ቀጥታ፡

ባርሴሎና ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 16/2019 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሐ ግብር ባርሴሎና ሳባህን 4 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በባኩ ኦሊምፒክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንቶኒ ጎርደን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ካሪም አዲዬሚ እና ጋቤርኤል ጄሱስ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ጆይ-ላንስ ሚኬልስ የሳባህን ጎል አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ ባርሴሎና በ12 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

የአዘርባጃኑ ክለብ በሶስት ነጥብ 32ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በሌላኛው መርሐ ግብር  ቪያሪያል ስላቪያ ፕራግን 1 ለ 0 ረትቷል።

በፎርቹና አሬና በተደረገው  ጨዋታ ታጆን ቡካነን በ62ኛው ደቂቃ ጎሉን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም