ቀጥታ፡

ብሬንትፎርድ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 14 /2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ብሬንትፎርድ ኤቨርተንን 4 ለ 0 ረትቷል።

ማምሻውን በጂቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኪን ሉዊስ-ፖተር ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቫይታሊ ጃንሌት እና ፋቢዮ ካርቫሎ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

የኤቨርተኑ ተከላካይ ጃኮብ ታርኮስኪ በ40ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

ይህም ለባለሜዳው ብሬንትፎሮድ መልካም አጋጣሚን ፈጥሯል።

በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው
ብሬንትፎርድ በ17  ነጥብ ደረጃውን ከ10ኛ ወደ 6ኛ ከፍ  አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኤቨርተን በ16 ነጥብ ከነበረበት 7ኛ ደረጃ ወደ 9ኛ ዝቅ ብሏል።

ጨዋታውን ተከትሎ 11ኛ ሳምንት ተጠናቋል።

የ12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከህዳር 18 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም