ድል የናፈቀው ማንችስተር ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ከብሬንትፎርድ ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
ድል የናፈቀው ማንችስተር ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ከብሬንትፎርድ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 19/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 12ተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ብሬንትፎርድን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ባለሜዳው ማንችስተር ዩናይትድ በስምንት ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኘው ክለብ ባለፉት ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።
ይህን ተከትሎም ማይክል ካሪክን አሰናብቶ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን ሾሟል።
ፖቼቲኖም በመጀመሪያ ጨዋታቸው ዩናይትድ በታሪካዊ ተቃናቃኙ ሊቨርፑል የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል።
ተጋጣሚው ብሬንትፎርድ በ17 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። በ11ኛ ሳምንት ኤቨርተንን በመርታት ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
በሁለተኛው ሳምንት ኤፕስዊች ታውንን 5 ለ 2 ካሸነፈ በኋላ ድል የናፈቀው ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ድል መንገድ ለመመለስ ይጫወታል።
ብሬንትፎርድ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይፋለማል።
የ39 ዓመቱ ሮበርት ጆንስ ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት እንዲመሩ ተመድበዋል።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ሊድስ ዩናይትድ ከኮቨንተሪ ሲቲ ምሽት 12 ሰዓት፣ ኤፕስዊች ታውን ከአስቶንቪላ ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።