ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡሩንዲ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስት ንዳይሺሚዬ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2019(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከCPHIA 2026 ጉባኤ ጎን ለጎን ከቡሩንዲ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስት ንዳይሺሚዬ ጋር መወያየታቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በቅርብ ጊዜ ያደረግናቸውን ምክክሮች መሠረት በማድረግ፣ ይህ ውይይት የጋራ ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ጉዳዮች ለመዳሰስ፣ የሁለትዮሽ ትብብራችንን ለማስፋት እንዲሁም የጋራ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ አጀንዳዎቻችንን ወደ ተጨባጭ ተግባራት ለመለወጥ የሚያስችሉ ሀሳቦችን እንድንለዋወጥ ዕድል ሰጥቶናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም