ብሬንትፎርድ ከኤቨርተን : የ11ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር - ኢዜአ አማርኛ
ብሬንትፎርድ ከኤቨርተን : የ11ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር
አዲስ አበባ፤ ህዳር 14 /2019 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል።
ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ብሬንትፎርድ ከኤቨርተን በጂቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ባለሜዳው ብሬንትፎርድ በ14 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።
ተጋጣሚው ኤቨርተን በ16 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል ቀንቶታል።
ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ከዚህ ቀደም 10 ጊዜ ተገናኝተዋል።
በዚህም ክለቦቹ በተመሳሳይ ሶስት ጊዜ አሸንፈዋል። በቀሪ አራት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
በ10ሩ ጨዋታዎች ላይ ቡድኖቹ በተመሳሳይ 13 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ባለሜዳው ብሬንትፎርድ በ10ኛ ሳምንት በብራይተን የ2 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል።
ኤቨርተን ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ድል ቀንቶታል።
ጨዋታው ብሬንትፎርድ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ፣ ኤቨርተን ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ የሚያደርጉት ነው።
የ47 ዓመቱ ክሬግ ፖውሰን ጨዋታዋን በዋና ዳኝነት እንዲመሩት ተመድበዋል።