ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ አርሰናል ነጥብ ጥሏል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 12/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ  ሳምንት መርሐ ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ እና  አርሰናል ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኤበሬቺ ኤዜ በ33ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል አርሰናል መሪ ሆኗል።

ሃርቪ ባርንስ በ49ኛው እና ማሊክ ቲያው በ62ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፏቸው ጎሎች ኒውካስትል መሪነቱን መውሰድ ችሎ ነበር።

ይሁንና ኖኒ ማዱዌኬ በ78ኛው ደቂቃ የአርሰናልን የአቻነት ጎል አስቆጥሯል።

በመጀመሪያው አጋማሽ አርሰናል፣ ኒውካስትል በሁለተኛው 45 ብልጫ ነበራቸው።

የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ ባጋጠመው ጉዳት በ70ኛው ደቂቃ ከሜዳ ወጥቷል።

ውጤቱን ተከትሎ የሊጉ መሪ አርሰናል ነጥቡን ወደ 28 ከፍ አድርጓል።

ኒውካስትል ዩናይትድ በ13 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በ12ኛ ሳምንት አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ የሚያደርገው ጨዋታ ከወዲሁ ይጠበቃል።

ኒውካስትል ከብራይተን ጋር ይጫወታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም