ቀጥታ፡

የምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄዎች እና አስተያየቶችን እያቀረቡ ነው 

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቧቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከል፦

✍️የቢሾፍቱ አየር መንገድ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አቅም እና ሀገሪቱንም የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል ለማድረግ ከፍተኛ እድል እንዳለው ይታወቃል።ለመሆኑ ወቅታዊ የግንባታ አፈፃፀሙ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

✍️የኢትዮጵያን የዕድገት ጉዞ ለማደናቀፍ የውጭ ኃይሎች ከሀገር ውስጥ ባንዳ ተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ መንግስት እንዴት ያየዋል?

✍️ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በተለይም የታክስ መሰረትን ለማዘመን እንዲሁም ሌብነትን ለመከላከል መንግሥት የያዘው እቅድ ቢብራራ


 

✍️የከተሞች ልማት ለሕዝብ ምቹ እና የአካታች ሆነው መገንባታቸው እጅግ የሚበረታታ ነው

✍️ ሀገሪቱ የምታስመዘግበው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ዘላቂ እንዲሆን በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ የሰላም እና የፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ መንግሥት ምን አቅዷል?

✍️ሌብነትን ለመከላከል እና ሕዝብ ከአገልግሎት ዘርፎች የሚያገኘውን እርካታ ለማሳደግ በመንግሥት በኩል የተያዙ እቅዶች ምንድናቸው ?

✍️የኢትዮጵያ መንግሥት ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለው ወቅታዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

✍️ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላትን አቅም ለማሳደግ እየተሰሩ የሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ናቸው

✍️በሀገራዊ ምክክር የቀረቡ ምክር ሀሳቦች መንግስት ለመተግበር እያደረገ ያለው ዝግጅት ምንድን ነው?

✍️የታላቁ መደመር ስትራቴጂን ወደ ተግባር ለመቀየር የተዘረጉት የአሠራር ሥርዓቶች ምንድን ናቸው? ከማን ምን ይጠበቃል?


 

✍️የመደመር መንግሥት የህግ የበላይነትን እና ሰላምን ለማረጋገጥ እያከናወኗቸው ያሉ ስራዎች ምን ይመስላሉ?

✍️የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን ሰላም የማይሻው የኤርትራ መንግስት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንዴት ያየዋል?

✍️የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ትግበራ አሁን ያለበት ደረጃ እንዴት ይገለጻል?

✍️የመደመር መንግሥት የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ለማስተካከል በዘላቂነት እየወሰደው ያለው እርምጃ ቢብራራ ?

✍️በጉባ ብስራቶች ይፋ የሆኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

✍️የመደመር መንግሥት የዜጎችን የቤቶች ፍላጎት ለመመለስ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች ቢብራሩ ? የሚሉ ይገኙበታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም