ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2019(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በCPHIA 2026 ጉባኤ ጎን ለጎን ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በውይይታችንም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ እና ለዘመናት የቆየ ግንኙነት በድጋሚ ያረጋገጥን ሲሆን፣ ተግባራዊ ትብብርን እና ተጨባጭ ውጤቶችን በማምጣት አጋርነታችንን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም