ከመቀሌ ወደ ሁሉም የትግራይ ከተሞች የሚደረገው የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ወደ መደበኛ ሥራው ተመለሰ - ኢዜአ አማርኛ
ከመቀሌ ወደ ሁሉም የትግራይ ከተሞች የሚደረገው የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ወደ መደበኛ ሥራው ተመለሰ
አዲስ አበባ፣ህዳር 19/2019 (ኢዜአ)፦ ከመቀሌ ተነስተው ወደ ሁሉም የትግራይ ክልል ከተሞች የሚጓዙ መካከለኛና ትላልቅ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች፣ ከዛሬ ጀምሮ ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው መመለሳቸውን የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ አስታወቀ።
ወደ ሥራ የተመለሱት ከ24 እስከ 60 ተሳፋሪዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው አውቶቡሶች ሲሆኑ፣ ከመቀሌ ወደ ተለያዩ የክልሉ ከተሞች ደርሰው ለመመለስ የሚያስችላቸው በቂ የነዳጅ አቅርቦት እየተመቻቸላቸው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገልጿል።
ቢሮው አያይዞም ተገልጋዩ ኅብረተሰብ ካልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዲጠበቅና የተረጋጋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ ለማስቻል፣ በታሪፍ አፈጻጸም ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ አስታውቋል።