ቀጥታ፡

ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ትሻለች

አዲስ አበባ፤ ህዳር 11/2019 (ኢዜአ)፦ ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ዘላቂ ልማትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማስፋት ፍላጎት እንዳላት አስታወቀች።

31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል።


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን፣ ከሲንጋፖር የዘላቂነትና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ግሬስ ፉ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

ሚኒስትሯ፣ ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ለማስተናገድ በመመረጧ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉ  ሲሆን፣ ሲንጋፖር በካርቦን ገበያ፣ በምግብ ዋስትና፣ በዲጂታል ፈጠራና በዘላቂ ልማት ዘርፎች ያላትን የትብብር ፍላጎት ገልጸዋል።

በዉይይታቸዉም  ለተሳካ ኮፕ 32 ዝግጅት ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

#COP31 #COP32 #ClimateAction

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም