ አሠራሮችን ሙሉ በሙሉ ያስቀራል ብዬ አስባለሁ” ሲል የመሶብ ማዕከልን የፀረ-ሙስና አስተዋፅኦ አድንቋል፡፡
የዮናስን አስተያየት የሚጋራው ሌላው ተገልጋይ ዳዊት ጳውሎስም ይህ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጊዜን እንዴት እንደሚቆጥብና እንግልትን እንደሚቀንስ ምስክርነቱን እንዲህ ገልፆታል።
“ጓደኞቼ ከሁለት ዓመት በፊት የዶክመንታቸውን ትክክለኝነት አረጋግጠው ነበር፡፡ እነርሱ እንደነገሩኝ አገልግሎቱ የሚሰጠው በሣምንት ሁለት ቀን ብቻ ነበር፡፡ ያውም ቅልጥፍና የጎደለው አሠራር ተጨምሮበት አገልግሎቱ እልህ አስጨራሽ ነበር፡፡ ዛሬ ወደዚህ ስፍራ ስመጣ እንደ ድሮው የተጓተተ አገልግሎት አሰጣጥ እንደሚኖር ጠርጥሬ፣ ምናልባትም አገልግሎቱ የማይሰጥበት ቀን ሊሆን እንደሚችል ገምቼ ነበር፡፡ ይሁንና አሁን በጣም ተቀይሯል፡፡ እኔ ዛሬ መጥቼ ዶክመንቴን
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
አውተንቲኬት ለማስደረግ የፈጀብኝ ጊዜ ሁለት ሠዓት እንኳን አይሞላም፡፡ ሁሉም ነገር በፍጥነትና ምቾትን በማይነሳ መንገድ ነው ያለቀው”
የዳዊት እማኝነት የመሶብ ማዕከል ያመጣውን የአገልግሎት ፍጥነትና ቅልጥፍና ያሳያል፡፡ ቀድሞ ቀናትና ሣምንታት ይወስዱ የነበሩ አገልግሎቶች አሁን በጥቂት ሠዓታት ውስጥ እንደሚጠናቀቁ አስረግጦ ተናግሯል፡፡
የተገልጋዮቹ አስተያየት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተቀናጀ እንደሆነና የዲጂታል መሠረተ ልማቱን በመጠቀም በርካታ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር ማግኘቱ ለተገልጋዮች ትልቅ እፎይታ እንደሆነ ያሳያል።
የማዕከሉ አስተባባሪ ሣራ ዳንኤል፤ ይህ የአሠራር ለውጥ እንዴት እንደተመቻቸ እንዲህ ትገልፃለች፡፡
“አስቀድሞ የነበረው አሠራር በተበታተኑ ተቋማት፣ ቅልጥፍና በጎደላቸው፣ ጊዜ በሚገድሉና ባረጁና ባፈጁ የወረቀት ማኅደሮች ላይ የተንጠለጠለ ነበር፡ ፡ በመሆኑም አገልግሎት ፈላጊዎች ጉዳያቸውን ለመጨረስ ወደ ተለያዩ ሕዝባዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት በመሄድ ከአንድ ቢሮ ወደሌላ ቢሮ መንከራተትና ተደራራቢ በሆኑ ወረፋዎች መንገላታት ይገጥማቸው ነበር፡፡ ለምሣሌ አንድ ሰው ሦስትና አራት መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ቢፈልግ እንደ ቀድሞው በተራራቁ የአገልግሎት መስጫዎች ለእያንዳንዱ ጉዳይ ወረፋ እየያዘ፣ ለተራዘሙ ሣምንታት ጊዜና አዕምሮው ተይዞ፣ ሥራ ፈትቶ መንገላታት አይጠበቅበትም፡፡ እዚሁ እኛ ጋር መጥቶ የሚፈልጋቸውን መንግሥታዊ አገልግሎቶች በሙሉ ከአንድ መስኮት ወደ ሌላ መስኮት እየሄደ ቀድሞ ወራት ይፈጅበት የነበረውን ጊዜ በሠዓታት መጨረስ ይችላል”ማውረድ ይችላል፡ ፡”
በቀደመው ጊዜ አሠራር አንድ ደንበኛ ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ለማቋቋም ቢፈልግ ወደተለያዩ መሥሪያ ቤቶችና ቢሮዎች ተዟዙሮ የሚጨርሰው የነበረው ጉዳይ በመሶብ ከቢሮ ወደ ቢሮ በዲጂታል እየተዘዋወረ፤ ገቢዎችም ሆነ ሰነዶች ወይንም ንግድና ቀጠናዊ ትስስር መሥሪያ ቤቶች መሄድ ሳያስፈልገው ሁሉንም ጉዳዮቹን ሲስተም ላይ ጨርሶ መሄድ ይችላል፡፡ ይህን ለማድረግም ምንም አይነት የወረቀት ሰነዶችን ይዞ መንከራተት አይጠበቅበትም እንደ ማዕከሉ አስተባባሪ ገለፃ።
የመሶብ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጠቀሜታዎች
የአንድ ማዕከል የመንግሥት አገልግሎት ማዕከላት ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ ለኢንቨስትመንት መስፋፋት፣ ለንግድ ስኬት እና ለመንግሥት ወጪ ቅነሳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ይታመናል፡፡
የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን ለዜጎች ምቹ ከማድረግ ባለፈ የአንድን አገር አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡ የመሶብ አይነት የመንግሥት አገልግሎት ማዕከላት (One Stop Government Service Centers) መቋቋም በተለይ ኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት ባስመዘገበችው የዲጂታል የለውጥ ስትራቴጂ ውስጥ ቁልፍ ከሆኑ እርምጃዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ እነዚህ ማዕከላት ለኢንቨስትመንት መበረታታት፣ ለንግድ ቅልጥፍና፣ ለአጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ዕድገት እንዲሁም ለመንግሥት ወጪ ቅነሳ ጉልህ ፋይዳዎች አሏቸው፡፡
ለኢንቨስትመንት እና ለንግድ መበረታታት ከሚኖረው አስተዋጽኦ አንፃርም ቀደም ሲል አንድ ባለሀብት ወይም ነጋዴ ኢንቨስትመንት ለመጀመር ወይም የንግድ እንቅስቃሴ ለማድረግ የተለያዩ የሥራ ፍቃዶችን ለማግኘት ወደ በርካታ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መሄድ፣ ተራ መጠበቅና ጊዜ ማጥፋት ይኖርበታል፡፡ ይህ አሠራር ኢንቨስትመንትን የሚያጓትትና የንግድ ሥራ መጀመርን የሚያወሳስብ ነው፡፡
የአንድ ማዕከል አገልግሎት ግን እነዚህን ሁሉ አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር በማሰባሰብ ሂደቱን በእጅጉ ያቀለዋል፡፡ ኢንቨስተሮች ንግዳቸውን ለመመዝገብ፣ ፍቃድ ለማግኘት፣ ግብር ለመክፈልና ሌሎች አስፈላጊ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህ የአሠራር ሂደት ቅልጥፍና የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኛል፡፡
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ጊዜና ጉልበት ቁጠባ፡-
ባለሀብቶችና ነጋዴዎች ቀደም ሲል በተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትና ቢሮዎች ያጠፉ የነበረውን ጊዜና ጉልበት በመቆጠብ ይባክን የነበረውን ጊዜ ለምርታማ ሥራዎች እንዲያውሉ ያስችላቸዋል፡፡ ጊዜ ገንዘብ ነውና ይህ በቀጥታ ለኢኮኖሚው ዕድገት አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
የአሠራር ግልጽነትና ተጠያቂነት፡-
ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ቦታና በዲጂታል ሥርዓት መከወን፣ ሙስናን የመቀነስና የአሠራር ግልጽነትን የመጨመር ዕድል ይፈጥራል፡፡ ይህ ደግሞ ለባለሀብቶች እምነት የሚጣልበትና አስተማማኝ የኢንቨስትመንት ከባቢ ይፈጥራል፡፡
የንግድ ሥራ መጀመሪያ ወጪ ቅነሳ፡-
የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና ለንግድ ሥራ
መጀመር የሚወጣውን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ወጪ ይቀንሳል፡፡ ይህም አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች እንዲፈጠሩና የንግድ ሥራዎች እንዲስፋፉ ያበረታታል፡፡
አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ማሳደግ፡-
የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ አዎንታዊ ነው፡፡ ለአብነትም፡-
የሀብት ምደባ ቅልጥፍና፡-
ዜጎችና የንግድ ተቋማት የመንግሥት አገልግሎት ለማግኘት የሚያጠፉትን ጊዜና ሀብት ሲቀንስ፣ እነዚያን ሀብቶች ለሌሎች ምርታማ ተግባራት እንዲውሉ ያስችላል፡፡ ይህ ለአገር ውስጥ ምርት ዕድገት አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
የኢንተርፕራይዞች ዕድገት፡-
በተቀላጠፈ አገልግሎት የተነሳ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች እንዲፈጠሩና ያሉትም እንዲያድጉ ያበረታታል፡ ፡ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በቀላሉ የንግድ ፈቃድ ማግኘት ሲችሉ ለአገር ውስጥ ገበያ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡
ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ይጨምራል፡-
ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት የአንድን አገር የንግድ ሥራ የመሥራት ምቹነት (Ease of Doing Business) ደረጃን ያሻሽላል፡፡ ይህ ደግሞ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን (Foreign Direct Investment) ለመሳብና የአገርን ኢኮኖሚያዊ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ወሳኝ ነው፡፡
የመንግሥት ወጪ ቅነሳ፡-
የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ለመንግሥትም ከፍተኛ ወጪ ቅነሳ ያስገኛሉ፡፡
ወረቀት አልባ አሠራር፡-
በወረቀት መዛግብት ላይ የተመሰረተውን አታካች አሰራር በዲጂታል መተካት፣ ወረቀት ለመግዛት፣ ለማተም፣ ለማከማቸትና ለማጓጓዝ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም ለሰነድ ማኅደርነት የሚያገለግሉ ቦታዎችን ይቀንሳል፡፡
የሰው ኃይል ቅልጥፍና፡-
ዲጂታል ሥርዓቶች የሰው ኃይል በሚጠይቁ የሥራ ሂደቶች ላይ የሚፈጀውን ጊዜ ስለሚቀንሱ የመንግሥት ሠራተኞች ለሌሎች ምርታማ ተግባራት እንዲመደቡ ያደርጋል፡፡ ይህም የሰው ኃይል አጠቃቀም ቅልጥፍናን ያሻሽላል፡፡
ሙስና እና ብልሹ አሠራር ቅነሳ፡-
ሙስና መንግሥት ከፍተኛ ገቢ እንዲያጣ ከሚያደርጉ ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ የዲጂታል አሠራር ግልጽነትን ስለሚያሰፍን፣ የሙስና አደጋን በመቀነስ ለመንግሥት ገቢ ማሰባሰብ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
በአጠቃላይ የመሶብ አይነት የአንድ ማዕከል የመንግሥት አገልግሎት ማዕከላት መቋቋም ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገትና ብልጽግና ወሳኝ እርምጃ ነው፡፡ እነዚህ ማዕከላት የኢንቨስትመንትና የንግድ ከባቢን ከማሻሻል፣ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ከማሳደግና የመንግሥትን ወጪ ከመቀነስ ባሻገር የዜጎችን የመንግሥት አገልግሎት እርካታ በማሳደግ መልካም አስተዳደርን እውን ያደርጋሉ፡፡
ዓለም አቀፍ መነሻዎች
የመሶብ- የአንድ ማዕከል ፅንሰ ሃሳባዊ መሠረት የተመሠረተው በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ ከሆኑ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
የአንድ-ማዕከል አገልግሎት ሞዴሎች በመነሳት ነው፡፡ ይህም ዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለኢትዮጵያ ልዩ ሁኔታ በመቀመር ውጤት ለማምጣት የተሄደበትን ርቀት የሚያሳይ ነው፡፡
መሶብ - የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከመነደፉ በፊት መንግሥት ስኬታማ ከሆኑ አገራት ተሞክሮ ለመውሰድ በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ፈጠራ የታከለባቸው አቀራረቦችን በመተግበር በሚታወቁ በርካታ አገራት አሠራሮች ላይ ሰፊ ጥናት አድርጓል። ይህ ጥልቅ ምርምር የኢትዮጵያን አስተዳደር ቅልጥፍና እና ውጤታማነት ለማሳደግ ሊተገበሩ የሚችሉ የተለያዩ አገራት ተሞክሮዎችን ለማግኘት አስችሏል።
ኤስቶኒያ፡-
አገሪቷ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን በከፍተኛ ደረጃ በማስፋት ትታወቃለች፡፡ ከሕዝቧ 99 በመቶ የሚሆነው መንግሥታዊ አገልግሎቶችን የሚያገኘው በዲጂታል አማራጮች ነው፡፡ የአገሪቷ ዜጎች ደህንነቱ በተጠበቀ የኤሌክትሮኒክ መታወቂያ (e-ID) ሥርዓት አማካኝነት ከመንግሥታቸው የሚፈልጉትን ማንኛውም ሕዝባዊ አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ ይህም የመንግሥትና ሕዝብን የግንኙነት መዋቅር ቀላልና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን አስችሏል። ይህ የአሠራር ሞዴል አስቀድሞ የነበረውን መንግሥታዊ የቢሮክራሲ ውጣ ውረዶች በእጅጉ መቀነስ አስችሏል፡፡ በዚያ የተነሳም የዜጎችን እርካታ በከፍተኛ ደረጃ ለመጨመር አስችሏል፡፡ ይህም በሕዝባዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ የዲጂታል የአገልግሎት አሰጣጥ መፍትሄዎች የሚያስገኙትን ጥቅም ያሳያል።
ሩዋንዳ፡-
የሩዋንዳው ኢሬምቦ ፖርታል ሌላው አነቃቂ ሞዴል ነው፡፡ ሲስተሙ ከ100 በላይ የሩዋንዳ የመንግሥት አገልግሎቶችን በኢንተርኔት መስመር ይሰጣል። መንግሥታዊ ዲጂታል አስተዳደርን በተመለከተ ኢሬምቦ በአፍሪካ ትልቅ ተምሣሌት መሆን ችሏል፡፡ ሩዋንዳ በቴክኖሎጂ ለታገዘ መንግሥታዊ አገልግሎት አሰጣጥ የሰጠችውን ብርቱ ትኩረት የሚያሳየው ፖርታሉ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን የበለጠ ተደራሽ በማድረግ ዜጎችን ከማገልገሉም በላይ በመንግሥት አሠራር ላይ ግልጽነት እና ተጠያቂነትን ማሳደግ አስችሏታል።
ሲንጋፖር፡-
በደቡብ ምስራቅ እስያ፣ የሲንጋፖር OneService መተግበሪያ ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ማዕከላዊ መድረክ ሆኖ ያገለግላል፣ ይህም ነዋሪዎች ችግሮችን እንዲያሳውቁ፣ መረጃ እንዲያገኙና ከየአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት ጋር በቀጥታ እንዲገናኙ በማስቻል ላይ ይገኛል። የሲንጋፖር መንግሥታዊ አገልግሎቶች በአንድ መተግበሪያ መቀናጀት በመንግሥትና በዜጎች መካከል ያለውን ግንኙነት በማቀላጠፍ፣ ምላሽ የመስጠት አቅምን በማሳደግና የማኅበረሰብ ተሳትፎን በማዳበር ረገድ በከፍተኛ ደረጃ ውጤታማ ሆኗል። በዓለም ላይ በምሣሌነት ከሚጠቀሱት መካከልም አንዱ ለመሆን ችሏል፡፡
ሞንጎሊያ፡-
በተመሳሳይ የሞንጎሊያ መንግሥት የአንድ-ማዕከል መንግሥታዊ አገልግሎት እ.አ.አ ከ2007 ጀምሮ የተቋቋመ ሲሆን የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ትምህርትን፣ ጤና አጠባበቅን የጡረታ መርሃግብርን ያካትታል፡፡ ይህም የአገሪቷ ዜጎች አስፈላጊ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በማገዝ ረገድ የሄደበትን ርቀት ያሳያል፡፡
የእኛ መሶብ
ኢትዮጵያ የጀመረችው መሶብ የአንድ ማዕከል
መንግሥታዊ አገልግሎት በዘርፉ የተገኙ ዓለም አቀፍ ስኬቶችን በምሣሌነት ይወስዳል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ እሴቶችና ባሕላዊ አውዶችን ታሳቢ በማድረግ የተመሠረተ ነው። መሶብ ዓለምአቀፍ ተሞክሮዎችን በትምህርትነት ቢወስድም በኢትዮጵያ ሁኔታ የተቃኘ የአካባቢያዊ ጠቀሜታና የማኅበረሰብ ተሳትፎን አስፈላጊነት ያጎላ ሆኖ ነው የተደራጀው።
መሶብ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ከኢትዮጵያ ሁኔታ፤ ፍላጎት እና ጥልቅ ግንዛቤ ጋር በማቀናጀት ልዩ ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ ሞዴል ለመፍጠር ያለመ ነው። ተነሳሽነቱ የመንግሥት አገልግሎቶችን ማዘመን ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ምኞት እና እሴቶች ጋር እንዲጣጣሙ ለማድረግ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው። የመሶብ - የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዓለም አቀፍ መነሻን በአገራዊ መንገድ የመቃኘት አስተሳሰብን ለማምጣት የተደረገው ጥረት በመንግሥት አስተዳደር መስክ ግንባር ቀደም ጥረት ያደርገዋል፡፡ አሠራሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሌሎች አገራት ለመኮረጅ የሚመኙት አዲስ ተምሣሌት ሊሆን የሚችል መንግሥታዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በጥቅሉ ኢትዮጵያ የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በመማር የራሷን ባሕላዊ ማንነት በመጠበቅ፣ የሕዝብ አገልግሎት ገጽታን እንደገና ለመወሰን ተዘጋጅታለች። መሶብ የአስተዳደርን የወደፊት ዕጣ ለመቅረጽ የትብብር ትምህርትና ፈጠራ ኃይል ማሳያ ሆኖ ቆሟል፡፡ ይህም መንግሥት ለዜጎቹ ይበልጥ ቀልጣፋ፣ አካታች እና ምላሽ የሚሰጥ እውነተኛ አገልግሎት እንዲሰጥ መንገድ ይከፍታል።
ከመለኪያ በላይ የሆኑ ጥቅሞች
ጊዜ፣ እምነት እና የኢኮኖሚ ዕድገት፡- የመሶብ የቅርብ ጊዜ ጥቅሞች ተጨባጭ እና ሰፊ ናቸው። ቀደም ሲል በርካታ ቢሮዎችን መጎብኘትና ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ሠዓታት እና ሣምንታት የሚጠይቁ የአገልግሎት ጥያቄዎች አሁን በአንድ ምቹ ቦታ ይከወናሉ። እነዚህም እንደ ብሔራዊ መታወቂያ እና ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎቶች፣ የሰነድ ማረጋገጫ፣ የገቢዎች፣ የንግድና ቀጣናዊ ውህደት፣ የሥራና ክህሎች ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና ፈተና አገልግሎት፣ ኢትዮ-ፖስት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ- ቴሌኮም ያሉ ወሳኝ ጉዳዮችን ያጠቃልላሉ።
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፤ የመሶብ ማዕከል አሁን በ23 ተቋማት በኩል 124 ወሳኝ የአገልግሎት ዓይነቶችን እየሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በመጪው አዲሱ የኢትዮጵያዊያ ዓመት (2018 ዓ.ም) ሁሉም ክልሎች ቢያንስ አንድ የመሶብ ማዕከል እንዲኖራቸውም ታቅዷል።
በአገልግሎት አሰጣጥ አዲስ ምዕራፍ
በመሶብ ማዕከል የሚሰጡ አገልግሎቶች የተለያዩና ወሳኝ የሚባሉ ናቸው። በመሆኑም የዜጎችን ሰፊ ፍላጎት ያሟላሉ። ከብሔራዊ መታወቂያና ፓስፖርት ማግኘት ጀምሮ የንግድ ምዝገባ፣ ግብር መክፈልና የተለያዩ የትምህርትና የፋይናንስ አገልግሎቶች ማዕከሉ እውነተኛ “አንድ ማዕከል” እንዲሆን ታስቦ የተሰራ ነው። የተቀናጀ የዲጂታል ግንኙነት ላይ የተሰጠው ትኩረት እንከን የለሽ አገልግሎት አሰጣጥን በማረጋገጥ የወረቀት
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ሥራን በመቀነስ ቅልጥፍናን ከፍ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።
መሶብ ኢትዮጵያ ለዜጎች አገልግሎት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ምልክት ነው። ኢትዮጵያ የዲጂታል ለውጥን በመቀበልና ምላሽ ሰጪ የመንግሥት አስተዳደር ባሕልን በማጎልበት፤ ቀድሞ በሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይስተዋል የነበረውን ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ከመቅረፍ ባሻገር ለወደፊት የሕዝብ አገልግሎቶች የዜጎችን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ፣ ቀልጣፋና ግልጽነትን ታሳቢ ያደረጉ አሠራሮችን ለመገንባት መሠረት የተጣለበት ነው። አገሪቷ ይህን የሙከራ ፕሮጀክት ማስፋፋቷን ስትቀጥል፤ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የበለጠ ተደራሽና አጥጋቢ አገልግሎት የመስጠት ቃል-ኪዳን ወደ ተጨባጭ ተግባር የተሸጋገረበት ነው።
ከራዕይ ወደ እውነት – ለአገልግሎት አዲስ ደረጃ
ከአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ እና ከሰፊው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተወለደው መሶብ፤ ዜጎች ለረጅም ጊዜ በሥርዓት መቆራረጥና ምላሽ በማይሰጥ ቢሮክራሲ ሳቢያ ለነበሯቸው ቅሬታዎች ቀጥተኛ ምላሽ ነው። እንከን የለሽና የተቀናጀ አገልግሎት በማቅረብ በመንግሥት አገልግሎቶች ላይ የሕዝብን እምነት ከፍ ለማድረግና ይበልጥ አሳታፊ የሆነ የዜግነት አገልግሎት ለማዳበር ያለመ ነው።
መሶብ በአገር ውስጥ በተገነቡ የሶፍትዌር ሥርዓቶች የተደገፈ በመሆኑ መረጃ በብሔራዊ ሥልጣን ሥር እንዲቆይ ከማድረጉ በላይ በኢትዮጵያ ዲጂታል መሠረተ ልማት ላይ እያደገ የመጣውን አቅም ያሳያል። የተጠቃሚ በይነገጽ (user interface) በቀላሉ ለመጠቀም እንዲቻል ተደርጎ በመሠራቱ ዜጎች አገልግሎቶችን ያለልፋት እንዲጠቀሙ ያስችላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የጀርባው ሥርዓት (backend) ለደህንነት ተብሎ የተገነባ ሲሆን፣ ሥርዓቱ ለወደፊት ፍላጎቶች መላመድ የሚችልና አስፈላጊ መረጃዎችን የሚጠብቅ መሆኑን ያረጋግጣል።
ከአካላዊ ቦታ በላይ የሆነው መሶብ፤ የተለያዩ የመንግሥት አገልግሎቶች የሚሰባሰቡበት፣ የሚገናኙበትና ዜጎችን በተሟላ መልኩ የሚያገለግሉበት ተለዋዋጭ መድረክ ሆኖም ያገለግላል። ይህ የተቀናጀ አቀራረብ የሥራ መደራረብን የሚቀንሱና የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያሻሽሉ ሂደቶችን ያቀላጥፋል። ማዕከሉ ኢትዮጵያ ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ለሕዝብ ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ መንግሥት እንዲኖር ያላትን ራዕይ ያሳያል።
በመሶብ የሚሰጡ አገልግሎቶች ሰፊ፣ የማኅበረሰቡን የተለያዩ ፍላጎቶች ያሚያሟሉ ናቸው። በሠለጠኑ ባለሙያዎች በተያዘው በእያንዳንዱ የአገልግሎት መስጫ ጠረጴዛ የሚበዙቱ ወጣቶችና ራሳቸውን ከዘመኑ ጋር የሚያስተሳስሩ በመሆናቸው የኢትዮጵያን ንቁ የሰው ኃይል እና የወጣቶችን አቅም የማጎልበት ቁርጠኝነት ያንፀባርቃሉ።
ይህ ተነሳሽነት የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ብቻ አይደለም፤ የፈጠራ እና አካታችነት መንፈስን ያካተተ እንጂ። መሶብ ለሁሉም ዜጎች ተደራሽነትን እና ክብርን መሠረት ያደረገ የወደፊት ሁኔታን ለማሳካት የገባ እርምጃን ይወክላል። ምላሽ የመስጠትና የቅልጥፍና ባሕልን በማዳበር
በኢትዮጵያ የንግድ ሥራ ምቹነት ደረጃን ለማሻሻልና ታሪካዊ በሆነ መልኩ የአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንትን ተስፋ የሚያስቆርጡ ቢሮክራሲያዊ ውጣ ውረዶችን ለመቀነስ ካላት ቁርጠኝነት ጋርም ይጣጣማል።
10ኛው የሲቪል ሰርቪስ ቀን “የሲቪል ሰርቪስ ተቋማትን ቅልጥፍና እና ጽናትን በማሳደግ በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን መሙላት” በሚል መሪ ሀሳብ በአፍሪካ ሕብረት መሶብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የአሠራር ባሕል ለውጥና ተጨባጭ ውጤት እያመጣች መሆኑን ገልፀዋል።
ማጠቃለያ
በእርግጥም የመሶብ የአንድ ማዕከል የመንግሥት አገልግሎት መቋቋም በኢትዮጵያ ዲጂታል ሽግግር ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ማዕከል መንግሥት ለዜጎቹ የሚሰጠውን አገልግሎት ደረጃ ከፍ በማድረግ፣ የመንግሥት ተቋማትን ቅልጥፍና በማሳደግ፣ የሕዝብን እርካታና እምነት በማጎልበት ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ይህ ታላቅ ራዕይ በቀጣዮቹ አስርት ዓመታት የኢትዮጵያን የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ገጽታ ሙሉ በሙሉ እንደሚለውጠው ይጠበቃል።
መሶብ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ስኬት መገለጫ እንደመሆኑ፤ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ከባሕላዊው አሠራር ወደ ዘመናዊና ዲጂታል መድረክ በማሸጋገር ረገድ ግንባር ቀደም ነው። ቀደም ሲል የነበሩትን ውስብስብ፣ አድካሚና ጊዜ የሚወስዱ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች በማቅለል፣ ዜጎች በአንድ ቦታ የተለያዩ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀላሉ፣ በፍጥነትና ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲያገኙ አስችሏል። በቀጣዮቹ ደግሞ ዜጎች ቀለል ላሉ መንግሥታዊ አገልግሎቶች ከቢሮ ቢሮ መንከራተታቸው ይቀርና የሚበዙትን አገልግሎቶች ጣቶቻቸውን በእጅ ስልኮቻቸው ላይ በማሳረፍ እንዲወሰን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም በዲጂታል መድረኩ የሚፈጠረው ግልጽነት የሙስና አድማስን በማጥበብ ለፍትሃዊና ተደራሽ አገልግሎት በር ይከፍታል። የሕዝብ አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮግራሙ ዋነኛ ግብ የሆነው የመንግሥትና የሕዝብ ግንኙነት መሻሻል በመሶብ አማካኝነት እውን ይሆናል። ይህም በቀጣዮቹ ዓመታት የመንግሥትን ገጽታ ከመሠረቱ ይለውጠዋል።
መሶብ የኢትዮጵያን ዘመናዊነትና አጠቃላይ ልማት የሚያፋጥን ቁልፍ ምሰሶ ነው። የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመንግሥት አገልግሎቶችን ማዘመን፣ አገሪቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆንና የዜጎቿን የኑሮ ጥራት እንድታሻሽል ያደርጋል።
ይህ የዲጂታል ለውጥ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ጎዳና በመምራት ዓለም አቀፍ የዲጂታል ኢኮኖሚ አካል እንድትሆን የሚያግዝ ነው። ለበለፀገች፣ ለዘመነችና ለዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ብሩህ ተስፋ የሚሰጥ ነው። በቀጣይ መሶብ በኢትዮጵያ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሥር-ነቀል ለውጥ በማምጣት ለዜጎች የተሻለ ነገን የሚፈጥር ታላቅ ተቋም ሆኖ ይቀጥላል።
ኢኮኖሚ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያን ማሳያ
ሌላኛው መንገድ - ማይስ
በቆንጂት ተሾመ
አዲስ አበባ አዳዲስ ውብ መልኮችን እየተላበሰች የምትገኝ ከተማ ሆናለች፡፡ ከተማይቱን እንደ ስሟ አዲስ የሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች በፍጥነት እየተገነቡ መታየት ችለዋል፡፡ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ እንደ እንጦጦ ፓርክ፣ አንድነት ፓርክ፣ የወዳጅነት አደባባይ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ያሉ በመንግሥት የተገነቡ ፕሮጀክቶች ለአዲስ አበባ አዳዲስ ውበትን ጨምረውላታል፡፡
በመዲናዋ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ አሁን ላይ በመንግሥት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች አገሪቷ የነበራትን ገጽታ በመልካምነት አጉልተው ከማሳየት ባሻገር ትርጉም እንዳላቸው መናገር ይቻላል፡፡
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ምንም አይነት ጠቀሜታ የሌላቸው… ለጥቂት ጊዜ ታይቶ የሚጠፋ ውበትን ብቻ የተጎናጸፉ የመዝናኛ መዳረሻዎች አይደሉም፡ ፡
ፕሮጀክቶቹ የከተማንና የአገርን መልካም ገጽታ ከማንጸባረቅ በተጨማሪ ለዜጎች የሥራ ዕድሎችን መፍጠራቸው ግልጽ እውነታ ነው፡፡ የተፈጠሩት የሥራ ዕድሎች ኑሮን ለማሸነፍ ለሚጥሩቱ ጥሩ የገቢ ምንጭ መሆን ችለዋል፡፡
በረጅም ጊዜ ዘለቄታዊ ጥቅሞችን የሚያስገኙ መሆናቸውን ግን በተገቢው መጠን መረዳት ያሻል፡፡ ይበልጡንም አዲስ አበባ የቱሪዝም ኮንፍረንስ ማዕከል እንድትሆንና ከዘርፉ የላቀ ገቢ እንዲገኝ ትልቅ አበርክቶ አላቸው፡፡ ይህንን ታሳቢ በማድረግ የተሰሩ ስለመሆናቸውም መናገር ይቻላል፡፡
ማይስ - ኢዲሱ የቱሪዝም አቅም
ቱሪዝም በሁለት ዋና ዋና ዘርፎች ተለይቶ ይገለጻል፡፡ ይኸውም ቢዝነስ ቱሪዝም እና ሌግዠሪ ቱሪዝም በመባል ይታወቃሉ፡ ፡ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ተዘዋውሮ መጎብኘት ከሌግዠሪ ቱሪዝም ሲመደብ፤ ኮንፈረንስ ቱሪዝም የሚጠቃለልበት ቢዝነስ ቱሪዝም ደግሞ ሌላኛው ዘርፍ ነው፡፡
የተለያዩ አህጉዊና ዓለምአቀፋዊ ጉባዔዎችን በማስተናገድ አገልግሎት - ኮንፍረንስ ቱሪዝም ውስጥ ደግሞ ማይስ ቱሪዝም ተፈጥሯል፡፡ በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል
ማይስ (MICE) ተብሎ ይጠራል፡፡ Meet- ings, Incentives, Conferences and Exhibitions ማለት ነው፡፡
የማይስ ቱሪዝምን በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅና ዘርፉ ራሱን ችሎ በተቋም እንዲመራ ከፍተኛ ጥረት ካደረጉ ባለሞያዎች መካከል የኦዚ ቢዝነስና ሆስፒታሊቲ ግሩፕ መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቁምነገር ተከተል አንደኛው ናቸው፡፡ ድርጅታቸው በኢትዮጵያ የተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ኤግዚቢሽኖችን የማዘጋጀትና የማማከር ሥራን ይሠራል፡ ፡ አሁን አሁን ከሌግዠሪ ቱሪዝም ይልቅ፤ ማይስ የሚገኝበት የቢዝነስ ቱሪዝም እጅጉን ተመራጭ እንደሆነ ይገልጻሉ፡ ፡ ኢትዮጵያም በዘርፉ የላቀ ጥቅም ለማግኘት የምትችልበት ዕድል መኖሩን መረዳት እንደሚገባም ይናገራሉ፡፡
“ሁልጊዜ እንደ አክሱም ሐውልት፣ የላሊበላን ወይም የሐረር ግንብን አሊያም የመስቀል ደመራ በዓልን አይነት መስህቦችን በማስጎብኘት የቱሪዝም ገቢን ለማሳደግ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡ ከዚህ አይነቱ ከሌግዠሪ ቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ከቢዝነስ ቱሪዝም ያነሰ ነው” ይላሉ፡፡
በዓለምአቀፋዊና አህጉራዊ ኮንፍረንሶች ላይ የሚታደሙ ሰዎች የሚያጠፉት የውጭ ምንዛሬ ለጉብኝት ከሚታደሙት ጎብኚዎች የበለጠ እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡
“ስብሰባዎች፣ የማነቃቂያ ጉዞዎች፣ ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽንን በጥምረት በመያዝ የሚዘጋጀው ኤክስፖ ወይም ማይስ የሚሰጠው ጥቅም የላቀ ነው፡፡ በርካታ አገራትም ማይስን ለውጭ ምንዛሬ ማግኛ አንደኛው መንገድ አድርገው በመውሰድ እየተጠቀሙበት ነው” ሲሉም የዘርፉን ጠቀሜታ አብራርተዋል፡፡
አህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ ኮንፍረንሶችና ኤግዚቢሽኖችን ከማስተናገድ ጋር ተያይዞ የሚገኝ ገቢ የአገርን የቱሪዝም ገቢ በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ በዚህ ዘርፍ አውሮፓና አሜሪካ ቅድሚያውን ወስደው ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡ ከአፍሪካ ደቡብ አፍሪካ እና ሩዋንዳ ከማይስ ቱሪዝም ገቢያቸውን ማሳደግ የቻሉ አገራት መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ ለማይስ ቱሪዝም ትኩረት ሰጥታ ወደ ትግበራ ለመግባት ብትዘገይም አሁን ላይ ግንዛቤው እንዲኖር ከማስቻል ጀምሮ የተሠሩ ሥራዎች ውጤት ማሳየት ችለዋል፡፡ ዘርፉን በተደራጀ ተቋም ለመምራት የተጓዘችበት የዓመታት ሒደት ተሳክቶ ከአራት ዓመት በፊት የማይስ ቱሪዝም የኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮ በይፋ ተመስርቷል፡፡
ይህ ቢሮ ኢትዮጵያ እንደ አፍሪካ መዲናነቷ አህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ ኮንፍረንሶችን ማዘጋጀት የምትችልበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የሚሠራ ነው፡፡ በዋናነትም ደረጃቸውን የጠበቁ የስብሰባ ማዕከላት እንዲገነቡ፣ ለስብሰባ ተሳታፊዎችም ሆነ ለጎብኚዎች የጉብኝት መዳረሻ የሚሆኑ መስህቦች እንዲቋቋሙ ማስቻል ነው፡፡
በዚህ ረገድ የታሪክ ሐብታም የሆነችው ኢትዮጵያ በርከት ያሉ የስብሰባ ማዕከላትን ያካተቱ የጉብኝት መዳረሻዎችን ማዘጋጀት ችላለች፡፡ ከማሳያዎች መካከል በዚህ ዓመት በይፋ የተመረቀው አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ተጠቃሽ ነው፡፡ የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ደግሞ የአፍሪካ ኩራት የሆነውን የአድዋን ድል ታሪክ አድምቀው የሚያሳዩ ክስተቶችን አደራጅቶ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ እንጦጦ ፓርክ፣ አንድነት ፓርክ፣ አብርሆት ቤተ መጻህፍት የመሳሰሉትም ከለውጡ በኋላ በመንግሥት የተሠሩና የጎብኝዎች መዳረሻ የሆኑ ተጠቃሽ የልማት ፕጀክቶች ናቸው፡፡
እነዚህና በቀጣይም ለአገልግሎት እንደሚበቁ የሚጠበቁ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች አንዳንዶች እንደሚያስቡት የቅንጦት አይደሉም፡፡ ከአገር ውስጥ ባለፈ ዓለምአቀፋዊ ጎብኚዎች የገቢ ማስገኛ ምንጭ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ የቱሪዝም ኮንፍረንስ ስበት ማዕከል እንድትሆን የሚያስችሉ ናቸው፡፡
በቱሪዝም ኮንፍረንስ የሚገኝ ገቢ ደግሞ የውጭ ምንዛሬ የሚገኝ ገቢን የሚያመነጭ በመሆኑ የአገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የላቀ አስተዋጽኦ አለው፡፡
የማይስ ቱሪዝምን የሚመራው የኢትዮጵያ ኮንቬሽን ቢሮ እንዲቋቋም አስተዋጽኦ በማድረግ የሚጠቀሱት ሌላኛው የዘርፉ ባለሞያ ነብዩ ለማ የፕራና ኤቨንትስ መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ድርጅቱ ላለፉት 15 ዓመታት ታላላቅ ዓለምአቀፍ ኤግዚቢሽኖችንና ሁነቶችን በኢትዮጵያ በማዘጋጀት ይታወቃል፡፡
“ዓለምአቀፍ ኤግዚቢሽኖችና ኮንፍረንሶችን ማዘጋጀት ለአገር የሚያበረክተውን የኢኮኖሚ ጥቅም በአግባቡ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ መንግሥት ዘርፉን ቸል ብሎት ቢቆይም አሁን ላይ ቢሮ እንዲቋቋም በማድረግ ራሱን ችሎ እንዲመራ ማድረጉ በእርግጥ መልካም ነው” በማለት የመንግሥትን ጅማሮ አድንቀዋል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ዘርፉን በባለሞያዎች እንዲመራ ማድረግና አገር ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ መሥራት ይገባል ይላሉ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ፉክክሩ የላቀ ልምድ ካላቸው ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆኑ ነው፡፡
“ዓለምአቀፍ የኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ጨረታዎችን በማሸነፍ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲዘጋጁ የማድረግ ብቃት ያላቸው ሙያተኞችን ማሳተፍ አስፈላጊ ነው” ሲሉ የሚመክሩት ነብዩ ለማ፤ ከዚህ በተጨማሪም መንግሥት በዘርፉ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራትና ድጋፍ
ማድረግ እንዳለበትም ይገልጻሉ፡፡
ምክንያቱም የማይስ ኢንዱስትሪ ምጣኔ ሀብታዊ ጥቅም ብቻ ሳይሆን የአገርን ገጽታ በመልካም በመገንባት ረገድም አዎንታዊ አስተዋጽኦ አለውና! ይህም ደግሞ ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ ሊያፈሱ የሚችሉ የውጭ ባለሃብቶችን መሳብ ያስችላል፡፡
የአዲስ አበባ ውበትም ሐብትም
ኢትዮጵያ የምታስተናግዳቸው ኮንፍረንሶች መልካም ገጽታን ከማስተዋወቅ ባሻገር የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን ለማጠናከር የሚያግዙ ናቸው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ በርካታ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ኮንፍረንሶች በስፋት እየተካሄዱ ይገኛሉ። የመዲናዋን የዲፕሎማቲክ መቀመጫነትና የአፍሪካ መዲናነት የሚመጥኑ መሰረተ ልማቶች መሟላት ደግሞ ለኮንፍረንስ ቱሪዝም መበራከት ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል።
ከተማዋ የምታስተናግዳቸው ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ስብሰባዎች ከአገር በጎ ገጽታ ግንባታ ያለፈ ጠቀሜታ አላቸው። የኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና የዲፕሎማሲ ሥራ ለአገር ወስጥም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማድረስ አንዱ ነው።
ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ውበትና ፀአዳን የተላበሱ የጉብኝት መዳረሻዎች በመገንባትና ለአገልግሎት በመብቃት ላይ ይገኛሉ፡፡ በተለይ የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ውበትም ሐብትም የሚያመነጩ በርካታ የጉብኝት መዳረሻዎች ለአገልግሎት በቅተዋል፡፡
እነዚህ የጉብኝት መዳረሻዎች ለከተማዋ ውበትን በማላበስ ገፅታዋን ማራኪ አድርገዋል፡፡ እናም በአዲስ አበባ የአጭር ጊዜ ቆይታ ለሚኖራቸው ጎብኚዎች ተመራጭ የጉብኝት መዳረሻ፤ ለነዋሪዎቿም ምቹ የእረፍት ግዜ ማሳለፊያ ሆነዋል፡ ፡ የቱሪዝም ዘርፉ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር ጎብኚዎች የሚገኘው ገቢ እንዲጨምር አድርጎታል፡፡ ይህም እንደ አገር የሚኖረው አስተዋጽኦ ቀላል እንዳልሆነ መናገር ይቻላል፡፡
ይህንን ባለመረዳት ይመስላል እነዚህን ፕሮጀክቶች ምንም ፋይዳ የሌላቸው የቅንጦት ብቻ አድርገው የሚመለከቷቸው አሉ፡፡ በአዲስ አበባ በርከት ያሉ የመዝናኛ መዳረሻዎች መገንባታቸው ተገቢ እንዳልሆነ ሲናገም የሚደመጡም አሉ፡፡
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሆቴል ማርኬቲንግ ማኅበር ፕሬዚዳንት ጌታሁን አለሙ፤ “በአዲስ አበባ የልማት ፕሮጀክቶችቹ ገና መቼ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ተሠሩና” ይላሉ፡፡ ከዚህም በላይ በብዛትና በጥራት መሠራት ይኖርበታል የሚል አቋም አላቸው፡፡
በመንግሥት የተገነቡት የጉብኝት መዳረሻዎች የሆቴል ቱሪዝሙን በማነቃቃት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ይጠቅሳሉ፡፡
ጥንታዊና ታሪካዊ ቦታዎችና ቅርሶችን ብቻ ሳይሆን በዘመናችን ኢትዮጵያን የሚገልጹ እንደ ዘመኑ የተሠሩ የጉብኝት መዳረሻዎችንም ለጎብኝዎች በአማራጭነት ማቅረብ አስፈላጊ እንደሆነም ይናገራሉ፡፡ ከተማዋ ከጎብኚዎች ማግኘት ያለባትን ገቢ እንድታገኝ የሚያደርጉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ከግሉ ዘርፍ ጋር በምክክር መሠራት እንደሚገባቸው በመጠቆም፡፡
መንግሥት አሁንም ድረስ እያከናወናቸው ያሉትን አይነት የልማት ፕሮጀክቶች ሥራን በቀጣይ በባለሃብቶች እንዲሠሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሚያስፈልግም ነው የገለጹት፡፡
ይህንን ሐሳብ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታው ስለሺ ግርማ ይጋሩታል፡፡ ኮንፍረንስ ቱሪዝሙ የሚሰጠውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ሙሉ ለሙሉ ለማግኘት ከተፈለገ የግሉን ዘርፍ ማሳተፍ አስፈላጊ መሆኑን ያምናሉ፡፡ ይህም በቱሪዝም ኢትዮጵያ በኩል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮ ሲቋቋምና ወደ ሥራ ከገባም በኋላ ከግሉ ዘርፍ ባለሀብቶችና ድርጅቶች ጋር ስምምነቶችን በመፈጸም የተሠሩ ሥራዎች አብነት መሆናቸውን ነግረውናል፡፡
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት በዘርፉ የተመዘገበው ውጤት ጥሩ ጅምር ማሳየቱና ይህም በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ ቅንጅት
የተገኘ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገልፀዋል። በበጀት ዓመቱ በአገር ውስጥ ቱሪዝም፣ በርካታ ዓለምዓቀፍ ኹነቶችን በማስተናገድ፣ በፕሮሞሽን፣ በመዳረሻ ልማት፣ በአገልግሎት ጥራት ደረጃ ምደባ እና በዲጂታይዜሽን ዙሪያ የተሠሩ ሥራዎች አፈጻጸም ተይዞ ከነበረው ዕቅድ አንጻር አመርቂ መሆኑም ተመላክቷል።
ከኮንፈረንስ ቱሪዝም የተወለደው የማይስ ቱሪዝም ለኢትዮጵያ አዲስ ከመሆኑ አንጻር በቂ ግንዛቤ ባለመኖሩ በሚፈለገው መጠንና ጥራት መልክ ይዞ እየተሠራበት ነው ለማለት እንደማይቻል ሚኒስትር ዲኤታው ያምናሉ፡፡ ይሁንና የኮንቬንሽን ቢሮ ከተቋቋመ በኋላ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ቀጥተኛ ትብብር በመፍጠር ለመሥራት እየተሞከረ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተለይም በሆቴልና ሆስፒታሊቲ የሥራ ዘርፍ ከተሰማሩ አካላት ጋር ስምምነት በመፍጠር ሁነቶችን በስኬት ማዘጋጀት መቻሉን በምሳሌነት ይናገራሉ፡፡
ቀደም ባሉት ጊዜያት ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት የተፈጥሮ፣ የታሪክ እና ባሕላዊ እሴቶችን ለማየት እንደሆነ ጠቅሰው፤ አሁን ግን በዓለም ላይ ከዚህ ዘርፍ የበለጠ ተመራጭ የሆነው የማይስ ቱሪዝም ወይም የኮንፈረንስ ቱሪዝም ነው ይላሉ፡፡
“ማይስ ቱሪዝም በተደራጀ ተቋም - በኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮ እንዲመራ ከተደረገ በኋላ ኢትዮጵያ የቱሪዝም ኮንፍረንስ ማዕከልነቷ በግልጽ መታየት ጀምሯል፡፡ በመንግሥት የተሠሩ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ እንደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም፣ አንድነት እና እንጦጦ ፓርኮች እና አዲስ ኮንቬንሽን ማዕከልን የመሳሰሉት የልማት ፕሮጀክቶች ለማይስ ቱሪዝም ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው አድርጓል”።
በኢትዮጵያ የአሥር ዓመቱ መሪ የቱሪዝም ዕቅድ መሰረት ሰባት ሚሊዮን ዓለምአቀፍ ጎብኝዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲመጡ ለማደረግ ታስቧል፡ ፡ ከዚህ ውስጥ ማይስ ቱሪዝም 20 በመቶ ያህሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ እንደሚገመት ነው የቱሪዝም ሚንስትር ዴኤታው ስለሺ ግርማ የገለጹት፡፡ ዕቅዱ እንደሚሳካም እምነት አላቸው፡፡
ለዚህ ዕቅድ መሳካት የአየር ትራንስፖርት ትስስሩ የጠነከረ መሆኑ፣ አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጽህፈት ቤት መገኛ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ በርካታ ስብሰባዎችን የማስተናገድ ሰፊ ዕድል ያላትና በየትኛውም ወቅት ተስማሚ የአየር ንብረት የተጎናጸፈች መሆኗን በዋና ምክንያትነት ይጠቅሳሉ፡፡
ይሁንና በኮንፍረንስ ቱሪዝም የተፈለገውን ዕቅድ ለማሳካት አስፈላጊ መረጃዎችን አደራጅቶ በዓለምአቀፍ ደረጃ የቱሪዝም ሀብትን ማስተዋወቅ፣ ዓለምአቀፍ የኮንፍረንስ መድረኮችን ለማዘጋጀት ጨረታዎችን ከግሉ ዘርፍ ጋር በቅንጅት መሥራትና የጎብኝዎች መዳረሻዎች 24 ሠዓት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን ማሟላት አሁንም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
ከምንም በላይ ደግሞ የአገር ሰላም የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሐሳባቸውን ያካፈሉን የሁሉም የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት መልዕክት ነው፡፡
ኢኮኖሚ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ከዘመን ጋር ለመዘመን
በፍቅርተ ባልቻ
የሰው ልጅ ዕለታዊ ተግባሩን ለማቅለል ብዙ ተመራምሮ እጅግ በርካታ አጋዥ ቁስ ፈጥሯል። ቴክኖሎጂንም ለሁለንተናዊ ሕይወት ማቅለያነት ተጠቅሟል። ጊዜ፣ ጉልበትና ሀሳብን ከፈጠራ ጋር አዋዶ የሕይወትን ውጣ ውረድ አቅልሏል። በዚህ ረገድ የዘመኑ ቴክኖሎጂ ልህቀት ደረጃ የሆነው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelli- gence - AI) ይጠቀሳል።
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ሰው ሰራሽ አስተውሎት ምንድን ነው?
ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰው ልጅ አስተውሎት የማሰብ፣ የማሰላሰል፣ የመተንተን፣ የመረዳት፣ ችግር የመፍታት አቅም ያለው ማሽን ነው። ይህ ማሽን እንደ ሰው ያስባል፣ ችግር ይፈታል፣ ይማራል፣ ያድጋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት እጅግ በርካታ ነገሮችን ማቅለልና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴን መርዳት የሚቻልበትን መንገድ አበጅቷል።
ዋረን ማክኩሎች እና ዋልተር ፒትስ ለዛሬው ሰው ሰራሽ አስተውሎት እርሾ የሆነ በነርቭ አውታረ መረብ የሚታገዝ ሒሳባዊ ሞዴል ፈጠሩ። አለን ተርኒግ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ማሽን
ፈለሰፈ። በ1960ዎቹ አጠቃላይ ችግር ፈቺ፣ ሎጂክ ቴዎሪስና መሰል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፕሮግራሞች በለጸጉ።
እ.አ.አ በ1950 ዓ.ም ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ራሱን ችሎ እንዲጠና ተወሰነ። ለውስብስብ ችግሮች ዓይነተኛ መፍትሄ መሆኑ ታመነበት። የሰው ሰራሽ አስተውሎት እንቅስቃሴዎች ቀደም ብለው የነበሩ ቢሆንም እንደ ፍልስፍና እና እሳቤ እውቅና የተሰጠው እ.አ.አ 1950 ዓ.ም ነው። ስያሜውን ያገኘው ደግሞ እ.አ.አ በ1955 ነው። የዘርፉ ሊቃውንት በ1970 እና 80ዎቹ የሰውን ልጅ የመወሰን አቅም የሚተካ የኮምፒዩተር ፕሮግራም ለማበልጸግ ጥረት
አድርገዋል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት የጥናት ዘርፍ የሰውን ስራና ሀሳብ በኮምፒዩተር መራሽ ቁሶች መተካት ነው። የሰው ልጅ ፍጥረት የሆኑ ማሽኖች መገንዘብ፣ መማርና ችግሮችን እንዲቀርፉ ማስቻልም ነው። ማሽኖች በሰው ልጅ ምትክ አካባቢን ማመዛዘን፣ መማር፣ ማቀድና መፍጠር፣ መተንተንና እንከኖችን ማምከን እንዲችሉ ማድረግ ነው። የሰውን የማሰብ ኃይል በኮምፒዩተር አዳብሮ በሰውኛ ጥበብ ሕይወትን ማቅለል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰው ልጅ ያሉትን የስሜት ህዋሳት ክህሎቶች ለማሽኖች በማስተማር ሰዎች ነገሮችን በቀላሉ እንዲያገኙና እንዲተገብሩ ማስቻል ነው። በዚህም የመስኩ ሊቃውንት ስልተ ቀመር (አልጎሪዝም) እና አስበው የሚሰሩ ማሽኖችን ወደ ስራ እያስገቡ ነው። ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዛሬ ላይ በሁሉም መስክ ገቢራዊ እየተደረገ ነው። በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በግብርና ዘርፎች ምርትና አገልግሎትን ለማቀላጠፍና ለመጨመር ቁልፍ አማራጭ ሆኗል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት ሦስት ደረጃዎች እንዳሉት መረጃዎች ያሳያሉ። አንደኛው ደረጃ ውስን የሰው ሰራሽ አስተውሎት Artificial Narrow Intelli- gence - ANI ነው። አንድ ተግባር ብቻ ማከናወን የሚችል እንደማለት ነው። ይህን በምሣሌ ብንገልጸው ቼዝ ይጫወታል ወይንም መኪና ይነዳል ማለት ነው። ሁለተኛው ደረጃ ጠቅላላ የሰው ሰራሽ አስተውሎት Artificial General In- telligence - AGI የሚሰኘው ሲሆን ይህኛው ልክ እንደ ሰው የሚያስተውል፣ የሚያመዛዝንና ራሱን የማስተማር አቅም ያለው ነው።
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ሶስተኛው ደረጃ ጥናቱ በቅርቡ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው ሰው ሰራሽ አስተውሎት Artificial Superintelligence ¬- ASI ነው። ይህ ከሰው ልጅ በብዙ እጥፍ የበለጠ አቅም ያለው ነው። እ.አ.አ 2050 (ኤ.ኤስ. አይ) ሙሉ ሲሆን አንድ ማሽን የአንድ ቢሊዮን ሰው ጭንቅላት ያህል አቅም ይኖረዋል። ስለዚህ አፍሪካ ውስጥ ያለው ሕዝብ በዚህ ማሽን አቅም ቢሰላ፣ የአፍሪካን አህጉር ሁለት ማሽኖች ብቻ ያንቀሳቅሳሉ እንደማለት ነው። (ይህ መልካም አጋጣሚ የመፍጠሩን ያህል ስጋት/አደጋም እንዳለው መገመት ይቻላል)።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት ካሉት ስድስት ይዘቶች መካከል አንዱ ራሱን እያስተማረ የሚያሻሽለው (Machine Learning) ይባላል፤ ይህ ማሽን ከተሰራ በኋላ አዳዲስ ነገር እየተማረ ራሱን የሚያሻሽል ማሽን ነው። ለምሣሌ ሰው አትግጭ ተብሎ የተሰጠውን መኪና አንድ ቦታ ከገጨ፣ የገጨው ደግሞ በአምስት ሜትር ከሆነ በሚቀጥለው በስድስት ሜትር ይቆማል። ሁለተኛው በጥልቅ የሚማር (Deep Learning) ብለን የምንገልጸው ነው። ከሰው ልጅ እዕምሮ ጋር በሚመሳሰል መልኩ የሰውን ቦታ በመተካት በርካታ ተግባራትን የሚያከናውን ነው። ሦስተኛው ስሌት በአስተውሎት (Cognitive Computing) ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት የሚያገለግል ነው። በተለይ እርስ በእርስ የሚጋጩ ነገሮችን መርምሮ ወይም ተንትኖ መፍትሔ ያስቀምጣል።
አራተኛው የነርቭ አውታር መረብ (Newral Net- work) ሲሆን የሰው አንጎል አሰራርን በመምሰል ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮችን ከሰው በፈጠነ መንገድ የሚሰራ ነው። አምስተኛው የሚያይ እና የሚያገናዝበው (Computer Vision) በምስል የምንሰጠውን መረጃ ምንነት የሚገልጽልን ነው። በዚህ መልኩ ለዓይነ ስውራን የተዘጋጁና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ታግዘው የተለያዩ መረጃዎችን
የሚናገሩ መነጽሮች አሉ። ስድስተኛውና የመጨረሻው ልክ እንደ ሰው የተፈጥሮ ቋንቋን ማጥናት፣ መማር፣ መናገር፣ መተርጎም የሚችል ነው።
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለምን?
ሰው ሰራሽ አስተውሎት በርካታና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች አሉት። የማጭበርበር ተግባርን መለየት፣ የሰዎች ጥበቃና ደህንነት፣ ጤና ነክ አገልግሎቶች፣ የፍርድ ቤት ጉዳዮች፣ የተፈጥሮ ኃብት በመሳሰሉት መስኮች ሁሉ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን መጠቀም የተቻለበት ዘመን ላይ እንገኛለን። በሰው ሰራሽ አስተውሎት በርካታ መረጃዎችን በአጭር ጊዜ መተንተን፣ ንድፎችን መለየት፣ አዝማሚያዎችን መተንበይ፣ ማስረጃን ተንተርሶ መወሰን፣ ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎችን በመስጠት ማማከር፣ ወዘተ … ተችሏል።
ለምሣሌ እንግሊዞች ካንሰርን በሚመለከት ጥሩ ግኝት ላይ መድረሳቸው ተነግሯል። አንድ ታካሚ የካንሰር ሕመም እንዳለበት ዶክተሩ ሳያውቅ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መለየት/ማወቅ ችሏል። ይህም ማለት ገና የመጀመሪያው ሴል መፈጠር ሲጀምር ምልክት አይቶ ሪፖርት ያደርጋል። ስለሆነም ካንሰር በባህሪው ካልተሰራጨና መኖሩ በቶሎ ከታወቀ የታመመውን ሰው የማዳን ዕድሉ ይሰፋል።
የክፍያ ሰነድ (ፔሮል) በሰው ሰራሽ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
አስተውሎት አማካኝነት ቢዘጋጅ ማጭበርበር አይታሰብም። የሐሰት ማንነት፣ አጠራጣሪ የገንዘብ ዝውውር፣ ያልተለመደ የባንክ እንቅስቃሴ ካጋጠመው ያስቆማል/ይይዛል። ይህ አንዱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጥቅም ነው። ሌላው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጥቅም ገንዘብ ለማበደር ወይም አንድ አዲስ ሥራ ለመሥራት ያለውን አዋጭነት እና ኪሳራ/ስጋት (Risk Management) አስቀድሞ ማሳወቁ ነው። ባለሀብቶች የተለያዩ ድርጅቶችን አክሲዮን/ሼር ለመግዛት አዋጭነቱን የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጥናት በማየት መወሰን ጀምረዋል።
የአንድን አገር ገቢ ለማሳደግ የግብር ሰብሳቢ ተቋማት የሚሠሩት ሥራ ወሳኝ ነው። አሁን ይህም በሰው ሰራሽ አስተውሎት መሥራት ተችሏል፤ የንግድ ተቋማቱ ያስገቡትን እቃ፣ የመጓጓዣ እና ሌሎች ወጪዎች በማስላት ይህን ያህል ግብር ክፈሉ በማለት በጣም ተቀራራቢ የሆነ ግምት ያሰላል። በተጨማሪም በሰዎች መካከል (በገቢ ሰብሳቢና በነጋዴ) የሚደረገውን ግንኙነት ስለሚቀንስ ለሙስና እና ለብልሹ አሰራር ያለውን ተጋላጭነት ያስቀራል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት በቅርብ ርቀት የጤና ሙያተኞችን ሥራ የመተካት ብቃት እየፈጠረ ነው። የሰው ልጅን ጤና ለማሻሻል የሚያስችል
አቅም ተፈጥሯል። አንድ ሃኪም አንድን ታካሚ ካየ በኋላ ደም ስጡ፣ ሽንት ስጡ ይላል፤ የታካሚውን ሕመም ለማወቅ በርካታ መረጃ ይወስዳል። የደም፣ የኤክስሬይ፣ የሲቲ ስካን፣ ወዘተ… ምርመራዎች ይታዘዛሉ። ሰው ሰራሽ አስተውሎት ይህን ሁሉ ውጣ ውረድ በማስቀረት ለእውነት የቀረበ ትንተና በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሰጣል።
የፖሊሲ ትንተና ማማከር አገልግሎት መስጠቱ ሌላው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጥቅም ነው። መንግሥታት ኩባንያዎች አማካሪ ይቀጥራሉ፤ አሁን ግን ለአማካሪ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር መክፈል አያስፈልግም። (Genere- tive AI chatGPT) በተፈለገ ጉዳይ በአምስት ደቂቃ ውስጥ ምርጥ የሚባል ውል (ኮንትራት) አዘጋጅተው ያቀርባሉ። ይህን ሁሉ የሚያደርገው ግን በርካታ ዳታ (ብዙ ኢሜጅ በክላውድ ውስጡ) ያለው ከሆነ ነው። ለምሣሌ፣ የአንድ ዓመት ልጆች፣ የአምስት ዓመት ልጆች፣ የሃያ ዓመት ልጆች የሚናገሩት የቋንቋ ጥልቀት እንደሚለያየው ሁሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማሽንም ብዙ በተማረ ቁጥር ብዙ አገልግሎት ይሰጣል፤ ስለዚህ ማሽኑን ብዙ ማስተማር ያስፈልጋል።
በምግብ ራስን ለመቻል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሚና ተነግሮ አያልቅም። ግብርና ላይ የሚሰሩና አመራር የሆኑ ሰዎች ሳይንስና ቴክኖሎጂን በደንብ ማወቅ ይኖርባቸዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት የአየር ሁኔታውን፣ ለዚያ አካባቢ የሚስማማውን የእህል ዓይነት፣ የሰብል በሽታዎችን እንዲሁም የገበያውን ሁኔታ በማጥናት ቀድሞ የሚያሳውቅ በመሆኑ በብዙ መልኩ የግብርና ሥራውን በማገዝ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በእጅጉ ይጠቅማል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት የመማር ማስተማሩን ሥራ የሚመራውን ሥርዓተ ትምህርት በግለሰብ ደረጃ ማዘጋጀት ችሏል። የአንድን ሰው ከልጅነት ጀምሮ ያለውን ዝንባሌ በምን ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ዝንባሌውን መነሻ በማድረግ እንዲማር ያደርጋል።
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
በሰው ሰራሽ አስተውሎት ግጥም እና ሥነ-ጽሁፍ ማዘጋጀት ተጀምሯል። የመማር ማስተማሩን ሥራ በከፍተኛ ደረጃ እያቀለለው ይገኛል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት በፍርድ ቤት ለሚሰጡ አገልግሎቶችም ይውላል። በፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ጠበቃው ምን አለ? ተከሳሽ ምን አለ? ምስክሮች ምን አሉ? ዳኛው ምን አሉ? የዚህ መረጃ ይያዛል፤ በቃል ያሉትም መረጃዎች ወደ ጽሑፍ ይቀየራሉ። ስለዚያ ጉዳይ አዋጆች፣ ሕጎች ምን ብለዋል በሚል ድንጋጌዎቹ ይታያሉ። እነዚህ መረጃ የመያዝ እና ሕጎቹን የማጣቀስ ሥራዎች ረጅም እና ውስብስብ ሂደት ነበራቸው። አሁን ግን ሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት በችሎት ወቅት ከሳሽ፣ ተከሳሽ፣ ዳኞች፣ ምስክሮች የሚናገሩት በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ጽሑፍ ተቀይሮ ይቀርባል፤ በጉዳዩ ላይ ያሉ የሕግ ድንጋጌዎችን ተንትኖ የሚያቀርብ በመሆኑ ያለ ምልልስ ዳኞች ውሳኔ ሰጥተው ባለጉዳዮችን ያሰናብታሉ። ስለሆነም ሰው ሰራሽ አስተውሎት በፍርድ ሥርዓቱ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ትርጉም ያለው እገዛ ያደርጋል።
በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ደንበኞችን ተቀብለው የሚያስተናግዱ፣ ቀጠሮ የሚያስይዙ፣ መረጃ የሚሰጡ ሮቦቶችም አሉ። እነዚህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤት የሆኑ ሮቦቶች ልክ እንደ ሰው ሰላምታ በማቅረብ ምን እንደምትፈልጉ ይጠይቃሉ፤ ለጥያቄውም ምላሽ ይሰጣሉ። በተለይ በጤና ተቋማት፣ በሆቴሎች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ሲሆን ያለምንም እረፍት ለ24 ሠዓት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ናቸው።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት ቀደም ሲል ከተጠቀሱት ጥቅሞች ባሻገር ከሕዝብ ጥበቃና ደህንነት አንጻር፣ በባንክ ዝውውር፣ በኢሚግሬሽን፣ በደህንነትና ፖሊስ እንዲሁም በሌሎችም መስኮች እጅግ ፈርጀ ብዙ ፋይዳ ያላቸውን አገልግሎቶች ቀላል አድርጓል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት በአፍሪካ
ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሽግግር ለማምጣት ትልቅ አቅም እንደሚሆን ይታመናል። የአፍሪካ ኅብረትን ዘላቂ የልማት ግቦች እንዲሁም የ2063 አጀንዳን ለማሳካት ወሳኝ ነው። አካታች የሆነ ዕድገት ለማምጣት በእጅጉ ያገለግላል። የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፣ ግብርናን በማዘመን፣ በትምህርት እና በጤና ዘርፎች የሚሠሩ ሥራዎችን በማቅለል፣ መረጃ በቀላሉ እንዲያገኙ እንዲሁም አካባቢን እና የተፈጥሮ ኃብቶችን በመጠበቅ በመሳሰለው መስክ መልካም አጋጣሚን ይፈጥራል።
በአንጻሩ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ተግባራዊ በመደረጉ የሚያጋጥሙ ስጋቶች እና ጉዳቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ያመላከተው በአፍሪካ ኅብረት የተዘጋጀው (African Union CONTINENTAL ARTIFICIAL INTELLIGENCE STRATEGY - Harnessing AI for Africa’s Development and Prosperity - July 2024) ሰነድ ነው።
የዚህ አንደኛው መነሻ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማሽኖችና መተግበሪያዎችን በመረጃ ከምናበለጽግበትና ከምናስተምርበት መንገድ ምሉዕ/እንከን የለሽ አለመሆን ነው። በተያያዘም ሴቶችን፣ ሕጻናትን፣ ስደተኞችን፣ አካል ጉዳተኞችን የማግለል ሁኔታ ሊያጋጥም እንደሚችል ስትራቴጂክ ሰነዱ ጠቁሟል። በአገር በቀል ዕውቀትና እሴቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያስድርም ተመላክቷል። የሰዎችን ሥራ ተክቶ ስለሚሠራም ሰዎችን ከሥራቸው ሊያፈናቅል መቻሉ አንዱ ስጋት ነው።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት ቅንጦት ሳይሆን የመጪው ዘመን መወዳደሪያ ሆኗል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence - AI) በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል። እ.አ.አ 2030 በዚህ ዘርፍ አማካኝነት 15 ነጥብ 7 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ እንደሚንቀሳቀስ ከወዲሁ ቅድመ ግምት ተሰጥቷል። ሆኖም ይህ ኃብት በዓለም ላይ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የተከፋፈለና እኩል አይደለም።
በተለይ አፍሪካ ለመስኩ ዕድገት የሚረዱ ግብዓቶችን በማቅረብ አስተዋጽኦ ያደረገች ብትሆንም የጥቅሙ/የትሩፋቱ ተቋዳሽ አልሆነችም። ከአፍሪካ አገራት መካከል እንደ ሩዋንዳ እና ሞሪሺየስ ያሉ አገራት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳቸውን ስትራቴጂ ቀርጸው ቀደም ብለው ወደ ትግበራ ከገቡ አገራት መካከል መሆናቸው ያስነበበው
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
የአፍሪካ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ‘AI in Af- rica: Key Concerns and Policy Consider- ations for the Future of the Continent,’ በሚል ርዕሰ ያዘጋጀው ሰነድ ነው።
በአህጉሪቱ አካታችና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ወሳኝ መሆኑ አያጠያይቅም። ሆኖም አፍሪካ በሌሎች አህጉራት በተሰሩ የቴክሎጂና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶች የተዋጠች/ጥገኛ ናት። እነዚህ የፈጠራ ሥራዎች ደግሞ ከአገራቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣሙ አይደሉም። ስለሆነም የአፍሪካን ችግሮች በአግባቡ እንዲፈቱ አይጠበቅም። ይህን ክፍተት እና ውስንነት በማየት የአፍሪካ ኅብረት መስኩ እንዴት መመራት እንዳለበት በጥልቀት የሚያሳይ ስትራቴጂ አዘጋጅቷል። የኅብረቱ አህጉራዊ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስትራቴጂ እ.አ.አ በ2024 ጸድቋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በወርሃ ግንቦት 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በጋራ ያዘጋጁት በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 መካሄዱ ይታወሳል። በኤክስፖው “አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር” በሚል ጭብጥ የአፍሪካን የሰው ሰራሽ አስተውሎት እንቅስቃሴ የተመለከተ መርሃ ግብር ቀርቧል።
ዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 በኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በቴክኖሎጂ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለዓለም ለማስተዋወቅና ትስስር ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ከ10 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች፣ ከ100 በላይ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንዲሁም ከ50 በላይ ስታርት አፖች ምርትና አገልግሎታቸውን ያስተዋውቁበት መድረክ ነበር።
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ ሰው ሰራሽ አስተውሎት በጂኦ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አንዱ የለውጥ ኃይል እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የአገራት ብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ፣ ኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ማረጋገጫ፣ የደህንነት ዋስትና የትኩረት ማዕከል ሆኗልም ብለዋል። ቴክኖሎጂው በፈጠራ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና፣ በፋይናንስ፣ በደህንነትና ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር የጎላ አበርክቶ እንዳለውም አንስተዋል።
በአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ሽግግርን በማቀላጠፍ በሁሉም ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በትብብር ገቢራዊ ማድረግ ይገባል። በአፍሪካ ከፍተኛ የሥራ ዕድል በመፍጠር የኅብረቱን አጀንዳ 2063 እውን ለማድረግ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ዕድገት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንዳለባትም ተጠቅሷል። በአፍሪካ አካታችና ዘላቂ ዕድገት ለማረጋገጥ ምቹ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሥነ ምህዳር መፍጠር ያስፈልጋል። በታዳሽ ኃይል፣ በወጣት የሰው ኃይል እና በማዕድን እምቅ አቅም ያላት አህጉር ነች። ስለሆነም ይህን አቅሟን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር በማቀናጀት ለችግሮች መፍቻ ቁልፍ አድርጎ መጠቀም ያስፈልጋል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት መስክ ለአፍሪካ የልህቀት ማዕከል እንድትሆን የተጀማመሩ
አበረታች ሥራዎች አሉ። ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ፣ ሮቦቶችን መሥራት ተጀምሯል። ለዚህም እንደማሳያ የሚጠቀሰው ሶፊያ የተሰኘችው ሰው መሳይ ሮቦት ስትሠራ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው የሶፍትዌር ፕሮግራሚንግ የማበልጸግ ተግባር በኢትዮጵያዊያን እንዲከናወን መደረጉ ነው። An International Journal of Information and Communication Tech- nology (June 2019) ‘ARTIFICIAL INTELLI- GENCE FOR ETHIOPIA’ በሚል ርዕስ ያቀረበው ጽሑፍ “የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማበልጸጊያ ማዕከል እንዲሆን መወሰኑ እና ይህም እየተሰራበት መሆኑ የተሰጠውን ትኩረት ያሳያል” ይላል።
ኢትዮጵያ ዘርፉን የሚመራውን ተቋም፤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን መስርታለች። ኢንስቲትዩቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምህዳር ተጠቃሽ ለማድረግ እየሠራ ይገኛል። ለሥራው አጋዥ የሆኑና በተለያዩ አካላት፣ በተለያየ ደረጃ ተፈጻሚ የሚደረጉ የሕግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ሥራ ላይ ለማዋል ሁለገብ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው። በቅርቡ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የሳይንስ ሙዚየም በዘርፉ የሚሠሩ ሥራዎችን ለማስተዋወቅ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት፣ በመስኩ የተሠማሩ እንዲሁም ለመሠማራት ፍላጎቱ እና ተሰጥኦ ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን በማነሳሳት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። በሌላ በኩል ለወጣት ሥራ ፈጣሪዎች (ስታርትአፖች) ሥልጠና በመስጠትና ክህሎቶቻቸውን በማሳደግ ዘርፉን እንዲቀላቀሉ እየተሠራ ነው።
ኢትዮጵያ አገር በቀል ሰው ሰራሽ አስተውሎትን
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
በማልማት ከአህጉራዊው አጀንዳ 2063 ግቦች ጋር የተጣጣመ ውጤት እያስመዘገበች መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት በአዲስ አበባ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ግንቦት 2017 ዓ.ም) ላይ መግለጹ ለዚህ እንቅስቃሴ የተሰጠውን እውቅና ያሳያል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስትራቴጂና አጀንዳ 2063 ማሳካት የሚያስችል የሰው ሰራሽ አስተውሎት እያለማች መሆኗም ተገልጿል።
በመስኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሦስት ነጥብ አንድ ትሪሊዮን ዶላር ኃብት ማንቀሳቀስ መቻሉ እየተነገረ ነው። በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ይህ አሃዝ አምስት ትሪሊዮን ዶላር እንደሚደርስ፤ እ.አ.አ በ2030 15 ትሪሊዮን ዶላር ኃብት እንደሚያንቀሳቅስ ይጠበቃል። ስለሆነም ኢትዮጵያ ከዚህ ኃብት ተቋዳሽ ለመሆን በዘርፉ ብዙ የቤት ሥራ መሥራት እንዳለባት ግልጽ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዚህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መስክ ከሚንቀሳቀስ ኃብት የተወሰነውን ሼር ለማግኘት መሠራት እንዳለበት ገልጸዋል። መንግሥት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠቱ በተለያዩ የሥራ መስኮች ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለመጠቀም እየተሠራ መሆኑንም አመላክተዋል። ጅምሮቹንም ማሳያዎችን በመጥቀስ አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ 112 ሚሊዮን የባንክ ደብተሮች አሉ፤ በቁጥር ደረጃ እስከ 40 ሚሊዮን ሰው (አንዳንዱ አምስት ስድስት ስለሚኖረው) እንደሚገለገል ይገመታል። እስካለፉት ሁለት ዓመታት ድረስ ሁሉም የኢትዮጵያ ባንኮች ተደምሮ ግማሽ ሚሊዮን ሰው አላበደሩም።
ቢያንስ 40 ሚሊዮን ሰው ነው የሚገለገለው ተበዳሪው ግን ግማሽ ሚሊዮን አይሞላም ለምን? ጥቂቶች ናቸው ኃብት የሚቀራመቱት። ባንኩ እኩል አያበድርም። ሞባይል መኒን በመጠቀም የኢትዮ-ቴሌኮም በአንድ ዓመት ውስጥ ለሶስት ሚሊዮን ሰዎች ማበደር ችሏል። ኢትዮ-ቴሌኮም ሁለት ዓመት ሳይሞላው ከሶስት ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ሰዎች ብር አበድሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ምን ያህል ለውጥ ማምጣት እንደምንችል ይህ አንዱ ማሳያ እንደሆነ አክለዋል።
ከኢትዮጵያ ገቢዎች አንጻር በየጊዜው ገቢን ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ ነው። Integrated task admin system – ITAS የሚባለው አዲሱ ሲስተም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ባህሪይ አለው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የገቢዎች ሚኒስቴር ‘አይታስ’ን ሙሉ ለሙሉ መጠቀም ሲጀምር በከፍተኛ ደረጃ አቅሙ እንደሚያድግ ይጠበቃል። በገቢ ሰብሳቢና በነጋዴ መካከል ያለውን ግንኙነት ይቀንሳል። ይህም ብዙ የሚባክን ብር እንድናገኝ፣ ሌብነት እንዲጠፋ ያግዛል።” በማለት እየተሠራ ያለውን ሥራ እና አገራዊ ጥቅሙን አብራርተዋል።
በአገራችን በቅርቡ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ዝናብ ለማዝነብ ተችሏል። ይህም በመስኩ በተሠራው ሥራ የተገኘ ውጤት ነው። ከጤና አንጻር የተገኙ ስኬቶችም አሉ፤ ከእነዚህ መካከል አንዱ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት ኮሌራን ማግኘት መቻሉ ነው። የከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች በቀጣይ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን እንዲጠቀሙ ታቅዶ ሲስተሙ እንዲበለጽግ እየተደረገ መሆኑም ተነግሯል።
በመስኩ እየተስፋፉ ከሚገኙ አገልግሎቶች መካከል አንዱ የቋንቋ ትርጉም (Machine Trans- late) ሲሆን በኢትዮጵያ አንዱን ቋንቋ ወደ ሌላ በመተርጎም አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በዚህም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአንድ መተግበሪያ የተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን መማር እንዲሁም ከድምጽ ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችል ሥርዓት አበልጽጎ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል።
ልቆ ለመገኘት …
የተለያዩ ጥናት እና ምርምሮችን በማቅረብ የሚታወቀው ሪሰርች ጌት የተሰኘው ድረገጽ Jan. 2024 ይፋ ያደረገው እና ROLE OF ARTIFI- CIAL INTELLIGENCE IN THE CREATION OF EMPLOYMENT OPPORTUNITIES በሚል ርዕስ ያቀረበው መረጃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የሥራ ዕድል ይቀንሳል ወይም የሥራ አጦች ቁጥር እንዲጨምር ያደርጋል የሚለውን ሀሳብ ውድቅ ያደረገ ነው። በድረገጹ የቀረበው ፅሑፍ የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም (የ2020 ሪፖርት) ዋቢ በማድረግ ያቀረበው መረጃ “በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች 97 ሚሊዮን ሲሆኑ የሚቀነሱ ሥራዎች 85 ሚሊዮን ናቸው” ይላል። ስለሆነም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ይታመናል ማለት ነው።
ከዚህ መረጃ በመነሳት አገራት ዜጎቻቸውን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ንቁ እና ብቁ ሆነው እንዲገኙ የማብቃትና የማዘጋጀት ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል። ካልሆነ በቴክኖሎጂው ተጠቃሚ መሆን አዳጋች ይሆናል። ከዚህ መረጃ በአገራችን በሚፈጠሩ አዳዲስ የሥራ መስኮች የሠለጠነ የሰው ኃይል እንዲኖር ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አማራጭ የሌለው መፍትሔ እንደሆነ መረዳት ይገባል።
ኢትዮጵያ በ2030 የአፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የልህቀት ማዕከል የመሆን ራዕይ ሰንቃለች። ይህን ራዕይ እውን ለማድረግ ብሎም ከመስኩ ማግኘት ያለብንን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ላይ እየተሠራ ያለውን ሥራ ማስፋት እና ለስኬታማነቱ መረባረብ የግድ ይላል።
በዓለም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እያሳደረ የሚገኘውን ተጽዕኖ በመረዳት ለዘርፉ ምርምሮች የሚደረገውን ድጋፍ የበለጠ ማጠናከር ያሻል። ዓለም የሚሄድበትን ፍጥነት በመመልከት አገራችንን የሚመስሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶችን ማበልጸግ አለብን። ሰው ሰራሽ አስተውሎት የአገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ የሳይበር ደህንነትን ለመጠበቅ፣ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ፣ ምርታማነትን ለመጨመር፣ ገበያን ለማስፋት እና ለመሳሰሉት ሥራዎች በእጅጉ አስፈላጊ ነውና።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘመኑ የደረሰበትን ልህቀት ያማከሉና ከዘርፉ ውጤት ለማግኘት በአጭር ጊዜ ውስጥ የተደረጉ እንቅስቃሴዎች አበረታችና ይበል የሚያሰኙ ናቸው። ነገር ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ልህቀት በመከተል አገራችንን የሚመስሉ የዘርፉን ውጤቶች ይበልጥ ማላቅ ያስፈልጋል።
ማኅበራዊ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
መጪውን ትውልድ ለመታደግ…
በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ
በመንገሻ ገ/ሚካኤል
በኅብረተሰብ ጤና ታሪክ ውስጥ ትልቅ ግኝት እንደሆነ የሚነገርለት ‘ክትባት’ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ይታደጋል። የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው ክትባት በየዓመቱ ከ3 ነጥብ 5 እስከ 5 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችን ሞት ይከላከላል። ለዘመናት የሰው ልጆች የጤና ጠንቅ የነበሩ በሽታዎች ከምድራችን እንዲጠፉና የሚደርሱት ጉዳት እንዲቀንስ በማድረግ ክትባቶች አይተኬ ሚና ተጫውተዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት እ.አ.አ በ1966 የክትባት ተደራሽነትን ለማሳደግ የሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም የማዳበር መርኃ-ግብር ይፋ በማድረግ በዓለም ዙሪያ ሕጻናትን ማዕከል በማድረግ ለስድስት
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
አይነት በሽታዎች ሲሰጥ ቆይቷል። ተቅማጥ፣ ከፍተኛ ሳል፣ ቲታነስ፣ ፖሊዮ፣ ኩፍኝ እና ሣንባ በክትባቱ የተጠቃለሉ በሽታዎች ናቸው። ይህ መርሃ-ግብር በኋላ ላይ 30 ተጨማሪ ክትባቶችን አካትቷል። ከእነዚህ መካከል 13ቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጡ ሲሆኑ የተቀሩት 17ቱ ደግሞ በተለየ አካሄድ ለተወሰኑ ቦታዎች ብቻ የሚቀርቡ ናቸው።
ክትባት ከመስፋፋቱ በፊት አሁን ሠለጠኑ በሚባሉ አገራት ጭምር በተለያዩ ወቅቶች የተከሰቱ ወረርሽኞች የሚሊዮኖችን ሕይወት ቀጥፈዋል። እ.አ.አ በ1630ዎቹ በአሜሪካ የተከሰተውና 70 በመቶ የሚሆነውን የአገሪቷን ሕዝብ የፈጀው የፈንጣጣ ወረርሽኝ አንዱ ማሳያ ነው።
ፈንጣጣ ውጤታማ በሆነ የክትባት ዘመቻ እ.አ.አ 1980 ሙሉ በሙሉ መጥፋቱ በዓለም ጤና ድርጅት የታወጀ ሲሆን፤ የፖሊዮ በሽታም ከፓኪስታን እና ከአፍጋኒስታን በስተቀር ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሁሉም አገራት ጠፍቷል። የሩቁን ትተን የቅርቡን እንኳን ብናነሳ ክትባት የሚሊዮኖችን ሕይወት የቀጠፈውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመግታት ኃያልነቱን አስመስክሯል።
ክትባት ምንድን ነው?
በጤና ሥርዓት ውስጥ በሽታዎችን መከላከል የሚያስችሉ በርካታ አማራጮች ቢኖሩም የክትባትን ያህል ውጤታማ ዘዴ አለ ተብሎ አይታሰብም። ክትባት ከሰው ልጅ ተፈጥሯዊ የበሽታ መከላከያ ጋር በመተባበር የበሽታ መከላከል አቅምን ያሳድጋል። የሰው ልጆችን በሽታ የመከላከልና የመቋቋም አቅም በማሳደግ ከሞት፣ ከሕመም እና ከአካል ጉዳተኝነት ይከላከላል። ክትባት ሕጻናትን ጨምሮ በየትኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በሽታ የመከላከል አቅማቸው እንዲጎለብት ከመታመማቸው በፊት
የሚወስዱት ሕክምና ነው።
የክትባት ተደራሽነት በኢትዮጵያ
የዓለም ጤና ድርጅት ከ30 በላይ በሽታዎችን መከላከል የሚያስችሉ ክትባቶችን አገልግሎት ላይ አውሏል። በአገራችንም የበሽታዎችን ስርጭት እንዲሁም የአገሪቷን የጤና ሥርዓት አቅም ባገናዘበ መልኩ በመደበኛ የክትባት መርሃ-ግብር 13 ዓይነት ክትባቶች እየተሰጡ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የክትባት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ አቶ መልካሙ አያሌው ይናገራሉ። እነዚህ ክትባቶች ለሕፃናት፣ ለልጃገረዶች፣ በመውለድ የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች የሚሰጡ ሲሆኑ ከ12 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች እየተሰጠ ያለው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባትም በዚሁ ውስጥ ተካቷል። ከመደበኛው ክትባት ባሻገር የተለያዩ ወረርሽኞች በሚከሰቱበት ጊዜ በዘመቻ መልክ የሚሰጡ ክትባቶች መኖራቸውንም ኃላፊው ገልፀዋል።
የጤና ሚኒስቴር ከሚያከናውናቸው የተለያዩ ተግባራት አንዱ በሽታን መከላከልና የጤና ማጎልበት ሥራዎችን መሥራት በቀዳሚነት ይጠቀሳል። አስቀድሞ ከመከላከል ባሻገር ሰዎች ለበሽታ በሚጋለጡበት ጊዜ ደግሞ የሕክምና ሥራዎች ይሠራል። ከበሽታ መከላከል ሥራዎች አንዱ ደግሞ ክትባት ነው። የክትባት አገልግሎት ራሱን ችሎ የቆመ ሳይሆን ከመጀመሪያ ደረጃ የጤና ሥርዓት ጋር በቅንጅት የሚሰጥ መሆኑን አቶ መልካሙ ይናገራሉ። የጤና ሚኒስቴር የዓለም ጤና ድርጅት በሚሰጠው ምክረ ሐሳብ መሰረት ክትባቶች የቅዝቃዜ ሰንሰለታቸውን ጠብቀው ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ አስፈላጊውን ግብዓትና የሰው ኃይል በመመደብ ያለመቆራረጥ ለኅብረተሰቡ እንዲደርሱ በማድረግ ላይ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ይገኛል። በዚህም የክትባት አገልግሎት ከጤና ኬላ ጀምሮ በሁሉም የጤና ተቋማት ይሰጣል።
ከመደበኛው ክትባት ጎን ለጎን በተለየ ሁኔታ በዘመቻ መልኩ የሚሰጡ ክትባቶች የመኖራቸው ምክንያት በሽታዎች የማኅበረሰብ ችግር የማይሆኑበት ደረጃ ለማድረስ ብሎም ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ሲሆን ከእነዚህ ክትባቶች የልጅነት ልምሻ ወይም ፖሊዮ እና ኩፍኝን ጨርሶ ለማጥፋት ከተያዙ በሽታዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የዓለም ጤና ድርጅት እነዚህን በሽታዎች ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ከሁለት እስከ ሶስት ዓመት ባለ ጊዜ ውስጥ ተመሳሳይ ክትባት መስጠት እንደሚያስፈልግ ምክረ ሃሳብ አስቀምጧል። በምክረ ሃሳቡ መሰረት ጤና ሚኒስቴር ለ18 ሚሊዮን ሕጻናት የኩፍኝ ክትባት በዘመቻ መልክ ሰጥቷል። እዚህ ላይ በመደበኛ የክትባት አገልግሎት የተከተቡ የኅብረተሰብ ክፍሎች በዘመቻ መልክ በሚሰጡ ክትባቶችንም መከተብ እንደሚጠበቅባቸው አቶ መልካሙ አስገንዝበዋል።
ጤና ሚኒስቴር እንደ ኮሌራ፣ ማጅራት ገትር፣ ቢጫ ወባ የመሳሳሉ በሽታዎች ወረርሽኝ በሚከሰትበት ጊዜ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የዘመቻ ክትባት አገልግሎት ይሰጣል።
ያጋጠሙ ችግሮችና የመፍትሔ እርምጃዎች
በኢትዮጵያ ክትባት በመርኃ-ግብር ደረጃ ተቀርጾ አገልግሎት መስጠት ከተጀመረ 45 ዓመታት ተቆጥረዋል። ይሁንና በአገራችን አሁንም ድረስ የክትባት ተደራሽነት ዝቅተኛ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ። ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2019 የጸረ አምስት/ፔንታቫለንት ክትባት ለሦስተኛ ጊዜ የወሰዱ ሕፃናት ቁጥር 61 በመቶ፣ ሁሉንም የክትባት ዓይነቶች ያጠናቀቁ ሕፃናት 44 በመቶ ቢሆኑም 19 በመቶ የሚሆኑት ሕፃናት ምንም ዓይነት ክትባት አላገኙም ይላል።
በአገር አቀፍ ደረጃ ክትባት ጀምሮ የማቋረጥ ምጣኔ ከፍተኛ ነው። በዚህም የመጀመሪያውን የጸረ አምሥት ክትባት ወስደው የኩፍኝ ክትባት ያልወሰዱ ሕጻናት 13 በመቶ ሲሆኑ፤ ሽፋኑ ከክልል ክልል ከፍተኛ ልዩነት አለው። የቅዝቃዜ ሰንሰለት መሰረተ ልማት አለመኖር፣ ዝቅተኛ የአገልግሎት አሰጣጥና ከፍተኛ የክትባት ጀምሮ ማቋረጥ፣ የመረጃ አለመጣጣም፣ አናሳ የባሕሪይ ለውጥ ተግባቦት፣ ደካማ የክትባት ፕሮግራም አስተዳደር (ዕቅድ፣ ትንበያ፣ ትመና፣ ክትትልና ግምገማ)፣ በዋነኛነት ለክትባት አገልግሎት ሽፋን ዝቅተኛ መሆን ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ይላል ሚኒስቴሩ።
የክትባትን አስፈላጊነት በተመለከተ በማኅበረሰቡ ዘንድ ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆን፣ በአንዳንድ አከባቢዎች በቦታ ርቀትና በፀጥታ ችግሮች ምክንያት የግብዓት መቆራረጥ መኖሩ የክትባት አገልግሎት ሽፋን ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጎታል የሚሉት አቶ መልካሙ፤ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥትና የግል የጤና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ክትባት የሚሰጥ ቢሆንም አገልግሎቱን በሚፈለገው ደረጃ ለመስጠት ዝግጁ ሆኖ ከመቆየት አንጻር ውስንነት መኖሩን ጠቅሰዋል። የክትባት ተደራሽነትን ለማስፋት በርካታ ሥራዎች የተሠሩ ቢሆንም አሁንም ክትባት ማግኘት ያለባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ሙሉ ለሙሉ ክትባት እያገኙ እንዳልሆነ አክለዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከአራት ልጆች አንዱ ያልተከተበ መሆኑን ጥናቶችም ያመላከቱ ሲሆን፤ እ.አ.አ በ2023 ይፋ የሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት በኢትዮጵያ የፀረ አምሥት የመጀመሪያ ደረጃ ክትባት የወሰዱ ሕፃናት 75 ከመቶ ብቻ መሆናቸውን ያሳያል።
ዓለም አቀፍ ክስተት የሆነው የኮቪድ-19 ወረርሽኝና ባለፉት ዓመታት የተከሰተው የአገራችን የፀጥታ መደፍረስ በክትባት አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳርፈዋል። በተለይም ሕፃናት በተቀመጠላቸው ጊዜ ክትባት እንዳያገኙ አድርጓል። በዚህም ከዚህ ቀደም በየዓመቱ የመከተቢያ ጊዜያቸው አልፏል በሚል ምክንያት ክትባት የማያገኙ ሕፃናት እንደነበሩ ያስታወሱት አቶ መልካሙ፤ ጤና ሚኒስቴር ችግሩን ለመቅረፍ ባለፉት አምሥት ዓመታት ያልተከተቡና ጀምረው ያቋረጡት ልጆችን በመለየት ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል የማካካሻ ክትባት ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ገልፀዋል። በዚህም ማንኛውንም ዕድሜው ከአምሥት ዓመት በታች የሆነ ሕፃን እስከ አሁን ያልተከተበ ወይም ደግሞ ጀምሮ ያቋረጠ ቢሆንም የክትባት ጌዜ አልፎበታል ሳይባል መከተብ የሚችልበት መንገድ የተመቻቸ በመሆኑ ወላጆች ይህንን ዕድል በመጠቀም ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ መክረዋል። እንደ እርሳቸው ገለፃ በቀጣይ አዳዲስ ያልተከተቡ ልጆች እንዳይኖሩ ለማድረግ መደበኛውን የክትባት ሥርዓት ካለው የጤና ሥርዓት ጋር በማቀናጀት እንዲሻሻል ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
በአስቸጋሪ መልክዓ ምድር ምክንያት የጤና ተቋማት በቅርበት ለማያገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችና ኑሯቸውን ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ ለሚመሩ አርብቶ አደሮችም የክትባት አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ተንቀሳቃሽ ጊዜያዊ የክትባት መስጫ ማዕከላት በማቋቋምና ማኅበረሰቡ እንዲያውቃቸው በማድረግ ክትባት እየተሰጠ ይገኛል።
እንደ አገር በራስ አቅም የማይበገር የጤና ሥርዓት መገንባት ቀደም ብለው የተዘረዘሩ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያስችላል። መደበኛውን የክትባት አገልግሎት ማጠናከርና የባለሙያዎችን አቅም መገንባት ይሻል። ለክትባት አስቸጋሪ በሆኑ አከባቢዎች ተንቀሳቃሽ እና ጊዚያዊ የክትባት መስጫ ማዕከላት ማዋቀር፣ ግብዓት እንዲሟላ ጥረት ማድረግ እንዲሁም በኤሌክትሪክ መቆራረጥ ምክንያት የሚጋጥምን የክትባት መቆራረጥ ለማስቀረት በፀሀይ ኃይል የሚሰሩ
ማቀዝቀዣዎችን ማሰራጨት በመፍትሔነት እየተተገበሩ ያሉ ሥራዎች ናቸው። የማኅበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ከመገናኛ ብዙኃን እና ከአጋሮች ጋር በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል የሚሉት አቶ መልካሙ፣ ከፖሊሲ ማሻሻል ጀምሮ በርካታ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ዘርዝረዋል።
የተገኙ ውጤቶች
በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ የክትባት ሽፋን እና ተደራሽነት እያደገ መምጣትና የአገልግሎቱ መስፋፋት በርካታ ውጤቶችን አስገኝቷል። በተፈጥሮ የሚገኘውን የልጅነት ልምሻ የሚያመጣ ቫይረስ በክትባት አማካኝነት ከአገር ለማጥፋት ተችሏል። ለዚህም ኢትዮጵያ ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት መቻሏን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ከዓለም ጤና ድርጅት ተቀብላለች። ይህ ክትባት ካስገኛቸው ድሎች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። ሆኖም አሁንም ለዚህ ቫይረስ ተጋላጭ በመሆናችን ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል የሚሉት አቶ መልካሙ ክትባት የሚሰጠውም ለዚሁ ዓላማ መሆኑን ያስረዳሉ። ባሕሪውን ቀይሮ የመጣ የፖሊዮ በሽታ በመኖሩ ክትባቱን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ባይ ናቸው።
ክትባት በአገራችን በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙ ወረርሽኞችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ ትልቅ አስተዋጽኦ ነበረው። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭትን መቆጣጠር የተቻለው በክትባት አማካኝነት ነው። በአጠቃላይ ክትባት በአገራችን ይደርስ የነበረውን ሞት፣ ሕመምና የአካል ጉዳት በመቀነስ ጉልህ አበርክቶ አለው።
የማካካሻ ክትባት ማዘጋጀት በበርካታ አገራት ዘንድ የተለመደ አይደለም የሚሉት አቶ መልካሙ በአገራችን የማካካሻ ክትባት መጀመሩ ትልቅ እመርታ እንደሆነና እስከ አሁን ከአንድ ሚሊዮን በላይ በተለያዩ ምክንያቶች መደበኛ ክትባት ያልተከተቡ ዜሮ ዶዝ ሕጻናት የማካካሻ ክትባት እንዲያገኙ መደረጉን ገልፀዋል። ተንቀሳቃሽ እና የውሎ ገብ የክትባት ማዕከላትን በማቋቋም፤ የጤና ኤክስቴንሽን አደረጃጀትን በመጠቀም እንዲሁም ከሃይማኖት አባቶች ጋር በመምከር ጭምር ያልተከተቡ ሕጻናትን በማስከተብ የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለማሳደግ የተሠራው ሥራ ውጤታማ ሆኗል። የክትባት አገልግሎት መስጠት ሚያስችል የሰው ኃይል ከማብቃትና የማኅበረሰቡን ግንዛቤ ከማሳደግ አንጻርም ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው።
ቀጣይ ዕቅዶች
መደበኛውን የክትባት አገልግሎት አጠናክሮ ማስቀጠል አሁንም በትኩረት የሚሠራበት ጉዳይ እንደሆነ የገለፁት አቶ መልካሙ፤ ያልተከተቡ ልጆችን ሙሉ በሙሉ በመለየት እንዲከተቡ ማድረግ ሌላው የትኩረት መስክ ነው። በአገሪቷ በርካታ ያልተከተቡ ልጆች ስለመኖራቸው መረጃዎች ያመላከቱ በመሆኑ እነዚህን ልጆች ፈልጎ ማግኘት ያስፈልጋል። ሙሉ በሙሉ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ እስከ አሁን ያልተከተቡ ወይም ጀምረው ያቋረጡ ሕፃናት እንዲከተቡ ይደረጋል። አዳዲስ የበጎ ተነሳሽነት ክትባቶች ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፤ የሰው ኃይል የአቅም ግንባታን በበለጠ ማጠናከር፣ ከመገናኛ ብዙኃን እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል በጤና ሚኒስቴር ቀጣይ ዕቅዶች ውስጥ ተካተዋል።
ማኅበራዊ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
የአገልግሎቶቹ የጀርባ አጥንት
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ
በፍቅርተ ባልቻ
ታሪክን የኋሊት …
ለሙያው መሰረት እንደጣለች የሚነገርላት ከእንግሊዝ ኃብታም ቤተሰቦች የተወለደችው ፍሎረንስ ናይቲንጌል (Florence Night- ingale) ሳይንሳዊ መርሆዎችን እና ፍልስፍናዎችን በመከተል፣ በትምህርትም በመታገዝ የሰዎችን ሕመምና ስቃይ እንዲሁም አጠቃላይ የጤንነት ሁኔታ በሚገባ ማሻሻል እንደሚቻል ያላትን እምነት በተግባር ያሳየች ትጉህ እና ባለ ብሩህ አዕምሮ ሴት ስለመሆኗ ታሪኳ ያስረዳል።
እ.አ.አ ከ1854 ዓ.ም ጀምሮ በእንግሊዝ የተካሄደውን ጦርነት
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
(Britain’s Crimean War) ይህን እሳቤዋን በተግባር ለመፈተሽ እንደተጠቀመችበት መዛግብት ከትበውታል። የመጀመሪያዋ ነርስ በመሆን በጦር ሜዳ ላይ የተጎዱ ወታደሮችን በማከምና በመንከባከብ አስደናቂ ሥራ እንደሠራች ታሪክ ምስክር ነው፡፡ በዚህ ወቅት የተገኘው ስኬት ለሕክምና ሙያ ዕድገትና መስፋፋት ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ይህን ተከትሎ የከተሞች ዕድገትና የኢንዱስትሪ መስፋፋት ቤት ለቤት ይሰጥ የነበረው የነርሶች አገልግሎት ለሕክምና ተቋማትም እንደሚያስፈልግ ግልጽ እንዲሆን አደርጓል። ይህን ፍላጎት ለማሟላትም ሆስፒታሎች ነርሶችን የሚያሠለጥኑበትን የመማር ማስተማር ሂደት ቀርጸው ሥራ ላይ አውለዋል።
ወደ አገራችን ስንመጣ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ነርስ ልዕልት ፀሐይ ኃይለስላሴ ናቸው፤ የአፄ
ኃይለሥላሴ ልጅ። ልዕልት ፀሐይ በውጭ አገር በነበራቸው ቆይታ ያገኙትን ዕውቀት በመጠቀም በነርስነት ማገልገላቸውን ታሪካቸው ያስረዳል። በኋላም እ.አ.አ በ1944 ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ አገራት በመሄድ በመስኩ መሠልጠናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የተከናወነውና ‘Paradigm shifting in postgraduate nursing education in Ethi- opia‘ በሚል ርዕስ እ.አ.አ 2023 በ Millennium Journal of Health የታተመው ጥናት “በኢትዮጵያ የነርሲንግ ሥልጠና መሰጠት የተጀመረው እ.አ.አ በ1949 በቀይ መስቀል ማኅበር አማካኝነት በአሁኑ የካቲት 12 ሆስፒታል በቀድሞው ኃይለሥላሴ ሆስፒታል ሲሆን፤ እ.አ.አ በ1953 ተማሪዎችን ማስመረቅ ተችሏል” ይላል።
በመቀጠልም እ.አ.አ በ1954 በጎንደር በተከፈተው የጤና ኮሌጅ ውስጥ የነርሶች ሥልጠና መስጠት ተጀምሯል። በኢትዮጵያ የነርሲንግ ትምህርት ለረጅም ጊዜ በዲፕሎማ ደረጃ የሚሰጥ ቢሆንም ወደ ሥራ ሲገቡ ሰፊ ትምህርት እና ጥልቅ ክህሎት የሚጠይቁ ውስብስብና ሰፊ ተግባራትን እንዲያከናውኑ የሚደረግ መሆኑን ጥናቱ ጠቅሷል።
ጥቂት ስለ ነርሲንግ
“ለታመሙ፣ ለተጎዱ፣ አደጋ ለደረሰባቸው፣ ለአቅመ ደካሞች፣ በጥቅሉ የተለያየ ዓይነት እገዛ ለሚሹ ሰዎች ተከታታይ ክትትልና እንክብካቤ የሚሰጥበት ሙያ ነው። ነርሲንግ የሠዎችን፣ የቤተሠብን፣ በአጠቃላይ የማኅበረሰብን ጤና የመጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት የተጣለበት የሙያ መስክ ነው” በሚል የገለጸው ‘Assessment on factors affect- ing implementation of nursing process among nurses in selected governmen- tal hospitals‘ በሚል ርዕስ በሙሉጌታ አስራቴ ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የተሰራው ጥናት ነው።
ጥናቱ አያይዞም ነርሶች መሰረታዊ የጤና አጠባበቅ እንዲሁም ልዩ አገልግሎቶች (Specialty Ser- vices) የሚሰጡበት ሙያ እንደሆነ፤ በተናጠል እንዲሁም ከሌሎች የሕክምና ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት የሚሠራበትና የተለያዩ አገልግሎቶች የሚሰጡበት መሆኑን ጠቅሷል።
ይህን ተግባር የሚከውኑት ሙያተኞች (ነርሶች) በጤና አጠባበቅ ጥናት እና ምርምሮች፣ ከጤና ጋር በተያያዙ የአስተዳደር ጉዳዮች፣ በፖሊሲ እና በሕግ ማዕቀፍ ዝግጅቶች ወቅት እንዲሁም ለሕሙማን ግንዛቤ በመፍጠር (Patient ad- vocacy) ሂደት ንቁ ተሳታፊዎች መሆናቸውንም ጥናቱ አስነብቧል።
እ.አ.አ ሰኔ 2025 ይፋ የሆነው Encyclope- dia Britannica መረጃ በአሜሪካ ብቻ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን የተመዘገቡ ነርሶች እንዳሉ ጠቅሶ “በጣም ሰፊ፣ ዘርፈ ብዙ እና የተከበረ ሙያ ነው” ሲል ገልጾታል። ነርሲንግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅ፣ ከመታወቅም አልፎ የበርካቶችን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል ፈርጀ ብዙ ኃላፊነቶችን እየተወጣ ያለ የሙያ መስክ ነው።
ነርሲንግ በራሱ ሙያ ሆኖ የተመሰከረለት፣ መተዳደሪያ ደንብ እና ፍልስፍናዎች ያሉት፣ የራሱን አሠራሮች የሚከተል የሙያ መስክ ነው። በነርሶች አማካኝነት የሚሰጡ አገልግሎቶች የሆስፒታሎች እና ሌሎች የጤና ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ በእጅጉ ለውጠውታል።
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ነርሲንግ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል
በአገራችን ይህንን የሙያ መስክ በተገቢው እና በአግባቡ መጠቀም ብሎም ሙያኞችን ማፍራት እንዲቻል የጤና እና የትምህርት ሚኒስቴሮች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰሩ ስለመሆኑ መረዳት ይቻላል። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚኒሊየም ሚዲካል ኮሌጅ ከመስኩ ተዋንያን ጋር በመተባበር የነርሲንግ ሙያተኞችን በማሠልጠን ወደ ሥራ ከሚያስገቡ ተቋማት መካከል ግንባር ቀደም ነው።
የጤና ሚኒስቴር ነርሲንግን ከዓለም አቀፍ ሁኔታዎች አንጻር እየቃኘ ሰነዶች፣ የአሰራር መመሪያዎች፣ ደንቦች እና የመሳሰሉትን ያዘጋጃል። እነዚህን ሰነዶች ኮሌጁ ከተቋሙ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማቆራኘት የራሱን የሕግ ማዕቀፎችና አሠራሮች በማዘጋጀት ሥራ ላይ ያውላል።
በተቋሙ የነርሲንግ ባለሙያዎችን እና ሥራዎቻቸውን የሚያስተባብር የሥራ ክፍል አለ። በተለያየ ጊዜ የተለያየ ስያሜና አደረጃጀት እየተሰጠው ቆይቷል። ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት (Nurs- ing/midwifery Directorate) በሚል ተደራጅቶ እስከ አሁን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል። ዳይሬክቶሬቱ ተጠሪነቱ ለሜዲካል ዳይሬክተሩ ሲሆን አንድ ዋና ዳይሬክተር እና አንድ ምክትል ዳይሬክተር አለው።
የተቋሙን የነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ አጠቃላይ ሥራዎች አፈጻጸም የሚከታተሉ ሁለት ቡድኖች አሉት። ኳሊቲ እና ኦዲት አንደኛው ቡድን ሲሆን የነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ ሱፐርቫይዘሪ ሁለተኛው ቡድን ነው። እነዚህ ሁለት ቡድኖች እያንዳንዳቸው 13 ባለሙያዎችን የያዙና መርኃ ግብር እየወጣላቸው ከሰኞ እስከ ሰኞ (24/7) የሚሠሩ፤ በአጠቃላይ በሆስፒታሉ የነርስ እና የሚድዋይፍ እንክብካቤ ምን እንደሚመስል የሚከታተሉ፤ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርጉ ናቸው።
ከዚህ በታች ያለው አወቃቀር በሥራ ክፍሎች ስር ያሉ አገልግሎቶችን ለመስጠት እንዲያመች ተደርጎ የተሠራ ነው። በተለያዩ ዳይሬክቶሬቶች ለነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ ዳይሬክቶሬት ተጠሪ የሆኑ 13 ምክትል ነርስ ኃላፊዎች አሉ። ለምሣሌ የውስጥ ደዌ፣ የቀዶ ሕክምና፣ የዓይን እና የጥርስ ሕክምናን በመሳሰሉ ሰፋፊ አገልግሎቶች በሚሰጥባቸው የሥራ ክፍሎች ውስጥ አንድ አንድ ምክትል ነርስ ኃላፊዎች አሉ። እነዚህ ኃላፊዎች ሁለትም ሦስትም ኬዝቲም አስተባባሪዎችን ይመራሉ፣ ያስተባብራሉ።
ከሥራ ክፍሎች ጋር አብረው የሚሠሩት ምክትል ኃላፊዎች የነርስ እና ሚድዋይፎችን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ይከታተላሉ፣ ይቆጣጠራሉ። ተጠሪነታቸውም ላሉበት የሥራ ክፍልና ለነርሲንግ እና ሚዲዋይፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ነው። ይህም እንደየሥራ ክፍሉ ባህሪይ ከሐኪሞች፣ ከላቦራቶሪ ባለሙያዎች እንዲሁም ከሌሎች ጋር በመቀናጀት አገልግሎት መስጠት እንዲቻል ታሳቢ ተደርጎ የተዘረጋ አሠራርና አደረጃጀት ነው።
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚኒሊየም ሚዲካል ኮሌጅ 1 ሺህ 134 ነርሶች እና ሚድዋይፎች ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥ 70 በመቶዎቹ ሴቶች፤ ቀሪዎቹ ወንዶች ናቸው። ባለሙያዎቹ በተለያየ ጊዜ ከሚወስዷቸው አጫጭር ሥልጠናዎች ባሻገር
በመደበኛ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ናቸው። እነዚህን ባለሙያዎች የሚከታተሉና ድጋፍ የሚያደርጉ በየደረጃው የሚገኙ 80 መካከለኛ አመራሮች በነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ ዳይሬክቶሬት ስር ይገኛሉ።
ተቋሙን በ1998 ዓ.ም የተቀላቀሉት ሲስተር እየሩሳሌም ክንፈ በባለሙያነትና በተለያዩ ኃላፊነቶች ሲያገለግሉ ቆይተው ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ አሁንም ድረስ (ለሰባት ዓመታት) የሥራ ክፍሉ ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። “ወደዚህ ዳይሬክቶሬት ስመጣ ሥራዬን የጀመርኩት በተቋማችን ነርሶች እንዴት እየሠሩ ነው፣ መሻሻል
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ያለባቸው ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው? ወደየትኛው ደረጃ ማድረስ እንችላለን? በሚሉ ነጥቦች ላይ ትኩረት በማድረግ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የተቋሙ ኃላፊዎችና ሐኪሞች ጋር በመነጋገር ነው” ይላሉ።
ሲስተር እየሩሳሌም ይህን ተከትሎ የተደረጉትን ለውጦችና የማሻሻያ እርምጃዎች “ነርሶች ምን እንደሚሰሩ (scope of practice) በግልጽ ያስቀመጡ መመሪያዎች እና ደንቦች እንዲኖሩ ተደርጓል። እያንዳንዱ አገልግሎት የሚሰጥበት መመዘኛ ተዘጋጅቷል። ሰነዶቹ አንድን ሥራ ማን እንደሚሠራው፣ እንዴት እንደሚሠራ፣ ምን እንደሚያስፈልግ በቀላሉ ለማወቅ ያስቻሉ ናቸው” በማለት ነው የገለጹት።
እያንዳንዱ ነርስ እና ሚድዋይፈሪ እርስ በእርሱ እንዲሁም ከተገልጋይ ጋር ምን ዓይነት ተግባቦት እንደሚኖረው የሚያስረዳ ሰነድ (Commu-
nication Protocol) ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ እንዲውል መደረጉን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም በየሥራ ክፍሎች የሥራውን መጠን ከነርሶች እና ሚድዋይፎች ቁጥር ጋር ለማመጣጠን በሚጠቀሙበት የበሽተኛ ነርስ/ሚድዋይፍ ምጣኔ (work force ratio) ስሌት መሰረት የባለሙያ ምደባ እንደሚደረግ አብራርተዋል።
አቅም ማጎልበት - ለላቀ አገልግሎት
በአትዮጵያ የነርሶች ማኅበር እ.አ.አ በ1952 ተመስርቶ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝና የአባላቱን አቅም ለማሳደግ ሁለገብ ሥራ በመሥራት ላይ የሚገኝ የሙያ ማኅበር ነው። ሲስተር እየሩሳሌም ከዚህ የሙያ ማኅበር እና ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር በመሆን ለባለሙያዎች የአጭር እና የረጅም ጊዜ ሥልጠናዎች እንዲያገኙ እየተመቻቸ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።
በአገራችን 109 ሺህ የሚሆኑ ነርሶች በመንግሥት ጤና ተቋማት በሥራ ላይ እንደሚገኙና እነዚህም የሙያ ማኅበሩ አባል መሆናቸውን ነግረውናል። ተከታታይነት ያለው የሙያ ማሻሻያ (Con- tinuous professional development) እና ሌሎች ሙያዊ ሥልጠናዎችን ለባለሙያዎቻችን ይሰጥልናል” ሲሉም የማኅበሩን እገዛ አንስተዋል።
በተቋሙ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ዶክተሮች ሰብ ስፔሻሊቲ ደረጃ ደርሰዋል። የነርሶች እና የሚድዋይፎችን ዕውቀት እና ክህሎት በዚያው ልክ ለማሳደግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን በዚህ ረገድ የተገኙ ውጤቶች አበረታች ናቸው።
የነርሲንግ ትምህርት ለዘመናት በዲፕሎማ ደረጃ ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም፤ አሁን ከመጀመሪያ ዲግሪ በተጨማሪ እስከ ፒኤችዲ መርሃ ግብር ወጥቶለታል። ነርሶች እና ሚድዋይፎች በውጭ አገራት ጭምር የአጭር እና የረጅም ጊዜ ሥልጠና እንዲያገኙ እየተደረገ ነው። ወደ ኮሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ታንዛያ፣ ሩዋንዳ፣ እና ሌሎችም አገራት እየሄዱ የስድስት ወር እና የአንድ ዓመት ሥልጠና እንዲወስዱ ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረላቸው ነው።
በመደበኛ ሁኔታ ከሚሠሩት የአቅም ግንባታ ሥራዎች ባሻገር እንደ ኮቪድ-19 ዓይነት ወረርሽኞች ሲከሰቱ በተለየ ሁኔታ ግንዛቤ የማስጨበጥና ባለሙያውን የማነቃቃት ተግባራት ይከናወናሉ። የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሐኪሞችን ሲያሠለጥኑ፣ ነርሶችም አብረው እንዲሠለጥኑ ይደረጋል።
“ነርሶች እና ሚድዋይፎች ስፔሻላይዝድ እንዲያደርጉ በራሳችን የነርሲንግ ኮሌጅ እናስተምራለን” ያሉት ሲስተር እየሩሳሌም በየዓመቱ በማሠልጠን ብቁ ባለሙያዎችን እያፈሩ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።
ከዚህ ቀደም ባለሙያዎቻችንን ሥራቸውን አቋርጠው ወደ ተለያዩ የጤና ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች በመላክ እንዲማሩ እናደርግ ነበር ያሉት ዳይሬክተሯ አሁን ግን በተቋማችን የነርሲንግ ትምህርት (Resi- dency program) በመጀመሩ ሥራቸውን እየሠሩ ጎን ለጎን ዕውቀትና ክህሎታቸውን እንዲያሳደጉ ማድረግ መቻሉ ትልቅ ስኬት እንደሆነ ነው የሚገልጹት።
ዳይሬክቶሬቱ በስሩ በርካታ ባለሙያዎችን የያዘ እንደመሆኑ በተለይ ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን አገልግሎቶችና ሕክምናዎች በመለየት በእነዚያ ላይ በቂ ዕውቅትና ክህሎት ያላቸው ባለሙያዎች እንዲሠለጥኑ እየተሠራ ነው። በተያያዘም በተለይ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ሰብ ስፔሻሊቲ የሚፈልጉ እንደ ፅኑ ሕሙማን፣ ንቅለ ተከላ፣ የጨረር ሕክምናዎች፣ የጨቅላ ሕጻናት ሕክምና፣ የልብ ማዕከላት እና የመሳሰሉት ላይ የሚመደቡ ነርሶች እና ሚድዋይፎች ስፔሻላይዝድ እንዲያደርጉ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
ስፔሻላይዝድ ያደረጉ ባለሙያዎች በሠለጠኑባቸው መስኮች እንዲሠሩ እንደሚደረግ የገለፁት ሲስተር እየሩሳሌም፤ “አንድ ክሪቲካል ኬር ማስተስርስ ያለውን ባለሙያ ለፅኑ ሕሙማን ታካሚዎች አስፈላጊ ስለሆነ አይሲዩ (ICU) ወይም ድንገተኛ (Emergency) ክፍሎች ውስጥ እንዲሠራ ነው የሚደረገው” በማለት ስለሚከተሉት አሠራር አብነት ጠቅሰዋል።
ተቋሙ በየጊዜው የሚደረጉ ክትትሎችን መነሻ በማድረግ የባለሙያዎችን ደረጃ በመለየት ዕውቅና ይሰጣል። የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች በልዩ ሁኔታ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ይደረጋል። ይህን አሠራር መከተላችን የአገልግሎት አሰጣጣችንን የተሻለ ለማድረግ አስችሎናል ይላሉ ዋና ዳይሬክተሯ። በተገልጋዮች በኩል ስላለው ግብረመልስ ሲገልጹም “እኛ እንደ ተቋም በተለይ ተኝተው የሚታከሙ ተገልጋዮችን እርካታ እንከታተላለን በዚህም ወደ ተቋሙ የሚመጣ አብዛኛው ታካሚ በባለሙያዎቻችን ደስተኛ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል” ነው ያሉት።
የቤት ሥራዎች
በኢትዮጵያ በመንግሥት መዋቅር ብቻ 109 ሺህ ነርሶች እንዳሉ መረጃዎች ያመላክታሉ። በግል የሕክምና ተቋማት የሚሠሩት ሲጨመሩ ቁጥሩ ከዚህ ይበልጣል። ይህ አሃዝ በጤና ሥርዓቱ ውስጥ ትልቁን ኃላፊነት ወስደው እየሠሩ ያሉት እነዚህ ባለሙያዎች መሆናቸውን ያመላክታል።
የነርሲንግ ሙያ እና ሙያተኞች በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን የሚያሳልጡ የአገልግሎቶቹ የጀርባ አጥንት ናቸው። የተቋማቱን የሥራ ጫና ከማቃለል ባሻገር የታካሚዎችን ሕመም እና ስቃይ ለማቅለል ደፋ ቀና የሚሉ፣ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ቀንም ሆነ ሌሊት ከሕሙማን ጎን የማይጠፉ የክፉ ቀን ደራሾች ናቸው። ሲስተር እየሩሳሌም “ሙያው እጅግ የተከበረና በጣም ዋጋ ያለው ቢሆንም፣ በዛ ልክ ነርስ እና ሚድዋይፎች በሚገባቸው ደረጃ ላይ ናቸው የሚል እምነት የለኝም” ይላሉ። ስለሆነም ሙያው እና ሙያተኞቹ በሚገባቸው ደረጃ ላይ እንዲገኙ ብዙ መሥራት ይጠይቃል።
በየትኛውም አይነት ሙያ ሥራ ላይ የተሠማራ ሰው ምርታማና ውጤታማ እንዲሆን ጤንነቱ መጠበቅ እንዳለበት እርግጥ ነው። በማኅበረሰቡ ጤና ላይ የሚሠሩ ባለሙያዎች የሚማሩበት መንገድ ክፍተቶች እንደሚስተዋሉበት ያልሸሸጉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በሙያው መሠልጠን ሥራ እንደ ሥራ ማግኛ ተደርጎ እየተወሰደ መሆኑን በማንሳት የማኅበረሰብ ጤና ከምንም በላይ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ በመሆኑ ይህ አመለካከት መቀየር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ይህንን እሳቤ ለማስተካከል በተለይ በመማር ማስተማሩ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ያስፈልጋል። ነርስ እና ሚድዋይፈሪ የተከበረ ሙያ እንዲሆን ባለድርሻ አካላት የተጣለባቸው ኃላፊነት ትልቅ ነው። የመስኩ ተዋንያንም ይህንን ተገንዝበው ለውጥ ለማምጣት መትጋት
ይጠበቅባቸዋል።
ከሥርዓተ ትምህርቱ ጀምሮ የመማር ማስተማሪያ ስልቶች (Methdologys) በአግባቡ ሊፈተሹ ይገባል። ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ በየደረጃው ባለሙያው (ዲፕሎማ፣ ዲግሪ፣ ማስተርስ፣ ፒኤች) ያለው ማን ምን ይሠራል የሚለውን ቁልጭ አድርጎ ማሳየት ቢቻል መልካም እንደሆነ ሲስተር እየሩሳሌም ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል። መንግሥትና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተለይ ሥነ-ምግባር የተላበሱ ሙያውን የሚወዱ ባለሙያዎችን ከማፍራት አንጻር ትልቅ ኃላፊነትና የቤት ሥራ አለባቸው።
“ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን (ISO) ያሟላ እውቅና የተሰጠው አገልግሎት እንዲኖረን እንፈልጋለን ለዚህም ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን” በማለት ሲስተር እየሩሳሌም ቀጣዩን ውጥናቸውን ገልጸዋል። ለዚህ ሥራ የሚመጥን ዕውቀትና ክህሎት ያለው ባለሙያ እንዲኖር ለማስቻል ክፍተቶችን ፈትሾ ለማረም እንደሚሰራ፤ ይህም በዋናነት ሙያተኞች በመማር ማስተማሩ ላይ እንዲሳተፉ በማመቻቸት እንደሚከወን ገልፀዋል።
ዕውቀትን ከክህሎት ጋር አጣምሮ በመሥራት፣ ክትትል በማድረግና ሥልጠናዎችን በመስጠት ሙያውን የላቀ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ‘ነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት’ በምስራቅ አፍሪካ የነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ አገልግሎቶች የልህቀት ማዕከል የመሆን ራዕይ ሰንቋል።
ፖለቲካ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ሉዓላዊነትን የማስጠበቅ
አንዱ እርምጃ
በፍቅርተ ባልቻ
የዓለማችን 295 ሚሊዮን ሕዝብ የምግብ ዋስትናው ያልተረጋገጠ ስለመሆኑ ይፋ ተደርጓል። ይህን መረጃ ይፋ ያደረገው “Global Report on Food Crises - GRFC” በሚል ርዕስ እ.አ.አ 2025 ‘Global Network Against Food Crises’ የተሰኘው ተቋም ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመሆን ያካሄደው የዳሰሳ ጥናት ውጤት ነው።
የዳሰሳ ጥናቱ በ65 የዓለም አገራት ላይ የተካሄደ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 53ቱ እጅግ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ የምግብ ዋስትና ችግር እንዳለባቸው አመላክቷል። በተጨማሪም ከስድስት እስከ 59 ወራት ዕድሜ ያላቸው 37 ሚሊዮን ሕጻናት
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
የተመጣጠነ ምግብ እንደማያገኙ፣ ከእነዚህም ውስጥ 10 በመቶው ሕይወታቸው አደጋ ላይ ስለመሆኑ ተገልጿል።
ይኸው ሰነድ አያይዞ እንደገለፀው በዓለማችን እየተስተዋሉ ያሉ የጂኦ ፖለቲካዊ ውጥረቶች፣ የዓለም ኢኮኖሚ ተለዋዋጭ መሆን፣ ከጸጥታ እና ደህንነት ችግሮች ጋር ተዳምረው እ.አ.አ 2025 የሚኖረውን የምግብ ዋስትና ችግር በተለይ በተወሰኑ አገራት ስር የሰደደ እንዲሆን እንደሚያደርጉ ጠቅሷል።
የዓለምን ሕዝብ የምግብ ዋስትና እየተፈታተኑ ካሉትና እንደመንስኤ ከተጠቀሱ ችግሮች መካከል አንደኛው የጸጥታ ሁኔታ ነው። ይህም ቀደም ሲል የተመላከተው ጥናት ከተካሄደባቸው አገራት መካከል በሃያዎቹ ውስጥ ለ140 ሚሊዮን ሕዝብ የምግብ እጥረት መንስኤ ስለመሆኑ ተጠቅሷል። የአየር ንብረት ለውጥ በምግብ አቅርቦት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ሌላው ምክንያት በመሆን 96 ሚሊዮን ሕዝብ ለችግሩ ተጋላጭ ማድረጉ ተረጋግጧል ሲል መረጃው አመላክቷል።
ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች በበኩላቸው ከ59 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የምግብ ዋስትና እንዳሳጡ ይህም ጥናቱ ከተሰራባቸው አገራት መካከል በ15ቱ መንስኤ መሆናቸው ታይቷል። ቀደም ሲል በተጠቀሱት መንስኤዎች ሳቢያ የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ እንደሚቸገሩ የተለዩ አብዛኞቹ አገራት በአፍሪካ የሚገኙ ሲሆኑ የተቀሩት የደቡብ አሜሪካ እና የካሪቢያን፣ የእስያ አገራት ናቸው። የሩሲያ እና ዩክሬይን ጦርነት በምግብ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳረፉ እንደማይቀር እየተነገረ ነው፡፡
የሥርዓተ ምግብ ምንነት
ሕይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ
ያለ ምግብ መኖር እንደማይችሉ ይታወቃል፡ ፡ ለዚህም ነው ምግብ መሰረታዊ ፍላጎትን ከሚያሟሉ ነገሮች አንዱ እንደሆነ የሚጠቀሰው፡ ፡ የሰው ልጅ በዚህ ዓለም በሕይወት እንዲቆይ አየር፣ ውሃ እና ምግብ እጅግ በጣም አስፈላጊ እና ጠቃሚዎች ናቸው። በመሆኑም እነዚህን ለሰው ልጅ በሕይወት መቆየት ወሳኝ የሆኑ አየር፣ ውሃ እና ምግብ እንዴት እየተንከባከባቸው ነው? እንዴትስ እየተጠቀመባቸው ነው? የሚሉት መሰረታዊ እና መነሳት ያለባቸው ጥያቄዎች ናቸው።
ምግብ ለሰውነታችን ሙቀትና ብርታትን ይሰጣል፣ ሰውነትን ይጠግናል፣ በሽታ ለመከላከል ይረዳል፣ ለሰውነትና ለአዕምሮ ዕድገት ጠቃሚ ከመሆኑ ባሻገር የዕለት ተዕለት ተግባራት እንዲከናወኑ ይረዳል።
የምግብ እጦት ከአካላዊ ድካም በዘለለ በሰው ልጅ አዕምሯዊ ደህንነትና ስሜት ላይ ጭምር ተጽዕኖ ያሳድራል። ይህም ሰዎች ለድህነት ያላቸውን ተጋላጭነት ከመጨመር አልፎ ለጤና እክል ይዳርጋል፣ ምርታማነትን ይቀንሳል።
በ2011 ዓ.ም የተዘጋጀው የኢትዮጵያ የምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ፖሊሲ “ማንኛውም በአንድ አገር ውስጥ እንዲበላ የተፈቀደ ምግብና መጠጥ ምግብ ይሰኛል” ሲል ይተረጉመዋል። ይኸው ፖሊሲ ሥርዓተ ምግብን “ምግብ መመገብን፣ የምግብ መፈጨትን፣ የምግብ በሰውነት ውስጥ መዋሃድንና የንጥረ ምግቦች ጥቅም ላይ መዋልን፤ ይህም ውህደት የሰውነት አካላዊና አዕምሯዊ ዕድገትና ብልጽግና፣ በሽታ የመከላከልና የመቋቋም ሂደትን የሚያጠና ሳይንስ ነው” ሲል ገልጾታል።
ስለሆነም ሥርዓተ ምግብ የምግብንና በምግብ ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ምግቦችን፣ የአመጋገብ ሥርዓትን፣ በሰውነታችን ውስጥ ያለ የምግብ አጠቃቀምና በምግብና በጤና መካከል ያለውን ግንኙነትና ለውጥ የሚያጠና ሳይንስ መሆኑን መረዳት ይቻላል።
ፖሊሲው የሥርዓተ ምግብ ዋስትና “ሁሉም ሰው በማንኛውም ጊዜ ፍላጎቱንና ምርጫውን የሚያሟላ ጤነኛና ብሩህ ሕይወት እንዲኖረው ጥራቱን የጠበቀና በዓይነት፣ በስብጥር፣ በደህንነትና በንጥረ ምግብ ይዘቱ በቂ የሆነ ምግብ የማግኘት እንዲሁም በቂ የጤና እንክብካቤ፣ በቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦትና ፅዱ የመኖሪያ አካባቢ፣ በቤተሰብና ማኅበረሰብ ደረጃ ስለ ሕጻናት ክብካቤ፣ ስለ ምግብ አዘገጃጀትና አያያዝ በቂ ዕውቀት ማግኘት ነው” ሲልም ያብራራል።
ንጥረ ምግቦች (Nutrients) በምግብ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች ሲሆኑ ለሰውነት ኃይል፣ ለህዋሶች መታደስ፣ በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቅመሞች በትክክል እንዲሰሩና ትክክለኛ የሰውነት ዕድገት እንዲኖር ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ በምግብ ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች ስለመሆናቸው ፖሊሲው ጠቅሷል።
ንጥረ ምግቦች ሰውነት እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በሚገባ እንዲያከናውን የሚረዱና በተለያዩ ምግቦች ውስጥ የሚገኙ ውህዶች ናቸው። የንጥረ ምግብ አለመመጣጠን (እጥረት) በተለያየ ምክንያት ሊከሰት ይችላል። የተለያዩ ንጥረ ምግቦች በሰውነት ውስጥ አለመሟላት ለተለያዩ የጤና ችግሮች ሊያጋልጡ እንደሚችሉ ግልጽ የመሆኑን ያህል የንጥረ ምግብ አለመመጣጠንንም ሊያስተጓጉሉ የሚችሉ አጋጣሚዎችም በርካታ ናቸው፡፡
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ከእነዚህም ውስጥ የአመጋገብ ሥርዓት መዛባትና የምግብ እጥረት፣ የኢኮኖሚ ችግሮች (የኑሮ ሁኔታ)፣ የሃይማኖትና የባሕል ተጽዕኖ፣ የአመጋገብ ልምድ ማነስና የግንዛቤ እጥረት፣ የተሟላ ጤና ያለመኖር እንደ ምክንያት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ሰውነታችን አስፈላጊ የሆኑ ቫይታሚን፣ ሚኒራሎች እና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች በማያገኝበት ጊዜ የምግብ እጥረት ተከሰተ እንላለን። አልሚ ምግብ (Nutrition) ሲበዛ ወይም ሲያንስ የምግብ እጥረት ይከሰታል።
ሁሉም ሰው ጥራት ያለው ጤነኛ ሕይወት ለመምራት እንዲሁም የቀን የምግብ ፍላጎቱንና የምግብ ምርጫውን የሚያሟላ በቂ፣ የተመጣጠነና ደህንነቱ የተረጋገጠ ምግብ በማንኛውም ጊዜ ለማግኘት ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ተደራሽነት ሲኖረው፤ በአንድ አገር የምግብ ዋስትና ተረጋግጧል እንላለን።
የምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ፖሊሲ
አንድ አገር ፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገት ለማምጣትና ዘላቂ የልማት አቅም ለመገንባት ለዜጎች በማንኛውም ጊዜ የምግብ አቅርቦትና ተደራሽነትን ማረጋገጥ ይጠይቃል። ተደራሽ የሚሆነውም ምግብ ጥራቱ፣ ደህንነቱና የንጥረ ምግብ ይዘቱ የተሟላ ሲሆን ጤናማ፣ አምራች፣ ረዥም ዕድሜና አስተማማኝ የፈጠራ ብቃት ያለው ዜጋ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ ያግዛል።
በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጤናማ ሕይወት እንዲኖራቸው የማኅበረሰቡን የተመጣጠነ ምግብ ዕውቀትና የምግብ አጠቃቀም ማሳደግ፤ የምግብና የንጥረ ምግብ ሥርጭት ሰንሰለት ውስጥ የምግብ ጥራትና ደህንነትን ማረጋገጥ፤ የምግብና የንጥረ ምግብ ብክነትን መቀነስና የምግብና ሥርዓተ ምግብ አደጋን የመከላከል ዝግጁነትንና የመቋቋም አቅምን ማሳደግ ወሳኝ ነው።
ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ መንግሥት ላለፉት ዓመታት የተቀናጁና ስር ነቀል የኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ መርኃ ግብሮችን በመተግበር አዎንታዊ የማኅበራዊና የምጣኔ ኃብት ዕድገት መመዝገቡ ይገለፃል። ይህንን ዕድገት ለማስቀጠል የምግብና ሥርዓተ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚኖረው አስተዋጽኦ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም። የምግብና ሥርዓተ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል አግባብነት ያለው ፖሊሲ መኖሩም በመስኩ የሚከናወኑ ተግባራትን ለማሳካት ጠቀሜታው የጎላ ነው።
የአገሪቷን የምግብና ሥርዓተ ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በርካታ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። በተያያዘ አርሶና አርብቶ አደሮችን በእርሻና ተፈጥሮ ኃብት፣ በእንስሳትና ዓሣ ኃብት መስክ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የተደረጉ ጥረቶች የሚጠቀሱ ናቸው። በአገሪቷ በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠሙ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን በራስ አቅም መከላከል መቻሉ አደጋዎችን የመቋቋም አቅም ማደጉን ያመላክታል።
የኢትዮጵያ የምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ፖሊሲ እንደሚገልፀው፤ በምግብና ሥርዓተ ምግብ ዙሪያ የተሠሩ ሥራዎች የሕጻናት መቀንጨርን ከ58 በመቶ ወደ 38 ነጥብ 4 በመቶ ሲቀንስ፤ የመክሳት ችግርን ደግሞ ከ41 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ዝቅ ማድረግ አስችሏል። የፖሊሲ ሰነዱ አክሎም የመቀጨጭ ችግር ከ12 በመቶ ወደ 9 ነጥብ 9
በመቶ መቀነሱን ጠቅሷል። በሕይወት ከሚወለዱ አንድ ሺህ ሕጻናት መካከል አምሥት ዓመት ሳይሞላቸው ይሞቱ የነበሩ 166 ሕጻናትን ቁጥር ወደ 67 መቀነሱን ሰነዱ ያመላከተ ሲሆን የዜጎች የዕድሜ ጣሪያ ከ45 ወደ 64 ዓመት ከፍ ማለቱን ገልጿል።
ሰነዱ ቀደም ሲል የተመላከቱት ለውጦች የተገኙ ቢሆንም አሁንም የሚስተዋሉ ችግሮች መኖራቸውን አልሸሸገም። ከዚህ አንጻር የሚጠቀሰው አንዱ ችግር የአገሪቷ የምግብ ምርት ዕድገት ከሕዝቧ ቁጥር ዕድገት ጋር ሲነጻጸር ያነሰ በመሆኑ የኅብረተሰቡን የምግብ ፍላጎት ለማሟላት አለመቻሉ ነው።
በዚህ ምክንያት በሁሉም የዕድሜ ክልልና የአኗኗር ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ለምግብና ሥርዓተ ምግብ ዋስትና ማጣትና ለተረጂነት እየተጋለጡ ይገኛሉ። በአገር አቀፍ ደረጃ 40 በመቶ የሚሆኑ ቤተሰቦች ከምግብ መገኘት ያለበት የኃይል እጥረት አጋጥሟቸዋል። ዝቅተኛ ምርትና ምርታማነት፣ ደህንነቱና ጥራቱ ያልተጠበቀ የምርት ሂደት፣ ደካማ የቅድመ እና የድህረ ምርት አያያዝ፣ ዝቅተኛ የእናቶችና የሕጻናት እንክብካቤ፣ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት እንዲሁም ከፍተኛ የግልና የአካባቢ ንጽህና ጉድለት አገሪቷን በዋናነት ለከፍተኛ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ዋስትና ችግሮች ዳርገዋታል።
እነዚህን ውስብስብና ፈርጀ ብዙ ተግዳሮቶች ለመፍታት መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በመታመኑ የምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ፖሊሲ ተቀርጾ በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱ ይታወቃል። ይህ ፖሊሲ ትኩረት የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለይቶም አቅጣጫ አስቀምጧል።
የተመጣጠነ፣ በንጥረ ምግብ ይዞታው የበለጸገና ደህንነቱ የተረጋገጠ ምግብ አቅርቦት፣ ተደራሽነትና አጠቃቀምን በዘላቂነት ማረጋገጥ አንደኛው አቅጣጫ ነው። የምግብ ደህንነት እና ጥራት ማረጋገጥ፤ የድህረ ምርት አያያዝን ማሻሻል፤ በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ዜጎች ተገቢ ሥርዓተ ምግብን ማረጋገጥ፤ ለተፈጥሮና ሰው ሰራሽ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
አደጋዎች ፈጣንና ተገቢ የምግብና የሥርዓተ ምግብ ምላሽ መስጠት፤ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ተግባቦትን ማጠናከር፤ የምግብና ሥርዓተ ምግብ አስተዳደር ማቋቋምና ማጠናከር የትኩረት መስኮች መሆናቸው በፖሊሲው ተመላክቷል።
ፖሊሲው የሥርዓተ ምግብን ጉዳይ ከሁሉም የዕድሜ ደረጃ ከሁሉም የትውልድ ዘመን አንጻር የሚያይ ነው። በተለይ ወሳኝ በሆኑት በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ማለትም ከፅንሰት እስከ ሁለት ዓመት፤ ሕጻናት ላይ ትልቅ ትኩረት የሚያደርግ መሆኑ ተጠቅሷል። በእነዚህ አንድ ሺህ ቀናት የሚደረገው የተስተካከለ አመጋገብ ሥርዓተ ምግብ በሕጻናቱ ሕይወት ዘላቂ የሆነ አዎንታዊ የአካልና የአዕምሮ ዕድገት የሚመጣና የወደፊት ሕይወታቸውን ብሩህ የሚያደርግ ስለመሆኑ በመስኩ ምሁራንም ይገለጻል።
የሥርዓተ ምግብ ሽግግር ጉባዔ
የዓለም መንግሥታት በጋራ መተግበር ፈተና ቢሆንባቸውም በጋራ ማቀድ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ከዚህ አንጻር
የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች (Millinium Development Goals/ MDG) እና ዘላቂ የልማት ግቦች (Sustainable Development Goals/SDG) የሚጠቀሱ የጋራ ዕቅዶች ናቸው። የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ደሀ አገራትን ማዕከል ሲያደርጉ፤ ዘላቂ የልማት ግቦች በሁሉም የዓለም አገራት የሚተገበሩ ናቸው።
እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር 2020 አሁን በትግበራ ላይ የሚገኙትን የልማት ግቦች ስኬት የገመገመው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሁሉም ግቦች በሚባል ደረጃ የተመዘገቡት ውጤቶች ከሚጠበቅባቸው በታች መሆናቸውን አረጋግጧል።
በተለይም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰት በኋላ በአንዳንዶቹ
ግቦች የአፈጻጸም መቀነስ መታየቱ ያሳሰበው የመንግሥታቱ ድርጅት የምግብ ሥርዓት ሽግግር ማምጣትን እንደ ስትራቴጂያዊ መፍትሔ መውሰዱን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬው ተገኘ (ዶ/ር) ይናገራሉ።
የእነዚህ የዘላቂ ልማት ግቦች ትግበራ በተያዘላቸው ፍጥነት እየተከናወኑ አለመሆኑን የአገራት መሪዎች መገምገማቸውን፤ ይህን ተከትሎ የአካሄድ ለውጥ ሊደረግ እንደሚገባ ከስምምነት ላይ በመድረሳቸው ሥራውን የሚመራ ግብረ ኃይል መቋቋሙን አስታውሰዋል።
ሽግግሩ የደረሰበትን ደረጃም የሁሉም አገራት መሪዎች በተገኙበት በሚካሄድ የዓለም የምግብ ሥርዓት ሽግግር ጉባዔ (UN Food System Summit) እንዲቀርብ ተወስኗል። የምግብ ሥርዓት ሽግግሩ የመጨረሻ ግብ እ.አ.አ በ2030 ለዓለም ሕዝብ በሙሉ ጤናማ የሆነ ምግብ ማቅረብ (Healthy Foods for All) ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተዘጋጁና ኢትዮጵያም ከተቀበለቻቸው ስምምነቶች መካከል ዘላቂ የልማት ግቦች እና የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ይገኙበታል። ኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ሽግግሩን አስፈላጊነት አምነው ከተቀበሉ የመጀመሪያዎቹ አገራት አንዷ ናት።
“ኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ሽግግርን ተቀብሎ ተግባራዊ በማድረግ ከቀዳሚዎቹ ጥቂት አገራት መካከል አንዷ ናት፣ በሐምሌ 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ሁነትም ለተጀመረው የምግብ ሥርዓት ሽግግር ሁለንተናዊ ጥረት እውቅና የሰጠ ነው” ሲሉ ዶ/ር ፍሬው ገልጸዋል።
“የሥርዓተ ምግብ ሽግግር ሥራውን ስንጀምር በመጀመሪያ ሥራው የሚመራበትን ጽሑፍ አዘጋጀን፤ በኋላም ወደ ተግባር ተለወጠ። ኢትዮጵያ የጀመረቻቸው በርካታ ኢኒሼቲቮች ስለነበሩ መልካም አጋጣሚ ሆነውልናል። ሥራውን እያስፋፋን ለመሄድም ጠቅመውናል” የሚሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ሽግግር ሥራዎችን መነሻ አብራርተዋል። ዋና ዳይሬክተሩ “በመጀመሪያ አካሄዳችንን አቀረብን፣ በቀጣዮቹ ጊዜያት ደግሞ የደረስንበትን እና ያገኘናቸውን ውጤቶች ለዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ እያሳወቅን ነው የመጣነው” ሲሉ ነው የነበረውን ሂደት የገለፁት።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ውይይት ሲካሄድ የምግብ ሥርዓቱን ሊያናጉ ከሚችሉ በርካታ መንስኤዎች ውስጥ አንዱ የአየር ንብረት ለውጥ እንደሆነ ተለይቷል። እንደ ዶ/ር ማንደፍሮ ገለፃ የአየር ንብረት ለውጡን ከምግብ ሥርዓት ሽግግር ጋር እንዴት አድርገን እናያይዘዋለን? የሚለው ንድፈ ሀሳብ እንዴት ወደ ተግባር እንደሚለወጥ በማጥናትና ወደ ዕቅድ በመለወጥ ወደ ማስፈጸም ነው የተገባው።
በሥርዓተ ምግብ ሽግግሩ የተሠሩ ሥራዎችና የተመዘገቡ ውጤቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ስለተሰጣቸው ጉባዔው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲካሄድ ተጽዕኖ አሳድሯል። “በጥቂት በመሥራታችን አፍሪካ ውስጥ በተለይም ኢትዮጵያ ላይ ይህ ትልቅ እና ዓለም አቀፍ ጉባዔ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
እንዲካሄድ የሚያደርግ ተጽዕኖ መፍጠር መቻሉ በቀጣይ ብዙ እንድንሠራ የሚያነሳሳ ነው” ሲሉም ዋና ዳይሬክተሩ አክለዋል።
የሥርዓተ ምግብ ሽግግሩን እውን የማድረግ ጥረቶች
ግብርና ዓለምን ከቀየሩ ዋና ዋና ክስተቶች አንዱ ነው። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ቀደምት ሥልጣኔ ከነበራቸውና የዕድገት ማማ ላይ ከነበሩ ጥቂት አገራት አንዷ ብትሆንም አሁን ወደኋላ ቀርታለች። ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች አሁንም እየወሰደች ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ አቅዳ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ገብታለች። ይህ ዕቅድ በአንድ በኩል ስኬቶች የተገኙበት ቢሆንም በዚያው ልክ በተለያዩ ውጣ ውረዶች ውስጥ እያለፈ ነው።
“ኢትዮጵያ በዓለም አገራት እና በዓለም ገበያ ላይ ጥገኛ ሳትሆን ዜጎቿን ለምን ያህል ጊዜ መመገብ ትችላለች? አገር ውስጥ ባለው ምርት ምን ያህል ጊዜ መቆየት ይቻላል?” ከምግብ ሉዓላዊነት ጋር በቀጥታ የተቆራኘ ጥያቄ እና ሀሳብ ነው። “እንደ አገር የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አለብን ስንል ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻ ያለውን የምግብ አመራረታችን በእኛ ቁጥጥር ስር መሆን አለበት ማለት ነው” ሲሉ የምግብ ሉዓላዊነትን ምንነት የሚያብራሩት የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ ናቸው።
በግለሰብ ደረጃ ሲገለጽ ገበያ ሳንወጣ፣ ወይም የሌላን ሰው እገዛ ሳንፈልግ ለምን ያህል ጊዜ መቆየት እንችላለን? የሚለው መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን በማንሳት፤ “መንግሥት ከውጭ የምናስገባውን ምርት በአገር ውስጥ መተካት አለብን ብሎ እየሠራ ያለው በምግብ ራስን መቻል አንዱ የሉዓላዊነት ማረጋገጫ ስለሆነ ነው” ብለዋል።
በቅድሚያ በዋናነት የምናስገባቸው ምግቦች የትኞቹ እንደሆኑ በመለየት ዕቅድ በማስቀመጥ ወደ ተግባር ተሸጋግሯል። በዚህ መሰረት ተሰርቶ ጥሩ ውጤት እየተመዘገበም ነው። ይሁንና አሁንም ቀሪ ሥራዎች አሉ። “ሉዓላዊነታችንን አረጋገጥን የምንለው ዜጎቻችን የሚመገቡት ምርት አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በአገራችን ቁጥጥር ስር ሲውል እና በራሳችን ማምረት ስንችል ነው” በማለት የሥራውን ክንዋኔ አብራርተዋል።
ማዳበሪያ፣ ሜካናይዜሽን፣ የመሳሰሉት… ማምረት፣ ማጓጓዝ፣ ማቀነባበር፣ ለጅምላ አከፋፋዮች እና ለቸርቻሪዎች ማሰራጨት በሙሉ የምግብ ሥርዓቱን ዕቅድ ተከትለው የሚሠሩ ናቸው። አንድ ዕቅድ ሲዘጋጅ እነዚህን በሙሉ ያካተተ መሆን አለበት። በሁለተኛ ደረጃ እዚህ ውስጥ ያሉ ተዋንያን እነማን እንደሆኑ ከግምት ውስጥ ያስገባ ዕቅድ ካልተዘጋጀ ስኬታማ መሆን እንደማይቻል ዶ/ር ማንደፍሮ አጽንኦት ሰጥተው ነው የገለፁት።
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
የምግብ ሥርዓት ከእርሻ እስከ ጉርሻ ያለውን የእሴት ሰንሰለት ያካትታል። ማምረት፣ መሰብሰብ እሴት መጨመር (ማቀነባበር)፣ ማጓጓዝ (ስርጭት)፣ ግብይት፣ መመገብ፣ ተረፈ ምርት ማስወገድ ወይም መጠቀምን ያካትታል። ስለዚህ ሥርዓተ ምግብ ‘ምግብ’ ከሚለው ጽንሰ ሃሳብ በዘለለ በሥርዓት ደረጃ ማሰብ፣ ማቀድን እና መተግበርን ይጠይቃል። ስለ ምግብ ሥርዓት ስንወያይ፣ ስናቅድ፣ ስንሠራ ሰው ተኮር መሆን ይኖርብናል ያሉት ዶክተር ፍሬው ምክንያቱ ደግሞ የምግብ ሥርዓት የሚሠራው ለሰው ስለሆነ ነው ይላሉ። ቀጣይነት ያለው ልማት ለማምጣት የሚሠሩ የምግብ ሥርዓት ሥራዎች በአካባቢው ላይ የሚኖራቸው አዎንታዊ እና አሉታዊ ተጽዕኖ ግምት ውስጥ መግባት አለበት። ይህ ሁሉ የሚሳካው የጸጋችን ማህፀን የሆነችውን መሬት በአግባቡ ስንጠቀምባት፣ ስንንከባከባት ነው።
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ሥርዓት ስትራቴጂን በመቀበል የዛሬ አራት ዓመት (ሐምሌ 2013 ዓ.ም) ሥራ ጀምራለች። በጥቅምት 2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሥርዓተ ምግብ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ትግበራ ተጀምሯል። በ2016 ዓ.ም ደግሞ የሚመለከታቸው 15 ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች እና ዘጠኝ የልማት አጋር አካላት የተሳተፉበት ጥናት ተካሂዷል። በመጀመሪያ ከተለዩት የኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓትን የሚያሸጋግሩ መፍትሔዎች ከ22 ወደ 24 ከፍ ብለዋል።
በዚህም ሥነ-ምግብን የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ማለትም ከግብርና፣ ከአየር ንብረት ለውጥ፣ ከብዝሃ ሕይወት ጋር የማጣጣም ሥራዎች ተሠርተዋል። የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ለመሥራት ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፤ የቅንጅት ሥራ ተጀምሯል፤ የክትትል እና ድጋፍ ሥርዓትም ተዘርግቷል።
በተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ 18 ተግዳሮቶች ተለይተዋል። ትርፍ የሚያመርቱ፣ የምግብ ዋስትናቸውን ያላረጋገጡ እንዲሁም ሌሎችም ችግሮች ያሉባቸው ተለይተዋል። 24 መፍትሔዎችም ተለይተው ተቀምጠዋል። የሚጠበቁ ውጤቶች እንዲመዘገቡ የሚያስችሉ ተግባራትም ተመላክተዋል። የተግባራቱ ቁጥር እየጨመረ ሄዶ አሁን 703 ደርሷል። እነዚህ በተለያዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች እና ባለድርሻ አካላት የሚከናወኑ ተግባራት እንደሆኑ ተለይቶ ተቀምጧል።
ይህ ሥራ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ከ120 በላይ ሰዎች የተሳተፉበት ሲሆን ወደ ስኬት ለመጓዝ ጥሩ ቅድመ ሁኔታ ነው ተብሎ እንደሚታመን ዶክተር ፍሬው ገልጸዋል። በተጨማሪም ወደ ፊት በሚሠሩ ሥራዎች 16 ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማት፣ ግብረሰናይ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ሌሎች አገር አቀፍ፣ አህጉር እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የልማት አጋር አካላት፣ የግሉ ዘርፍ እና ሕዝቡ በአጠቃላይ ባለቤት ሆነው ተሳትፈዋል።
ለምግብ ሥርዓት ሽግግር ስኬታማነት የበላይ አመራሩ ሚና እና የፖለቲካ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑ ከግምት ውስጥ በመግባቱ ከፌዴራል እስከ ክልል ባለው መዋቅር በየደረጃው ያለው አመራር ሥራውን የሚመራበትና የሚከታተልበት አሠራር ተዘርግቷል። በዚህ መሰረት በፌዴራል ደረጃ
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ 16 ሚኒስትሮች እና የክልል ካውንስል አባላት የሚሳተፉበት አጠቃላይ አመራር እና አቅጣጫ የሚሰጥ ዓብይ ኮሚቴ አለ።
በጤና እና በግብርና ሚኒስትሮች በጋራ የሚመራ 16ቱን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ያቀፈ አመራር እና አቅጣጫ የሚሰጥ ኮሚቴና የቴክኒክ ድጋፍ የሚሰጥ ክፍል ተቋቁሟል፤ የሰው ኃይልም ተደራጅቷል። ይህ መዋቅር በክልል ደረጃ የሚሠራውን ሥራ የሚመራና የሚያስተባብር ካውንስል አለው።
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ሽግግር ሴክሬታሪያት በመሆኑ እንደ አገር ይህንን ሥራ የሚመራው ዓብይ ኮሚቴ ጸሐፊ ሲሆን የተለያዩ ሰነዶችን በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። ተቋሙ ቀደም ሲል የተመላከቱትን ነጥቦች ታሳቢ በማድረግ ለሽግግሩ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ደፋ ቀና እያለ ስለመሆኑ እየተገለጸ ነው።
ከአጋር አካላት አብዛኞቹ መንግሥትን ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል። በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ግብዓት አቅራቢዎች፣ በችርቻሮ እና ጅምላ ንግድ የሚሳተፉ ነጋዴዎች፣ አከፋፋዮች፣ አስመጪና ላኪዎች፣ የግብርና ውጤቶች አቀነባባሪዎች፣ አርሶ እና አርብቶ አደሮች፣ ማኅበራት፣ ሥራ ፈጣሪዎች ወዘተ … የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ በትኩረት እንደሚሰራም ዶክተር ፍሬው ጠቁመዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ እና ሥርዓተ ምግብ
ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ አስተዋጽኦ ካደረጉ አገራት መካከል አይደለችም። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የኢትዮጵያ አስተዋጽኦ ከዜሮ ነጥብ .02 በመቶ በታች ነው- እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው። እንደ አፍሪካ አህጉር ያለን አስተዋጽኦም በጣም አነስተኛ ነው። ለሰው ልጅ የሚያስፈልገው አየር፣ ውሃ፣ ምግብ … የምንተነፍሰው አየር በነጻ የምናገኘው፣ ምድር የምንላት ፕላኔት ላይ ብቻ የሚገኝ ነው። ከዚህች ዓለም ወደ ሌሎች ስንሄድ ኦክስጂን ተሸክመን መሄድ የግድ ይለናል።
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ለኢንዱስትሪ ዕድገት ባደረግነው እንቅስቃሴ ሕይወትን በምትሸከመው ምድር ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትለናል። እጅግ በጣም የበለጸጉ አገራት ከፍተኛ ጉዳት አስከትለዋል። “የአየር ንብረት ዓለም አቀፋዊ ነው። በተናጠል ኢትዮጵያዊያን ብቻ ቆመን የአየር ንብረትን መከለል አንችልም” የሚሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ እና ሥነ ቀመር ኮሌጅ ዲን እና የሥነ ምህዳር ተባባሪ ፕሮፌሰር ቢቂላ ወርቅነህ (ዶ/ር) ናቸው። “ምንም እንኳን እኛ ያመጣነው ባይሆንም አሁን ያለው የአየር ንብረት እየጎዳን ያለው እኛን ነው፤ እየጮህን እየሠራን ያለነውም እኛ ነን፤ ከጉዳቱ ለማገገም የሌሎች እርዳታ፣ የዓለም ትብብር ያስፈልገናል” ሲሉ መፍትሔውን ጭምር ጠቁመዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ ላይ ያስከተለውን ጉዳት “ለረሃብ እየተጋለጥን በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎቻችን
የተጎዱበት፣ ብዙ ድርቅ የተከሰተበት አገር ውስጥ ነው ያለነው። ይህ ድርቅ በተከታታይ የተከሰተው በርካታ ጥናቶች እንደመሰከሩት ከአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ ነው። የራሳችን ባልሆነ ጥፋት ተጎጂዎች ሆነናል” ሲሉ ገልጸውታል። ይሁንና ተጎጂዎች ነን ብለን መቆም እንደሌለብንም መክረዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ከሚያመጣቸው ጉዳቶች አንዱ ተከታታይ የሆኑ ሰብልን የሚያጠፉ ነፍሳት እና ወረርሽኞች መከሰት ነው። መጠኑን ያልጠበቀ ዝናብ ጎርፍ አስከትሎ ግብርና ላይ (ማሳ ላይ) አደጋ በማስከተል የምግብ ሥርዓታችንን እየጎዳ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ።
የአገራችን ግብርና ዝናብ ጠብቆ የሚሠራ እና በዝናብ ላይ የተመሰረተ መሆኑ እንዲጎዳ ምክንያት ሆኗል። የአየር ንብረት ለውጡ ዝናቡ ወቅቱን እንዳይጠብቅ ከማድረግ አልፎ ጎርፍ የሚያስከትል ዝናብ እንዲዘንብ እና ያልተመጣጠነ ዝናብ ባልተፈለገ ጊዜ እየመጣ አደጋ እንዲከሰት ምክንያት እየሆነ ነው። ዝናብ ወቅቱን ካለመጠበቁ የተነሳ ሰብሎች ፍሬ እንዳያፈሩ በማድረግ በአገራችን ከፍተኛ ጉዳትን አስከትሏል፣ እያስከተለም ይገኛል። የዝናብ መፈራረቅ፣ የአየር ሙቀት መጨመር ከሚያስከትሏቸው ጉዳቶች መካከል አንደኛው የግብርና
ምርታማነትን መቀነስ ነው።
በአገራችን ኢኮኖሚው ውስጥ ትልቁን ድርሻ የያዘው ግብርና ምርታማነት ሲቀንስ ገቢያችን እንደሚቀንስ ግልጽ ነው። በአጠቃላይ የአየር ንብረት ለውጥ የሰውን ልጅ የኑሮ ሥርዓት የሚያናጋ በህልውናው ላይ የተደቀነ አደጋ ነው። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ፊት አውራሪ አገር ነች። ።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ከመምጣቱ በፊት ከ1980ዎቹ ጀምሮ ስትሠራ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። አሁን እየተተገበረ ባለው የአስር ዓመት የአገራችን የልማት ዕቅድ ውስጥም ተካቶ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። ለምሣሌ በአረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ ውስጥ በትምህርት ቤት ካሉ ሕጻናት ጀምሮ ሁሉም ማኅበረሰብ የሚሳተፍበትን ንቅናቄ የፈጠረ ትልቅ እንቅስቃሴ ነው። ነገር ግን ይህ በእኛ አገር ብቻ ቀርቶ ውጤታማ አይሆንም፣ ሌሎች አገራትም ሊከተሉን ይገባል። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምታደርገው ጥረት የዓለም እገዛ ያስፈልገዋል። ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን መሥራት ይጠይቀናል።
ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሰራች ባለችው ኢትዮጵያ በተለይ በግብርና ከእንስሳት እርባታ ጋር በተያያዘ ምርታማነትን መጨመር፣ የመስኖ ልማት ማስፋፋት፣ የደን ልማት ጥበቃ እና ከለላ እንዲሁም የአፈር እና የውሃ መከላትን የሚከላከሉ ዕቅዶች ተዘጋጅተው ወደ ትግበራ የተገባ ሲሆን ውጤቶችም ተገኝተዋል።
የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን በማውጣት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ያለው የግብርና ምርምር የተሻሻሉትን ዝርያዎች ለአየር ንብረት ለውጥም የማይበገሩና በሽታን መቋቋም የሚችሉትን የሰብል ዝርያዎች በማዳቀልና በማባዛት ለአርሶ አደሮች እንዲደርስ እየተሠራ ይገኛል።
“የአሜሪካ አርሶ አደር የሚያርሰው ዓለምን ስለመመገብ እያሰበ እንጂ አሜሪካንን ስለመመገብ አይደለም፤ የኢትዮጵያ አርሶ አደርስ አካባቢውን ከመመገብ አልፎ ዓለምን መመገብን እንደ ዓላማ መያዝ አይችልም ወይ? ብለን ለመሥራት መነሳሳት አለብን። ይህ እሳቤ ዜጎቻችን ውስጥ፣ የሥራ ባሕላችን ውስጥ መስረጽ አለበት” ሲሉ በቁጭት የሚናገሩት ዶክተር ቢቂላ፤ ይህን ስናደርግ ለአየር ንብረት ለውጥ አይበገሬ ለመሆን መሪዎች እንደሆንን በምግብ ሉዓላዊነትም ለአፍሪካዊያን ተምሣሌት መሆን እንችላለን ብለዋል።
የመስኩ ተዋንያን ሚና
ቀደም ሲል እንደተገለጸው የሥርዓተ ምግብ ጉዳይ በአንድ ተቋም ወይም በተወሰኑ አካላት ተሳትፎ ብቻ የሚሳካ አይደለም። ይልቁንም የብዙ ባድርሻ አካላት እንዲሁም የአጠቃላይ ማኅበረሰቡን ተሳትፎና ርብርብ የሚጠይቅ መጠነ ሰፊ ሥራ ነው። በተለይ የምግብ ሰንሰለቱ ውስጥ የሚያልፉ/ የሚሳተፉ ተዋንያን በርካቶች ናቸው።
ከእርሻ እስከ ጉርሻ ያለውን የምግብ ሥርጭት ሰንሰለት በእርሻ ወይም በእርባታ፣ በምግብ ማቀነባበር፣ በምግብ መጓጓዝና ማከማቸት ለሽያጭ ማቅረብ እንዲሁም በተለያዩ የምግብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ የምግብ ዝግጅት፣ በቤት ውስጥ ምግብን ማዘጋጀትና
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
መመገብን ሁሉ ያጠቃልላል።
የሥርዓተ ምግብ ሽግግሩን እውን በማድረግ ሂደት መንግሥት የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል። ለሽግግሩ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት፣ ምቹ አሠራር ለመፍጠር የሚረዱ የሕግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት፣ ሥራውን የሚከታተሉና የሚደግፉ ተቋማትን በማደራጀት አቅማቸውንም በመገንባት፣ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም ለማኅበረሰቡ ስለ ሥርዓተ ምግብ ምንነት እና ስለ ሽግግሩ ግንዛቤ ማስጨበጥ የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን፣ የክትትልና ግምገማ ሥርዓት በመዘርጋት እና ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ከመንግሥት ትልቅ ሥራ ይጠበቃል።
በምግብና ሥርዓተ ምግብ መስክ የተሰማሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት ያላቸውን የሰው ኃይል፣ የፋይናንስና የመሰረተ ልማት አቅም ከመንግሥት ጋር አቀናጅተው በመሥራት የሥርዓተ ምግብ ሽግግር ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት መደገፍ ይኖርባቸዋል።
ከእርሻ እስከ ጉርሻ ባለው የምግብ ሥርጭት ሰንሰለት ውስጥ የተሰማሩ ባለኃብቶች ምግብን ለብክነት የማያጋልጡና የምግብ ጥራትና ደህንነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ የአሠራር ሥርዓቶችን በመዘርጋት ብሎም በተግባራዊ እንቅስቃሴው ግንባር ቀደም ሆነው መሳተፍ አለባቸው። ለምግብና የሥርዓተ ምግብ ዋስትና መረጋገጥ ኅብረተሰቡ በባለቤትነት ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ማድረጉ ለሽግግሩ ስኬታማነት ወሳኝ ነው።
ወደ መዳረሻችን ለማምራት
መንግሥት የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚን የሚያበረታታ ሲሆን ለግብርና ምርታማነት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷል፤ ዶክተር ፍሬው ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከፍተኛ ለውጥ የታየበት ይህ ዘርፍ ባለፉት ስድስት ዓመታት እምርታዊ ለውጥ አምጥቷል ይላሉ። ለዚህም የኩታ ገጠም እርሻ እና የመስኖ (የበጋ) ስንዴ ምርት እና ምርታማነት ጥሩ ማሳያ ነው። የኩታ ገጠም እርሻ እና የበጋ መስኖ ስንዴ በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ተጀምሮ በግብርና ሚኒስቴር የተስፋፋ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ማለትም በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት እውቅና የተሰጠው፤ ውጤት የታየበት በስንዴ ራስን የመቻል ሥራም የተሠራበት ነው።
የሌማት ትሩፋት መልካም ጅማሮ እና ተጨባጭ ውጤቶች እንደ ምሣሌ ይጠቀሳሉ። በግብ ደረጃ የተያዘው የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ የውጭ ገበያን ማበረታታት፣ ከውጭ የሚገባ ምርትን መተካት እና ግብርና ላይ የተመሰረተ የሥራ ፈጠራን በትክክል ማሳካት የሚቻል መሆኑን ማየት ተችሏል።
ሌላው ማሳያ ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘው የአረንጓዴ አሻራ ኢንሼቲቭ ነው። በዚህም የአገራችን የደን ሽፋን የዚህን ዓመት ሳይጨምር ከ17 ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ ብሏል። በሌላ በኩል በሺህዎች የሚቆጠሩ ሕጻናትን ተጠቃሚ ያደረገው የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር ትውልድን ለመቅረጽ በሚደረገው ጥረት በተምሣሌትነቱ የሚጠቀስ ሆኗል።
አሁን አርሶ አደሮቻችን በጋራ ማምረት እንጂ በጋራ ማከማቸት፣ በጋራ እሴት መጨመር፣ ማቀነባበር፣
ወደ ገበያ ማቅረብ አልቻሉም ሲሉ እያጋጠማቸው ያለውን ችግር የገለጹት ዶክተር ፍሬው እነዚህን ሁሉ መሰረታዊ ችግሮች ለመፍታት የገጠር መሰረተ ልማቶች እንደሚያስፈልጉ እና ይህም በግብርና ፖሊሲው ተካቶ እንዲጸድቅ መደረጉን ጠቁመዋል።
ዶክተር ፍሬው በሰብል፣ በእንስሳት እና በዓሣ ምርቶች እየተሠራ ያለው ሥራ ሰፍቶ ነገ ላይ የግሉ ዘርፍ ተረክቦት የሚስፋፋው ዕቅድ አለ። በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በአርሶ አደሮች ባለቤትነት የሚተዳደሩ ወደ 50 ኩባንያዎችን መስርተን ምሣሌ የሚሆን ውጤት ይዘን እንመጣለን ሲሉ በቀጣይ የተያዘውን ውጥን አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ሽግግር ራዕይ የተሸጋገረ፣ ለተለያዩ ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች የማይበገር፣ ቀጣይነት ያለው እና አካታች የምግብ ሥርዓት ማየት ነው። ተልዕኮው ደግሞ ለዚህ ራዕይ ስኬት የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት ማስተባበር። የምግብ ሥርዓት ሽግግር በዓለም ላይ እስከ አንድ ግለሰብ ድረስ የምግብ ዋስትና ይረጋገጥ ዘንድ ምን መሠራት አለበት ተብሎ ከምዕተ ዓመቱ ቀጣይ የልማት ግቦች ጋር እንደ አገር ተጀምሯል።
ትልቁን ሚና የሚጫወቱት እነማን ናቸው ከተባለ መሪዎች ቀድመው
ከማስጀምር አንጻር፣ የፖለቲካ ትኩረት ከመስጠት አንጻር ኅብረተሰቡ የራሱ መሆኑን እንዲገነዘብ ከማስተባበር አንጻር የመሪዎች ሚና የላቀ ነው። የኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ሽግግር ተግባራዊ ይሆንና የምግብ ሉዓላዊነት ይረጋገጥ ዘንድ እንደ ኢትዮጵያ መሪዎች የጀመሩት ይህ ሥራ ቀጣይነት የሚኖረው ሕዝብ ባለቤት ሲሆን፤ ፈጻሚ ተቋማትም በቅንጅት ሲሰሩ ነው።
በተለመደው መንገድና አሠራር የተለየ ውጤት ማስመዝገብ አይቻልም የሚሉት ዶክተር ፍሬው፤ ሁሉም መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት፣ ሕዝብ፣ መገናኛ ብዙሃን፣ ወዘተ… የሚሳተፉበት፤ የሚጠበቅባቸውን የሚወጡበት መዋቅር እና አሠራር መዘርጋቱን ገልጸዋል። ስለሆነም የተሸጋገረ፣ ለተለያዩ ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች የማይበገር ቀጣይነት ያለው እና አካታች የምግብ ሥርዓት ሽግግር ለማምጣት የተበጀውን አሰራር በመጠቀም በጋራ እና በትብብር መሥራት ይጠይቃል።
ማኅበራዊ
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
አለርት -
(በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ)
በፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና. . .
በመንገሻ ገ/ሚካኤል
የመላው አፍሪካ የሥጋ ደዌ፣ የሳንባ ነቀርሳ እና የመልሶ ማቋቋም ማሠልጠኛ ማዕከል (ALERT) በጤና አጠባበቅ ረገድ የላቀ ትሩፋቱ የሚጀምረው እ.አ.አ. በ1934 በሱዳን ሚሽነሪዎች ሲሆን አመሰራረቱ የሥጋ ደዌ በሽታ ሕክምና ተቋም ሆኖ ነው። በቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ሲቋቋም ልዕልት ዘነበወርቅ መታሰቢያ ሆስፒታል ተብሎ የተሰየመው ሆስፒታሉ ከጊዜ በኋላ በአፍሪካ እየተባባሰ የመጣውን የሥጋ ደዌ ሕመም ችግር ለመፍታት ሲባል ዓላማው ተለወጠ። ታኅሣሥ 11ቀን 1965 ዓ.ም ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች አለርት እንደ ሥጋ ደዌ ሕክምና፣ የማገገሚያ እና የሥልጠና ማዕከል ሆኖ እንዲቋቋም ትብብር አደረጉ።
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ባለፉት ዓመታት ውስጥ ተቋሙ የሥጋ ደዌ ሕክምና እና የኢትዮጵያ ዋና ሪፈራል ሆስፒታል ሆኖ አድጓል። በአለርት ሆስፒታል የፕላስቲክ ሪኮንስትራክቲቭ እና የእጅ ቀዶ ጥገና ክፍል ከ40 ዓመታት በላይ በማዕከሉ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ካሉት ክፍሎች (Depart- ments) አንጋፋው መሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡
ለሥጋ ደዌ ሕሙማን ነፃ ሕክምና ለመስጠት የተቋቋመው ይህ ዲፓርትመንት በአሁኑ ጊዜ በአገሪቷ ዋና የሪፈራል ማዕከል ሆኗል፡ ፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በፕላስቲክ እና ሪኮንስትራክቲቭ ሕክምና በድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ስፔሻሊስቶችን በማሠልጠን ላይ ይገኛል።
የፕላስቲክ ሰርጀሪ ሕክምና ምንድን ነው?
የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና በአደጋ፤ በካንሰር ወይም በተፈጥሮ የተጎዳውን አካል ወደ ቀድሞ ሁኔታው መመለስ፣ መልሶ መገንባት ወይም ማሻሻል ላይ ያተኮረ ልዩ የሕክምና መስክ ነው፡፡ እነዚህም በተፈጥሮ የተፈጠሩ ጉድለቶችን፣ ቁስሎችን፣ ኢንፌክሽኖችን፣ እጢዎችን እና የተግባር ጉድለቶችን እና ውበትን (የኮስሞቲክስ) ቀዶ ሕክምናን ያጠቃልላል፡፡ መልክን ለማሻሻል ዋና ዋናዎቹ ዘርፎች የራስ ቅል እና የፊት እክል ሕክምና፣ የመንጋጋ እና የፊት አጥንት ጉዳዮች፣ የእጅ እና የእግር፣ የነርቭ እና የጅማት ቀዶ ሕክምና፣ ነፃ የቲሹ ሽግግር እና የነርቭ ጥገናን የሚያካትት የማይክሮ ቀዶ ሕክምና፣ የቃጠሎ እንክብካቤ የቀዶ ሕክምና፣ ኦንኮፕላስቲክ እና የጡት ሪኮንስትራክቲቭ ቀዶ ሕክምናን ያካትታሉ።`
በአገራችን የሚሰጡ የፕላስቲክ ሰርጀሪ ሕክምና ዓይነቶች
በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና አገልግሎቶች በዋነኛነት በማስተማሪያ ሆስፒታሎች፣ በክልል ሪፈራል ማዕከላት እና በዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ትብብር እየተስፋፋ የመጣ ነው። ቀደም ባለው ጊዜ ይህ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ሕክምና ነው፡ ፡ እንደ የካቲት 12 እና የቅዱስ ጳውሎስ አቤት ሆስፒታል ባሉ ተቋማት ውስጥ በዋናነት የቃጠሎ እና ከቃጠሎ ጋር
የተያያዙ ሕክምናዎች ይሰጣሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የፕላስቲክ እና ሪኮንስትራክቲቭ ቀዶ ሕክምና ዘርፈ ብዙ በመሆን የእጅ እና የእግር የነርቭ እና የጅማት ሕክምና፣ የፊት ላይ አደጋዎችን ጨምሮ እያከመ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ አገልግሎቶች ለቁስሎች እና እጢዎች ለስላሳ ቲሹ ( soft tissue) መልሶ መገንባት፣ ከካንሰር ቀዶ ሕክምና በኋላ ኦንኮሎጂካል መልሶ ግንባታ (reconstruction) እና በተመረጡ ማዕከሎች ውስጥ ውስን የሆነ ማይክሮሰርጅን ይካተታሉ። የኮስሞቲክስ ቀዶ ሕክምና በአብዛኛው በአዲስ አበባ በሚገኙ የግል ክሊኒኮች ብቻ ተወስኗል።
የፕላስቲክ ሰርጀሪ ሕክምና ተደራሽነት
በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ተደራሽነት በአንፃራዊነት የተገደበ ሲሆን አብዛኛው አገልግሎት እንደ አዲስ አበባ፣ ጅማ፣ ጎንደር እና መቀሌ ያሉ ከተሞች በሚገኙ የመንግሥት ማስተማሪያ ሆስፒታሎች እና በክልል ሪፈራል ማዕከላት ይገኛል። በእነዚህ ማዕከላት እንደ የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ጥገና፣ የቃጠሎ እና መሰረታዊ የአካል ጉዳት መልሶ መገንባት ያሉ አስፈላጊ ሕክምናዎች
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ሲኖሩ፤ እንደ ማይክሮሰርጀሪ፣ ውስብስብ የአንገት በላይ ካንሰር ቀዶ ሕክምና እና አጠቃላይ የውበት ሕክምናዎች በጣም አናሳ ናቸው፡፡ እንደ Oper- ation smile እና Smile train ያሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ ተደራሽነቱን ለማሻሻልና በተወሰኑ አካባቢዎች እንደ ከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ እንክብካቤና የቃጠሎ የሕክምና ክፍተቶችን ለመቀነስ ቢረዳም የጂኦግራፊያዊ አቀማማጥ፣ የፋይናንሺያል እና የስፔሻሊስቶች ውስንነቶች ለአብዛኛዉ ሕዝብ በተለይም በገጠር አካባቢዎች ተደራሽነትን ይገድባሉ።
በአለርት የቀዶ ሕክምና ክፍል የሚሰጡ አገልግሎቶች
በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ክፍል ሁሉም አገልግሎቶች በሣምንቱ ቀናት በመደበኛ የሥራ ሠዓት የሚሰጡ ሲሆኑ፣ የአደጋ ጊዜ እና የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ከሥራ ሠዓት ውጪም ተደራሽ ነው፡ ፡ ይህም በቀን 24 ሠዓት፣ በሣምንት ሰባት ቀናት ቀጣይነት ያለው ሽፋን ይሰጣል። የሕክምና ክፍሉ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የእጅ እና የነርቭ ቀዶ ሕክምና፣ እንደ Brachial plexus ቀዶ ሕክምና ያሉ ውስብስብ ሕክምናዎች፣ የጅማት እና የነርቭ በድንገተኛ/በአደጋ የመጡ ጉዳቶችን ማከም፣ ከሥጋ ደዌ ጋር በተያያዘ ለሚመጡ የተለያዩ ችግሮች ሕክምና፣ የሥጋ ደዌ መልሶ ማቋቋም (Reconstructive) ቀዶ ሕክምና፣ ኦንኮሎጂ፣ ለተለያዩ የጡንቻ እጢዎች የሚደረግ ሕክምና የተለያዩ ሽፋኖችን በመጠቀም ለስላሳ
ቲሹ ሽፋን፣ የጭንቅላት እና የአንገት ቀዶ ሕክምና፣ Exploration እና እንደ የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ያሉ በተፈጥሮ የሚመጡ እክሎችን ማከም፣ እንደ Maxillofacial እና Orthoge- netic ቀዶ ሕክምና ያሉ ከባድ የፊት ጉዳቶችን ማከም፣ እንዲሁም ጉዳትን ማቃጠል፣ የበልባል፣ የኤሌክትሪክ፣ የኬሚካል ቃጠሎዎችና ከቃጠሎ በኋላ የሚመጡ ችግሮች ማከም ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በተለየ ሁኔታ የአለርት ፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና (Plastic Surgery) ክፍል የእጅ እና የነርቭ (Bra- chial Plexus), Microsurgery እና ከአንገት በላይ የካንሰር ሕክምናዎች መስጠቱ ከሌሎች ተቋማት ለየት ያደርገዋል፡፡ በሕክምና ክፍሉ በሣምንት አራት ጊዜ የተመላላሽ ክፍል ሲኖር ይህም የድንገተኛ (Trauma) ክፍልን ያካትታል፡፡ ሁለት አስተኝቶ ማከሚያ ክፍል እና ሁለት የቀዶ ሕክምና ክፍሎች አሉት፡፡ በዓመት በአማካኝ ከ12 ሺህ በላይ ቀዶ ሕክምናዎች የድንገተኛ ሕክምናን ጨምሮ ከ12 ሺህ 500 በላይ አስተኝቶ ሕክምና እንዲሁም 12 ሺህ 800 ተመላላሽ ታካሚዎችን ያስተናግዳል፡፡
የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ክፍሉ ከአጠቃላይ የመልሶ ግንባታው (Reconstructive) የፕላስቲክ ክሊኒክ በተጨማሪ ልዩ ልዩ ክሊኒኮችን አስተዋውቋል። እነዚህ ክሊኒኮች የእጅ እና የነርቭ፣ የጭንቅላት እና የአንገት መልሶ ግንባታ፣ Craniofacial ክሊኒክ እንዲሁም በቅርብ የተጀመረው እና በጥሩ ሁኔታ እያደገ ያለው የማይክሮ ሰርጀሪ (Microsur- gery) ሕክምናዎች ናቸው፡፡ የDay care Surgery ሕክምና አቅጣጫ በክፍሉ ከሚሰጡ ለየት ያሉ እና እንደ Pilot የሚታይ ዘርፍ ነው፡፡ ታካሚዎች አልጋ ሳይዙ ቀዶ ሕክምናው በመጡበት ቀን ተሰርቶላቸው ወደ ቤታቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ሲሆን ይህም የአልጋ ወረፋ የሚይዙ ታካሚዎችን ይቀንሳል፡፡ በዋናነት ደግሞ በቅርቡ መሰረት የተጣለውን የ Dermatoplastic ማዕከል ለአገሪቷ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ተወዳዳሪ የሆነ የፕላስቲክ እና ሪኮንስትራክቲቭ ቀዶ ሕክምና ለመስጠት ክፍሉ በትኩረት እየሠራ ነው፡፡
በዚህ ክፍል የታካሚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና የስፔሻሊቲ ሥልጠናዎችን ለማሻሻል በቴክኖሎጂ የታገዙ ሕክምናዎች ይሰጣሉ፡፡ የታካሚዎችን ውጤት በአግባቡ ለመረዳት እንደ CT Scan, CT anjio በእጅ የሚያዙ ዶፕለሮች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ በተጨማሪም በማይክሮ ሰርጀሪ ቀዶ ሕክምና ወቅት Surgical Microscope እና loups በመጠቀም ለዓይን እይታ አዳጋች የሆኑ የደም ስሮችን መስፋት ይቻላል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሕክምና ክፍሉ የሚጠቀመው የኦፕሬሽን ክፍል ካሜራ (Proximie) ደግሞ ተማሪዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ሳይጣበቡ ከውጭ ሆነው የቀዶ ሕክምናውን ሂደት እንዲከታተሉና እንዲማሩ የሚረዳ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ ነው፡፡
የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በኢትዮጵያ ብቁ የፕላስቲክ ሪኮንስትራክቲቭ ቀዶ ሕክምና ሐኪሞችን በማሠልጠን ጠንካራ የሆነ የድህረ ምረቃ መርኃ ግብር አለው፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበርና በምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ አፍሪካ የቀዶ ሕክምና ኮሌጅ (COSECSA) እውቅና ያለው የሰብ ስፔሻሊቲ ሥልጠና በመስጠት ትልቅ ሚና ይጫወታል። ከአጠቃላይ ቀዶ ሕክምና፣
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም
ኦርቶፔዲክስ፣ ማግዚሎፋሺያል እና ኒውሮሰርጀሪ ሬዚደንት ሐኪሞችን ከተለያዩ ተቋማት ተቀብሎ የአጭር ጊዜ ሥልጠና ይሰጣል፡፡ አጋሮች - Re- Surge International፣ እና Smile Train ጨምሮ እንደ ማይክሮ ቀዶ ሕክምና፣ የእጅ ቀዶ ሕክምና፣ የክራኒዮፋሻል እና የላንቃ እና ከንፈር መሰንጠቅ እንክብካቤ እንዲሁም የነርቭ ጥገና ባሉ ቴክኒኮች የላቀ ሥልጠና በማፍለቅ የአጭር ጊዜ ትስስርን በመጠቀም የክህሎት ልቀትን ይጨምራል።
የአለርት ሆስፒታል የፕላስቲክ፣ ሪኮንስትራክቲቭ እና የእጅ ቀዶ ጥገና ክፍል በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጠንካራ ትብብር እንዲኖርም አድርጓል። በአገር ውስጥ የመማር ማስተማር መርኃ ግብሩን ተከትሎ በዋነኛነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር ሬዚደንት ሐኪሞችን በማስተማር ጉልህ ሚና ይጫወታል፡ ፡ በተጨማሪም ከተለያዩ የክልል ሆስፒታሎችና ኮሌጆች ጋር የአጭር ጊዜ የሐኪሞች ሥልጠናን ይሰጣል፡፡
ከምስራቅ፣ ከመካከለኛው እና ከደቡብ አፍሪካ የቀዶ ሕክምና ኮሌጅ (COSECSA ) ጋር በመተባበር የድህረ ምረቃ (Sub speciality) ትምህርት በመስጠት ከቀጣናው አገራት ጋር ጥሩ ትስስር ፈጥሯል፡፡ ከቡሩንዲ፣ ዛምቢያ እና ታንዛኒያ የመጡና ለሦስት ዓመታት የሚቆዩ ሬዚደንት ሐኪሞች መኖራቸውም የዚህ ውጤት ነው፡፡ እንዲሁም እንደ Smile train, 2nd Chance, Re surgery international እና B First ከመሳሰሉ ዓለምአቀፍ ጅርጅቶች ጋር በመተባበር የትምህርት ሂደቱና የታካሚዎች ውጤታማ ሕክምና ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለመፍጠር ይሠራል፡፡
የዘርፉ መልካም አጋጣሚዎች እና ፈተናዎች
በኢትዮጵያ የፕላስቲክ እና የሪኮንስትራክቲቭ ቀዶ ሕክምና ብዙም ትኩረት ያላገኘ ዘርፍ ነው፡፡ የቃጠሎ አደጋዎች፣ የተሽከርካሪ አደጋዎች፣ በጦርነት ምክንያት የሚደርሱ ጉዳቶችና የካንሰር ሕመም እየጨመረ በመምጣቱ ዘርፉ ከባድ ፈተናዎች እየገጠሙት ነው፡፡ በሌላ በኩል ከዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የቀዶ ሕክምና ማኅበራት እና የአካዳሚክ ትስስሮች የሥልጠናና የአቅም ግንባታ መንገዶችን እየፈጠረ በመምጣቱ የኢትዮጵያ የፕላስቲክ እና የመልሶ ግንባታ ቀዶ ሕክምና ዘርፍ ትልቅ ዕድሎችም አሉት። ይሁን እንጂ የሰለጠነ የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ሐኪሞች እጥረት፣ የልዩ መሣሪያዎች አቅርቦት ውስንነት፣ ወጣ ገባ የአገልግሎት ስርጭትና በቂ መሠረተ ልማት አለመኖሩ የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምናው መስክ የላቀ እንዳይሆን አድርጎታል።
አለርት እንደ ብሔራዊ የልህቀት ማዕከል ለመሆን ከሚሄድበት መንገድ አንፃር ከዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የአገር ውስጥ ማዕከላት ጋር እየሠራ መሆኑ ደግሞ የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ዘርፉ እንዲስፋፋ ያግዛል፡፡
የሕክምና ክፍሉ ቀጣይ ራዕይ
የሕክምና ክፍሉ በምስራቅ አፍሪካ በፕላስቲክ ሪኮንስትራክቲቭ እና የእጅ ቀዶ ሕክምና ግንባር ቀደም የልህቀት ማዕከል ለመሆን፤ ተደራሽ፣ ከፍተኛ ጥራት እና ርህራሄ ያለው የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በመስጠት፣ ልዩ ሥልጠናዎችን በማሳደግ እና በተሃድሶ ቀዶ ሕክምና፣ በምርምር፣ በቴክኖሎጂ እና በጠንካራ አገራዊና ዓለምአቀፍ አጋርነት ላይ ፈጠራን የማንቀሳቀስ ህልም ሰንቋል።
ነጋሪ 8ኛ ዓመት ቁጥር 30 ጳጉሜን 2017 ዓ.ም