አትሌት ይስማው ድሉ የ2019 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
አትሌት ይስማው ድሉ የ2019 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ፤ህዳር 13/2019(ኢዜአ)፦አትሌት ይስማው ድሉ በ2019 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበውን የወንዶች የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር በማሸነፍ አንደኛ ወጣ።
አትሌት ይስማው ድሉ ባለፈው ዓመትም የውድድሩ አሸናፊ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ በዘንድሮው ውድድር ድሉን በመድገም በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል።
አትሌት ይስማው ድሉ በውድድሩ አሸናፊነቱ የ500 ሺህ ብር ሽልማት አግኝቷል።
ታከለ ሞሴ ውድድሩን በሁለተኝነት ሲያጠናቅቅ፣ ሮባ መርጋ 3ኛ ደረጃ ይዞ ጨርሷል።