ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2019 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከCPHIA 2026 ጉባኤ ጎን ለጎን ከዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ ጋር ስብሰባ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።
ውይይታችን ታሪካዊ ግንኙነታችንን ወደ ላቀ የሁለትዮሽ ትብብር እና የጋራ ቀጣናዊ እድገት መለወጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ብለዋል።