ቀጥታ፡

ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መዲና ጀማል እና አስራት ዓለሙ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ብሩክታዊት አየለ  የልደታ ክፍለ ከተማን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

ውጤቱን ተከትሎ ባህር ዳር ከተማ በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ከሰባተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።

ልደታ ክፍለ ከተማ በስምንት ነጥብ ከነበረበት ሶስተኛ ደረጃ ወደ አራተኛ ዝቅ ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም