የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ጥሏል - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ጥሏል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከድሬዳዋ ከተማ ባደረገው ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይቷል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊድያ ኢያሱ በ26ኛው ደቂቃ ባስቆጠረችው ጎል ንግድ ባንክ መሪ ሆኗል።
ነፃነት መለሰ በ60ኛው ደቂቃ ለድሬዳዋ ከተማ የአቻነቱን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ውጤቱን ተከትሎ የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥቡን ወደ 13 ከፍ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ነጥቡን ያገኘው ድሬዳዋ ከተማ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃ ይዟል።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ሸገር ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማን፣ ይርጋጨፌ ቡና አዳማ ከተማን እና ቦሌ ክፍለ ከተማ ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከልን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን 2 ለ 1 ረትቷል።