ቀጥታ፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሀላባ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሀላባ ከተማን 1 ለ 0 ረትቷል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጋቦናዊው አጥቂ ካሌብ ስቴፍ ሜልቪን በ55ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።

በሊጉ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ10 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ በስምንት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም