ቀጥታ፡

የዛሬ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች : ፒኤስጂ ከሮማ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ከስፖርቲንግ ሊዝበን እና ክለብ ብሩዥ ከሊቨርፑል 

አዲስ አበባ፤ ህዳር 16 /2019 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ማምሻውን ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

የወቅቱ የሻምፒዮንስ ሊጉ አሸናፊ ፒኤስጂ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ሮማን በፓርክ ደ ፕሪንስ የሚያስተናግድበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።


ፒኤስጂ በ12 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ሮማ በአራት ነጥብ 23ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ፒኤስጂ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ያደረጋቸውን አራት ጨዋታዎች በድል ተወጥቷል።

በአንጻሩ ሮማ ከአራት ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ያሸነፈ ሲሆን በሁለቱ ሽንፈት ሲያስተናግድ በቀሪው መርሐ ግብር ነጥብ ተጋርቷል። 

በአራተኛ ዙር መርሐ ግብር በማንችስተር ዩናይትድ የ3 ለ 2 ሽንፈት አስተናግዷል።

ፒኤስጂ ካሸነፈ ወደ መሪነቱ ይመለሳል። ሮማ የድል መንገድን ለማግኘት ፍልሚያ ያደርጋል።

ሌላኛው መርሐ ግብር ስፖርቲንግ ሊዝበን እና ማንችስተር ዩናይትድን ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በጆዜ አልቫላዴ ስታዲየም ያገናኛል።

ስፖርቲንግ ሊዝበን በዘጠኝ ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።  ማንችስተር ዩናይትድ በስድስት ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዟል።

በአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ስፖርቲንግ ሊዝበን ሻካታር ዶኔስክን 1 ለ 0፣ ማንችስተር ዩናይትድ ሮማን 3 ለ 2 አሸንፈዋል።

ሁለቱ ክለቦች ተከታታይ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይጫወታሉ።


ምሽት አምስት ላይ ክለብ ብሩዥ ከሊቨርፑል በጃን ብሬይድል ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል።

ክለብ ብሩዥ በዘጠኝ ነጥብ 11ኛ  ደረጃን ይዟል። ሊቨርፑል በተመሳሳይ ዘጠኝ ነጥብ በግብ ክፍያ በልጦ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።


ሳባህ ከባርሴሎና በዳልጋ አሬና ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታሉ።

የአዘርባጃኑ ክለብ በሶስት ነጥብ 30ኛ ደረጃን ሲይዝ ባርሴሎና በዘጠኝ ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ባየር ሙኒክ ወደ ፒዬር-ማውሮይ ስታዲየም በማምራት ከሊል ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።

የጀርመኑ ክለብ በስምንት 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሊል በአንድ ነጥብ 35ኛ ደረጃን ይዟል።

በሌሎች መርሐ ግብሮች አትሌቲኮ ማድሪድ ከቫይኪንግ፣ ኢንተር ሚላን ከስቱትጋርት እና ሻካታር ዶኔስክ ከፊነርባቼ በተመሳሳይ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

ስላቪያ ፕራግ ከቪያሪያል ምሽት 2 ሰዓት ከ45 በፎርቹና አሬና ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም