ቼልሲ ሽንፈት ሲያስተናግድ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ቼልሲ ሽንፈት ሲያስተናግድ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 12/2019 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።
በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊድስ ዩናይትድ ቼልሲን 4 ለ 1 አሸንፏል።
ኖሃ ኦካፎር ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ዶምኒክ ካልቨርት-ሉዊን በፍጹም ቅጣት ምት እና ብሬንደን አሮንሰን ቀሪዎቹን ጎሎች ለሊድስ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ኢማኑኤል ኢሜግሃ የቼልሲን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ16 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። ሊድስ ዩናይትድ በ17 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ ኤፕስዊች ታውንን 2 ለ 0 ረትቷል።
በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተደረገው መርሐ ግብር ሉካ ዊሊያምስ-ባርኔት እና ዶምኒክ ሶላንኬ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ15 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል። ኤፕስዊች ታውን በ11 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
አስቶንቪላ ከሰንደርላንድ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ቦርንማውዝ ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0፣ ኮቨንተሪ ሲቲ ክሪስታል ፓላስን 3 ለ 1 አሸንፈዋል።
ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ኒውካስትል ዩናይትድ የሊጉን መሪ አርሰናልን በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም የሚያስተናግድበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።