የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አየር መንገድ በመባል አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አየር መንገድ በመባል አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 13/2019 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በ2026 በተካሄደው የአረቢያን ካርጎ ሽልማት (Arabian Cargo Awards) ላይ ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ "የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አየር መንገድ" በመባል አሸንፏል።
አየር መንገዱ ይህንን ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘት የቻለው በአፍሪካ ብሎም በመላው ዓለም ፈጣን፣ ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ የካርጎ ማጓጓዝ አገልግሎት በላቀ ሁኔታ እየሰጠ በመሆኑ ነው።
ይህ ተከታታይ ስኬት የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ያለውን ተወዳዳሪነትና አስተማማኝነት በድጋሚ ያረጋገጠ መሆኑን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።