አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር አቻ ሲወጡ ሪያል ማድሪድ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር አቻ ሲወጡ ሪያል ማድሪድ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 15/2019 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሐ ግብር የአምስተኛ ዙር የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ማምሻውን ተደርገዋል።
በኤምሬትስ ስታዲም በተካሄደው ጨዋታ አርሰናል እና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ባደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ቪክቶር ዮኮሬስ ለአርሰናል፣ ማክሲሚላን ቤየር ለዶርትሙንድ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በ11 ነጥብ አምስተኛ፣ ዶርትሙንድ በ10 ነጥብ 7ኛ ደረጃን ይዘዋል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ እና ናፖሊ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
አዩብ ቡአዲ እና ራያን ቸርኪ የሲቲን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ራስመስ ሆጅሉንድ እና ኖአ ላንግ የናፖሊን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ማንችስተር ሲቲ በ10 ነጥብ 6ኛ ደረጃን ሲይዝ ናፖሊ በአራት ነጥብ 27ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ሪያል ማድሪድ ፒኤስቪ አይንድሆቨንን 5 ለ 1 ረትቷል።
በበርናባው ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቪኒሸስ ጁኒየር፣ ጁድ ቤሊንግሃም እና ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ቀሪዎችን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ኢቫን ፔሪሲች በፍጹም ቅጣት ምት የፒኤስቪን ጎል አስቆጥሯል።
ሪያል ማድሪድ በ15 ነጥብ መሪነቱን ከፒኤስጂ ተረክቧል።
ፒኤስቪ በአራት ነጥብ 28ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ኮሞ ኤኢኬ አቴንስን እና ፖርቶ ፌይኖርድ ሮተርዳምን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
አርቢ ላይፕዚግ ሌንስን 3 ለ 1 እና ሪያል ቤቲስ ስሎቫን ብራቲስላቫን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።
ዛሬ አስቀድመው በተደረጉ ጨዋታዎች ጋላታሳራይ አስቶንቪላን፣ ቦዶ ግሊምት ላስክን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።