ቀጥታ፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መደበኛ ጉባኤን በመጪው ሐሙስ ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ህዳር 15/2019 (ኢዜአ)፦ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በመጪው ሐሙስ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሂዳል።

በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ምሽን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ መግለጫው አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም