ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 14 /2019 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከCPHIA 2026 ጉባኤ ጎን ለጎን ከታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በውይይታችንም የቆየውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እና የጋራ ጥቅም ባላቸው ዘርፎች ላይ ትብብራችንን ማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም