ቀጥታ፡

በተጠባቂው ጨዋታ ሊቨርፑል ማንችስተር ዩናይትድን 4 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ማንችስተር ዩናይትድን 4 ለ 0 ረትቷል።

ማምሻውን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም  በተደረገው ጨዋታ ዶምኒክ ስቦዝላይ፣ ፍሎሪያን ዊትዝ፣ ሪዮ ንጉሞሃ እና ቪክቶር ሙኞዝ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ሌና ዮሮ በስምንተኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ወጥቷል።

ይህም  ሊቨርፑል  በጨዋታው ከፍተኛ ብልጫ እንዲወስድ አድርጎታል። ተጨማሪ ጎሎችን ማስቆጠር የሚችልባቸውን እድሎች መጠቀም አልቻለም።

በሊጉ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሊቨርፑል በ21 ነጥብ  አራተኛ ደረጃን ይዟል።

በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማንችስተር ዩናይትድ በስምንት ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ዩናይትድ ባለፉት ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

አዲሱ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ሽንፈት አስተናግደዋል።

ዛሬ ቀን ላይ በተካሄደ መርሐ ግብር ሁል ሲቲ ብራይተንን 2 ለ 0 አሸንፏል።

የሊጉ 11ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ብሬንትፎርድ እና ኤቨርተን ነገ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም