በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 14 /2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡናን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በሃዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ በተካሄደው ጨዋታ ምትኬ ብርሃኑ፣ መሰረት ወርቅነህ እና ዳግማዊት ሰለሞን ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ጤናዬ ለታሞ የሲዳማ ቡናን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው በ10 ነጥብ ከነበረበት 7ኛ ደረጃ ወደ 2ኛ ከፍ ብሏል።
ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ዝቅ አድርጓል።
በአንጻሩ በሊጉ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና በአራት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።