ድምጻዊ ሚኪያስ ቸርነት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ - ኢዜአ አማርኛ
ድምጻዊ ሚኪያስ ቸርነት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 12/2019 (ኢዜአ)፦በበርካታ የሙዚቃ ስራዎቹ የሚታወቀው ድምጻዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
ድምጻዊ ሚኪያስ ቸርነት በሙዚቃ ስራ ላይ በነበረበት ወቅት በድንገት ባጋጠመው ህመም ህይወቱ ማለፉ ታውቋል፡፡
ድምጻዊ ሚኪያስ "ግርማ ሞገሴ ነሽ፣ ሰላም አላት፣ የኔ ደሃ፣ አሁን ገባኝ፣ አትጨናነቅ" የተሰኙትን ጨምሮ በርካታ ተወዳጅ ሙዚቃዎችን ለአድማጭ አድርሷል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በድምጻዊው ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ፤ ለቤተሰቦቹ፣ ለሥራ ባልደረቦቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡