የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ መርሐ ግብሮች - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ መርሐ ግብሮች
አዲስ አበባ፤ ህዳር 19/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ10 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።
ተጋጣሚው ሀዲያ ሆሳዕና በአራት ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በስድስተኛ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሀላባ ከተማን 1 ለ 0 ሲረታ ሀዲያ ሆሳዕና በቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 0 ተሸንፏል።
ጨዋታው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ፣ ሀዲያ ሆሳዕና ከተከታታይ ሽንፈቱ ለማገገም የሚያደርጉት ነው።
በሌላኛው መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ መድን ከቀኑ 10 ሰዓት በባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ፋሲል ከነማ በሶስት ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ተጋጣሚው ኢትዮጵያ መድን በሰባት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።
ፋሲል ከነማ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ለማግኘት ይጫወታል።
በስድስተኛ ሳምንት በባህር ዳር ከተማ የ3 ለ 1 ሽንፈት ያስተናገደው ኢትዮጵያ መድን ወደ ድል መንገድ ለመመለስ ይፋለማል።
ሁለቱም ክለቦች በተመሳሳይ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ አላቸው።