ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች

አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል።

ከቀኑ 8 ሰዓት ሲዳማ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ይጫወታሉ።

ሲዳማ ቡና በአራት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሰባት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በአምስተኛ ሳምንት ሲዳማ ቡና ከቦሌ ክፍለ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይቷል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአምስተኛ ሳምንት ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 0 ረትቷል።

ጨዋታው ሲዳማ ቡና ወደ አሸናፊነት ለመመለስ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ የሚያደርጉት ነው።

ቡድኖቹ በ2018 ዓ.ም የውድድር ዓመት እርስ በእርስ ባደረጓቸው ሁለት ጨዋታዎች ኢትዮ ኤሌክትሪክ በማሸነፍ የበላይነቱን ወስዷል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በጨዋታዎቹ በተመሳሳይ 2 ለ 0 አሸንፏል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ከመቻል በሃዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሀዋሳ ከተማ በአምስት ነጥብ 10ኛ፣ መቻል በአራት ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በአራተኛ ሳምንት ሀዋሳ ከተማ በኢትዮ ኤሌክትሪክ 2 ለ 0፣ መቻል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2 ለ 1 ሽንፈት አስተናግደዋል።

የዛሬው ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ የሚያደርጉት ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም