ቀጥታ፡

የዕለቱ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች: አርሰናል ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ ሪያል ማድሪድ ከፒኤስቪ እና ማንችስተር ሲቲ ከናፖሊ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 15 /2019 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አምስተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል።

በዕለቱ ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ምሽት አምስት ሰዓት ላይ አርሰናል ቦሩሲያ ዶርትሙንድን በኤምሬትስ ስታዲየም ያስተናግዳል።

አርሰናል እስከ አሁን ካደረጋቸው  አራት ጨዋታዎች መካከል በ10 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በዘጠኝ ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ጨዋታው ሳቢ እና ተመጣጣኝ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ከፒኤስቪ አይንድሆቨን ስታዲየም ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በበርናባው ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል።

የ15 ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ በ12 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ፒኤስቪ በአራት ነጥብ 24ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ማድሪድ ጨዋታውን የማሸነፍ ሰፊ ግምት አግኝቷል።


ማንችስተር ሲቲ ከናፖሊ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በኢትሃድ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታም ይጠበቃል።

ባለሜዳው ሲቲ በዘጠኝ ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።  የጣልያኑ ክለብ በሶስት ነጥብ 27ኛ ደረጃን ይዟል።

ጨዋታው ማንችስተር ሲቲ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ናፖሊ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ነው።

ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ጋላታሳራይ ከአስቶንቪላ በራምስ ፓርክ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

ጋላታሳራይ በስድስት ነጥብ 18ኛ፣ አስቶንቪላ በዘጠኝ ነጥብ 6ኛ ደረጃን ይዘዋል።

በሌሎች መርሐ ግብሮች ኮሞ ከኤኢኬ አቴንስ፣ አርቢ ላይፕዚግ ከሌንስ፣ ፌይኖርድ ከፖርቶ እና ስሎቫን ብራቲስላቫ ከሪያል ቤቲስ በተመሳሳይ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ቦዶ ግሊምት ከላስክ ጋር በአስፕማይራ ስታዲየም ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም