ቀጥታ፡

ሸገር ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 12/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ሸገር ከተማ ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 1 ረትቷል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኦዳ መሐመድ እና ቢንያም ፍቅሩ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ጌታነህ ከበደ የሀዋሳ ከተማ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ሸገር ከተማ በስምንት ነጥብ አምስተኛ፣ ሀዋሳ ከተማ በአምስት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዘዋል።

በሰባተኛ ሳምንት ሸገር ከተማ ከጋሞ ጨንቻ እና ሀዋሳ ከተማ ከአዳማ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም