ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 14 /2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ሀዋሳ ከተማን 3 ለ 1 ረትቷል።

በሃዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ በተደረገው ጨዋታ ትዕግስት ወርቁ፣ ሰርካለም ባሳ እና ትንቢት ሳሙኤል ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ዮርዳኖስ ምዑዝ የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ውጤቱን ተከትሎ መቻል በሰባት ነጥብ ደረጃውን ከ11ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል።

ሀዋሳ ከተማ በአምስት ነጥብ ከነበረበት 10ኛ ወደ 11ኛ ዝቅ ብሏል።

ዛሬ አስቀድሞ በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡናን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም