ቀጥታ፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ደማቅ፣ሰላማዊና የማይረሳ ሁነት ሆኖ በስኬት ተጠናቋል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13/2019 (ኢዜአ)፡- 26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ድንቅ፣ ደማቅ፣ ሰላማዊና የማይረሳ ሁነት ሆኖ በስኬት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ከሕፃናት እስከ አዛውንቶች እንዲሁም ከኢትዮጵያውያን እስከ ዓለም አቀፍ አትሌቶች የተሳተፉበት ታላቁ ሩጫ በደስታ፣ በፍቅርና በአንድነት በስኬት መጠናቀቁን አመልክተዋል።

በውድድሩ ኢትዮጵያ ውበቷን፣ ሰላሟንና የእንግዳ አቀባበል ባህሏን ለዓለም ማሳየቷንም ጠቅሰዋል።

ከንቲባ አዳነች ለሁነቱ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ አዘጋጆች፣ የጸጥታ አካላት፣የከተማዋ ነዋሪዎችና ለሁሉም ተሳታፊዎች ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም