ቀጥታ፡

ነገሌ አርሲ መሪነቱን ያጠናከረበት ድል አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ ጋሞ ጨንቻን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በሀዋሳ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መሐመድኑር ናስር በ24ኛው ደቂቃ ግቡን አስቆጥሯል።

በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ነገሌ አርሲ በ14 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ጋሞ ጨንቻ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን 18ኛ ደረጃን ይዟል።

ጋሞ ጨንቻ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ይቀረዋል። 

በባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

አናንያ ጌታቸው በ36ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ11 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ፋሲል ከነማ በሶስት ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ ስድስተኛ ሳምንት ተጠናቋል።

የሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከህዳር 18 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም