ባህር ዳር ከተማ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ያደረገበት ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ባህር ዳር ከተማ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ያደረገበት ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 12/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ 1 ረትቷል።
በባህር ዳር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዮዳሄ ዳዊት፣ አንተነህ ተፈራ (ፍጹም ቅጣት ምት) እና ደሳለኝ አሻግሬ የማሸነፊያ ግቦችን አስቆጥረዋል።
ወገኔ ገዛኸኝ በፍጹም ቅጣት ምት የኢትዮጵያ መድንን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ባህር ዳር ከተማ በ10 ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።
ኢትዮጵያ መድን በሰባት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።
የባህር ዳር ከተማው አጥቂ አንተነህ ተፈራ በሊጉ ከመረብ ላይ ያሳረፋቸውን ጎሎች ብዛት ወደ ስድስት ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን መምራት ጀምሯል