የወቅቱ ሻምፒዮን ሲዳማ ቡና በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
የወቅቱ ሻምፒዮን ሲዳማ ቡና በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 12/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ጨዋታ መስፍን ታፈሰ በ78ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ሲዳማ ቡና መሪ ሆኗል።
እዮብ ማትያስ በ88ኛው ደቂቃ የአዳማ ከተማን የአቻነት ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ ሲባል አቤል ያለው በ95ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ሲዳማ ቡና ጣፋጭ ድል ተቀዳጅቷል።
ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ ሻምፒዮን ሲዳማ ቡና በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ያስመዘገበ ሲሆን በአራት ነጥብ ከነበረበት 16ኛ ደረጃ ወደ 14ኛ ከፍ በማለት ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በስድስት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።