ቀጥታ፡

ባህር ዳር ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 16/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በየነ ባንጃ በ38ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ወልዋሎ መሪ ሆኗል።

አንተነህ ተፈራ በ50ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት የባህር ዳር ከተማን የአቻነት ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ባህር ዳር ከተማ በ11 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሶስት ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

የዛሬው መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ ተሳትፎ ምክንያት የተራዘመ ነው።

ወልዋሎ ከፋሲል ከነማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ጋር ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታዎቹን የሚያደርግ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም