ቀጥታ፡

ብራይተን በሁል ሲቲ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ሁል ሲቲ  ብራይተንን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በኤምኬኤም ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኦሊ ማክበርኒ በ92ኛው እና በ95ኛው ደቂቃ ግቦቹን አስቆጥሯል።

የብራይተኑ ተከላካይ ኮስቲንሃ በ89ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

በጨዋታው ብራይተን ያገኛቸውን የግብ እድሎች መጠቀም አልቻለም።

በሊጉ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ብራይተን በ22 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ከስምንት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሁል ሲቲ በ14 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ሊቨርፑል ከማንችስተር ሲቲ በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም