የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ወደ አክሱም በረራ ይጀምራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ወደ አክሱም በረራ ይጀምራል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 17/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ አክሱም ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከነገ ከሰአት ጀምሮ እንደሚጀምር አስታወቀ።
ደንበኞች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ በመሄድ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከል 6787 በመደወል የጉዞ ምዝገባ ማስያዝ እንደሚችሉም አመልክቷል።