ቀጥታ፡

26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2019 (ኢዜአ)፦ 26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር “ሩጫዬ ቀለሜ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው።

በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 60 ሺህ ተሳታፊዎች እየተሳተፉ ሲሆን፣ 500 አትሌቶች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላትና የውጭ ዜጎችም ተቀላቅለዋል።

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ውድድር መጨናነቅን ለመቀነስ በሦስት የተለያዩ ማስጀመሪያዎች እየተካሄደ ሲሆን፣ የፈጣን ሯጮች ውጤትም በዘመናዊ የቺፕ ቴክኖሎጂ እየተመዘገበ ነው።

ውድድሩ ከስፖርታዊ ፉክክር ባሻገር የአንድነት፣ የሰላምና የአብሮነት መድረክ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያን የአትሌቲክስ ልዕልና፣ የእንግዳ ተቀባይነት ባህልና የአዲስ አበባን የኮሪደር ልማት ገጽታ ለዓለም የሚያስተዋውቅ ትልቅ የቱሪዝም መድረክ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም