ቀጥታ፡

ቼልሲ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናገደ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 19/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ኖቲንግሃም ፎረስት ቼልሲን 3 ለ 2 አሸንፏል።

በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሞርጋን ጊብስ -ዋይት በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኢጎር ጄሱስ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ኢማኑኤል ኢሜጋ የቼልሲን ግቦች አስቆጥሯል።

ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቼልሲ በ16 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።

ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኖቲንግሃም ፎረስት በ12 ነጥብ ደረጃውን ከ17ኛ ወደ 14ኛ ከፍ አድርጓል።

በ13ኛ ሳምንት ቼልሲ ከክሪስታል ፓላስ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከሁል ሲቲ ጋር ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም