ባህር ዳር ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ : የአራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር - ኢዜአ አማርኛ
ባህር ዳር ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ : የአራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር
አዲስ አበባ፤ ህዳር 16/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ተስተካካይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።
ባህር ዳር ከተማ በ10 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሁለት ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ 1 ሲረታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከመቻል ጋር ያለ ግብ አቻ ተለያይቷል።
ጨዋታው ባህር ዳር ከተማ በድል ጉዞው ለመቀጠል፣ ወልዋሎ የመጀመሪያ ድሉን ለማግኘት የሚያደርጉት ነው።
ክለቦቹ በ2018 ዓ.ም በሊጉ ባደረጉት ሁለት የእርስ በእርስ ጨዋታ አቻ ተለያያተዋል።
ሁለቱም ጨዋታዎች ያለ ግብ በአቻ ውጤት የተጠናቀቁ ነበሩ።
የዛሬው መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ ተሳትፎ ምክንያት የተራዘመ ነው።
ወልዋሎ ከፋሲል ከነማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ጋር ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታዎቹን የሚያደርግ ይሆናል።