ቀጥታ፡

ታላቁ ሩጫ የሀገር ገጽታን በሚገነባና የስፖርት ቱሪዝምን በሚያነቃቃ መልኩ ተጠናቋል - የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13/2019 (ኢዜአ)፡- 26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሀገር ገጽታን በሚገነባና የስፖርት ቱሪዝምን በሚያነቃቃ መልኩ መጠናቀቁን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ።

ሩጫው ከ61 ሺህ በላይ ሰዎችን በማሳተፍና የመደመር መንግሥት ስፖርትን ሀገራዊ ልማታዊ አጀንዳ ማድረጉን በተግባር ያሳየ መሆኑንም ገልጿል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለና እያደገ የመጣው ይህ ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ፣ የዘንድሮው መርሐ ግብር ከምንጊዜውም በላይ ደረጃውን ጠብቆ እንዲካሄድ የመደመር መንግሥት ለስፖርቱ ዘርፍ የሰጠው ልዩ ትኩረትና ሁለንተናዊ ድጋፍ ከፍተኛውን ድርሻ መወጣቱን አስታውቋል።

መንግሥት የስፖርት ዘርፉን ለማዘመንና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ውድድሮችን ለማስተናገድ የዘረጋው አሠራር፣ ውድድሩ የሀገሪቱን ገጽታ በሚገነባና የስፖርት ቱሪዝምን በሚያነቃቃ መልኩ እንዲጠናቀቅ ማስቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

#ታላቁሩጫበኢትዮጵያ #ስፖርት #ኢዜአ #ENA

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም