ቀጥታ፡

ታላቁ ሩጫ የአዲስ አበባን አዲስ ውበትና ለውጥ ለዓለም ያሳየ ታላቅ አጋጣሚ ሆኗል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ህዳር 13/2019 (ኢዜአ)፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአዲስ አበባን አዲስ ውበትና ለውጥ ለዓለም ያሳየ ታላቅ አጋጣሚ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ እንደ ስሟ እያበበች ያለችው አዲስ አበባ 26ኛውን ታላቁ ሩጫ በደማቅና በደስታ በተሞላ ድባብ እያስተናገደች መሆኗን አመልክተዋል።

የከተማዋ ዘመናዊ መንገዶች፣ አረንጓዴ ስፍራዎችና የተሻሻሉ መሠረተ ልማቶች፣ በኢትዮጵያ ሕብረ ቀለማት ለተዋቡና በፍቅርና በአብሮነት ለተሳሰሩ 60 ሺህ ተሳታፊዎች ውብ መድረክ መፍጠራቸውንም ጠቅሰዋል።

ይህ ኩነት የከተማዋን አዲስ ውበትና ለውጥ ለዓለም ያሳየ ታላቅ አጋጣሚ መሆኑን የገለጹት ከንቲባ አዳነች፤ "አብሮነታችን ውበታችን፤ አንድነታችን ጉልበታችን ነው" ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም